

- Main
- Catalog
- Real Estate
- Advertising on the Telegram channel «@Seleslamenwk»
Channel statistics
Full statisticschevron_rightበዶ/ር ዴቪድ ውድ
(ክፍል 2)
በመሐመድ ምሁራን መካከል የተፈጠረው አለመግባባት
ነገር ግን ሁሉም ሙስሊሞች በአዲሱ ቁርአን አልተስማሙም ነበር። አንዳንድ ዓበይት የመሐመድ ቁርአን ቀሪዎች የዛይድን ቅጂ አልተቀበሉትም ነበር።
በአንድ ወቅት መሐመድ ተከታዮቹን እንዲህ ብሏቸው ነበር "የቁርአንን አቀራር ከአራት ሰዎች ተማሩ፤ ከአብደላህ ኢብን መስኡድ፥ ነጻ የወጣው የአቡ ሁዴይፋ ባሪያ ሳሊም፥ ሙዓድ ኢቢን ጀባል እና ኡባይ ኢብን ካዓብ" [4] ነገር ግን በሚያስገርም ሁኔታ መጀመሪያ መሐመድ ቁርአንን ከእርሱ ተማሩ ያለው ኢብን መስኡድ ቁርአን መቶ አስራ አንድ (111) ምዕራፎች ብቻ እንዳሉት ገልጾ ነበር። አሁን ያለው ቁርአን ግን መቶ አስራ አራት (114) ምዕራፎች ብቻ ነው ያሉት። በእርሱ ገለፃ መሰረት በአሁኑ ቁርአን ውስጥ ያሉት ምዕራፍ 1፥ 113 እና 114 የቁርአን አካል አይደሉም።
በእዚህ እና በሌሎች በመቶ የሚቆጠሩ ልዩነቶች ምክንያት ኢብን መስኡድ የመጨረሻውን የቁርአን እትም ማታለያ (deception) ብሎት ነበር! "ሰዎቹ በቁርአን አቀራር ዙሪያ ማታለልን ፈጽመዋል። እኔ ከዛይድ ይልቅ በምወደው በእርሱ (በመሐመድ) አቀራር ብቀራው ይሻለኛል" ነበር ያለው። [5]
ሙስሊሞች ይህን ማታለል መቀበል ነበረባቸው? በማያስገርም ሁኔታ፥ ኢብን መስኡድ ሙስሊሞች የዛይድን ቅጂ እንዳይቀበሉና በፊት የነበሯቸውን ቅጂዎች እንዲጠብቁና በሰአቱ በነበረው የኡትማን መንግሥት እንዳይወሰዱ እንዲደብቋቸው ሁሉ ይመክራቸው ነበር። እንዲህ አለ፦ "እናንተ ሕዝበ ሙስሊም ሆይ! የዚህን ሰው መጽሐፍና አቀራር ከመኮረጅ ታቀቡ። በአላህ! እኔ እስልምናን ስቀበል እርሱ (ዛይድ) ገና በማያምን ሰው ወገብ ውስጥ ነበር (አልተወለደም ነበር)" ይህንንም አስመልክቶ ነበር አብደላህ ኢብን መስኡድ "የኢራቅ ሕዝብ ሆይ! ከእናንተ ጋር ያሉትን የቁርአን ቅጆች ያዟቸው፥ ደብቋቸውም" ያለው [6]
ነገር ግን ከመሐመድ ዓበይት የቁርአን ቀሪዎች መካከል በዛይድ ኢብድ ታቢት የቁርአን ቅጂ ያልተስማማው አብደላህ ኢብን መስኡድ ብቻ አይደለም። ኡባይ ኢብን ካዓብ አለ የሚባለው የመሐመድ የቁርአን ቀሪ ሲሆን፥ መሐመድ በሕይወት በነበረበት ሰአት ቁርአንን ካሰባሰቡት ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ ነበር። ነገር ግን ኡባይ ኢብን ካዓብ የዛይድ ቁርአን ሁለት ምዕራፎች እንደሚጎድሉት ያምን ነበር! (የዛይድ ቁርአን አሁን ያለው ቁርአን ስለሆነ፥ እንደ ኡባይ ኢብን ካዓብ እምነት አሁን ያለው ቁርአን ሁለት ምዕራፎች ይጎድሉታል)
በዚህም ምክንያት ሙስሊሞች አንዳንድ የኡባይ ኢብን ካዓብን አነባቦች ላለመቀበል ተገድደው ነበር። ዑመር እንዲህ አለ፦ "ኡባይ ከእኛ መካከል በቁርአን አቀራር አንደኛ ነበር፥ ነገር ግን እርሱ አንዳንድ እርሱ የሚቀራውን እንተወዋለን" ኡባይ ግን እንዲህ ብሏል "ይህን ከአላህ መልእክተኛ አፍ የወሰድኩት ነው፥ በምንም ሁኔታ አልተወውም" [7]
መሐመድ በመረጣቸው የቁርአን ቀሪዎች አለመግባባት የተነሳ ሙስሊሞች አጣብቂኝ ውስጥ ናቸው። ዛሬ ላይ ያለው ቁርአን በትክክል ተጠብቋል የሚሉ ከሆነ መሐመድ እነዚህን የቁርአን ቀሪዎች ሲመርጥ ተሳስቷል ወይም ዋሽቷል ሊባል ነው። የመረጣቸው የቁርአን ቀሪዎች አሁን ካለው ቁርአን ጋር አይስማሙምና። በተቃራኒው ደግሞ መሐመድ እነዚህን የቁርአን ቀሪዎች ሲመርጥ አልተሳሳተም ወይም አልዋሸም ካሉ፥ አሁን ላይ ያለው ቁርአን እንዳልተጠበቀ ማመን አለባቸው። አሁን ላይ ያለው ቁርአን በመሐመድ የተመረጡት የቁርአን ቀሪዎች ከነበራቸው ቁርአን ጋር ይለያያልና።
ማጣቀሻዎች
[4] Sahih Al Bukhari 3808
[5] Ibn Sa'd, Kitab al Tabaqat al-kabbir, Vol.2, p.444
[6] Jami At-Tirmidhi 3104
[7] Sahih Al Bukhari 5005
ይቀጥላል
በዶ/ር ዴቪድ ውድ
(ክፍል 3)
የጠፉ የቁርአን ምዕራፎች
ቁርአን በትክክል ተጠብቋል የሚለው ሀሳብ ስህተት እንደሆነ እነዚህ እውነታዎች ብቻ በበቂ ሁኔታ ያሳያሉ። ነገር ግን አጠር ባለ መልኩ አንዳንድ ችግሮችን የምንመለከት ይሆናል።
"የሁለተኛው ካልፋ ልጅ የሆነው ኢብን ዑመር ሰዎች ሙሉውን ቁርአን እንደሚያውቁ ሲናገሩ ሲሰማ፥ እንዲህ ብሏቸው ነበር፦ "ማናችሁም "ሙሉውን ቁርአን ተምሬዋለሁ" አትበሉ፥ እንዴት አንድ ሰው ሙሉው ምን እንደሆነ ያውቃል? አብዛኛው ጠፍቶ ሳለ?! ይልቁኑ "የተረፈውን ተምሬያለሁ" ይበል" [8]
ከመሐመድ ተከታዮች አንዱ የነበረው አቡ ሙሳ ከዚህ ሀሳብ ጋር ይስማማል። የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች በስንፍናቸው የተነሳ ሁለት ሱራዎችን እንደረሱ ተናግሯል፦
አቡ ሙሳ አል-አሽዓሪ ወደ ባስራ የቁርአን ቀሪዎች መልእክት ላከ። ቁጥራቸው ሶስት መቶ (300) ሲሆን ወደ እርሱ መጡ፥ ቁርአንንም ቀሩ። ከዚያም እንዲህ አላቸው "ከባስራ ነዋሪዎች እናንተ የላቃችሁ ናችሁ፥ ከእነርሱ መካከል የቁርአን ቀሪዎች እናንተ ናችሁና። ስለዚህ መቅራቱን ቀጥሉ። ነገር ግን እንዳትረሱ! ለረዥም ጊዜ ቁርአንን መቅራታችሁ ከእናንተ በፊት እንደነበሩት ቀሪዎች ልብ የእናንተም ልብ እንዳያደነድን። እኛ ከሱራ ባራዓት (የሱራ 9 ሌላ ስም) ጋር በርዝመቱ እኩል የሆነ ሱራ እንቀራ ነበር። ነገር ግን "ለሰው ልጅ በሀብት የተሞሉ ሁለት ሸለቆች ቢኖሩ፥ ሶስተኛ ሸለቆን ይመኛል፥ ከአቧራ በቀር የሰውን ልጅ ሆድ የሚሞላ ምንም ነገር የለም" ከሚለው አንቀጽ በቀር እንዳለ ረስቼዋለሁ። ደግሞም ከሙሳቢሃት ሱራዎች ጋር የሚመሳሰል ሱራንም እንቀራ ነበር፥ ነገር ግን ረስቼዋለሁ" [9] (ሙሳቢሃት ሱራዎች አላህን በማሞገስ የሚጀምሩ ሱራዎች ሲሆኑ ሱራ 57፥ 59፥ 61፥ 62፥ 64፥ 87 ናቸው)
ይህ ሙሉ የቁርአን ምዕራፎች እንደተረሱና እንደጠፉ ያሳያል
የጠፉ የቁርአን አንቀጾች
ከዚህ በተጨማሪም ከአንዳንድ የቁርአን ምዕራፎች ረዣዥም ክፍሎች እናውቃለን። ለምሳሌ የመሐመድ ሚስት አዒሻ በአማካይ የሱራ 33 ሁለት ሶስተኛው (2/3) እንደጠፋ ተናግራለች፦
"አዒሻ አለች፦ ሱረቱል አሕዛብ (ሱራ 33) በነብዩ ጊዜ ሲቀራ ሁለት መቶ (200) አንጾች ነበሩት። ነገር ግን ኡትማን የእርሱን ቅጂ ሲያሰባስብ አሁን ካሉት 73 አንቀጾች በቀር ሌሎቹን ማግኘት አልቻለም" [10]
እንደ አዒሻ ምስክርነት የቁርአን ሰብሳቢዎቹ ሙሉን ሱረቱል አሕዛብ (ሱራ 33) ማግኘት አልቻሉም። ለምን? በፊት ለማየት እንደሞከርነው፥ ብዙ ሀፊዞች በየማማ ጦርነት ተገድለው ነበር። ስለዚህ ሙሉውን ምዕራፍ የሚያውቅ ሰው ከጦርነቱ አልተረፈም ነበር ማለት ነው።
የጠፉ የቁርአን ጥቅሶች
ከዚህም ባሻገር አዒሻ የጠፉ የቁርአን ጥቅሶች እንደጠፉ ተናግራለች። የጠፉበት መንገድም ፈገግ ያደርጋል፦
"አዒሻ የተናገረችው እንዲህ ተዘግቧል፦ "የውግራትና አዋቂን አስር ጊዜ ጡት የማጥባት ጥቅስ ወርዶ ነበር፥ ወረቀቱም ከእኔ ጋር ከትራሴ ስር ነበር። የአላህ መልእክተኛ ሲሞት በሞቱ ምክንያት ተዋክበን ነበር። ያኔም አንዲት ለማዳ በግ መጣችና በላችው" [11]
በአሁኑ ቁርአን ውስጥ የውግራትና አዋቂን አስር ጊዜ ጡት የማጥባት ጥቅስ የለም። ለምን? የአዒሻ በግ በልታዋለች
ማጣቀሻዎች
[8] Abu Ubaid, Kitab Fada'il-al-Quran
[9] Sahih Muslim 2286
[10] Abu Ubaid, Kitab Fada'il-al-Qur'an
[11] Sunan Ibn Majah 1944
ይቀጥላል
በዶ/ር ዴቪድ ውድ
መግቢያ (ክፍል 1)
ሙስሊሞች እስልምና እውነት መሆኑን እናረጋግጣለን በሚል ከሚጠቀሟቸው ታዋቂ ሙግቶቻቸው አንዱ "የቁርአን በትክክል መጠበቅ" የሚለው ሙግታቸው ነው። በዚህ ሙግት መሰረት ቁርአን ለአስራ አራት ምዕተ ዓመታት በትክክል ስለተጠበቀ አምላክ ተአምራዊ በሆነ መንገድ ሲጠብቀው ነበር። ይህ ሙግት በሚከተለው የቁርአን አንቀጽ ላይ የተመሰረተ ነው፦
إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا ٱلذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡ (ሱራ 15: 9)
ይህን አንቀጽ ከጠቀሰ በኋላ፥ የእስልምና ዓቃቤ እምነት ማዝሃር ካዚ የሚከተለውን ይላል፦
"ሙስሊሞችም ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችም እንደሚስማሙት በቁርአን ጽሑፍ (The Text of The Quran) ውስጥ አንድም ለውጥ አልተካሄደም። ከላይ ያለው ትንቢት (ሱራ 15:9) እውነት የሆነው ለቁርአን ጽሑፍ ዘላለማዊ ጥበቃና እንከን አልባነት ብቻ ሳይሆን፥ እንደ ሥርዓተ ነጥብ (punctuation) ባሉት አነስተኛና ዝርዝር ጉዳዮችም ነው። ባለፉት አስራ አራት ምዕተ ዓመታት አንድም የቁርአን ቃል፥ ፊደል፥ ሥርዓተ ነጥብና አናባቢ ነቁጥ (diacritical mark) አለመለወጡ የቁርአን ተአምር ነው" [1]
ነገር ግን ይህ መከራከሪያ በሁለት ምክንያቶች የተነሳ ፈጽሞ አያስኬድም። በመጀመሪያ አንድ መጽሐፍ ለአስራ አራት ምዕተ ዓመታት መጠበቁ ተአምር አይደለም። የሙት ባህር ጥቅሎች፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎችና ሌሎች ጽሑፎችም ከ1,400 ዓመታት በላይ ተጠብቀው ቆይተዋል። ስለዚህ ጥበቃ ቁርአን መለኮታዊ ጥንሳሴ (divine inspiration) እንዳለው ማሳያ ሊሆን አይችልም። ሲቀጥል ቁርአን በትክክል ተጠብቋል የሚለው ሀሳብ ሀሰት ነው! ጥንታዊ የሚባሉ የእስልምና ምንጮችን ስንመለከት ሙሉ የቁርአን ምዕራፎች፥ ከቁርአን ምዕራፎች ረዣዥም ክፍሎች እንደጠፉ፥ ጥቅሶች እንደተረሱ፥ ቃላትና ሀረጋት እንደተቀየሩ እናረጋግጣለን። በተጨማሪም የመሐመድ ተዓማኒ የቁርአን ቀሪዎች የትኞቹ ምዕራፎች በቁርአን ውስጥ መካተት እንዳለባቸው መስማማት እንዳልቻሉ ከተአማኒ እስላማዊ ዘገባዎች እንረዳለን።
የቁርአን አሰባሰብ ታሪክ በአጭሩ [2]
ሙስሊሞች የመጀመሪያው የቁርአን መገለጥ ወደ መሐመድ የመጣው በ610 ዓ/ም ነው ብለው ያምናሉ። ከዚያም በቀጣዮቹ ሀያ ዓመታት ውስጥ መሐመድ ተጨማሪ የቁርአን አንቀጾችን ለጸሐፊዎቹና ለተከታዮቹ እንዲሸመደዱና እንዲጻፉ አስተላልፎ ነበር። እነዚህ የቁርአን አንቀጾች የተጻፉት በዘንባባ ቅጠሎች፥ በአጥንቶች፥ በሞቱ እንስሳት፥ በጠፍጣፋ ድንጋዮች እና ሙስሊሞቹ ባገኙት ነገር ሁሉ ነበር። እናም በዚህ ጊዜ የተሟላ የቁርአን ዕደ-ክታብ አልነበረም
መሐመድ ከሞተ በኋላ የቁርአን መገለጥ እንደቆመ በሙስሊሞች ዘንድ ይታመናል። መሐመድ ከሞተ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ካሊፋ አቡ በከር አንድ የተቀሰቀሰን ተቃውሞ ለማስቆም ብዙ ሀፊዞችን (ቁርአንን የሸመደዱ ሰዎችን) በየማማ ጦርነት እንዲዋጉ ልኮ ነበር። በጦርነቱ ግን አብዛኞቹ ሀፊዞች ሞቱ። ከዚያም እስላማዊ ምንጮች እንደሚናገሩት አንዳንድ የቁርአን ክፍሎች ጠፉ። አብዛኞቹ የቁርአን አንቀጾች ይታወቁ የነበሩት በየማማ ጦርነት ወቅት በሞቱት ሀፊዞች ሲሆን ከጦርነቱ በተረፉት ሰዎች አይታወቁም ነበር። አልተጻፉምም ነበር። በሰአቱም አቡበከር፥ ኡመርና ኡትማን ቁርአንን ሰብስበው አልነበረም። ከጦርነቱ በሕይወት ከተረፉት ሰዎች ዘንድ ከአንዱም አልተገኙም ነበር።
ከዚያም አቡበከር ተጨማሪ የቁርአን አንቀጾች እንዳይጠፉ ቁርአን መሰብሰብ እንዳለበት ወሰነ። ይህንንም ስራ ለዛይድ ኢብን ታቢትን ሰጠው። ዛይድ ኢብን ታቢት በ634 ዓ/ም የራሱን ቅጂ ካጠናቀቀ በኋላ ይህ የዛይድ ቅጂ በአቡበከር ዘንድ ነበር። አቡበከር ከሞተ በኋላም ለቀጣዩ ካሊፋ ለካሊፋ ዑመር ተላለፈ። ዑመር ከሞተ በኋላ ደግሞ የመሐመድ ሚስት ለነበረችው ለሀፍሳ ተሰጠ።
መሐመድ ከሞተ ከ19 ዓመታት በኋላ በካሊፋ ኡትማን ዘመን በትክክለኛው የቁርአን አቀራር ዙሪያ አለመግባባቶች ተነሱ። ከዚያም ኡትማን የሀፍሳ ቅጂና ሌሎች የታወቁ የቁርአን ዕደ-ክታባት ተሰባስበው ይፋዊ የሆነ የቁርአን እትም እንዲዘጋጅ አዘዘ። ዛይድ ኢብን ታቢት፥ አብደላህ ቢን አዝ-ዙቤይር፥ ሳዓድ ቢን አል-አስ እና አብዱር ራሕማን ቢን ሃሪስ በታታሪነት የተከለሰ የቁርአን እትም አዘጋጁ። ባለቀ ጊዜም ኡትማን ለእያንዳንዱ ሙስሊም ግዛት እነርሱ ያዘጋጁትን እትም አንድ አንድ ቅጂ ላከ። ከዚያም እርሱ ከላከው ውጪ ያሉትን ሌሎች የቁርአን ዕደ-ክታባትን (በከፊልም ይሁኑ በሙሉ) እንዲቃጠሉ አዘዘ [3] አሁን ያለው ቁርአን ከዚያ እትም የመጣ ነው።
ማጣቀሻዎች
[1] Mazhar Kazi, 130 Evident Miracles in the Quran (Richmond Hill: Crescent Publishing House, 1997), pp. 42-43
[2] Ibn Abi Dawud, Kitab al-Masahif
[3] Sahih Al-Bukhari 4987
ይቀጥላል
ሙሐመድ ከኸዲጃ ጋር በጋብቻ እስከ ተጣመረበት ጊዜ ድረስ በድኽነት ይኖር የነበረ ተንከራታች ወጣት ነበር። በዚያ የችግር ዘመን ደርሳ ከድኽነት ያስጣለችው ኸዲጃ ናት። እርሷ በሕይወት በነበረችበት ዘመን በአንድ ለአንድ ጋብቻ ተወስኖ የመኖሩም ምስጢር ይኸው ነው። በእርሷ ንብረት ከድኽነት ወጥቶ በቤቷ እየኖረ በእርሷ ላይ ደርቦ ማግባት የማይታሰብ ነው። ከእርሷ ህልፈት በኋላ በአንድ ለአንድ ጋብቻ ተወስኖ ቢኖር ኖሮ ከኸዲጃ ጋር በዚያ መንገድ የኖረው በፈቃዱ እንጂ ተገድዶ እንዳልሆነ መደምደም በቻልን ነበር። ከእርሷ ህልፈት በኋላ ደስ ያሰኘችውን ሴት ሁሉ (ዘመዶቹን ጨምሮ) እንዲያገባ አላህ እንደ ፈቀደለት በመናገር የቻለውን ያህል ሴት አግብቶ ኖሯል። ለምሳሌ ተከታዩን ጥቅስ እስኪ እንመልከት:-
ሱራ 33:50 “አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን ሚስቶችህን፣ አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም እነዚያን እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች፣ እነዚያንም ከአንተ ጋር፣ የተሰደዱትን የአንጎትህን ሴቶች ልጆች፣ የአክስቶችህንም ልጆች፣ የየሹማህንም ሴቶች ልጆች ፣ የየሹሜዎችሕንም ሴቶች ልጆች (ማግባትን) ለአንተ ፈቅደንልሃል፤ የአመነችንም ሴት ነፍሷን (ራሷን) ለነቢዩ ብትሰጥ ነቢዩ ሊያገባት የፈለገ እንደ ሆነ፣ ከምእምናን ሌላ ላንተ ብቻ የጠራች ስትሆን፣ (ፈቀድንልህ)፤ በነርሱ (በምእምናን) ላይ በሚስቶቻቸውና እጆቻቸውም በጨበጧቸው (ባሮች ነገር) ግዴታ ያደረግንባቸው በእርግጥ አውቀናል፤ ባንተ ላይ ችግር እንዳይኖር፣ (ያለፉትን ፈቀድንልህ)፤ አላህም መሐሪ አዛኝ ነው።"
በዚህ የአላህ ፈቃድ መሠረት ሙሐመድ የአክስቱ ልጅ የነበረችውን ለማደጎ ልጁ ተድራ የነበረችውን ዘይነብን ጭምር ከባሏ ነጥቆ አግብቷል። እነ አሕመዲን መልስ የሌለውን ጉዳይ አንስተው ራሳቸውን ከሚያስጨንቁ ዝም ቢሉ ይሻላቸው ነበር። ለበለጠ መረጃ ይህንን ጽሑፍ ያንብቡ https://ewnetlehulu.net/zaynab/
Ali bin Al-Husain from Safiya:-Safiya went to the Prophet (ﷺ) while he was in Itikaf. When she returned, the Prophet (ﷺ) accompanied her walking. An #Ansari man saw him. When the Prophet (ﷺ) #noticed him, he called him and said, " #Come here. She is #Safiya. (Sufyan a sub-narrator perhaps said that the Prophet (ﷺ) had said, "This is Safiya"). And #Satan #circulates in the #body of #Adam's offspring as #his #blood #circulates in it." (A sub-narrator asked Sufyan, "Did Safiya visit him at night?" He said, "Of course, at night.").""አሊ ቢን አል-ሁሴን ከሳፊያ እንደተረከው፦ #ሳፊያ #ኢቲካፍ ላይ #እያሉ ወደ ነብዩ (ﷺ) ሄደች ልክ ስትመለስ ነብዩ (ﷺ) በእግራቸው #ሸኟት። አንድ #የአንሳር ሰውም እሳቸውን #አያቸው፦ ነብዩም (ﷺ) እሱን ባዩት ጊዜ #ጠሩት እና እንዲህ አሉት እሷ #ሳፊያ ናት አሉት። ( ሱፍያን ግማሹን ተራኪው ምን አልባት ነብዩ (ﷺ) “ይቺ ሳፊያ ናት” ብለው ተናግረው ይሆናል)። እና #ሰይጣን #በአደም #ዘር #ሰውነት ውስጥ ደም #እንደሚዟዟር #ይዟዟራል። (ግማሹን ተራኪው ሱፊያን፦ ሳፊያ በለሊት እሱን ጎብኝታዋለች? እሱም እንዲህ አለ አዎ በለሊት ጊዜ በትክክል።"
حَدَّثَنَا إِسْمَاعِيلُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ أَخْبَرَنِي أَخِي، عَنْ سُلَيْمَانَ، عَنْ مُحَمَّدِ بْنِ أَبِي عَتِيقٍ، عَنِ ابْنِ شِهَابٍ، عَنْ عَلِيِّ بْنِ الْحُسَيْنِ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ صَفِيَّةَ، أَخْبَرَتْهُ. حَدَّثَنَا عَلِيُّ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، حَدَّثَنَا سُفْيَانُ، قَالَ سَمِعْتُ الزُّهْرِيَّ، يُخْبِرُ عَنْ عَلِيِّ بْنِ الْحُسَيْنِ، أَنَّ صَفِيَّةَ ـ رضى الله عنها ـ أَتَتِ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم وَهْوَ مُعْتَكِفٌ، فَلَمَّا رَجَعَتْ مَشَى مَعَهَا، فَأَبْصَرَهُ رَجُلٌ مِنَ الأَنْصَارِ، فَلَمَّا أَبْصَرَهُ دَعَاهُ فَقَالَ " تَعَالَ هِيَ صَفِيَّةُ ـ وَرُبَّمَا قَالَ سُفْيَانُ هَذِهِ صَفِيَّةُ ـ فَإِنَّ الشَّيْطَانَ يَجْرِي مِنَ ابْنِ آدَمَ مَجْرَى الدَّمِ ". قُلْتُ لِسُفْيَانَ أَتَتْهُ لَيْلاً قَالَ وَهَلْ هُوَ إِلاَّ لَيْلٌ
Reference : Sahih al-Bukhari 2039In-book reference : Book 33, Hadith 14USC-MSA web (English) reference : Vol. 3, Book 33, Hadith 255 (deprecated numbering scheme)
Reviews channel
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «@Seleslamenwk» is a Telegram channel in the category «Недвижимость», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 1.7K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 7.1, with 0 reviews and an average score of 0.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 2.4 ₽, and with 0 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий