
- Main
- Catalog
- Religion & Spirituality
- Advertising on the Telegram channel «ኦርቶዶክሳዊ 📖📖📖 መጻሕፍት ✝️✝️✝️»

Advertising on the Telegram channel «ኦርቶዶክሳዊ 📖📖📖 መጻሕፍት ✝️✝️✝️»
በዚህ channel ውስጥ መንፈሳዊ መጻሕፍትንና የየዕለቱን ስንክሳር ያገኛሉ።
Channel statistics
Full statisticschevron_right" #ለእመ_ኮነ_መስከረም_25_በሰንበት_ዘፀአተ_ክረምት_፫ተኛ_መዝሙር_ትብሎ_መርዓት "።
#መስከረም_25
ዕብራውያን 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፥ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መሥዋዕት የሚቀርቡትን ሊፈጽም ከቶ አይችልም።
² እንደዚህማ ባይሆን፥ የሚያመልኩት አንድ ጊዜ ነጽተው ከዚያ በኋላ በሕሊናቸው ኃጢአትን ስላላወቁ ማቅረብን በተዉ አልነበረምን?
³ ነገር ግን በዚያ መሥዋዕት በየዓመቱ የኃጢአት መታሰቢያ አለ፤
⁴ የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና።
⁵ ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ፦ መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤
⁶ በሙሉ በሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ኃጢአት በሚሰዋ መሥዋዕት ደስ አላለህም።
⁷ በዚያን ጊዜ፦ እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ አልሁ ይላል።
⁸ በዚህ ላይ፦ መሥዋዕትንና መባን በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ስለ ኃጢአትም የሚሰዋ መሥዋዕትን አልወደድህም በእርሱም ደስ አላለህም ብሎ፥ እነዚህም እንደ ሕግ የሚቀርቡት ናቸው፥
⁹ ቀጥሎ፦ እነሆ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል። ሁለተኛውንም ሊያቆም የፊተኛውን ይሽራል።
¹⁰ በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።
1ኛ ጴጥሮስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ጴጥሮስ፥ እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ እንዳወቃቸው በመንፈስም እንደሚቀደሱ፥ ይታዘዙና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ይረጩ ዘንድ ለተመረጡት በጳንጦስና በገላትያ በቀጰዶቅያም በእስያም በቢታንያም ለተበተኑ መጻተኞች፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
³-⁵ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋ እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን። የማያረጀውን፥ የማይለወጠውንና፥ የማይጠፋውን፤ በሰማያት ለእኛ እና ለእናንተ ተጠብቆልን ያለውን ለመውረስ፥ በኃላ ዘመን በኃይማኖት ትገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀችው ድኅነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁት፥
⁶ እስከ ዘለዓለም ደስ ይላችኃል፤ ነገር ግን በሚመጣባችሁ ልዩ ልዩ መከራ አሁን ጥቂት ታዝናላችሁ።
ሐዋርያት 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ ይህን በሰሙ ጊዜ በአንድነት ቃላቸውን ወደ እግዚአብሔር ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፦ ሰማዩንና ምድሩን ባሕሩንም በውስጣቸው ያለውን ሁሉ የፈጠርህ እግዚአብሔር ሆይ፥
²⁵ በመንፈስ ቅዱስም በብላቴናህ በአባታችን በዳዊት አፍ፦ አሕዛብ ለምን ተሰበሰቡ? ሕዝቡስ ለምን ከንቱን ነገር ተናገሩ?
²⁶ የምድር ነገሥታት ለምን ተነሡ? አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሲሕው ለምን ዶሐቱ?።
²⁷-²⁸ በቀባኸው በቅዱሱ ልጅህ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከወገኖቻቸውና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ በእውነት በዚች ሃገር ላይ ዶለቱ።
²⁹-³⁰ እጅህና ምክርህ እንዲደረግ የወሰኑትን ይፈጽሙ ዘንድ። አሁንም አቤቱ ትምክህታቸውን ተመልከት፤ ቃልህንም በግልጥ ያስተምሩ ዘንድ ለባሮችህ ስጣቸው። በቅዱሱ ልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሕሙማንን ትፈውስ ዘንድ እጅህን ዘርጋ።
#ምስባክ
ለምንት እንገለጉ አሕዛብ። ወሕዝብኒ ነበቡ ከንቶ። ወተንስኡ ነገሥተ ምድር።
#ትርጉም፦
አሕዛብ ለምን ዶለቱ፥ ወገኖችስ ለምን ከንቱ ይናገራሉ? የምድር ነገሥታት ተነሱ፥
መዝ.2÷1-2
#
ዮሐንስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³² ፈሪሳውያንም ሕዝቡ ስለ እርሱ እንደዚህ ሲያንጐራጕሩ ሰሙ፤ የካህናት አለቆችም ፈሪሳውያም ሊይዙት ሎሌዎችን ላኩ።
³³ ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ ገና ጥቂት ቀን አብሬያችሁ እኖራለሁ ከዚህ በኃላ ወደ ላከኝ እሄዳለሁ።
³⁴ ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም አለ።
³⁵ አይሁድም፦ እርስ በእርሳቸው እንዲህ አሉ፦ እኛ ልናገኘው የማንችል ይህ ወዴት ይሄዳል? ወይስ በግሪክ ሰዎች መካከል ተበትነው ወደሚኖሩት ሊሄድና የግሪክን ሰዎች ሊያስተምር ይሄዳልን?
³⁶ እርሱ፦ ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም የሚለው ይህ ቃል ምንድር ነው?
³⁷ ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ጌታችን ኢየሱስ ቆመና፦ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።
³⁸ በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል።
³⁹ ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ቅዱስ ተናገረ፤ ጌታችን ኢየሱስ ስላልከበረ መንፈስ ቅዱስ ገና አልወረደም ነበርና።
✝️ ቅዳሴ #እግዚእነ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² እኛ የዚህን ዓለም መንፈስ የተቀበልን አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሰጠንን ጸጋ እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሚሆነውን መንፈስ ተቀበልን።
¹³ ይህ ትምህርታችን ከሰው የተገኘ ትምህርት አይደለም፤ የአነጋገር ጥበብም አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስ የገለጠው ትምህርት ነው እንጂ፤ መንፈሳዊ ጥበብም ከመንፈስ ቅዱስ የሚሆነውን መርምረው ለሚያውቁ ለመንፈሳውያን ነው።
¹⁴ ለሥጋዊ ሰው ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ይመስለዋልና፤ አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቅ አይችልም።
¹⁵ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል እርሱን ግን የሚመረምረው የለም።
1ኛ ዮሐንስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ እናንተስ ከቅዱሱ ያገኛችሁት ቅብዐት አላችሁ፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ።
²¹ እውነትን የምታውቁ ስለ ሆናችሁ፥ ውሸትም ሁሉ ከእውነት እንዳልሆነ ስለምታውቁ እንጂ እውነትን እንደማታውቁ አድርጌ አልጽፍላችሁም።
²² ኢየሱስን መሲሕ አይደለም ብሎ ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ሐሳዊ መሲሕ ይህ ነው።
²³ ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ በወልድ የሚያምን ግን አብ አለው።
²⁴ እናንተስ ከመጀመሪያ የሰማችሁት ትምህርት በእናንተ ጸንቶ ይኑር። ቀድሞ የሰማችሁትም ትምህርት በእናንተ ዘንድ ካለ፥ እናንተ በአብና በወልድ ትኖራላችሁ።
²⁵ እርሱም የሰጠን ይህች ተስፋ የዘላለም ሕይወት ናት።
²⁶ ስለሚያስቱአችሁም ይህን ጽፌላችኋለሁ።
²⁷ እናንተ ግን ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅብዐት አለቻችሁ፥ በእናንተ ዘንድም ትኖራለች፤ ማንም ሊያስተምራችሁ አትሹም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ሁሉን ያስተምራችኀል፤ የታመነም ነው፤ ሐሰትም አደለም እንደተማራችሁት በእርሱ ኑሩ።
²⁸ አሁንም፥ ልጆች ሆይ፥ በሚገለጥበት ጊዜ መወደድን እናገኝ ዘንድ፥ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱ የተነሣ እንዳናፍር በእርሱ ጸንታችሁ ኑሩ።
ሐዋርያት 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁹ እኛም በአይሁድ አገርና በኢየሩሳሌም ባደረገው ነገር ሁሉ ምስክሮች ነን፤ እርሱንም በእንጨት ላይ ሰቅለው ገደሉት።
⁴⁰ እግዚአብሔር ግን በሦስተኛው ቀን ከሙታን ለይቶ አስነሣው በግልጥ እንዲታይ አደረገው።
⁴¹ ይኸውም ለሕዝብ ሁሉ አይደለም ነገር ግን በእግዚአብሔር አስቀድሞ ለመረጣቸውና ምስክሮች ለሚሆኑት ብቻ ነው እንጂ፤ የመረጣቸው የተባልንም እኛ ነን፤ ከሙታንም ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን።
⁴² ለሕዝብም እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደ ሆነ እንመሰክር ዘንድ አዘዘን።
⁴³ በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል።
⁴⁴ ጴጥሮስ ይህን ነገር ገና ሲነግራቸው ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ።
⁴⁵ ከጴጥሮስም ጋር የመጡት ከአይሁድ ወገን የሆኑ ምዕመናን ሁሉ ደነገጡ፤ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በአሕዛብ ላይ ወርዷልና።
⁴⁶ በልዩ ልዩ ቋንቋ፥ ሲናገሩ እግዚአብሔርንም ሲያመሰግኑ ሰምተዋቸዋልና።
⁴⁷ ጴጥሮስም፦ እንደ እኛ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኃላ እንግዲህ በውኃ እንዳይጠመቁ ውኃን ሊከለክላቸው የሚችል ማን ነው? አለ።
#የቅዳሴ_ምስባክ👇
ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። ወውስተ ፀሓይ ሤመ ጽላሎቶ።
#ትርጉም፦
ቃላቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ፥ ነገራቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ። በፀሐይ ውስጥ ድንኳኑን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ በመንገዱ እንደሚራመድ አርበኛ ደስ ይለዋል።
መዝ.18፥4-5።
#ወንጌል 👇
ሉቃስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ከዚህም በኋላ ጌታችን ሌሎች ሰባ ሰዎችን መረጠ፥ ሁለት ሁለትም አድርጎ ሊሄድበት ወዳለው ከተማና መንደር በፊቱ ላካቸው።
² ጌታችን ኢየሱስም አላቸውም፦ መከሩ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ ለመከሩ ሠራተኛ ጨምሮ ይልክ ዘንድ ባለመከሩን ለምኑት።
³ ሂዱ፤ እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ።
⁴ ከረጢትም፥ ስልቻም፥ ጫማም ምንም ምን አትያዙ፤ በመንገድም ማንንም ሰላም አትበሉ።
⁵ ወደ ገባችሁበትም ቤት አስቀድማችሁ፦ ለዚህ ቤት ሰዎች ሰላምይሁን በሉ።
⁶ በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር፥ ሰላማችሁ ያድርበታል፤ አለዚያም ሰላማችሁ ይመለስላችኋል።
⁷ በዚያም ቤት ተቀመጡ፤ ከእነርሱ የተገኘውንም ብሉ፤ ጠጡም፤ ለሠራተኛ ዋጋው ይገባዋልና። ከቤት ወደ ቤት አትተላለፉ።
⁸ ወደ ማናቸውም ከተማ ብትገቡ፥ የዚያ ከተማ ሰዎችም ቢቀበሉአችሁ ያቀረቡላችሁን ብሉ፤
⁹ በውስጧም የሚገኙትን ድውያንንም ፈውሱ፦ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ቀረበች በሉአቸው።
¹⁰ ነገር ግን ወደምትገቡባት ከተማ ሁሉ ባይቀበሉአችሁ፥ ወደ አደባባይዋ ወጥታችሁ፦ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ።
¹¹ ከከተማችሁ የተጣበቀብንን ትቢያ እንኳን እናራግፍላችኋለን፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ እንደ ቀረበች ይህን እወቁ በሉ።
✝️ ቅዳሴ #ዮሐንስ(ኀቤከ) ቅዳሴ ነው።
2ኛ ጢሞቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንግዲህ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ።
² ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ።
³ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል።
⁴ የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም።
⁵ ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም።
⁶ የሚደክመው ገበሬ ፍሬውን ከሚበሉት መጀመሪያ እንዲሆን ይገባዋል።
⁷ የምለውን ተመልከት፤ ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ።
⁸ በወንጌል እንደምሰብከው፥ ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤
⁹ ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፥ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም።
¹⁰ ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን መዳን ከዘላለም ክብር ጋር እንዲያገኙ ስለ ተመረጡት በነገር ሁሉ እጸናለሁ።
1ኛ ጴጥሮስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶-⁷ በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።
⁸-⁹ እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።
ሐዋርያት 24
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ እሰግድ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣሁ ከአሥራ ሁለት ቀን እንዳይበልጥ ልታውቀው ትችላለህ።
¹² ከአንድም ስንኳ ስነጋገር ወይም ሕዝብን ስሰበስብ በመቅደስ ቢሆን በምኵራብም ቢሆን በከተማም ቢሆን አላገኙኝም።
¹³ አሁንም ስለሚከሱኝ ያስረዱህ ዘንድ አይችሉም።
¹⁴ ነገር ግን ይህን እመሰክርልሃለሁ፤ በሕጉ ያለውን በነቢያትም የተጻፉትን ሁሉ አምኜ የአባቶቼን አምላክ እነርሱ ኑፋቄ ብለው እንደሚጠሩት መንገድ አመልካለሁ፤
¹⁵ እነዚህም ራሳቸው ደግሞ የሚጠብቁት፥ ጻድቃንም ዓመፀኞችም ከሙታን ይነሡ ዘንድ እንዳላቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ዘንድ አለኝ።
¹⁶ ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።
¹⁷ ከብዙ ዓመትም በኋላ ለሕዝቤ ምጽዋትና መሥዋዕት አደርግ ዘንድ መጣሁ፤
¹⁸ ይህንም ሳደርግ ሳለሁ ሕዝብ ሳይሰበሰብ ሁከትም ሳይሆን በመቅደስ ስነጻ አገኙኝ።
¹⁹ ነገር ግን በእኔ ላይ ነገር ያላቸው እንደ ሆነ፥ በፊትህ መጥተው ይከሱኝ ዘንድ የሚገባቸው ከእስያ የመጡ አንዳንድ አይሁድ አሉ።
²⁰-²¹ ወይም በመካከላቸው ቆሜ፦ ዛሬ ስለ ሙታን መነሣት በፊታችሁ በእኔ ይፈርዱብኛል ብዬ ከጮኽሁት ከዚህ ከአንድ ነገር በቀር፥ በሸንጎ ፊት ቆሜ ሳለሁ በእኔ አንድ ዓመፃ ያገኙ እንደ ሆን እነዚህ ራሳቸው ይናገሩ።
#ምስባክ👇
ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት። ወይድኅኑ ፍቁራኒከ።
#ትርጉም
ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው። ወዳጆችህ እንዲድኑ በቀኝህ አድን፥ አድምጠኝም።
መዝ.59(60)÷4-5
#ወንጌል 📖👇
ማርቆስ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።
¹² ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ። ይገድሉአቸውማል፤
¹³ በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
¹⁴ ነገር ግን በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፥
¹⁵ በሰገነትም ያለ ወደ ቤት አይውረድ ከቤቱም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይግባ፥
¹⁶ በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።
¹⁷ በዚያን ወራትም ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።
¹⁸ ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፤
¹⁹ በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዓይነት ይሆናልና።
²⁰ ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ።
²¹ በዚያን ጊዜም ማንም፦ እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ፥ ወይም፦ እነሆ፥ ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤
²² ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ።
²³ እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ።
²⁴ በዚያን ወራት ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥
²⁵ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ።
²⁶ በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።
²⁷ በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል።
²⁸ ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤
²⁹ እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህን ሁሉ መሆኑን ስታዩ ቀርቦ በደጅ እንደ ሆነ እወቁ።
³⁰ እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።
³¹ ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።
✝️ ቅዳሴ #ባስልዮስ ቅዳሴ ነው።
Reviews channel
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «ኦርቶዶክሳዊ 📖📖📖 መጻሕፍት ✝️✝️✝️» is a Telegram channel in the category «Религия и духовность», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 5.3K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 17.5, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 1.2 ₽, and with 4 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий