
- Main
- Catalog
- News and Media
- Advertising on the Telegram channel «•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•| |ወንጌል ለአለም ሁሉ»
Advertising on the Telegram channel «•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•| |ወንጌል ለአለም ሁሉ»
I will advertise to anyone who wants to advertise on my channel at a discounted price. I have 20k+ subscribers family my price only 2$ for short time discount time 80% so harry up
Channel statistics
በጣም አስገራሚ ትምርት ነው
𝕾𝖎𝖟𝖊
◒◒◒◒◒◒◒
🔼 ይ🀄️ላ🀄️ሉን 🔼
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʀᴇp
ይህ ጥቅስ ስለ ክርስቶስ የምድር አገልግሎት የሚናገር ነው፡፡ ጌታችን በምድር ላይ በነበረበት ዘመን ብዙ ተዓምራትን አድርጓል፣ የምሥራቹንም ለብዙዎች አድርሷል፡፡ ነገር ግን ይህንን ኀላፊነትና ሥልጣን ለደቀ መዛሙርቱ በመስጠት ወደ ሰማይ አርጓል፡፡ “ከእነዚህም የሚበልጥ ያደርጋል” ሲል ሐዋርያት እርሱ በምድር ላይ በነበረበት ዘመን ከነበረው ተደራሽነት በላይ ተደራሽነት እንደሚኖራቸው ለመናገር እንጂ ከእርሱ የበለጠ ተዓምራትን የማድረግ ኃይል ይኖራቸዋል ለማለት አይደለም፡፡ ንግግሩም ብዛትን እንጂ ጥራትን የሚያመልክት አይደለም፡፡ ቀድሞውኑ ተዓምራትን እንዲያደርጉና ወንጌልን እንዲሰብኩ ሥልጣንን የሰጣቸው ራሱ ክርስቶስ ነው (ማቴዎስ 10፡1፣ ማርቆስ 6፡7፣ ሉቃስ 9፡1፣ 10፡19፣)፡፡ ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ በስሙ እንጂ በራሳቸው ስም አይደለም (ማርቆስ 9፡39፣ ማርቆስ 16፡17፣ ሉቃስ 10፡17፣ የሐዋርያት ሥራ 3፡1-8፣ 3:16፣ 16፡16-18)፡፡ ስለዚህ ይህ የኢየሱስ ንግግር ሐዋርያት ከእርሱ እንደሚበልጡ ለማሰብ እንኳ የሚያስደፍር አይደለም፡፡
20. ዮሐንስ 10፡36 ላይ “ታዲያ፤ “የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ” ስላልሁ፣ አብ ለራሱ ለይቶ የቀደሰውንና ወደ ዓለም የላከውን፣ ተሳድበሀል ብላችሁ ለምን ትወነጅሉኛላችሁ?” ይላል፡፡ ኢየሱስም “አምላክ ነው” ከተባለ ፣ እንዴት አምላክ ይቀደሳል? ኢየሱስ ተለይቶ ከመቀደሱ በፊት ምን ነበር? እንዴትስ አምላክ ይባላል?
ጠያቂው የክርስቶስን አምላክነት በግልፅ ከሚናገረው ከዚህ ምዕራፍ ውስጥ አምላክነቱን የሚቃወም ሐሳብ ለመፈለግ መሞከራቸው በእጅጉ አስገራሚ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ጌታችን ኢየሱስ የሚከተሉትን ነጥቦች ግልፅ አድርጓል፡-
የዘለዓለምን ሕይወት ይሰጣል (ቁ. 28)
በጎቹን (ምዕመናንን) ማንም ከእጁ መንጠቅ አይችልም (ቁ. 28)
እነርሱን የሰጠው አባቱ ከነጣቂዎቹ ሁሉ ይበልጣል፤ እርሱና አብ ደግሞ አንድ ናቸው (ቁ. 29 እና 30)
አብ በእርሱ ነው እንዲሁም እርሱ በአብ ነው (ቁ. 38)
እነዚህን ሁሉ ነገሮች ከሰሙ በኋላ አይሁድ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን እየተናገረ እንደሆነ በማሰብ ሊወግሩት መፈለጋቸው አያስገርምም፡- “አይሁድም፦ ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብህ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት” (ቁ. 38)፡፡ እርሱም ንግግራቸውን ከመቃወም ይልቅ ከብሉይ ኪዳን ጥቅስ በመጥቀስ አምላክነቱን ሲያረጋግጥላቸው እናያለን፡- “ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ እኔ፦ አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን? መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፦ ትሳደባለህ ትሉታላችሁን?” (ቁ. 34-36)፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዝሙረ ዳዊት 82 ላይ የተጠቀሱት ሰብዓውያን ባለ ሥልጣናት “አማልክት” የሚል ማዕርግ ከተሰጣቸው አብ ከሌሎች በተለየ ሁኔታ ያከበረውና ወደ ዓለም የላከው አንድያ ልጁ አምላክ ቢባል ምን ያስገርማል? እያለ ነው፡፡ በሌላ አባባል እነዚህ ሰብዓውያን ምፀታዊ በሆነ ሁኔታ “አማልክት” የሚል መጠርያ ቢሰጣቸውም እርሱ ግን የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ በመሆኑ ምክንያትና አብ በእርሱ ውስጥ እርሱም በአብ ውስጥ እንደመኖሩ አምላክ መባሉ ተገቢ መሆኑን እየተናገረ ነው፡፡ ወደ አሕመዲን ጥያቄ ስንመጣ ስህተታቸው የመነጨው “መቀደስ” ማለት “መለየት” ማለት መሆኑን ካለማወቅ ነው፡፡ “ሀጊያዞ” የሚለው የግሪኩ አቻ ቃል በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ተጠቅሷል፡፡ ለምሳሌ ያህል ጌታችን ባስተማረው ጸሎት ውስጥ “ስምህ ይቀደስ” ተብሏል፡፡ በቀጥታ ከተተረጎመ የእግዚአብሔር ስም ቅዱስ ስለሆነ እኛ ልንቀድሰው አንችልም፡፡ “ስምህ ይቀደስ” ስንል የእግዚአብሔርን ስም እንደሌሎች ስሞች እንደማንመለከትና ተገቢውን ክብር እንደምንሰጥ ለመናገር ነው፡፡ 1ጴጥሮስ 3፡15 ላይ “ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት” ይላል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ቅዱስ በመሆኑ እርሱ ይቀድሰናል እንጂ እኛ ልንቀድሰው አንችልም፡፡ ይህ ቃል በልባችን ጌታችን ኢየሱስ ልዩ መሆኑን እውቅና መስጠት እንደሚገባን የተነገረ እንጂ እኛ ለእርሱ ቅድስናን መስጠት እንችላለን ለማለት የታለመ አይደለም፡፡ በተመሳሳይ “አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን” ሲል የሰው ልጆችን ለመዋጀት ተልዕኮ እግዚአብሔር አብ አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደመረጠና ወደ ዓለም እንደላከ ያመለክታል፡፡ ስለዚህ የቃሉን ትርጉም በትክክል ከተረዳን “ኢየሱስ ከመቀደሱ በፊት ምን ነበር?” ብሎ የሚያስጠይቅ ምክንያት የለም፡፡
በዶ/ር ዴቪድ ውድ
(ክፍል 4)
የጠፉ የቁርአን ሀረጎች
ሙሉ ምዕራፎች፥ ረዣዥም የምዕራፍ ክፍሎች እና ጥቅሶችና ከቁርአን ውስጥ ስለጠፉ አጫጭር የቁርአን ሀረጎች መጥፋታቸው አስገራሚ አይሆንም። ለዚህ ሁለት ምሳሌዎችን እንመልከት፦
በመጀመሪያ ሱራ 33:6 እንዲህ ይላል፦ "ነቢዩ በምእምናን ከነፍሶቻቸው ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው.." ነገር ግን ኡባይ ኢብን ካዓብ እና ሌሎች ቀደምት ሙስሊሞች "እርሱም አባታቸው ነው" የሚል ሀረግ እንደጠፋ ያምኑ ነበር። እውቁ የቁርአን ተርጓሚ ዩሱፍ አሊ በማብራሪያው ላይ ይህንን አምኗል። አሊ እንዲህ ይላል፦ "እንደ ኡባይ ኢብን ካዓብ ባሉ በአንዳንድ ቂራዎች (አነባቦች) "እርሱም አባታቸው ነው" የሚሉት ቃላት አሉ። እነዚህ ቃላት "ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው" ከሚሉት ቃላት ጋር ያለውን መንፈሳዊ ግንኙነትና ቁርኝት ያመለክታሉ" [12] ስለዚህ ሙስሊሞች ሀረግ የጎደለው ጎዶሎ ጥቅስ አላቸው ማለት ነው።
ሁለተኛው በዘመናችን ያለውን ቁርአን ስንከፍት ሱራ 2:238 ላይ ሙስሊሞች የሚከተለውን ትዕዛዝ ታዘዋል "በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡ ታዛዦች ኾናችሁም ለአላህ ቁሙ" ነገር ግን እንደ አዒሻ ዘገባ መሐመድ ይህንኑ አንቀጽ ይቀራ የነበረው "በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት በሳላት አል-አስር ላይ ተጠባበቁ፡፡ ታዛዦች ኾናችሁም ለአላህ ቁሙ" ብሎ ነበር [13] ስለዚህ "ሳላት አል-አስር" የሚለው ሀረግ ከዛሬው ቁርአን ውስጥ ጠፍቷል።
ግምገማ
ቁርአን በዘመናት መካከል ወሳኝ በሚባል መልኩ እንደተቀያየረ ግልጽ ነው። ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት ሙሉ ምዕራፎች፥ ረዣዥም የምዕራፍ ክፍሎች ጠፍተዋል፥ ጥቅሶች ተረስተዋል፥ ሀረጎች ጎድለዋል። ዓበይት የመሐመድ ቁርአን ቀሪዎች እንኳን የትኞቹ ምዕራፎች የቁርአን አካል እንደሆኑ አልተግባቡም ነበር።
ይህ ግልጽ ጥያቄዎችን ያስነሳል። በትክክል በተጠበቀ መጽሐፍ እና በትክክል ባልተጠበቀ መጽሐፍ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው? ሙስሊሞች ልክ ከሆኑ ምን ልዩነት የለም! የአንድ በትክክል ያልተጠበቀ መጽሐፍ ማሳያዎች 1) የጠፉ ሀረጎች 2) የጠፉ አንቀጾች 3) የጠፉ የጠፉ ምዕራፎች 4) ዋናው የእናት ቅጂው የቱ እንደሆነ አስመልክቶ አለመግባባቶች ወዘተ ናቸው። ቁርአን እነዚህ ነገሮች ሁሉ ደርሰውበታል።
ስለዚህ ይህ ማስረጃ እያላቸው ነገር ግን አሁንም ቁርአን በትክክል ተጠብቋል ማለት የሚፈልጉ ሙስሊሞች ማለት የሚችሉት ይህንን ነው፦ "አዎ ቁርአን በትክክል ያልተጠበቀ መጽሐፍ የሚኖሩት ማሳያዎች አሉት፥ ነገር ግን በትክክል ተጠብቋል" ይህ ትርጉም ሊሰጥ የሚችል መከራከሪያ ነው?! ስለዚህ "የቁርአን በትክክል መጠበቅ" የሚለው ሙግት የከሸፈ ሙግት ስለሆነ እስልምና እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ የሚፈልጉ ሙስሊሞች ከዚህ ሙግት የተለየ ሌላ ሙግት መፈለግ አለባቸው።
ማጣቀሻዎች
[12] Abdullah Yusuf Ali, The meaning of the Holy Quran, Note 3674
[13] Jami at-Tirmidhi 2982
መሲሁ ኢየሱስ!
በዶ/ር ዴቪድ ውድ
(ክፍል 3)
የጠፉ የቁርአን ምዕራፎች
ቁርአን በትክክል ተጠብቋል የሚለው ሀሳብ ስህተት እንደሆነ እነዚህ እውነታዎች ብቻ በበቂ ሁኔታ ያሳያሉ። ነገር ግን አጠር ባለ መልኩ አንዳንድ ችግሮችን የምንመለከት ይሆናል።
"የሁለተኛው ካልፋ ልጅ የሆነው ኢብን ዑመር ሰዎች ሙሉውን ቁርአን እንደሚያውቁ ሲናገሩ ሲሰማ፥ እንዲህ ብሏቸው ነበር፦ "ማናችሁም "ሙሉውን ቁርአን ተምሬዋለሁ" አትበሉ፥ እንዴት አንድ ሰው ሙሉው ምን እንደሆነ ያውቃል? አብዛኛው ጠፍቶ ሳለ?! ይልቁኑ "የተረፈውን ተምሬያለሁ" ይበል" [8]
ከመሐመድ ተከታዮች አንዱ የነበረው አቡ ሙሳ ከዚህ ሀሳብ ጋር ይስማማል። የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች በስንፍናቸው የተነሳ ሁለት ሱራዎችን እንደረሱ ተናግሯል፦
አቡ ሙሳ አል-አሽዓሪ ወደ ባስራ የቁርአን ቀሪዎች መልእክት ላከ። ቁጥራቸው ሶስት መቶ (300) ሲሆን ወደ እርሱ መጡ፥ ቁርአንንም ቀሩ። ከዚያም እንዲህ አላቸው "ከባስራ ነዋሪዎች እናንተ የላቃችሁ ናችሁ፥ ከእነርሱ መካከል የቁርአን ቀሪዎች እናንተ ናችሁና። ስለዚህ መቅራቱን ቀጥሉ። ነገር ግን እንዳትረሱ! ለረዥም ጊዜ ቁርአንን መቅራታችሁ ከእናንተ በፊት እንደነበሩት ቀሪዎች ልብ የእናንተም ልብ እንዳያደነድን። እኛ ከሱራ ባራዓት (የሱራ 9 ሌላ ስም) ጋር በርዝመቱ እኩል የሆነ ሱራ እንቀራ ነበር። ነገር ግን "ለሰው ልጅ በሀብት የተሞሉ ሁለት ሸለቆች ቢኖሩ፥ ሶስተኛ ሸለቆን ይመኛል፥ ከአቧራ በቀር የሰውን ልጅ ሆድ የሚሞላ ምንም ነገር የለም" ከሚለው አንቀጽ በቀር እንዳለ ረስቼዋለሁ። ደግሞም ከሙሳቢሃት ሱራዎች ጋር የሚመሳሰል ሱራንም እንቀራ ነበር፥ ነገር ግን ረስቼዋለሁ" [9] (ሙሳቢሃት ሱራዎች አላህን በማሞገስ የሚጀምሩ ሱራዎች ሲሆኑ ሱራ 57፥ 59፥ 61፥ 62፥ 64፥ 87 ናቸው)
ይህ ሙሉ የቁርአን ምዕራፎች እንደተረሱና እንደጠፉ ያሳያል
የጠፉ የቁርአን አንቀጾች
ከዚህ በተጨማሪም ከአንዳንድ የቁርአን ምዕራፎች ረዣዥም ክፍሎች እናውቃለን። ለምሳሌ የመሐመድ ሚስት አዒሻ በአማካይ የሱራ 33 ሁለት ሶስተኛው (2/3) እንደጠፋ ተናግራለች፦
"አዒሻ አለች፦ ሱረቱል አሕዛብ (ሱራ 33) በነብዩ ጊዜ ሲቀራ ሁለት መቶ (200) አንጾች ነበሩት። ነገር ግን ኡትማን የእርሱን ቅጂ ሲያሰባስብ አሁን ካሉት 73 አንቀጾች በቀር ሌሎቹን ማግኘት አልቻለም" [10]
እንደ አዒሻ ምስክርነት የቁርአን ሰብሳቢዎቹ ሙሉን ሱረቱል አሕዛብ (ሱራ 33) ማግኘት አልቻሉም። ለምን? በፊት ለማየት እንደሞከርነው፥ ብዙ ሀፊዞች በየማማ ጦርነት ተገድለው ነበር። ስለዚህ ሙሉውን ምዕራፍ የሚያውቅ ሰው ከጦርነቱ አልተረፈም ነበር ማለት ነው።
የጠፉ የቁርአን ጥቅሶች
ከዚህም ባሻገር አዒሻ የጠፉ የቁርአን ጥቅሶች እንደጠፉ ተናግራለች። የጠፉበት መንገድም ፈገግ ያደርጋል፦
"አዒሻ የተናገረችው እንዲህ ተዘግቧል፦ "የውግራትና አዋቂን አስር ጊዜ ጡት የማጥባት ጥቅስ ወርዶ ነበር፥ ወረቀቱም ከእኔ ጋር ከትራሴ ስር ነበር። የአላህ መልእክተኛ ሲሞት በሞቱ ምክንያት ተዋክበን ነበር። ያኔም አንዲት ለማዳ በግ መጣችና በላችው" [11]
በአሁኑ ቁርአን ውስጥ የውግራትና አዋቂን አስር ጊዜ ጡት የማጥባት ጥቅስ የለም። ለምን? የአዒሻ በግ በልታዋለች
ማጣቀሻዎች
[8] Abu Ubaid, Kitab Fada'il-al-Quran
[9] Sahih Muslim 2286
[10] Abu Ubaid, Kitab Fada'il-al-Qur'an
[11] Sunan Ibn Majah 1944
ይቀጥላል
በዶ/ር ዴቪድ ውድ
(ክፍል 2)
በመሐመድ ምሁራን መካከል የተፈጠረው አለመግባባት
ነገር ግን ሁሉም ሙስሊሞች በአዲሱ ቁርአን አልተስማሙም ነበር። አንዳንድ ዓበይት የመሐመድ ቁርአን ቀሪዎች የዛይድን ቅጂ አልተቀበሉትም ነበር።
በአንድ ወቅት መሐመድ ተከታዮቹን እንዲህ ብሏቸው ነበር "የቁርአንን አቀራር ከአራት ሰዎች ተማሩ፤ ከአብደላህ ኢብን መስኡድ፥ ነጻ የወጣው የአቡ ሁዴይፋ ባሪያ ሳሊም፥ ሙዓድ ኢቢን ጀባል እና ኡባይ ኢብን ካዓብ" [4] ነገር ግን በሚያስገርም ሁኔታ መጀመሪያ መሐመድ ቁርአንን ከእርሱ ተማሩ ያለው ኢብን መስኡድ ቁርአን መቶ አስራ አንድ (111) ምዕራፎች ብቻ እንዳሉት ገልጾ ነበር። አሁን ያለው ቁርአን ግን መቶ አስራ አራት (114) ምዕራፎች ብቻ ነው ያሉት። በእርሱ ገለፃ መሰረት በአሁኑ ቁርአን ውስጥ ያሉት ምዕራፍ 1፥ 113 እና 114 የቁርአን አካል አይደሉም።
በእዚህ እና በሌሎች በመቶ የሚቆጠሩ ልዩነቶች ምክንያት ኢብን መስኡድ የመጨረሻውን የቁርአን እትም ማታለያ (deception) ብሎት ነበር! "ሰዎቹ በቁርአን አቀራር ዙሪያ ማታለልን ፈጽመዋል። እኔ ከዛይድ ይልቅ በምወደው በእርሱ (በመሐመድ) አቀራር ብቀራው ይሻለኛል" ነበር ያለው። [5]
ሙስሊሞች ይህን ማታለል መቀበል ነበረባቸው? በማያስገርም ሁኔታ፥ ኢብን መስኡድ ሙስሊሞች የዛይድን ቅጂ እንዳይቀበሉና በፊት የነበሯቸውን ቅጂዎች እንዲጠብቁና በሰአቱ በነበረው የኡትማን መንግሥት እንዳይወሰዱ እንዲደብቋቸው ሁሉ ይመክራቸው ነበር። እንዲህ አለ፦ "እናንተ ሕዝበ ሙስሊም ሆይ! የዚህን ሰው መጽሐፍና አቀራር ከመኮረጅ ታቀቡ። በአላህ! እኔ እስልምናን ስቀበል እርሱ (ዛይድ) ገና በማያምን ሰው ወገብ ውስጥ ነበር (አልተወለደም ነበር)" ይህንንም አስመልክቶ ነበር አብደላህ ኢብን መስኡድ "የኢራቅ ሕዝብ ሆይ! ከእናንተ ጋር ያሉትን የቁርአን ቅጆች ያዟቸው፥ ደብቋቸውም" ያለው [6]
ነገር ግን ከመሐመድ ዓበይት የቁርአን ቀሪዎች መካከል በዛይድ ኢብድ ታቢት የቁርአን ቅጂ ያልተስማማው አብደላህ ኢብን መስኡድ ብቻ አይደለም። ኡባይ ኢብን ካዓብ አለ የሚባለው የመሐመድ የቁርአን ቀሪ ሲሆን፥ መሐመድ በሕይወት በነበረበት ሰአት ቁርአንን ካሰባሰቡት ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ ነበር። ነገር ግን ኡባይ ኢብን ካዓብ የዛይድ ቁርአን ሁለት ምዕራፎች እንደሚጎድሉት ያምን ነበር! (የዛይድ ቁርአን አሁን ያለው ቁርአን ስለሆነ፥ እንደ ኡባይ ኢብን ካዓብ እምነት አሁን ያለው ቁርአን ሁለት ምዕራፎች ይጎድሉታል)
በዚህም ምክንያት ሙስሊሞች አንዳንድ የኡባይ ኢብን ካዓብን አነባቦች ላለመቀበል ተገድደው ነበር። ዑመር እንዲህ አለ፦ "ኡባይ ከእኛ መካከል በቁርአን አቀራር አንደኛ ነበር፥ ነገር ግን እርሱ አንዳንድ እርሱ የሚቀራውን እንተወዋለን" ኡባይ ግን እንዲህ ብሏል "ይህን ከአላህ መልእክተኛ አፍ የወሰድኩት ነው፥ በምንም ሁኔታ አልተወውም" [7]
መሐመድ በመረጣቸው የቁርአን ቀሪዎች አለመግባባት የተነሳ ሙስሊሞች አጣብቂኝ ውስጥ ናቸው። ዛሬ ላይ ያለው ቁርአን በትክክል ተጠብቋል የሚሉ ከሆነ መሐመድ እነዚህን የቁርአን ቀሪዎች ሲመርጥ ተሳስቷል ወይም ዋሽቷል ሊባል ነው። የመረጣቸው የቁርአን ቀሪዎች አሁን ካለው ቁርአን ጋር አይስማሙምና። በተቃራኒው ደግሞ መሐመድ እነዚህን የቁርአን ቀሪዎች ሲመርጥ አልተሳሳተም ወይም አልዋሸም ካሉ፥ አሁን ላይ ያለው ቁርአን እንዳልተጠበቀ ማመን አለባቸው። አሁን ላይ ያለው ቁርአን በመሐመድ የተመረጡት የቁርአን ቀሪዎች ከነበራቸው ቁርአን ጋር ይለያያልና።
ማጣቀሻዎች
[4] Sahih Al Bukhari 3808
[5] Ibn Sa'd, Kitab al Tabaqat al-kabbir, Vol.2, p.444
[6] Jami At-Tirmidhi 3104
[7] Sahih Al Bukhari 5005
ይቀጥላል
በዶ/ር ዴቪድ ውድ
መግቢያ (ክፍል 1)
ሙስሊሞች እስልምና እውነት መሆኑን እናረጋግጣለን በሚል ከሚጠቀሟቸው ታዋቂ ሙግቶቻቸው አንዱ "የቁርአን በትክክል መጠበቅ" የሚለው ሙግታቸው ነው። በዚህ ሙግት መሰረት ቁርአን ለአስራ አራት ምዕተ ዓመታት በትክክል ስለተጠበቀ አምላክ ተአምራዊ በሆነ መንገድ ሲጠብቀው ነበር። ይህ ሙግት በሚከተለው የቁርአን አንቀጽ ላይ የተመሰረተ ነው፦
إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا ٱلذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡ (ሱራ 15: 9)
ይህን አንቀጽ ከጠቀሰ በኋላ፥ የእስልምና ዓቃቤ እምነት ማዝሃር ካዚ የሚከተለውን ይላል፦
"ሙስሊሞችም ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችም እንደሚስማሙት በቁርአን ጽሑፍ (The Text of The Quran) ውስጥ አንድም ለውጥ አልተካሄደም። ከላይ ያለው ትንቢት (ሱራ 15:9) እውነት የሆነው ለቁርአን ጽሑፍ ዘላለማዊ ጥበቃና እንከን አልባነት ብቻ ሳይሆን፥ እንደ ሥርዓተ ነጥብ (punctuation) ባሉት አነስተኛና ዝርዝር ጉዳዮችም ነው። ባለፉት አስራ አራት ምዕተ ዓመታት አንድም የቁርአን ቃል፥ ፊደል፥ ሥርዓተ ነጥብና አናባቢ ነቁጥ (diacritical mark) አለመለወጡ የቁርአን ተአምር ነው" [1]
ነገር ግን ይህ መከራከሪያ በሁለት ምክንያቶች የተነሳ ፈጽሞ አያስኬድም። በመጀመሪያ አንድ መጽሐፍ ለአስራ አራት ምዕተ ዓመታት መጠበቁ ተአምር አይደለም። የሙት ባህር ጥቅሎች፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎችና ሌሎች ጽሑፎችም ከ1,400 ዓመታት በላይ ተጠብቀው ቆይተዋል። ስለዚህ ጥበቃ ቁርአን መለኮታዊ ጥንሳሴ (divine inspiration) እንዳለው ማሳያ ሊሆን አይችልም። ሲቀጥል ቁርአን በትክክል ተጠብቋል የሚለው ሀሳብ ሀሰት ነው! ጥንታዊ የሚባሉ የእስልምና ምንጮችን ስንመለከት ሙሉ የቁርአን ምዕራፎች፥ ከቁርአን ምዕራፎች ረዣዥም ክፍሎች እንደጠፉ፥ ጥቅሶች እንደተረሱ፥ ቃላትና ሀረጋት እንደተቀየሩ እናረጋግጣለን። በተጨማሪም የመሐመድ ተዓማኒ የቁርአን ቀሪዎች የትኞቹ ምዕራፎች በቁርአን ውስጥ መካተት እንዳለባቸው መስማማት እንዳልቻሉ ከተአማኒ እስላማዊ ዘገባዎች እንረዳለን።
የቁርአን አሰባሰብ ታሪክ በአጭሩ [2]
ሙስሊሞች የመጀመሪያው የቁርአን መገለጥ ወደ መሐመድ የመጣው በ610 ዓ/ም ነው ብለው ያምናሉ። ከዚያም በቀጣዮቹ ሀያ ዓመታት ውስጥ መሐመድ ተጨማሪ የቁርአን አንቀጾችን ለጸሐፊዎቹና ለተከታዮቹ እንዲሸመደዱና እንዲጻፉ አስተላልፎ ነበር። እነዚህ የቁርአን አንቀጾች የተጻፉት በዘንባባ ቅጠሎች፥ በአጥንቶች፥ በሞቱ እንስሳት፥ በጠፍጣፋ ድንጋዮች እና ሙስሊሞቹ ባገኙት ነገር ሁሉ ነበር። እናም በዚህ ጊዜ የተሟላ የቁርአን ዕደ-ክታብ አልነበረም
መሐመድ ከሞተ በኋላ የቁርአን መገለጥ እንደቆመ በሙስሊሞች ዘንድ ይታመናል። መሐመድ ከሞተ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ካሊፋ አቡ በከር አንድ የተቀሰቀሰን ተቃውሞ ለማስቆም ብዙ ሀፊዞችን (ቁርአንን የሸመደዱ ሰዎችን) በየማማ ጦርነት እንዲዋጉ ልኮ ነበር። በጦርነቱ ግን አብዛኞቹ ሀፊዞች ሞቱ። ከዚያም እስላማዊ ምንጮች እንደሚናገሩት አንዳንድ የቁርአን ክፍሎች ጠፉ። አብዛኞቹ የቁርአን አንቀጾች ይታወቁ የነበሩት በየማማ ጦርነት ወቅት በሞቱት ሀፊዞች ሲሆን ከጦርነቱ በተረፉት ሰዎች አይታወቁም ነበር። አልተጻፉምም ነበር። በሰአቱም አቡበከር፥ ኡመርና ኡትማን ቁርአንን ሰብስበው አልነበረም። ከጦርነቱ በሕይወት ከተረፉት ሰዎች ዘንድ ከአንዱም አልተገኙም ነበር።
ከዚያም አቡበከር ተጨማሪ የቁርአን አንቀጾች እንዳይጠፉ ቁርአን መሰብሰብ እንዳለበት ወሰነ። ይህንንም ስራ ለዛይድ ኢብን ታቢትን ሰጠው። ዛይድ ኢብን ታቢት በ634 ዓ/ም የራሱን ቅጂ ካጠናቀቀ በኋላ ይህ የዛይድ ቅጂ በአቡበከር ዘንድ ነበር። አቡበከር ከሞተ በኋላም ለቀጣዩ ካሊፋ ለካሊፋ ዑመር ተላለፈ። ዑመር ከሞተ በኋላ ደግሞ የመሐመድ ሚስት ለነበረችው ለሀፍሳ ተሰጠ።
መሐመድ ከሞተ ከ19 ዓመታት በኋላ በካሊፋ ኡትማን ዘመን በትክክለኛው የቁርአን አቀራር ዙሪያ አለመግባባቶች ተነሱ። ከዚያም ኡትማን የሀፍሳ ቅጂና ሌሎች የታወቁ የቁርአን ዕደ-ክታባት ተሰባስበው ይፋዊ የሆነ የቁርአን እትም እንዲዘጋጅ አዘዘ። ዛይድ ኢብን ታቢት፥ አብደላህ ቢን አዝ-ዙቤይር፥ ሳዓድ ቢን አል-አስ እና አብዱር ራሕማን ቢን ሃሪስ በታታሪነት የተከለሰ የቁርአን እትም አዘጋጁ። ባለቀ ጊዜም ኡትማን ለእያንዳንዱ ሙስሊም ግዛት እነርሱ ያዘጋጁትን እትም አንድ አንድ ቅጂ ላከ። ከዚያም እርሱ ከላከው ውጪ ያሉትን ሌሎች የቁርአን ዕደ-ክታባትን (በከፊልም ይሁኑ በሙሉ) እንዲቃጠሉ አዘዘ [3] አሁን ያለው ቁርአን ከዚያ እትም የመጣ ነው።
ማጣቀሻዎች
[1] Mazhar Kazi, 130 Evident Miracles in the Quran (Richmond Hill: Crescent Publishing House, 1997), pp. 42-43
[2] Ibn Abi Dawud, Kitab al-Masahif
[3] Sahih Al-Bukhari 4987
ይቀጥላል
👳♂️ ❔ 19. በዮሐንስ 14፡12 ላይ ኢየሱስ“እውነት እላችኋለሁ በኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ ይሰራ፤ እንዲያውም እኔ ወደ አብ ስለምሄድ፤ ከእነዚህም የሚበልጥ ያደርጋል” ብሏል፡፡ እንግዲህ ክርስቲያኖች “ኢየሱስን አምላክ ነው” እንደሚሉት ካሰብን በኢየሱስ የሚያም ሰው ከአምላክ በላይ ሥራን መስራት ሊችል ነው ማለት ነው፡፡ ታድያ ከአምላክ መብለጥ ተቻለ ማለት አይደል? ከአምላክ እንኳን ሊበልጥ ይቅርና ሊነፃፀር የሚችል ስራ ማን መስራት ይችላል?
👳♂️ ❔ 20. ዮሐንስ 10፡36 ላይ “ታዲያ፤ “የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ” ስላልሁ፣ አብ ለራሱ ለይቶ የቀደሰውንና ወደ ዓለም የላከውን፣ ተሳድበሀል ብላችሁ ለምን ትወነጅሉኛላችሁ?” ይላል፡፡ ኢየሱስም “አምላክ ነው” ከተባለ ፣ እንዴት አምላክ ይቀደሳል? ኢየሱስ ተለይቶ ከመቀደሱ በፊት ምን ነበር? እንዴትስ አምላክ ይባላል?
በጎቹን (ምዕመናንን) ማንም ከእጁ መንጠቅ አይችልም (ቁ. 28)
አብ በእርሱ ነው እንዲሁም እርሱ በአብ ነው (ቁ. 38)
✞●▬▬๑۩✞ ◒ ✞۩๑▬▬●✞
━⊱✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━
━⊱✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━
━⊱
✞●▬▬๑۩✞ ✞۩๑▬▬●✞
◒◒◒◒◒◒◒
◒◒◒◒
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʀᴇ
👳♂️ ❔ . መጽሐፍ ቅዱስ (የ1980 እትም) በዕብራዊያን 5፡7-8 ላይ ስለ ኢየሱስ እንዲህ ተገልጿል፡- “እርሱም በሥጋው ወራት ከሞት ያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤እግዚአብሔርንም ስለመፍራቱ ተሰማለት፤ ምንም ልጅ ቢሆን ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ” ይላል፡፡ ክርስቲያኖች እንደሚሉት ኢየሱስ “አምላክ” ከሆነ አምላክ እንዴት ከልምድ ይማራል? ጥቅሱ ይቀጥልና “እግዚአቢሔርንም ስለመፍራቱ ተሰማለት” ሲል ይገልጻል፡፡ ኢየሱስ እግዚአብሔር ከሆነ እግዚአብሔር ራሱን ይፈራልን? ኢየሱስ አምላክን እንደሚፈራ በዚህ ጥቅስ ተገልጿል፡፡ ታዲያ “ኢየሱስ አምላክ ነው” ከተባለ እንዲሁም “አምላክ አንድ ነው” ካልን ኢየሱስን የፈራው እራሱን ነው ማለት አይሆንምን? እንዴትስ አምላክ ራሱን ይፈራል? ወይስ ከሦስት አማልክ ውስጥ አንዱ ሌላኛውን ይፈራል?
👳♂️ ❔ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ በሚከተሉት ጥቅሶች ላይ “ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው” አምላክ መሆኑ ተገልጿል፡፡ እነርሱም ፡- ሮሜ 10፡9፣ ገላቲያ1፡1፣ ኤፌሶን 1፡20-21፣ ቆላስይስ 2፡11-12፣ 1ኛ ጴጥሮስ 1፡21፣ የሐዋርያት ሥራ 2፡23-24፣ 3፡15፣ 10፡40፣ 13፡33-34፣ 3፡26፣ 4፡10፣ 13፡37፣ 6፡14 ናቸው፡፡ በቀረበው ማስረጃ “ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው” አምላክ ከሆነ ታድያ እንዴት “ኢየሱስ ሞትን ድል አደረገ “ይባላል? እንዴትስ “በሞት ላይ ስልጣን ስላለው ተነሳ” ልንል እንችላለን?
◒◒◒◒◒◒◒
ʲᵒᶦⁿ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʀᴇp
Reviews channel
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•| |ወንጌል ለአለም ሁሉ» is a Telegram channel in the category «Новости и СМИ», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 14.3K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 12.5, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 3.6 ₽, and with 1 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий