

- Main
- Catalog
- Books, Audiobooks & Podcasts
- Advertising on the Telegram channel «❤❤የኪያ ደብዳቤዎች❤❤»
Channel statistics
Full statisticschevron_rightኮንዶም አትወድም።ገና ኮንዶም ስታይ ያንቀጠቅጣታል ይነዝራታል።ሴተኛ አዳሪ ሆና ኮንዶም የምትጠላ እሷን አየሁ።እስካሁን ልጅ አለመውለዷ ደሞ ይደንቀኛል።ፀባይ ሳይቀር ውበቷን ጨምሮ ቁርጥ እናቷን ናት።አናቷም ልክ እንደሷ ቀጭን ፤ረጅም ፤አይኗ ጎላ ብሎ ጥይምናዋ የሚጣራ ፤ከንፈሯ ስስ ፤አንገቷ ረጅም፤ አገጯ ሳይቀር እንደጉንጯ ስርጉድ ያለው ፤ቅንድቧ አንዳች ውበት የሚያበስር መልከቀና ነበረች።አልጋ ማከራየት የእለት እንጀራዋን መቁረሻ ፥አለፍ ሲል ደሞ ደንበኛዋን ስታስደስት ከሳንቲም ወደ ብር ክፍያው ያድጋል።ቀለሟም የእናቷን ሙያ ወርሳለች። ከእናቷ ያልወረሰችው ኮንዶምን ብቻ ነበር።ስለ ኮንዶም ስታስብ መፈጠሯን ትጠላለች።ህይወቷን ትረግማለች ።ከሴትነቷ ባትጣላም ትገላመጣለች። "ኤጭ ይሄ ሴትነት ትላለች" ሴትነቷ ጭኗ እንጀራዋ ነው ።በሌላ በኩል ደሞ ህመሟ ነው....
አልጋ አለ ...አልጋ አልጋ......ና አባቴ አልጋ ነው?(የእናቷ ድምፅ ትንሽ አረፍ ስትል ትዝታዋን እየጎለጎለ ይመጣል
አህህህ......አንተ ሰው ቀስ በል.......ወይኔ እድሌ......አ....አህህህ
ይሄ ድምፅ ሲመጣባት ደሞ እንባ ከአይኗ ይንቆረቆራል።የአልጋው ፂጥ ፂጥ ፤የእናቷ የምጥ ድምፅ ፤የጎረምሳ ቁና ቁና ትንፋሽ ጆሮዋን ያቃጥለዋል።በተለይ ከተደራቢው አልጋ አንዳች ነገር አቁሮ እየተምዘገዘገ መሬቱ ላይ የሚወድቀው ኮንዶም ድምፁ አሁንም ይረብሻታል።ከወንዱ እኩል እናቷን የገደለባት ኮንዶም ይመስላታል
የኔ ልዕልት ተነሳሽ በይ ነይ እንቁላልሽን ብዪ....
ሌላ አምርራ ምትጠላው እንቁላል ነው።እናቷ የወንድ የቀረና ብብት ስር ታፍና ያምትሰራላት እንቁላል አይጥማትም። ልጅ ናት ብላ ታስብ እንጂ የእናቷን ህመም ታቀዋለች።ለሊት ተነስታ ያን ግማታም ኮንዶም ስትለቅም ታስታውሳለች።
ብዪ እንጂ የኔ ቆጆ አይጣፍጥም እንዴ?(የእናት ስቃይ እንዴት ይጣፍጣል?ብላ ብጠይቃት ደስ ባለት።ግን እየመረራትም ቢሆን ትበላለች።አንድ ቀን ከትምህርት መልስ እናቷ ያለወትሮዋ ጋደም ብላ ጠበቀቻት። የሚላስ የሚቀመስ የለም።ሰሞኑን በአል ስለነበር እንቅስቃሴውም ቀንሷል።ቀለሟ የእናቷ እለት እለት መክሳት ካለመብላቷ እንደሆን ብታቅም ሰሞኑን የተማረችው የባዮሎጂ ትምህርት ውስጧን ረብሿታል ኮንዶም ኤች አይ ቪ የሚሉ ቃላትን ስትሰማ የመጀመርያዋ ነበር
እማ ለምን አትታከሚም አለቻት እዛው ተደራቢ አልጋዋ ላይ እንዳለች እየተንጠራራች
አይ አላመመኝምኮ አረፍ ልበል ብዬ ነው ።የሁል ጊዜ ሰበቧ መሆኑን ቀለሟም ታቃለች።እንዳለችው ግን ትንሽ ሲመሽላት ልጇ መተኛቷን ስታስብ ተነስታ አራት ኮቴ ሆና ትመጣለች።አንዱ የሚያሰቃያት ሰው መሆኑ አይጠረጠርም።ልጇ የእናቷን ሰቀቀን ላለመስማት ከብርድ ልብሱ ጋ ብትታገልም እናቷ ትንሽ አቃስታ ዝም ማለቷ ገርሟታል።"አስካሁን ከመጡት ይኼ የተባረከ ነው"አለች በውጧ ።ባታየውም እናቷን ስላላስጮሀት መረቀችው።አልጋው ሲወዛወዝ እናቷም ሳታቃስት ሶስተኛ ኮንዶም ተጥሎ ሊነጋጋ ሲል ግን ሰውየው ቢወጣም እናት ግን ከአልጋዋ አልወረደችም እንቁላል አልሰራችም
እማ አልተነሳሽም እንዴ አለች ቀለሟ አፏ ከልቧ ጋ እየተንቀጠቀጠ።መልሱ ዝም ነው።
እማ አለች ደግማ።እጇ በላብ ረጥቦ ከአልጋዋ እየተነሳች።በድንጋጤ ነክቷት የማያቀውን ኮንዶም መርገጧን አትረሳውም።ከዛች ቅፅበት ወዲህ ግን ትዝ የሚላት እናቷ የተቀበረችበት አቡጀዲ እና ወደ ጉርጓድ በፍጥነት የሚወረወር አፈር ነበር።በቃ እናንዬን ቀብራ ስትመለስ እነዛ ሶስት ኮንዶሞች አሰበቻቸው ያ ደግ ነው ያለችው ሰው የእናቷ እሬሳ ላይ በስሜት ሲጋልብ እንደነበር አሰበች።ገሏት ሂሳቧን ሳይጥልላት መሄዱ አንገበገባት።ምናለ ትንፋሿ ፀጥ ሲልበት ቢተዋት?ትላለች.....
ቤቶች አልጋ አለ???ቀለሟ አልጋ አለ???
ከስቃይ ሀሳቧ ብንን ብላ "አለ "አለች።
ቀለሟ አትኑር እንጂ አሁንም አልጋ አለ!!ኢንስትራክተር በጣም እናዝናለን፤ ፈተናውን ለመፈተን የማያስችል እንከን ገጥሞናል። ምክንያታቸውን አስከተሉ፦
አንድ ሰርግ ላይ ታድመን ነበር፤ እናም ከፕሮግራሙ በኋላ በመመለስ ላይ እያለን በመንገዳችን ላይ መኪናችን ብልሽት ገጠማት። የመኪናችንን ብልሽት ለመጠገን እንደምትመለከተን በአስቀያሚ ሁኔታ ቆሽሸናል።
#ሌክቸረሩም ከምክንያተቸው በመነሳት ተረዳቸውና ወደቤታቸው እንዲመለሱ ለፈተና ዝግጅት 3ት ቀን ሰጣቸውና አሰናበታቸው።
ከ3ት ቀን በኋላ ለተዘጋጀላቸው ፈተና በበቂ ሁኔታ አጥንተውና ተዘጋጅተው መጡ።
ሌክቸረሩ አንድ ውሳኔ ወሰነና እንዲህ አደረገ ...
ሶስቱም ተራርቀው የተለያየ ወንበር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ። ተማሪዎቹም በጣም ተራርቀው ተቀመጡ፤ የፈተና ወረቀትም ተሰጣቸው። ጥያቄዎቹ የሚከተሉት ነበሩ፦
ጥያቄ ቁጥር 1 - ማን ነበር ያገባው ? (25 % ማርክ)
ጥያቄ ቁጥር 2 - የት ነበር የሠርግ ፕሮግራሙ የተካሄደው ? (25 % ማርክ)
ጥያቄ ቁጥር 3 - መኪናዋ የተበላሸችበት ትክክለኛ ቦታ የት ነው ? (25 % ማርክ)
ጥያቄ ቁጥር 4 - የተበላሸችው መኪና ሞዴሏ ምን አይነት ነው ? (25% ማርክ)
ከጥያቄዎቹ መጨረሻም #ማስጠንቀቂያው እንዲህ ይላል - መልሳችሁ የግድ ተመሳሳይ መሆን አለበት !!!
___
Africa 10 ን ላይ - ተወስዶ የተተረጎመ
#Tom1_Tube
ከፈገግታህና ከኔ የቱን ትመርጣለህ አለቺኝ አንቺን አልኳት.. እንዴ ለምን አለቺኝ ምክንያቱም ያለአቺ መሳቅ ስለማልችል አልኳት..
ትግስተኛ ሰው አደለሁም ግን እስካሁን የአንቺን ምላሾች እየተጠበኩ ነው... እመኚኝ አንቺ ለኔ መተኪያ የሌለው ልዩ ሰው ነሽ
፨ ያኔ ግንባሩ ተልቆ ፊቱ ወደ ውስጥ የገባውን ሰው ምን አሉት? ቤት እስከ በረንዳው እንግዲ ግንባሩ በረንዳ ሆኖ ፊቱ ቤት መሆኑ ነው። ተተራርበው የሚኖሩት ነገር ውስጥ ቀልድ እና ተረባ ለጉድ ነው። ሴቷ ሽንሽን ቀሚሷን በባዲ አርጋ ቆዳ ጫማዋን ተጫምታ በብታጋዝ መተኮሻ ፀጉሯን ተተኩሳ አይኗን ድብን ያለ ኩል ተቀብታ የውሀ ቻፒስቲክ ጣል አርጋ ፊት ማፅጃ ተብሎ የተሰራውን ፊር ተቀብታ አልያም ደሞ ፀጉሯን ፈርዛ አንጨብርራ የሄደች እንደሆን አንድ እንስት እንደሷ ሞናኒዛ እዛ ሰፍር የለም።
፨ ለከፋ በሽ ነበር። አንድ ካሜዲያን ሲቀልድ ፀጉሯን አንጨባራ ስትሄድ እናት እናንተ ሰፍር ጭድ ይሸጣል እንዴ ሲላት በፀጉሯ ሙድ እየያዘ ድሮም ለአህያ የሚታየው ምግብ ነው። የሚለውን ቀልድ ስሰማ የእነሱን ዘመን ይገልፅልኛል። በዛው ልክ ከጓደኞቹ ስብስብ ውስጥ አንድ ሙድ የሚያዝበት ግን ደሞ የሚወደድ ልጅ አለ። እነሱ ቦዲ እና ቲሸርታቸውን አርገው ቁምጣቸውን በሲሊፐር አርገው ሲፈነዱ እሱ የአባቱን ኮት እና ሱሪ አርጎ ሹል ጫማውን አርጎ የሚቀላቀላቸው እሱም አይተውም እነሱም አይሰለቻቸውም።
፨ ታዲያ አንድ በስብስባቸው ጊዜ የሚያዝናናቸው ነገር አለ። 10 ከሆኑ አስሩም ተሰብስበው በእየተራ ቀልድ መቀለድ ቀልዱ ካላሳቃቸው የዘጠኑ ኩርኩም ያርፍበታል። ግን አውቀው ላለማሳቅ በጭራሽ አይሞክሩም ለመሳቅ ዝግጁ ናቸው። የሆነ ጊዜ ሰብሰብ ብለው እየተጫወቱ ይህ ሀሳብ መጣላቸው ታዲያ ሁሉም ቀልደው የሚካረኮመው ተካርኩሞ የሚያስቀው አስቆ አንድ ልጅ ቀረ። እንዴት እንደሚያስቃቸው እያሰበ ነበር።
፨ ኑ ብሎ ሁሌም ልጃች በራቸው ላይ ሲጫወቱ የሚያባሩ እርግማናቸውም ሰቅጣጭ የሆኑ ሰውዬ ነበሩ። ታዲያ ይሄ ልጅ ጓደኞቹን ጋሽ ክንዴ በር ላይ ሰብስቦ ክንዴ ክንዴ ክንዴዴዴዴ ብሎ መጣራት ጀመር። ጓደኞቹ ያምሀል ሲሉት ዝም እንዲሉ ነግሯቸው መጣራቱን ቀጠለ። ጋሽ ክንዴ በድንጋጤ ከቤታቸው አቤት ልጄ ብለው ሲወጡ ወኔ ክንዴ ወይኔ ክንዴ ወይኔኔኔ ክንዴ ብሎ ክንዱን ያዘ ጓደኞቹ ከሳቁ እንደሚያስበሉት ቢገባቸውም እየሳቁ አይዞክ ሲሉ ጋሽ ክንዴ ግን እየተራገሙ ወደ ቤታቸው ገብ....
እውነተኛ ታሪክ ተፈርሾ✍️✍️✍️✍️
ስኖር ከሰማውት
ደራሲዋ biz gitar ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ )✍️✍️
@decokoyenelove
የቻናሌ ሊንክ ነው ገባ ገባ በሉ በሞቴ
🖌121
"ይትባረክ እንደ አብረሀም :
ይትባረክ እንደ አብረሀም እህህ ዘለአለም ዘለአለም ......."
...የሰርጉ ሙዚቃ ይደመጣል ።
የሰርጉ ግርግር በቤተሰቡ እና በጎረቤት : ጓደኞች ደምቆ ይታያል።
የሙሽራው ጓደኛም ፣ ሚዜም ነኝ ። ከመሀል ስቦኝ ወደ ጥግ ወሰደኝ እና
"ለሰርጌ ጠራኋት እኮ ...!! " አለኝ
ማንን ??...አልኩት ...
" ህብስትን !! "
.....አለኝ የቀድሞ ፍቅረኛው ናት
ደነገጥኩ እና አፍጥጫ በመገረም ተመለከትኩት
ተረጋግቶ ንግግሩን ቀጠለ ።
ይሄ ላደረገችኝ ሁሉ የበቀል ምላሽ ሳይሆን በመጨረሻ የማ'ደርግላት ምርጥ ነገር ነው ። አየህ ማንም እኔን ጨምሮ መክሯት ተለይታው : ተለይቷት ልትማር አልቻለችም ።
አለኝ ።
አያቴ
" በንፁህ ልብ ባፈቀሩን : በወደዱን ሲቀልድ ለተገኘ ቅጣቱ ግዜ ነው " ትለን ነበረ። አባባሏ ትዝ አለኝ።
በ ግዜ መቀጣት ከባድ ነው። ግ ዜ!
ነገር ግን በቤቷ ውስጥ ለብቻዋን የሚሰማት ስሜት ይገባኛል ።
.........ግን አልዋሽም አሳዝናኛለች !!
121
121😊
መናፈቅ ይሉት ነገር ደጄን ኳንኳ ስንት ዘመናት አለፉ... ስንት በጋ እና ክረምት ተፈራረቁ...ግን እውነት ስልሽ አለደበረኝም... አልከፋኝም ነበር... ለምን ካልሽኝ አለሜ ናፍቆትሽን ገና ድሮ ነበር ያስገባሁት ልክ ባንኳኳበት ቅፅበት እና እልሻለሁ ይህው ደባል ሆኖ እየኖርን ነው... ብታይ እዳይደብረኝ በሀሳብ ሰረገላ አንቺን ይዞልኝ ይመጣ ነበር እውነት እንዴት የተባረከ መሰለሽ... ግን አለሜ አንቺስ እንደኔ ናፍቆት ደጅሽን አላንኳኳም..? ወይስ በርሽን ዘጋሽበት...? ለመሆኑ መኖር እንዴት እያረገሽ ነው..? ደሞ መኖር ካስጨነቀሽ ንገሪኝ ዋጋውን ነው ምሰጠው...
😊ያንቺው አለም
121
Reviews channel
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «❤❤የኪያ ደብዳቤዎች❤❤» is a Telegram channel in the category «Книги, Аудиокниги и Подкасты», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 5.9K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 12.4, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 4.8 ₽, and with 1 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий