
Get clients in any niche!
Delegate the launch of advertising to us — for free
Learn more
13.3

Advertising on the Telegram channel «የ መዝሙር ግጥሞች»
5.0
11
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$24.00$24.00local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
💚ኢትዮጵያ 💛 ሀገራችን❤️
የእምነት የታሪክ የባህል ማህደር
የክርሰቲያን ደሴት ሀገረ እግዚአብሔር
የጽሑፍ የፊደል የስሌቱ ቁጥር
በፀሐይ ምእዋድ በጨረቃ ምህዋር
ልዩ የሆንሽበት በቀን አቆጣጠር
ኢትዮጵያ ሀገራችን በጣም ደስ ይበልሽ
የመለኮት ዙፋን መክበሪያው ስለሆንሽ
የሥልጣኔ ምንጭ የጥቁር ዘር ኩራት
የሚታወጅብሽ ቅዳሴ መላእክት
ለልጆችሽ ብርሃን ለጠላትሽ እሳት
መሆንሽን አይረሳም የቀመሰው ፋሺስት
ለዘመቻ አድዋ የጀግና ጀግንነት
ነበር በሀይማኖት ነበር በአንድነት
ለካሌብ ዘመቻ በሃገረ ናግራን
ምክንያት ነበረ እግዚአብሔርን ማመን
እኛም እንድናመልጥ ከታሪክ ጥየቃ
ሥራችንን ሠርተን ለፍሬ እንድንበቃ
በመካከላችን መለያየት ያብቃ
ታሪክ እንዲደገም እምነት እንዲሰፋ
እኛ ክርስቲያኖች አለን ብሩህ ተስፋ
ኢትዮጵያ ሀገራችን በጣም ደስ ይበልሽ
የመለኮት ዙፋን መክበሪያው ስለሆንሽ
💚 💛 ❤️
ውዷ ሀገራችን የቅዱሳን ገዳም
የሰው ዘር መገኛ የተዋሕዶ ሙዚየም
ሰንደቅ አላማሽን ያላስረክብሽ ለባዕድ
የነጻነት እርካብ ሰማያዊ ሰነድ
💚 💛 ❤️
ኢትዮጵያ ሀገራችን በጣም ደስ ይበልሽ
የመለኮት ዙፋን መክበሪያው ስለሆንሽ
💚 💛 ❤️
በአዲሱ ዘመን በአንድ ልብ ሆነን
በአንድ ማህጸን ውስጥ መለያየት ትተን
ባንዲቱ ባንዲራ ሰንደቅ ባንድ ተጠልለን
እናሳውቅ ለዓለም ፈለግ ውርሳችንን
💚 💛 ❤️
ኢትዮጵያ ሀገራችን በጣም ደስ ይበልሽ
የመለኮት ዙፋን መክበሪያው ስለሆንሽ
💚 💛 ❤️
ከተበተንበት ከስድት ከተማ
ተጎናጽፈን መጣን የናፍቆትን ሸማ
ታጅበን በመዝሙር በያሬድ ውብ ዜማ
ተቀበይን ከደጅ ኢትዮጵያ እማማ
💚 💛 ❤️
ኢትዮጵያ ሀገራችን በጣም ደስ ይበልሽ
የመለኮት ዙፋን መክበሪያው ስለሆንሽ
ሊቀ ጉባዔ ጌታሁን ደምጸ
ዘበዓታ
💚 💛 ❤️
"ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ
እግዚአብሔር ትዘረጋለች።"
መዝ ፷፯፥፴፩
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
21757
20:34
01.03.2025
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
፭፻፺፫ በስ ፸፯ ከካህናት ወገን ማንም ቢሆን በ፵ ጾም በአርብና በረቡዕም ጾም ወይን መጠጣት አይገባውም፡፡ወደ መዋት (ውሽባ ቤት) አይግባ፡፡ ዐቢይ ጾም ወራት ሰው ሚስቱ ጋር አይተኛ፡፡
.
.
.
፭፻፺፮ ክብርት በምትሆን በ፵ ጾም በመጀመሪያው ሱባዔ ፀሐይ እስኪገባ ድረስ ይጹሙ:-
መጀመሪያው ሱባዔ ካለፈ በኋላም እስከ ፲፩ ሰዓት ድረስ ይጹሙ፡፡
በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ ድረስ ይጹሙ፡፡በነዚህም ወራቶች አያጊጡ፡፡
፭፻፺፯ ሴቶችም ጌጣቸውን ይተዉ፡፡ሁሉም ለእያንዳንዱ በ፵ ጾምና በሰሙነ ሕማማት መጠበቅ ይገባዋል፡፡ድኅነታችንና የኃጢአታችን ስርየት በእነርሱ ነውና ይኸውም ሥራ አንዱስ እንኳ በ፵ ጾም ወራት በምንጣፍ ፈጽሞ እንዳይገናኝ ከጋብቻ ሕግ የወጣ ነው፡፡
ክብርት በምትሆን በሕማማት ወራት ይህቺን ኃጢአት የሚሰራት ሰው ወዮለት፡፡
በ፵ ጾም በተድላ በደስታ ፈቃዳችንን ካደረግን ትንሣኤውን ባየን ጊዜ ተድላ ደስታችን ወዴት አለ?
፭፻፺፱ ጾም ከእህል ውሃ መከልከል አደለም ከእግዚአብሔር ፊት የሚደርስ ጾምስ የልብ ንጽሕና ነው፡፡
ሥጋ ቢራብ ቢጠማ ነፍስ ግን ፈቃዷን ብትፈጽም ልብም ከጣዕሙ የተነሣ ደስ ቢለው የጾምህ ጥቅሙ ምንድን ነው?
፭፻፺፱ ሥርዋጽ ክርስጣ ፴ በተባሕትዎ በትሕትና ፵ ቀን ጾምን ይጹሙ፡፡ ከጥሉላት መከልከል ይገባል፡፡ አያግቡም፡፡
💥 💥 💥 💥 💥 💥 💥
(ፍትሀ ነገሥት አንቀጽ ፲፭ ገጽ ፻፶፭)
💥 💥 💥 💥 💥 💥 💥
"ወስብሐት ለእግዚአብሔር "
●🔸 @Behila_Abew 🔸●
●🔸 @Behila_Abew 🔸●
29823
12:20
24.02.2025
የእመቤታችን መከራዋን ማሰብ
✝መስቀል ተሸክሞ ወደሞት ሲሄድ ያየችው ጊዜ✝
በፍጡራን መካከል ካለ ፍቅር በጥልቅ የምትወድ እንደ እናት ማንም የለም። እጅጉን የጠበቀ ነው የሚባለው የባልና ሚስት ፍቅር እንኳ እናት ለልጇ ካላት ፍቅር አይተካከልም ለምን ቢሉ ባል ከሚስቱ የሚፈልገው የሚስት ፍቅር ስላለ ነው የወደዳት ሚስትም ከባሏ የምትሻው ፍቅር ስላለ ነው የወደደችው። እናት ግን የምትወደው ልጇ ስለሆነ ብቻ ነው። ማንም ሰው እናቴ የምትወደኝ ከዚህ ተነስታ (on account of this....) ብሎ መናገር አይችልም።
እናት ደስታዋ ከልጇ በምታገኘው ነገር ሳይሆን ለልጇ በምትሰጠው ነገር ነው። ደስታዋም የልጇ መሆንና አለመሆን ነው። እናት ልጇ ራሷ ለእናትነት ደርሳም ቢሆን ዛሬም እንደታናሽነቷ ታስብላታለች። እናት የምትኖረው ለልጇ ነው። ደስታዋም ልጇ ነው። የልጇ ስብራት የእርሷን ያህል እኩል ይሰማታል። የእናት ምጥ የወለደች ልት ብቻ የሚያበቃ አይደለም። ልጆቿ በተጎዱ ቁጥር ልቧ በኀዘን ሰይፍ ይወጋል። አንድ ደራሲ እናት ስለልጇ የምታዝነውን ኀዘን "All mother feel the suffering of their children as their own. ሁሉም እናቶች የልጆቻቸውን መከራ እንደራሳቸው ይሰማቸዋል" ሲል የገለጸው እርግጥ ነው። በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ አንዲት ሴት ልጇን ጋኔን አሞብባት ነበርና ወደ ጌታ መጥታ እየጮኸች "ልጄን አሞብኛልና እባክህ እርዳኝ" ብላ ነበር የለመነችው። ማቴ15÷22
ልብ በሉ ይህች ሰው ጌታን "እባክህ ልጄን እርዳት" አላለችም ይልቁንም የልጇን ኀዘን እንደራስዋ ቆጥራ ይሰማት ነበርና "እባክህ እርዳኝ" አለችው እንጂ። እናስተውል ይህች ሴት ልጇ ታማለች እንጂ የሚደበድባት የለም፣ እናቷም የማስታመም እድል አላት፣ የሞት ፍርድ አልተፈረደባትም ግን የታመመች ብቻ እናቷ እስክትጮህ ድረስ አለቀሰች እንጂ።
እስኪ የእመቤታችንን ኀዘን እናስብ
ጌታ ከጲላጦስ አደባባይ እስከ ጎልጎታ አስራ አራት ምዕራፎች ያሉት የመስቀል ጉዞ አድርጓል። አራተኛው ከእናቱ ጋር የተያዩበት ቦታ ነው። ወዮ ያቺ ሰአት ምን ያህል አስጨናቂ ናት። እናት ልጇ ሲነግስላት፣ ዘውዱ ሲደፋላት ደስ ይላታል ድንግል ግን አንዱን የድንግልናዋን ፍሬ ራሱን የሚበሱ የእሾህ ጉንጉኖች በራሱ ላይ ደፍቶ አየችው። ከእነዚያ አንዱን እሾህ እንኳን ለልጇ መንቀል አለመቻሏ ለድንግሊቱ እናት ምን ያህል መራራ ነው።
እሾሁን ልትነቅልለት ይቅርና እየወደቀ እየተነሳ ሲገረፍ ሲዳፋ ያደረ በደም የተሸፈነ ፊቱን ለማየትስ እንኳን እድል አላገኘችም። የልጇን ደስታ ለምትሻ እናት የመከራ ፊቱን አቅፋ እንዳታለቅስ እንኳን ስትከለከል እንደምን ያለ የተሳለ የኀዘን ሰይፍ ወግቷት ይሆን። ወየው እመቤቴ አዕላፈ እስራኤል በልጅሽ ላይ እየደነፉ ላንቺ አንድስ እንኳን የሚያረጋጋ አልነበረሽም። ስቃዩ ገርፈው ይለቁታል እንዳይባል ደግሞ እንደዚያ እያደረጉ የሚወስዱት ሊገድሉት መሆኑ ሰይፉ ይበልጡን ልብዋን እንደምን ይወጋው።
የእናት ሀዘን ለታመመች ልጅ የሚያስጨንቅ ከሆነ አጥንቱ እስኪቆጠር ተገርፎ ሊሞት የሚወስደን ልጇን ለምታይ ድንግልማ ምን ያህል የሀዘን ሰይፍ ይሆን? ነብዩ ኤርምያስ የሚያጽናናኝ የነፍሴን የሚያበረታታት ከእኔ ርቋልና ስለዚህ አለቅሳለሁ። አይኔ ውሃ ያፈሳል ፣ ጠላት በርትቷል ፣ ልጄም ጠፍቷል ብሎ እተናገረው ያላጽናኝ እየተገፋፋሽ ባለቀሰሰሽ በድንግል ተፈጸመ። ሰቆ 1÷15 እመቤታችንን የምንወዳት ይህንን የመሰለው መከራዋ ሲረዳን ነው።
አሐቲ ድንግል ገጽ 553 - 554
በአባ ገብረ ኪዳን ግርማ
https://t.me/abagebrekidan
https://t.me/abagebrekidan
27377
06:54
22.02.2025
imageImage preview is unavailable
42049
16:56
11.02.2025
play_circleVideo preview is unavailable
✞ሰላም አላገኝም✞
ሰላም አላገኝም ከእርሱ ተለይቼ
ሁሌ ላመስግነው ከቤቱ ገብቼ
ምሕረቱ ብዙ ነው ጌታ ውለታው
ለእኔ ያደረገው ልዩ ነው ሥራው
ብርሃን ተሰውሮኝ ከቦኝ ጨለማው
በኢያሪኮ መንገድ አየኝ በግርማው
የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ ለመንኩት
ብርሃኔን አበራ እኔም አመንኩት
አዝ= = = = =
በአውሬ መኖሪያ በዋሻ ሲጥሉኝ
አዘዘ አናብስቱን አንዲጠብቁኝ
ተስፋዬን ቀጠለ ደርሶ መዳኛዬ
ከሞት አዳነኝ ቸሩ አረኛዬ
አዝ= = = = =
ሦስት ቀን ያደረው በዓሣ ተውጦ ድኖ ቆሟል ወጥቶ ታሪክ ተለውጦ የነነዌ ሰዎች ዮናስ ሰባኪው ምሕረትን አግኝቶ ከቸር ፈጣሪውአዝ= = = = = ለብዙ ዘመናት በደዌ ተይዤ ስተኛ ነበረ ስቃይ ተሞልቼ አምላኬ ፈቀደ ተነሣሁ ከአልጋ ፈውሶ አቆመኝ ይኸው ያለዋጋ መዝሙር ዲያቆን ሙሉጌታ ማሞ ማር ፲፥፵፮ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮ @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
37647
17:59
10.02.2025
ጾመ ነነዌ በፈለገ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንትምህርት ክፍል አንድ ትምህርት ክፍል ሁለት ትምህርት ክፍል ሦስት ትምህርት ክፍል አራት
የጾመ ነነዌ መዝሙራትነነዌን ሊያቃጥል አወጽአኒ እግዚእየ ለንስሐ ሞት አብቃኝ አድኅነነ እግዚኦ
ትንቢተ ዮናስምዕራፍ አንድ ምዕራፍ ሁለት እና ሦስት ምዕራፍ አራት ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮ @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
37734
11:50
10.02.2025
play_circleVideo preview is unavailable
✞እኔ ግን በምህረትህ ብዛት✞
እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት
እኔ ግን በይቅርታህ ብዛት
ወደ ቤትህ እገባለሁ
አመልክሃለው እዘምርልሃለሁ
በሕይወቴ ዘመን አንዲት ነገር ሻትኩኝ
በቤትህ ተጥዬ መኖሬን መረጥኩኝ
ከኃጢአት ድንኳን የአንተን ደጅ ይሻላል
እረፍቴ ጌታዬ እቅፍህ ይሞቃል(፪)
አዝ= = = = =
የክብርህን ሥፍራ ማደርያ ወደድኩት
መቅደስህ ቀደሰኝ ዙፋኔን ጠላሁት
ከዚህች ለምለም ስፍራ ወዴት እወጣለሁ
የተሰበረ ልብ ይዤልህ እመጣለሁ
አዝ= = = = =
በመከራዬ ቀን የተናገርኩትን
ከደጅህ መጥቼ ከንፈሮቼ ያሉትን
ስዕለቴን ልፈፅም ማልጄ እነሣለሁ
የአምልኮ መስዋዕቴን እሰዋልሃለው(፪)
አዝ= = = = =
እንደ ሰብአ ሰገል ይዤ ወርቅ ዕጣኔን
አምሃ አኮቴት መባዬን ከርቤዬን
ልቤን አየሰዋሁ እሰግድልሃለው
ኦሜጋ አልፋ ነህ እቀኝልሀለው
መዝሙር
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
"እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።"
መዝ፭፥፯
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
44425
17:29
05.02.2025
play_circleVideo preview is unavailable
✞ና ና አማኑኤል✞
ና ና አማኑኤል ና መድኃኒቴ
ጽድቅህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ
የምህረት አባት - - አማኑኤል
የቸርነት ጌታ - - አማኑኤል
ፊትህ የተመላ - - አማኑኤል
ሁሌ በይቅርታ - - አማኑኤል
ካለው ፍቅር በላይ - - አማኑኤል
አባት ለአንድ ልጁ - - አማኑኤል
አምላክ ይወደናል - - አማኑኤል
አይጥለንም ከእጁ- - አማኑኤል
አዝ= = = = =
መድኃኒቴ ልበል - - አማኑኤል
ድኛለው በሞትህ - - አማኑኤል
ቁስሌ ተፈውሷል - - አማኑኤል
በቁስልህ በሞትህ - - አማኑኤል
ስሸጥህ አቀፍከኝ - - አማኑኤል
ስወጋህ አይኔ በራ - - አማኑኤል
በፍቅርህ አወጣኸኝ - - አማኑኤል
ከዚያ ከመከራ - - አማኑኤል
አዝ= = = = =
አንተ ከኔ ጋር ነህ - - አማኑኤል
አዎ ከኔ ጋራ - - አማኑኤል
ድል አርገህልኛል - - አማኑኤል
የጭንቄን ተራራ - - አማኑኤል
በጉባኤ መሃል - - አማኑኤል
አፌ አንተን አወጀ - - አማኑኤል
የከበረ ደምህ - - አማኑኤል
ነፍሴን ስለዋጀ - - አማኑኤል
አዝ= = = = =
የድንግሏ ፍሬ - - አማኑኤል
የብላቴናዋ - - አማኑኤል
የቤቴ ምሰሶ - - አማኑኤል
የነፍሴ ቤዛዋ - - አማኑኤል
መሰረቴ አንተ ነህ - - አማኑኤል
ያሳደገኝ እጅህ - - አማኑኤል
አትተወኝም አንተ - - አማኑኤል
ስለሆንኩኝ ልጅህ - - አማኑኤል
መዝሙር
ሲስተር ሕይወት ተፈሪ
"እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።"
ኢሳ፯፥፲፬
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
33160
03:43
05.02.2025
imageImage preview is unavailable
🛑እነሆ አዲስ ቻናል ይዘንሎት መጣን🛑
በማርያም ይህን ቻናል ሳይቀላቀሉ እንዳያልፉ ይደሰቱበታል መርጠን ለናንተ አቀረብንሎ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲ █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
1668
17:13
16.12.2024
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
1 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
c
**ffeenold@******.io
On the service since June 2022
13.11.202416:38
5
Everything is fine. Thank you!
Show more
New items
Channel statistics
Rating
13.3
Rating reviews
5.0
Сhannel Rating
32
Followers:
140K
APV
lock_outline
ER
--%
Posts per day:
0.0
CPM
lock_outlineSelected
0
channels for:$0.00
Followers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий