Save up to 70% on New Year Sale
Make the most of the season — grab the best ad placements by January 10!
Get discount
7.1
Advertising on the Telegram channel «ግጥም በ ኤዶምገነት»
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$1.20$1.20local_mall
0.0%
Recent Channel Posts
...
"ነገ" ከትላንት ፡ ቢጎብዝም
ሲያድር ቢሆንም ፡ ሁሉ መልካም፤
የሄደ ሁሉ ፡ እንዳልነበር
በሚመጣ ሰው ፡ አይተካም።
እርግጥ ነው ቃሉን ፡ አልክደውም
ተረት አይደለም ፡ መጫወቻ፤
ግን ሰዎች አሉ ፡ የተለዩ
ከአዕላፍ መሃል ፡"አንድ"ብቻ።
#mikiyas_feyisa
"ነገ" ከትላንት ፡ ቢጎብዝም
ሲያድር ቢሆንም ፡ ሁሉ መልካም፤
የሄደ ሁሉ ፡ እንዳልነበር
በሚመጣ ሰው ፡ አይተካም።
እርግጥ ነው ቃሉን ፡ አልክደውም
ተረት አይደለም ፡ መጫወቻ፤
ግን ሰዎች አሉ ፡ የተለዩ
ከአዕላፍ መሃል ፡"አንድ"ብቻ።
#mikiyas_feyisa
961
20:47
30.11.2024
**
ሲያለቅሱ ሳይ
አይናቸውን ሲያባብሱ፣
ስለናፍቆት
ስለማጣት እያዎሱ፣
የሚብሰኝ
የሚያደርገኝ ሆደ ባሻ፣
የሚያስነባኝ
ከንጋቱ እስከ ማምሻ፣
ናፍቆት አለኝ
ያላገኘ መጨረሻ።
.
.
ካልሰማሁኝ ሲቃቸውን
ካላየሁኝ እያነቡ፣
ደርሶ ሊከፋኝ ይቅርና
እንኳን ልሆን ሆደ ቡቡ፣
ደስተኛ ነኝ ያለምክንያት
ፈገግታዬ መች ያበቃል፣
ይሄ ጥርሴ አስመሳይ ነው
ከሳቁ አልፎ ያሳስቃል።
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
ሲያለቅሱ ሳይ
አይናቸውን ሲያባብሱ፣
ስለናፍቆት
ስለማጣት እያዎሱ፣
የሚብሰኝ
የሚያደርገኝ ሆደ ባሻ፣
የሚያስነባኝ
ከንጋቱ እስከ ማምሻ፣
ናፍቆት አለኝ
ያላገኘ መጨረሻ።
.
.
ካልሰማሁኝ ሲቃቸውን
ካላየሁኝ እያነቡ፣
ደርሶ ሊከፋኝ ይቅርና
እንኳን ልሆን ሆደ ቡቡ፣
ደስተኛ ነኝ ያለምክንያት
ፈገግታዬ መች ያበቃል፣
ይሄ ጥርሴ አስመሳይ ነው
ከሳቁ አልፎ ያሳስቃል።
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
3400
18:08
01.12.2024
137
22:04
01.12.2024
የተደበቀ ንስሀ
"""""""""""""""""
አስመሳይ ነኝ ወረተኛ
ታውቀኛለህ የኔ ጌታ፣
እየጠራሁ ለማመስገን
አንደበቴም አይፈታ፣
እልልታዬ ጊዜያዊ ነው
ማወደሴ ማሞገሴ፣
በቃልህ ጠግቤ ባድርም
ሽንገላ ነው ጠዋት ቁርሴ፣
አትማርም! ሀጢያት ተንኮል
ማታለል ነው ግብሯ ነብሴ፣
ክብር አድርገህ ያለበስከኝ
ተቀዳዷል ፀጋህ ልብሴ፣
ጎደሎ እምነት የበዛውን
ጾም ጸሎቴን አርገህ መባ፣
ለይስሙላ ደጆህ ስቆም
ብትፈቅድልኝ እንድገባ፣
ምህረትህ አረስርሳኝ
በንስሀ ብታጠብም፣
ዛሬም ልቤ ክፉን ብቻ
በጎን ነገር አያስብም።
ታውቀዋለህ ክንብንቤን
ገመናዬን ሁሉ ገልጠህ፣
ግን አኖርከኝ በም'ረትህ
ከበደሌ እኔን መርጠህ፣
ተዘርግተዋል እጆችህ
ሊቀበሉኝ በይቅርታ፣
ስሼሽ አይተህ አተዎኝም
አንተን መቅረብ ሳመነታ፣
በሀጢያቴ ስቅበዘበዝ
በስህተቴ ስደናቀፍ፣
አትሰለችም በምህረት
በቃሽ ብለህ እኔን ማቀፍ፣
ይቅር ባይ ነህ አትለወጥ
ለዘላለም በጎ መልካም፣
በቤትህ መመላለሴን
ቆጥረህልኝ እንደ ድካም፣
የሚያድነኝ አጣሁ ብልም
ብታነቅም በሾህ መሀል፣
ትርጉም የለሽ ልመናዬ
ጭንቅ ሀዘኔ ተሰምቶሀል።
ትሰማለህ ሹክሹክታዬን
ትረዳለህ የኔን ስሜት፣
አቻየን ካገኘሁ ቤትህ
ይቀናዋል ላኣፌ ሀሜት።
በከበረው አፀድ ቅጥር
ያንደበቷ ቃል የማይጥም
ብኩን ልጁን የሚያስገባት፣
የት ይገኛል ከአንተ በቀር
የሰማይስ የምድር አባት?
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
"""""""""""""""""
አስመሳይ ነኝ ወረተኛ
ታውቀኛለህ የኔ ጌታ፣
እየጠራሁ ለማመስገን
አንደበቴም አይፈታ፣
እልልታዬ ጊዜያዊ ነው
ማወደሴ ማሞገሴ፣
በቃልህ ጠግቤ ባድርም
ሽንገላ ነው ጠዋት ቁርሴ፣
አትማርም! ሀጢያት ተንኮል
ማታለል ነው ግብሯ ነብሴ፣
ክብር አድርገህ ያለበስከኝ
ተቀዳዷል ፀጋህ ልብሴ፣
ጎደሎ እምነት የበዛውን
ጾም ጸሎቴን አርገህ መባ፣
ለይስሙላ ደጆህ ስቆም
ብትፈቅድልኝ እንድገባ፣
ምህረትህ አረስርሳኝ
በንስሀ ብታጠብም፣
ዛሬም ልቤ ክፉን ብቻ
በጎን ነገር አያስብም።
ታውቀዋለህ ክንብንቤን
ገመናዬን ሁሉ ገልጠህ፣
ግን አኖርከኝ በም'ረትህ
ከበደሌ እኔን መርጠህ፣
ተዘርግተዋል እጆችህ
ሊቀበሉኝ በይቅርታ፣
ስሼሽ አይተህ አተዎኝም
አንተን መቅረብ ሳመነታ፣
በሀጢያቴ ስቅበዘበዝ
በስህተቴ ስደናቀፍ፣
አትሰለችም በምህረት
በቃሽ ብለህ እኔን ማቀፍ፣
ይቅር ባይ ነህ አትለወጥ
ለዘላለም በጎ መልካም፣
በቤትህ መመላለሴን
ቆጥረህልኝ እንደ ድካም፣
የሚያድነኝ አጣሁ ብልም
ብታነቅም በሾህ መሀል፣
ትርጉም የለሽ ልመናዬ
ጭንቅ ሀዘኔ ተሰምቶሀል።
ትሰማለህ ሹክሹክታዬን
ትረዳለህ የኔን ስሜት፣
አቻየን ካገኘሁ ቤትህ
ይቀናዋል ላኣፌ ሀሜት።
በከበረው አፀድ ቅጥር
ያንደበቷ ቃል የማይጥም
ብኩን ልጁን የሚያስገባት፣
የት ይገኛል ከአንተ በቀር
የሰማይስ የምድር አባት?
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
2900
23:57
04.12.2024
imageImage preview is unavailable
#የጠፋው_ፎቶ
ብርቱነት ደግነት የሚነበብበት፣
አሳዛኝ ገፅታው ፈገግታው ያለበት፣
ሳልወለድ በፊት ገና ወጣት ሳለ፣
በጥቁር እና ነጭ ቀለም የተሳለ፣
በጊዜ በሂደት እየተጣጠፈ፣
ጓደኛዬ ሆኖኝ ዘመን ያሳለፈ፣
ካቧራ ከውሀ ከንፋስ ጠብቄ፣
በክብር ሳጥን ውስጥ
ያኖርኩት ደብቄ፣
የአባዬ ምስል የጉብዝናው ፎቶ፣
የነብሴ መፅናኛ አደከመኝ ጠፍቶ።
መደርደሪያ አፈረስኩ
ከፈትኩኝ ቁምሳጥን፣
ያ'ባቴን ትዝታ ለማግኘት ስፈጥን፣
ፈተሽኩት ቦርሳዬን ጎረጎርኩኝ ሻንጣ፣
ከትውስታዎቹ ብቸኛውን ባጣ፣
አነሳሁኝ ምንጣፍ አራገፍኩኝ ልብሴን፣
ሣስስ አምሳያየን ስፈልግ እራሴን።
ድሮ ልጅ እያለሁ እማ የሰጠችኝ፣
"ይህ ነው ጀግና አባትሽ" ብላ ያሳየችኝ፣
ነብስ ያለው እውነታ ጉልበት ያለው ተስፋ፣
የአባባ ታሪክ ከፎቶው ጋር ጠፋ!
ገባሁ ሌላ ክፍል ከመፅሀፍ ክምር፣
ላላነብ ልገልፅ ላላውቅ ልመረምር፣
መሳቢያ እየሳብኩኝ ልበትን ወረቀት፣
ፍርሀት ሊያውከኝ ሊጫጫነኝ ጭንቀት።
አሰበረኝ እቃ አስጣለኝ ብርጭቆ፣
ብቻዬን መቅረቴን ልቦናዬ አውቆ፣
ቃኘሁ በየክፍሉ በግድግዳው ስፋት፣
ምልክት ላላገኝ አይኖቼን ለማልፋት።
ባካል ባውቀው ኑሮ በሂወቱ ሳለ፣
እንዳባት ቢጠራኝ ልጄ ሌጄ እያለ፣
እያወጋኝ ቢሄድ አርጎኝ በትከሻው፣
ይሆነኝ ነበረ ድምጹ ማስታዎሻው!
ሲያዝን ሲስቅ ባየው ሲቀያየር መልኩ፣
ይሆነኝ ነበረ ትዝታው ታሪኩ።
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
ብርቱነት ደግነት የሚነበብበት፣
አሳዛኝ ገፅታው ፈገግታው ያለበት፣
ሳልወለድ በፊት ገና ወጣት ሳለ፣
በጥቁር እና ነጭ ቀለም የተሳለ፣
በጊዜ በሂደት እየተጣጠፈ፣
ጓደኛዬ ሆኖኝ ዘመን ያሳለፈ፣
ካቧራ ከውሀ ከንፋስ ጠብቄ፣
በክብር ሳጥን ውስጥ
ያኖርኩት ደብቄ፣
የአባዬ ምስል የጉብዝናው ፎቶ፣
የነብሴ መፅናኛ አደከመኝ ጠፍቶ።
መደርደሪያ አፈረስኩ
ከፈትኩኝ ቁምሳጥን፣
ያ'ባቴን ትዝታ ለማግኘት ስፈጥን፣
ፈተሽኩት ቦርሳዬን ጎረጎርኩኝ ሻንጣ፣
ከትውስታዎቹ ብቸኛውን ባጣ፣
አነሳሁኝ ምንጣፍ አራገፍኩኝ ልብሴን፣
ሣስስ አምሳያየን ስፈልግ እራሴን።
ድሮ ልጅ እያለሁ እማ የሰጠችኝ፣
"ይህ ነው ጀግና አባትሽ" ብላ ያሳየችኝ፣
ነብስ ያለው እውነታ ጉልበት ያለው ተስፋ፣
የአባባ ታሪክ ከፎቶው ጋር ጠፋ!
ገባሁ ሌላ ክፍል ከመፅሀፍ ክምር፣
ላላነብ ልገልፅ ላላውቅ ልመረምር፣
መሳቢያ እየሳብኩኝ ልበትን ወረቀት፣
ፍርሀት ሊያውከኝ ሊጫጫነኝ ጭንቀት።
አሰበረኝ እቃ አስጣለኝ ብርጭቆ፣
ብቻዬን መቅረቴን ልቦናዬ አውቆ፣
ቃኘሁ በየክፍሉ በግድግዳው ስፋት፣
ምልክት ላላገኝ አይኖቼን ለማልፋት።
ባካል ባውቀው ኑሮ በሂወቱ ሳለ፣
እንዳባት ቢጠራኝ ልጄ ሌጄ እያለ፣
እያወጋኝ ቢሄድ አርጎኝ በትከሻው፣
ይሆነኝ ነበረ ድምጹ ማስታዎሻው!
ሲያዝን ሲስቅ ባየው ሲቀያየር መልኩ፣
ይሆነኝ ነበረ ትዝታው ታሪኩ።
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
2700
20:35
06.12.2024
#ዶሮን_ሲያነቃቋት
.
ላባም ክንፍም አለሽ እንደ አዋፋቱ፣
በግዝፈትም ቢሆን
ንስር ካንች አያንስም ቢለካ ክብደቱ፣
ትበሪያለሽ ተነሽ
ጭልፊትም አትበልጥሽ ካሞራም አታንሺ፣
እንደ ድንቢጦቹ
በረዥሙ ዛፍ ላይ ጎጆሽን ቀልሺ።
.
አሏት
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
.
ላባም ክንፍም አለሽ እንደ አዋፋቱ፣
በግዝፈትም ቢሆን
ንስር ካንች አያንስም ቢለካ ክብደቱ፣
ትበሪያለሽ ተነሽ
ጭልፊትም አትበልጥሽ ካሞራም አታንሺ፣
እንደ ድንቢጦቹ
በረዥሙ ዛፍ ላይ ጎጆሽን ቀልሺ።
.
አሏት
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
752
08:18
07.12.2024
2400
20:58
08.12.2024
እውነቱን ልንገርህ...?
በጨለመ ጎጆ ደጁ ባልተዘጋ፣
የተለኮሰች ጧፍ እንደማትረጋ፣
ልክ እንደዚች ጧፍ
የምትርገበገብ፣
የምትወዛገብ፣
የማታርፍ ጠፍታ የማትፈካ በርታ፣
ደምቃ እየፈዘዘች የምታመነታ፣
ፍርሀት ጥርጣሬ ሰርክ የሚቃትታት፣
እድሜ ቆይታዋን መወሰን ያቃታት፣
በንፋስ ሽውታ የምትርበተበት፣
ወላዋይ አይነት ናት
ባንተ ላይ የእኔ እምነት።
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
በጨለመ ጎጆ ደጁ ባልተዘጋ፣
የተለኮሰች ጧፍ እንደማትረጋ፣
ልክ እንደዚች ጧፍ
የምትርገበገብ፣
የምትወዛገብ፣
የማታርፍ ጠፍታ የማትፈካ በርታ፣
ደምቃ እየፈዘዘች የምታመነታ፣
ፍርሀት ጥርጣሬ ሰርክ የሚቃትታት፣
እድሜ ቆይታዋን መወሰን ያቃታት፣
በንፋስ ሽውታ የምትርበተበት፣
ወላዋይ አይነት ናት
ባንተ ላይ የእኔ እምነት።
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
628
15:23
11.12.2024
*
እማኮ
በጭንቀቴ ብታዝን እንጂ
ግድ የላትም ባገኝ ባጣ፣
አትመጣም እንደ ሌላው
ከጨለማው ቀኔን መርጣ።
.
እናቴኮ
ሁሌም ብትደግፈኝ እንጂ
በውድቀቴ አትሰለችም፣
የአብራኳ ክፋይ ነኛ
ለኔ ባዳ አይደለችም።
.
እምዬ
ለተራበ ብታጎርሳት
ያለቻትን ከማጀቷ፣
ሲቸግረኝ ስንቄ ሆኖ
ከፍሎልኛል ደግነቷ።
.
ለእኔ እናት
ይገባታል ውዱ ነገር
የምርጥ ምርጥ የተሻለ።
ለነገሩ.. ከልጆቿ የበለጠ
ውድ ለሷ ምንስ አለ?
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
እማኮ
በጭንቀቴ ብታዝን እንጂ
ግድ የላትም ባገኝ ባጣ፣
አትመጣም እንደ ሌላው
ከጨለማው ቀኔን መርጣ።
.
እናቴኮ
ሁሌም ብትደግፈኝ እንጂ
በውድቀቴ አትሰለችም፣
የአብራኳ ክፋይ ነኛ
ለኔ ባዳ አይደለችም።
.
እምዬ
ለተራበ ብታጎርሳት
ያለቻትን ከማጀቷ፣
ሲቸግረኝ ስንቄ ሆኖ
ከፍሎልኛል ደግነቷ።
.
ለእኔ እናት
ይገባታል ውዱ ነገር
የምርጥ ምርጥ የተሻለ።
ለነገሩ.. ከልጆቿ የበለጠ
ውድ ለሷ ምንስ አለ?
#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@arifgtmbcha
2000
19:33
17.12.2024
ሰላም ሰዎች🥰
https://t.me/+2W3uLWV6xy0wMTc0
👆👆ይሄ ቻናል 91,803 subscribers አለው። መግዛት የሚፈልግ ሰው
👇👇👇
@air_me1 inbox
https://t.me/+2W3uLWV6xy0wMTc0
👆👆ይሄ ቻናል 91,803 subscribers አለው። መግዛት የሚፈልግ ሰው
👇👇👇
@air_me1 inbox
301
17:48
18.12.2024
close
Reviews channel
No reviews
Top Rated in the Topic
New items
Channel statistics
7.1
0.0
0
1.4K
29.5%
0.0
lock_outline
Selected
0
channels for:$0.00
Followers:
0
Views:
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий