Save up to 70% on New Year Sale
Make the most of the season — grab the best ad placements by January 10!
Get discount
17.7
Advertising on the Telegram channel «Amharic Spritual Books»
5.0
Blogs
Language:
English
191
1
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ መፅሐፍት ፣ መፅሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚረዱ ... የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያዎች ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች እንዲሁም መንፈሳዊ ጹሑፎች ይቀርባሉ ። "Christlikeness is the goal of every true believer."
Share
Add to favorite
Channel temporarily not accepting requests
Choose another channel from recommendations or get a tailored list within your budget using AI
AI Channel Picker
Recent Channel Posts
#ሁልጊዜ_በእግዚአብሔር_ደህና_ሆኖ_መኖር!
በመንፈስ ቅዱስ፣ በእግዚአብሔር ጸጋ ተጠብቆ መኖር፣ ከመንፈሳዊ ድርቅ ራስን መሸሸግ፣ ዘወትር በእግዚአብሔር ጸጋ ላይ በመደገፍ ሁለንተናን ማበርታት፣ እግዚአብሔር ሰፈር በመዋል ለእግዚአብሔር መብዛት፣ መንፈሳዊነትን በሚናጠቅ በዚህ ዓለም ላይ እየኖሩ ዘወትር በእግዚአብሔር ደህና፣ ጤነኛ መሆን ከእኛ ይጠበቃል። በወደቀው ዓለም፣ በክፉና በጠማማ ትውልድ መሃል ለእግዚአብሔር እንደ ከዋክብት ማብራት፣ የልጁን የኢየሱስን መልክ እንደ መስታወት እያንጸባረቁ መኖር የሚቻለው እግዚአብሔር ላይ የሙጥኝ በማለት፣ ዘወትር በህልውናው በመሞላት ነው።
ጸጋ ይብዛልን!!
900
20:42
19.12.2024
"በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእርሱ የተነሣ ነው፤ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፣ ጽድቃችንና ቅድስናችን፣ ቤዛችንም ሆኗል።"
1ቆሮ 1:30
830
07:58
20.12.2024
#የነፍስ_መልሕቅ
ከፊት ያለውን ተስፋ ለመያዝ ወደ እግዚአብሔር ለሸሸ ሰው የነፍስ መልሕቅ አለው፤ ተስፋውም እግዚአብሔር በራሱ የማለበት ጽኑ እና አስተማማኝ ተስፋ ነው። ከከንቱው ዓለም ወደ እግዚአብሔር ለሸሸ ሰው በነውጥ ውስጥ የሚያጸና ጽኑ ተስፋ አለው፣ የነፍስ መልሕቅ አለው። እግዚአብሔር የማይለወጥ ዐላማውን የተስፋው ቃል ወራሾች ለሆንነው ለእኛ በራሱ ምሎ ግልጽ አድርጓል፤ በዚህም ብርቱ መጽናናት አግኝተናል። የተገባልን ቃል ኪዳን፣ የተሰጠን የተስፋ ቃል ጽኑና አስተማማኝ መሆኑን የምናውቀው ከመጋረጃው በስተ ጀርባ ወዳለው ውስጠኛ መቅደስ ስለ እኛ ቀድሞ የገባውን፣ በዚያም እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነውን ኢየሱስን በማየት ነው። በነፍሳችን መልሕቅ ከነውጥ ተጠብቀን፣ አይኖቻችንን ጽኑና አስተማማኝ በሆነው ተስፋችን ላይ ተክለን መኖር ይሁንልን!!
ዕብራውያን 6 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጥ ይምላሉ፤ መሐላውም የተባለውን ነገር ስለሚያጸና፣ በመካከላቸው የተነሣው ክርክር ሁሉ ይወገዳል።
¹⁷ እግዚአብሔር የማይለወጥ ዐላማውን ለተስፋው ቃል ወራሾች ግልጽ ለማድረግ ስለ ፈለገ፣ በመሐላ አጸናው፤
¹⁸ እግዚአብሔር ከቶ ሊዋሽ አይችልም፤ እርሱ በሁለት በማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንድናገኝ አድርጎአል።
¹⁹ እኛም የነፍስ መልሕቅ የሆነ ጽኑና አስተማማኝ ተስፋ አለን፤ ይህም ተስፋ ከመጋረጃው በስተ ጀርባ ወዳለው ውስጠኛ መቅደስ ይገባል።
²⁰ ይህም ስፍራ ኢየሱስ ስለ እኛ ቀድሞ የገባበት ነው። እርሱም እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት ሆኖአል።
907
00:13
21.12.2024
ፈጥኖ መብቀል ላለመጠውለግና ላለመድረቅ ዋስትና አይሆንም። ፈጥኖ መብቀል ሥር መስደድ ካልታከለበት ዋስትና የለውም። ምክንያቱም በፀሐይ በተመቱ ጊዜ ሳይጠወልጉ፣ ሳይደርቁ ጸንተው የሚቆሙት ስስ ዐፈር ስላለው ፈጥኖ ለመብቀል በሚያመቸው ድንጋያማ መሬት ላይ የተተከሉት ሳይሆኑ በመልካም መሬት ላይ ተተክለው፣ ሥር የሰደዱትና የጸኑት ናቸው። የእግዚአብሔርን ቃል በደስታ ሰምተን በፍጥነት እንደምንቀበለው ሁሉ በደስታ እንጽናበት፣ ሥር እንስደድበት፣ ፍሬ እናፍራበት።
ማቴዎስ 13 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ አንዳንዱ ዘር ዐፈሩ ስስ በሆነ፣ ድንጋያማ መሬት ላይ ወደቀ፤ ዐፈሩ ስስ ስለ ሆነም ፈጥኖ በቀለ።
⁶ ነገር ግን ፀሓይ ሲመታው ጠወለገ፤ ሥር ባለ መስደዱም ደረቀ።
…
²⁰ በድንጋያማ መሬት ላይ የተዘራው፣ ቃሉን ሰምቶ ወዲያውኑ በደስታ የሚቀበለውን ሰው ይመስላል።
²¹ ነገር ግን ሥር መስደድ ባለመቻሉ ብዙ አይቈይም፤ በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት ሲመጣ ወዲያውኑ ይሰናከላል።
1053
08:43
21.12.2024
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው።
830
20:28
22.12.2024
«ከወንጌሉ የሚመችህን ብቻ መርጠህ እያመንክ የማይመችህን ገለል የምታደርግ ከሆንክ፣ እያመንክ ያለኸው በወንጌሉ ሳይሆን በራስህ ነው።»
ቅዱስ አውገስጢኖስ
550
21:00
25.12.2024
close
Often Purchased with This Channel
Top Rated in the Topic
New items
Selected
0
channels for:$0.00
Followers:
0
Views:
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий