Save up to 70% on New Year Sale
Make the most of the season — grab the best ad placements by January 10!
Get discount
12.4
Advertising on the Telegram channel «😱 ኢስላሚክ ፅሁፍ 😱»
5.0
Education
Language:
English
124
0
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
Advertising publication cost
local_activity
$3.60$2.52local_mall
30.0%
Recent Channel Posts
ለማንም አትቃጠል
ፀሀይ ለኛ ብላ ራሷን አቃጠለች እኛ ግን ዛሬ ድረስ ጨረቃን ከወመውደድ አልተቆጠብንም።
.....
........አቦ ሰላም እደሩልኝ....!!

277
21:58
14.12.2024
ንቄ ያለፍኳቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ በተለይ እኔ አዋቂ ነኝ ብለው እራሳቸውን ከፍ የሚያደርጉ ሰዎች እናም እራሳቸውን መመልከት ትተው ሰው ላይ ስም ለመለጠፍ ሚሯሯጡ እንጭጭ ሰዎች!
#አስለሃሁሙሏህ
#አስለሃሁሙሏህ
294
21:45
14.12.2024
ንዴትና ስሜትህን ስትቆጣጠር
ደካማ ጎንህ ይደበቃል።
😊
ደካማ ጎንህ ይደበቃል።
😊
264
11:56
15.12.2024
"የሸሂዶች "ሚስት" ክፍል" 4
እንደ አብደላ ለመናዘዝ፤ ከርሳቸው ቡሃላ ምን ማድረግ እንዳለባት ሳይነግሯት፣ ቃል ኪዳን የለ፤ አደራ የለ፤ ለሱብሂ ሰላት እንደወጡ ወደ ቤት ሳይመለሱ ቀሩ። የዓቲካ ሐዘን ከባለፈው እጅግ ከፋ። የሚገርመው ግን ዓቲካ ያገባቻቸው ወንዶች በሙሉ ሸሂዶች ብቻ ሳይሆኑ፤ ዓቲካን እንደወደዱ፤ እንዳፈቀሩ፤ ሐቃቸውን እንደጠበቀች፤ በዚያ ወደር በሌለው ቁንጅናዋ ሳትኩራራ፤ ለአሉባልታና ሐሜት የትዳር በሯን ሳትከፍት፤ የዓቲካን የትዳር የህይወት የቀመሱ ወንዶች ሁሉ በጀነት አላህ ባገናኘን እያሉ እየተመኙ ነበር የሸሂድ ሞት የሚሞቱት፤ ዓቲካን ያገባ ሁሉ ሸሂድ ነው፤ ሸሃዳን የተመኘ ዓቲካን ያገባል፡፡
የሚገርመው ሸሃዳን ፈልጎ ዓቲካን ማግባት ያልቻለ፤ ዓቲካን ተመኝቶ በዚሁ ምኞቱ ሸሃዳ ያገኛል፡፡ ዓቲካ ግን በዑመር መሞት የነበረባት ሐዘን አልወገድልሽ አላት። ለሰላት መስጂድ እየሄደች መመለስና በብቸኝነት ከሰው በመገለል አላህን መገዛት ተያያዘች። ትልቁ ችግር የማታው አስፈሪ ህልም ነበር፤ ዓቲካ ከዚያን ቀን ጀምሮ በህልማ አቡ ሉእሉዕ ሰይዲና ዑመርን ሊወጋቸው ሲል ሰይዲና ዑመርን አድናለሁ ብላ ስትወራጭና ስትጮህ በላብ ተጥለቅልቃ ጸጥ ረጭ ባለበት ሌሊት ከእንቅልፏ ሃይለኛው ጩኸቷ ያባንናታል፡፡ ዓቲካ ልዩ የፍቅር ተምሳሌት ናት፤ ዓቲካ ለባለትዳር ሴቶች ጥሩ አርዓያ ናት።
በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች ከቀን ወደ ቀን ትንሽ እያገገመች ሶስት የሃዘን ወራትን ትጨርሳለች። ይህቺን ውብ ሴት የትዳር ህይወት በቃት ይሆን? የዓቲካ የትዳር ጥያቄ አሁንም አላበቃም። እርሷንና ሀዛንን ለብቻቸው እንተዋት የሚል አልነበረም። ቢያገባት ወዲያው ሸሂድ እንደሚሆን ልቡ እያወቀ ዓቲካን ለትዳር ከመጠየቅ ወደ ኋላ አይልም ነበር. አሁን ደግሞ ማን ይሆን ዓቲካን ለትዳር የሚጠይቃት ዓቲካ ከሰይዲና ዑመር ረዲየላሁ አንሁ ቡሃላ ማንም ሰው ለትዳር ይፈልገኛል ብላ አላሰበችም። ድንገት አንድ የማትጠብቀው ሰሃባ ዓቲካን ለትዳር እንደሚፈልጋት በአንድ ሰው መልዕክት ላከባት።
ስለዚህ ታላቅ ሰሀባ ነቢዩ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል " ሁሉም ነቢያቶች ሐዋሪያ ነበራቸው፤ የኔ ሐዋሪይ እርሱ ነው " በማለት የተናገሩለት ውድ ሰሃቢ ነው፡፡ ሐዋሪይ ማለት ከነቢይ የማይለይ፤ የሚካድም፤ አማካሪ፤ መልዕክት የሚያስተላልፍ፤ ለነቢይ ቅርብ የሆነ ሰው ማለት ነው። ይህ አሁን ዓቲካን ለትዳር የጠየቀው ሰሃቢ በረሱል ሐዋሪይ የሚል ቅፅል ስም የተሰጠው ነው። እንዲሁም የረሱል አክስት የሶፊያ ልጅም ነው። በተጨማሪም ከአስሩ በጀነት ቃል ከተገባላቸው ከሰሃቦች አንዱ ሲሆን፡፡ ከስድስቱ የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አማካሪዎች አንዱም ነው፡፡
ይህ አስሃባ እስልምና የገባው በስምንት ዓመቱ ህፃን ሆኖ አጎቱ በእሳት እያቃጠለው በሙሐመድ ክፈር እያለ ሲያሰቃየው የነበረ፤ በአስራ ስምንት ዓመቱ ከመካ ወደ መዲና የተሰደደ በርቅዬ ሰሃባ ነው። ይህ ታላቅ ሰሃቢይ ወደ ሃበሻ በመሰደድ እኛ ከጠጣነው ዉሃ የጠጣ እኛ ያደግንበትን አፈር የረገጠ ነው። በፍፁም ነቢያችን ጦርነት ወጥተው ተለይቷቸው የማያውቅ ሰሃቢ ነበር። ማን ይሆን ይህ ታላቅ ሰሃቢ?
ዓቲካስ ይህን የጋብቻ ጥያቄ ትቀበል ይሆን? ዙቤይር ኢብኑል ዓዋም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ይባላል፡፡ ነገር ግን ዓቲካ ረዲየላሁ ዐንሀ የመጣላትን የትዳር ጥያቄ ማመን አልቻለችም።
አሁን ግልፅ የሆነላት ነገር ቢኖር ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው እንደሚሆን ነው፡፡ ገና ሳታገባው ለምታገባው ሰው ትሳሳለት ጀመር። አሁን አግብቶኝ ትንሽ ሳይቆይ ሸሃዳ ሊያገኝ እንዳይሆን ብቻ በማለት አሰበች። ዓቲካ የዙቤይር ኢብኑየል ዓዋምን ደረጃውን ታውቃለች። የረሱል የአክስት ልጅ፤ የነቢይ ሃዋሪይ፤ ታሪኩ ተወርቶ የማያልቅ ታላቅ ሰሃቢ መሆኑን ጠንቅቃ ታውቃለች። ኒካህ ከመደረጉ በፊት ዓቲካ አንድ ሸርጥ ታስቀምጣለች። ምንድነው ሸርጢሽ ዓቲካ ብለው ጠየቋት? የዓቲካ ሸርጧ አምስት ወቅት ሰለት መስጅድ ሄዳ መስገድ እንደምትፈልግና ዙቤይርም (ረዲየሏሁ ዐንሁም አጅማኢን) እንዳይከለክላት ነበር። ሰይዲና ዙቤይርም በዚህ ሸርጥ ተስማምተው ከዓቲካ ጋር ኒካህ አሰሩ፡፡
ሰይዲና ዙቤይር በየቀኑ ለዓቲካ ያላቸው ውዴታና ፍቅር እየጨመረ ይሄዳል። እንዴት አይጨምርም? አኽላቋ የሚረታ፤ ውበቷ የሚማርክ፤ ያገባችውን ባል በሙሉ አላህ የደነገገባትን ሀቆች አሳምራ ሰጥታ ማታ እጇን ወደ ሰማይ ዘርግታ ያረብ የባሌን ሐቅ አሟልቼ እንድሰጥ እርዳኝ ላጎደልኩትም ማረኝ የምትል ሴት ላይ እንዴት ውዴታ አይጨምርም። ከጊዜ ቡሃላም ሰይዲና ዙቤይር ረዲየላሁ አንሁ ላይ አዲስ ባህሪ ይታይባቸው ጀመር። ይህውም ዓቲካ ላይ መቅናት መጀመራቸው ነው፡ ሰይዲና ዙቤይር ረዲየሏሁ ዐንሁ በየቀኑ ቅናታቸው እየጎላና ከአንደበታቸው ማውጣት ጀመሩ። አንድ ቀን ዓቲካ መስጂድ ልትሄድ ስትወጣ፡፡
ያ ዓቲካ አሏት፤ «ወላሂ ከቤት የምትወጪው እኔ መውጣትሺን እየጠላሁ ነው፡፡» አሏት፤ እርሷም ከበር ተመልሳ፤ በተረጋጋ መልኩ ከፈለግክ አልሄድም አቆማለሁ በማለት ጠጋ ብላ ታባብላቸዋለች፤ ያ ሰላም...ያ አላህ አኽላቃችንን አሳምርልን ተመልከቱ እሳቸው ባላቤቷ ዙበይር የሚመልሱትን፤ እንዴት እከለክልሻለሁ ስታገቢኝ ሸርጥሽ ሆኖ ብለው ከቤት አውጥተው ወደ መስጂድ ይሸኟታል፡፡ ዓቲካ በረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የአክስት ልጅ ላይ እያሳደረች የነበረው ተጽኖ ወደር አልነበረውም፤ ሰዪዲና ዙቤይርም ግን መቋቋም አልቻሉም፤

337
21:12
15.12.2024
የ" ሸሂዶች "ሚስት" ክፍል 5
ለሁለተኛ ጊዜ ዓቲካን መስጂድ መሄዳን መጥላታቸውን ሲገልጹላት፤ ዓቲካም ይህ ጥያቄያቸው በቅናት ላይ የተመሰረተና ሊቀይሩት ይችሉ ዘንድ በለዘብታ፤ የዓዋም ልጅ ሆይ (በዚያን ጊዜ የሚወዱትን ሰው ሲጠሩ በአባቱ ስም ነበር) ረሱል ሰለላሁ ወሰለም ጋር አቢበክርና ዑመር ጋር የሰገድኩበትን ሙሰላዬን ለቅናትህ ብዬ እንድተው ፈለግክ ወይ ብላ ጠየቀቻቸው፤ሰይዲና ዙቤይርም ላ ወላሂ አልከለክልሺም አሉ፤ነገር ግን ያደረባቸው ቅናት ቀላል አልነበረም፤ በጣም ያሳዝናሉ፤ ለሰላት ከወጣች የምትመለስ አይመስላቸውም፤ ልባቸው አልረጋ አለ፤ማስገደድ ባህሪያቸው አልነበረም፤ አትሂጂ ማለትም አይበቃላቸውም፤ ነገር ግን ይህ ቅናት ወደሚያስገርም ድርጊት ይመራቸዋል፤
ኢኽዋኒ ወአኸዋቲ ከዚህ በታች በምነግራቹህ የሰዪዲና ዙቤይር ድርጊት ተገርማችሁ ምንም አይነት ኔጌቲቭ ኮመንተ እንዳታደርጉ፤ ሲጀመር በሃሳባችሁም ውስጥ እንዳታመጡት፤ ምክንያቱም ከረሱል ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም ሰሃባዎች ጋር አደብ ሊኖረን ይገባል፤ ነብያችንም አለይሂ ሰላቱ ወሰላም አስጠንቅቀዋል፤ልብ ብለን እናንበው፤ አላህ አላህ በሰሃቦቼ (አላህን ፍሩ ሰሃባዎቼን በሚመለከት ) እኔ ከሞትኩ ቡሃላ እስልማናን ለመውጋት እነርሱን አላማ አታድርጋቸው እነርሱን የወደደ እኔ እንደምወደው ሆኖ ነው የሚወዳቸው እነርሱን ያስከፋ ያስቆጣ እኔ እንደምከፋበት እንደምቆጣበት ሆኖ ነው የሚያስቆጣቸው እነርሱን አዛ ያደርገ እኔን አዛ እንዳደረገ ነው እኔን አዛ ያደረገ አላህን አዛ እንዳደረገ ነው አላህን አዛ ያደረገ አላህ ክፉኛ ሊወስደው ተቃርቦዋል አሉ በሌላ ሐዲስ ላይ አስሃባዎቼን እንዳትሰድባቸው አስሃባዎቼን እንዳትሰድባቸው ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለሁ አንዳቹህ የእሁድን ተራራ የሚያክል ወርቅ ብታወጡ የአንዳቸውንም ደረጃ አትደርሱም ነበር ወላ ግማሹን አሉ ከዚህ አስፈሪ ማስጠንቀቂያ ቡሃላ እንግዲህ ሰሃቦችን በክፉ ማንሳት ወይም ሊያስብ የሚዳፈር ያለ አይመስለኛም ወደ ዓቲካ ታሪክ ስንመለስ፤
ሰዪዲና ዙቤይር ረዲየላሁ አንሁ ዓቲካ ላይ ከመቅናታቸው የተነሳ አንድ የሚያስገርም ነገር ይሰራሉ፤ አንድ ቀን የሱብህ ሰላትን ለመስገድ ወደ መስጂድ ስትሄድ፤ ሰዪዲና ዙቤይር ውዱእ አድርገው ቀድመዋት ወጡና በኒ ሰዐድ የሚባለው ቦታ ላይ አድፍጠው ጠብቀዋት፤ በዚያ ጨለማ ሰውነቷን መታ አድርገዋት በፍጥነት ተሰወሩ፤
ዓቲካም ደንግጣ ዞር ብላ ስታይ ማንም የለም፤ ምን ሆነሃል አላህ እጅህን ይቁረጠው አለችና በጣም ተደናግጣ የነቢዩ አሌይሂ ወሰላም መስጂድ መሄዳን ትታ ወደ ቤታ ተመልሳ ትሄዳለች ሰላታንም እቤት ሰግዳ ሰዎች እንዲህ አደብ አጡ በማለት በጣም አዝና ስለደረሰባት ነገር እያሰላሰለች ሳለ ሰይዲና ዙበይር እቤት ተመልሰው ምነው መስጂድ አላየሁሽም ይላታል፤አላህ ይርሃመክ የአብደላ አባት ካንተ ቡሃላ ሰዎች ተበላሹ፤ ዛሬ ለሴት ልጅ መስጂድ ሄዳ ከመስገድ ጋዳ ውስጥ መስገድ ይሻላታል በማለት ከዚያን ቀን ጀምሮ መስጂድ ሄዳ መስገድ አቆመች፤ ሰዪዲና ዙቤይር ድርጊታቸው ቢጸጽታቸውም ሊቋቋሙት ያልቻሉት ስሜት እዚህ አደረሳቸው፤
ዓቲካ ሰይዲና ዙበይርን ወዳ፤ ቤቷን አሙቃ ትዳራን አሳምራ በደስታ እየኖሩ ሳለ፤ ዓቲካን ሃዘናን ማስረሳት ሳይሆን የሚሸፍኑላት ሰይዲና ዙቤይር ከልክ ያለፈ ውዴታን እናክብካቤ በማሳየት ነበር፤ያ ነቢያችን አሌይሂ ሰላቱ ወሰላም ተንቢየው ያለፉት ፊትና መዲና ውስጥ እንደ እሳት ሲቀጣጠል ወንድሜን አሊይ ኢብን አቢ ጣሊብን አልዋጋም በማለታቸው ብቻ ሰዪዲና ዙቤይር ተቃዉሞ ከፋሲቆች ገጥማቸው መንገድ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ በዓምሩ ኢብኑ ጀርሙዝ ይገደላሉ፤ ሰዪዲና ዙቤይር መንገድ ላይ ደማቸው ፈሶ ሙጅሪሞች ያ ንጹህ ደማቸው ላይ ተራመዱ፤ ሰይዲና ዙበይር ባላሰቡበት ወቅት ነው የተገደሉት ዓቲካ ፊታ ጠቆረ፤ ዙቤይር ያስጀመርከኝን ፍቅር ሳታስጨርሰኝ እንደወጣህ ቀረህ..በማለት ታነባ ጀመር፤ ዓቲካ የሐዘን ማዕበል መታት፤ ሌት ተቀን አለቀሰች፤ ሶስት ባል ፤ ሶስት ትዝታ፤ ሶስት ሸሂድ...ሰዪዲና ዙቤይር ብዙ ንብረት ስለነበራቸው ከሌላ ሚስት የወለዳቸው ልጃቸው አብደላ ወደ ዓቲካ መጥቶ ዓቲካ ሆይ አንቺም እናታችን ነሽ የአባታችን ሐቅ ይገባሻል ነይ ውርስ ተካፊዪ ብሎ ሲጠራትየዙቤይር ትዝታ ይበቃኛል ብላ እንቢ ብላ መለሰቻቸው፤ ተመለከቱ እዚህ ላይ ጠያቂዎቹንም ምላሿንም፤
ያ አላህ..አብደላም እቤት ሂዶ ተመልሶ ወደ አቲካ መጥቶ ድርሻዋን ስድስት መቶ ሺህ ዲርሃም አስረከባት፤ የአብደላን እናትንም እዚህ ላይ አደንቃለሁ፤ አይመስላቹሁም?"ሸሃዳን የፈለገ እሷን ያግባት" ሰዪዲና አብደላህ ኢብኑ ዑመር ዓቲካ ሶስተኛ ባሏን አጣች፤ ሰዪዲና ዙበይር ኢብኑ ዓዋም ብዙ ትዝታና የማይረሱ ቀናትን አሳይተዋት ነበር፤ ነገር ግን ከዚህ ሁሉ ሐዘን ጋር የቀረባት ላይ ፈገግ ብላ፤ ሊያጽናናት የሞከረውን ይልቅ እርሷ የአላህ ራህመት ሰፊነቱን በመንገር ትሸኛቸው ነበር ነገር ግን ሰዎች ተሰናብተዋት ሲሄዱ ቤት ውስጥ የሰይዲና ዙበይር ድምጽ፤ አካል የሌለበት ቤት ውስጥ ጭር ብሎ በትዝታ ውቅያኖስ ውስጥ ትዋኝ ነበር።
ሰይዲና ዙበይር አንድ ነገር ትተውላት የሄዱት ልብሳቸው ላይ የነበረው የሚወዱት ኢጥር (ሽታቸው) ነበር፤ ዓቲካ ምነኛ ቻይ ሴት ነች፤ሰዪዲና ዙበይርንም ከመውደዳ የተነሳ ሞተውም እንኳን የሚፈልጉትን ነገር አማልታለች፤ ያ የተወችውንም የመስጂድ ሰላት፤ እንደዚያው ለማቆም ወስና ነበር፤ የባል ሃቅ ከሞት ቡሃላም......... ያሰላም ያ አላህ ወንዶቻችንና ሴቶቻችንን በህይወት እያሉ ያለባቸውን ሁቁቆች የሚያማሉ አድርጋቸው። እዚህ ላይ አሳሳቢው ነገር ለሰይዲና ዙቤይር መገደል መንሲኤ የነበረው በመዲና ውስጥ የተፈጠረው ፊትና ከባድ ደረጃ ላይ መድረሱ ነው፤ከሰዪዲና ዑመር ኢብኑ አል ኸጣብ ቡሃላ ኸሊፋ የነበሩት አሚረል ሙእሚኒን ሰዪዲና ዑስማን ኢብኑ አፋን ከአስሩ በጀነት ቡሽራ ያገኙት ናቸው ረሱል ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም ሰዪዲና ዑስማንን እንደወደዳቸው እንዳወደሳቸው ነው የሞቱት፤ እንዲያውም በኡሁድ ጦርነት ላይ፤ ነቢያችን አሌይሂ ሰላቱ ወሰላም ከሰዪዲና ዑመር ኢብኑ ኸጣብና ሰዪዲና ዑስማን ጋር ይህ ተራራ ላይ ሲወጡ፤ የኡሁድ ተራራ ተንቀጥቅጦ ነበር፤
ረሱልም ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም "ያ እሁድ ተረጋጋ እላይህ ላይ ያለው ነቢይና ሁለት ሸሂዶች ናቸው" ብለው ነበር፤ይህ ፊትና የተጠነሰሰው የመን ውስጥ ይኖር የነበረው የሁዲ ቅጽል ስሙ ኢብን ሰውዳእ ወይም የጥቁራ ልጅ ተብሎ የሚጠራ የአላህ ጠላት ነው፤ እናቱ በጣም ጥቁር ነበረች ይባላል፤ ይህ ሰው የሰዪዲና ዑመርን መሞት እድል ተጠቅሞ እስልምና ተቀብያለሁ በማለት ብዙ ተካታዮችን አፍርቶ መዲና በመሄድ የእስልምናን አቂዳ በመቀየር ማስተማር ጀመረ ፤ ከዚያ ሰሃባዎችን ለማከፋፈል ሞከረ፤ በመጨረሻም አሚር አልሙእሚኒን ዑስማን መገደል አለባቸው አለ፤ሰዪዲና ዑስማን ቤታቸው ቁጭ ብለው ቁርዓን እየቀሩ ሳለ የፊትና ሰዎች መጥተው የቤታቸውን በር በእሳት ካቀጣጠሉ ቡሃላ፤ ቤት ገብተው በሰይፍ ዘጠኝ ጊዜ ወግተዋቸው፤ ሶስቱ ለአላህ ነው ስድስቱ ለራሳችን በማለት....
የመጨረሻ ክፍል ነገ ማታ

266
23:04
18.12.2024
የፈለገ አመድ ቢለብስ እንዳሻው ቢጨቀይ ውበቱ የማይዘንፍ ህፃን ልጅ በጀርባዋ አዝላ መንገድ ዳር ላይ ቆማ ስታለቅስ ጠጋ ብለህ ምን እንደሆነች ጠይቀህ....ባለችበት እንዳትረጋ የቤት ኪራይ ወደአገሯ እንዳትመለስ ትራንስፖርት የቸገራት እንደሆነች ሰምተህ ምንም ነገር ማድረግ ሳትችል ቀርተህ ታውቃለህ?
ታድያ ለምን እንዳስብ ትጠይቀኛለህ? ካሰብኩ ስለሷ...ስለቆንጆው ልጇ አባት መዳረሻ...ምንም ስላለማድረጌ...ለአንድ ምሳ ስለምናወጣው ገንዘብ....ስላሉኝ ልብሶች ውድነት....ስለነዚህ ብሎም ሌሎች ያልነገርኩህ ነገሮች ጋር ሁሉ እጓዛለው #እንዳስብ_እንዳትጠይቀኝ_1

179
22:51
20.12.2024
የ" ሸሂዶች" ሚስት" ክፍል 6
የመጨረሻ ክፍል
ከፍተኛ ወንጀል ሰርተው ነበር፤ ሰይዲና ዑስማን ደማቸው ቁርዓን ላይ ፈሰሰ፤ከዚህ ቡሃላ የፊትና በርን የሚዚጋ ወንድ ጠፋ፤ የአላህ ራህመት ሆኖ ታላላቆቹ ሰሃባዎች ይህ ክስተት ከመፈጠሩ በፊት በጥቂት ጊዜ አከታትለው ታመው ሞቱ፤ በዚህም ሰበብ መዲና ውስጥ እርስ በእርስ ደም መፋሰስ ሆነ፤ይህንን ማየት ያልፈለገውና ወደ አላህ ቶሎ በፍጥነት መሄድ የፈለገው ታላቁ ሰሃቢ ሰዪዲና አሊይ አቢ እብኒ ጣሊብን አንድ መፍትሄ መጣላቸው፤ ዓቲካ!ዓቲካን ለትዳር ጠየቃት፤ ዓቲካም የነበረባት ሐዘን ሳይቀልላት ሰዪዲና አሊይ አቢ እብኒ ጣሊብን አግብታቻቸው ምን እንደሚፈጠር ታውቃለች
ስለዚህ ወዲያው ፍቃደኛ ሳትሆን "ያ አሊይ እኔ ቃል ኪዳን እገባላሃለሁ፤ በቅርቡ ሸሃዳን እንደምታገኝ" አለቻቸው፤ ያ አሊይ ሸሃዳን ለማግኘት እኔን ማግባት አያስፈልግህም አለቻቸው፤ ሰዪዲና አሊይ ዓቲካን በተመኛት በጥቂት ቀናት ሸሃዳን አገኙ፤ ረዲየላሁ አንሁም አጅመዒን፤ከዚህ ቡሃላ ለትዳር የጠየቃትና ለአራተኛ ጊዜ ያገባት ሰዪዲና ሑሴይን አሊይ አቢ ኢብን ጣሊብ የረሱሉላህ ሰለላሁ አሌይህ ወሰለም የልጅ ልጅ ናቸው፤
ዓቲካ ከሰዪዲና ሑሴይን ጋር በመገባታ ከረሱል ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም አማችነትን አገኘች፤ ምነኛ የታደለች ሴት ነች፤እዚህ ላይ ግን ዓቲካ እስካሁን ቤት ሆና ነበር የባሎቻን ሸሃዳ ስትሰማ የነበረው፤ አሁን ግን ሰዪዲና ሑሴይን የሄዱበት ቦታ አብራቸው በመሄድ ጂሃዱ ላይም በመሳተፍ ላይ ነበርች፤ ሸሃዳም ከመጣ ከባላ ጋር አብራ ሸሃዳን አንድ ላይ መቅመስን የምትጠላ ማን ሴት አለች፤ ነገር ግን ኩፋ በሚባለው የኢራቅ ከተማ ውስጥ ሰዪዲና ሑሴይን ዓቲካ ፊት ለፊት ይገደሉና እራሳቸውን ከዚያ አፈር ላይ ብድግ አድርጋ ያለቀሰችው ለቅሶ ገዳዮቹም ሊያዩት ያልቻሉት የሚያሳዝን ክስተት ነበር፤ዓቲካ ሀዘና የከፋ ነበር፤ ዓቲካ ከዚያን ቀን ቡሃላ ተገልላ ስትኖር አይና ይሰወራል፤
አዎ ዓቲካ እነዚያን ወጣቶች በመልካ ማርካ ሊያገባት ቤቷን ጠዋፍ ያደረጉላት፤ ታላልቅ ሰሃባዎችን የማረከች፤ ብዙ ሰው በውበታ ያደነቃት ዓቲካ አይነ ስውር ሆነች፤ ኢባዳዋን አልተወችም፤ እንደገና ለትዳር የሚጠይቃትን ሁሉ ረሱል ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም አማቼ ናቸው፤ በሳቸው ላይ ማንንም አልጨምርም ብላ ተከለከለች፤ዓቲካ በሂጅራ አቆጣጠር በአርባኛው አመት ምህረት ታማ ትሞታለች፤ያ ሁሉ ኸይራት ስራዎቻ፤ አኽላቃ፤ የባል ሐቅ፤ ውዴታና ፍቀራ፤ ሰብርና ዒባዳዋ........... ስንቱ ይወሳል፤ በዚህ ሁሉ ታጅባ ወደ አላህ ሄደች፤ይህቺ ሴት ለአለም ሴቶች ትምሳሌት ነች፤
ዓቲካስ ወደ አላህ ይዛ የሄደችውን ይዛ ሄዳለች፤እህቴ ሆይ አንቺስ ምን ይዘሽ ነው ወደ አላህ የምትሄጂው???

180
22:23
21.12.2024
እዳስብ_እዳትጠይቁኛ የሚል አጭር አስተማሪ ታሪክ እንጀምራለን ከ 7 ደቂቃ ብሀላ
147
22:15
22.12.2024
#እንዳስብ_እንዳትጠይቀኝ_1
የፈለገ አመድ ቢለብስ እንዳሻው ቢጨቀይ ውበቱ የማይዘንፍ ህፃን ልጅ በጀርባዋ አዝላ መንገድ ዳር ላይ ቆማ ስታለቅስ ጠጋ ብለህ ምን እንደሆነች ጠይቀህ....ባለችበት እንዳትረጋ የቤት ኪራይ ወደአገሯ እንዳትመለስ ትራንስፖርት የቸገራት እንደሆነች ሰምተህ ምንም ነገር ማድረግ ሳትችል ቀርተህ ታውቃለህ?
ታድያ ለምን እንዳስብ ትጠይቀኛለህ? ካሰብኩ ስለሷ...ስለቆንጆው ልጇ አባት መዳረሻ...ምንም ስላለማድረጌ...ለአንድ ምሳ ስለምናወጣው ገንዘብ....ስላሉኝ ልብሶች ውድነት....ስለነዚህ ብሎም ሌሎች ያልነገርኩህ ነገሮች ጋር ሁሉ እጓዛለው#እንዳስብ_እንዳትጠይቀኝ_1

145
22:47
22.12.2024
#እንዳስብ_እንዳትጠይቀኝ_2
ቤት ውስጥ አስቀምጦ ለሚንከባከባቸው እጅ እጁን ለሚያዩት ነፍሶች ሲል እየለፋ የሚውል....ለምሳው እንኳን ብር ማውጣት የተሻለ ህይወት ለመስጠት የሚያጠራቅመውን ገንዘብ አጉዳይ ሆኖበት ምግብ አምጣ የሚለው ስሜቱን እንደምንም ገቶ አመሻሽ ላይ ቤት ሲገባ ምግብ የማይዘጋጅለት <<እንዳንተ አልደላኝም ከፈለክ አብስለህ ብላ ያውልህ>>የሚባል ባል....በወለዳቸው ልጆች ስክነት ቀርቶ ንቀት የሚቀበል አባት አይተህ ታውቃለህ?
ታድያ ለምን እንዳስብ ትጠይቀኛለህ? ካሰብኩ ስለ እሱ....ባልነቱም አባትነቱም ከንቱ የሆነበት ሰው ስለሚሰማው ስሜት.... መሪ የተናቀበት አለም ምን እንደምታፈራ....አባት በዝምታ የሚብሰለሰልበት በደል ምን አይነት በላዕ ይዞብን እንደሚመጣ....ስለብዙ ነገሮች ጭንቅ ይይዘኛል #እንዳስብ_እንዳትጠይቀኝ_2

53
21:50
25.12.2024
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
1 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
c
**ffeennew@******.io
30.10.202412:56
5
Everything is fine. Thank you!
Top Rated in the Topic
New items
Channel statistics
12.4
5.0
1
2.2K
4.4%
0.0
lock_outline
Selected
0
channels for:$0.00
Followers:
0
Views:
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий