
Monetize Telegram Mini App with Telega.io
Connect your app, set CPM, and watch your revenue grow!
Start monetizing
18.5

Advertising on the Telegram channel «TIKVAH-ETH»
5.0
16
Not everyone has the time to look up to news channels on TV every night to stay updated about the news. you are in the right place to get breaking news.
stay updated.
Share
Add to favorite
Channel temporarily not accepting requests
Choose another channel from recommendations or get a tailored list within your budget using AI
AI Channel Picker
Recent Channel Posts
BREAKING
ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ የተለያዩ የምስጋና ስጦታዎችን አበረከተ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017
ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት ጥሩ አፈጻጸም በማስመዝገቡ ከዛሬ ሌሊት 6 ሰዓት ጀምሮ የምስጋና ስጦታዎችን ለደንበኞቹ አበርክቷል።
በዚህ መሰረትም ለ3 ቀናት የሚያገለግል 1 ጂቢ የኢንተርኔት፣ በየቀኑ የ5 ደቂቃ የድምጽ እና በየቀኑ 8 የአጭር የጽሑፍ መልዕክት ስጦታን ለደንበኞቹ አበርክቷል፡፡
እንዲሁም የ10 ደቂቃ ዓለም አቀፍ ጥሪ የምስጋና ስጦታን ለደንበኞቹ ማበርከቱ ነው የተመላከተው፡፡
ስጦታዎቹን ከዛሬ ሌሊት 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 12 ሰዓት ድረስ መጠቀም እንደሚቻል ተጠቁሟል፡፡
@Tikfahethiopia
1581
19:50
24.07.2025
imageImage preview is unavailable
🙏ስለአብሮነትዎ ምስጋና!!
🎊 የ2017 በጀት ዓመት እና የሶስት ዓመት መሪ የዕድገት ስትራቴጂያችንን በስኬት ማጠናቀቃችንን በማስመልከት ካበረከትንልዎ የ1 ጊ.ባ ዳታ፣ የ15 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ እና የ25 የጽሑፍ መልዕክት ስጦታዎች በተጨማሪ የቴሌብር ሱፐርአፕ ተጠቃሚ በመሆንዎ ተጨማሪ የ1 ጊባ ዳታ ስጦታ አበርክተናል!
🎁 ስጦታውን እስከ ሐምሌ 20/2017 ዓ.ም ድረስ ከሌሊት 6:00 እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት መጠቀም ይችላሉ።
ስለአብሮነታችሁ ከልብ እናመሰግናለን!
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
1745
09:02
25.07.2025
imageImage preview is unavailable
“በማህበራዊ ሚዲያ ሀገሪቱን የብጥብጥና የሁከት ማዕከል ለማድረግ በሚሰሩ ሰዎች ላይ ኦፕሬሸን ይካሄዳል” - ፌደራል ፖሊስ
የፌደራል ፖሊስ በውጭና በሀገር ውስጥ ሆነው በማህበራዊ ሚዲያ ሀገሪቱን የብጥብጥና የሁከት ማዕከል ለማድረግ የሚዲያ ዘመቻ በሚያካሄዱት ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ የተጠናከረ ኦፕሬሸን ይካሄዳል ሲል አስታወቀ።
ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር ሙከራ የሚያደርጉ ግለሰቦች እና ቡድኖችን ለሕግ የማቅረብ ሥራን አጠናክሬ እቀጥላለሁም ብሏል።
“በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያ እንዲሁም በሁሉም መግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ አሰሳና ፍተሻ እንደሚካሄድ ገልጿል፤ ዋነኛ ትኩረቴ “በፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ” ነው ሲል አስታውቋል።
ፌደራል ፖሊስ ይህንን ያስታወቀው በቀጣይ ሦስት ወራት (ከሐምሌ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም) በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ሁነቶች ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ በተዘጋጀ የፀጥታ ዕቅድ ላይ በተደረገ ውይይት መሆኑን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩትም ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከሪፐብሊካን ጋርድ፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተውጣጡ ስትራቴጂክና ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸውን ጠቁሟል።
@Tikfahethiopia
1910
11:44
25.07.2025
imageImage preview is unavailable
420,000 ብር የተበላው ወጣት
ይህ ወጣት የጉዞ ፕሮሰስ ለሚያደርግ ድርጅት 420ሺህ ብር ከፍሎ ቪዛ ተመቶልሃል ቲኬቱም ይኸው ብለው ይሰጡታል ተቀብሎ ቤተሰብ ተሰብስቦ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ሸኝተው ይመለሳሉ። እሱም ሰርቼ ቤተሰብ እለውጣለሁ ብሎ ወደ ተርሚናል ሲገባ ቪዛው የሃሰት ፌክ ቪዛ ነው መግባት አይቻልም ብለው መልሰውታል።
@Tikfahethiopia
1591
20:58
26.07.2025
imageImage preview is unavailable
በአለም ከመጠን በላይ የወፈሩ ሰዎች ብዛት አንድ ቢልየን አልፏል ተባለ
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው ሰዎች ቁጥር ከአንድ ቢሊዮን በላይ መድረሱን ዘ ላንሴት በተባለ ሳይንሳዊ መጽሔት ላይ የወጣ አንድ ጥናት አመለከተ።
ትንታኔው በፈረንጆቹ 1990 እስከ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ190 በሚበልጡ አገሮች የተገኘውን መረጃ ያካተተ ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ከመጠን ያለፈ ውፍረት በልጆችና በአዋቂዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።
ይህም በሴት ልጆች ከ1.7% ወደ 6.9% እንዲሁም በወንድ ልጆች ከ2.1% ወደ 9.3% ከፍ ብሏል።
እ.ኤ.አ. በ2022 ወደ 160 ሚሊዮን የሚጠጉ ታዳጊዎች ከመጠን በላይ ውፍረው ነበረ።
በአዋቂዎችም ዘንድ ችግሩ ተባብሷል። ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው ሴቶች መጠን ከ 8.8% ወደ 18.5% ሲጨምር፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው ወንዶች መጠን ደግሞ ከ 4.8% ወደ 14% ከፍ ብሏል።
@Tikfahethiopia
1306
09:46
28.07.2025
imageImage preview is unavailable
አልጋ በሚያከራዩ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የከተማውን ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግና አጠራጣሪ ጉዳዮች ባጋጠሙበት ወቅት ጭምር ድንገተኛ ፍተሻና አሰሳ ያደርጋል።
ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ ሰባት ልዩ ቦታው 32 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ አልጋ ቤቶች ላይ በተደረገ ፍተሻ አራት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ከ298 ጥይቶች ጋር መያዙን ፖሊስ ገልጿል፡፡
ፖሊስ ምን ጊዜም ህብረተሰቡን የፀጥታ ስራው አጋር በማድረግ የከተማውን ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ ሽፍት በማጠፍ ጭምር የወንጀል መከላከል ተግባራቱን እያከናወነ ሲሆን የተገኘው ውጤትም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን አስታውቋል፡፡
በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳታፊ የነበሩት ፍቃዱ ማናየ፣ አዳነች ጎበዜ፣ ዮሀንስ ፍቃዱ እና ዮናስ በቀለ ላይ ተገቢው ምርመራ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን በማሰባሰብ በህግ አግባቢ ለማስጠየቅም ይሰራል ብሏል ፖሊስ፡፡
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ማዘዋወርም ሆነ መጠቀም በህግ የሚያስጠይቅ ድርጊት መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሲያጋጥሙም በአቅራቢያ ለሚገኝ የፀጥታ አካል መረጃ መስጠት እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
@Tikfahethiopia
1175
22:01
28.07.2025
አሳዛኝ መረጃ‼️
በኦሮሚያ ክልል ከፍቸ ወጣ ብሎ ኢስት ሴመንት ፋብሪካ አካባቢ አንድ ከአዲስ አበባ ደብረ ማርቆስ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ባስ ላይ ጥቃት መድረሱን ተሳፋሪ ታፍኖ መወሰዱን ገልፀን ትክክለኛ መረጃ ይዘን እንደምንመለስ ተናግረን ነበር።
አሁን በደረሰን መልዕክት የታጠቁ ወንበዴዎች የባሱን ተሳፋሪዎች ለማፈን ሲሞክሮ ሹፌሩ አልቆምም በማለት ጥሶ በመውጣት ህዝቡን ከአጋቾች ማዳኑን እርሱ ግን በጥይት ተመቶ ህይወቱ ማለፉን ሌሎች አንድ የካሶኒ ሹፌር ከእነ ረዳቱ ታፍኖ መወሰዱን ደርሶናል። ሌሎች የደረሱ ጉዳቶችን ማወቅ አልቻልንም።
Via የሹፌሮች አንደበት
@Tikfahethiopia
514
21:03
30.07.2025
Telegram premium መግዛት የሚፈልግ በ አሪፍ ዋጋ inbox👇
@Beki_Boy
313
21:53
30.07.2025
close
New items
Selected
0
channels for:$0.00
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий