
Monetize Telegram Mini App with Telega.io
Connect your app, set CPM, and watch your revenue grow!
Start monetizing
17.6

Advertising on the Telegram channel «የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር»
5.0
Religion & Spirituality
Language:
English
38
1
Content creater ,Video editing ,freelance,photo editing,upwork,crypto currency ,
posting sing song and post any advertisements
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$3.60$3.60local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
play_circleVideo preview is unavailable
(የደብረታቦር መዝሙር በዜማ )
ቡሄ በሉ ...
ቡሄ በሉ *2* ልጆች ሁሉ የኛማ ጌታ
የዓለም ፈጣሪ የሰላም አምላክ
ትሁት መሀሪ በደብረ ታቦር የተገለጠው
ፊቱ እንደ ፀሐይ በርቶ የታየው
ልብሱ እንደብርሃን ያንፀባረቀው
ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና *2*
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን *2*
ያዕቆብ ዮሐንስ እንዲሁም ጴጥሮስ
አምላክን አዩት ሙሴ ኤልያስ
አባቱም አለ ልጄን ስሙት
ቃሌ ነውና የወለድኩት
ታቦር አርሞንኤም ብርሃን ታየባቸው
ከቅዱስ ተራራ ስምህ ደስ አላቸው
ሰላም ሰላም የታቦር ተራራ
ብርሀነ መለኮት ባንቺ ላይ አበራ
በተዋህዶ ወልድ የከበረው
የእግዚአብሔር አብ ልጅ
ወልደማርያም ነው
ቡሄ በሉ *2* የአዳም ልጆች
ብርሃንን ተቀበሉ
አባቴ ቤት አለኝ ለከት
እናቴ ቤት አለኝ ለከት
አጎቴም ቤት አለኝ ለከት
ተከምሯል እንደ ኩበት
የዓመት ልምዳችን ከጥንት የመጣው
ከተከመረው ከመሶቡ ይውጣ
ከደብረ ታቦር ጌታ ሰለመጣ
የተጋገረው ሙልሙሉ ይምጣ
እንዲሁ እንዳላችሁ በፍቅር አይለያችሁ
ላመቱ በሰላም በፍቅር ያድርሳችሁ
ክርስቶስ በቀኙ በፍቅር ያቁማችሁ
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር ያድርጋችሁ
እንዲሁ እንዳለን በፍቅር አይለየን
ለዓመቱ በሰላም በፍቅር ያድርሰን
አማኑኤል በቀኙ በፍቅር ያቁመን
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር ያድርገን
የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት *2* ይግባ በረከት (2)
እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
ባህላችንን የአባቶች ትውፊት (3)
@orthodox_tewahdo19
@orthodox_tewahdo19
@orthodox_tewahdo19
1457
14:44
18.08.2025
play_circleVideo preview is unavailable
ታቦር አበራታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና እንቅልፍ የለንም ታላቅ ነጎድጕድ ሆኗልና አነቃን ለምስጋና ሙሴም የቀደመው ሰዉ ኤልያስ ኃይለኛው ተገኝተዋል በታቦር ምስክርህ ሆነው እኛም ከገናናው ክብር ያባቱን ቃል ሰምተናል በረዶ ሆኗል ልብሱ እፁብ እፁብ ብለናል አዝ= = = = = ቃል ገብተህልኝ ነበር ልታሳየኝ ክብርህን ንገስ ከሞት ገስግሰህ አይቸሃለሁ አሁን የሳት ፈረሶች አሉህ ታዋጊው የኔ ጌታ አርሙኒየም ደስ አለው ሲሳራን ስለመታ አዝ= = = = = እጠብቅሃለሁኝ በምታልፍበት ቆሜ መብራቶቼን አብርቼ ነጩን ልብስ ተሸልሜ የዳዊት ልጆ ሆይ ግባ ኢየሱስ ወደቤቴ ጵንኤል እልሀለሁ ድናለች ሰውነቴ አዝ= = = = = ሁሉንም ብታከብር ሁሉንም ብትምረው ማነው ቸርነትህን የሚከለክለው ጠዋትም የተጠራ አምሽቶ የገባው ሆነዋል ባለዋጋ ከበዛው ስጦታው አዝ= = = = = የረዳኸው ይናገራል ያሰበከው በሕይወቱ አቤነዘር እያለ ይዘምር ባንደበቱ በደስታዬም ቀን አለህ አይሃለሁ ከጎኔ ከኔ ጋር አልቅሰሃል አሳዝኖህ ሀዘኔ @orthodox_tewahdo19 @orthodox_tewahdo19 @orthodox_tewahdo19
1388
14:49
18.08.2025
✞ ሃሌ ሉያ አንተ ሰው ሆይ ✞
ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ (፬)
ቡሄ መድረሱን ሰምተሃል ወይ
ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ
መስማቱንማ ሰምቼ ነበር
ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ
ከዚያ ቢያደርሰኝ ልዑል እግዚአብሔር
ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ
እናቴ ሆይ.......... ሆ
ይህን ባየሻ ........ሆ
በቁርማ ዳቦ .......ሆ
ሲጥለኝ ውሻ........ሆ
ደጓ ጫማዋን ......ሆ
አውልቃዋለች.......ሆ
ውሃ ሲጠማ.........ሆ
አጠጥታዋለች......ሆ
የስዋ ውዳሴ .......ሆ
ሆኖኛል ውይን ......ሆ
ዘሬም ብዘምር ......ሆ
እኖራለሁኝ ...........ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (፪)
በእምነት እንውጣ .ሆ
ከተራራው ላይ......ሆ
ይታይ ብርሃኑ........ሆ
ክብሩ ኤልሻዳይ....ሆ
ሙሴን እንጠይቅ...ሆ
የጥንቱን ነገር .......ሆ
ምን እንደሚለው ...ሆ
ጌታን ሲያናግር......ሆ
ድምጹን እንስማ ....ሆ
እንደ ትሁትነቱ.......ሆ
እንቀበለው ..........ሳ
እኛም በትሩን .......ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (፪)
ተቁኙለት በልልታ ላዳኙ ጌታ(፪)
ተራራውማ ..........ሆ
ነውና አምሳል.......ሆ
ለቤተ ክርስቲያን...ሆ
መንበረ ልዑል........ሆ
ወጥተን እንጠይቅ .....ሆ
ኤልያስን.............ሆ
እንድንዳስሰው.....ሆ
ጸጓራር ክንዱን....ሆ
ሰማይ በትለጉም...ሆ
ባህር ቢከፍል.......ሆ
እሳት ብታወርድ.....ሆ
ጠላትም ቢርድ......ሆ
በሰረገላ ..............ሆ
የተነጠከው...........ሆ
ይህ ሁሉ ክብር .....ሆ
በማን ስልጣን ነው....ሆ
ለሁላችን መልካም ነው በዚህ መኖር(፪)
የእመብርሃን .........ሆ
የምዬ ልጅ............ሆ
ተጥሎ ላይቀር .....ሆ
ተረስቶ ደጅ...........ሆ
ሰአሊ ለነ .............ሆ
ባለበት
@orthodox_tewahdo19
@orthodox_tewahdo19
@orthodox_tewahdo19
1325
15:01
18.08.2025
✞ ሆያ ሆዬ ✞
ሆያ ሆዬ.........ሆ ሆያ ሆዬ.........ሆ ሆያ ሆዬ.........ሆ ሆያ ሆዬ.........ሆእዚያ ማዶ..............ሆ ምን ይታያል............ሆ ታቦር ተራራ.............ሆ ብርሃን ልብሷል........ሆ ጌታ ቀሚሱ.............ሆ ያፀባርቃል...............ሆ በክብር ውበት..........ሆ በግርማ ቆሟል.........ሆ ሆያ ሆዬ በሉ ክርሲቲያኖች በሙሉ( ፪) አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሆያ ሆዬ.......ሆ ሆያ ሆዬ.......ሆ ሆያ ሆዬ.......ሆ ሆያ ሆዬ........ሆጴጥሮስ በግርማው..........ሆ እጅግ ደንግጦ ................ሆ መሬት ወደቀ ...................ሆ እራሱን ስቶ .....................ሆ ኤልያስ ሙሴ...................ሆ መጡ ከፊቱ.....................ሆ የእግዚአብሔርን ልጅ..........ሆ ኑ ተመልከቱ.....................ሆ ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ(፪) አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሆያ ሆዬ.......ሆ ሆያ ሆዬ.......ሆ ሆያ ሆዬ.......ሆ ሆያ ሆዬ.......ሆአብ በሰማያት..........ሆ ድምፁን አሰማ.........ሆ ብፁል እንበል .........ሆ እሱን እንስማ...........ሆ በፍቅሩ ብርሃን.........ሆ እንዲያደምቀን.........ሆ እንቅረብ ፊቱ...........ሆ ስሙን አውቀን.........ሆ ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ (፪) አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሆያ ሆዬ..........ሆ ሆያ ሆዬ..........ሆ ሆያ ሆዬ..........ሆ ሆያ ሆዬ..........ሆበደብረ ፂዮን..............ሆ ህዝቡን ይጠራል.........ሆ በዚህ በግርማው.........ሆ ዳግም ይመጣል..........ሆ ከሙሴ ጋራ................ሆ ከኤልያስ...................ሆ ያቁመን ቀኙ................ሆ እኛን በነፍስ................ሆ ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ (፪) አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሆያ ሆዬ..........ሆ ሆያ ሆዬ..........ሆ ሆያ ሆዬ..........ሆ ሆያ ሆዬ..........ሆየሙሴ ጌታ.............ሆ ሙሴ ነው ሲሉ.........ሆ እነ ኤልያስ...............ሆ ነብይ እያሉ..............ሆ አይሁድ ቢስቱ..........ሆ ቢዋሹበት...............ሆ ኤልያስ ሙሴ..........ሆ መሰከሩለት............ሆ ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ(፪) አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሆያ ሆዬ..........ሆ ሆያ ሆዬ..........ሆ ሆያ ሆዬ..........ሆ ሆያ ሆዬ..........ሆጴጥሮስ በግርማው........ሆ እጅግ ደንግጦ...............ሆ መሬት ወደቀ..................ሆ እራሱን ስቶ....................ሆ ኤልያስ ሙሴ.................ሆ መጡ ከፊቱ...................ሆ የእግዚአብሔርን ልጅ........ሆ ኑ ተመልከቱ...................ሆ ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ(፪) አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሆያ ሆዬ..........ሆ ሆያ ሆዬ..........ሆ ሆያ ሆዬ..........ሆ ሆያ ሆዬ..........ሆ የዓመት ክብራችን..........ሆ ከጥንት የመጣ.............ሆ የቡሄ ለታ....................ሆ ችቦ ሲወጣ.................ሆ ከእማምዬ ቤት.............ሆ ሙል ሙሉ ይምጣ .......ሆ ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ (፪) አመት አውዳመት.......... ድገምና ዓመት ......... ድገምና ዓመት አውዳመት.......... ድገምና ዓመት ......... ድገምና ያአባብዬን ቤት.......... ድገምና ዓመት ......... ድገምና ሰላም ይሙላበት.......... ድገምና ዓመት ......... ድገምና የእማምዬን ቤት.......... ድገምና ዓመት ......... ድገምና ፍቅር ይሙላበት.......... ድገምና ዓመት ......... ድ
ገምና ክበር በንሰሐ ክበር በጸሎት የነ አባብዬን ቤት ጌታ ይግባበት ክበር በንሰሐ ክበር በጸሎት የነ እማምዬን ቤት ጌታ ይግባበት ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE @orthodox_tewahdo19 @orthodox_tewahdo19 @orthodox_tewahdo19 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
1422
15:01
18.08.2025
✞ ቡሄ በሉ ✞
ቡሄ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ ....ሆሆ
ሲገለፅ ብርሀኑ......................ሆሆ
በታቦር በዚያ በተራራ. .............ሆሆ
ክርስቶስ ሲያበራ....................ሆሆ
ተገልጦ አየን ሚሥጢሩን..........ሆሆ
የተዋሕዶን...........................ሆሆ
ቡሄ በሉ ሕፃናት በሙሉ............ሆሆ
ሲገለፅ ብርሀኑ......................ሆሆ
በታቦር በዚያ በተራራ...............ሆሆ
ክርስቶስ ሲያበራ....................ሆሆ
ተገልፆ አየን ሚሥጢሩን............ሆሆ
የተዋሕዶን............................ሆሆ
አድርሶን ለዓመቱ መጣን ከቤቱ (፪)
በፍቅር በደስታ በሩን ክፈቱ (፪)
ሆያ ሆዬ.........ሆ (፬)
ሀለቱን ነብያት................ሆ
ሦስቱን ሐዋርያት............ሆ
ተመርጠው አዩ..............ሆ
ይህንን እውነት...............ሆ
ያበራ ነበር....................ሆ
እንደ ፀሐይ...................ሆ
በደብረ ታቦር ................ሆ
ጌታ ሲታይ...................ሆ
አድርሶን ለዓመቱ መጣን ከቤቱ (፪)
በፍቅር በደስታ በሩን ክፈቱ (፪)
ሆያ ሆዬ..........ሆ (፬)
ይህንን ያዩ..................ሆ
የጌታን መንፈስ.............ሆ
ያዕቆብ ዩሐንስ..............ሆ
ሐዋርያው ጲጥሮስ.........ሆ
እንስራ አሉ...................ሆ
ሦስት ዳስን..................ሆ
መልካም ነዉ እና............ሆ
እዚ እንሁን....................ሆ
አድርሶን ለአመቱ መጣን ከቤቱ (፪)
በፍቅር በደስታ በሩን ክፈቱ (፪)
ሆያ ሆዬ........ሆ (፬)
አብ ከሰማያት................ሆ
ድምፁን አሰማ...............ሆ
በጉም በጭጋግ.............ሆ
ጋርዶ ደመና..................ሆ
የምወደው ልጄ..............ሆ
ይህ ነው አለ...............ሆ
እድንሰማው..................ሆ
አብ መስከረ..................ሆ
በፍቅር በደስታ ዘምር ለጌታ (፪)
ሆያ ሆዬ......ሆ (፬)
ከባሕላችን.................ሆ
የኢትዮጵያ.................ሆ
ቡሄ ነው አንዱ............ሆ
ለአለም ማሳያ............ሆ
ከሀገር ልብሱ.............ሆ
የጢሱ ሽታ................ሆ
ይናፍቀናል................ሆ
ቡሄ እስኪመጣ..........ሆ
አድርሶን ለዓመቱ መጣን ከቤቱ (፪)
በፍቅር በደስታ ዘምር ለጌታ (፪)
ሃሌ በል ሃሌ የተዋሕዶ ልጅ (፪)
ይህንን ምሥጢር ለዓለም አውጅ
እግዚአብሔር ነው የእግዚአብሔር ልጅ
ወንጌሉን ገልጠን ዘመኑን እንዋጅ
ዓመት አውዳመት........ ድገምእና
ዓመት...................... ድገምእና
ደግሞ የዛሬ አመት........ድገምእና
ዓመት........................ድገምእና
አድርሶን በሕይወት........ድገምእና
ዓመት........................ ድገምእና
እናንተም ሳትሞቱ.........ድገምእና
ዓመት.........................ድገምእና
እኛም ሳንሞት.............ድገምእና
ዓመት.......................ድገምእና
ለማመስገን ያብቃን.......ድገምእና
ዓመት......................ድገምእና
ደግሞ በዚህ ቤት..........ድገምእና
ዓመት......................ድገምእና
እንዲሁ እንዳላችሁ............አሜን
አይለያችሁ.....................አሜን
ለዓመቱ በሰላም ..............አሜን
ያድርሳችሁ.....................አሜን
አገር ሰላም ይሁን..............አሜን
ፍቅር ይስጣችሁ...............አሜን
የተወለዱትን ...................አሜን
ባርኮላችሁ......................አሜን
ሕዝቡን ከደብሩ................አሜን
ሳይለየው........................አሜን
ታቦት ከመንበሩ................አሜን
ያኑረው...........................አሜን
ሀገር ሰላም ሕዝቧ ጤና ይሁን በሙላ
ዳሯን እሳት መኃሏን ገነት አርጎ የእኛ አባት
ይጠብቀን እድሜ ሰጥቶ ከዓመት እሰከ ዓመት
ያድርግልን መጪን ጊዜ ዘመነ ምሕረት
ክበር በፍቅር ጽና በእምነት እንድታገኝ ምህረት
ጠብቅ ሐብትህን ትውፊት ባህልህን የአባቶችን [፪]
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
@orthodox_tewahdo19
@orthodox_tewahdo19
@orthodox_tewahdo19
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
1442
15:01
18.08.2025
play_circleVideo preview is unavailable
✞ ሆያ ሆዬ ✞
ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ
ሆያ ሆዬ ሆያ ሆዬ (፪)
ተገለፀ.......ሆ
በታቦር ላይ......ሆ
ብርሃኑን...... ሆ
ለእኛ ሊያሳይ...... ሆ
የምሥራች...... ሆ
እልል በሉ...... ሆ
ለሁሉ አባት...... ሆ
ለአዳኙ...... ሆ
በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን ታየባቸው [፪]
አዝ▸▸▸▸▸▸▸►
ፅልመት ጠፍቶ......ሆ
ብርሀን ሆነ ...... ሆ
በክርስቶስ .... ሆ
ተከወነ ...... ሆ
ያን ጨለማ ....ሆ
በአንተ አልፈናል...ሆ
አምላክ ክበር ..... ሆ
ሰው ሆነናል ...... ሆ
በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን ታየባቸው [፪]
አዝ▸▸▸▸▸▸▸►
ጴጥሮስ ያዕቆብ... ሆ
ዮሐንስ .............. ሆ
ሙሴ ኤልያስ ..... ሆ
በ ኢየሱስ .......... ሆ
ተመርጠው ነው... ሆ
በዚህች እለት ..... ሆ
ይህን ክብር ....... ሆ
ለማየት.............. ሆ
በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን ታየባቸው [፪]
አዝ▸▸▸▸▸▸▸►
ለእኛ በዚህ ........ ሆ
ብንኖር ............. ሆ
መልካም ነበር..... ሆ
ሕያውም ክብር... ሆ
ሦስት ዳስ ........ ሆ
እንስራና........... ሆ
እዚህ እንኑር ..... ሆ
በምሥጋና ....... ሆ
በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን ታየባቸው [፪]
አዝ▸▸▸▸▸▸▸►
ተገለፀ ........... ሆ
በታቦር ላይ...... ሆ
ብርሃኑን ......... ሆ
ለእኛ ሊያሳይ... ሆ
የምሥራች....... ሆ
እልል በሉ ...... ሆ
ለሁሉ አባት.... ሆ
ለ አዳኙ ........ ሆ
በስምህም ደስ አላቸው ታቦር አርሞንዔም ብርሃን ታየባቸው [፪]
ዓመት ለዓመት ያድርሰን በእወነት [፬]
ዓመት ለዓመት ያድርሰን በእወነት
ያድርሰን በህይወት ያድርሰን በህይወት[፪]
1988
15:01
18.08.2025
play_circleVideo preview is unavailable
✞ ደብረ ታቦር ደብረ ሲና ✞
🌿የቡሄ መዝሙር 🌿
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@orthodox_tewahdo19
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
1753
15:01
18.08.2025
✞ ደብረ ታቦር ደብረ ሲና ✞
ቡሄ በሉ - - - - - - - - ሆ
ቡሄ በሉ - - - - - - - - ሆ
ልጆች ሁሉ - - - - - - ሆ
ለአምላክ ክብር - - - - ሆ
ይቅረብ ምስጋና - - - - ሆ
በደብረ ታቦር - - - - - -ሆ
ተገልጧልና - - - - - - -ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ - - - - ሆ
በርቶ ደመቀ - - - - - - -ሆ
ልብሱ ነጭ ሆኖ - - - -ሆ
አንፀባረቀ - - - - - - - - ሆ
ደብረ ታቦር ደብረ ሲና ብርሀን በእናንተ አለና
ያዕቆብ ዮሐንስ - - - - - - -ሆ
ጴጥሮስ ሆኑና - - - - - - - ሆ
ፈጣሪን አዩት - - - - - - - - ሆ
በታቦር ተራራ - - - - - - - - ሆ
ሙሴ ኤልያስ - - - - - - - - ሆ
ከፊቱ ነበሩ - - - - - - - - - -ሆ
ስለጌትነቱ - - - - - - - - - - ሆ
እየመሰከሩ - - - - - - - - - ሆ
ደብረ ታቦር ደብረ ሲና ብርሀን በእናንተ አለና
አብም መሰከረ - - - - - - - - ሆ
በብሩህ ደመና - - - - - - - - ሆ
ቃሌን ስሙት አለ - - - - - - ሆ
ልጄ እሱ ነውና - - - - - - - - ሆ
ለመኖር ፈልጎ - - - - - - - - - ሆ
ጴጥሮስ በተራራ - - - - - - - ሆ
አምላኩን ጠየቀ - - - - - - - - ሆ
ብሩህ ዳስ እንስራ - - - - - - - ሆ
ደብረ ታቦር ደብረ ሲና ብርሀን በእናንተ አለና
ታቦር አርሞኒየም - - - - - - - - ሆ
ደስታ ሞላባቸው - - - - - - - - -ሆ
የመለኮት ብርሃን - - - - - - - - ሆ
ስለበራባቸው - - - - - - - - - - -ሆ
ቡሄ በሉ - - - - - - - - - - - - - - ሆ
ሕዝቦች ሁሉ - - - - - - - - - - - -ሆ
ብርሃንን - - - - - - - - - - - - - - ሆ
ተቀበሉ - - - - - - - - - - - - - - ሆ
ደብረ ታቦር ደብረ ሲና ብርሀን በእናንተ አለና
ወልድ ከበረ - - - - - - - - - - - - ሆ
በተዋሕዶ - - - - - - - - - - - - - - ሆ
የእግዚአብሔር ልጅ - - - - - - - - ሆ
ከድንግል ተወልዶ - - - - - - - - - ሆ
በታቦር ተራራ - - - - - - - - - - - - ሆ
ለከበረው ጌታ - - - - - - - - - - - - ሆ
ቡሄ እንበል - - - - - - - - - - - - - - ሆ
ሕዝቦች በደስታ - - - - - - - - - - - -ሆ
ደብረ ታቦር ደብረ ሲና ብርሀን በእናንተ አለና
ጌታ ሲመጣ - - - - - - - - - - -ሆ
ከደብረ ታቦር - - - - - - - - - - ሆ
ብርሃን ሞልቶ - - - - - - - - - - ሆ
የእረኞች መንደር - - - - - - - - ሆ
ልጆች ጨፈሩ - - - - - - - - - - ሆ
ቡሄ ብለው - - - - - - - - - - - - ሆ
እናቶች መጡ - - - - - - - - - - ሆ
ሙልሙል ይዘው - - - - - - - - ሆ
ደብረ ታቦር ደብረ ሲና ብርሀን በእናንተ አለና
ከትውልድ ትውልድ - - - - - - - - ሆ
ተላልፎ የኖረ - - - - - - - - - - - - ሆ
የቡሄ ትርጉም - - - - - - - - - - - ሆ
ይሄ ነበረ - - - - - - - - - - - - - - -ሆ
የዓመት ልምዳችን - - - - - - - - - ሆ
ዛሬም እንዳይቀር - - - - - - - - - - ሆ
በእማሚዬ ቤት - - - - - - - - - - - ሆ
ሙልሙል ይጋገር - - - - - - - - - - ሆ
ደብረ ታቦር ደብረ ሲና ብርሀን በእናንተ አለና
አባቶቻችን - - - - - - - - - ሆ
ችቦ ሲያበሩ - - - - - - - - ሆ
የቡሄን ምሥጢር - - - - - ሆ
እየተናገሩ - - - - - - - - - ሆ
ሲሰጡን ለኛ - - - - - - - - ሆ
ዘመን አሻግረው - - - - - -ሆ
አደራ አለብን - - - - - - - ሆ
እንድንጠብቀው - - - - - - ሆ
ደብረ ታቦር ደብረ ሲና ብርሀን በእናንተ አለና
ኢትዮጵያዊያን - - - - - - - - ሆ
ታሪክ ጠብቁ - - - - - - - - ሆ
ለባሕላችሁ - - - - - - - - - - ሆ
ሁል ጊዜ ንቁ - - - - - - - - - ሆ
ታሪካችሁ ነው - - - - - - - - -ሆ
የብሄ ሥርዓት - - - - - - - - - ሆ
በሕብረት እንውጣ - - - - - - ሆ
ችቦ ለማብራት - - - - - - - - -ሆ
ደብረ ታቦር ደብረ ሲና ብርሀን በእናንተ አለና
ጌታ ላክልን - - - - - - - ሆ
ፍቅር በረከት - - - - - - ሆ
ኢትዮጵያ ትሁን - - - - - ሆ
ዛሬ እንደ ትላንት - - - - -ሆ
ለአንተ እንገዛ - - - - - - -ሆ
ስጠን ልቦና - - - - - - - -ሆ
የቡሄ ፀጋ - - - - - - - - - -ሆ
እላያችን ይብራ - - - - - - ሆ
ደብረ ታቦር ደብረ ሲና ብርሀን በእናንተ አለና
ዓመት አውደ ዓመት ድገምና ዓመት ድገምና
በጋሽዬ ቤት ድገምና ዓመት ድግምና
ይውረድ በረከት ድገምና ዓመት ድገምና
ለማምዬ ቤት ድገምና ዓመት ድገምና
ይውረድ በረከት ድገምና ዓመት ድገምና
ማርና ወተት ድገምና ዓመት ድገምና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገምና ዓመት ድገምና
እንዲው እንዳላችሁ - - - - በፍቅር
አይለያችሁ - - - - - - - - - -በፍቅር
ለዓመቱ በሰላም - - - - - - በፍቅር
ያድርሳችሁ - - - - - - - - - - በፍቅር
ለስጋ ወደሙ - - - - - - - - -በፍቅር
ያብቃችሁ - - - - - - - - - - -በፍቅር
መንግሥተ ሰማያት - - - - በፍቅር
ያውርሳችሁ - - - - - - - - - በፍቅር
እንዲሁ እንዳለን - - - - - - በፍቅር
አይለየን - - - - - - - - - - - -በፍቅር
ለዓመቱ በሰላም - - - - - - -በፍቅር
ያድርሰን - - - - - - - - - - - - በፍቅር
ለስጋ ወደሙ - - - - - - - - - በፍቅር
ያብቃን - - - - - - - - - - - - - በፍቅር
የመንግሥቱ ወራሽ - - - - - በፍቅር
ያድርገን - - - - - - - - - - - - -በፍቅር
የቅዱሳን መላእክት የጻድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት (፪)
በሁሉም ቤት(፪) ይግባ በረከት (፪)
በአንድ ሐሳብ ሆነን በአንዲት ሃይማኖት
ፀንተን እንቁም ርቀን ከጥፋት
የጥንቱን ቱፊት ይዘን በአንድነት
እናስተላልፈው ለመጪው ትውልድ (፬)
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
@orthodox_tewahdo19
@orthodox_tewahdo19
@orthodox_tewahdo19
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
1985
15:01
18.08.2025
play_circleVideo preview is unavailable
✞ ሃሌ ሉያ ✞
ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ (፬)
ቡሄ መድረሱን ሰምተሃል ወይ
🌿የቡሄ መዝሙር 🌿
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@orthodox_tewahdo19
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
1978
15:01
18.08.2025
እንኳን አደረሳችሁ
ነሐሴ 13/2017 #በዐለ_ደብረ_ታቦር
#ፆመ_ፍልሰታ_ለማርያም_13ኛ_ቀን
በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነዉ
እርሱን ስሙት ማቴ.17፥1-8
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችንና መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ብርሐነ መለኮቱን ለገለጠበት አመታዊ #የደብረ_ታቦር ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን
👉ይህ በአል ከጌታችን ዘጠኙ #አበይት_በዐላት መካከል አንዱ ነው በአሉ በየአመቱ ነሐሴ 13 ላይ ይከበራል
👉#ቡሔ ማለት በደብረ ታቦር የተገለጠወ የጌታችን የፊቱ ብርሐን ፀዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መሆን ያስረዳል ስለዚህ የብርሐን ብርሐናዊ ማለት ነው
👉ታሪኩም በሶስቱ ወንጌላት ላይ የተፃፈ ሲሆን ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ ክርስቶስ ስምንቱ ሐዋርያትን ከእግር ደብር፣"ሶስቱን ጴጥሮስ ያዕቆብ ዮሐንስን" ይዙአቸው ወደ ደብረ ታቦር ተራራ በመውጣት የሞተውን ሙሴን አስነሰቶ የተሰወረውን ኤሊያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ #የሕያዋን_አምላክ እና ሙታንን አንሺው እርሱ መሆኑን ብርሀኑን የገለፀበት እለት ነዉ ማቴ.17፥1-9
👉ብዙ ተራራ እያለ #ደብረ_ታቦር_ተራራን የመረጠበት አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገለፅ በነብዩ ዳዊት
ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ይደሰታሉ መዝ.88፥12
👉በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሀኑን ሲገልፅ የብርሐኑ ነፀብራቅ እስከ #አርሞንኤም_ተራራ ድረሰ እንደሚታይ የተነገረው ትንቢትን ለመፈፀም ነው
👉ለምን ሙሴ እና ኤሊያስን መረጠ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠየቃቸው እንደመለሱለት ሁሉ በእውነት #የሙሴ እና #የኤሊያስ ጌታ እና አምላካቸው እርሱ #ኢየሱስ_ክርስቶስ መሆኑን በተራራው ላይ መስክረዋል ማቴ.16፥13
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከበዐሉ ረድኤትና በረከት ያሣትፈን እንዲሁም በዚህ እለት የሊቀ ነብያት #ቅዱስ_ሙሴ የልደቱ መታሠቢያ ክብረ በአል ነዉ ረድኤት በረከቱ ይድረሰን #እመቤታችን_ማርያም ልጅሽ #ክርስቶስ ፀጋና ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
👉ዲ/ን ዳንኤል ነሐሴ 13/2017 ዓ/ም
3189
22:34
18.08.2025
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
1 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
c
**ffeenold@******.io
On the service since June 2022
21.05.202521:16
5
Everything is fine. Thank you!

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር
On the service since August 2023
15.08.202510:47
Thank you
Show more
New items
Channel statistics
Rating
17.6
Rating reviews
5.0
Сhannel Rating
1
Subscribers:
33.7K
APV
lock_outline
ER
3.1%
Posts per day:
13.0
CPM
lock_outlineSelected
0
channels for:$0.00
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий