
- Main
- Catalog
- News and Media
- Advertising on the Telegram channel «👳♂ዝክረ ቅዱሳን ቅዱሳን👳♂»
Advertising on the Telegram channel «👳♂ዝክረ ቅዱሳን ቅዱሳን👳♂»
Our voice for our united religion for our Ethiopian country. May the peace of God, the intercession and prayer of our mother, the Holy Virgin Mary, the protection of the angels and the blessings of the saints be with you, Amen!
Channel statistics
ቅድስት ሥላሴ የአንድነት መጠሪያ ስማቸው ‘እግዚአብሔር’ የሚልነው፡፡‘እግዚአብሔር’ የሚለው ስመ አምላክ በዝርዝር ቃላት ቅድስትሥላሴን ሲያመለክት እንደሚከተለው ነው፡-
ቅድስት ሥላሴ የአንድነት መጠሪያ ስማቸው ‘እግዚአብሔር’ የሚልነው፡፡‘እግዚአብሔር’ የሚለው ስመ አምላክ በዝርዝር ቃላት ቅድስትሥላሴን ሲያመለክት እንደሚከተለው ነው፡-
🤩 ጥያቄ፡- በእግዚአብሔር (በቅድስት ሥላሴ) ‘አሐዱ አምላክ- አንድ አምላክ’ ማመናችን እንዴት ይለጻል?
ኢይኩን ብዑደ ወኢፍሉጠ፡፡ ንፍልጥ ወንሌሊ ከመ ኢይኩንሕዉሰ፡፡ አኮ ዘንብል ሠለስቱ ከመ አብርሃም ይስሐቅወያዕቆብ፡፡ አላ አሐዱ ውእቱ እንዘ ሠለስቱ ግጻዌ፡፡ ወአኮዘንብል አሐዱ ከመ አዳም ቀዳሜ ኩሉ ፍጥረት አላ ሠለስቱእንዘ አሐዱ ህላዌ ናሁ ንሰምዖሙ ለአይሁድ እኩያንወለእስማኤላውያን ጊጉያን እለ ይብሉ አሐዱ ገጽ🤩 “ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ሚስቱንም ይከተላል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፡፡” ይላል /ዘፍ.፪፥፳፬/፡፡🤩 “እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ነው” /ዘዳ.፮፥፬/፡፡እግዚአብሔር አንድ🤩 “የፈጠራችሁ አንድ እግዚአብሔር አይደለምን? የሁላችሁስ አባት አንድ አይደለምን?” /ሚል.፪፥፲/፡፡ በአባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ገለጠልን እንጂእግዚአብሔርንስ ከቶ ያየው የለም፡፡” /ዮሐ.፩፥፲፰/፡፡🤩 “እኔና አብ አንድ ነን፡፡” /ዮሐ.፲፥፴/፡፡🤩 “ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አንተ በእኔ እንዳለህ፥ እኔም በአንተእንዳለህ፥ እነርሱም እንደ እኛ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አንተምእንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፡፡ እኔም የሰጠኸኝን ክብርሰጠኋቸው፤ እኛ አንድ እንደሆን እነርሱም እንደ እኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ፡፡” /ዮሐ.፲፯፥፳፩-፳፪/፡፡🤩 “ያመኑትም ሁሉ አንድ ልብና አንዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር” /ሐዋ.፬፥፴፪/፡፡🤩 “ሁላችን ብዙዎች /ሮሜ.፲፪፥፭/፡፡ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን”🤩 “የሚተክልም፥ የሚያጠጣም አንድ ናቸው፤ ድካማቸው ዋጋቸውን ይቀበላሉ፡፡” /፩ኛቆሮ.፫፥፰/፡፡ሁሉም እንደ🤩 “መንፈስ ቅዱስ አንድ ሲሆን ስጦታው ልዩ ልዩ ነው፡፡ ጌታም አንድሲሆን ልዩ ልዩ አገልግሎቶች አሉ፡፡ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግእግዚአብሔርም አንድ ሲሆን ልዩ ልዩ አሠራር አለ፡፡” /፩ኛቆሮ.፲፪፥፬-፮/፡፡
ታዲያ ሙሴ ‘ (ኤሎሂም)’ በማለቱ ብዙ የሆኑ አማልክትን እንዳያስቡ “አምላካችንእግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው” በማለት ለእስራኤል አስተማረ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም “አሐዱ እግዚአብሔር -እግዚአብሔር አንድ ነው” በማለት ጽፎአል /፩ኛጢሞ.፪፥፭/፡፡ ከአንዱ አምላክ ከእግዚአብሔር በቀር ሌሎች አማልክት ጣዖታትእንጂ እውነተኛ አምላክ አይደሉም፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር“እግዚአብሔር አምላክ እኔ ነኝ፡፡ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክትአይሁኑልህ” ያለው ለዚህ ነው /ዘፀ.፳፥፪/፡፡ ጣዖት ማለት በኅሊና የሚታሰብ፣ በአፍ የሚነገር በእጅ የሚሠራማምለኪያ (ባዕድ አምልኮ) ማለት ነው፡፡ አሕዛብ ጣዖትን የመሥራትልማድ አላቸው፡፡ “አማልክቲሆሙ ለአሕዛብ ዘወርቅ ወዘብሩር፡፡ግብረ እደ ዕጓለ እመሕያው፡፡ - የአሕዛብ ጣዖታቶች የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው፡፡” እንዲል /መዝ.፻፲፫፥፲፪/፡፡‘ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!’ ስንልየቅድስት ሥላሴ አንድነት በአምላካዊ ባሕርይ ተገልጧል ማለት ነው፡፡ የአብ አምላካዊ ባሕርይ የወልድ አምላካዊ ባሕርይ ነው፤ የመንፈስቅዱስም አምላካዊ ባሕርይ ነው፡፡ የወልድ አምላካዊ ባሕርይ የአብአምላካዊ ባሕርይ፣ የመንፈስ ቅዱስ አምላካዊ ባሕርይ ነው፡፡የመንፈስቅዱስ አምላካዊ ባሕርይ የአብ አምላካዊ ባሕርይ፣ የወልድ አምላካዊባሕርይ ነው፡፡ በዚህ አምላካዊ ባሕርይ ቅድስት ሥላሴ ይታመናሉ(ይመሰገናሉ፣ ይመለካሉ)፡፡ ስለዚህ አብ አምላክ ነው፤ ወልድ አምላክ ነው፤ መንፈስ ቅዱስአምላክ ነው፡፡ ቅድስት ሥላሴ በአምላክነት አንድ ናቸው ማለት ነው፡፡ነገር ግን አንድ አምላክ ቢባል እንጂ ሦስት አማልክት አይባልም፡፡ ሊቁቅዱስ አባት ዲዮናስዮስ “እርሱ አንድ አምላክ ነው፤ ሦስት አማልክትአይደለም አንድ ፈጣሪ ነው ብዙ አይደለም የማይመረመር አምላክነትክብር ለመለኮት ገንዘቡ ነው” በማለት እንደመሰከረው /ሃይ. አበውዘቅዱስ ዲዮናስዮስ ፺፬፥፭/፡፡“ እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐተ ስግደተ፡፡ እንዘአሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ፡፡ ይሤለሱ በአካላትወይትዋሐዱ በመለኮት፡፡ - አንድ ሲሆኑ ሦስት፣ ሦስት ሲሆኑ አንድ፤በአካል ሦስት ሲሆኑ በመለኮት (በአምላክነት) አንድ ለሚሆኑ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለሁ፡፡” ጸሎትዘዘወትር/፡፡
በሴት አንቀጽ “ቅድስት ሥላሴ” ያልነውን በወንድ አንቀጽም “ሥሉስ ቅዱስ (ቅዱስ እግዚአብሔር)” ይለዋል፡፡“አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽነበር፡፡” /ኢሳ.፮፥፫/፤ “አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎችአሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም፡፡” /ራእ.፬፥፰/፤ “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባዖት ፍጹም ምሉዕ ሰማያተ ወምድረቅድሳተ ስብሐቲከ፡፡ አሸናፊ እግዚአብሔር ሆይ፣ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስተብለህ ትመሰገናለህ፤ ምስጋናህም በሰማይና በምድር የመላ ነው፡፡” /ጸሎት ዘዘወትር/፤ “ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያውዘኢይመውት - የማይሞተው ቅዱስ ሕያው ቅዱስ ኃያል ቅዱስእግዚአብሔር” /ኪዳን ዘነግህ/፤ “አሐዱ አብ ቅዱስ፤ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፤ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ፡፡ - አንዱ አብ ቅዱስ ነው፤ አንዱወልድ ቅዱስ ነው፤ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡” /ሥርዓተ ቅዳሴ/፡፡
ሌላው ምሥጢር አምላካችን ቅድስት ሥላሴ “ቅድስት” የመባሉምሥጢር ‘እመ ዓለም የዓለም እናት (ፈጣሪ፣ ሠራዒና መጋቢ)’መሆናቸውን ያመለክታል፡፡ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫበምሳሌያዊ አገላለጽ፡-“ኀበ ርኅራኄክሙ በዝኀ ወኀበ አልቦቱ መሥፈርትእለ ትሠመዩ በስመ ብእሲት ሥላሴ ዕደወ ምሕረት ግናይ ለክሙ፡፡ - ቸርነታችሁ ከበዛና መሥፈሪያም ከሌለው ዘንድ ቅድስት ተብላችሁ በሴት ስም የምትጠሩ የይቅርታ ወንዶች ሥላሴ ሆይ ለእናንተ መገዛትይገባል” እንዳለው ማለት ነው፡፡
ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው የቅዱስ እግዚአብሔር (ቅድስትሥላሴ) በወንድና በሴት አንቀጽ መጠራት ምሳሌነት ያለው ነው፡፡ወንድ ኃያል ነውና ቢመታ ያደቅቃል፤ ቢወረውር ያርቃል፤ ቢያሥርያጠብቃል፡፡ ቅድስት ሥላሴም ከቸርነታቸው በቀር ፍጥረቱን ሁሉእናጥፋው ቢሉ ይቻላቸዋል፡፡ አንድም ወንድ ወጥቶ ወርዶ ነግዶሚስቱን ይመግባል፤ ልጆቹን ያሳድጋል፡፡ ቅድስት ሥላሴም በመፍጠርወላድያነ ዓለም ናቸውና የፈጠሩትን ፍጥረት በዝናብ አብቅለው፣
አብስለው ይመግቡታልና በወንድ አንቀጽ “ቅዱስ” ተብለውይጠራሉ፡፡ በሴት አንቀጽ “ቅድስት” ተብለው መጠራታቸው ደግሞ ሴት እናትናት፤ ቅድስት ሥላሴም የፍጥረቱ እናት ናቸው፡፡እናት በልጅዋወለደችው (አልወለደችው) ተብላ አትጠረጠርም፤ ቅድስት ሥላሴምይህን ዓለም ፈጠሩት (አልፈጠሩት) ተብለው አይጠረጠሩም፡፡“ነአምን በቅድስት ሥላሴ ዘውእቶሙ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፡፡- በቅድስት ሥላሴ እናምናለን፤ እነርሱም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡” እንዲል /ሃይ. አበው ዘቅዱስ ዮሐንስ አንጾኪያዊ ፻፲፫፥፫/፡፡ እናት ልጅዋ ቢታመምባት (ቢሞትባት) አትወድም፤ ቅድስትሥላሴም ከፍጥረታቸው አንዱ እንኳ በዲያብሎስ እጅ ቢገባባቸው(በኃጢአቱ ቢሞት) አይወዱም፡፡
አንድም እናት ፈጭታ፣ ጋግራ ቤተሰቦቿን ትመግባለች፤ ቅድስት ሥላሴም በዝናም አብቅለው በፀሐይአብስለው ፍጥረቱን ሁሉ ይመግባሉ፡፡በዚህ ሁሉ ርኅራኄያቸውለ“ቅድስት ሥላሴ” የአምልኮ ክብርና ምስጋናን “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” ብለን ቅዳሴያችንን እንሠዋለን፡፡ ይቀጥላል
Reviews channel
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «👳♂ዝክረ ቅዱሳን ቅዱሳን👳♂» is a Telegram channel in the category «Новости и СМИ», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 21.4K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 12.5, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 2.4 ₽, and with 3 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий