

Advertising on the Telegram channel «🎙Zena Adis Ethiopia🎙»
ይህ ዜና አዲስ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። 👇#ጥቆማ ለመስጠት 📢ለማስታወቂያ ሥራ👉 #Ethiopian_News 🇪🇹#ዜና_አዲስ_ኢትዮጵያ 🇪🇹#ወቅታዊ #መረጃዎች 🇪🇹#ልዩ_ልዩ #ዘገባዎች 🇪🇹#መዝናኛ #ዜናዎች_but 🇪🇹#ጠቃሚ #ጥቆማዎች_ይደርሶታል
Channel statistics
Full statisticschevron_rightኔታኒያሁ በንግግሩ አይሁድ ጠልነት አይሁድን በመጥላት ብቻ የሚቆም አንደለም ይልቁንስ ጥቁሮችን መጥላትን ጌይ የሆኑ ማህበረሰብን መጥላትንም ያስከትላል ይህ ደግሞ የማህበረሰብን ውድቀት ያስከትላል በማለት አስጠንቅቋል።
በመሆኑም የነዚህ መብቶች እንዲጠበቅ አይሁድ ላይ የሚደረገው ጥላቻ መቆም አለበት ብሏል።
እስራኤል በመካከለኛው ምስራቅ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን የምትፈቅድ ብቸኛ ሀገር ስትሆን የእስራኤል ተወላጆች አለም አቀፍ ድርጅቶችን በመጠምዘዝ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን መብት እንዲጠበቅ ዋነኛ ጠምዛዦቼ ናቸው።
የምእራባውያን የፋይናንስ እና ፖለቲካ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ሚና ያላቸው እስራኤላውያን በአለም እነኝህን አስተሳሰቦች ኤክስፖርት በማድረግ ቀዳሚ ናቸው።
የመጀመሪያውን የፅታ መቀየሪያ ሆስፒታል የገነቡት እነርሱ ናቸው።
@Zena_Adis_Ethiopia
@Zena_Adis_Ethiopia
የሰው ልጅ ደም በቀይ የደም ሕዋሳት ላይ ያሉትን ንጥረ ነገሮች መሠረት በማድረግ ኤ (A) ፣ ቢ (B) ፣ ኤቢ (AB) እና ኦ (O) ተብሎ በአራት ይከፈላል፡፡ የተመገብነው ምግብ በአንጀታች ውስጥ ከተፈጨ በኋላ በደማችን አማካኝነት ወደተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች ይሠራጫል፡፡ በዚህም ሂደት ውስጥ ምግባችን ውስጥ ያሉ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች ከደማችን ጋር ኬሚካላዊ ግንኙነትና ውሕድ ይፈጥራሉ፡፡ ይህንንም ተከትሎ ከደማችን ዓይነት ጋር የሚስማማ ምግብ ከተመገብን የምግብ የመላም ሂደት ሊፋጠን፣ አላስፈላጊ ክብደት ልንቀንስ፣ የላቀ ጉልበት ሊኖረን እንዲሁም የበሽታ የመከላከል ዓቅማችንም ሊዳብር ይችላል፡፡ከዚህ በመቀጠልም ከእያንዳንዱ የደም ዓይነቶች ጋር የሚጣጣሙ የምግብ ዓይነቶችን እንጠቅሳለን፡፡
1) የ ኦ (O)ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት
ይህ የደም ዓይነት ከሌሎች ቀድሞ የነበረ ጥንታዊ ሲሆን ከእንስሳት አዳኞች የተወረሰ የደም ዓይነት ነው፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ዓሣ፣ የባህር ምግብ፣ ቀይ ስጋ፣ ጨው፣ ዶሮ፣ ሲኳር ድንችና የመሳሰሉትን ምግቦች እንዲያዘወትሩ ይመከራል፡፡በዚያውም ልክ እንቁላል፣ የእንስሳት ተዋጽኦዎች፣ ስንዴና ባቄላን ከገበታቸው ማራቅ አለባቸው፡፡
2) የ ኤ (A) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት
ይህ የሰው ልጆች ወደ እርሻ ሲገቡ በተፈጠረው የአመጋገብ ለውጥ ምክንያት የተከሰተ የደም ዓይነት ነው፡፡ በዚያ ዘመንም የሰው ልጆች ለመኖነት ፊታቸውን ወደ አትክልቶች በማዞራቸው ምክንያት በጊዜ ሂደት እጅግ የዳበረ የምግብ ማላም ስርዓትን አዳበሩ፡፡ በአንጀታችው ውስጥ የሚገኙት የባክቴሪያዎች ዓይነትና ቁጥርም እጅግ ተበራከተ፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ፖም፣ አቮካዶ፣ ሰላጣ፣ ካሮት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ባቄላ፣ እርጎ፣ የስንዴ ዳቦና ፓስታ እንዲመገቡ ይመከራል፡፡ ነገር ግን እንቁላል፣ ስጋ እና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦዎችን በተገቢው መንገድ ለማብላላት አንጀታቸው አልዳበረም፡፡
3) የ ቢ (B) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት
የጥንቶቹ አዳኞች ወደ ሒማሊያስ ተራሮች በመሰደድ እንስሳትንም በማላመድ የአርብቶ አደር ሕይወትን መምራት ሲጀምሩ የተፈጠረ የደም ዓይነት ነው፡፡ ቀይ ስጋ፣ ዓሣ፣ እርጎ፣ ዓይብ፣ ወተት፣ ሙዝ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ወይንና አናናስ ተስማሚ ከሚባሉት ምግቦች መካከል ሲጠቀሱ ዶሮ፣ ስንዴ፣ ቲማቲም እንዲሁም ለውዝ እንዳይመገቡ ይመከራል፡፡
4) የ ኤቢ (AB) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት
ኤቢ የደም ዓይነት በቅርብ ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ከዓለም ህዝብም በአምስት ፐርሰንቱ ውስጥ ብቻ ይገኛል፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ስጋንና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦዎችን መፍጨት ቢችሉም የጨጓራቸው አሲድ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት የተመገቡት ምግብ በስብ መልክ ይከማቻል፡፡ ፍራፍሬዎችና አረንጓዴ አትክልቶች፣ ሀብሀብ እና ወይን፣ እንደ ቱና እና ሰርዲን ያሉ የባህር ምግቦችን ማዘውተር ተገቢ ሲሆን ከበቆሎ፣ የበሬና አሳማ ስጋ እነዲሁም ከአልኮሆልና ቡና መራቅ ያስፈልጋቸዋል፡፡
@Zena_Adis_Ethiopia
@Zena_Adis_Ethiopia
የህዝብ ተወካዮች የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት የትምህርት ዘርፉን የ1ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ተመልክቷል።የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ወቅት፥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን የወጥነት ችግር እንደነበረበት አንስተዋል።
በክብር ዶክትሬት አሰጣጡ ወጥ አሠራር መከተል በማስፈለጉ ሀገራዊ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ከዚህ በኋላ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን በመመሪያው መሠረት መፈጸም እንደሚኖርባቸው ጠቁመዋል።የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት በመመሪያው የተቀመጡ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው ብለዋል።
በሙያው የተለየ ሥራ ያበረከተ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ በመመሪያው የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።ይሁን እንጂ የተሰጠውን የክብር ዶክትሬት ለመጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል ተናግረዋል።
@Zena_Adis_Ethiopia
@Zena_Adis_Ethiopia
የህዝብ ተወካዮች የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት የትምህርት ዘርፉን የ1ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ተመልክቷል።የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ወቅት፥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን የወጥነት ችግር እንደነበረበት አንስተዋል።
በክብር ዶክትሬት አሰጣጡ ወጥ አሠራር መከተል በማስፈለጉ ሀገራዊ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ከዚህ በኋላ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን በመመሪያው መሠረት መፈጸም እንደሚኖርባቸው ጠቁመዋል።የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት በመመሪያው የተቀመጡ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው ብለዋል።
በሙያው የተለየ ሥራ ያበረከተ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ በመመሪያው የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።ይሁን እንጂ የተሰጠውን የክብር ዶክትሬት ለመጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል ተናግረዋል።
@Zena_Adis_Ethiopia
@Zena_Adis_Ethiopia
⚡️ Launch your Telegram ads in minutes with access to verified channels, groups, mini apps, and bots.
Reach real, bot-free audiences — from crypto to lifestyle — with automated placements, live analytics, and measurable results.
How it works:
1️⃣ Sign up via this link: Telega.io
2️⃣ Add funds
3️⃣ Choose channels and add your ad post
➡️ We’ll take care of the rest
Stay ahead — 6 000+ channels to test, track, and scale!
እያሳየሁት ያለወ ወታደራዊ ትዕግስት "ገደብ የለሽ እና ቅድመ ሁኔታ የሌለው አይደለም" ስትል አስጥንቅቃለች
ኢትዮጵያ ኤርትራ "ታጣቂ ቡድኖችን ትደግፋለች፣ ሉዓላዊነቴንም እየጣሰች ነው" ስትል ከሰሰች፣ "የአሰብ ወደብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቅድሚያ የምትሰጠው ብሔራዊ ጉዳይ" መሆኑንም አስታውቃለች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ይህን ያሉት ሆርን ሪቪው እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ባዘጋጁት እና ትናንት ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ፎረም ላይ ነው።
በዚሁ ወቅት የኢትዮ-ኤርትራ ውጥረቶች ታሪካዊ እና አሁናዊ መነሻዎች ላይ ዝርዝር ግምገማ የቀረበ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያ ችግሩን ለመፍታት ያላት አካሄድ መቀመጡ ተገልጿል።
Via-addisstandard
@Zena_Adis_Ethiopia
@Zena_Adis_Ethiopi
ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር አደጋዎች ቅናሽ አሳይተዋል ተብሏል።
በ2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም 7 ሺ 8መቶ አደጋዎች መመዝገባቸዉ የተገለፀ ሲሆን፥ከባለፈዉ ዓመት ጋር ሲነፃፃር አደጋዎች ቀንሰዋል ነው የተባለው።
የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ፥ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወር ላይ ከ8 ሺህ 5መቶ በላይ አደጋዎች መመዝገባቸዉን አስታውሰዋል።
ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፃርም በ2018 የደረሰዉ አደጋ በከባድና በቀላል አደጋ ላይ መቀነስ ማሳየቱን ተናግረዋል።
በ2018 የነበሩትን የአደባባይ በዓላትን በሰላም አጠናቀናል ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፥ ቀጣይ የሚቀሩትንም 3 ሩብ አመታትን ከህብረተሰቡ ጎን በመሆን ዉጤታማ ስራዎችን እንሰራለን ብለዋል።
@Zena_Adis_Ethiopia
@Zena_Adis_Ethiopia
ለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ቄስለምሪ ፒሊ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በላኩት የማጽናኛ ደብዳቤ በአርሲ በኦርቶዶክሳውያን ላይ በደረሰው ግድያ ጉባኤው በጥልቅ ማዘኑን ገልጸው ጥቃቱን አውግዘዋል።
ዋና ጸሐፊው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በላኩት የማጽናኛ ደብዳቤ፤ “ይህ በሰዎች ላይ በዘፈቀደ የሚፈፀም ግድያ የሚያመላክተው የሰላሙ ሁኔታ ያልተረጋጋ መሆኑን የሚያመላክት ነው። ይህም አስቸኳይ እርቅ ለመፈጸምና ለሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ሰብዓዊ ጥበቃ ማድረግ ግዴታ መሆኑን የሚያመላክት ነው” ብለዋል።
“በዚህ አስከፊ የሃዘን ወቅት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና ከመላው ኢትዮጵያውያን በጋራ አብረን የምንቆም መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን፤ በዚህ ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡት ነፍሳቸውን በሰላም እንዲያሳርፍልን በጥቃቱ ለተጎዱት ሁሉ መጽናናትንና ጥንካሬን እንዲሰጥልን እግዚአብሔር አምላካችን በጸሎት እንጠይቃለን” ብለዋል ዋና ጸሐፊው ለቤተ ክርስቲያኗ በላኩት የማጽናኛ ደብዳቤያቸው።
“የግጭቶችን መሠረታዊ መንስኤ በመለየትና ንግግሮችና ምክክሮች እንዲኖሩ በማድረግ የሰው ልጆች ሕይወትና ክብር ይጠበቅና ይረጋገጥ ዘንድ እግዚአብሔር አምላክ በሁሉም ደረጃ ለሚገኙ መሪዎች ጥበብንና ቁእጠኝነትን እንዲሰጥልን እንጸልያለን” ብሏል ጉባኤው።
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀም እንዲህ ዓይነቱን ግድያ በጥብቅ የሚያወግዝ መሆኑን የገለጹት ዋና ጸሐፊው፣ ሰላምን፣ ፍትሕንና በሕዝቦች መካከል ተቻችሎ በሰላም ለመኖር ለሚደረገው ጥረት ደግሞ ጉባኤው የማያቋርጥ ድጋፍ ያለው መሆኑን ገልጿል።
በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ በጉና፣ በመርቲ፣ በሸርካ እና ሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታዮች መገደላቸውን ቤተ ክርስቲያኒቱን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገልጸው የነበረ ቢሆንም የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኋላ አደረግሁት ባለው ማጣራት ጥቃቱ በአንድ ሃይማኖት እና ብሔር ላይ ያነጻጸረ አለመሆኑን መግለጹ ይታወሳል።
@Zena_Adis_Ethiopia
@Zena_Adis_Ethiopia
የናይጄሪያ መንግሥት የመጀመርያ ደረጃ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ የሚያዘውን አወዛጋቢ ፖሊሲ መሰረዙን አስታወቀ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ቱንጂ አላኡሳ ከሦስት ዓመት በፊት ተግባር ላይ የዋለው ይህ ፕሮግራም የታለመለትን ግብ ስላልመታ ከአሁን ጀምሮ ጥቅም ላይ እንዳይውል ተወስኗል ብለዋል።
በዚያ ምትክ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ድረስ እንግሊዘኛ የትምህርት መስጫ ቋንቋ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።
አሁን የተሰረዘው በአፍ መፍቻ እንዲማሩ የሚያዘው ፖሊሲ ሥራ ላይ የዋለው በቀድሞው የትምህርት ሚኒስትር አዳሙ አዳሙ ሲሆን፣ ሕጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ይበልጥ ይማራሉ ሲሉ ይከራከራሉ።
አዳሙ ሕጻናት "በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲማሩ" ጽንሰ ሃሳቦችን በቀላሉ ለመረዳት ያስችላቸዋል ብለዋል።
ይህ የቀድሞው ሚኒስትር ሃሳብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቅድመ መደበኛ ትምህርት ላይ ባካሄዳቸው በርካታ ጥናቶች ላይም ተቀባይነት ያገኘ ነው።
የናይጄሪያ ትምህርት ሥርዓት በትምህርት ጥራት ማነስ፣ በቂ የሆነ የማስተማሪያ መሣሪያ ባለመኖር፣ በዝቅተኛ የመምህራን ደሞዝ እና በርካታ የትምህርት ማቆም አድማዎች በመካሄዳቸው ተግዳሮቶች ገጥሞታል።
በአገሪቱ ውስጥ 85 በመቶ የሚሆኑ ሕጻናት ወደ መጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሄዱም ሁለተኛ ደረጃን ግን የሚያጠናቅቁት ግማሽ ያህሉ ብቻ ናቸው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
@Zena_Adis_Ethiopia
@Zena_Adis_Ethiopia
ትምህርት ቤቶች የክፍያ አፈጻጸሞችን በትምህርት ቤቱ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች እና ድህረ ገጾች ላይ በግልጽ ካላሳወቁ፤ 100 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት እንደሚጣልባቸውም በረቂቅ መመሪያው ላይ ተደነግጓል።
“ነጻና የግዴታ ትምህርት አተገባበር” የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ መመሪያ የተዘጋጀው በትምህርት ሚኒስቴር ነው።
የትምህርት ማህበረሰብ እና ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጡበት ዛሬ ሐሙስ ህዳር 4፤ 2018 ዓ.ም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይፋ የተደረገው ይህ ረቂቅ መመሪያ፤ በስድስት ክፍሎች እና በ35 አንቀጾች የተከፋፈለ ነው።
በመመሪያው ከተካተቱ ክፍሎች አንዱ “የግል ትምህርት ቤት የትምህርት ክፍያዎችን” የሚመለከት ነው።
በዚህ ክፍል የትምህርት ክፍያዎች ፍትሃዊነት እና ተመጣጣኝነት፣ የክፍያ አወሳሰን፣ የክፍያ ዘዴዎች፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት እንዲሁም የተከለከሉ ክፍያዎች ምንነትን የሚዘረዝሩ ድንጋጌዎች ተካትተዋል።
“ግልጽነትን” የሚመለከተው የመመሪያው ድንጋጌ፤ ሁለም የግል ትምህርት ቤቶች በወር ወይም በተርም የሚከፈለውን የተማሪዎች የትምህርት ክፍያ እና መመዝገቢያ “በይፋ መግለጽ” እንዳለባቸው ያስቀምጣል። ትምህርት ቤቶቹ ይህን ማድረግ የሚጠበቅባቸው “የትምህርት ዘመኑ ከመጀመሩ” በፊት እንደሆነም በድንጋጌው ላይ ሰፍሯል።
@Zena_Adis_Ethiopia
@Zena_Adis_Ethiopia
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በንጉስ ተክለሀይማኖት ክፍለ ከተማ ቀበሌ 04 ልዩ ቦታው ማርዘነብ ወፍጮ በስተጀርባ በኩል የጎርፍ መሄጃ ቦይ ውስጥ የቆራሊዮ ብረት በመልቀም ላይ እያለ ቦንብ አግኝቶ ሲነካካው በመፈንዳቱ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት ደርሷል።
ጉዳት የደረሰበት ግለሰብ በደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኝ ብስራት ሬዲዮ ከደብረማርቆስ ፖሊስ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
ህፃናት የሚፈነዱ ነገሮችን ካለማወቃቸው የተነሳ ሲነካኩ ለጉዳት የሚዳረጉ በመሆኑ ቤተሰብ እና ማህበረሰቡ የተለያዩ ብረቶችን አንስተው መነካካት የሌለባቸው መሆኑን በደንብ ማስተማር እና ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
@Zena_Adis_Ethiopia
@Zena_Adis_Ethiopia
Reviews channel
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «🎙Zena Adis Ethiopia🎙» is a Telegram channel in the category «Образование», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 35.2K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 12.5, with 0 reviews and an average score of 0.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 12.0 ₽, and with 1 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий