
- Main
- Catalog
- Religion & Spirituality
- መንፈሳዊ ስነ ፁሑፎች
መንፈሳዊ ስነ ፁሑፎች
በተለያዩ ሰዎች የተፃፉ ግጥሞች መነባነቦች ትረካዎች እና የተለያዩ ጭውውቶች ኪነጥበቦች እና መንፈሳዊ አስተማሪ ታሪኮችን ጥያቄ እና መልሶች የሚለቀቁበት ቻናላችን ነው ይቀላቀሉን ለሌሎችም ሼር ያድርጉ🙏
Channel statistics
#ሩትነት_ማለት !!!
፧
#ቅድመ_ታሪክ
፦
በመሳፍንት ፡ ዘመን ~
በድንቋ ፡ ከተማ ~ ረሀብ ፡ ጥርስ ፡ አወጣ ፣
ሞትን ፡ እየፈራ ~
ቃል ፡ ኪዳን ፡ ያለው ፡ ሕዝብ ~ ሀገር ፡ ጥሎ ፡ ወጣ ፤
፧
የምድርን ፡ እርግማን ~ ከሞት ፡ ፊት ፡ ሲያመልጡ ፣
አቤሜልክ ፡ እና ~ መላ ፡ ቤተሰቡ ~
እንጀራን ፡ ፍለጋ ~ ሙዐብ ፡ ተቀመጡ ፣
፧
ነፍሳቸው ፡ ሳትረካ ~
ከሙሀብ ፡ እንጀራ ~ በሞት ፡ ተሸነፉ ፣
አባትና ፡ ልጆች ~
ከሚስት ፡ በስተቀር ~ ሁሉም ፡ ረገፉ ፤
፧
እናት ፡ ለብቻዋ ~
የአዘን ፡ ካባ ፡ ለብሳ ~ በሙሀብ ፡ ስትኖር ፣
ከምራቶቿ ፡ ጋራ ~
ተስፋ ፡ ባጣ ፡ እምነት ~ በለቅሶ ፡ ስታድር ፤
፧
ለትውልድ ፡ መንድሯ ~
ምህረት ፡ እንደሆን ~ ወሬ ፡ ብትሰማ ፣
ኑሐሚን ፡ ተነሳች ~
ጉዞ ፡ ልትጀምር ~ ወደ ፡ አባቶቿ ፡ ሀገር ~ ቅድስቷ ፡ ከተማ ፤
፧
ምራቶቿን ፡ ሁሉ ~
በበረከት ፡ ባርካ ~ በእንባ ፡ እየሸኘች ፣
ይህቺ ፡ ምስኬን ፡ እናት ~
ለልጆቿ ፡ ሚስቶች ~ ይህን ፡ ተናገረች ፤
፧
በሙላት ፡ ወጥቼ ~
ባዶ ፡ ስለቀረው ~ ስሜን ፡ ማራ ፡ በሉት ፣
እዚህ ፡ በመሆኔ ~
ደስታዬን ፡ አጥቼ ~ አዘንን ፡ ነው ፡ ያተረፍኩት ፤
ኑሐሚን ፡ አትበሉኝ ~
ደስታ ፡ ከእኔ ፡ ርቋል ~ የሀዘን ፡ ማቅ ፡ ነው ፡ ልብሴ ፣
ማራ ፡ በሎኝ ፡ እንጂ ~
አዘን ፡ አጥግቦኛል ~ ምሬትን ፡ ለነፍሴ ፤
፧
የቀረኝ ፡ ዘር ፡ የለም ~
ትውልዴን ፡ 'ሚያስጠራ ~ ብቻዬን ፡ ትቶኛል ፣
የአባቶቼ ፡ አምላክ ~
በሙላት ፡ ወጥቼ ~ ባዶ ፡ መልሶኛል ፤
፧
ልጆቼ ፦
፡
ለእናንተ ፡ የሚሆን ~
ምን ፡ ቀረኝ ፡ ከእንግዲህ ~ ዘራችሁን ፡ እንዲረዝም ፣
ባሎች ፡ የሚሆን ~
ከሞቱት ፡ በስተቀር ~ ሌላ ፡ ልጅ ፡ የለኝም ፤
፧
ሂዱ ፡ ከቤታችሁ ~
ለእናንተ ፡ ባሉች ፡ ከወገኖቻችሁ ~ ምረጡና ፡ አግቡ ፣
ምሬት ፡ ስለሞላኝ ~
ለራሳችሁ ፡ እንጂ ~ ስለእኔ ፡ አታስቡ ፤
፧
እያለች ፡ በእንባ ~
እያለች ፡ በሲቃ ~ ጉዞዋን ፡ ስትጀምር ፣
ዖርፋ ፡ ስትመልስ ~
ፍቅር ፡ የረታት ፡ ሴት ~ እንባን ፡ እያዘራች ፡ ትከተላት ፡ ነበር ፤
፧
==============================
#ያቺ_የፍቅር_ሴት_ይሄ_ነበር_ቃሏ
፧
ለሰማይ ፡ ለምድር ~ ቃሏን ፡ እየሰጠች ፣
ፍቅርሽን ፡ ከእምነቴ ~ አለይም ፡ አለች ፤
፧
አምላክሽ ፡ አምላኬ ~ ጌታሽ ፡ ጌታዬ ፡ ነው ፣
ከእቅፍሽ ፡ ሚነጥቀኝ ~ አንድ ፡ ሞት ፡ ብቻ ፡ ነው ፤
፧
ፍጹም ፡ አልተውሽም ~
ሕዝብሽ ፡ ሕዝቤ ፡ ይሁን ~ ባደርሽበት ፡ ልደር ፣
ለሰጠሽኝ ፡ ተስፋ ~
ችግርሽን ፡ ስጋራ ~ በዋልሽበት ፡ ልኑር ፤
፧
ብላ ፡ እየማለች ~
እምነቷን ፡ አጽንታ ~ የምትከተላት ፡ ያቺ ፡ ሙሀባዊት ፣
መልከ ፡ መልካሟ ፡ ሴት ~
ሩት ፡ ነበረች ~ የኬልዎን ፡ ሚስት ፣
፧
==============================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ይህውልሽማ
፡
ከእምነት ፡ የመነጨ ~
እውነተኛ ፡ ፍቅር ~ ከልብ ፡ 'ካደረ ፣
ሞትንም ፡ አይፈራም ~
ታማኝ ፡ ቃሉን ፡ ሲሰጥ ~ በአምላክ ፡ ፊት ፡ የኖረ ፤
፧
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
==============================
#ሩትነት_ማለት
፡
በፍቅር ፡ ሰንሰለት ~
የፊጢኝ ፡ ታስሮ ~ የእምነት ፡ ባርነት ፡ ነው ፣
የቀደመ ፡ ኑሮን ~
የትውልድን ፡ ጸባይ ~ ማፍቀር ፡ እየሻረው ፤
፡
እስከ ፡ ሞት ፡ መታመን ~
ችግር ፡ ያጠናውን ~ ዘመን ፡ ለመሻገር ፣
ቃልን ፡ እየሰጡ ~
ሀሰትን ፡ ሲቀብሩ ~ ለእውነት ፡ መፈጠር ፤
፧
#ሩትነት_ማለት ፦
፧
በታማኝነት ፡ ዕዳ ~
ተግተው ፡ ሲተከተሉ ~ መከራን ፡ መጋፈጥ ፣
አምላክን ፡ ለማመን ~
ከባዕድ ፡ ምድር ፡ ወጥቶ ~ የእምነት ፡ እርሻን ፡ መርገጥ ፤
፧
ህግ ፡ የማይገዛውን ~
ፍቅር ፡ መላበስ ፡ ነው ~ በትህትና ፡ መኖር ፣
በእርግማን ፡ ዓለም ፡ ስር ~
ተስፋን ፡ እየቃኙ ~ ቤተልሔም ፡ ማደር ፤
፧
#ሩትነት_ማለት
፡
ከልማድ ፡ ህግ ፡ ወጥቶ ~
በፍቅር ፡ መወለድ ~ ለአዲስ ፡ ኪዳኑ ፡ በግ ፣
ዳግም ፡ መፈጠር ፡ ነው ~
አምላክን ፡ ለማመን ~ እያረጁ ፡ ማደግ ፤
፧
ለሰው ፡ ልጆች ፡ ተስፋ ~
አዳምን ፡ ለሚያድን ~ ሆኖ ፡ የዳዊት ፡ ዘር ፣
በፍቅር ፡ ሲታዘዙ ~
ከኋላ ፡ ተነስተው ~ ወደ ፡ ፊት ፡ መቆጠር ፤
፧
#ሩትነት_ማለት
፡
ለራስ ፡ እየሞቱ ~
ለሌሎቹ ፡ ደስታ ~ መስዋዕት ፡ መሆን ፡ ነው ፣
በትህትና ፡ ገዝፎ ~
በከፍታ ፡ መቆም ~ ጥላቻንም ፡ ቀብረው ፤
፧
#ሩትነት_ማለት
፡
ሳይጻፉ ፡ ኖረው ~
በአፍቃሪነት ፡ ጸንቶ ~ ታሪክን ፡ መገልበጥ ፣
አይሆንም ፡ ያሉትን ~
በእምነት ፡ በመጓዝ ~ ከስሩ ፡ መለወጥ ፤
፧
#አየሽ_ሩት_መሆን
==============================
~~
#ድህረ_ታሪክ
፡
ይሄ ፡ ታሪክ ፡ ማለት ፦
፡
አሁን ፡ በዚህ ፡ ዘመን ~
በዘመነ ፡ ምህረት ~ ለሚኖር ፡ ፍጥረቱ ፣
ስለሰጠው ፡ ኪዳን ~
መንገዱ ፡ ነበረ ~ ጌታ ፡ ለመምጣቱ ፤
፧
ፍጹም ፡ እንዳልወጣ ~
የጌታ ፡ መወለድ ~ ከዳዊት ፡ የዘር ፡ ግንድ ፣
ፍቅር ፡ አስገደደው ~
የሞሀቧ ፡ ፍሬ ~ አምላክ ፡ ይህን ፡ ሊያደርግ ፤
፧
በዘር ፡ ዓረጉ ፡ ስር ~
ከባህዳን ፡ መካከል ~ ሙሀባዊት ፡ አለች ፣
በቡኤዝ ፡ እርሻ ፡ ላይ ~
የስንዴ ፡ ርጋፊ ~ ቃርሚያ ፡ እየለቀመች ፤
፧
መልከ ፡ መልካሟ ፡ ሴት ~
ለቤተልሔማዊው ~ በዋጋ ፡ የተቤዥች ፣
ከእልፎች ፡ መካከል ~
ለፍቅር ፡ የኖረች ~ አንድ ፡ ሩት ፡ ተገኘች ፤
፧
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#እናልሽ ፦
፡
ሩትነት ፡ ማለት ~
ውስጥሽ ፡ ያለው ፡ እምነት ~ በፍቅር ፡ ሲገለጥ ፣
መሆን ፡ ላይ ፡ መቆም ፡ ነው ~
በተስፋ ፡ እየጸኑ ~ አለመሆንን ፡ መርገጥ ፤
፧
#ለእኔ_ሩትነት
፡
አድጎ ፡ መወለድ ፡ ነው ~
በመልክ ፡ በጸባይ ~ ትሁት ፡ እየሆኑ ፣
በጎበጠ ፡ ቀን ፡ ላይ ~
ስለ ፡ ሌሎች ፡ ደስታ ~ በፍቅር ፡ እየቀኑ ፤
፧
የእምነት ፡ ባለዕዳነት ~
ለፍቅር ፡ ባሪያ ፡ መሆን ~ ዘወትር ፡ ሳይሰለቹ ፣
ዳግም ፡ መፈጠር ፡ ነው ~
ዛሬ ፡ እንደተወለድሽ ~ በፍቅር ፡ ጣቶቹ ፤
፧
#እናም_ሩትነት
፡
በዘመን ፡ ርጋፊ ~
በእምነት ፡ እየጸኑ ~ በፍቅር ፡ ቤት ፡ ሲያድሩ ፣
ልክ ፡ እንደ ፡ አንቺ ፡ ነው ~
ከሙሀብ ፡ መሰደደ ~ ቤተልሔም ፡ ሊኖሩ ፣
፧
በሕይውት ፡ መዝግብ ፡ ላይ ~
ሩትነት ፡ ሲጻፍ ~ እኔ ፡ እንዳነበብኩት ፣
መታሰቢያ ፡ እንዲሆን ~
ለልደትሽ ፡ ቀን ፡ ነው ~ ይህንን ፡ የጻፍኩት ፤
፧
ሩትነት ፡ ብዬ ~
ከቅዱስ ፡ መዝገብ ~ ስገልጥ ፡ እንዳገኘው ፣
በቅንነት ፡ ዓለም ~
ከዕድሜ ፡ በዘለለ ~ ለፍቅር ፡ መኖርን ፡ ነው ፤
https://t.me/menfesawesinetsuhuf
ስደተኞቹ ተከታታይ ትረካ
ክፍል 11
የሲሪናይካ ህዝብ ከዛሬ ነገ ድራጎን ሀገሪቱን ይገለባብጣታል እያለ በስጋት ተውጧል።
/ ማርቆስ ከዋናው አዛዥ ጋር ወደ ከተማው ሲገባ ጣሩን ለመቀበል የወጣው ህዝብ ማነው? እያለ አዛዡን ስላስጨነቀው ታሪኩን ዘርዝሮ በአደባባይ ነገራቸው።
ንጉሡ ግን አልተዋጠላቸውም ነበር። እንደ አዩት ድንጋጤ ወርሷቸው ነበር። ወደ እልፍኛቸው አስገቡትና "መልከህ ለኔ እንግዳ አልሆነብኝም" ሲሉት ልቡ ደረቱን ስንጥቃ ልትወጣ ደረሰች።
"እኔ አላውቀውትም" ድምፁ ከማዱ የሚመጣ ይመስላል።
"አንተማ ልጅ ነህ። እኔ ግን የካርቴጅ ንጉሥ ልጁን ሲድር ተጠረቼ ሄጄ በነበረ ጊዜ ያገኘኋቸው የሲሪናካው ንጉሥ የሲፕሪዮን ልጅ መሆንህን አውቃለሁ። እንደውም አጠገባቸው አቁመው በኩራት ስለ አንተ የነገሩኝን ሁሉ አስታውሳለሁ። እስክንድሪያ ተምረሀል አይደል?"
ንጉሡ የመገረም ሁኔታ ይነበብባቸዋል። ደጋግመው አንገታቸውን ይወዘውዛሉ የእግራቸውን ጣቶች አቆራኝተው አውራ ጣቶቻቸውን አንዱን ከአንዱ ያሽከረክሯቸዋል። በነገስታት ወግ።
ማርቆስ መናገር ተሳነው። በጦር አሳጅበው ወደ ሲሪናይካ ሲመልሱት ያሰበው ተደናቅፎ በመንግስቱ ግቢ በአይነ ቁራኛ እየተጠበቀ እድሜ ልኩን የጉጉት ኑሮ ሲኖር ይታየው ነበር።
በር ተንኳኳ።
ንጉሡ በቀኝ እጅ የነበረውን ቀጭን የብር ዘንግ አንስተው ወደ በሩ ዘረጉትና እጅታውን በብር ቁልምም ሰበው በሩን ከፈቱት።
ይህንን በር ሌላ ሰው ሊከፍት መብት የለውም።
ንጉሡ የአንኳኳ ሰው እንዲገባ ሲፈቅዱለት ብቻ እራሳቸው ይከፍቱለታል።
ረዘም ወፈርና ደልል ለሚሉ ሴት እጅ እየነሱ ገቡ።
"ሞኒካ! ገቢ!"
ንጉሡ አይናቸውን ከማርቆስ ላይ አንስተው ወደ ሴትዮዋ ወረወሩ።
"እንግዳው ልጅህ ይሄ ነው?"
ሞኒካ ወደ ማርቆስ ተጠጉ።
"አዎ የሚገርም እኮ ነው!"
"ምኑ?"
"የማን ልጅ እንደሆነ ታውቂያለሽ?"
"ወደ ፀሐይ መውጫ ከሚጓዙት የፀሐይ መልእክተኛ መካከል አንዱ ነው" ሲሉ ሰምቻለሁ።
"ይሄ ሞኞች ወታደሮች የሚያወሩት ነው፤ ጥንት የሚነገረውን ተረት ይዘው። ታዲያ ምንድነው?"“የተከበሩት የሲረናይካ ንጉሥ የሲፕሪዮ ልጅ ነዋ። በካርቴጅ ከተማ ተገናኘን ብለህ የነገርከኝ፤ አስታውሰሻል? ታዲያ ምን ወደ በረሃ ወሰደው?”
“ለኔም እንቆቅልሽ የሆነብኝ ነገር ቢሆን ይህ ነው። እስኪ ወደ ሀገሩ እስኪመለስ ካንቺ ጋር ይሰንብት።”
ማርቆስ የእማማ ሞኒካን ቤት ወዶታል። ሞኒካ የንጉሡ እናት ናቸው። የሀገሩ ሰው በርኅራኄያቸው አጥብቆ ይወዳቸዋል። ንጉሡ ጨከን ሲሉባቸው ወደ ሞኒካ ጎራ ማለት የሚያዘወትሩት አያሌ ናቸው። ለማርቆስም ይኸው የርኅራኄ ልባቸው ተከፍቶ ነበር የጠበቀው። ነገር ግን የሲረናይካው ልዑል ልጅ በበረሃ ሊገኝ የቻለበትን ምስጢር ህሊናቸው ለማወቅ እንደጓጓ ነው። በግቢው ውስጥ ከአሽከሮቻቸው በቀር ሌላ ሰው አብሯቸው አይኖርም። ባላቸው ከሞቱ በኋላ ብቸኝነቱን ወድደውታል። አሽከሮቻቸውም ቢሆኑ የሚኖሩት ከዋናው ቤት ጀርባ በሚገኙት ክፍሎች ሲሆን፣ ዋናው ቤት ፀጥታ የነገሰበት ነው።
አንድ ቀን ማርቆስ ከእርሳቸው ጋር ለማዕድ እንደቀረበ በበረሃ የተገኘበትን ምክንያት ጠየቁት። በመጀመሪያ ሊነግራቸው ስላልፈለገ ዝምታውን መርጦ ነበር። በኋላ ግን ለእርሱ ያላቸው ፍቅርና ርኅራኄ ግልጽ እንዲሆንላቸው አደረገ።
“ልጄ ብትነግረኝ ምንኛ ደስ ይለኝ ነበር። ለማንም እንደማልነግር ቃል እገባልሃለሁ። ያለ ምክንያት ሲረናይካን ለቀህ አልወጣህም። በነገስታት ቤት እኮ ብዙ መከራ አለ። ያማሩ ቤቶች ሁሉ ያማረ ኑሮ አይገኝባቸውም። በተዋቡ ግቢዎች ውስጥ ስንት አስቀያሚ ሕይወት አለ መሰለህ?” አሉ ረጋ ብለው።
“እማማ የምነግርዎት ነገር አዲስና ግራ የሚያጋባዎት ሊሆን ስለሚችል ቢቀርብዎት ይሻላል።”
ይቀጥላል
https://t.me/menfesawesinetsuhuf
#በዚህች_ቀን_ያውም_ለአንተ_ክብር
፡
(#ይድረስ፦ ለሊቀ ፡ መላእክት ፡ ቅዱስ ፡ ሚካኤል #ተጻፈ፦ ከአንዱ ፡ ልጅህ ፡ ወልደ ፡ ገብርኤል )
፧
ታውቀኝ ፡ የለ ~
የሰዓታቱን ፡ ደውል ~ ፍጹም ፡ ሳልታገስ ፣
ገስግሼ ፡ ነበር ~
ለሊቱን ፡ ሳልፈራ ~ ከመቅደሱ ፡ ምድረስ ፤
፧
ስጋዬን ፡ ለማሰብ ~ ለአፍታ ፡ እንኳ ፡ ሳ'ልሰንፍ ፣
ልቤ ፡ እየቸኮለ ~ ለቅኔው ፡ ስሰለፍ ፤
፧
#እንዲህ_እንደዛሬው ~
ከአልጋዬ ፡ ሳልውድቅ ~ ደዌ ፡ ሳይጠናብኝ ፣
በወደድኩት ፡ አካል ~
ፍቅርን ፡ በማለቴ ~ ጥላቻ ፡ ሳይቀጣኝ ፤
፧
ደዌ ፡ ደንድኖ ~ ጤናዬ ፡ ሲከዳኝ ፣
ከአልጋዬ ፡ እያማጥኩ ~ ቅዳሴው ፡ 'ሚሰማኝ ፤
፧
መንፈሴ ፡ ታመመ ~ እሾህ ፡ ወጋው ፡ እግሬን ፣
ደፍሬ ፡ እንዳልመጣ ~ አሰለለው ፡ አቅሜን ፤
፧
ናርዶስ ፡ ሰውነቴ ~ ጠረኑ ፡ ከረፋ ፣
ጊዜ ፡ እምነትን ፡ ሲሽር ~
የማምነውን ፡ ሳጣ ~ የሚያምነኝም ፡ ጠፋ ፤
፧
#እንኳን_ላሳደከኝ ~
ከደጅህ ፡ ተጥዬ ~ ያለ'እናት ፡ ያለ'አባት ፣
እኔ ፡ አውቀው ፡ የለምውይ ~
#ሚካኤል ፡ ለሚልህ ~ ስታድል ፡ ምህረት ፤
፧
#ለምን ? ከ'አልጋ ፡ ተውከኝ ~
ነገድ ፡ እንደሌለው ~ እንደ ፡ ከዳተኛ ፣
ያለ'አንዳች ፡ ጠያቂ ~ ነሳህኝ ፡ መጽናኛ ፤
፧
#ለምንድን_ዝም_አልከኝ ~
ነፍሴ ፡ ቅኔ ፡ ልትዘርፍ ~ ቀንህን ፡ ስናፍቅ ፣
ምስጋናን ፡ ልሰዋ ~
የጌታ ፡ ቀን ፡ ብዬ ~ በጉጉት ፡ ስጠብቅ ፤
፧
#እንዴት_ችላ_አልከኝ ~
ዘምር ፡ ዘምር ፡ ሲለኝ ~ ልቤን ፡ ዜማ ፡ ሞልቶት ፣
ለክብርህ ፡ የቆመ ~
ዝናህን ፡ ሊናገር ~ ሕዝብ ፡ በሞላበት ፤
፧
#እንደምን_አራቀኝ ~
ደዌ ፡ በእኔ ፡ ጠንቶ ~ ለፍቅር ፡ ብተጋ ፣
ምህረትህ ፡ ሳጣ ~
እሞታለው ፡ ብዬ ~ ለምን ፡ ነፍሴ ፡ ሰጋ ፤
፧
#እኔ_እውቅህ_የለ ~
እንኳን ፡ ልቡ ፡ አዝኖ ~
ቃላት ፡ እያማጣ ~ ማረኝ ፡ ላለህ ፡ ቀርቶ ፣
እንባ ፡ እያዘነበ ~
ከመቅደሱ ፡ ደፍ ፡ ላይ ~ በፍቅር ፡ ተደፍቶ ፤
:
ትደርስለት ፡ የለ ~
ከአፉ ፡ ቃል ፡ ሳይወጣ ~ ከልቦናው ፡ ፈጥነህ ፣
ክንፍህን ፡ እያማታህ ~
እንባውን ፡ አብስህ ~ የምታማልደው ፡ ከአምላክህ ፤
፧
#ታዲያ_ለምንድን_ዝም_አለከኝ ~
ተራዬ ፡ ነው ፡ ብዬ ~ አልጋዬን ፡ ልሸከም ፣
ምልጃህን ፡ ታምኜ ~
ከጨለማ ፡ እልፍኜ ~
ተግቼ ፡ ስጠብቅ ~
አንተም ፡ አልመጣህም ፤
፧
#እናም_በእኔ_በኩል
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
፧
#ዛሬ ፡ በክብርህ ፡ ቀን ~
መቅደስህን ፡ ልሳለም ~ ፍቅርህ ፡ ግድ ፡ ቢለኝ ፣
በማፍቅረ ፡ የዛለው ~
ስጋዬ ፡ አቅም ፡ አጣ ~
የጥንቱን ፡ አስበህ ፡ እንዳትቀየመኝ ፤
፧
#ሚካኤል_አባቴ !!
እኔ ፡ አልመጣም ፡ ዛሬ ~ ጉብዝናዬ ፡ ረግፏል ፣
ያሳደከው ፡ ልጅ ~
ከወገን ፡ ርቆ ~ ብቻውን ፡ ቁጭ ፡ ብሏል ፤
፧
" መኑ ፡ ካመከ" ፡ ዜማ ~
በሩቅ ፡ እየሰማው ~ ደጅህን ፡ ብናፍቅ ፣
መምጣት ፡ ቢሳነኝ ፡ ነው ~
በጨለማው ፡ ስፍራ ~
ከአልጋዬ ፡ ተኝቼ ~ አንተን ~ 'ምጠብቅ ፤
፧
፧
#ና_ና_ና_ሚካኤል_ና_ና ~
አዝኛለሁና ፡ በ'አንተ ፡ ልጽናና ፤
፧
ድምጽ ፡ በሌለው ~
እልልታ ፡ ታጅቤ ~ በናፍቆት ~ ስጠራህ ፣
በእንባ ፡ ተጠምቄ ~ ስዘምርልህ ፣
ና ፡ ሚካኤል ፡ ና ~ ድረስልኝ ፡ ፈጥነህ ፤
፧
ለአምላኬ ፡ ቃሌን ~ እንድታደርስልኝ ፣
ልጅህ ፡ ነኝ ፡ አባቴ ~ ፈጥነህ ፡ ቅረበኝ ፤
፧
#ናፍቆቱ_ጠናብኝ ~
የደጀ ፡ ሰላሙ ~ የአባቶች ፡ ምርቃት ፣
የእናቶች ፡ ሽርጉድ ~ ትህትና ፡ የሞላበት ፤
፧
የሕጻናት ፡ ዝማሬ ~
የሰንበት ፡ ተማሪው ~ ያሬዳዊ ፡ ዜማ ፣
ከአውደ ፡ ምህረቱ ~
በእልልታ ፡ ታጅቦ ~ ጭብጨባው ፡ ሲሰማ ፤
፧
#እንደምን_ልቻለው ~
ይህን ፡ ሁሉ ፡ ስርዓት ~ መቅደሱን ፡ ርቄ ፣
#እስከመች ፡ ልኖር ፡ ነው ?
ከጨለማው ፡ እልፍኝ ~ እንዲህ ፡ ተደብቄ ፤
:
#ና_ና_ሚካኤል_ና_ና
ነጠላውን ፡ ባለብስ ~ እግሬ ፡ ጸንቶ ፡ ባይቆም ፣
ከትንሿ ፡ አልጋዬ ~ በደዌ ፡ ብወድቅም ፣
ዝክርህ ፡ ለማሰብ ~ በጭራሽ ፡ አልደክምም ፤
ና
ና
ና
ና
#ሚካኤል_ና_ና
ረዳት ፡ የሌለኝ ~ ብቸኛ ፡ ነኝና
ና
ና
ና
ና
እግሬ ፡ እስኪጸና ~
መንፈሴ ፡ ጠንከሮ ~ አልጋዬን ፡ እስካዝል ፣
ከአምላክህ ፡ ማልደህ ~
ጥላቻን ፡ አርቄ ~ መልክህን ፡ እስክመስል ፤
ና
ና
ና
ና
#ሚካኤል_ና_ና ፣
አዝኛለውና ፡ በአንተ ፡ ልጽናና ፤
፧
፧
፧
#ሚካኤል_አባቴ_በምህርት_ቅረበኝ !!!
:
https://t.me/menfesawesinetsuhuf
https://youtube.com/watch?v=rDZj6a2WgOI&si=LtEzcHH0wU_ihIpc
ከሰማይ ፡ ሸራ ፡ ላይ ፣
፤
፤
እግዜር’ ፡ ባለዘበው ~ የሰማይ ፡ ብራና ~ ለመጻፍ’ ፡ ምተጋው ፤
ሸራው ፡ ባዶ ፡ እንዳይሆን ~ ለ’ራሱ ፡ ብዬ ፡ ነው ፤
፡
፡
ሁሌም ፡ አዲስ ፡ ታሪክ ~ መጻፍ ፡ ስለሚወድ ፤
የትናንቱን ፡ ፍቆ ~ በአዲስ ፡ የጻጻፍ ፡ ስልት ~ በአዲሱ ፡ መንገድ ፤
በእጁ ፡ በሰራው ~ የ’ራሱ ፡ ብራና ~ መዝገቡን ፡ ለሙላት ፤
እኔው ፡ ነኝ ፡ ለእርሱ ~ ለሚጽፈው ፡ ታሪክ ~ መነሻ ፡ የሆንኩት
፡
፡
እርሱም ፡ አስቀድሞ ~ ለሚከትበው ፡ ነገር ፡ መንሻ ፡ እንድሆነው ~ በቃሉ ፡ አጽንቶ ፡ ከሰራው ፡ በረሀ’ ፤
በፍቅር ፡ ለፋለው ~ በእምነት ፡ ተጋለው ፣ ታሪኬ ፡ እንዳይነጠል ~ ከሕይወቱ ፡ ውኃ ፤
፡
በቀደም ፡ እግዚር ~ ነገርን ፡ ሹክ ፡ አለኝ ~ ግርማ ፡ ባለው ፡ ድምጹ ፤
በምኔ’ ፡ ልረዳው ~ የቃላቱን ፡ ቁጭት ~ ሳያሳየኝ ፡ ገጹ ፤
፡
፡
ብቻ ፡ ግን ፡ ባ’አንዳች ~ ልቡ ፡ እንደተከፋ ~ ሽኩሽክታው ፡ ነገረኝ ፤
እንዲህ ፡ ይመስለኛል ፣ ለእኔ ፡ እንደተረዳኝ ~ ደግሞም ፡ እንደገባኝ ፤
፡
ዛሬን ፡ ስጠብቅህ ፡ ቀለሜን ፡ በጥብጬ ፡ ሸራዬን ፡ አለዝቤ ፤
ከደጎቹ ፡ ጎራ ፡ ተነጥለህ ፡ ባይህ ~ ተከፋብኝ ፡ ልቤ ፤
ባለፉት ፡ ገጾች ፡ ላይ ~ ምንም ፡ ነገር ፡ ሳልጽፍ ~ ሁለት ፡ ቀን ፡ አለፈኝ ፤
አስተከዘኝ ፡ ልጄ ፡-
ከመዝገቤ ፡ መኃል ~ ለአንተ ፡ ያልኩት ፡ ምዕራፍ ~ ባዶ ፡ ሲሆንብኝ ፤
፡
፡
እግዜር ፡ የጨነቀው ፡-
የእኔን ፡ ስንክ ፡ ሳር ~ አሳምሮ ፡ ሊጽፍ ፤
በረበበ ፡ ዓይኑ ~ በምድር ፡ ፊት ፡ ቢያልፍ ፤
ቢያጣብኝ ፡ ነው ፡ እኮ ~ አንዳች ፡ መልካም ፡ ነገር ፤
በዘመን ፡ በሰራው ፣ ባለዘበው ፡ ሸራ ~ የሚከተብ ፡ ሚስጥር ፤
፡
፡
እግዜር ፡ እንዳዘነ ~ በእኔ ፡ እንደተከፋ ~ በቁጭት ፡ ሊነግረኝ ፤
በድንግዝግዝ ፡ አየሁ ~ በትር ፡ የጨበጠ ~ መላክ ፡ ሲቀርበኝ ፤
፡
፡
አልባሱ ፡ ነጭ ፡ ነው ~ በረድ ፡ የመሰለ ፤
አማላጅ ፡ ነው ፡ መስል ~ ለእኔ ፡ እየተላከ ~ ስማኝ ፡ ልጄ ፡ አለ ፤
፡
በዘመን ፡ ያረጀ ፡ የሸመገለው ፡ ሰው ~ እንዲህ ፡ አለኝ ፡ ቀጥሎ ፤
በሰማዩ ፡ ሸራ ፡ የተጻፍክ ፡ ለታ ~ ይህንን ፡ ይመስላል ፡ የቅያችን ፡ ውሎ ፤
፡
፡
መልካም ፡ የሰራህ ፡ ቀን ~ እግዚአብሔር ፡ ሲፈግግ ~ ሰማይ ፡ ታወራለች ፤
ጽድቅ ፡ ጽድቅ ፡ ’ሚሸት ~ ጨረቃም ፡ ሳትታክት ~ ዜማን ፡ ታቀርባለች ፤
ከዋክብት ፡ በተራ ~ ውበት ፡ አመሳቅለው ~ ለምድር ፡ ይነግራሉ ፤
በእርሱ ፡ መልካም ፡ ስራ ~ እግዜር ፡ ደስ ፡ አለው ~ ፈገገ ፡ አለ ፡ እያሉ ፤
፡
፡
ሳር ፡ ቅጠሉ ፡ ሁሉ ~ በአንድ ፡ ይዘምራል ፣ ነፋሳት ፡ ሲነፍሱ ~ ነፍስም ፡ ይነጠቃል ፤
እግዜር ፡ በአንተ ፡ ነገር ~ ደስታ ፡ ሲታይበት ~ ባሕርም ፡ ይስቃል ፤
ምን ፡ አለፋህ ፡ ልጄ ~ ዓለም ፡ ለብቻዋን ~ ጮቤ ፡ ትረግጣለች፤
በአንተ ፡ መልካምነት ~ ፊቱ ፡ የፈካውን ~ እግዜሩን ፡ እያየች ፤
፡
፡
አይገባህም ፡ እንጄ ~ እግዜር ፡ የሳቀ ፡ እለት ፣ ደስታው ፡ ወሰን ፡ ሲያጣ ~ ሰማይ ፡ ይከፈታል ፤
አንተ ፡ ጥሩ ፡ ሰርተህ ~ የዋልክበት ፡ ቀን ፡ ላይ ~ የእርሱ ፡ ፈገግታ ፡ በአንተ ፡ ውበት ፡ ይደምቃል ፤
፡
፡
አሉኝ ፡ እንደግና ~ ደጋግመው ፡ ቃል ፡ በቃል ፣ እንዲገባኝ ፡ ብለው ~ ልቤን ፡ እንዲረዳኝ ፤
የእግዜሩ ፡ ፈገግታ ~ ምንጩ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሲሉኝ ፤
እግዜር ፡ ‘ሚስቀው ~ ልቡን ፡ ደስ ፡ ‘ሚለው ፣ የሚከትበው ፡ ታሪክ ~ ከአንተ ፡ ሲያገኝ ፡ ነው ፤
ይህን ፡ ሳትዘነጋ ~ ዛሬስ ፡ ውሎህ ~ የት ፡ ነው ? ፤
፡
፡
ብለውኝ ፡ አረጉ ~ በዘመን ፡ ያረጁት ፣ የሸበቱት ፡ አባት ~ መልሴንም ፡ ሳይሰሙ ፤
በእግዜር ፡ ሰማይ ፡ ስር ~ በሚሰሯቸው ፡ ጽድቅ ~ ከእኔ ፡ የቀደሙ ፤
፡
፡
በማመን ፡ ሕግ ፡ ስር ~ እምነት ፡ ተጠልዬ ፤
መናገር ፡ ጀመርኩኝ ~ ይሰሙኛል ፡ ብዬ ፤
፡
፡
አባ ፡ ንገሩልኝ ፡-
ከእርሶ ፡ ዘመን ፡ ላይ ~ የተረፈ ፡ ካለ ፡ ከመዝገቦ ፡ ሲጻፍ ፤
ትርፎ ፡ ተሰብስቦ ~ በእኔ ፡ ባዶ ፡ ቦታ ~ ከደሙ ፡ ጋር ፡ ይረፍ ፤
፡
፡
‘ሚደሰት ፡ ከሆነ ~ እግዜር ፡ በእኔ ፡ ነገር ~ የእኔን ፡ ታሪክ ፡ ሲጽፍ ፤
ትናንት ፡ የዘለለው ~ የእኔ ፡ ባዶ ፡ ምዕራፍ ~ ይከተብ ፡ ከእርሶ ፡ ትርፍ ፤
ስራም ፡ ስሌለኝ ~ ከቶ ፡ አይሞላለትም ~ ያንን ፡ ባዶ ፡ ቦታ ፤ እኔን ፡ ካልደመረኝ ~ በእናንተ ፡ ከፍታ ፤
፡
፡
አባ ፡ ንገሩልኝ ፡-
ልጅነት ፡ ይዞትነው ~ ከቶ ፡ አትዘንበት ፣ ትንሽ ፡ ጊዜ ፡ ስጠው ፤
ብለው ፡ ይንገሩልኝ ፣ ፍቅርህ ፡ ይበርታና ~ ትህግስትህ ፡ ይለውጠው ፤
ለአጥንት ፡ እንዳልደረስኩ ~ በዳዴ ፡ ስድህ ~ ወተት ፡ እንደምጋት ፤
ብላቴናነቴን ፣ አፌ ፡ ያልተፈታ ~ ኮልታፋም ፡ እንደሆንኩ ፣ ይህንን ፡ ንገሩት ፤
፡
፡
ከመዝገቡ ፡ መኃል ፣ ዛሬን ፡ የምትዘለው ፣ ባዶነቱን ፡ አይተህ ~ ልብህም ፡ ‘ሚያዝነው ፤
ጠፍቶ ፡ እንዳይቀርብህ ፣ ወጥቶ ፡ እስኪመጣ ~ ተስፋ ፡ ስላለህ ፡ ነው ፤
፡
ታሪኩን ፡ ባትጽፍም ~ ስሙን ፡ ግን ፡ ጽፈሀል ~ በወርቃማው ፡ ቀለም ፡ በደምህ ፡ ታትሟል ፤
ታሪክ ፡ የሌለው ፡ ገጽ ~ የአንተ ፡ ነውና ~ ስሙም ፡ ይነበባል ፤
፡
፡
ብላችሁ ፡ ንገሩት ፡-
እድል ፡ ከሰጠህው ~ ገጹ ፡ ባዶ ፡ አይቀርም ፣
ትኮራለህ ፡ አንተም ፡ በልጅህ ፡ አታፍርም ፤
ውሎውን ፡ ሲውለው ~ በቅኖች ፡ መስክ ፡ ላይ ፣ በደጎች ፡ ቤት ፡ ሲያድር ፤
ያን ፡ ጊዜ ፡ ይሞላል ~ ከስም ፡ የተረፈው ~ ያሳዘነህ ፡ መስመር ፤
፡
፡
አውቃለው ፡-
ለእኔ ፡ ባለው ፡ መዝገብ ~ ፍጹም ፡ እንዳፈር ~ ልቡን ፡ እንደከፋው ፤
በእኔ ፡ ተስፋ ፡ ሳይቆርጥ ~ ‘ሚጸፈው ፡ ሲፈልግ ~ ሁለት ፡ ቀን ፡ አለፈው ፤
የእኔ ፡ ስንክሳር ~ የታሪኬ ፡ ልኬት ~ አለው ፡ ስርዝ ፡ ድልዝ ፤
አውቃለው ፡ እሱም ፡ ያውቃል ~ በቅጽበት ፡ ያጥበዋል ~ ከልቤ ፡ ስናዘዝ ፤
፡
፡
ብቻ ፡ ግን ፡ ንገሩት ~ ይህን ፡ ያክል ፡ ዘመን ~ ይህን ፡ ያክል ፡ ጊዜ ፤
አንድ ፡ ቀን ፡ ስመጣ ~ የእንባን
፡ መባ ፡ ይዤ ፤
ለእኔ ፡ በሰራኽው ~ ደክመህ ፡ ባለዘብከው ~ ከሰማይ ፡ ሸራ ፡ ላይ ፤
እድል ፡ አትንፈገኝ ~ ከደምህ ፡ ስር ፡ ልታይ ፤
የአንተ ፡ ፈገግታም ~ በእኔ ፡ ውበት ፡ ይታይ ፤
፡
፡
( #አቤል_ካሳሁን_ማስታወሻ )
( #ታሪክ_ሳይኖረኝ_በስሜ_ለጠራኽኝ_ለአንተ_ነው ፡፡ )
https://t.me/menfesawesinetsuhuf
♥️©
:
፧፡•፨•፨•፨•፨•፨•፨•፨•፨•፨•፡፧
፧፧ #ማርያምን_ልጇ_ነው !!!!!!! ፧፧
፧፧================== = =፧፧
፧
እንካ ፡ ጣፋጭ ፡ እውነት ፦
እንኪ ፡ ጣፋጭ ፡ እምነት ፦
♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️
ከወዲያም ፡ ያላህው ~
እንካ ፡ ታላቅ ፡ ሚስጥር ...
ከወዲያ ፡ ያልሽው ~
እንኪ ፡ ድንቅ ፡ ምክር ፣
፧
፧
ይህውልህማ ፡ እዛ ፡ ማዶ...
ከሶስቱ ፡ መኅል ፥
በህላዌው ፡ ያለ ....
ንጉስ ፡ ይታይኅል ፦
በፍቅር ፡ እርካብ ፡ ላይ
በተግባር ፡ የቆመ ፥
በሌሎቹ ፡ ስቃይ
ቆስል ፡ የታመመ ፤
÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷
በሚሽር ፡ ጠባሳ
ብዙው ፡ ያከመ
ከዙፋኑ ፡ ወርዶ ...
እንጨት ፡ ተሸከመ
በአንድ ፡ ድንጋይ ፡ ራስ
መቅድሱን ፡ የመታ....
የሞትን ፡ ሰሰለት
በሞቱ ፡ የፈታ.....
#ማርያምን_ልጇ_ነው ~
በቀራኒዮ ፡ ላይ...
በደሙ ፡ ያጌጠው ~
የምንዱባን ፡ ሲሳይ
ስማማ ፡ ሌላ ፡ እውነት ~
ንዋይ ፡ የሌለበት...
ስሚኝ ፡ ሌላ ፡ እምነት ~
ፍቅር ፡ የሞላበት ፤
ስማማ ፡ እዛ ፡ ማዶ
ጆሮህን ፡ የያዝከው
ስሚኝማ ፡ ውዷ
ይሄኛው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፤
በገነት ፡ መካከል ፦
በኩር ፡ የሆነው ፡ አዳም ...
በመፈጠር ፡ ጥበብ ~
የሚደርሰው ፡ የለም....
ይሄ ፡ የማርያም ፡ ልጅ ~
ጥበብ ፡ ማያልቅበት...
ከአፍር ፡ ሰራውና ~
ሕይውትን ፡ ዘራበት
በገዛ ፡ መዳፉ ~
ከምድር ፡ አፈር ፡ ዘግኖ ...
እራሱን ፡ ቀረጸ ~
መልኮት ፡ ሰው ፡ ሆኖ....
ምን ፡ ይገርማል ፡ ታዲያ ~
አሁን ፡ በዚህ ፡ መኅል .....
ምን ፡ ይደንቃል ፡ ታዲያ ~
ግዴታውን ፡ ሰርቷል...
እንደምን ፡ አይገርምም ~
እስትንፋስ ፡ ሲገብር ...
እንደምን ፡ አንደንቀም ~
እራሱን ፡ ሲፈጥር....
============================
#ማርያምን_ልጇ_ነው ~
ድንቅ ፡ ጥበበኛ ....
በኋላኛው ፡ ዘመን
የመጣው ፡ ወደኛ ፤
=============================
እንካ ፡ ሌላ ፡ ሚስጥር ~
ልብን ፡ የሚሞላ ፤
እንኪ ፡ ሌላ ፡ ሚስጥር ~
ከእምነቱ ፡ ጥላ ፣
አምላክ ፡ ቤቱን ፡ ሰራ ~
ከአፈርና ፡ ከአጥንት ፤
በዘመን ፡ ፍጻሜ ~
ገብቶ ፡ ሊኖርበት ፤
አዳሜ ፡ ሲበድል ~
ከቅድስና ፡ ዛፍ ~ ወድቆ ፡ ሲሰባበር ፣
ሔዋኔ ፡ ነጻ ፡ ልትሆን ~
ምክኒያት ፡ ስትደረድር ፣
#ወላዲቷን_ስለህ
===========
የእምነት ፡ መሰሶ ~ በክደት ፡ ሲሰበር
ያን ፡ ጌዜ ፡ ፈጣሪ ~
የራሱን ፡ ማደሪያ ~ እየሰራ ፡ ነበር ፤
÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷
#ድንግልን_ልጇ_ነው ~
ዓለም ፡ ሁሉ ፡ ረክሶ ....
የክፋት ፡ ጨለማ ~
በምድር ፡ ላይ ፡ ነግሶ....
÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷
የዘመን ፡ አዳፋ ~
ሲኖር ፡ ቀንበር ፡ ሆኖ ፣
የሰው ፡ ዘርም ፡ ተስፋ ~
በሞት ፡ ዓለም ፡ ገኖ ፤
በመስዋዕቱ ፡ በግ ~
የማይጸዳው ፡ እድፍ ....
በዋኖሶች ፡ መስዋዕት
በሽታው ፡ የማይረግፍ ....
የታመመው ፡ አዳም ~
ዘመኑን ፡ ሲተባ ~ መዳንን ፡ ፍለጋ ፣
መቼ ፡ ቃሉን ፡ ተወ
የጨለመበትን ~ ሌቱን ፡ ሳያነጋ ፣
በምክኒያት ፡ ሽሽት ~
ነፍሷ ፡ ለከረመች ፣
የአዳም ፡ ጎን ፡ አጥንት ~
መች ፡ ተሰብራ ፡ ቀረች ፤
#እመ_ብርሃንን_ስልህ....
÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷
ይሄ ፡ ብርቱ ፡ ጌታ ~
መስራት ፡ ማይታክተው ፣
ጥንት ፡ የሰራውን ፡ ቤት ~
በቃሉ ፡ ከፈተው ፣
#ማ_ር_ያምን !!!
ሰውን ፡ ከሰራበት ~
እራቂቅ ፡ ጥበቡ....
ከመፍጠር ፡ ይልቃል ~
የማዳን ፡ አሳቡ...
ከዘመናት ፡ በፊት ~
ከአፍረና ፡ ከአጥንት ...
በረቂቅ ፡ ጥበቡ ~
የሰራው ፡ ጭቃ ፡ ቤት ፤
ከዓለም ፡ እርኩሰት
በጥባብ ፡ ጠብቆ ~ ጸጋ ፡ እ'የጋረዳት ፣
በዘመን ፡ ፍጻሜ ~
ቃሉን ፡ ለመጠበቅ ~ መጥቶ ፡ አደረባት ፤
ይታየሀል ፡ እዛ ~
ከጉብታው ፡ ተርታ ~ ከፍ ፡ ያለ ፡ ጉብታ ፣
በወጎ ፡ ተሰቅለው ~
ከተመሳቀለው ፡ ከእንጭቱ ፡ ተርታ ፣
ዓለምን ፡ ሲፈጥር ~
በረቀቀው ፡ ጥበብ ~ እ'ቤቱን ፡ የሰራው ፣
ከወንበዴዎቹ ~
መካከል ፡ ላይ ፡ ያለው ፣
የዓለም ፡ መድኃኒት ~
#ማርያምን_ልጇ_ነው ፤
+++
፧
፧
፧፡•፨•፨•፨•፨♥️♥️♥️♥️፨•፨•፨•፨•፡፧
፧፧ #ስብዕት_ወክብር_ለስሉስ_ቅዱስ ፧፧
፧፧=======================፧፧
#ለወላዲተ_አምላክ
፧፡•፨•፨•፨• ♥️
#ከአቤል_ካሳሁን_ማስታወሻ።
#21_08_2012ዓ/ም
https://t.me/menfesawesinetsuhuf
፧
ይህው ፡ ቂም ፡ ይታያል ~ ይህው ፡ ጥላቻው ፡ ገኖ ፣
የቀደመው ፡ ፍቅር ~ በነበር ፡ ተከድኖ ፤
፧
አስታርቂን ፡ እመ ፡ አምላክ ~ አሳስቢው ፡ ለልጅሽ ፣
በአንቺ ፡ የመጣውን ~ መቼም ፡ እንቢ ፡ አይልሽ ፤
፧
የቀደመው ፡ ፍቅር ~ በልባችን ፡ ይንገስ ~ ጥላቻን ፡ አርቀሽ ፣
ቂማችንን ፡ ሁሉ ~ በይቅርታ ፡ አጥፍተሽ ፤
፧
ዕድሜ ፡ ሳይጨላልም ~ ነይ ፡ በነፍስ ፡ ድረሽ ፤
በተሰጠሽ ፡ ኪዳን ~ ልጆችሽን ፡ ፈውሽ ፤
፧
#እያልኩ ፦
፡
ፊትሽ ፡ የማነባው ~
በእንባ ፡ ተጠምቂ ~ ሁሌ ፡ ምለምንሽ ፡ እንድታስታርቂኝ ፣
የይቅርታ ፡ እስራኛ ~
ፍቅርን ፡ የተራብኩኝ ~ ልጅሽ ፡ መጻጉ ፡ ነኝ ፤
፧
ድንግል ፡ ሆይ ፡ አደራ ! ~
በወዳጆቼ ፡ ልብ ~ ይቅርታን ፡ አንግሰሽ ፣
የአዘን ፡ ጠረኔ ~
በደስታ ፡ እንዲተካ ~ ናርዶሴንም ፡ መልሽ ፤
፡
ታርቀን ፡ እንድንቆም ~
በአንቺ ፡ መክበሪያ ፡ ቀን ~ በፍቅር ፡ አጊጠን ፣
ልጅሽ ፡ ባ'ስተማረን ~
ዘመን ፡ ተሻጋሪ ~ ይቅርታ ፡ አደግድገን ፤
፡
ቂማችን ፡ ተሱዶ ~
ከልባችን ፡ ጓዳ ~ ቅንነትም ፡ ይንገስ ፣
ሰላም ፡ ነው ~ ፍቅር ፡ ነው
ብለን ፡ እንዘምር ~ ልባችን ፡ ይፈወስ ፤
፧
#ብዬ_ምለምንሽ .................
፧
ከፊትሽ ፡ ወድቄ ~
ዘወትር ፡ እያነባው ~ አስታርቂኝ ፡ የምልሽ ፣
የወዳጆቼ ፡ ፍቅር ~
ይቅርታቸው ፡ የራበኝ ~ መጻጉ ፡ ነኝ ፡ ልጅሽ ፤
፧
#መታሰቢያነቱ !!
፡
👉የቀደመው ፡ ፍቅር ፡ ለቀዘቀዘብን ፡ ለእኛ ።
👉ይቅርታ ፡ ለነፈግን ፡ ለእኛ ።
👉በደልን ፡ በመቁጠር ፡ ለተጠመድን ፡ ለእኛ ።
👉ቂም ፡ በልባችን ፡ ለቋጠርን ፡ ለእኛ ።
፡
#ለእኛ_ለሁላችን_እንዋደድ_ለነበርን
፧
፡
(እንቅልፍ ፡ በማጣት ፡ በወርሀ ፡ ጥር ፡ 20 ፡ ቅዳሜ ፡ ለሊት ፡ ለእሁድ ፡ አጥቢያ ፡ ለአስተርዮ ፡ ማርያም ፡ ዓመታዊ ፡ ክብረ ፡ በዓል ፡ ካህናቱ ፡ በማህሌት ፡ እኔም ፡ ከስዕልሽ ፡ ፊት ፡ ተደፍቼ ፡ በጭንቀት ፡ ጻፍኩትኝ ) በ2009 ዓ.ም #አቤል_ካሳሁን_ማስታወሻ
https://t.me/menfesawesinetsuhuf
++ ሥነጽሑፍ - የተማጽኖ ግጥም !
( ርዕስ - #እባክህ ጌታ ሆይ ... )
ምነው ጌታ ዝማልክ
ምህረትህ ዘገየ ፣
በአስራት ሀገሩ
ያንተ የደም ዋጋ ሞተ ተሰቃየ ፣
አንተን በመጠበቅ
ህዝብህ ቁሞ እያየ ።
ምነው ጌታ ዝማልክ
ፍርድህ ወዴት አለ ፣
የታቦት ማደሪያህ እየተቃጠለ ፣
የቀባህውን ካህን እየተገደለ ።
ምንድነው ዝምታህ
ፍርድህ ወዴት ሄደ ፣
አንተን ያመነ ህዝብ
ቆሞ እየታረደ ፣
ከቤተክርስቲንያን ጋር አብሮ እየነደደ ።
ምነው የድንግል ልጅ
አይሳንህ መፍረድ
አታጣልን መላ ፣
እንዴት ነዉ ያስቻለህ
በጅብ ስንበላ ።
ባክህ ታደገን
እንደ ወንዝ ውሀ
ደም እኮ ፈሰሰ ፣
በአውሬነት ግብር
ሰውነት ፈረሰ ፣
እንጀራ ይመስል
መሬት ተቆረሰ ፣
አፈር ዋጋ አውጥቶ
ሰው መሆን አነሰ ።
....
በአምሳልህ አርገህ
የሰራሀው አካል ፣
ላንተ አልሆንም ብሎ
ህዝብህን ያውካል ።
..
ያንተ እየሩሳሌም
ምድር ላይ ያቆምካት ፣
ዘወትር ውዳሴ የምታገኝባት ፣
ስለ ዓለም ሰላም ስለ ሀገር ክብር
የሚሰበክባት ፣
ምነው ይች መቅደስ
የክርስቲያኖች ቤት መከራ በዛባት ፣
ጠላት ተነሳባት ።
ምንድነው ጥፋቷ ?
ሊቃውንትን ወልዳ
ጥበብ ባስተማረች ፣
ሁሉን አስጠግታ
አክብራ በኖረች ።
ምንድነው ግድፈቷ ?
በቀን በሌሊቱ ላገር በፀለየች ፣
ፊደልና ቀመር ጥዑም ዜማ ሰርታ
ለሀገር ባኖረች ፣
ግሩም ቅርስ ሰርታ
የቱሪስት መስህብ ገቢ ስለሆነች ።
እንዲ ነው ወይ መልሷ
ክብሯን አሳንሶ
ላይዋ ላይ መራመድ ፣
ህዝቦቿን ማሳደድ ፣
አማኞቿን ማረድ ፣
መቅደሶቿን ማንደድ ፣
መፅሀፍቶቿን መቅደድ ።
እንዲህ ነው ወይ መልሷ
ለሆነችው መሆን
ምስጋና ባይተርፋት ፤
ደጆቿን ዘጋግቶ
ሀብቶቿን ዘራርፎ
አንገቷን ማስደፋት ፣
መቆም ላስተማረች ፣
እንድትወድቅ መግፋት ።
እንዲህ ነው ወይ መልሷ?
ንገረኝ ፈጣሪ
ይህን ያደረጉት ያንተ ፍጥረት ናቸው ፣
ቢመከሩ አልሰሙም
ድፍን ነው ጆሯቸው ፣
መግደል ነው ስራቸው ፣
መቁረጥ ነው ግብራቸው ።
ምነው የማርያም ልጅ
እንባችንን ናቅከው ፣
ስለ ድንግል ብለህ እባክህ ንገረን
ምንድን ነው የሆንከው ፣?
ሀገር እያለቀ ቆመህ የታዘብከው ።
ንገረን እባክህ
በድለናል በርግጥ
ሀጢአትን ሰርተናል፣
አለም ሰልጥኖብን አንተን ረስተናል ፣
ዘር እና ሀይማኖት ቋንቋ ከፋፍሎናል ።
አወ በድለናል
አንተም ታውቀናለህ
እኛም አንክድም ፤
ሀላፊ ቁስ እንጅ
ሀይማኖት አንወድም ።
ፀብ ማባባስ እንጅ
እርቅን አናወርድም ።
መዘላለፍ በዝቷል ፣
መነቋቆር ብዝቷል ፣
መተማመን ጠፍቷል ፣
ከእንሰሳት አንሶ
ሰው ክብሩን አጥቷል ።
አወ ታውቀናለህ
ደም አለ በጃችን ፡
ገንዘብ ነው ጌታችን ፡
ዝሙት ነው ስራችን ፡
እናመስግን ብለን የምንዘምርልህ ፣
እንፆምለን ብለን የምንፆምልህ ፣
ልባዊ አይደለም ፣
ለፅድቅ የሚሆን
አንዳች ስራ የለም ።
ቅሉ ይህ ቢሆንም
ግራ ቢገባህም
የኛ ሰቦች ነገር ፣
ዝም ብለህ አትየን
እየጠፋ ሀገር ።
አይኖችህን ክፈት
አይተህ ዝም አትበለን ፡
ዛሬም እንጮሀልን ፡
ገና እንጠራሀለን፡
እናም እባክህን
ስለ ሰማእታት
ስለ መላእክትህ
ሥለፃድቃኑ
ስለ ሀዋርያትህ
አንተን ስላመኑ ፣
አድስ ቀን አምጣልን
ጠቁሮብናል ቀኑ ።
መገደሉ ይብቃ
መታረዱ ይብቃ
ደም መፍሰሱ ይብቃ
መሰደዱ ይብቃ
ህዝብህ አይዋረድ ፡
ውረድ አንልህም
ባለህበት ፍረድ ።
ይኽ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ በቅድስት ቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናት፣ ዲያቆናት እና በንጹሐን ምዕመናን ላይ ስለሚደረገው ወቅታዊ ወከባ ስደትና ግድያን አስመልክቶ የተዘጋጀ የመማጸኛ ግጥም ነው ።
ስለሁሉም ነገር ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያና ቤተ ክርስቲያንን ሠላሟን ይመልስልን !!
https://t.me/menfesawesinetsuhuf
Reviews channel
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
መንፈሳዊ ስነ ፁሑፎች is a Telegram channel in the category «Религия и духовность», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 1.5K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 22.1, with 0 reviews and an average score of 0.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 1.2 ₽, and with 0 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий