Get clients in any niche!
Delegate the launch of advertising to us — for free
Learn more
12.3
Advertising on the Telegram channel «አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center»
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$4.80$4.80local_mall
0.0%
Recent Channel Posts
imageImage preview is unavailable
ባለሀብቱ በራቸው ላይ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ
(መሠረት ሚድያ)- ታዋቂው የአክሰስ ኮም ኩባንያ ባለቤት እና የሸበል በረንታ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢረሳው ምናለ ትናንት ምሽት 1:30 ላይ ቤታቸው በር ላይ በጥይት ተመትተው እንደተገደሉ ታውቋል።
መሠረት ሚድያ የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው ባለሀብቱ በለሚ ኩራ፣ ወረዳ ዘጠኝ 'አትሌቶች መንደር' መውረጃ አስፓልት አጠገብ በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው በር ላይ መኪና ውስጥ ሆነው የግቢው በር እንዲከፈት ክላክስ እያደረጉ ባሉበት ወቅት በጥይት ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።
"በሰዓቱ የአስፓልቱና የአካባቢው መብራት ጠፍቶ ነበር" የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎች በአካባቢው ምንም የፀጥታ አካል አልነበረም፣ በስፍራው የደረሱትም ነግቶ ነው ብለዋል።
የምስራቅ ጎጃም ቢቸና ወረዳ ተወላጅ የሆኑት እና የ 'ምናሉ ሆቴል' ባለቤት አቶ ቢረሳው የቀብር ስነስርዐት በዛሬው እለት በሳሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።
መሠረት ሚድያ የአዲስ አበባ ፖሊስን በግድያው ዙርያ መረጃ የጠየቀ ሲሆን "መረጃው አልደረሰንም" የሚል ምላሽ አግኝቷል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia

130
19:02
14.01.2025
(ጥቅምት 1/2017 ዓ/ም በመሠረት ሚድያ ቀርቦ የነበረ ዜና)
መንግስት ነዳጅ ላይ ሊያደርግ ባሰበው ፊፎርም ምክንያት የዛሬ አመት አንድ ሊትር ነዳጅ ከ117 ብር በላይ እንደሚሆን ታውቋል
(መሠረት ሚድያ)- የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከቀናት በፊት የዓለም የነዳጅ ዋጋን መነሻን በማድረግ የነዳጅ ችርቻሮ ዋጋን በየሶስት ወሩ እንደሚጨምር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
በዚህ መግለጫ ላይ ይፋ የተደረገው መረጃ "የተሟላ ማስተካከያ" እስከሚደረግ ድረስ ይህ በየሶስት ወሩ የሚደረገው ጭማሪ እንደሚቀጥል ነው።
ከዚህ መግለጫ ጋር አብሮ የተለቀቀ አንድ ሰነድ እንደሚያሳየው የአለም የነዳጅ ዋጋ አሁን ባለበት የሚቀጥል ቢሆን የዛሬ አመት የነዳጅ ዋጋ 117 ብር ይገባል።
ምናልባትም ይህ የአለም የነዳጅ ዋጋ አሁን ካለበት በበርሜል 77 ዶላር የሚጨምር ቢሆንም ሁሉንም ጭማሪ ወደ ተጠቃሚው በማዞር ነዳጅ ላይ ለአመታት ሲደረግ የነበረውን ድጎማ ለማንሳት መታቀዱ ታውቋል።
በአዲሱ ማስተካከያ አንድ ሊትር ቤንዚን በ9 ብር ገደማ የጨመረ ሲሆን ነጭ ናፍጣ በበኩሉ በሊትር 7 ብር ገደማ የዋጋ ጭማሪ ተደርጎበታል።
ይህ ይፋ የተደረገው የነዳጅ ጭማሪ ድጎማ ተነሳ በተባለበት ወቅት ከተተገበረው ጭማሪ ወዲህ እጅግ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፍተኛ ጭማሪው የተደረገው በአለም ገበያ የታየውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መሰረት በማድረግ ነው ቢልም መሠረት ሚድያ ባደረገው ዳሰሳ የእስራኤል እና ሄዝቦላ ግጭት የጀመረ ሰሞን በበርሜል 90 ዶላር ገብቶ የነበረው የአለም የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ አሁን ተመልሶ 77 ዶላር ገብቷል፣ በመጪው ወራትም የነዳጅ ፍላጎቶች እንደሚቀንሱ አመላካች ሁኔታዎች አሉ።
መንግስት "መጠነኛ" እና "አነስተኛ" ብሎ የገለፀው ይህ ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ መሸጫ ጭማሪ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በርካታ ምርቶች እና አገልግሎቶች ላይ ጭማሪ ማስከተሉ የማይቀር ቢሆንም መንግስት ካሁኑ እንደዚህ ቀደሙ ለነጋዴዎች ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
መንግስት እስከ አንድ አመት ድረስ አደርገዋለሁ ባለው "የተሟላ ማሻሻያ" መሰረት አንድ ሌትር ቤንዚን፣ ኬሮሲን እና ነጭ ናፍጣ እያንዳንዳቸው 117 ብር፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ መቶ ብር፣ እና የአውሮፕላን ነዳጅ 106 ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለፓስፖርት ከሚከፈል ገንዘብ እስከ ባንኮች ማስከፈል የጀመሩት ቫት፣ እንዲሁም እንደ ውሀ፣ ኤሌክትሪክ፣ ቴሌኮም ወዘተ ያሉት አገልግሎቶች በሙሉ እስከ 700 መቶ ፐርሰንት የሚደርስ ጭማሪ ባሳዩበት ወቅት ይህ የነዳጅ ጭማሪን መንግስት ማድረጉን በርካቶች ማህበራዊ ሚድያ ላይ በመተቸት ላይ ይገኛሉ።
መረጃን ከመሠረት!
@MesretMedia

179
19:02
14.01.2025
መሠረት ሚድያ ቃሊቲ አካባቢ ስለሚገኝ የወጣቶች ማጎርያ ካምፕ በቅርቡ ያወጣውን ዜና የሚያረጋግጥ መግለጫ ኢሰመኮ ሰጠ
(መሠረት ሚድያ)- መንግስታዊው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) መሠረት ሚድያ ታህሳስ 19/2017 ዓ/ም ቃሊቲ ማሰልጠኛ አካባቢ ስለሚገኝ የወጣቶች ማጎርያ ካምፕ ያወጣውን ዜና የሚያረጋግጥ መግለጫ ማምሻውን አውጥቷል።
ሚድያችን በዚህ ዘገባው በአዲስ አበባ ከቃሊቲ ማሰልጠኛ ውሀ ልማት ጀርባ በሚገኘው እና ምስሉ ላይ በሚታየው ማጎርያ ካምፕ ውስጥ እድሜያቸው ከ15 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ጭምር በየግዜው እየገቡበት እንደሆነ ጠቁሞ ነበር።
ለውዝ አዟሪ፣ ሊስትሮ፣ የሀይላንድ እቃ ሰብሳቢ፣ መንገድ ላይ የሚለምኑ፣ የቀን ሰራተኞች ወዘተ መንገድ ላይ እየተያዙ ያለምንም ጥያቄ ተጭነው እየተወሰዱ እንደሚገኙም መረጃ አጋርተን ነበር።
ኢሰመኮ ዛሬ ባወጣው መግለጫው በታኅሣሥ ወር 2017 ዓ.ም. ባደረግኳቸው ክትትሎች በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ 'ቃሊቲ አካባቢ' ተብሎ በሚጠራው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ሰፈር ባለ ሰፊ መጋዝን ውስጥ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውንና ይህ ሰዎችን የመያዝና ወደ ማቆያ ማእከል/ቦታ የማስገባት ድርጊት አሁንም መቀጠሉን ተገንዝቤያለሁ ብሎ የመረጃውን እውነትነት አረጋግጧል፡፡
"ወደ ማቆያው ከገቡት ሰዎች መካከል በማእከሉ ከመቆየት እና የእርሻ ሥራ ከመሥራት እንዲመርጡ በማድረግ፤ የእርሻ ሥራ ለመሥራት የመረጡ ሰዎች በተለያዩ አካባቢዎች ወደሚገኙ እርሻ ጣቢያዎች ተወስደው እንዲሠሩ እንደሚደረግ ለመገንዘብ ተችሏል። ይህም የነጻነት መብታቸውን ጨምሮ ሌሎች መሠረታዊ የሰብአዊ መብቶቻቸውን የሚጥስ ነው" በማለት ኢሰመኮ አስታውቋል።
አክሎም "በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበሩ ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት፣ የሚደረጉ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ጉባኤዎች እንዲሁም ከሌሎች ተመሳሳይ ኹነቶች ጋር በተያያዘ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎችን በኃይል በማንሳት በአንድ ስፍራ እንዲቆዩ የማድረግ አሠራር እንዲቆም፤ ወደመጡባቸው አካባቢዎች የመመለስ እና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ሰብአዊ መብቶቻቸውን ባከበረ መልኩ ማከናወን እንደሚገባ እና ችግሩ ሁሉ አቀፍ የፖሊሲ ምላሽ የሚያስፈልገው መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱ የኢሰመኮ ክትትሎች ተጠቁሟል" ብሏል።
በዚህ ስፍራ ታስረው የተለቀቁ ዜጎች "መኝታ እና ምግብ ብሎ ነገር የለም፣ ጤነኛ ሆኖ የገባው ህይወቱ አልፎ ሲወጣ አይተናል" በማለት ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።
መረጃን ከመሠረት!
@mesretmedia

849
19:02
14.01.2025
#ልዩመረጃ ትናንት ምሽት በደቡባዊ ኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የታየው ክስተት የሰው ሰራሽ ጠፈር ስብርባሪ ወደ ምድር ንፍቀ ክበብ ሲመለስ የተፈጠረ መሆኑን የአውሮፓ ስፔስ ኤጀንሲ ለመሠረት ሚድያ አስታወቀ
- ስብርባሪው የቻይና ሺጂያን-19 መንኩራኩር ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል
(መሠረት ሚድያ)- ትናንት ከምሽቱ 1:30 ገደማ በደቡብ ኢትዮጵያ ባሉ በርካታ ዞኖች አንድ ግዙፍ 'ክስተት' ሰማይ ላይ መታየቱን በአካባቢ ያሉ ሰዎች መመልከታቸውን ሲናገሩ እና ምስሎችን ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲያጋሩ ቆይተዋል።
በዚህ ዙርያ መሠረት ሚድያ ለአውሮፓ ስፔስ ኤጀንሲ (European Space Agency) ማብራርያ የጠየቀ ሲሆን በኢትዮጵያ የታየው ክስተት ሰው ሰራሽ የጠፈር ቁስ ስብርባሪ ወደ ምድር ንፍቀ ክበብ ሲመለስ (re-entry ሲያደርግ) መሆኑን አብራርቷል።
ኤጀንሲው አክሎም ስብርባሪው የቻይናው ሺጂያን-19 (ShiJian-19) ሊሆን እንደሚችል ጨምሮ ገልጿል።
"በየአመቱ ከመቶ ቶን በላይ የሰው ሰራሽ የጠፈር ቁሶች ከቁጥጥር ውጭ ሆነው ወደ መሬት ይመለሳሉ" ብሎ መረጃውን ለመሠረት ሚድያ ያጋራው የአውሮፓ ስፔስ ኤጀንሲ ይህም በየአመቱ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ክስተቶች መታየት ምክንያት ነው ብሏል።
አክሎም "አንዳንዱ [የጠፈር ቁስ ስብርባሪ] መሬት ላይ ሊወድቅ ይችላል፣ ነገር ግን እንደ ጠፈር ሮኬት ያሉ ሁሉንም ቁሶች ተቆጣጥሮ ሰው በማይኖርበት አካባቢ እንዲወድቁ ማድረግ አይቻልም። አነስተኛ ቁሶች ራሳቸው ተቃጥለው ያልቃሉ፣ ትልልቅ አካላትን ግን ተቆጣጥሮ ወደ ምድር መመለስ ገና እያደገ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፣ እድገቱም ዘገምተኛ ነው" በማለት የኤጀንሲው ቃል አቀባይ ለሚድያችን ተናግሯል።
የትናንት ምሽቱ ክስተት እንደ ምዕራብ ጉጂ፣ ወላይታ፣ አርባ ምንጭ እና ሞያሌ አካባቢ መታየቱ የተገለፀ ሲሆን በኬንያ ማርሳቢት ግዛትም መታየቱ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በበኩሉ የክስተቱን ተፈጥሮ በእርግጠኝነት ለማብራራት ሁኔታውን በቅርበት እያጣራን እንደሚገኝ አስታውቋል።
የጠፈር ስብርባሪ ማለት አገልግሎታቸው ያበቃ ሳተላይቶች፣ ግልጋሎት የማይሰጡ መንኩራኩሮች፣ የሮኬት ማቀጣጠያ ተተኳሾች፣ ከጠፈር ላይ ግጭት የተረፉ ስብርባሪዎች እንዲሁም በጠፈር በረራ ወቅት ተገንጥለው ያመለጡ ቁሳቁሶች ሊሆኑ እንደሚችሉ መረጃዎች ይጠቀማሉ።
እነዚህ በከፍተኛ ፍጥነት የሚጓዙ ስብርባሪዎች ለሌሎች ሳተላይቶች ስጋት ቢሆኑም መሬት ላይ ላሉ ሰዎች የሚፈጥሩት የሞት ወይም የአካል ጉዳት ስጋት ከአንድ ትሪሊየን ውስጥ አንድ ብቻ መሆኑን የ 'ዘ ኦሮስፔስ ኮርፖሬሽን' መረጃ ይጠቁማል።

679
19:02
14.01.2025
ከቤታችሁ ሳትፈናቀሉ ዘመናዊ ቤት ይሰራላችኋል ተብለው የነበሩት የለገሀር ኤግል ሂልስ ፕሮጀክት ሳይት ነዋሪዎች የቆርቆሮ ቤት ግቡ እንደተባሉ ታወቀ
(መሠረት ሚድያ)- ከስድስት አመት በፊት የለገሀር ኤግል ሂልስ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ሲጣል በ1.8 ቢልዮን ብር የመኖርያ ቤት ተገንብቶላቸው እዛው እንደሚኖሩ ተነግሯቸው የነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ከቤታቸው ተነስተው ከቆርቆሮ የተሰራ ቤት ግቡ እንደተባሉ ለመሠረት ሚድያ ተናገሩ።
"ዶ/ር አብይ የመሰረት ድንጋይ ሲያስቀምጡ ባደረጉት ንግግር በአካባቢው ላይ እየኖሩ ለሚገኙ 1,650 አባወራዎች እዛው ፕሮጀክቱ አካባቢ ሰርተን በዘመናዊ ቤት ኑሮ እንዲኖሩ እናደርጋለን፣ ለዚህም የኤግል ሒልስ ባለቤቶች 1.8 ቢልየን ብር ሰጥተውናል ብለው ተናግረው ነበር" የሚሉት ነዋሪዎች አሁን አዲስ ዱብዳ የሆነ መረጃ ተነግሮናል ብለዋል።
"አሁን በፍጥነት አካባቢውን ለማንሳት እንቅስቃሴ ጀምረዋል፣ ከዚህ በፊት በማህበራዊ ሚዲያ ነገሩ እንዲዘገብ አድርጋቹሀል በሚል የቂም በቀል ሰበብ ከ6 ዓመት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቃል የተገባውን እዛው አካባቢ በዘመናዊ ቤት የማስፈር ሀሳብ በማጠፍ ቦሌ አራብሳ በቆርቆሮ በተሰሩ ቤቶች እንዲኖሩ እጣ አስወጥተው ህብረተሰቡን ከመሀል ከተማ ወደዛ ለማዘዋወር እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ" የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ቃል ስለተገባው ጉዳይ የወረዳው አስተዳዳሪ ሲጠየቅ "ዶ/ር አብይ የገባውን ቃል እኛ አናውቅም" ብሎ ምላሽ ሰጥቷል ብለዋል።
ዛሬ በ30/4/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7:30 የህብረተሰቡ መኖሪያ መንደር ድረስ በመምጣት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ተገኝተው እጣ 8:30 ላይ እንዲያወጡ ነግረዋቸው እና አስጠንቅቀዋቸው በመሄዳቸው ለቆርቆሮ ቤቶቹ እጣ መውጣቱ ታውቋል።
"ነዋሪው በጣም ተደናግጧል፣ እስቲ ብትዘግቡልን እና ህዝብ ቢያውቅልን ስንል አደራ እንላለን" ያሉት ነዋሪዎች ተስፋ አድርገው ለአመታት ቢጠብቁም ቃል ታጥፎ ከከተማ ውጭ እንዲሄዱ መደረጋቸው እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።
ይህ ከአልሚው ኢግል ለተነሺዎች ቤት መገንቢያ ተብሎ ተሰጥቶ የነበረው 1.8 ቢልዮን ብር የት እንደደረሰ በመንግስት የተባለ ነገር የለም።

364
19:02
14.01.2025
imageImage preview is unavailable
መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዲፕሎማቶች ለመንግሥት ሳያሳውቁ ከከተማ እንዳይወጡ ደብዳቤ ተላከላቸው
(መሠረት ሚድያ)- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መቀመጫውቸን በአዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ለመንግሥት ሳያሳውቁ ከከተማ እንዳይወጡ ማሳሰቢያ ሰጠ፡፡
ሪፖርተር የተመለከተውና ከአንድ ሳምንት በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአገሪቱ ድንበር ውስጥ ለሚያደርጓቸው ማናቸው እንቅስቃሴዎች ቅድመ ፈቃድ እንዲጠይቁ አሳስቧል፡፡
በአዲስ አበባ ለሚገኙ ዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ተቋማት፣ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ድርጅቶችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ከአዲስ አበባ ውጭ የሚያደርጓቸውን ጉዞዎች በተመለከተ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በተቀመጠ የቅድሚያ ማሳወቂያ ፎርም ከሞሉ በኋላ መሆን እንዳለበት አመላክቷል፡፡
ይሁን እንጂ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ የተጻፈው ደብዳቤ ማስጠንቀቂያው ለሥራ ወይም ለግል ጉዳይ የሚጓዙትን እንደሆነ በግልጽ አያስረዳም፡፡
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው ከዚህ ተመሳሳይ ድበዳቤ ተጽፎ የነበረ ቢሆንም፣ አንዳንድ ዲፕሎማቶች አሁንም ከፌዴራል መንግሥቱ ዕውቅና ውጭ ሲንቀሳቀሱ በመገኘቱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከዓመት በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት፣ ክልሎች በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ለፌዴራል መንግሥቱ ብቻ በተሰጠው የውጭ ግንኙነት ሥራ ላይ እየተሳተፉ በመሆኑ ፓርላማው ማሳሰቢያ እንዲሰጥ ተጠይቆ ነበር፡፡
ምንጭ: ሪፖርተር

239
19:02
14.01.2025
imageImage preview is unavailable
Enjoy our content? Advertise on this channel and reach a highly engaged audience! 👉🏻
It's easy with Telega.io. As the leading platform for native ads and integrations on Telegram, it provides user-friendly and efficient tools for quick and automated ad launches.
⚡️ Place your ad here in three simple steps:
1 Sign up
2 Top up the balance in a convenient way
3 Create your advertising post
If your ad aligns with our content, we’ll gladly publish it.
Start your promotion journey now!
https://t.me/telega_adv_bot/catalog_en?startapp=n_mesretmedia

82
12:12
15.01.2025
close
Reviews channel
No reviews
Top Rated in the Topic
New items
Channel statistics
12.3
0.0
0
13.8K
--%
0.0
lock_outline
Selected
0
channels for:$0.00
Followers:
0
Views:
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий