
Get clients in any niche!
Delegate the launch of advertising to us — for free
Learn more
13.0

Advertising on the Telegram channel «Ministry of Education»
5.0
3
Education
Language:
Amharic
433
0
The Ministry of Education channel offers curated, diverse educational content with engaging presentations and expert contributions, ensuring high quality and relevance.
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$12.00$12.00local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑ ተገለፀ።
በክልሉ ከሚገኙ አስር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዝግጅቱን አጠናቆ ተማሪዎቹን ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዝግጅት ምዕራፉን በክረምት ወቅት ሲሠራ መቆየቱን የገለፁት የተቋሙ ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኘ (ዶ/ር) ፤ በክልሉ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ተቋሙ የቅድመ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር አቅዶት ከነበረው ጊዜ መዘግየቱን ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት ከጀመረ በኋላ ለድህረ ምረቃ ተማሪዎች ትምህርት እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ.ም መደበኛ መማር ማስተማር ሥራ ለመግባት በተዘጋጀበት ወቅት በክልሉ የሰላም ችግር መፈጠሩን ጠቁመዋል፡፡
"ዩኒቨርሲቲው ዝግጅቱን ጨርሶ ተማሪዎችን ለመቀበል እየጠበቀ ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ፤ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚመጡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው መሔድ የሚችሉበት ሁኔታ ሊፈቀድ ይገባል ብለዋል።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
3700
08:08
10.11.2023
#ለጥንቃቄ
በአዲስ አበባ በከተማ " ጉንፋን መሰል " ህመም መከሰቱና ነዋሪዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው የጤና ባለሙያዎች እየመከሩ ናቸው።
በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሃኪም ዶ/ር ስንሻው አባይ ፤ በአዲስ አበባ በከተማ ለተከሰተው " ጉንፋን መሰል ህመም " ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ጉንፋን መሰል ህመሙ፦
- ከአፍንጫ ብዙ ፈሳሽ መውጣት፣
- ሳል፣
- ራስ ምታት፣
- ጉሮሮን የማቃጠል ስሜት፣
- ድካም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
ዶክተሩ ፤ ሰሞኑን የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም የላይኛውን የመተንፈሻ አካል ክፍል የሚያጠቃ ነው ብለዋል፡፡
ህመሙን ለመከላከል እና ለማስታገስ ፦
* ፈሳሽ መውሰድ፣
* ከቅዝቃዜ ራስን ማራቅ (ሙቀቱን የተመጣጠነ ማድረግ)፣
* መኖሪያ ቤትን አየር እንዲያገኝ ማድረግ፣
* በቂ የሆነ እረፍት መውሰድ እና የመሳሰሉትን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን መክረዋል።
በሌላ በኩል ፤ በቤት ውስጥ የእፅዋት ዝርያዎችን በፍም (እሳት) ላይ በማጨስ ጭሱን መታጠን ሳንባ እንዲያብጥ ወይም እንዲቆጣ በማድረግ ለጉዳት እንደሚዳርግ ተናግረዋል፡፡
ማህበረሰቡ ፦
° በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ውስጥ መስኮቶችን በመክፈት፣
° በንግድ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሰው በተሰበሰበበት ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በማድረግ፣
° የእጅን ንፅህና በአግባቡ በመጠበቅ እንዲሁም አስም ያለባቸው ምልክቶቹ እንደታዩባቸው ወደ ህክምና ተቋማት ሄደው መታየት እንዳለባቸው መክረዋል።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
5300
17:04
09.11.2023
የፌደራል መንግስት እና እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለዉ የኦነግ አማፂ ቡድን በኢጋድ አደራዳሪነት በአንዲት አፍሪካዊት ሀገር ለድርድር መቀመጣቸው ተሰምቷል ።
ከዚህ በፊት በታንዛኒያ ያልተሳካለት የተባለ ድርድር በሁለቱ ሀይሎች መካከል መደረጉ ይታወሳል ።
ይኼኛው ግን ለየት የሚያደርገዉ ድሪባ ኩማ ወይም በጫካ ስሙ ጃል መሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በድርድሩ ላይ መገኘቱ ነዉ ተብሎለታል ።
@Moe_Ethopia
@Moe_Ethopia
7200
08:32
08.11.2023
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።
ከጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ቀደም ሲል በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
ቀደም ሲል የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ?
- ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
- ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ16 ሳንቲም
@Moe_Ethopia
@Moe_Ethopia
7000
04:30
08.11.2023
በአማራ ክልል በማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በመከላከያ ሠራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ሰሞኑን ውጊያ መካሄዱን ዋዜማ ከአካባቢዎቹ ምንጮቿ ሰምታለች።
ኹለቱ ወገኖች፣ በደቡብና ሰሜን ወሎ ዞኖችም ውጊያ እንዳካሄዱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በውጊያው ሳቢያ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች እንዲኹም ከወረታ ከተማ ወደ ወልድያ ከተማ የሚወስዱ መንገዶች ለትራስፖርት ተዘግተዋል ተብሏል።
በምዕራብና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች ባለፉት ቀናት በተካሄዱ የተኩስ ልውውጦችም፣ ከአዲስ አበባ በሞጣና ደብረማርቆስ በኩል ወደ ባሕርዳር የሚወስዱ መንገዶች ለትራንስፖርት እንደተዘጉ ዋዜማ ትናንት ነዋሪዎችን ጠቅሳ መዘገቧ ይታወሳል።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
8100
05:55
07.11.2023
**በምን አለሽ ተራ በደረሰ የእሳት አደጋ 41 ሱቆች እና አራት መኖሪያ ቤቶች ወደሙ!**
በምን አለሽ ተራ በደረሰ የእሳት አደጋ ስድስት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።አደጋው ዛሬ ለሊት 7:26 ሰዓት ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ምን አለሽ ተራ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ የደረሰ ሲሆን የእሳት አደጋ ስድስት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ሲደርስ በአራት መኖሪያ ቤቶችና በአርባ አንድ የንግድ ሱቆች ወድመዋል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቭዥን እንደተናገሩት የእሳት አደጋዉ የደረሰባቸዉ የተለያዩ ቁሳቁሶች ማምረቻና ልዩ ልዩ የንግድ አገልግሎት የሚሰጥባቸዉ ሲሆን የንግድ ሱቆቹም አንድ ሜትር በሁለት ሜትር ገደማ የሚሆኑ እጅግ ጠባብ ሱቆች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
8700
09:54
06.11.2023
2ኛ ዙር ብሔራዊ የድኅረ-ምረቃ የመግቢያ ፈተና (GAT) ምዝገባ ዛሬ ይጀምራል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለሚሰጡት 2ኛ ዙር ብሔራዊ የድኅረ-ምረቃ የመግቢያ ፈተና (GAT) ምዝገባ ዛሬ የተጀመረ ሲሆን እስከ አርብ **ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም** የሚቆይ ይሆናል።
የመግቢያ ፈተናው ከ**ህዳር 03 እስከ 07/2016 ዓ.ም** ይሰጣል።
ፈተና በመጀመሪያ ዙር የመግቢያ ፈተናው መውሰድ ላልቻሉ እንዲሁም ፈተናው ወስደው ማለፍ ላልቻሉ ተጨማሪ ዕድል የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፖርታል ላይ በመግባት ምዝገባ ያድርጉ፦ **https://portal.aau.edu.et**
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
7200
07:48
06.11.2023
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ከ9,000 በላይ ተማሪዎች 657 በማምጣት ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው የቀላሚኖ ት/ት ተማሪ ሙሴ ኪዳነ " መድረስ ከነበረብኝ የትምህርት ደረጃ ባለመድረሴ ዓመታት ከእድሜ ላይ ተሰርቋል " ሲል ገልጿል።
የትግራይ #ሃውዜን ነዋሪ የሆነው ተማሪ ሙሴ አሁን ላይ እድሜው 22 ሲሆን ፤ ባስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ደስ መሰኘቱን ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግሯል።
አስከፊው ጦርነት በይከሰትና ወደኃላ ባይቅር ኖሮ አሁን ላይ የ4ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እንደነበርም ገልጿል።
ሙሴ ኪዳነ ፥ " አሁን የመጣው የፈተና ውጤት ጥሩ ነው። ደስም ብሎኛል ከውጤቱ ጋር አያይዤ ማለት የምፈልገው ሁሉም ሰው ያሰበውን ደረጃ ለመድረስ የሚያስችለውን ጥረት ካደረገ ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ ነው። " ብሏል።
መድረስ ከነበረበት የትምህርት ደረጃ ባለመድረሱ ዓመታት ከእድሜው እንደተሰረቀበት የሚገልፀው ተማሪ ሙሴ አሁን የሚገባውን ሁሉ የሚማርበት እድል ሊመቻች ይገባል ሲል ለትግራይ ቴሌቪዥን ተናግሯል።
በትግራይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ከ9,000 በላይ ተማሪዎች 73.09 በመቶ የሚሆኑት የተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም 51.38 በመቶ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች በአጠቃላይ 66.96 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አግኝተዋል።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
7400
04:40
06.11.2023
imageImage preview is unavailable
በአማራ ክልል ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን እንደማይጠሩ ተገለፀ
በዐማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ምክንያት፣ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ መደበኛ ሥራቸው በቅርቡ እንደማይመለሱ፣ የክልል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም አስታውቋል፡፡
የፎረሙ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራቸው ቆይታ፣ በክልሉ የሚገኙ ዐሥሩም ዩኒቨርሲቲዎች፣ የክልሉ ጸጥታዊ ኹኔታ እስኪሻሻል ድረስ ተማሪዎቻቸውን እንደማይጠሩ፣ የጋራ መግባባት ላይ እንደደረሱ ገልጸዋል፡፡
ተለዋዋጭነት ባለው የክልሉ ጸጥታ ምክንያት መንገድ መዘጋቱ፣ ተማሪዎች ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ግጭት ቢነሣ ዩኒቨርሲቲዎቹ ሓላፊነት መውሰድ ስለማይችሉ፣ እንዲሁም ከምግብ ጀምሮ ለዩኒቨርሲቲዎች ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ያቀርቡ የነበሩ አካላት፣ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ማስታወቃቸው፣ ለፎረሙ ውሳኔ መሠረት እንደኾኑ ጸሐፊው አስረድተዋል፡፡
ይኹንና ያነጋገርናቸው ተማሪዎች፣ በአሁኑ ሰዓት ዩኒቨርሲቲዎቹ ቢጠሯቸው እንደሚገቡ ገልጸዋል፡፡ የተማሪዎቹ ወላጆች በአንጻሩ፣ የፎረሙን ውሳኔ እንደሚቀበሉት ተናግረዋል ሢል የአሜሪካ ድምፅ ነው የዘገበው።
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
8986
05:43
05.11.2023
imageImage preview is unavailable
**የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የፈተና ውጤት ይፋ ሆነ!**
በትግራይ ክልል የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ዛሬ ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ውጤቱ÷ ዛሬ ከምሽቱ 3 ሠዓት ጀምሮ ይፋ መደረጉን ነው አገልግሎቱ ያስታወቀው፡፡
ተፈታኞችም eaes.et ላይ በመግባት የፈተና አዳራሽ መግቢያ መታወቂያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስም ብቻ በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ ነው የተባለው፡፡
@Moe_Ethiopia
@Moe_Ethiopia
7837
05:09
05.11.2023
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
1 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
c
**ffeenold@******.io
On the service since June 2022
15.12.202420:49
5
Everything is fine. Thank you!
Show more
New items
Channel statistics
Rating
13.0
Rating reviews
5.0
Сhannel Rating
5
Subscribers:
124K
APV
lock_outline
ER
--%
Posts per day:
0.0
CPM
lock_outlineSelected
0
channels for:$0.00
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий