
21 mezmur
በ👉21 mezmur በየቀኑ አዳዲስ እና የድሮ መዝሙሮችን አጫጭር መንፈሳዊ ታሪኮችን መንፈሳዊ ጥያቄ እና መልስ መንፈሳዊ ፊልሞች እንዲሁም መንፈሳዊ ኮርሶችን በየጊዜው ያገኛሉ 😍😍 እርሶም share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ :: 👉 ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገር ናት!
Channel statistics
ክርስቶስ ወንጌልን ለመስበክ እንጂ ለማጥመቅ አልላከኝምና... የመስቀሉ ነገር በሚጠፉ ሰዎች ዘንድ ስንፍና ነውና፣ ለምንድነው ለእኛ ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው" (1ቆሮ 1: 17-18)ኦርቶዶክሳዊው የትምህርትና የዕውቀት ጎዳና፣ ኅሊና እና አእምሮን ብቻ ግምት ውስጥ የሚያስገባ አይደለም፤ ልብንም እጅግ አስፈላጊ አድርጎ የሚያስብ ነው እንጂ። ይኸውም ዕውቀትን የሚገልጥ ፍቅርና ትሕትና መገለጫዎቹ የሆኑ፣ አካላዊ እግዚአብሔርን የሚዘክሩ ባለመሆኑ ነው። በእኛ ዘንድ ጥበብ ዘርውት ሳትሆን አካላዊ ናት። [16] የሰውን ዐይኖች ገልጣ ራሷን የምታሳይ፣ የሰውን አእምሮ ከፍታ ራሷን የምታሳውቅ ናት (ሉቃ 24: 29-35)።
1.1. ዕውቀት እና ሃይማኖትአመክንዮ እና ሃይማኖት "ሳይጋቡ የተፋቱ" መሆናቸውን መናገር ጥቂት ለማይባሉ ሰዎች የተለመደ ሆኗል። የዚህ ክፍለ መጽሐፍም ዋና ዓላማ አመክንዮ እና ሃይማኖት ያላቸውን ጋብቻ ለመግለጽ መሞከር ነው። ይኸውም በሃይማኖትም ሆነ ከሃይማኖት ውጪ ነን ብለው ሃይማኖትን ከአመክንዮ ጋር ፈጽሞ ስምምነት እንደሌለው አድርገው ለሚመለከቱ ሰዎች መሞገቻ ይሆናል ተብሎ በመታሰቡ ነው። ሃይማኖት እና ዕውቀት፣ መገለጥ እና አመክንዮ ሊዋሃዱ የማይችሉ መሆናቸውን መናገር ጥቂት ለማይባሉ ሳይንስ አዋቂዎች አንዱ መግለጫ ሆኖ ይታያል። በዚህም ምክንያት አንድ ሰው ሳይንስን እና ዘመናዊ ትምህርቶችን ከተማረ ራሱን ከእምነት ተፅዕኖ ነፃ እንዲያደርግ እስከመጠበቅ የደረሱም አሉ። ምክንያቱም እምነት የሰውን የማሰብ፣ የመጠየቅና የመመርመር አቅሙን የሚያደክም፣ የሰው ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴን ቀላል ማድረግ ወደሚችሉ የተሻሉ ግኝቶች ተራምዶ እንዳይደርስ ጎታች አድርገው የሚያስቡ ስላሉ ነው። እንደውም ሃይማኖት የሰውን አእምሯዊ (የዕውቀት) አቅም ቀስ በቀስ የሚያደክም ሕዋስ (ቫይረስ)፣ ከዚያም በላይ ደግሞ ሃይማኖት "የአእምሮ ሕመም" (Mental illness) እንደሆነም ተነግሯል። ነገር ግን የዚህ ሁሉ ጉዳይ ማጠንጠኛ ሐሳብ ምን ይሆን? ብለን መጠየቅ ይገባናል። ይህ ጽሑፍም ውግኑነቱ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ክርስትና በመሆኑ እምነት (ሃይማኖት) ሲል ክርስትናን እንደሆነ በመገንዘብ ዋናው ጉዳያችንን ወደ መረዳት እንግባ። ቀደም ብለን ያነሳናቸው የሳይንስ አዋቂዎች፦ ከላይ ያነሳናቸውን እምነትን የሚያስተሐቅሩ ምልክታዎችን ሲያቀርቡ ሁለት ጉዳዮችን ከማሰብ ጋር ነው። የመጀመሪያው ሃይማኖት የዕውቀት ዋና መሠረት እና አንቀሳቃሽ ከሆነው አመክንዮ (Reason) ጋር አብሮ መሄድ እንደማይችል ማሰባቸው ነው። እምነት እንደ ሰው የግል አመለካከት ተደርጎ ይወሰዳል። በአመክንዮ አለመኖር ምክንያት በሰዎች ዘንድ የተንሰራፋ ከንቱ ነገር እንደሆነም የሚያስቡ አሉ። ሁለተኛውም ሳይንስ ምንም ዓይነት እምነታዊ ምልክታ ሳይኖረው ተጠንቶና ተረጋግጦ የተደረሰበት ሐቅ ብቻ እንደሆነ ማሰባቸው ነው። በዚህ አስተሳሰብ ጉያ ውስጥ የሚኖሩ ሐሳባውያን አንድ ሰው እምነትን ሊይዝ የሚችለው አመክንዮ ሲጎድለው ወይም ሙሉ ለሙሉ ከአመክንዮ ተቃራኒ በመሆኑ እንደሆነ ያስባሉ። ነገር ግን የትኛውም አመክንዮ ሰዎች በሚከተሉት (በያዙት) ርዕዮተ ዓለም (Worldview) ውስጥ ሆኖ ከሆኑ እምነታዊ ግምቶች (Presuppositions) የሚነሳ ነው። እነዚህ እምነታዊ ግምቶች በራሳቸው በሳይንስ ያልተረጋገጡ ነገር ግን ለአመክንዮም ለሳይንስም ወሳኝ መሠረቶች ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው። ይኸውም የሳይንስ መሠረቱ እምነት (ማመን) ነው እንደማለት ነው። ሆኖም በዚህ አግባብ እምነት (ማመን) ያልነው ግን ከክርስትና (ወይም ከሌላ እምነት) ጋር የግድ ይመሳሰላል ማለታችን አይደለም። ሳይንስ ዕውቀቶቹን ለመሰብሰቢያነት የሚጠቀምባቸው መንገዶች፤ ማለትም ምልክታ (Observation)፣ ምርምር (Experimentation) ወይም ሌሎች መንገዶች ወሳኝ መሠረታቸው እነዚህ እምነታዊ ግምቶች (Presuppositions) ናቸው። ለምሳሌ፦ ዓለም ወጥነት (Uniformity) እንዳላት ካለምንም ማረጋገጫ መታመኑ በተለያዩ ጊዜያት ለተሠሩ ምርምሮችና ውጤቶቻቸው ቅቡልነት ወሳኝ ሚና አለው። ከዓመታት በፊት የተሠሩ ምርምሮች እና ግኝቶቻቸው ዛሬም ተቀባይነት የኖራቸው፣ እንዲሁም ለሰው ኑሮ ችግር ፈቺ ሆነው መቅረባቸው፣ ከዓመታት በፊት ያሉት ዓለም እና አሁን የምንኖርበት ዓለም ውስጥ ወጥነት (Uniformity) አለ ተብሎ በመታመኑ ነው። አመክንዮ ከእምነት ተለይቶ የሚታሰብ አይደለም፤ የአመክንዮ መሠረቱ እምነት ነው። ጥቂት የማይባሉ ሰዎች የእምነትን እና የአመክንዮን ግንኙነት ከላይ ካነሳነው በተቃራኒው ያስባሉ። እምነት አመክንዮን እንደሚቀድመው አላስተዋሉም። አመክንዮ በራሱ እምነትን የሚቃወም አይደለም። ስለ ምንም ነገር ከማሰባችን አስቀድሞ እምነት አለ። ማለትም ቀድሞ የተመሠረተ ርዕዮተ ዓለምን (Worldview) መነሻ በማድረግ አመክንዮን እንጠቀማለን። የትኛውም አመክንዮአዊ ድምዳሜ ቀድሞ ከተያዘ እምነታዊ ግምት መነሻን ከማድረግ ውጪ መሆን አይችልም። "አመክንዮ" እና "እምነት" የሚጣሉ ባሕርያት የሏቸውም። ነገር ግን ሰው የሁለቱን ግንኙነት በአግባቡ ካልተረዳ፣ የተጣሉ መምሰላቸው፣ ሰውም ከእውነት መለየቱ የማይቀር ይሆናል። አመክንዮ አቅም ሆኖ ከፈጣሪ ለሰው የተሰጠ ቢሆንም፣ እርሱን መቆጣጠር እና በአግባቡ መጠቀም የተቀባዩ የሰው ድርሻ ነው። እምነት (ሃይማኖት) ደግሞ ምንጩ አምላካዊ መገለጥ ብቻ ነው። የሁለቱን ግንኙነት ስናስብ የአመክንዮ አቅጣጫው ከሰው ወደ እግዚአብሔር፣ ከምድር ወደ ሰማይ፣ ከሚታወቀው ወደ የማይታወቀው፣ ከተሰጠው ወደ የሚሰጠው ሆኖ ይታያል። በሌላ በኩል ደግሞ ሃይማኖት ከእግዚአብሔር የተገለጠ እንደመሆኑ አቅጣጫው ከእግዚአብሔር (ከፈጣሪ) ወደ ሰው (ፍጥረት)፣ ከልዑሉ ወደ ትሑቱ ሆኖ ይታያል። "አመክንዮ" ወደ ልዕልና (ወደ ከፍተኛው) እንዲደርስና የበለጠ ዕውቀት ጋር እንዲደርስ፣ ሃይማኖት (መገለጥ) ከላይ መጥቶ አመክንዮን ወደ ልዕልና ማውጣት አለበት። አመክንዮ እስከሚያየው "ደመና" ድረስ እንጂ ከዚያ በላይ ስላለ ምስጢር ማወቅን ቢፈልግ፣ ከሃይማኖት ጋር መተባበርን መፈለግ እና መናፈቅ አለበት። ከሃይማኖት ጋር ከተባበረ ሃይማኖት አመክንዮን ወደ ላይ አውጥቶ ስለመገኛው (ስለ እግዚአብሔር እና ቅዱሳኑ) ሲነግረው አመክንዮ ዝም ብሎ ይሰማል እንጂ ያልደረሰበትን ቤት "ልግለጽ" ብሎ ራሱን አያደክምም። ሃይማኖትና አመክንዮ እየተደጋገፉ እስከ ሰማይ ቢደርሱም ከዚያ በላይ ልዕልና ያላቸውን ምስጢራት አመክንዮ ሊገልጽ አይቻለውም። ነገር ግን አመክንዮ ጠፋ ማለት አይደለም። እንደውም አመክንዮ ከልቡና (ከዕውቀት) የማይለይ በመሆኑ በፍቅር በሚቀርብ ምስጋና ሃይማኖትን (ማመንን) ለልዑል አምላክ ሲያቀርብ ይኖራል። "ማየት ማመን ነው" ተብሎ ሲነገር ብዙ ጊዜ እንሰማለን። እውነት ነው፤ በማየት በኩል ሰው ዕውቀትን ገንዘብ አድርጎ እምነት (ሃይማኖት) ላይ ይደርሳል። ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራትና መንክራት ጀርባ ያለው ዋናው ጉዳይ ይኸው ነው፤ ሰዎች አይተው እንዲያምኑ። እንደ ማየት ሁሉ በመስማትም፣ በመዳሰስም ማመን ላይ ይደረሳል። ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ የክርስቶስ ትንሣኤ እውነተኛ መሆኑን ጎኑን በመዳሰስ እንዲያምን የክርስቶስ ፈቃድ ሆኗል (ዮሐ 20:27)። መስማትም እንዲሁ ወደ ሃይማኖት ያደርሳል። "እምነት ከመስማት ነው፤ መስማትም የእግዚአብሔር ቃል ነው" (ሮሜ 10:17) ብሎ የተወደደ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረ። ቢሆንም ግን "ማየት ማመን ነው" ብቻውን ግማሽ ጌጥ ነው፤ ሙሉ አይደለም። "ማየት ማመን ነው" ሙሉ ይሆን ዘንድ "ማመን ማየት ነው" የሚለውን ይፈልጋል። ማየት (ዕውቀት) ወደ ማመን እንደሚያደርስ እንዲሁ ሃይማኖት ወደ ማየት (ርዕይ - ዕውቀት) ያደርሳል። የመጀመሪያው በአካሄድ ስህተት የተነሳ ወደ እውነተኛ ሃይማኖት ባያደርስ እንኳ እውነተኛ ሃይማኖት ግን ወደ እውነተኛ ዕውቀት (ጥበብ) ያደርሳል። ማመን ወደ ዕውቀት ሲያደርስም በልብ ውስጥ ባሉ የውስጥ ሕዋሳት መንገድነት ነው።
Reviews channel
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
21 mezmur is a Telegram channel in the category «Другое», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 21.8K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 12.3, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 6.0 ₽, and with 9 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий