

- Main
- Catalog
- Recreation & Entertainment
- Advertising on the Telegram channel «🎬 Žeburã film production 🎬 #Your Islamic Channal»
Advertising on the Telegram channel «🎬 Žeburã film production 🎬 #Your Islamic Channal»
#እንኳን_በደህና_ወደ_ዘቡራ_ፕሮዳክሽን_መጡ!
#Welcome_to_Zebura_Productions
Channel statistics
Full statisticschevron_rightክፍል አራት
✍️ተምር አህመድ
በመሀል ቢኒያም ወደ ውስጥ ገብቶ....ለትንሽ ደቂቃ ከኋላዋ ቆሞ ካስተዋላት በኋላ..
<<ማሯ እረፊ.....አንቺ እንኳን እስኪ ጠንካራ ሁኚ በማርያም?.......እኔ እኮ ግራ ገባኝ...ሁለታችሁም በአንዴ ብቻዬን ጥላችሁኝ መሔዳችሁ ሳያንስ ጭራሽ ተለያይታችሁ የተለያየ ቦታ መሆናችሁ የበለጠ አስጨኘቀኝ....እግዚአብሔርን ማሯ ...አልቻልኩም......... ማሚ እና ኤልሲ ፊት ብቻ ምንም ያልመሠለኝ ጠንካራ ለመምሰል እንደምሞክር ታውቂያለሽ....አንቺም ብቶኚ ድክመትሽን በውስጥሽ ደብቀሽ እነሡ ፊት ለመጠንከር እንደምትሞክሪ በደንብ አውቃለሁ.......ግን እባክሽ እንደዚህ አትሁኚ ያንቺ መልፈስፈስ እኔን በጣም ይጎዳኛል....እባክሽ ለኔ ስትይ ጠንካራ ሁኚ.............ሀሳቤ እኮ የምትመደቡበት ሀገር መጥቼ ስራ መጀመር እና እስከምትመረቁ ድረስ አብሬያችሁ ከጎናችሁ መሆን ነበር....ተመልከች አሁን ግን እንደዛ ማድረግ አልችልም.....የትኞቻችሁ ጋር ሆኜ የትኞቻችሁ ጋር እቀራለሁ?.......ማሯ ታውቂያለሽ ያለ ኤልሲ ምንም ነገር እንደማይሆንልኝ....ምግብ እንኳን ካለሷ ብቻዬን እንደማልበላ ታውቂያለሽ.....አንቺንም አይንሽን ሳልመለከት...ስትኮሳተሪብኝ እና ፊት ስትነሺኝ የሚጎላውን ውበትሽን ሳላይ መዋል እንደማልችል ታውቂያለሽ...??ቆይ በዚህ ሰአት ከኔ በላይ የሚያሳዝን ማን አለ?.....>>ሳያስበው እያለቀሰ ነበር...
በዚህ ጊዜ መርየም ከተቀመጠችበት በፍጥነት እምባዋን እየጠረገች ተነስታ አይኗን ወደ መሬት እንደተከለች
<<ይበቃል ቢኒያም.......አሁን ትልልቅ ልጆች ሆነናል....ሁላችንም የራሳችንን መንገድ ለብቻችን መጀመር መቻል አለብን.......ስማኝ ቢኒያም ከዚህ በኋላ የማይጨበጥ እና ፈፅሞ እውን የማይሆን ህልም እያለምክ የወጣትነት ጊዜህን በከንቱ ከማባከን ብትቆጠብ እና የሚጠቅምክ ነገር ላይ ብታተኩር መልካም ነው....... ሒወት ሁልጊዜ እኛ ባሰብነው እና በፈለግነው መንገድ አትሔድም...ሰው እስከሆንን ድረስ መፈተን ያለ ነው......ልክ ነህ እኮ ፈተናው በጣም ይከብዳል......ግን ደግሞ ጠንካራ መሆን የሚቻለው ከባባድ ፈተናዎችን ማለፍ ስንችል ነው......ለምን ከበደኝ አትበል የከበደው ሊያጠነክርክ ካለህበት ከፍ ሊያደርግህ መሆኑን አትርሳ....ይልቁንም እለፈው እና ጠንካራ ሁን ኢንሻአላህ ያኔ ሁሉም ይስተካከላል........እኔም ኤልሲ ሳትኖር መማርን ሌሎች ጓደኞች መያዝን አየከበደኝም ቢሆን እለምደዋለሁ.........ታውቃለህ ካለሷ ማንንም እንደማልቀርብ...ግን ምን ማድረግ እችላለሁ.... አልሃምዱሊላህ ሁሉም የሚሆነው ለኸይር ነው....እንደዛ ብናስብ የተሻለ ነው...ምን አልባት ይህ መሆኑ ለኛ የበለጠ ይጠቅመን ይሆናል...እና ደግሞ በቃ አንተም የራስህን ሒወት መጀመር አለብክ ቢኒያም ይበቃል......ቤተሰቦቻችን እኔንም ኤልሲን በአንዴ ማጣታቸው ምን ያህል እንደጎዳቸው አይታይህም??.....እባክህን አንተም ተጨምረክ ሌላ ራስ ምታት አትሁንባቸው.... እባክህ አዚሁ ጠንካራ ሰራተኛ በመሆን ከጎናቸው ቆመህ አበርታቸው......ቤተሰቦቻችንንም አደራ.......ከዚህ የተሻለ የመሰናበቻ ጊዜ ድጋሚ ስለማላገኝ ደህና ሁን.....ከልጅነቴ ጀምሮ ከኤልሲ ሳትለይ ወንድምነትህን ስላሳየኸኝ አመሠግንሀለሁ ሁሌም ዱአ አደርግልሀለሁ....ቻው >>ብላ የሱን መልስ ሳትጠብቅ በፍጥነት ሱሪውን ከቁምሳጥኑ ውስጥ መዛ በማውጣት ወደ ጓሮ ከነፈች........ቢኒያምም ፊቱን ከጠራረገ በኋላ ክፍሉ በመግባት አልጋው ላይ ጋደም ብሎ ስለ መሬም ማሰብ ጀመረ........ራሱን በብዙ ጥያቄዎች በመወጠሩ ራሱን እያመመው እንኳን ማቆም አልቻለም....
"መቼ ነው መርየም እንዲህ እኔነቴን የተቆጣጠረችው ፤መቼ ነው ለኔ የሴቶች መለኪያ ሚዛን የሆነችው.....አይደለም ከሌላ እምነት ካለች ልጅ ፍቅር ሊይዘው የያዛቸውን ልጆች ለመመለስ የሚጥረውን የቤተክርስቲያን አገልጋዩ ቢኒያምን ራሱን ያስረሳችው መቼ ነው???....አሁንም ይጠይቃል....
*
መርየም ሻንጣውን አስተካክላ ጨርሳ የ ኤልሲን ፀጉር እየሰራቻት ነው....በመሀል የማሯ እናት ወ/ሮ ሀዋ መጥተው
<<የኔ ቆንጅዬ ለምቦጫም...... በይ ለምቦጭሽን ሰብስቢ እና ቆራጥ ሁኚልን ሁሌ ልጅነት የለም አሁን አድጋችኋል ሁለታችሁ እርስበርሳችሁ ብቻ ሳይሆን ከእኛ ጋርም ትለያያላችሁ....ከቀዪአችሁም...ከለመዳችሁት ትምህርት ቤታችሁ እና ጓደኞቻችሁ ጋር ትለያያላችሁ
..አዲስ ጓደኛ ትመሠርታላችሁ አዲስ ሀገር ትለምዳላችሁ ዱንያ እንዲህ ናት የኔ ልጅ......እናንተ የኔ ልጆች ደግሞ ጠንካራ ናችሁ... በሄዳችሁበት ሁሉ ከፍ በሉልኝ ...አዲስ ሀገር መልመድ ለብቻ ኑሮን መምራት መጀመር ቀላል አይደለም...አብሽሩ ሁሉንም ትለምዱታላችሁ...ኤልሲዬ ይቺ እንደምቶጂው አድርጌ ያዘጋጀሁልሽ ቆንጆ ዳቦ ቆሎ እና ኩኪስ ናት። የሁዳዴ ፃም እየደረሰ ስለሆነ ወተት እና እንቁላል አልተጠቀምኩም ለፃም ጊዜም ይሆንሻል .....በይ አሁን ለዕናትሽ ቃል ግቢላት ከአሁን በኋላ ንዴቱም ሀዘኑም ይበቃል...የኔ ኤልሲ አመስጋኝ ነገሮችን በመቀበል የምታምን ናት.....እንዲህ በዘን ውስጥ ለረጅም ጊዜ እያማረረች የምትቆይ ልጅ የለችኝም....>>
<<ልክ ነሽ ሀዋዬ አሁን እኮ አላዘንኩኝም.....አሁን ሁሉንም ተቀብያለሁ ሁሉም ለበጎ ነው ሚሆነው ማን ያውቃል ደግሞ አምላኬ ይቺን የማትረባ ከህይወቴ አስወጥቶ ሌላ ቆንጅዬ ጓደኛ ሊሰጠኝ ይሆናል እኮ...>>ብላ ከት ብላ ሳቀች
ኤልሲ እንደዚህ ናት....የፈለገችውን ነገር ለማሳካት እስከጥግ ድረስ ትጥራለች...መክፈል ያለባትን ሁሉ ትከፍላለች ግን ሳይሳካ ሲቀር ለአንድ ቀን እንኳን አዝና መቆየት አትችልም። ወዲያው ራሷን አሳምና ትቀበለዋለች....ከማማረር ይልቅ አመስግና እየተፍለቀለቀች ወደ ሌላ ጉዞ ትሔዳለች...አይደክማትም....ተስፋ አትቆርጥም...ሁሌም ፈገግ ትላለች...
**
ምንም እንኳን ቢኒያም ኤልሲን ለማድረስ ቤተሰቦቹን ለማሳመን ቢሞክርም አባቷ አቶ ዘነበ ልጃቸውን ራሳቸው እንደሚያደርሷት ተናግረው አሻፈረኝ በማለታቸው ሀሳቡ ውድቅ ሆኗል.......ቢኒያምም የአባቱን ፀባይ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ሳያንገራግር ወዲያው በአባቱ ሀሳብ ተስማምቶ ለአቶ ዘነበ እና ለኤልሲ የፕሌን ትኬት የቆረጠላቸው ከቀናት በፊት ይኸው ዛሬ በረራቸው ደርሶ ኤልሲና አቶ ዘነበ ስንብት ላይ ናቸው.......
ቢኒያም መተኪያ የሌላት እህቱን እንደ ጨቅላ ወስጡ ሽጉጥ አድርጎ ከአቀፋት በኋላ በደመነፍስ ግንባሯን ጉንጯን ደጋግሞ እየሳማት....
<<እሺ ታላቅየው አንተም ራስህን ጠብቅ>>ፈገግ ብላ
<<አሺ አንቺ ማስጠሊት ቻው በቃ መልካም ጉዞ>>ከእንባው ጋር እየተናነቀ ቢያወራትም መጨረሻ ላይ መቆጣጠር ስላቃተው ከክፍሉ ገብቶ ተንሰቀሰቀ።
መርየም እንዴት ብላ እንደምትሰናበታት ጨንቋታል..ሻንጣዋን ታክሲው ውስጥ አስገብታላት እንዳቀረቀረች ወደ ተሰበሰቡበት ተቀላቀለቻቸው
ኤልሲም ወደ ማሯ ዞራ
<<አብሮአደጌ በይ እንግዲህ ቻው...መቼም የኔ ናፍቆት ባህርዳር አብሮ እስኪያመጣሽ ቻው😂....እስኪ ይሄን ለንቦጭሽን ደግሞ ሰብስቢው...አያምርብሽም...>>ፈገግ ብላ ጉንጯን እየጎተተች
<<እረ አይገርምሽም ራስሽ ቀድመሽ እኔጋ ትመጫለሽ እስኪ እናያለን....ለማንኛውም ራስሸን ጠብቂ....እያንዳንዱን ነገር ሪፖርት ማድረግ እንዳትረሺ... ደግሞ ስልክሽ እንዳይዘጋ.....>>
<<እሺ አጅሪት ነይ አሁን እቀፊኝ>>>
ማሯ ተሰናብታት ከመዞሯ እየተንሰቀሰች እነሱ ቤት ካለው ክፍላቸው ገብታ ቆሐፈችው...ክፍሉ ገና ከአሁኑ ጭር አለባት...ብቸኝነት ተሰማት...የበለጠ ጮክ ብላ ስታለቅስ የክፍሉ በር ተንኳኳ
.
.
.
.
.ክፍል አምስት ይቀጥላል❤️❤️
ክፍል ሶስት
✍ተምር አህመድ
መቼም ሰሞኑን በእነ ኤልሲ እና መርየም ቤተሰብ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው ደስታ በቃላት መግለፅ ያዳግታል.....አቤት ደስታ.....አቤት ኩራት....
እነዚህ ቤተሰቦች በልጆቻቸው የተነሳ ከወዳጆቻቸው ደስታ፣ ክብር እና አድናቆት ሲቸራቸው ከርመዋል......
በተለይ ደግሞ መርየም ከትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ውጤት በማምጣቷ በመምህራኖቿ፣በጓደኞቿ፣በጎረቤቶቿ...እንዲሁም በዘመድአዝማዶቿ ከፍ ያለ አድናቆትን አስተናግዳለች... ሁሉም በተቻለው እና አቅሙ በፈቀደ መልኩ ሲያመሰግናት፣ሲመርቃት እና ሲሸልማት ከርሟል....ኤልሲም ብትሆን ከትምህርት ቤቱ ቶፕ-5 ውስጥ መግባት በመቻሏ ...ደስታቸውን እጥፍ ድርብ አድርጎላቸዋል...
ከልጅነታቸው ጀምሮ የመሰረቱት ጓደኝነት ተራ እና ጊዜያዊ ፍሬ አልባ እንዳልሆነ በተግባር አረጋግጠዋል ይልቁንም ጓደኝነታቸው ቁምነገር ያለው ከጥቅም የራቀ በንፁህ መግባባት ላይ የተፈጠረ ቤተሰባዊ እና እውነተኛ እህትነት መሆኑን በብዙዎች አስመስክሮላቸዋል....... ስለጓደኝነታቸው ትክክል ያልሆነ አመለካከት የነበራቸውን እና ያልተገባ ወሬ ያወሩ የነበሩትን ሰዎች ሁሉ በሀፍረት አንገት አስደፍተው ፣አፋቸውን አዘግተዋል......አዎ ከቃላት ጭቅጭቅ በላይ በተግባራቸው እውነተኛ የቁምነገር መዛመድ እንዳላቸው አሳይተዋል.....
*
ታዲያ ...ዛሬ ግን ይህ ቤተሰብ ያለወትሮው ቀዝቅዟል....ግቢው ያለመደበትን ጭውውውውው ብሏል....
አሁን ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ሆኗል....... ኤልሲ እና መርየም ድብርት እና ፍርሀት ውስጥ ሆነው እነማሯ ቤት ካለው ክፍላቸው ውስጥ ሻንጣ እያስተካከሉ ነው..... .............በነገራችን ላይ ኤልሳ እና መርየም ሁለት የጋራ ክፍሎች ሲኖሯቸው አንዱ እነ ኤልሲ ቤት ያለ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ እነ መርየም ቤት ያለነው....ሁለቱም ከልጅነታቸው ጀምሮ አንድ ቀን እነኤልሳ ቤት ሌላኛው ቀን ደግሞ እነ መርየም ቤት ካለው ክፍላቸው እያደሩ ነው ያደጉት....አንድም ቀን ተነጣጥለው ተኝተው አያውቁም....የፈተና ሰሞን እርስበርሳቸው እየተረዳዱ እና እየተበረታቱ ሲያነቡ ያድራሉ..... ፈተና በሌለ እና እረፍት በሆኑ ሰአት ደግሞ የኤልሲን የማያልቅ ወሬ እየሰሙ ፣እየተጨቃጨቁ እና እየሳቁ...... ሳያስቡት ሳይተኙ ይነጋባቸዋል..........ወይ ደግሞ በቢኒያም ጋባዥነት የተሰጣቸውን መፅሀፍ አንድ ላይ ያነባሉ አልያም ደግሞ ፊልም በጋራ እያዩ ያለቅሳሉ .......
*
መርየም ልብሶቹን እየመረጠች አጣጥፋ ሻንጣ ውስጥ እያስገባች ሳለ በመሀል
<< ኤልሲ የምቶጂው ጅንስ ሱሪ እዚህ አጣሁት ቆይ እናንተ ቤት ካለው ክፍል ሄጄ ልፈልገው ደግሞ ነግሬሻለሁ እስክመጣ ፀጉርሽን ፈተሽ ጨርሺ....የምር ዝም ብለሽ ተቀምጠሽ ባገኝሽ ዋ.....>>እየሳቀች አስጠንቅቃት ወጣች
ኤልሳም እንደደበራት ከአልጋው ላይ ተነስታ ፀጉሯን ማፍተልተል ጀመረች.....
*
ምንም እንኳን ኤልሲ እና መርየም የዩንቨርስቲ ምርጫቸውን ሙሉለሙሉ አመሳስለው ቢሞሉ የምደባው ውጥት ግን እንደፈለጉት ሳይሆንላቸው ቀርቷል......በወቅቱ በነበረው የፀጥታ ጉዳይ ከክልላቸው ውጪ የሆነ ሀገር አስቀድመው እንዳይሞሉ ቤተሰብ ስላስጠነቀቃቸው ከአዲስአበባ ቀጥሎ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ የማድረግ ምርጫቸው ከጎንደር እና ከባህርዳር ነበር.....ሆኖም የመሬም ቤተሰቦች ባህርዳር በዛ ያሉ ዘመዶች ስለነበራቸው እና ኤልሲም እዛው ባህርዳር ዩንቨርሲቲ ለመመረቅ ሁለት አመት የሚቀረው የአክስት ልጅ ስለነበራት ሁለቱም ተስማምተው ባህርዳርን ሁለተኛ አድርገው ጎንደርን በማስከተል ሌላውንም ሙሉለሙሉ አንድ አይነት አድርገው ሞልተው ነበረ።
ነገር ግን ከትምህርትቤታቸው አዲስአበባ ዩንቨርስቲ መግባት የቻሉት ሶስት ተማሪዎች ብቻ ስለነበሩ ኤልሲ ሁለተኛ ምርጫዋን አገኘች.......በዚህም ኤልሲ ባህርዳር መርየም ደግሞ አዲስአበባ ዩንቨርሲቲ ተመደቡ.....ሁለቱም ምደባቸውን ባወቁ በጥቂት ቀናት ውስጥ ዩንቨርስቲዎቻቸው ጥሪ ቢያደርጉላቸውም የኤልሳ የመግቢያ ቀን ይቀድም ስለነበር መርየም ነገ የምትለያትን ኤልሲ እቃ እያስተካከለች ነው.......ኤልሲ የምደባ ውጤት ከወጣ ጀምሮ ድብርት ውስጥ ናት በጣም ከፍቷታል....መርየምም በሷ ፊት ጠንካራ ለመምሰል ተሞክራለች እንጂ አጋጣሚውን ባገኘች ቁጥር እየተደበቀች ተንሰቅስቃ ታለቅሳለች.....ካለ ኤልሲ ምን ልትሆን እንደምትችል ስታስብ....ምናለ ሁሉም ቀርቶ እንዲሁ የሀይስኩል ተማሪ ሆነን በቀረን ትላለች.....አሁንም ክፍሉ ውስጥ ገብታ የኤልሲን ጅንስ ሱሪ ለማግኘት እቃውን እያተራመሰች ታለቅሳች......በመሀል ቢኒያም ወደ ውስጥ ገብቶ..........
.
.
.
.
.
ክፍል አራት ይቀጥላል.........❤❤
ማክሰኞ የካቲት 18/2017.........2:22
https/t.me/halalwithtemir
ክፍል ሁለት
✍ተምር አህመድ
ቢኒያምም እህቱን በስስት እያየ
<<ነይ እስኪ እቀፊኝ የኔ ቀበጥ...ወንድምሽ ስለአንቺ የማይጨነቅ ነው የሚመስልሽ ...ምንም እንኳን ውጤት ዛሬ እንደሚለቀቅ ባትነግሩኝም ከእናንተ ይምጣ ብዬ እንጂ ከሁላችሁም ቀድሜ ውጤታችሁን ያየሁት እኔ ነኝ .....ተመልከች አንቺም አልፈሻል የኔ የዋህ ይኸው 530 አምጥተሽ አልፈሻል.....>>
<<የምርህን ነው ወንድሜ ኦውውውውውው...>>በጩኸት እያለቀሰች ተጠመጠመችበት
<<መርየምም አልሃምዱሊላህ አልሀምዱሊላህ...ብላ ወይዘሮ ሙሉን አቀፈቻቸው>>
ቤቱ በድጋሚ በዕልልታ ቀለጠ....አቶ ዘበነ ልጃቸውን ግንባሯን ስመው እንደ ህፃን ጉልበታቸው ላይ አስቀምጠው በደስታ ያወሯታል።
ቢኒያምም ከቆመበት ተንቀሳቅሶ ሶፋው ላይ አረፍ አለ በዚህ ጊዜ ማሯ የምስጋና ሶላቷን ለማድረስ ወደ መታጠቢያ ቤት ለመውጣት ስትነሳ በኒያም ዘወር ብሎ
<<anyways ማሯ ኤልሲ ልክ ናት እስከአሁን የትምህርት ቤቱ ሰቃይ ነሽ congra ...>>አላት
መርየምም <<አመሰግናለሁ ቢኒያም....>>ብላ ወደ እሱ ሳትዞር መንገዷን ቀጠለች....
<<በይ ሚጡ ይበቃል እስከአሁን ሳትተኙ ቆያችሁ አሁን ግቡ እና ረፍት አድርጉ ተነሽ.....>>አቶ ዘበነ ነበር
<<እረ አባዬ እኔ ለሀዋዬ ሳልነግራትማ አልተኛም እኔ እስከጠዋት መጠበቅ አልችልም...>>
<<ተይ ልጄ በዚህ በለሊት ታስደነግጫታለሽ አይሆንም ሁሉም ጠዋት ይደርሳል>>¶
<<እምቢየው ሀዋዬ አትተኛም ይኼን ጊዜ ጨንቋት ነው ሚሆነው በጓሮ በር ሔጄ አንኳኳለሁ በጓሮ በር የምናንኳኳው እኛ እንደሆንን ስለምታውቅ አትደነግጥም....>>
<<ይህ እኮ ደስታ ነው ቀስ ብሎ ይደርሳል ግድ የለሽም ልጄ አትረብሿት እናንተም እረፉ>>¶ ወይዘሮ ሙሉ ነበሩ
<<አይሆንም ማሚ እነግራታለሁ....>>ወሬወዋን ሳትጨርስ ከአባቷ እግር ላይ ተስፈንጥራ ወደ ጓሮ ከነፈች።
<<ወዲያው ከነ ሀዋ ቤት የእልልታ ጩኸት አስተጋባ እነ ሙሉም ወደነሀዋ ቤት እየተሯሯጡ ሔዱ፤ቢኒያም በዕህቱ ቅብጠት ተገርሞ ፈገግ እያለ ወደ ክፍሉ ገብቶ ተኛ።
መርየምም ሁሉን ረስታ በዕኩለ ለሊት በባዶ ክፍል ውስጥ ከመስገጃዋ ላይ ተደፍታ ጌታዋን እያለቀሰች ታመሰግናለች፤ፍርሀት፣ጩኸት፣ጨለማ...ይህ ሁሉ አይሰማትም፣ልቧ ከጌታዋ ጋር ይበልጥ ተሳስሮ በዙሪያዋ ያለውን ሁሉ ረስታለች።....
ልክ ዱአዋን ጨርሳ ከመስገጃዋ ላይ ለማረፍ በሚመስል ሁኔታ ጋደም እንዳለች የስልኳ ጥሪ ተሰማት እና ከተኛችበት ተነስታ ስልኩን ስትመለከት አባቷ አቶ አደም ናቸው....
<<ቢስሚላህ ባባ በዚህ ሰአት ምን ሆኖ ነው የደወለው?ያረቢ ለኸይር አድርገው >>ብላ ፈራ ተባ እያለች አነሳችው
<<ሀሎ ባባ አሠላሙአለይኩም>>
<<ወአለይኩምሰላም ወረህመቱላህ የኔ ልጅ አሁን እኮ እናትሽ ደውላልኝ ነው አልሃምዱሊላህ እንኳን ደስ አለሽ ልጄ ....ደስ ስላለኝ ድምፅሽን ሳልሰማ አላድርም ብዬ እኮ ነው>>
<<እሺ ባባዬ እንኳን ደወልክልኝ አዎ አልሃምዱሊላህ ጀሊሉ ምን ይሳነዋል?>>
<<ምንም እናቴ ምንም ....ኮርቼያለሁ ልጄ አልሀምዱሊላህ አኩርተሽኛል ..አላህ ኸይሩን ብቻ ያድርግልሽ የኔ አስተዋይ...>>
<<አሚን ባባዬ አሚን..>>
<<በቃ ጠዋት እደውልላችኋለሁ አሁን አረፍ በሉ...>>
<<እሺ ባባ ደህና ደርልኝ ወሰላሙአለይኩም>>
ስልኩን አውርታ እንደጨረሰች በድጋሚ መስገጃዋ ላይ ቁጭ ብላ ዱአ አደረገች።
**
<<ማሯ...ማሯ...አንቺ ማሯ...ነይ እንጂ እቤት ሀዋዬን አግኚያት ሰው ሁሉ እኮ እናንተ ቤት ተሰብስቧል >>ኤልሲ ነበረች በዚህ ጨለማ በሙሉ ወኔ ከወዲያ ወዲህ እየዘለለች
<<ውይይ ኤልሲ ጠዋት እኮ ይደርስ ነበር ሰው መረበሹ ቆይ ለምን አስፈለገ>>
<<አንቺ ደግሞ ማን ይረበሻል?ሁሉም ደስ ብሏቸዋል .....ብታይ ደግሞ ኡስማን አላለፈም እህቱ እኮ ናት አሁን የነገረችኝ>>
<<ኤልሲ እንግዲህ ዝምምም በይ.....ነግሬሻለሁ>>ሂጃቧን እያስተካከለች ፈገግ ብላ ተቆጣቻት
<<እኔ እኮ ሳልጠይቃት ራሷ ናት የነገረችኝ ማለቴ እናንተ ቤት የሀዋዬን እልልታ ሰምተው ሁሉም ጎረቤቶች መጥተዋል ከዛ እማዬ የኡስማን እናትን የአንቺስ ልጅ እንዴት ሆነልሽ ስትላት አልነገረኝም አለች ከዛ እኔ እህቱን ቀስ ብዬ ስጠይቃት ወድቋል አለችኝ...>>ብላ ሳቀች
<<አንቺ አልጠየቅሻትም አይደል......ራሷ ነገረችሽ? ....እየዉልሽ ደግሞ አትሳቂ ነግሬሻለሁ እንዳይደገም>>እየተሯሯጡ በጓሮ በኩል እነመርየም ግቢ ገቡ
የወይዘሮ ሀዋን የደስታ እልልታ የሰሙ ጎረቤቶች ምን ተገኘ በዚህ ጨለማ.....ምንድነው እሱ?እያሉ እየተሯሯጡ ወደነ ሀዋ ግቢ ተሰብስበዋል፤
ወይዘሮ ሀዋ በደስታ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ሱጁድይወርዳሉ፣ይነሳሉ፣ይቀመጣሉ፣ይንቆራጠጣሉ.....ብቻ ባለአቅማቸውን ደስታቸውን በምስጋና ለመግለፅ ይታትራሉ፤
<<ልጄ አለፈችልኝ...ሙሉዬ ልጃችን እኮ አኮራችን፣ፀሀይዬ ልፋትሽ ከንቱ አልቀረም ልጅሽ አላሳፈረችሽም፤ሉቤ.. ሰማሽልኝ መሬምዬ እኮ አለፈች ነው ምትለኝ ኤልሲ ፤እሷም አለፈችልን አልሀምዱሊላህ ልጆቻችን እኮ አኮሩን .....አልሀምዱሊላህ.... ..ዩንቨርስቲ ልገቡልን እኮ ነው .....ደስታቸው አስደስቷቸው ለመጡት ጎረቤቶቻቸው እና ጓደኞቻቸው በሙሉ ደስታቸውን ለማጋራት በፍጥነት እያወሩ ያቅፏቸዋል።
<<እልልልልልልልልልልል....እሰይ እግዚአብሔር ይመስገን እሰይ ሀዋዬ እሰይ ሙሉዬ እንኳን ደስ አላችሁ አቤት አንተ አምላክ ምን ይሳንካል እሰየው..እልልልል.....>>
<<አዎ አልሃምዱሊላህ .....የዘንድሮው እንኳን ያስፈራል፣የልጆቻችንን ነገር እንጃ እያልሽ ስትጨነቂ ፤ጌታዬ አያሳፍረኝም፥ያስደስተናል ብዬሽ አልነበረም...ጠይቄው እምቢ አይለኝም ይሰማኛል እንደሱ አትጨነቂ አላልኩሽም ሙሉዬ??>>
<<ብለሻል....ተናግረሻል ሀዋዬ አንቺ እኮ የዋህ ነሽ ይሰማሻል፤ መች ያንቺ ልመና ጠብ ብሎ ያውቃል እሰየው ....>>ብለው አቀፏቸው
*
መርየምም እና ኤልሳ ከእህትማማቾች በላይ ተቀራርበው ያደጉ አብሮአደጎች ናቸው።
ቤተሰቦቻቸው ትዳር መስርተው ይኸን ከተማ ሲቀላቀሉ ጎረቤታሞች ስለሆኑ ከ30አመታት በላይ አንድ ላይ መከራ ና ደስታ፣ማጣትእና ማግኘትን በጋራ አሳልፈዋል፣ከደሳሳ ጎጆ እና ጭር ካለ ሰፈር ወደ ሞቀ ከተማ እና ዘመናዊ መኖርያ ቤት....ከዝቅተኛ ኢኮኖሚ ከፍ ወዳለ የተንደላቀቀ ኑሮ....ከወጣትነት ወደ ሽምግልና....አብረው ተጉዘዋል፣በጭንቅ ጊዜ እርስበረሳቸው እየተመካከሩ፣በመከራ ወቅት ቤታቸውን ዘግተው ለሀዘን እየተቀማመጡ፣በደስታ እና በአለም ደግሞ ወገባቸውን አስረው ከስራው እስከ ፍፃሜው ድረስ ሳይታክቱ ተረዳድተዋል።
ይህ ትስስር ጉርብትና ብቻ አይደለም አብሮ መኖር፣አብሮ መቆየት የፈጠረው ከስጋ ውህደት የበለጠ በመላመድ የመጣ መዛመድ ነው...ይህ ቤተሰብ የሰፈሩ ሁሉ ምሳሌ ነው..... ልጆች ወልደው ያለምንም ልዩነት የኔ የአንቺ ሳይሉ አንድ ላይ የሁለታቸውንም ጡት እያጠቡ አሳድገዋል.....አንደኛው ልጅ ሲታመም ሁለት እናት ሆነው ተጨንቀዋል....አንደኛው ሲያጠፋ የኔ፣የአንቺ ሳይሉ ተቆጥተው ተጋርፈዋል...
.
.
.
.
.
ክፍል ሶስት ይቀጥላል........❤❤
ረቡዕ የካቲት 12/2017..........1:56
ክፍል አንድ
✍️ተምር አህመድ
ፀሀይ አድማሷን አጥብባ ለተተኪዋ ፅልመት ቦታዋን ከለቀቀች ቆየች፣ፅልመትም በሰአቱ ሙሉውን የፀሀይን ቦታ ተቀብሎ ተንሰራፍቷል።
ሰው ሁሉ እንደለመደው ከአሰልቺው የቀንከቀን ትርኪምርኪ ውሎ በሩን ዘግቶ ከቤተሰቦቹ ጋር አረፍ ብሏል......አሁን ከምሽቱ 5:00 ሆኗል.....ነገር ግን ኤልሳ እና መርየም ዛሬ ይህን ለማድረግ አልታደሉም።
ቀን ከወዲያወዲህ ሲሉ የሳለፉትን የድካም ጊዜ በዚህ ምሽት እፎይ ብለው ተኝተው ሊያሳልፉ አልታደሉም.... ሁለቱም ክፍላቸው ውስጥ በጭንቀት ጭብጥ ብለው ተቀምጠው የሞባይል ስልካቸው ላይ አፍጠዋል።
ዛሬ የቁርጥ ቀን ነው.....የ12 አመት የልፋት ውጤት ይፋ የሚሆንበት የጭንቅ ቀን .......ሁለቱም አስር ሰአት ላይ ከትምህርት ሚኒስተር የተላለፈውን መግለጫ ከሰሙ በኋላ እስከአሁን ከቀልባቸው አይደሉም....
ምንም እንኳን በትምህርት ቤታቸው ሰቃይ እና የደረጃ ተማሪ ቢሆኑም በእነሱ ጊዜ የነበረው የአፈታተን ስርአት ከሌላው ጊዜ የተለየ በመሆኑና ከትምህርት ሚኒስቴር የወጣው አስደንጋጭ መግለጫ ደግሞ ከተፈተኑት እጅግ በጣም ትንሽ ቁጥር ያለው ተማሪ እንዳለፈ ስለተነገራቸው በራሳቸው ላይ የነበረውን መተማመን ገደል ከቶባቸው ይኸው በዚህ ምሽት ውጤታቸውን ለማየት በር ዘግተው በጉጉት ተቀምጠው እየተጠባበቁ ነው.....
መርየም በየሰአቱ ኡዱ አድርጋ እየመጣች ሁለት ሁለት ረከአ ሶላት እየሰገደች ጌታዋን ትለምናለች...ኤልሲም የፀሎት መፅሀፏን እያነበበች ከክፍሉ ጎን ላይ ወደ ተሰቀለው ስዕለ አድኖ ዞራ ፀሎቷን ታሰማለች.....
የመርየምም ይሁን የኤልሲ ወላጆች ከመግለጫው ቡኀላ ልጆቻቸው እንደማያልፉ ስላወቁ በቃ ፈጣሪ ያለው ሆናል ብለው ልጆቻቸውን ምንም ነገር ቢፈጠር ምንም እንዳይሰማቸው አሳምነው ጨርሰዋል....
ልጆቹም ወላጆቻቸውን ደስ ለማሰኘት ምንም ቢፈጠር እንደማይጎዱ ቃል ገብተው የፈተናው ውጤት የሚወጣው ማታ መሆኑን ለወላጆቻቸው ሳይናገሩ ወደ ክፍላቸው ገብተዋል......
ልክ ከምሽቱ 7፡00 ላይ መርየም ከስልኳ ላይ ቀና ብላ ኤልሲን አየቻት...
<<እእእ አዲስ ነገር አለ ማሯ?እስካሁን እኔ ሊሰራልኝ አልቻለም እዩልኝ ብዬ ኮድ ቁጥሬን የምልክላቸው ሁሉ እየመለሱልኝ አይደለም......ደግሞ እስከአሁን የትምህርት ቤታችን ከፍተኛ ውጤት 600 ነው አላዛር ነው እንደዛ ያመጣው.....እንደሱ አትዪኝ ሀይሚ እኮ ናት የነገረችኝ.....>>
ስለማንም ውጤት ላለማውራት አስቀድመው ቃል ቢገቡም ኤልሲ ሰምታ ዝም ማለት አላስቻላትም.....
<<ኤልሲ አብሽሪ እኔ ለዛ አይደለም ያየሁሽ ....ተመልከች የኔ ውጤት ወቷል..........>>
ፍፁም በተረጋጋ መንፈስ ስልኳን አቀበለቻት
<<የምርሽን ነው ማሯ?ምንንን......ማሯ በደንብ አይተሽዋል ግን.... ማሯ እኔ አላምንም ዋይይይይ....>>ሳታስበው ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ ስልኩን እየቀማቻት ጮኸች.....
<<ኤልሲ አንቺ ኤልሲ አትጩኺ ሰው ታስደነግጫለሽ ተረጋጊ...ሁሉም ሰው ተኝቷል እኮ...>>
<<ይረበሿ ገና እጮሀለሁ ነይ እቀፊኝ እግዝአብሔር ይመስገን፣አቤት እመቤቴ...ተመስገን ...ተመስገን......>>
<<አልሀምዱሊላህ ኤልሲዬ ቆይ ተረጋጊ...የኔን ውጤት ለላከችልኝ ልጅ ኮድሽን ልኬልሻለሁ የአንቺም አሁን ይመጣል.....እኔ ኡዱ አድርጌ መጣሁ እንቺ ስልኩን ተረጋግተሽ ጠብቂ...እሺ...>>ብላት በሩን ከፍታ ወደ መታጠቢያ ቤት ሔደች
ኤልሳም በፍጥነት ወደ ወላጆቿ ክፍል ሄዳ
<<እማ፣ጋሼ፣በሩን ክፈቱ ውጤት ተለቋል...ተነሱ ...ተነሱ ...ወንድሜ ቢኒ ..ክፈት ውጤት ተለቀቀ...የመሬምን አየነው ...ማሯ አለፈች....>>በደስታ የምታደርገው ስለጠፋት እየተዟዟራች በሩን ትደበድባለች።
<<እልልልልልልልልል......እግዚአብሔር ይመስገን አቤት አቤት አንተ አምላክ አያልቅብክ....አቤት ....እሰይ ተመስገን...እሰይ ...ማሯዬ ...እሰይ...>>
እያሉ የኤልሲ ወላጆች በማደሪያ ልብሳቸው መሬት እሳሙ ወደሳሎን ወጡ።
መርየምም ኤልሳ እስኪነጋ አላስችል ብሏት ወላጆቿን ቀስቅሳ እንደተናገረች ሲገባት ከመታጠቢያ ቤት ወደ ሳሎን ሔዳ ተቀላቀለቻቸው ....
የኤልሳ እናት ወ/ሮ ሙሉ ልክ መርየምን እንዳዩአት ዘለው ተጠመጠሙባት....
<<እሰይ የኔ የልጅ አዋቂ..የኔ አመለ መልካም እሰይ እንኳን ደስ አለሽ!ይገባሻል.......እልልል>>እያሉ አገላብጠው ሳሟት....
አቶ ዘነበም (የኤልሳ አባት)...
<<ጎሽሽሽ የኔ ልጅ በዕውነት ኮርቼያለሁ እኔ መች ጠፋኝ?ሰሚ አላገኘሁም እንጂ አይደለም ሀያ ዘጠኝ ሺ ..ከዛም ያነሰ ተማሪ ቢያልፍ የኔ ልጆች አይወድቁም ስል እኮ ነው የከረምኩት...በዕውነት ኮርቼባችኋለሁ...>> አሉ ቦሮጫቸውን እንደማሸት ብለው ሶፋው ላይ እየተቀመጡ
<<ደግሞ እኮ ጋሼ ማሯ እስከአሁን የትምህርት ቤታችን ሰቃይ ናት ተመልከት 620 እኮ ነው ያመጣችው ....አየኸው??>> ኤልሳ ነበረች ስልኩን ወደ አባቷ አዙራ ደስታዋን ለማጋባት ትጥራለች
በዚህ ጊዜ መርየም አንገቷን አቀርቅራ
<<እረ ቆይ አትቸኩዪ ኤልሲ የሁሉም ሰው ውጤት እኮ ገና አልታወቀም ....ገና ነው ጋሼ >>አለች
<<እህትየው ለመሆኑ አንቺ ስንት አምጥተሽ ነው ቆይ?እንዲህ ምትፈነድቂው?>> የክፍሉን በር ተደግፎ ቆሞ እሰከአሁን ሲያደምጣቸው የነበረው ቢኒያም ነበር...
<<ባክህ የኔ ገና አልወጣም ...ግን ማሯ 620 አመጣች...አይገርምህም?እስካሁን የትምህርት ቤታችን ሰቃይ እሷ ናት....ካላመንከኝ ...ተመልከት>>
በደስታ ከመስከሯ የተነሳ ከመቅፀብት ወደ ወንድሟ ተጠግታ ስልኳን እያሳየችው...
በዚህ ጊዜ የኤልሲ ወላጆች ፊት በድንጋጤ ተሞላ ምንም እንኳን መርየም በማለፏ ቢደሰቱም የልጃቸው ውጤት አለመታወቅ ግን ደስታቸውን አጎደለው... ለቅፅበት ከነበሩበት ደስታ ወጥተው አምላካቸው የልጃቸውን ደስታ እንዲሁ እንዲያቆየው እና እሷም አልፋ ደስታቸው ሙሉ እንዲሆን ፀሎት አደረጉ....ይቺ የጓደኛዋ ደስታ ከራሷ በላይ ያስደሰታት ሚስኪን ነፍስ የማይሆን ውጤት አምጥታ እንዳትሰበርባቸው እጅጉን ሸጉ፤ በእርግጥ የመርየምም ሰጋት ይህ ነበር ኤልሲ ካላለፈች የሷ ማለፍ ብቻውን ለሷ ትርጉም የለውም .....ለዛ ነው ሙሉ ለሙሉ ደስተኛ መሆን ያልቻለችው.......
ቢኒያምም .........
.
.
.
.
.
ክፍል ሁለት ይቀጥላል.....❤❤
ማክሰኞ የካቲት 11/2017.....3:05pm
🌙ቢላል የቁርኣን ማእከል
⭕ምንሰጣቸው አገልግሎቶች ለሁሉም ሲሆን ምንም አይነት የፆታም ሆነ የእድሜ ገደብ የለውም።
አሁን ምዝገባ ላይ ስለሆንን መጥተው መመዝገብ ይችላሉ
📞 09-34-61-64-95
📞 09-35-19-99-67
በቴሌግራም ለማናገር 👇
✉️ @OumerHassen
📍 አድራሻ ፦ መሳለሚያ ቢላል መስጂድ ቢላል ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ያገኙናል።
❤️ አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዐለይህ! ❤️
#ሸጋ_ጁመዓ
@zburafilms
እስላማዊ ቻናል ይፈልጋሉ
ስልኩን
≼
┌───────────┐╯
│⫸╭─━━━━━━╮⫷│╯
│⫸│ ╰─ ━ ─╯ │⫷│╯
│⫸│▅▅▅▅▅▅▅│⫷│╯
│⫸│╰╮ • ★•╭╯ │⫷│╯
│⫸┃┊ 🄷🄷🅆 ┊ ┃⫷│╯
│⫸┃┊ 🄳🄳🅅 ┊ │⫷│╯
│⫸┃┊ 🄷🄳🄴 ┊ ┃⫷│╯
│⫸┃┊ ▓⓪▓ ┊ ┃⫷│╯
│⫸┃╰─◦◇◦╯ ┃⫷│╯
│⫸┃██████ ┃⫷│╯
│⫸│→ ━ ←┃⫷│╯
│⫸╰━━━━━━━╯⫷│╯
╰━━━━━━━━━━━╯╯
👇👇
Reviews channel
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «🎬 Žeburã film production 🎬 #Your Islamic Channal» is a Telegram channel in the category «Отдых и развлечения», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 16.4K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 12.5, with 0 reviews and an average score of 0.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 12.0 ₽, and with 1 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий