
- Main
- Catalog
- Motivation & Self-Development
- Advertising on the Telegram channel «ራስህን መለወጥ»
Advertising on the Telegram channel «ራስህን መለወጥ»
Cryptocurrenices. airdrop. book review. motivation. self development .
Channel statistics
Full statisticschevron_rightበህይወትህ ትዕግሥት ይነሩህ !
አንተ ሀብት እየፈለክ ከሆነ ፤ ሌላ ሰዉ ጤናውን እየፈለገ ነዉ ።
ጤናህን እየፈለክ ከሆነ ፤ ሌላ ሰዉ እየሞተ ነዉ።
አንተ ስልጣንን እየፈለክ ከሆነ ፤ ሌላ ሰዉ አግኝቶ ተጠቅሞበታል፤ አሁን እርሱ ስልጣን የለዉም ።
የቅንጦት መኪና በነዳህ ቁጥር ፤ የሆነ ቦታ ያለ ሰዉ በመኪና አደጋ እየሞተ ነዉ ።
አድስ መኖሪያ ቤት በተገነባ ቁጥር ፤ አድስ መቃብር ከምድር በታች ይቆፈራል።
አንድ ፍራፍሬ በጣልክ ቁጥር ፤ የሆነ ቦታ ያለ ሰዉ ለመኖር ፍራፋሬ እየለቀመ ነዉ ።
ምግብን ወደ ቆሻሻ መጣያ በጣልክ ቁጥር ፤ ሌላ ሰዉ የምበላዉን ትሪፍራፊ እየፈለገ ነዉ ።
ፈጣሪ አሁን ያለህን ሁኔታ እንዲያሻሽልልህ ወይም እንዲለዉጥልህ በጠየቅክ ቁጥር ፤ ሌላ ሰዉ አሁን ወዳለህበት ሁኔታ ለመድረስ እየጸለየ ነዉ ።
በፕላኔቷ ላይ ላለ እያንዳንዱ ፈገግታ ፤ በሌላ የፕላኔቷ ክፍል የእምባ ጠብታ እየፈሰሰ ነዉ ።
ለእያንዳንዱ የልጅ መወለድ ብስራት ፤ የቀብር መርዶ አለ።
ሽንት ቤት በገባህ ቁጥር ወይም ዉሃ በጠጣህ ቁጥር፤ አንድ ሰዉ ለዝሁ አላማ አርቲፊሻል ተገጥሞለት እየተጠቀመ መሆኑን አስታዉስ ።
ስለዚህ ሁልጊዜ አመስጋኝ ሁን🙏❤
መልካም ቀን❤❤
➡Telegram
@rasehnmelewet33
ጊዜ እያለን ልክ እንደሌለው የምንኖረው፣ ያንን ያለንን ጊዜ በሚገባ የማንጠቀምበት ከሆነ ነው፡፡
ጊዜያችን ሲባክን ደግሞ ባለን ጊዜ ሰርተን ማግኘት የሚገባንን ገንዘብም ሆነ ሌሎች የገንዘብ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች አብረው ይባክናሉ፡፡ ስለሆነም፣ ጊዜ ባከነ ማለት ሁሉም ነገር ባከነ ማለት ነው፡፡ ጊዜ አተረፍን ማለት ደግሞ ብዙ ነገር አተረፍን ማለት ነው፡፡
ማንኛውንም ነገር የምናተርፈው በቅድሚያ ጊዜያችንን ስናተርፍ ነው፡፡ አንድ ሰው ጊዜውን በትክክል ሲጠቀምና ጊዜ ሲተርፈው፣ ተጨማሪ ገንዘብን ለማትረፍ የማሰቢያ እና የመስሪያ ጊዜ ያገኛል፡፡
የብዙ ነገራችን መዘባረቅ መነሻው ጊዜያችንን በትክክል ስለማንጠቀም ይሆን?
ዶ/ር እዮብ ማሞ
➡Telegram
@rasehnmelewet33
ኦሾ
መልካም ቀን 🙏
➡Telegram
@rasehnmelewet33
፦በጣም ዝምተኛና እህል የማያበላሽ ሰውን የማይተናኮል የወፍ ዝርያ ነው
፦እባብና ሌሎች በመርዝ የሚገድሉ ነፍሳት መርዛቸው አይጎዳውም
፦የሚበላውን ለማግኘት ካልሆነ በስተቀር ዝም ብሎ እንደሌሎች አእዋፋት ብዙ ቦታ ላይ አይታይም
፦ሲራመድ አንገቱን ደፍቶ መሬት መሬት እያየ ነው ይህም የትህትና ምሳሌ ነው ይባላል
፦ማነኛውንም ግዳይ ሲጥል ከመጉረሱ በፊት ወደ ሰማይ ቀና ይላል (አመስግኖ እየበላ ነው ይባላል
፦ሲራመዱ ሴትና ወንዱ ሁለት ሁለት ሆነው በፍጹም አይነጣጠሉም ብቻውን ከታየ ጓደኛዋ ሞቷል ትዳሯ ወይንም ትዳሩ ፈርሷል ማለት ነው ከዚያም በኋላ በፍጹም ከሌላ እርኩም ጋር ግንኙነት አይኖረውም እንቁላል ጥለው ለመቀፍቀፍ(ለመፈልፈል)አርባ ቀን ይወስድባቸዋል ጫጩት ለማሳደግ 3 ዓመት ሙሉ በአንድ ላይ ይደክማሉ ይህም የጥሩ ባለትዳር ምሳሌ ነው ይባላል
፦አንድ እርኩም እርኩም ከ50 እስከ ሰባ ሰማንያ ዓመት በሕይወት እንደሚኖር ሳይንስ ያረጋገጠ ሲሆን በአፈ ታሪክ ግን በመቶዎች የሚቆጠር ዘመንን ይኖራል ይባላል
በሁለት እርኩሞች መሃል ማለፍ እድሜን ያስረዝማል ይባላል ሥጋቸው ከማይበላ አእዋፋት መካከል ቢሆንም የእርኩም ሥጋ የበላ ሰው ቶሎ አያረጅምም ስለሚባል እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች በሽምግልና ዘመናቸው እንደ ወጣት ሲሆኑ እገሌማ የእርኩም ሥጋ በልቷል ይባላል
፦እርኩም እንዲህ መልኩ ጥቁር ሆኖ እንኳን ሲታይ ግርማ ሞገስና ደስ የሚል ነገር አለው
እናልህ ወዳጄ አንተም እንደ እርኩም ከመብላትህ በፊት አመስግን በሕይወትህ ስክነት የሚባል ነገር ይኑርህ ለጓደኝነት ቦታ ይኑርህ ለትዳርህ ከእርኩም በላይ ታማኝ ሁን
ማንንም የማትተናኮል የዋህና ቸር ሁን ከራስህ ሕይወት ውጪ ማንንም መጥቀም ባትችል እንኳን ማንንም አትጉዳ
ማን ያውቃል ከእርኩሙ በላይ እድሜህን ያረዝምልሃል የማንም መርዛማ ነገር እንዳይጎዳህ ያደርግሃል ግርማ ሞገስና ክብርን ያለብስሃል
እንደ እርኩም ትሁት ሰብእናን ገንዘብ አድርግ
ከእርኩሙ ባንበልጥ እንኳን እንደ እርኩሙ መኖር እንዴት ያቅተናል?
የህይወት ፍልስፍና
➡Telegram
@rasehnmelewet33
"በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ፤ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ፤ ወይም
ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ፤ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ
ልታገኘው ትችላለህ፤ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ
፣ ይችላሉ።
"በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም
ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው
አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ
ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።
"ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ
በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"
አንድ ነገር ልንገራችሁ፥ በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ፤ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡልችሀል፤
መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑችሁዋል። ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆናቹኋል፤ ምርጥ ሰዎች ትዝታ
ይሆኑላችሁዋል።
➡Telegram
@rasehnmelewet33
በገመድ አልባ የጆሮ ማዳመጫዎች ደህንነት ላይ በቅርቡ የተደረገ አንድ ጥናት፣ የብሉቱዝ ጨረር በሰው አካል ላይ ስለሚያስከትለው ውጤት ክርክሩን እንደገና ቀስቅሷል። ጥናቱ እንዳመለከተው፣ እንደ ኤርፖድስ (AirPods) ያሉ ገመድ አልባ ማዳመጫዎች ከባህላዊ ባለገመድ የጆሮ ማዳመጫዎች እስከ 150 እጥፍ የሚበልጥ የኤሌክትሮማግኔቲክ ጨረር (electromagnetic radiation) ያመነጫሉ — ይህ በተለይ በየቀኑ ለሰዓታት ለሚጠቀሙ ሰዎች አሳሳቢ ነው። እያንዳንዱ መሳሪያ በራሱ ዝቅተኛ መጠን ያለው ጨረር ቢያመነጭም፣ ከጭንቅላትና ከአንጎል ጋር ያለው የማያቋርጥ ቅርበት ስለሚያስከትለው የረጅም ጊዜ ተጋላጭነት ጥያቄዎችን ያስነሳል።
የብሉቱዝ ቴክኖሎጂ የሚሰራው የድምፅ ሞገዶችን በሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ ኤሌክትሮማግኔቲክ ፊልድስ (RF-EMFs) በማስተላለፍ ነው። እነዚህ ምልክቶች በጆሮና በጭንቅላት አካባቢ በሚገኙ ስስ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ ያልፋሉ፤ እነዚህም ለሙቀት-አማቂና ሙቀት-አልባ የጨረር ውጤቶች በቀላሉ ተጋላጭ ናቸው። ምንም እንኳን አሁን ያሉት የደህንነት ገደቦች በሰውነት ክፍሎች ላይ ሙቀት እንዳይፈጠር ለመከላከል ላይ የተመሰረቱ ቢሆኑም፣ አዳዲስ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ለረጅም ጊዜ ለዝቅተኛ ጨረር መጋለጥ በነርቭ ሥርዓትና በሴሎች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። በአንፃሩ፣ ባለገመድ የጆሮ ማዳመጫዎች ድምፅን የሚያስተላልፉት በኤሌክትሮማግኔቲክ ሳይሆን በሜካኒካል መንገድ በመሆኑ ከጨረር ነፃ ናቸው።
የጤና ባለሙያዎች ምቾትን ሳይሰዉ ለጨረር መጋለጥን ለመቀነስ ቀላልና ተግባራዊ እርምጃዎችን ይመክራሉ። እነዚህም፦
* ለረጅም ጊዜ ያለማቋረጥ ማዳመጥን መገደብ፣
* ጥቅም ላይ በማይውሉበት ጊዜ የጆሮ ማዳመጫዎችን አውጥቶ ማስቀመጥ፣
* ለረጅም ሰዓት በሚሰሩበት ጊዜ ወደ ባለገመድ ወይም ከጆሮ በላይ የሚደረጉ ማዳመጫዎችን መቀየር፣ እንዲሁም
* ለስልክ ጥሪዎች የስፒከር ሁነታን (speaker mode) መጠቀምን ያካትታሉ።
የገመድ አልባ ቴክኖሎጂ ከዕለት ተዕለት ህይወታችን ጋር የማይነጣጠል እየሆነ ሲመጣ፣ ዋናው መፍትሔው ልክን ማወቅና ጥንቃቄ ማድረግ ነው — ይህም ፈጠራን እየተቀበሉ የሰውነትን ወሳኝ አካል ሊደርሱ ከሚችሉ ተደራራቢ ውጤቶች መጠበቅ ነው።
➡Telegram
@rasehnmelewet33
ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው፣
ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር፣ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም።
➋. የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነት አይገልፅም!
ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው፣ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል ፣ ለሁሉም ጊዜ አለውና ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና።
➌. መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል!
ጊዜህ ሲደርስ መኪናዎች ወይም ‘አውሮፕላን’ ትገዛለህ ፣ ያውም ለመኖር አስፈላጊ ከሆነ ፣ ደግሞስ እንዴት እንደገዛው የት ታውቃለህ?
እርሱን ተወውና በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው።
➍. ለሰዎች ለደስታቸው እንጂ ለሀዘናቸው መንስዔ አትሁን!
►በሰዎች ደስታ→ደስ ይበልህ!
►ለሰዎች→ክፉ አትመኝ፣
►በሃዘናቸውም→አብረህ እዘን፣
►ሰዎች ሲያዝኑ→አትደሰት፣
►ሰው ከሆንክ→የሰው ነገር ይሰማህ፣
ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ጋር ተደሰት ማለት አይደለም። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋ ሁን፣ አስተውል።
➎. በጊዜ ስራ እንጂ ጊዜ ባንተ ላይ አይስራ!
ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም። አንተንም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት፣ በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን።
➏. መክሊትህን ፈልግ!
►ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ?
►ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁና።
አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለም እየኖረች ያለችው። በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት። አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ ፈልገውና አውጣው።
►ቁፋሮ ነው ወይስ ቾክ ይዞ ማስተማር ነው ወይስ መምከር መገሰፅ ነው?
►ቆንጆ ሽሮ ወጥ እየሰሩ መሸጥ ነው?
►የድንጋይ ቅርፅ (ኮብልስቶን) እየሰሩ መኖር ነው?
►ምንድነው ???
እባክህ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው፣
"ምን ይሻለኛል ?" እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ። በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው።
➐. መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን እንዳልሆነ አስተውል!
ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀየር ብቃት አለው። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል።
-መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው፣
-መጥፎነት ከአንተ ይራቅ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም።
➑. "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን አባባል አስታውስ!
የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል። ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ ራስህን አትሸውድ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ፣ ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።
➒. ለራስህ ስትል መልካም ሁን፣ በጎውንም አስብ!
ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም።
➓. በማንም ላይ አትፍረድ!
►የመፍረድ ኃላፊነት በፍፁም የለህም።
►ፍርድ የፈጣሪ ነው።
►ለመፍረድ እንከን አልባ መሆን ያስፈልጋል፣
►ፍጥረት ሁሉ ፍጥረት በመሆኑ ብቻ እንከን አለበት ፣ ጎደሎ አለበት።
►የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል።
➊➊. መልካም ጓደኛ ከፈጣሪ የሚሰጥ ጸጋ መሆኑን አትርሳ!
የጓደኛህን ስሜት ለመረዳት ሞክር፣ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት፣ አበረታታው፣ እንደማይጠቅም አትንገረው፣ ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን።
➊➋. መልካም ጓደኛ ሁን!
መልካም ጓደኛ፦ የማይቀና አሳቢና መካሪ ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ተባርከሃል፣ ታድለሃል። ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ መልካም በመሆን ጀምር ፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ። ነገር ግን ያለምክንያት ከሄድክ በምክንያት አትምጣ። በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ በሕይወትህ ውስጥ ጉዳት እንጂ ጥቅም የሌላቸው ሰዎች በራሳቸው ሰዓት ከሕይወትህ ሲወጡ እጅግ መታደል ነው።
➊➌. ከአጓጉል ሀሳብና ጭንቀት ራስህን ጠብቅ!
ያለ መጠን ማሰብ ጭንቀትንና፣ ሀዘንን ያስከትላል። ከአቅምህ ከምትችለው በላይ አታስብ፣ መመለስ በማትችለው ነገር ላይ አትወጠር፣ የተመለሱ ነገሮችህ ላይ ትኩረት አታድርግ፣ አንዳንድ መልሶች በድጋሚ ጥያቄወች ሆነው እንደሚመጡ አትዘንጋ። ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር።
➊➍. ደግነት አይለይህ!
ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው፣ "ያስከፍላል" ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ። እናም ዘወትር ደግ ሁን። ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም ፣ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ በረከታቸውና ሰላማቸው ልክ የለውም።
➊➎. ደስታህንና ሰላምህን ካንተ ዘንድ አኑራቸው!
ደስታህንና ሰላምህን የሆነ ሰው ወይም ነገር ላይ አታስቀምጥ!
ያ ነገር ወይም ሰው ከአጠገብህ ሲርቅ ወይም ሲጠፋ ደስታህም አብሮ ይጠፋል። ደስታና ሰላም በአንተ ውስጥ ናቸው።
►በራስህ በአፈጣጠርህ→ደስ ይበልህ፣
►ውለህ በመግባትህ→ደስ ይበልህ፣
►በአለህ ትንሽ ነገር→ደስ ይበልህ።
➊➏. ፍቅርን ፈልጋት!
♡ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ አይኑርህ።
♡በመውደድ የተጠመደ ሰው ለመጥላት ጊዜ የለውም።
➊➐. ዘመንህን ከርኩሰት ጠብቀው!
እድሜህን በተመለከተ፣ የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ካለፈው ከተቃጠለው ጊዜህ ይልቅ ወደፊት የምትኖረው ብዙ ነው። ዋናው ደግሞ የኖርክበት የእድሜ ብዛት ሳይሆን በኖርክበት ዘመን ያሳየኸው መልካምነትና የሰራኸው ደግነት ነው።
➊➑. "መኖርህ ማንንም ካልጠቀመ መሞትህ ማንንም አይጎዳም" የሚለውን አባባል አስታውስ!
ይህም ማለት የሕይወት ዓላማ ሊኖርህ ይገባል ማለት ነው። የየኖሩበት እድሜ ትንሹም ቢሆን በቂ ነው ይባላል። የማቱሳላ እድሜው እንጅ የሰራው ስራ አይታወቅም፣ "ኖሮ ሞተ" ብቻ ከመባል ፈጣሪ አምላክ ይጠብቅህ፣
መኖርህ ሰዎችን ካልጠቀመ መሞትህ ላይጎዳቸው ይችላል፣ መኖር ማለት መጥቀም መጠቃቀም ነው። ለራስ መኖር፣ ለሌሎች መኖር።
➊➒. ከማማረር ማመስገንን ልመድ!
የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ረስተን፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ ነው። ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል። በማማረር በረከት የለም።
የቴሌግራም ቻናላችን 👇👇ቤተሰብ ሁኑ
@rasehnmelewet33
1. እኔ ማን ነኝ፤
2.ለምን ወደዚህ አለም መጣሁ ፤
3.ቀጣይ ወዴት ነው ምሔደው ፤ እነዚህን 3 ጥያቄዎች
ጠይቆ መልስ ያገኘ ሰው የአለማችን አዊቂ ሰው ይባላል ይላሉ ።።እውነት ነው ስንቶቻችን አኒዚን 3 ጥያቄዎች መልስ አግንተን ተቀምጠናል ወገን ፤እሰኪ እራሳችንን እናብብ ፤ራሱን ያነበበ እና ያወቀ ሰዉ መጀመሪያ ለራሱ፤ ቀጥሎ ለቤተሰብ ፤ከዚያም ለሀገር ይተርፋል ።ሰናይ ጊዜ ተመኘሁ ተመሳሳይ መረጃ እንዲዳርስዎ follow ያርጉ፡፡
➡Telegram
@rasehnmelewet33
ምንም ከሌለው ጥበበኛ ጋር ተቀመጥኩ፤ ነገር ግን ቃሉ ከሰማሁት ሁሉ በላይ ባለጠጋ ነው። ከሚናገረው በላይ ዝም ያለ ነበር። ቢሆንም ሲናገር እያንዳንዱ ቃል ለተዘጋ በር ቁልፍ ያበጃል። እኔና ጓደኛዬን እንዲህ አለን፦“ህይወት የሚያስፈልጋት ብዙ ገንዘብ ሳይሆን ጥልቅ ማስተዋል ነው።” ብዙ ነገር ባይኖረንም እንኳን የምናከብረውን ህይወት ለመገንባት 10 ወርቃማ ህጎች እነሆ፦
1.ለሁሉም ሰው ክብር ስጡ፤ ነገር ግን ማንም እንዲረግጣችሁ አትፍቀዱ!።
2.ምኞታችሁን በማይረዱ ሰዎች ፊት ስለ እቅዳችሁ አታውሩ።
3.በንዴት ጊዜ ዝም ማለት የበሰለ ሰው ኃይል ነው።
4.በየትኛውም ግንኙነት መቋረጥ ውስጥ ሁሌም ክብራችሁን አስቀድሙ!።
5.እራሳችሁን ብዙ አታመጻድቁ፤ ማድረግ የሚፈልጉ ሳያብራሩ ያደርጋሉ።
6.በዝምታ ውለታ ዋሉ ምስጋናን ለማግኘት አትጓጉ።
7.መልካም እንደሆነ ከሚያስመስል ሰው ተጠንቀቁ።
8.ስትበሉ አታዉሩ፤ ከአፍ የሚነጥቅ አውሬ የገዛ ወዳጃችን ነው።
9.ጸጥ ማለት አለማወቅ ማለት አይደለም፤ ጥበበኝነት ጫጫታ አያስፈልገውም።
10.ዋጋችሁን ሰው እስኪተምነው አትጠብቁ፤ የራሳችሁን ክብር በራሳችሁ ገንቡ።
እናም ሰው ሆይ ክብር በመልክ አይኖርም፤ ነገር ግን በህግ ይገዛል። ተጽህኖ ብዙ ወሬ አያመጣውም ይልቁኑም የተግባራችንን ጽናት ይመዝናል።
#ዘምአድ
➡Telegram
@rasehnmelewet33
Reviews channel
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «ራስህን መለወጥ» is a Telegram channel in the category «Мотивация и саморазвитие», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 2.6K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 6.1, with 0 reviews and an average score of 0.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 1.2 ₽, and with 0 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий