
- Main
- Catalog
- News and Media
- Sheger Press️️
Sheger Press️️
New information
Information is delivered through the channel without delay or overnight
Over 40,000 Subscribers Interactive and Highly Active Audience, Stay in a Business and Stay ahead of your Competitors.
You can advertise here with us
Channel statistics
ሀገሬ ቴሌቪዥን አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጣምራ የሚዘጋጁትን የ 2026 ዓለም ዋንጫ በኢትዮጵያ በብቸኝነት የማሰራጨት መብት አግኝቷል።
የቴሌቪዥን ተቋሙ ከሰሀራ በታች አለም ዋንጫዉን የማሰራጨት መብት ካለዉ ኒው ወርልድ ጋር ከስምምነት በመድረስ ለማስተላለፍ ተስማምቷል።
በመጀመሪያ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የነበረ ሲሆን ጌታችን ሲመጣ እርሱን ተከትሏል፡፡ ከጌታ ዕርገት በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉም ጸጋው በዝቶ ከታደሉት አንዱ ነበር፡፡ 8 ሺውን የክርስቲያን ማኅበር እንዲመሩ ሰባት ዲያቆናት ሲሾሙም ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ሆኗል፡፡ ወንጌልን እየሰበከ ሲጋደል አይሁድ ትምህርቱን ቢሳናቸው ክርስትናን ለማጥፋት እርሱን መግደል እንዳለባቸው ስላመኑ በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ወልድን በአብ ቀኝ ይመለከተው ነበር። ስለ ወጋሪዎቹ ምሕረትን ሲለምን ሰማያዊ የሰማዕትነት አክሊል ተቀዳጀ።
ቅዱስ እስጢፋኖስ ከአረፈ ከ300 ዓመት በኋላ በኢየሩሳሌም የሚኖር ሉኪያኖስ የተባለ ደግ ሰው በተደጋጋሚ በራዕዪ እየተገለጸለት "ሥጋዬን አውጣ" ሲለው ለጳጳሱ ነገራቸው። ጳጳሱም ካህናትና ምዕመናንን ሰብስበው ወደ አፀደ ገማልያል ማለት ወደ መምህሩ ሄደ። ቦታውንም በቆፈሩ ጊዜ ታላቅ መነዋወጥ ሆነ። መላዕክት ሲያጥኑም በጎ መዓዛ ሸተተ። ዝማሬ መላዕክትም ተሰማ። ሕዝቡና ጳጳሱም በቅዱስ እስጢፋኖስ ፊት ሰግደው በታላቅ ዝማሬና በሐሴት ዐፅሙን ከዚያ አውጥተው በጽርሐ ጽዮን በተቀደሰችው ቤት አኖሩት። እለ እስክንድሮስ የተባለ ደግ ሰውም ቤተክርስቲያን አነጸለት ወደዚያ አገቡት።
ከአምስት ዓመታት በኋላም እስክንድሮስ ሲያርፍ በሳጥን አድርገው በቅዱሱ ጎን አኖሩት። የእለ እስክንድሮስ ባለቤት ግን ወደ ሀገሩዋ ቁስጥንጥኒያ ስትመለስ የባሏ ሥጋ መስሉዋት የቅዱስ እስጢፋኖስን ቅዱስ ሥጋ በመርከብ ጭና ወሰደችው። መንገድ ላይም ከሳጥኑ ውስጥ ዝማሬ ሰምታ ብታየው ያመጣችው የቅዱሱን ሥጋ ነው። እጅግም ደስ አላት አምላክ ለዚህ አድሉዋታልና። እርሷም ወስዳ ለታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጥንጢኖስ አስረከበችው። በከተማው ታላቅ ሐሴት ተደረገ። ሥጋውን ሊያኖሩት በበቅሎ ጭነው ሲወስዱትም በቅሎዋ በሰው ልሳን ተናግራ ማረፊያውን አሳወቀች። በዚያም ላይ ትልቅ ቤተክርስቲያን ታንጾለታል። ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አሳልፈው የሰጡ ቅዱሳንና ሰማዕታትን የሚዘክሩ በአማላጅነታቸው የሚማጸኑ ገዳማውያን በረከታቸው የበዛ ነው፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
በአጭር ቪዲዮዎቹና በሚያስቅ የፊት እንቅስቃሴዎቹ በመላው ዓለም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮችን ማፍራት የቻለው ኡጋንዳዊው ታዋቂ የሶሻል ሚዲያ ኮከብ ቴንጌ ቴንጌ (Tenge Tenge) በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በሚካሄደው ታሪካዊው የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ላይ ለመገኘት ጉዞውን ወደ አዲስ አበባ ማድረጉ ተረጋግጧል።
ኢትዮጵያ እመጣለሁ!" ሲል መልዕክቱን ያስተላለፈው ቴንጌ ቴንጌ፣ በጉባኤው ላይ ከሚገኙ ከ200 በላይ የአፍሪካ ታዋቂ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች መካከል አንዱ ይሆናል።
ይህ ጉባኤ "ተፅዕኖ ለተሻለች አፍሪካ" በሚል መሪ ቃል በታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚካሄድ ነው።
የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026)
May 7 & 8, 2026 አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም.
ይህ ጉዞ ለቴንጌ ቴንጌ ደጋፊዎች ትልቅ አጋጣሚ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ቆይታውም ከተለያዩ የኢትዮጵያ የጥበብና የዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎች ጋር እንደሚገናኝ ይጠበቃል።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቆናል።
በሌላ በኩል ፦
- የሬሜዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም ➡️ ግንቦት 19 ኢድ አልአድሃ
- የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም
- የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሃምሌ 29 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም
- የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ጥናትና ምርምር መረጃ መሰብሰብ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ... ይሰጣል።
tikvah
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቆናል።
በሌላ በኩል ፦
- የሬሜዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም ➡️ ግንቦት 19 ኢድ አልአድሃ
- የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም
- የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሃምሌ 29 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም
- የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ጥናትና ምርምር መረጃ መሰብሰብ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ... ይሰጣል።
tikvah
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ብልጽግና ፓርቲን በመወከል በአዲስ አበባ ከተማ ለፓርላማ አባልነት ዕጩ ሆነው ቀርበው የነበሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተተኩ። ዶ/ር ሳሙኤል ከምርጫው ራሳቸውን ያገለሉት “በግል ምክንያት” እንደሆነ ለ“ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
ዶ/ር ሳሙኤል ገዢው ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ ለፓርላማ እንዲወዳደሩ ካቀረባቸው 20 ዕጩዎች መካከል አንዱ ነበሩ። ዕጩው በስድስተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲን በመወከል ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ተመርጠው እንደነበር ይታወሳል።
ብልጽግና ፓርቲ ባለፈው መጋቢት ወር መጀመሪያ ይፋ ባደረገው የዕጩዎች ዝርዝር፤ ዶ/ር ሳሙኤል ፓርቲውን በመወከል በአራዳ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ምርጫ ክልል 2 እና 14 ለፓርላማ እንደሚወዳደሩ አስታውቆ ነበር። ዶ/ር ሳሙኤል ገዢው ፓርቲ ባዘጋጃቸው የዕጩዎች ማስተዋወቂያ ይፋዊ መድረኮች ላይ በመገኘት ተወዳዳሪነታቸውን አረጋግጠዋል።
ሆኖም የእርሳቸው ዕጩነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኃላፊነታቸው ጋር የሚቃረን መሆኑን በህግ በማስደገፍ የገለጹ ወገኖች ተወዳዳሪነታቸውን ጥያቄ ውስጥ ከተውታል። እነዚህ ወገኖች የሚጠቅሱት ድንጋጌ፤ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎችን ለመደንገግ በ2016 ዓ.ም በወጣ አዋጅ ላይ የተካተተ ነው።
Via Ethiopia Insider
"ቴዲ አፍሮ እስካሁን በደኅና ሁኔታ ላይ ይገኛል" ተብሏል
የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ስቱዲዮ በታጠቁ አካላት መዘረፉን የጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ዘግቧል።
ዘረፋው የተፈፀመው ትላንት ሚያዚያ15/2018
ዓ.ም. ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ ሲኤምሲ አካባቢ በሚገኘው የአርቲስቱ ስቱዲዮ ውስጥ ነው።
መሣሪያ የታጠቁ እና በተሽከርካሪ የመጡ አካላት የስቱዲዮን ጠባቂዎች በመደብደብ አርቲስቱ ለሙዚቃ ሥራው የሚጠቀምባቸውን ንብረቶች መውሰዳቸውን ዘገባው አመልክቷል።
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን «ኢቶሪካ» የተሰኘው የሙዚቃ አልበሙ ከመውጣቱ በፊት ጀምሮ የሥነልቡና ጫና ሊያደርሱ የሚችሉ ወከባዎች በአካባቢው እየተፈጸሙ ቢሆንም፣ እንቅስቃሴው ቢገታም እስካሁን በደኅና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ዶቼ ቬለ ከምንጮቼ አገኘሁት ባለው መረጃ ገልጿል።
ቴዲ አዲሱን አልበም ለአድማጮች ካደረሰ በኋላ የቅርብ ወዳጁ እንዲሁም ቃልአቀባዩ እና ምክትል ማናጀሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።
@sheger_press
@sheger_press
የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳኗ ዘወትር ይታሰባል
ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ የኪዳነ ምሕረት ሥዕል በመባል የሚታወቀው ሥዕል በቤተ ክርሰቲያናችን በስፋት ከሚሳሉት የወላዲተ አምላክ ሥዕል ጭብጦች ውስጥ አንዱ ሲሆን። ከጌታችን ኢየሱስ ቃልኪዳን ስትቀበል በጎሎጎታ የሚያሳየው ሥዕል ትክክለኛው ገላጭ ሥዕል ሲሆን፤ ይህ ሥዕል እንደ ቤተ ክርስቲያኑ ስፋት የሚጨመረው ጭብጥ ሊለያይ ይችላል፡፡
ለምሳሌ በዚህ ሥዕል ዘይቤ ላይ የሚታዩት መላእክት ቁጥራቸው ሊበዛ አሊያም ሊያንስ ይችላል፡፡ በዚህ ሥዕል እመቤታችንና ጌታችን ቆመው አሊያም ተቀምጠው ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ የእናቱን ቅዱሳን እጆች በመያዝ ቃል ኪዳን ሲገባላት አሊያም በቅዱሳት እጁ ቃል ሲገባላት የሚያሳይ ዓይነት ሥዕል ነው፡፡ በዚህ መልኩ እመቤታችን ከተሳለችባቸው አብያተክርስቲያናት መካከል ጎርጎራ ደብረ ሲና (17ኛው መ.ክ.ዘ)፣ አብርሐወ አጽብሐ (19ኛው መ.ክ.ዘ)፣ መቐለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (20ኛው መ.ክ.ዘ)፤ ከጥንታውያን ብራና መጻሕፍት ከተመለከትን በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ግምጃ ቤት የሚገኘው የ17ኛው መ.ክ.ዘ ተአምረ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ገዳማውያንም ዘወትር በሥዕሏ ፊት ቆመው ይለምኗታል፡፡ እርሷም ልመናና ጸሎታቸውን ታሳርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸውመ እንካፈል፡፡
ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተሰጠው ኪዳን፣ ቀድመው ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነው፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም ዕለቱ በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ ለሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና የተቸገሩትን መርዳት ይገባናል፡፡ ገዳማውያን በበቃል ኪዳኗ ታምነው፣ ዘወትር በሥዕሏ ፊት በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
በአዲስ በተሻሻለው የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 310/2018 የተካተቱ ነጥቦች፦👇👇
የአማራ ክልል መንግሥት የነበረውን አዋጅ ቁጥር 252/2009 በመሻር አዲሱን የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 310/2018 በሥራ ላይ አውሏል።
ይህ አዋጅ ከፌደራል የገጠር መሬት ሕግ (1324/2016) ጋር የተጣጣመ ሲሆን፣ ከመሬት ምዝገባ ጀምሮ እስከ ይዞታ ዝውውር፣ ከብድር ዋስትና እስከ መሬት ኪራይ እንዲሁም የባለይዞታዎችን መብትና ግዴታ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያሉና መሠረታዊ ለውጦችን ይዟል።
የባለይዞታዎችን መብት የሚያሰፉ 9 ዋና ዋና ነጥቦችን እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርበዋል።
1. የአዋጁ ተፈጻሚነት ወሰን (Scope of Application) አንቀጽ 3 በቦታ ረገድ (Territorial Scope)፦
🔎 በገጠር መሬት ላይ፦ በክልሉ ውስጥ በሚገኝ ማንኛውም የገጠር መሬት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።
🔎 በከተማ አስተዳደሮች ሥር ባሉ የገጠር ቀበሌዎች፦ በከተማ አስተዳደር ሥር ቢሆኑም የገጠር ይዘት ባላቸውና በገጠር ቀበሌነት በተዋቀሩ አካባቢዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።
🔎 ርክክብ ባልተፈጸመባቸው የከተማ ወሰን መሬቶች፦ አንድ አካባቢ ወደ ከተማ ወሰን እንዲገባ ተደርጎ፣ ነገር ግን በከተማውና በገጠር መሬት አስተዳደር መካከል የይዞታ ርክክብ እስካልተፈጸመ ድረስ በዚህ አዋጅ መመራቱን ይቀጥላል።
👉በይዞታና ጉዳዮች ረገድ (Subject Matter Scope)፦
🧿 በሁሉም የይዞታ ዓይነቶች፦ በግል፣ በወል (በጋራ) እና በመንግሥት የገጠር መሬት ይዞታዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።
🧿 የሕግ ተቃርኖን ለመፍታት፦ የገጠርና የከተማ መሬት አስተዳደር ወሰን ላይ ይፈጠሩ የነበሩ ግራ መጋባቶችን ለመቅረፍ እንዲቻል፣ የገጠር መሬት ይዞታ ምን ማለት እንደሆነና የሚገኝበትን አስተዳደራዊ ወሰን በማያሻማ ሁኔታ ይገልጻል።
👉ልዩ ሁኔታዎች (Exceptions)፦
🧿 ልዩ ጥበቃ የሚደረላቸው መሬቶች፦ ለደን ልማት፣ ለዱር እንስሳት ጥበቃና ለማዕድን ልማት ተከልለው የተያዙ መሬቶችን በተመለከተ፣ አዋጁ እንደ አስፈላጊነቱ ተፈጻሚ ቢሆንም፣ በዘርፉ የወጡ ልዩ ሕጎች (Specific Laws) ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚችል ይጠቁማል።
2. የመሬት ማግኘት መብትና ተጠቃሚነት (አንቀጽ 4-8)
🧿 ነፃ መሬት፦ በግብርና መተዳደር የሚፈልግ የክልሉ ነዋሪ (ዕድሜው 18+) መሬት በነፃ የማግኘት መብት አለው።
🧿 ቅድሚያ የሚሰጣቸው፦ ወላጅ የሌላቸው ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ አቅመ ደካሞች፣ ሴቶችና ወጣቶች ልዩ ትኩረትና የቅድሚያ መብት ይሰጣቸዋል።
🧿 የመብት ቆይታ፦ የአርሶ አደሮች፣ ከፊል አርብቶ አደሮችና የሃይማኖት ተቋማት መብት የጊዜ ገደብ የሌለው (ለዘላለም) ነው። መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግን ለሥራቸው አስፈላጊ እስከሆነ ጊዜ ብቻ ይፈቀድላቸዋል።
3. የይዞታ ዝውውር (ኪራይ፣ ስጦታና ውርስ)
🎙 ኪራይ (አንቀጽ 9)፦ ባለይዞታው ከግማሽ የማይበልጥ ይዞታውን ማከራየት ይችላል። (አረጋውያንና አቅመ ደካሞች ግን ሙሉውን ማከራየት ይችላሉ)። የጊዜ ገደብ፦ ለቋሚ ተክል እስከ 30 ዓመት፣ ለሰብል እስከ 10 ዓመት።
🎙 ስጦታ (አንቀጽ 11)፦ ለሥጋ ዘመድ ወይም "በይጦረኛል" ውል ለማንኛውም ሰው በጽሑፍ መስጠት ይቻላል።
🎙 ውርስ (አንቀጽ 12)፦ ማንኛውም ሰው (የመንግሥት ሠራተኛን ጨምሮ) በኑዛዜ ወይም ያለኑዛዜ በፍትሐ ብሔር ሕጉ መሠረት መሬት መውረስ ይችላል። ይህም ቀደም ሲል የነበረውን ገደብ ያነሳ ትልቅ ለውጥ ነው።
4. ንብረት መሸጥና በጋራ ማልማት (አንቀጽ 13-19)
🖍 የንብረት ሽያጭ፦ በመሬት ላይ የለማን ቋሚ ንብረት (ቤት ወይም ቋሚ ተክል) መሸጥ ይቻላል። ቋሚ ተክል ከሆነ ሙሉ በሙሉ ከለማ ግማሹን፣ በከፊል ከለማ ግን የለማውን ማሳ መሸጥ ይፈቀዳል።
🖍 ከባለሀብት ጋር ማልማት፦ ባለይዞታው የመጠቀም መብቱን እንደ ካፒታል በመጠቀም ከባለሀብት ጋር በጋራ ማልማት ይችላል።
5. የብድር ዋስትና (አንቀጽ 15)
🖲 የመሬት የመጠቀም መብትን (Usufruct right) ለፋይናንስ ተቋማት ለብድር ዋስትና ማስያዝ ይቻላል።
🖲 የዋስትና ዘመኑ ቢበዛ እስከ 10 ዓመት ይቆያል። ተበዳሪው ካልከፈለ አበዳሪው መሬቱን ለተወሰነ ጊዜ በመጠቀም ዕዳውን ያስመክሳል።
6. ዲጂታል ምዝገባና የይዞታ ማረጋገጫ (አንቀጽ 61-62)
📡 ዲጂታላይዜሽን፦ የመሬት መረጃ አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ በዲጂታል ሥርዓት መመራት እንዳለበት በአስገዳጅነት ተደንግጓል።
💳 የምስክር ወረቀት፦ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በመሬት ላይ ያለን መብት የሚያረጋግጥ "የመጨረሻና ፍጹም" ማስረጃ ሆኖ ያገለግላል።
7. ይርጋና የግጭት አፈታት (አንቀጽ 14 እና 73)
⚫️ የይዞታ ክስ ይርጋ፦ መሬት ያለአግባብ የተወሰደበት ሰው በ15 ዓመት ውስጥ ክስ ማቅረብ አለበት (ቀደም ሲል 10 ዓመት የነበረው መሻሻሉን ልብ ይሏል)።
⚫️ የወርሻ ይርጋ፦ ውርሱ ከተከፈተ በ3 ዓመት ውስጥ መጠየቅ አለበት።
⚫️ ሽምግልና፦ ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓቶችና ሽምግልና እንደ አማራጭ የመፍትሔ መንገድ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
8. የተጋላጭ ወገኖችና የአንድ በላይ ሚስት መብት (አንቀጽ 25)
✏️ አንድ ባል ከአንድ በላይ ሚስት በሚኖረው ጊዜ፣ የሴቶችን መብት ለመጠበቅ ሲባል የጋራ መሬቱ ተከፋፍሎ በየስማቸው እንዲመዘገብና ባልየው አዲስ በሚመሠርተው ትዳር ላይ በራሱ ድርሻ ላይ ብቻ እንዲመዘገብ ይደረጋል።
9. የአጠቃቀም ገደቦችና ግዴታዎች (አንቀጽ 33-35)
🖍 መሬትን የመንከባከብና የአፈር መሸርሸርን የመከላከል ግዴታ ተጥሏል።
🖍 ተዳፋትነቱ ከ60% በላይ የሆነ መሬት ለሰብል እርሻ መጠቀም የተከለከለ ሲሆን ለዛፍ ልማት ብቻ መዋል አለበት።
🖍 ግዴታን አለመወጣት ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ የመጠቀም መብትን እስከ ማጣት የሚያደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ ያስከትላል።
👉 አዋጁ የጸናበት ቀን፦ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም
መረጃው የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ነው።
Reviews channel
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Sheger Press️️ is a Telegram channel in the category «Новости и СМИ», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 37.0K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 7.4, with 0 reviews and an average score of 0.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 48.0 ₽, and with 24 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий