
Monetize Telegram Mini App with Telega.io
Connect your app, set CPM, and watch your revenue grow!
Start monetizing
12.4

Advertising on the Telegram channel «የመምህራን አንደበት !»
5.0
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$3.60$3.60local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
ከስብራት ሁሉ የአስተሳሰብ ስብራት ቶሎ ካልታከመ ህመሙ ከባድ ነው!
(በመምህር እምኩሉ )
ሰው ከብጤው የሰው ልጅ ጋር ሲኖር የሚጋራቸው መልካም ነገሮች እንዳሉ ሁሉ መጥፎ ነገርንም ሳይወድ በግዱ ይካፈላል፡፡ መተቃቀፍ ብቻ ሳይሆን መተናነቅም አለ፡፡ መሳሳም እንዳለ ሁሉ መነካከሰም ይኖራል፡፡ በፍቅር እፍፍ ማለት ብቻ ሳይሆን በጥላቻም ትፍፍ መባባልም የገሃዱ ዓለም አውነታ ነው፡፡ በዚህ ሰጥቶ መቀበል በሚመስል ማህበራዊ ውል ውስጥ መጠቃቀም ብቻ ሳይሆን መጎዳዳትም የማይቀር ነው፡፡ መዋደድ እንዳለ ሁሉ መደባበርም ይኖራል፡፡ ያለሷ ያለእሱ አይሆንልኝም እንደተባለ ሁሉ እሱ-እሷ እያሉ ጣት መጠቋቆምና መፈራረጅ ጊዜውን ጠብቆ ሊመጣ ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ በፍቅር የተጀመረ ሁሉ በፍቅር አያልቅም፡፡ ለወዳጅነት ያልነው ጠላት ሆኖ አላስወጣ አላስገባ ባይ ሊሆን ይችላል፡፡ ሚዛን፣ ማስተዋል፣ መጠን፣ ወሰን፣ ገደብ፣ ፍሬን፣ ቀይ መስመር የሌለው ምንም ነገር አደጋ ማምጣቱ የማይቀር ነው፡፡ ልብን የሚሰብር፣ ህሊናን የሚጎዳ የትኛውም አደጋ ግን ከሁሉ የከፋ ነው፡፡
ህሊናው ሳይበደል ልቡ ሳይጎዳ የሚኖር ሰው አይገኝም፡፡ ያሰቡት ሳይሳካ፣ የተመኙትን ሳያገኙ ሲቀር ልብ ይጎዳል፡፡ ልብ ስሜታዊ ነው፤ ተስፋ ለመቁረጥ ይቸኩላል፡፡ ልብ በደል አይችልም፤ ልብ የለመደውን ማጣት ይከብደዋል፡፡ ልብ ከሚወደው ሲለይ ያዝናል፡፡ ልባችን ያልተሰበረበት ነገር ማግኘት አዳጋች ነው፡፡ እንግሊዛዊው የስነመለኮት ሊቅ ሲኤስ ሊዊስ ሚስቱን በሞት ሲነጠቅ የገጠመው የልብ ስብራት ሃያል ነበር፡፡ ‹‹A Grief Observed›› በተባለ መፅሐፉ ‹‹ልብ የተሰራው ሊሰበር ነው (The heart was made to be broken.)›› እስከማለት ደርሷል፡፡ በእሱ አገላለፅ የልብ ስብራት ወይም የስሜት ጉዳት የተፈጥሯችን አንድ አካል ነው ማለቱ ነው፡፡ ሊዊስ እንደጥልቅ አሳቢነቱና እንደስነመለኮት ተመራማሪነቱ ብቻ የዳር-ተመልካች ሆኖ አይደለም የስሜት ጉዳትን በመፅሐፎቹ የሚገልጸው፡፡ በተግባር ሚስቱን አጥቶ በሀዘን ውስጥ ሆኖ መከራውን ቀምሶ ነው የደረሰበትን የስሜት ጉዳት ጠባሳ የሚተነትነው፡፡ ሊዊስ ‹‹The Problem of Pain›› በተባለ በሌላኛው መፅሐፉ ‹‹እግዚአብሔር በደስታችን ጊዜ ሹክ ይለናል፤ በህሊናችን ያወጋናል፡፡ ስሜታችን በተጎዳ ጊዜ ግን ጮክ ብሎ ይናገረናል፡፡ በዚህ ድምጹ ነው ይሄን ደንቆሮ ዓለም የሚቀሰቅሰው፡፡ God whispers to us in our pleasures, speaks in our conscience, but shouts in our pain: it is His megaphone to rouse a deaf world.›› በማለት ነበር ሀዘን ሊያስደነግጠን ብቻ ሳይሆን አስተምሮ ሊያነቃን እንደሚችል የሚገልፀው፡፡ ሊዊስ የስሜት ጉዳት ወይም Trauwma ምናልባት ሰንበር ወይም ምልክት ሊተው ይችል ይሆናል ነገር ግን ለተማረበት ብዙ ትምህርትም ያገኝበታል የሚል እምነት አለው፡፡ ሀዘን ወይም መከራ አንገት የምንደፋበት ብቻ ሳይሆን ትምህርት ቀስመንበት አንገታችንን ቀና የምናደርግበት መሆኑን ያሰምርበታል፡፡
ብዙዎቻችን ህክምና የምንሄደው ለአካላዊ ጉዳታችን ነው፡፡ ለተጎዳው ስሜታችን፤ ለተጎሳቆለው መንፈሳችን፤ ለልባችን ቁስል እህህ እያሉ ከመሰቃየት ውጪ ለመታከም የምንፈቅድ በጣም ጥቂቶች ነን፡፡ ያልታከመ፣ ያልደረቀ፣ ያልሻረ ቁስል ይዘን እያከክነው የምንሰቃይ ብዙ ነን፡፡ በልጅነታችን አዕምሮ ውስጥ ተቀርፆ የቀረ ውሰጣችንን እያመነመነ ያለ የአስተሳሰብ ህመም በብዙዎቻችን ዘንድ አለ፡፡ በጥርስ የሸፈንነው፤ በልብስ የደበቅነው፣ በቅባት የሸሸግነው፣ በገንዘብ የጋረድነው፤ በመከበብ ሆነ ብለን ችላ ያልነው ብዙ ውስጣዊ መከራ አለብን፡፡ በግልም ይሁን በሀገር ደረጃ ያልጠገንነው ልብና ያልታከምነው ጠባሳ እልፍ ነው፡፡ በተለይ በእኛ ሐገር የቆሰለ ልብ በየቦታው ሞልቷል፡፡ የስነልቦና፣ የመንፈስ፣ የአስተሳሰብ፣ የስሜትና የአካል ቁስል ያልደረሰበት አይኖርም፡፡ ህጻናቱ እንኳን በማያውቁት ነገር በአዋቂዎች ስነልቦናዊ፣ ባህላዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጣጣ ትንሸዋ ሕሊናቸው እየቆሰለች ነው፡፡ ሴት ወንድ፤ ትንሽ ትልቅ፤ የተማረ ያልተማረ፤ ተራ ባለስልጣን፤ ባለዝና፣ ወዘተ ሁሉም የልብ ስብራት የደረሰበትና በጠባሳ የተመታ ነው፡፡ ጥቂቱ ከቁስሉ ያገገመ ነው፡፡ አብዛኛው ግን ቁስሉ በደንብ ያልሻረ፣ ጠባሳውን እያደማ ሁልጊዜ የሚሰቃይ ነው፡፡
ወዳጄ ሆይ… መፅሐፈ ሲራክ ‹‹ከቁስል ሁሉ የልብ ቁስል ይከፋል›› እንዲል በጊዜው ያልታከመ የአስተሳሰብ ቁስል መላ ሕይወትህን ይረብሻል፡፡ ዘመናዊው የስነልቦና ሳይንስ እንደሚለው ጠባሳ ማለት የሆነብህ ወይም የደረሰብህ ነገር ሳይሆን በሆነብህ ወይም በደረሰብህ ነገር ምክንያት የተጎዳው ስሜትህ ነው (Trauma is not what happens to you, it’s what happens inside you as a result of what happened to you.)፡፡ የደረሰብህን ወይም የሆነብህን ነገር ባትወደውም መቀበል ፍቱን መድሐኒት ነው፡፡ አዳፍነህ መተውም የአዕምሮ ሰላም አይሰጥህም፡፡ በመጠጥ ወይም በሌላ አጉል ሱስ ልትሸሸው ብትሞክር አይቻልህም፡፡ ከስካርህ ስትወጣ ወይም ከሽሽትህ ስትመለስ በህይወት መንገድ ላይ ጋሬጣ ሆኖ ይጠብቅሃል፡፡ መሸሽ ሳይሆን መጋፈጥ ነው መፍትሄው፡፡ አንዳንዴ እጅ መስጠት ከአላስፈላጊ ጣጣ ይጠብቃል፡፡ ሽንፈትን መቀበል፤ ልትለውጠው የማትችለውን ማመን ለምን አልቻልኩም ወይም ለምን ተሸነፍኩኝ በሚል ከሚመጣ አጉል ጭንቀትና መብከንከን ያድናል፡፡ የሆነብህን አምኖ በትምህርትነቱ መረዳት ዘወትር ቁስልህ እያመረቀዘ ህመም እንዳይፈጠርብህና ዛሬህ እንዳይበላሽ ያደርጋል፡፡
ከስብራት ሁሉ ያልታከመ የልብ ስብራት መላሕይወትን ሲያሰቃይ ይኖራል፡፡
ከጠባሳ ማምለጥ ባይቻልም ከህመሙ መዳን ግን ይቻላል!
ቸር ድነት!
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ!
--------------------------------------
477
13:59
30.08.2025
አማርኛ እንግሊዝኛን ያስከነዳዋል!
________________
በእኔ አመለካከት፣ አማርኛ በትክክል የነገሮችን አነባበብ (pronunciation) በመግለፅ አቅሙ እንግሊዝኛን በሺህ እጥፍ ያስከነዳዋል።
እንግሊዝኛን አወቅኩ ብለህ አናባቢዎቹን ጨርሰህ ልታውቃቸው የሚሳንህ እጅግ ተለዋዋጭ ድምፀት በሚሰጡ ሆሄያት የተሞላ ነው። አማርኛ ለያንዳንዷ ድምፅ የየራሷን ሆሄ ቁጭ በማድረግ ያለመዛነፍ እኔድታነበው ተደርጎ የተቀረፀ አስገራሚ precision ያለው ቋንቋ ነው።
አንዳንድ ቋንቋዎች ውስጥ ያሉ ለየት ያሉ ቅላፄዎችን በተመሳሳይ ሳያሳስት እንዲገልፅ ጥቂት ጭማሪዎችን (ማሻሻያዎችን) ጨምሮ ለሁልጊዜም ማገልገል የሚችል ቋንቋ ነው።
የፊደል ገበታው ብዛት አዲስ ተማሪዎችን እንዳያሸሽ፣ ዋናዎቹን የመጀመሪያ ፊደሎች (ግዕዞቹን) ብቻ አስቀምጦ፣ ካዕብ፣ ሣልስ፣ ራብዕ፣ ሃምስ፣ ሳድስ፣ ሳብዕ ቅጥያዎቹን በጭረቶች እንደ አናባቢ መግለፅ እንደሚቻል ባጭሩ ገልፆም የብዛቱን መጀመሪያ ላይ ሲታይ የሚሰጠውን አዳጋችነት ወይም አስደንጋጭነት መቀነስም ይቻላል።
የአማርኛው የመግለፅ ብቃትና አድማስ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ እንዲያድግ ኮስተር ብሎ መሥራት በሁሉም የሙያ መስክ ከተሠማሩ ኢትዮጵያውያን የሚጠበቅ የትውልድ መዋጮ (አደራ ወይም ኃላፊነት) ነው ብዬ አስባለሁ።
በብዙ አስቂኝ ምሣሌዎች የእንግሊዝኛ አነባበብ፣ ፈረንሳይኛ፣ ሌሎችም ላይ የሚታየውን ግራ አጋቢነት ከአማርኛው ጋር አነፃፅሮ ማሳየትም ቀላል ነው። ላሁኑ ዋና ሃሳቤን ለመግለፅ ተጨማሪ ዝርዝሮች ውስጥ መግባቱ ግን አስፈላጊ አልመሠለኝም።
ያለንን ወርቅ አናንቀን እንደ መዳብ ባንቆጥር፣ የቀደሙ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን፣ ቋንቋዎቻችንን ሁሉ በበለጠ አቅም ብናጠና፣ ብናሳድግ፣ ብናስፋፋ። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካዝና የተከረቸመባቸውን እጅግ ብዙ የቋንቋና ስነልሣን ጥናቶች ወደ ማኅበረሰባችን አምጥተን ይበልጥ ለትውልድ ጥቅምና ግልጋሎት ብናውላቸው፣ ነገ በራሱ ቀጥ ብሎ የሚቆም፣ በተውሶ አስተሳሰቦች የማይንበረከክ፣ ኩሩና ምሉዕ ዜጋ እንፈጥራለን ብዬ አስባለሁ።
ከዚህ ሁሉ ውጭ ግን፣ ማንኛውንም ቋንቋ ማወቅ በውስጡ ያሉ ህልቆ ወ መሣፍርት የሌላቸው ማኅበረሰባዊ ዕውቀቶችና አተያዮች፣ አገላለፆች፣ ጥበባዊ እፍታዎች ለማወቅ ምትክ የሌለው በጎ አስተዋፅዖ ስላለው፣ በተቻለ መጠን ቋንቋችንን ማብዛት፣ መማር፣ ማወቅ - በተለይ የራሳችንን ሀገራዊ ቋንቋዎች - ሁልጊዜም ጥቅም እንጂ ጉዳት የሌለው ተግባር ነው ብዬ አምናለሁ።
ሸጋ ቀን ተመኘሁ!
🙏🏿❤️
መምህር አሰፋ ሀይሉ
910
14:04
30.08.2025
imageImage preview is unavailable
ዝምተኛው የቲክቶክ ንጉስ!
• በአንድ ፖስት 750 ሺህ ዶላር ይከፈለዋል
ካቢ ላሜ በሴኔጋል ተወልዶ በጣሊያኗ ቱሪን ከተማ ያደገ ወጣት ነው። ቤተሰቦቹ ወደ ጣሊያን ተሰደው ይኖሩ ነበር። ከቲክ ቶክ ዝናው በፊት ካቢ የፋብሪካ ማሽን ኦፕሬተር ሆኖ ሰርቷል።
ካቢ ከሚሰራበት ፋብሪካ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተባረረ። መባረሩ ግን እንደሌሎች ሰዎች መጥፎ ዕድልን ብቻ ይዞ የመጣ አልነበረም። በተባረረበትና የኮቪድ ወረርሽኝ በተስፋፋበት ወቅት ካቢ ወላጆቹ ቤት ሆኖ የቲክቶክ ቪዲዮዎችን መልቀቅ ጀመረ።
የሚሰራቸው ቪዲዮዎች ይዘት አስቂኝና አስተማሪ ሲሆኑ፤ በተለይም ደግሞ አስቂኝ በሆነ መልኩ ከመጠን በላይ የተወሳሰቡ ቪዲዮዎችን ለህዝቡ በማጋራት ከፍተኛ ተቀባይነትን ሊያገኝ ቻለ። የሚለቃቸው ቪዲዮዎች ላይ የሚያሳየው የፊት ገጽታና የእጅ ምልክቶች በበርካታ የዓለም ህዝብ ተወዳጅ ያደረገው ሌላው ነገር ነው።
ካቢ ባሁኑ ሰዓት 161 ነጥብ 6 ሚሊዮን የቲክቶክ ተከታዮችን በማግኘት የዓለማችን ቁጥር አንድ ቲክቶከር ሲሆን፤ ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ መውደድን (ላይክ) ማግኘት ችሏል።
በዚህም በ2024 ብቻ ቲክቶክ 20 ሚሊዮን ዶላር ከፍሎታል። በአሁኑ ጊዜም በአንድ ፖስት 750 ሺህ ዶላር ይከፍለዋል።
በጣም አስገራሚው ነገር ደግሞ ካቢ ይህን ክፍያ ሲያገኝ በቪዲዮቹ ላይ አንድም ቃል ተናግሮ አለማወቁ ነው። ቲክቶክ ከሚከፍለው ክፍያ በተጨማሪ ወጣቱ ከሁጎ ቦስ እንዲሁም ከበርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የመስራት እድሉን አግኝቷል።
በተጨማሪም ካቢ ባለው አስተማሪ የህይወት ጉዞ በፎርብስ መጽሄት ላይ ሊወጣ የቻለ ሲሆን፤ ዩኒሴፍም የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርጎ ሾሞታል።
ጋዜጣ+
694
14:28
30.08.2025
imageImage preview is unavailable
ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው። አንዱ አጠገቡ ላለው ጓደኛው እንዲህ
አለው። "ቄሱ ቆንጆ ሚስት አለቻቸው። እንዋደዳለን። አሁን እሷ ጋ ልሄድ
ነው። አንተ ከቅዳሴ በኋላ ቄሱን በወሬ ያዝልኝ። ከመምጣትህ በፊት
አስቀድመህ ደውልልኝ አደራ" አለው።
ጓደኛው ከቅዳሴ በኋላ ቄሱን አስቁሞ የባጥ የቆጡን ያወራላቸው ጀመር።
ቄሱም በሰውዬው የተዘበራረቀ ንግግር ግራ ገባቸውና ምን እንደፈለገ
በቁጣ ጠየቁት።
ሰውዬም የሃጢአተኝነት ስሜት ተሰማውና ዕውነቱን ነገራቸው "ይቅር
ይበሉኝ አባቴ! ጓደኛዬ ከእርስዎ ሚስት ጋር ሊተኛ ሄዶ እኔ እርስዎን በወሬ
እንድይዝሎት ነግሮኝ ነው" ብሎ እግራቸው ላይ ወደቀ።
ቄሱም ፈጥነው አነሱትና እንዲህ አሉት "አንተ ሞኝ! አሁኑኑ ወደ ሚስትህ
ፈጥነህ ሂድ! እኔ ሚስቴ ከሞተች 5 ዓመት አልፏታል".....አለው ይባለል.. !😂😂
ምን ለማለት ፈልጌ ነው ዛሬ አንዱ ጅል (መምህር ይህም አይሁን አላወቅንም) የሚከተለውን አጭር መልእክት ላከልን።
" እናንተ ግን ምንድን ነው አላማችሁ ? በመምህራን ፔጅ ፖለቲካም ትምህርትም፣ሀይማኖትም ትፅፋላችሁ፣ ስለ መምህራን ብቻ ለምን አትፅፋም ? ደደብ ናችሁ እሽ !" ብሎ ፃፈልም። እና ይሄ ሰው ጅል ነው። ሚስቱን እያስነ፣** ቄሱን አጃጃልኩኝ ብሎ ራሱን እንዳጃጃለው አይነት ሰው ነው።
ይህ ፔጅ የመምህራን አንደበት ነው። ስለ ሁሉም ነገር ይዳሰስበታል ! መምህር ፖለቲካ አይችልም ያለው ማን ነው ? ትምህርት ፖለቲካ ነው ወንድሜ !
ፖለቲከኞች አይደሉም እንዴ ሲያሸኑህ የሚውሉት ? አግኝተኸው ነው ፖለቲከኛነቱን !
ወዳጄ ፖለቲካ የማይወራው ተማሪዎች ፊት እና ትምህርት ቤት ውስጥ ብቻ ነው ! ሌላ ቦታ ይቻላል !
591
22:48
30.08.2025
imageImage preview is unavailable
ከቀናት በፊት በትራምፕ ዕጅ ላይ የታየው የህመም ምልክት ለህይወት ቆይታ የሚሰጠው ፋታ ከ 6 ወር ያልበለጠ እንደሆነ ተነግሯል!
ባለሙያዎቹ እንዳሉት ይሄ በሽታ በዋነኝነት የሰውነት ሚዛንን የሚያጠፋ እና ደም ስሮችን ከጥቅም ውጪ የሚያረግ ነው ያሉ ሲሆን በህይወት የማቆያ ጊዜ ቢበዛ 6 ወር ነው
አብዛኛዎቹ የዚህ ህመም ተጠቂዎች ከ 2ቀን እሰከ 1 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ነው ህይወታቸውን ያጡት
ታዲያ ይሄ ምልክት በትራምፕ ዕጅ ላይ በታየ በሳምንቱ የትራምፕ ደብዛ ጠፍቷል ያለፉትን ሶስት ቀናት መገኘት በነበረበት ፕሮግራሞች ላይ አልተገኘም
ሊደረጉ ተሰናድተው የነበሩ ፕሮግራሞችም ተሰርዘዋል ይህንን ተከትሎ ነው በርካታ የመገናኛ ብዙሃኖች ትራምፕ ሙቷል አልያም ህመሙ ዕረፍት አሳጥቶት ስቃይ ውስጥ ነው ሲሉ የዘገቡት
በነገራችን ላይ የኢንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤት የዚህ በሽታ ምልክት በተመሳሳይ በዕጇ ላይ በታየ በማግስቱ ነበር ህይወቷ ያለፈው።
ሀገሪቱ እሰከአሁን በጉዳዩ ዙሪያ ዝምታን መርጠዋል🤐
በነገራችን ላይ ትራምፕ እቡይ ስለሆነ ይሙት አይባልም እንጅ ቢሞትም የማይጎዳ ሰው ነው !
በተለይ ለእኛ ለኢት'ያዊያን ነቀርሳ ነው። የኑሮ ውድነቱ የእሱ ስራ ነው !
ጌታ(አላህ ) ሆይ ለክፋዎች ማረፊያቸውን አዘጋጅ !
578
23:38
30.08.2025
የህዳሴውን ብሔር ንገረኝ!
______________
የህዳሴው ግድብ ሣይገነባም ስንፅፍ ነበር። ሕዝብ በሚያየው ጋዜጣ። መፅሔት። ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ዘር የላቸውም። ብሔር፣ ጎሳ፣ ነገድ፣ ገለመሌ የላቸውም።
የትውልድ ሥራ፣ የጋራ የተባበረ ክንድ ውጤት፣ የሀገር ሀብት ናቸው። የረቀቁ፣ የመጠቁ ነገሮች ሁሉ ከዘር ዝባዝንኬ በላይ ናቸው። ትውልድን ማስተሳሠሪያ የወል አርማዎች ናቸው።
ትንሽ ባሰብን ቁጥር ወደ ትንሹ የብሔር ጎተራ ውስጥ እንሸጎጣለን። ትልቅ ባሰብን ቁጥር ከደቂቁ የብሔር ምናምንቴ ተመንድገን እንወጣለን።
የዘር ሊቃውንት ሆይ፣ ዛሬ የህዳሴውን ብሔር ንገረኝ እልሃለሁ።
ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብኩት "ቀይ አንበሣ" ተብሎ በተተረጎመው (ኩባዊው ደራሲ ግን "ነጭ ሰው ባልሠለጠኑ ሕዝቦች ምድር" ብሎ በፃፈው የ1928 ዓመተ ምኅረቱን የጣልያን ወረራና ጦርነት በሚያወሳው የአሌኻንድሮ ዴል ባዬ የጉዞ ማስታወሻ ላይ ነበር።
ዴል ባዬ አንድ በአዲስ አበባ ዙሪያ ፋሺስቶችን ሊፋለሙ ጦር ያደራጁ የነበሩ የኦሮሞ የጦር ጄነራል አንዳንድ አዋሻኪዎች አማራ፣ ኦሮሞ ምናምን እያሉ ዕረፍት ሲነሷቸው፣ አንድ ቀን ሁሉንም ሰብስበው ጤፍ ለቅማችሁ አምጡልኝ አሉ ይሏቸዋል።
ከዚያ ሁሉም እያዩ ያመጡላቸውን ጤፍ በትልቅ እንቅብ ላይ ደባለቁት። እና መልሰው ጠየቋቸው፦ አሁን ይሄን ጤፍ የትኛው ከየት እንደሆነ ነገሩኝ ዘሩን አሏቸው! ሁሉም በእፍረት አቀረቀሩ። አያችሁ ኢትዮጵያም እንደዚህ ነች፣ ሀገርም እንደዚህ ነች፣ የኛ የነፃነት ሠራዊትም እንደዚህ ነው። ብለው ሸኟቸው ይለናል ፀሐፊው።
ህዳሴ ግድቡም እንደዚያ ነው። ለግማሽ ክፍለዘመን የዘርና የብሔር ቀለም ልንሰጠው ስንጋጋጥ ይኸው እዚህ ደርሰናል፣ እንጂ የሀገር መከላከያ ሠራዊትም እንደዚያው ነው።
ጄነራል ባጫ ደበሌ በአንድ ወቅት፣ የኦሮሞ መከላከያ ሠራዊት የለም። የአማራ የለም። የትግሬ። የአፋር። የሶማሌ የለም። እኔ የምመራው የመከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ይባላል። ከብሔር ጋር ልታጣብቁት ብትፍጨረጨሩም አትችሉም - ሲል የሚገርም ንግግር በአደባባይ ቆሞ ተናግሮ ነበር። ሀገር የሚገነባው በዚህ የአስተሳሰብ ከፍታ ነው።
ዛሬ ላይ ቆሜ፣ አንተ የብሔር ምናምንቴ ዝተታም፣ እስቲ የህዳሴውን ግድባችንን ብሔርና ዘር ንገረኝ እልሃለሁ። ከፍ ያለ ነገር ዘር የለውም። ብሔር የለውም። ሀገር ሀገር ይላል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትርን ብሔር ንገረኝ እስቲእልሃለሁ። የአርት ስኩልን ብሔር ብሔረሰብ ተንትንልኝ እልሃለሁ። የኔልባልድያንን አፍሪካ አፍሪካ ሀገራችን እያለ ያቀነቀነ ኦርኬስትራ ብሔር ንገረኝ እልሃለሁ። የያሬድን የሙዚቃ ትምህርት ቤት ብሔር ንገረኝ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ብሔር ንገረኝ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድን ብሔር ንገረኝ። የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርትን ብሔር ንገረኝ። የአባይን ወንዝ ብሔር ንገረኝ። የጥቁር አንበሣ ሆስፒታልን ብሔር ንገረኝ። የጳውሎስን። ንገረኝ የፓስተርን ኢንስቲትዩት ብሔር። ...
የአዋሽን፣ የሸበሌን፣ የገናሌን፣ የተከዜን፣ የአትባራን፣ የቦርከናን ብሔር ንገረኝ ብዬ እጠይቅሃለሁ። የባንዲራዋን ብሔር ንገረኝ። የመጠቁ ነገሮች ከወረደ የብሔር አጀንዳ ከፍ ያሉ የትውልድ ተስፋዎች ናቸው። ሀገርን ይመስላሉ።
የህዳሴው ግድብ እውነተኛ ሀገር ምን እንደሚመስል ማሳያ ነው። ብሔርህ፣ ዘርህ፣ ነገድህ፣ ጎሣህ ሁሉ በዚህ ታላቅ የጋራ ውሃ ውስጥ ገብተው ይሰምጣሉ። ላይለያዩ ይዋሃዳሉ። አንድ ይሆናሉ። ባንድ ላይ ይፈሳሉ። በጉልበት። በኃይል። በጥበብ። በግርማና በሞገስ የሀገርን፣ የትውልድን ህያው ማንነት ያዜማሉ።
የህዳሴው ግድብ ከዚህ ከወረሰንና ካዋረደን የዘቀጠ የብሔር ቅብጥርሶ ነቀርሳ የመላቀቂያችን መባቻ አዋጅ ይመስለኛል። የዚህ ትውልድ ከፍ ያለ ሀገራዊ ተስፋ ነጋሪት ድምፅ ነው። የህዳሴው ግድብ በኋላቀርነት አታሞ መቺዎች ላይ የተነፋ የኢትዮጵያችን ምፅዓት መለከት ነው!!
ሀገር ከጎጥና ከዘር ማንዘር ነቀርሳ የአፍታ ፋታ ስታገኝ ህዳሴውን ግድብ ትመስላለች! የህዳሴው አብዮት ከዘረኞች የፀዳ የአዲስ ሀገር ማዋለድ የክተት አዋጅ እንዲሆንልን ከልቤ እመኛለሁ!
የህዳሴውን ብሔር ንገረኝ።
ሠርገኛ ግድብ ነው።
It's the foretelling monument of the true Ethiopian Renaissance in the making! ይህ የምናየው የህዳሴ ግድብ፣ ዘረኝነትን ከሀገራችን ጠራርጎ የሚያጠፋ የአዲሱ ትውልድ ህያው ሐውልት ነው!
ዕውቀት ይስፋፋ። አብሮነት ይጠናከር። ሀገርነት ከፍ ይበል። ወገንነት ይለምልም። ባንዲራችን ቀስተደመና ሆኖ ሠማያችንንና ምድራችንን እስኪያለብሰው ድረስ ኢትዮጵያዊነትን እንዘምር። ሀገርነትን እንላበስ። ትንሽነት ይብቃን። ጥሬነት ያቀርሸን። እንምጠቅ። እንብሰል። ሀገር ሀገር እንበል።
የሥልጣኔ መንገዱ፣ የህዳሴያችን ፋናው፣ የጥበብ ዳናው፣ የጋራ ሀገራዊ እኛነት ነው!
አንት አረም! የህዳሴውን ብሔር ንገረኝ!
አበቃሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያችንን አብዝቶ ይባርክ!
ነቄውን ትውልድ ያስነሳ፣ ያበርታልን!
እናት ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
🟢🟡🔴
🙏🏿💦
💙
(መምህር አሰፋ ሃይሉ)
531
14:03
30.08.2025
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
1 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
c
**ffeennew@******.io
On the service since June 2022
31.08.202518:58
5
Precise task compliance
New items
Channel statistics
Rating
12.4
Rating reviews
5.0
Сhannel Rating
1
Subscribers:
2.8K
APV
lock_outline
ER
24.1%
Posts per day:
6.0
CPM
lock_outlinekeyboard_double_arrow_left
shopping_cart
Channels:
0
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Total:
$0.00
Add to Cart
Clear the cart
Are you sure you want to clear the cart?
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Clear my cart
Cancel
Комментарий