
Monetize Telegram Mini App with Telega.io
Connect your app, set CPM, and watch your revenue grow!
Start monetizing
23.8

Advertising on the Telegram channel «Society of construction law in Ethiopia»
5.0
5
Job Listings
Language:
Amharic
0
0
This Channel Give Detail Description About Law Of Crypto And Trading According Ethiopian Rule of Law
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$1.20$1.20local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
imageImage preview is unavailable
👉ወጋገን ባንክ በመቐለ ከተማ ባለ 25 ፎቅ ሕንፃ ሊገነባ ነው
🏷ከአሸናፊው ተቋራጭ የግንባታ ቦታ ርክክብ አድርጓል
💫ወጋገን ባንክ በመቐለ ከተማ ለሚያስገነባው ለሁለገብ አገልግሎት የሚውል ባለ 25 ወለል ህንፃ ለአሸናፊው የግንባታ ተቋራጭ የዛምራ ኮንስትራክሽን የግንባታ ቦታ ርክክብ ፈጸመ፡፡
በግንባታ ቦታ ርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባንኩ ቺፍ ሰፖርት ሰርቪስስ ኦፊሰር አቶ መንገሻ ፍሰሃ የህንፃው ግንባታ ጅማሮ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየ መሆኑን ጠቅሰው የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ማኔጅመንት በሰጡት ከፍተኛ ትኩረት ግንባታውን ለማከናወን ለተቋራጭ ድርጅቱ የግንባታ ቦታ ርክክብ መፈፀሙን ተናግረዋል፡፡ አቶ መንገሻ ፍሰሃ ዛምራ ኮንስትራክሽን ሥራውን በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት በጥራት ሰርቶ በማጠናቀቅ እንደሚያስረክብ ያላቸውን ከፍተኛ እምነት ገልፀው አማካሪው ድርጅት ኢኢኤስ ኮንሰልቲንግ አርክቴክቶች እና ኢንጂነሮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ለግንባታው በስኬት መጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡🚧በግንባታ ቦታ ርክክቡ ወቅት የወጋገን ባንክ የዋና መስሪያ ቤት፣ የሰሜን ሪጅናል ኦፊስ፣ የመቐለ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ፣ የዛምራ ኮንስትራክሽን እና የኢኢኤስ ኮንሰልቲንግ አርክቴክቶች እና ኢንጂነሪንግ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ @etconp
406
12:41
27.08.2025
🏷ምዝገባ ጨርሰናል🙏
💫ሁለተኛ ዙር የ "Quantity Surveying" Full Course በ ኦንላይን ለመማር የተመዘገባቹ በ ሙሉ ዛሬ ቅዳሜ ማታ አንድ ሰዓት ክላስ ይጀመራል ተዘጋጁ❤
📩ለበለጠ መረጃ @Philemona7 ወይም 0925446661 ይደውሉ
@etconp
528
13:18
30.08.2025
የ"Site Diary" ጥቅምና ይዘት {The importance and Format of Site Diary}📌በግንባታ ሂደት ውስጥ የምናገኛቸው የተለያየ ዓላማና ይዘት ያላቸው ሰነዶች አሉ። ለምሳሌ ያህል፦ የውል ሰነድ (contract document)፣ የሥራ ፍቃድ (Work Permit/order)፣ የግንባታ ፍቃድ (Building Permit)፣ የሥራ ምዘና መዝገብ (Checklists)፣ የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary)፣ ንድፎች (Drawings) ... የመሳሰሉት ይገኙበታል። በሀገራችን የውል ፈጻሚዎች (አሠሪ፣ ተቋራጭ እና አማካሪ) ግጭት ውስጥ ለመግባታቸው አንዱና ዋነኛው ምክንያት እነዚህ ሰነዶች በግንባታ ሥራ አለመሟላታቸው መሆኑን የተጠኑ ጥናቶችም ጠቁመዋል። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነውን የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary) እንመለከታለን። ብዙ ጊዜ ስለዚህ ሰነድ ያለን ትኩረት ለዘብ ያለ ሆኖ የሚስተዋል ቢሆንም ብዙ የሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች እና አሠሪዎች ከስረውበታል።
ክፍል አንድ ዋና ዋና ጥቅሙ፦1ኛ). የዕለት ተግባራትን መመዝገቢያ፡ ይህ የማስታወሻ ጥራዝ ወይም ሰነድ በየቀኑ በግንባታ ቦታው ላይ የተከናወኑ ሥራዎችን እንመዘግብበታለን። የተሰሩ ሥራዎችን፣ ግንባታው ያለበትን ደረጃ፣ በዕለቱ ያለውን የአየር ሁኔታ፣ ለግንባታ ሥራው የተሳተፉ ባለሙያዎችንና የጉልበት ሰራተኞችን ብዛት፣ የገጠሙ ችግሮችን፣ የተወሰዱ መፍትሔዎችን፣ በባለድርሻ አካላት የታዘዙ ልዩ ትእዛዞች (ካሉ) እነዚህ መረጃዎች የምንመዘግብበት የሁሉም የግንባታ ስራዎች አጠቃላይ ዕለታዊ መዝገብ ሆኖ ያገለግላል። ይህ ሰነድ የፕሮጀክቱን እድገት ለመከታተል ወሳኝ ሲሆን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ውስጥ ግልፅነትን ያረጋግጣል፣ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ስለቦታው ሁኔታ እንዲያውቁ ያግዛል። 2ኛ). ቅሬታ ወይም የክርክር የሚፈታበት ነው፦ በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ መጓተትን፣ የአቅም ለውጥን ወይም የሥራ ጥራትን በተመለከተ አለመግባባቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። በመሆኑም የዕለት ክስተት ማስታወሻው ሰነድ በቦታው ላይ ስለ ሁነቶች እና ሁኔታዎች ማስረጃ የሚያቀርብ ህጋዊ የግንባታ ሰነድ ሆኖ የሚቆጠር ስለሆነ በየትኛውም የፍትህ መንገድ ቅቡልነት አለው። ለምሳሌ ያህል፦ የጊዜ መጓተት የሚፈጥሩ ክስተቶች ካሉ (ለአብነት) ቀኑን ሙሉ ዝናብ ቢውል ወይም አካባቢው ረብሻ ቢሆን እነዚህ ክስተቶች የወሰዱትን ጊዜ (ሰዓት፣ ቀን፣ ወር) በቁጥር የምናሰላው ከ'Site Diary ላይ ለቅመን ስለሆነ ክስተቶቹ ባስተጓጎሉት የጊዜ መጠን ልክ በውሉ ላይ የነበረውን ግንባታ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ለማራዘም ያግዛል። በሌላም በኩል (ለምሳሌ) የግንባታ ግብአት ማቅረብ የአሠሪው (Client/employer) ድርሻ ቢሆን እና የግንባታ ጊዜ በዚህ የተነሳ ቢጓተትበት ሥራ ተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ እና የሠራተኞች ያለሥራ የቆዩበትን ክፍያ አሠሪው እንዲከፍል ሊጠይቅበት የሚችለው በ'Site Diary ላይ በአግባቡ የተቀመጠ መዝገብ ካለ ነው። 3ኛ) ጥራትን ለመቆጣጠር ማረጋገጫ ይሆናል፦ site diary መያዝ የጥራት ቁጥጥር እርምጃዎችን እና ፍተሻዎችን ለመመዝገብ ያስችላል። ለምሳሌ፦ በዕለቱ የተሠራው ሥራ የፌሮ ብረት እና የአርማታ ሙሌት ነው ብለን ብናስብ ለእያንዳንዱ ስትራክቸር የተጠቀምንው የፌሮ ብረት አይነትና ብዛት፣ የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠር ብዛት፣ የተከናወኑ የቤተሙከራ ሥራዎችና ውጤቶቻቸው እና የተስተዋሉ ያልተሟሉ ጉዳዮችን የምንመዘግብበት ስለሆነ የግንባታ ሥራ በዲዛይኑ መሰረት ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልቶ እየተከናወነ ስለመሆኑና ስላለመሆኑ ጥራቱን እንድንቆጣጠር፣ የሚፈለገውን ደረጃና መስፈርት የሚያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ፣ ተጠያቂነትን ለማስፈን እና አጠቃላይ የፕሮጀክት ጥራትን ለማሻሻል ያግዛል።
ክፍል ሁለት፡ ይዘቱ ምን መምሰል አለበትይቀጥላል ..... @etconp
418
13:49
31.08.2025
imageImage preview is unavailable
👉በ 14 ዓመታት የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ጉዞ ውስጥ ከ15ሺ በላይ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል !!
💥ሕዳሴ የደም ዋጋም ተከፍሎበታል !
ሪፖርተር የእንግሊዘኛው መጽሔት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ጋር ያደረገውን ቆይታ አውጥቷል።
በቆይታው ማብቂያ ጠያቂው ጋዜጠኛ በእውቀት አበበ ይህን ጠየቀ ...እርሳቸውም መለሱ
Is it true that as many as 15,000 people died while building the dam over the past 14 years?
Yes, that is true.
በገንዘብ በጊዜና በብዙ መስዋዕትነት ብቻ አይደለም ሕዳሴ በ15 ሺ የአገራችን ልጆች ደምም ጭምር ነው የተገነበው😢❤
©️ ኤርሚያስ በጋሻው ገሰሰ
📜ሪፖርተር ጋዜጣ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ ጋር ያደረጉትን ሙሉ ቃልመጠየቅ አንበቡ👇
https://thereportermagazines.com/4076/?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR5S6q17e_MubeBe6FwfpnOGpkMwpRxlipphXfneiSHIpYNitSAJ5MadMPygKg_aem_pDAw4-7glxVrzIgiOqC4SA
@etconp
260
20:22
02.09.2025
imageImage preview is unavailable
ADVERTISMENT
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)
🔅 የተለያዩ [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።
♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።
☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1
አድራሻ፦ ቁ 1.መርካቶ
ቁ.2 አየር ጤና ኪዳነ ምህረት
ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
359
08:36
03.09.2025
👉ተጠባቂው የብድር አቅርቦት መሻሻልና የሪል እስቴት ልማትና ግብይት
❇️በመጪው አዲስ ዓመት የባንክ ብድር አቅርቦት ይሻላል መባሉንና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም 50ቢሊየን ብር ብድር ለዲያስፖራ ማዘጋጀቱንና ብድሩ የቤት ግዢንም የሚያካትት መሆኑን ሰምተናል።
⏺እነዚህ ዜናዎችን የተመለከተ በሪል እስቴት ዘርፍ ውስጥ ያለ አልሚም ሆነ ቤት ገዢ እንዲሁም የግብይት ባለሙያ ብድር መለቀቁ ለዘርፉ የተሻለ ነገር ያመጣል ብሎ እየጠበቀ ነው። እንደጥበቃቸው መልካም እንዲሆን እየተመኘሁ የገንዘብ አቅርቦት መሻሻል ልዩ በሆነው የሀገራችን የሪል እስቴት ኢንቨስትመንትና ግብይት ውስጥ ሊኖረው የሚችለውን አስተዋጽኦና ተጽዕኖ በገባኝ መጠን ካለንበት ተነስቼ ወደ ምንሄድበት በጥቂቱ ላስቀምጥ።
📍የት ነን?
⏺በሪል እስቴት ግብይት ዑደት መሰረት ግብይቱ አሁን የሚገኘው ውድቀት (recession) በሚባለው ወስት ላይ ይገኛል።
⏺በውድቀት ወቅት መገለጫዎች መሰረት ብዙ ቤቶች የገዢ እጥረት ገጥሟቸዋል፣ ወደ ዘርፉ የሚገቡ አዳዲስ አልሚዎች ቁጥር ቀንሷል፣ ተደጋጋሚ የዋጋ ቅናሾች እየተደረጉ ነው....
📍ወዴት እንሄዳለን?
💫በዘርፉ ተፈጥሯዊ ዑደት መሰረት ቀጣይ ተጠባቂው ወቅት የማገገሚያ (recovery) ወቅት ነው።
⏺ዘርፉን ከውድቀት ወደ ማገገም ለማስገባት ከሚደግፉ ተግባራት አንዱ የገንዘብ አቅርቦት መሻሻል ነው።
⏺ምንም እንኳን የሚለቀቀው ብድር ቀጥታ ለቤት ግንባታና ግዢ ባይሆንም የተለያዩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን በማነቃቃት ከስድስት ወራት በኋላ በሪል እስቴት ዘርፍ ላይ ግብይቱን ያነቃቃል ተብሎ ይጠበቃል።
🎲ነገር ግን የገንዘብ አቅርቦት መሻሻል ብቻውን በሀገራችን ያለውን የሪል እስቴት ግብይት ከውድቀት ወደ ማገገም ሊወስደው አይችልም።
📜ምክንያቶቹ እነሆ:-
፩) የመግዛት አቅም እጅጉን ተዳክሞ መቆየቱ
፪) የብድር ወለድ ምጣኔ ከፍተኛ መሆን
፫) የዋጋ ጭማሪ የሚጠበቅ መሆኑ
፬) የመሬት አቅርቦት ቢሻሻልም አሁንም ውድ መሆኑ
፭) የግንባታ ግብዓት ዋጋ እየጨመረ መሄዱ
፮) የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ቢሻሻልም የብር ዋጋ ከሌሎች አንጻር እየቀነሰ መሄድ መቀጠሉ
፯) ገበያው ውስጥ ያሉት ቤቶች ተመሳሳይ/ተቀራራቢ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸው ዜጎችን ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸው...
🏷ምን ቢደረግ ይበጃል?
🚧በሀገራችን ዘርፉ በቅጡ እንዲያገግምና ዜጎችም የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚከተሉት ቢከወኑ የተሻለ ይሆናል:-
፩) ለቤት ገዢዎች እጅግ በጣም አናስተኛ በሆነ የወለድ ምጣኔ በረጅም ጊዜ የሚከፈል ብድር ቢመቻች
፪) አናስተኛ ገቢ ላላቸው በዜሮ ወለድ በረጅም ጊዜ የሚከፍሉት የቤት አማራጭ ቢኖር
፫) ለአልሚዎች በጣም አነስተኛ በሆነ ዋጋ መሰረተ ልማት የተሟላለት መሬት በማቅረብ ቀድሞ በተወሰነ ቁርጥ ዋጋ በተገደበ ጊዜ ቤት እንዲያቀርቡ ቢደረግ
፬) በአነስተኛ ዋጋ ቤት ለሚያቀርቡ አልሚዎች ከቀረጥ ነጻ የግንባታ ግብዓት የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት
፭) ለመጀመሪያ ጊዜ ቤት ለሚገዙ ዜጎች የተጨማሪ እሴት ታክስና የስም ማዞሪያ ወጪዎች እንዳይከፍሉ ቢደረግ።
፮) ተኪ የግንባታ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ በስፋት እንዲመረቱ ቢደረግ
፯) ለሽያጭ ከሚቀርቡ ቤቶች በተጨማሪ ዜጎች በኪራይ ሊገለገሉባቸው የሚችሉ መሰረታዊ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትን የሚያሟሉ ቤቶችን ( core products) በብዛት ገንብቶ ማቅረብ
፰) በከተማችን አስገዳጁ ለአንድ ቤት አንድ መኪና ማቆሚያ መስፈርት በአነስተኛ ዋጋ ቤት ለሚያቀርቡ አልሚዎች ቢቀር/ቢሻሻል
💫ከላይ የተጠቃቀሱትን የመሳሰሉ መፍትሄዎች አብረው ካልቀረቡ በስተቀር የገንዘብ አቅርቦት ብቻውን ዘርፉን ከውድቀት ወደ መረጋጋትና መስፋፋት የሚወስድ ሳይሆን በተቃራኒው ውድቀት ውስጥ ተጨማሪ ጊዜያትን እንዲያሳልፍ የሚያደርግ ነው የሚሆነው።
Via ኢ/ር ደሳለኝ ከበደ የሪል እስቴት ቢዝነስ አማካሪ
@etconp
332
20:27
03.09.2025
imageImage preview is unavailable
👉ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1500ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ❤
@etconp
358
09:32
04.09.2025
👉አዲስ አመት ምክንያት በማድረግ ቀድመው ለሚመዘገቡ 10 ለ 5 ሰዎች ብቻ የ Full Quantity Surveying Online Course በ 50% ቅናሽ እንዳያመልጥዎ😇
⚡️አሁኑኑ ይመዝገቡ ጷግሜን 5 ወደ ነበረበት ዋጋ ይመለሳል!
📩ለበለጠ መረጃ በ @Philemona7 ይፃፉልን ወይም በ 0925446661 ይደውሉል🙏
@etconp
204
14:02
08.09.2025
imageImage preview is unavailable
ADVERTISMENT
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)
🔅 የተለያዩ [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።
♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።
☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1
አድራሻ፦ ቁ 1.መርካቶ
ቁ.2 አየር ጤና ኪዳነ ምህረት
ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
132
08:34
10.09.2025
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
1 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
c
**ffeennew@******.io
On the service since June 2022
13.04.202523:31
5
Everything is fine. Thank you!
New items
Channel statistics
Rating
23.8
Rating reviews
5.0
Сhannel Rating
13
Subscribers:
2.6K
APV
lock_outline
ER
7.3%
Posts per day:
2.0
CPM
lock_outlinekeyboard_double_arrow_left
shopping_cart
Channels:
0
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Total:
$0.00
Add to Cart
Clear the cart
Are you sure you want to clear the cart?
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Clear my cart
Cancel
Комментарий