
Advertising on the Telegram channel «DBU Info»
Information sharing channel about Debre Berhan University. It shares the information to inside and outside community.
Channel statistics
የዚህና የሌሎች በርካታ አንቱ የሚያስብሉ መልካም ስራዎች ባለቤት ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን አንቱ ብለን በክብር ታሪካቸውንና አስተዋፅኦዋቸውን እናነሳለን፡፡
ከ1933 ዓ.ም በኋላ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የቀዶ ጥገና ሀኪም የሆኑት ፕሮፊሰር አስራት ወልደየስ ከአባታቸው ከአቶ ወልደየስ አልታየ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ በሰልፍ ይዋሉ ፅጌ ሰኔ12 ቀን 192ዐ ዓ.ም ነበር በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡
ትውልዳቸው አዲስ አበባ ቢሆንም ያደጉት ድሬድዋ ነው፡፡ በድሬድዋ የህፃንነት ቆይታቸው የአብነት ትምህርት በመማር ዳዊት ደግመዋል፡፡ የድሬድዋ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ዲያቆን በመሆንም አገልግለዋል፡፡
የካቲት 12 ቀን 1929 ማርሻል ግራዝያኒ ብዙ ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በግፍ ሲጨፈጭፍና፤ሲያስር ሰላባ ሆነው ህይወታቸውን ካጡት መካከል የያኔው የ 8 ህፃን ፕሮፌሰር አስራት አባት አቶ ወልደየስ አልታየ ይገኙበታል፣ አያታቸው ቀኝ አዝማች ፅጌ ወረደም ወደ ጣሊያን ሀገር በግዞት ተወስደው ታስረዋል፡፡
እናታቸው ወይዘሮ በሰልፍ ይዋሉ ፅጌም በምድር ላይ ብዙም አልቆዩም ነበርና የፕሮፌሰር አሥራት የልጅነት ጊዜ በሀሴት የተሞላ አልነበረም፡፡
በድሬድዋ ከአጐታቸው ጋር ከቆዩ በኋላ በ1934 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ፡፡ በ1934 ዓ.ም በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ዘመናዊ ትምህርታቸውን ቀጥለው በ1935 ዓ.ም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
ፕሮፌሰር አሥራት በትምህርታቸው ያስመዘግቡ የነበረው የላቀ ውጤት ወደ ግብፅ ሄደው በቪክቶሪያ ኮሌጅ እንዲማሩ አስቻላቸው፡፡ ከዚያም ወደ እንግሊዝ በማቅናት የህክምና ትምህርታቸውን ኤዴንበርግ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው በከፍተኛ ውጤት ተመርቀዋል፡፡ በእንግሊዙ ሮያል ኮሌጅ ኦፍ ሰርጀን ቀዶ ጥገናን ለይተው /ሰፔሻላይዝ አድርገው/ በሙያው ተክነው ነበር ወደ ሀገራቸው የተመለሱት፡፡
በ1947 ዓ.ም ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በልዕልት ፅሀይ ሆስፒታል /በአሁኑ ጦር ሀይሎች/ መስራት ጀመሩ፡፡ ፈረንጆች ሳይቀር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በፕሮፌሰር አስራት ይታከሙ እንደነበር ይገለፃል፡፡ በታዋቂ ቀዶ ጥገና ሀኪምነታቸው በሀገሬው ሰው እስከ መመለክም ደርሰው ነበር፡፡
የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህክምና መምህርም ሆኑ፡፡ ከመምህርነታቸው ባሻገር በሀገራችን ከፍተኛ የህክምና ግልጋሎት የሚሰጥበትን ጥቁር አንበሳ ሆስፒታልን አቋቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ፣ የምስራቅ አፍሪካ፣ የእንግሊዝ እና የዓለም ሀኪሞች ማህበር አባል እና መሪ የነበሩት ፕሮፌሰር አስራት፤ በቀዶ ጥገናው ዘርፍ ላበረከቱት በጐ አስተዋፅኦ አምስት ኒሻኖችን ተሸልመዋል፡፡
በ1950ዎቹ የጤና ሚኒስትር ሆነው ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ ቢጠየቁም የነፍስ ጥሪዬ የህክምና ሙያ ነው በማለት ሳይቀበሉት ቀርተዋል፡፡
በደርግ ጊዜ ፕሮፌሰር አስራት የሶሻሊዝም ሰባኪ እንዲሆኑ ተፈልጐ እንደበርና እሳቸው ግን ፍላጎቱን ባለማሳየታቸው ከደርግ ጋር የተፈጠረው ቅሬታ ንጉሰ ነገስት ሀ/ስላሴ እንዴት እንደሞቱ ላላወቀው ህዝብ “በልብ በሽታ እንደሞቱ ተናገር” ፕሮፌሰር አስራት ሲባሉ አሻፈረኝ በማለታቸው ከደርጎች ጋር የለየለት ቅዋሜ ውስጥ ገቡ፡፡
የህይወት ታሪካቸውን አንፀባራቂው ኮከብ በሚል ርዕሰ የከተበው አቶ ጋሻው መርሻ እንደሚለው ፕሮፌሰሩ “ለደርግ ትዕዛዝ አሻፈረኝ በማለታቸው ወደ ሰሜን ግንባር ምፅዋ ተልከው እንዲገደሉ ተፈልጐ ነበር፡፡
ወታደሩን ለማከም ወደ ምፅዋ የሄዱት ፕሮፌሰር አስራት ለልብ ድካም ቢዳረጉም በጥይት ሳይመቱ ተመልሰዋል፡፡ “በህክምና ሳይንስ ጠላት የለም፡፡ ጃንሆይንም፤ የደርግ ባለስልጣናትንም ያለምንም ልዩነት አክማለሁ፡፡ ህክምና የሰውነት ስራ ነው” ይላሉ፡፡
ጃንሆይን ማከማቸው በደርግ እንደተጠላው ሁሉ፤ የደርግ ባለስልጣናትን ማከማቸው ደግሞ በነ ህዋኃት እና መሠል ድርጅቶች አልተወደደላቸውም፡፡ ደርግ ፊውዳላዊ አድርጐ ሲያሳድዳቸው፣ ኢህአዴግ ደግሞ ደርግ አድርጐ ቆጥሯቸዋል፡፡
ግንቦት 2ዐ ቀን 1983 ዓ.ም አዲስ አበባን ኢህአዴግ ሲቆጣጠር በሽግግር መንግስቱ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በመወከል ከእነ አቶ መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወርቄ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም የብሄር ፌዴራሊዝም አስቸጋሪነቱን የኤርትራ መገንጠልም ለዘላቂ ሰላም እንደማይበጅ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ በወቅቱ “ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚቅበዘበዙ ሁሉ እነሱ ቀድመው ይጠፋሉ፡፡” በሚለው ዝነኛ ንግግራቸውም ይታወቁ ነበር፡፡
አማራውን በጨቋኝነት ፈርጆ፣ ኢትዮጵያዊነትንም ጠልቶ የተጠነሰሰው የዘውግ ፖለቲካ ፕሮፌሰር አስራት ረፍት ነሳኝ አሉ፡፡
አማራ ባለመደራጀቱ እረኛ እንደሌለው ከብት ተበትኖ የሀገር ውስጥ ስደተኛ ሆነ፣ ተፈናቀለ በማለት የህክምና ጋውናቸውን አውልቀው፣ ይጠሉት ወደነበረ የብሄር ፖለቲካ ገቡ፡፡
ጥር 1984 የመላው አማራ ህዝብ ድርጅትን መሰረቱ፡፡ ፖለቲካውን ከተቀላቀሉ በኋላ በፕሮፊሰር አስራት ላይ ተደጋጋሚ ወከባ ይደርስባቸው እንደነበር ይነገራል፡፡ በ1985 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተባረሩት 42 መምህራን መካከል ፕሮፌሰሩ ቀዳሚው ነበሩ፡፡
በዚህ ብቻ አላባራም በደብረ ብርሃን ከተማ ቀስቃሽ ንግግር በማድረግ እና ከጐጃም ገበሬዎች ጋር ለመፈንቅለ መንግስት አሲረዋል በሚል አምስት ዓመት ከ ስድስት ወር ተፈረደባቸው፡፡ በማረሚያ ቤት እያሉ ግፍና መከራን ተቀበሉ፡፡ ህክምናም ተከልክለዋል፡፡
የመሰረቱት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲያገለግላቸው እንዳልተፈቀደ አንፀባራቂው ኮከብ በሚለው መፅሀፉ የሚናገረው አቶ ጋሻው መርሻ ፕሮፌሰር አስራት 150 ጊዜ ፍርድቤት እንደቀረቡ ፅፏል፡፡ በመጨረሻ ከደከሙ በኋላ በመአህድ እና በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ጥረት በ1991 ዓ.ም ለህክምና ወደ አሜሪካ ቢሄዱም ሊተርፉ አልቻሉም፡፡
አሜሪካ አርፈው አዲስ አበባ ባለወልድ ቤተክርሲቲያን ስርአተ ቀብራቸው በ1991 ዓም ተፈፅሟል፡፡
በመአህድ አማካኝነትም ለበጐ አድራጐት የሚተጋ የፕሮፌሰር አስራት ፋውንዴሽን ተቋቁሟል፡፡
“ፕሮፌሰር አስራት በህክምና፣ ሀገርን በመውደድ እና ራስን አሳልፎ ለህዝብ በመስጠት አርአያ ሰው ናቸውና ፋውንዴሽኑ ተገቢ ነው” ይላል የህይወት ታሪክ ከታቢያቸው አቶ ጋሻው መርሻ፡፡
ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን በቅርብ የሚያውቋቸው ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ
ፕሮፌሰር አስራት ኢትዮጵያን በተለየ መንገድ ይወዷታል፡፡ ስለሚወዷት ጎሰኝነትን አጥብቀው ይቃወሙ ነበር፡፡ በዚያ ላይ ደፋር ነበሩ፡፡
ያን ባያደርጉ ይሄኔ የደርግ ገዳይነት ተሸፍኖ ህዝቡ ጃንሆይ ታመው ሞቱ የሚለውን ያምን ነበር ሲሉ መስክረውላቸዋል፡፡
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲም የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስን በስማቸው ሰይሞላቸዋል::
Source: https://yenevibe.com
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ከጥቅምት 20/2018 - 22/2018ዓ.ም ለ1920 አዲስ ገቢ ተማሪዎች የህይወት ክህሎትና ሌሎች ስልጠናዎችን ሰጠ
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፈፃሚ ወ/ሮ አዲስ አስፋውወሰን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁው መልካም እንዲሆንላቸው እንዲሁም ውጤታማና ስኬታማ ሆነው እንዲወጡ ከማድረግ አኳያ የተለያዩ ችግሮች እንዳይገጥማቸው የቅድመ-መከላከል ስራና ችግር ቢፈጠርም ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያሳውቁ የተለያዩ ስልጠናዎች በመምህራን እንደተሰጠ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የስልጠናው ዋና አላማ በራሳቸው የሚተማመኑና ሙሉ ስብእና ያላቸው ተማሪዎችን ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡
መክፈቻ ንግግሩን ያደረጉት የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ ገዛኸኝ ነጋ (ዶ/ር)እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አዲስ ለገቡ ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና እጅግ ወሳኝ መሆኑን በመግለፅ በግቢም ሆነ ከግቢ ውጭ ለሚያጋጥማቸው የተለያዩ ችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ ለማግኘት የሚያግዝ ስልጠና እንደወስዱ በመናገርና ለቀጣይ የትምህርት ጊዜ የሚያጠናክር ስልጠና መሆኑን አሳስበዋል፡፡
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ እንደ ቤተሰብ ተንከባክቦ የተቀበላት መሆኑን የገለፀችው ሰልጣኝ ተማሪ በረድኤት ይርጋ በስልጠናው በፆታ ትንኮሳ የሚመጡ መሰናክሎችን እንዴት መቅረፍ እንደምትችልና ሌሎች እንቅፋቶችን በቀላሉ ለማለፍ የሚያስችል ስልጠና የወሰደች መሆኑንም ተናግራለች ፡፡
ሌላኛው ሰልጣኝ ተማሪ ዳግም ወንድሙ በስልጠናው ውጤታማ የአጠናን ዘዴን በተመለከተና የአቻ ግፊት የሚያስከትለውን መዘዝ እንዲሁም በማህበራዊ ግንኙነት ዙሪያ ሰፊ እውቀትንና ክህሎትን ያገኘበት ስልጠና መሆኑን አብራርቷል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመራቂዎች የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል። በመደረኩ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የከፍተኛ ትምህርት ተማራቂዎች የመዳረሻ ጥናት የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ አንዱ መንገድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ፕሮግራሞቻቸውን የመዳረሻ ጥናት ካላካሄዱ ምን እየሰሩ እንደሆነ ለማወቅ እንደሚቸገሩና በገበያው የማይፈለግ የሰው ሀብት ሊያሰለጥኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመራቂዎች የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ትኩረት በመስጠት በትምህርት ፕሮግራም ደረጃ ወጥ በሆነ መንገድ ሊሰሩ እንደሚገባ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ ህይወት በበኩላቸው የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ለፖሊሲ ውሳኔ ፣ ለስርዓተ ትምህርት ክለሳና ለሌሎችም አገራዊ እቅዶች ግብዓት ስለሚሆን በተቀናጀ አግባብ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በሌላ በኩል የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) የአካዳሚክ ዋና ስራ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች በዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም የ2016 ተመራቂዎች የመዳረሻ ጥናት በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከጥቅምት እስከ ሚያዚያ 2018 ዓ.ም ድረስ ወጥ በሆነ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መካሄድ እንዳለበትም ዶክተር ኤባ ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተሮች የተገኙ ሲሆን መዳረሻ ጥናትን በሚመለከት ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በኢንዱስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከየኮሌጁ ለተመለመሉ መምህራን የፓተንት (የፈጠራ ሥራ ባለቤትነት ማረጋገጫ)አፃፃፍ ስልጠና ከጥቅምት 20/2018--21/2018 ዓ.ም ሰጠ፡፡
የመክፈቻ ንግግሩን ያደረጉት የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ር ሰለሞን ደርቤ እንደተናገሩት በቴክኖሎጂ ፈጠራና የፓተንት እና የቴክኖሎጂ መረጃዎች አፈላለግ ዘዴን በሚመለከት ከኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን የመጡ አሰልጣኞች ስልጠናውን ለተመራማሪ መምህራን የተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ስልጠናውን ሲሰጡ ያገኘናቸው ከኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ትራንስፈር ዲስክ ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ታደሰ እንደገለፁት በየተቋሙ በርካታ የጥናትና ምርምር ውጤቶች መኖራቸውን በመጥቀስ ተመራማሪያን ምርምሮቻቸውን በአእምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን እንዲደገፉ ለማድረግ እንዲሁም ወደ ተቋሙ በመምጣት ምዝገባ በማድረግ ጥበቃ እንዲያገኙ፣ በፓተንት ሊመዘገቡ የሚችሉትን የምርምር ፅሁፎች ማመልከቻ በማዘጋጀት የጥበቃ ሰርተፍኬት ለማግኘት እና እውቅና የተሰጣቸው ምርምሮችን ወደ ገበያ በማውጣት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ትልቅ ሚና ያለው ስልጠና የሰጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስልጠናውን ሲከታተሉ ያገኘናቸው የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ መ/ርት ኤልሳቤጥ ገበየሁ የፓተንት አፃፃፍንና በስሩ የተለያዩ ስልጠናዎችን የወሰዱ መሆኑን በመናገር ፅሁፎች (ፕሮጀክቶች )ከመታተማቸው አስቀድሞ ወደ ማህበረሰቡ ወርደው ገበያ ላይ ከመዋላቸው በፊት አእምሮአዊ ንብረት ምዝገባ ማግኘት (እውቅናና ምዝገባ ) ማግኘት እንዳለባቸው በስልጠናው ጥሩ ግንዛቤን ያገኙ መሆናቸውንና በተጨማሪም ከአእምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን (IP)ጋር በጋራ በመሆን ዩኒቨርሲቲው ቢከፈት እና ጠንክሮ ቢሰራበት ጥሩ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በአፀደቃቻው መመሪያዎች ዙሪያ ከሁሉም ኮሌጅ መምህራን፣ ከትምህርት ክፍል ሀላፊዎችና ቴክኒካል ረዳቶች ጋር ውይይት አደረገ፡፡
ውይይቱ በዋናነት የሚተያተኩረው የተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር ፣ ተከታታይ ምዘና ፣ ማጠቃለያ ፈተና ፣ የመምህራን አቅም ግንባታ ፣ ኮርስ ኦዲትና በፕሮግራሞች እውቅና ዙሪያ መሆኑ ታውቋል፡፡
ከውይይቱ በኋላ ሁሉም አካላት ጉዳዩን ተገንዘበው ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የታሰበ መድረክ መሆኑ ተነግሯል።
በኤሌክትሮኒክ ትምህርት አሰጣጥ ሥርዓት ውስጥ ለተሳተፉ አካላት እንደ ይዘት ዝግጅት ክብደት እና ባህርይ መሰረት የሚከተሉት ማበረታቻዎች ይደረጋሉ።
1. በኤልክትሮኒክ ትምህርት በትምህርት አይነት ዝግጅት እና በትምህርት አሰጣጥ ሂደት ላይ ተሳትፎ ላደረጉ መምህራን የምስክር ወረቀት በመስጠት፣
የሚሰጠውም የምስክር ወረቀት ለአመታዊ የስራ አፈፃጸም ምዘና እንደ አንድ መስፈርት ያገለግላል፡፡
2. በኤልክትሮኒክ ትምህርት የትምህርት አይነት የሚያስተምሩ መምህራን ከመደበኛ የማስተማር ስራ ጫና ጋር ተመጣጣኝ ሆኖ ይቆጠራል፡፡
3. በትምህርት ሚኒስቴር እዉቅና የተሰጠዉ ከኤልክትሮኒክ ትምህርት ጋር ተያያዥ የሆነ ከ 3 ወር ያላነሰ የአጭር ጊዜ ሥልጠና የሚሰለጥኑ መምህራን እንደ ከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም ሠልጣኞች ተቆጥሮ ተመሳሳይ ማበረታቻ የሚያገገኝ ሲሆን 3 ሳምንት እና ከ3 ወር በታች ስልጠና የወሰዱ መምህራን 2 ክሬዲት ይደረግላቸዋል፡፡
4. በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና የተሰጠው ከኤልክትሮኒክ ትምህርት ጋር ተያያዥነት ያለዉ ከ 3 ወር እስከ 4 ወር ስልጠና የሚሰጥ አሰልጣኝ መምህር በመንፈቀ ዓመት 6 ክሬዲት እንዲሁም ከ 3 ወር ካነሰ ለያንዳንዱ የስልጠና ፕሮግራም የ 2 ክሬዲት ተቀናሽ ይደረግለታል።
5. በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና የተሰጠው በኤልክትሮኒክስ ትምህርት ንድፍ ስራ ለተሳተፈ ባለሙያ መምህር፣ የንድፍ ስራ የሚሰራለትን የትምህርት
አይነት ክሬዲት ግማሽ ለአንድ ሲሚስተር ብቻ ስራ ጫና ይያዝለታል፡፡
6. የኤልክትሮኒክስ ትምህርት ይዘትን ለሚያዘጋጅ መምህር አግባብነት ባለው በገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ መሰረት ማበረታቻውን እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡
7. የኤልክትሮኒክ ትምህርት ይዘት ከተዘጋጀበት ተቋም ውጪ ለሌላ ተቋም በገንዘብ የሚተላለፍ ከሆነ ይዘቱን ያዘጋጁት መምህራን ክፍያን በተመለከተ አግባብ ባለው ህግ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤሌክትሮኒክ ትምህርት ማስተግበሪያ መመሪያ ቁጥር 1044/2017
ቻይና በማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦች የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ወይም በሚያስተላልፉት የመረጃ ዘርፍ ላይ የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት መያዝ እንዳለባቸው ጥብቅ መመሪያ አውጥታለች።
ከአሁን በኋላ በቻይና ያሉ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እንደ ህክምና፣ ህግ፣ ትምህርት ወይም ፋይናንስ ባሉ ስስ ጉዳዮች ላይ አስተያየት እና መረጃ የሚሰጡ የማህበራዊ ሚዲያ አቅራቢዎች የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ወይም የሙያ ማረጋገጫ ሊኖራቸው ይገባል ተብሏል።
ባለስልጣናት የተሳሳተ መረጃን ለመግታት እና የመረጃን ተአማኒነት ለማረጋገጥ ሲባል ይህንን ደንብ ያላከበሩ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እስከ 15,000 ዶላር የሚደርስ ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
ማህበራዊ ሚዲያ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ተከትሎ የውሸት መረጃን ለመከላከልና ግለሰቦችን ከማጭበርበር ለመታደግ ቻይና የወሰደችው እርምጃ ለበርካታ ሀገራት ተሞክሮ ይሆናል ተብሎ ታምኖበታል።
Reviews channel
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «DBU Info» is a Telegram channel in the category «Образование», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 5.9K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 7.2, with 0 reviews and an average score of 0.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 2.4 ₽, and with 0 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий