
- Main
- Catalog
- Books, Audiobooks & Podcasts
- Advertising on the Telegram channel «ልብ❤️ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች💞»
Advertising on the Telegram channel «ልብ❤️ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች💞»
A place to learn something from our story if its sad or happy.
Channel statistics
ከዚህ በፊት እኮ እንደዚህ አይነት ባህሪ የለሽም አሁን ይሄን ባህሪ ከየት አመጣሽው አለች ለራሴ ግራ ተጋብቻለው አንቺ ቀልጂብኝ አልኳት አንደ መሳቅ አለችና እኔምልሽ ልጠይቅሽ ያልኩትን አታረሳሽኝና አብሪሽን ግን ትወጂዋለሽ እንዴ አለችኝ ደነገጥኩ ምን ማለት ፈልገሽ ነው ስላት ኮሰተር አለችብኝ አንዴት እንደዛ ልትይኝ ቻልሽ ስላት በተደጋጋሚ ሰለ እሱ ሳወራ ጥሩ ፊት አታሳይኝም በዛ ላይ ያንቺን ፎቶ ስልኩ ላይ ያየሁ መሰለኝ አለች እና ምን ይጠበስ አልኳት ካለሰቸገርኩሽ አሳ በቤዚን አለችኝ ተሳስቀን አለፍ ነው ሌላ ወሬ ጀመርን ድጋሚ ሳታነሳብኝ ቀረች ከዛን ቀን በኋላ ግን የፍቅርተ ጤንነት በጣም ያሰጋኝ ጀመር በጣም ትታመማለች ከበፊት ባህሪዋ ወጣለች ልውጥውጥ ብላለች አንድ ቀን አብሪሽ ጋር ጋር እያለሁ ደወለችልኝ ላነሳ ብዬ አመነታሁ ተውኩት ድጋሚ አልደወለችም በነጋታው እቤታቸው ልጠይቃት ሄድኩ ሳላገኛት ሁለት ሳምንት አልፎኝ ነበር ወደ ቤታቸው ስገባ እናቷ በሃዘን ተውጣ በረንዳ ላይ ቁጭ ብላለች እማ ምን ሆንሽ ብዬ ሰላም አልኳት ለመናገርም ከበዳት አይኖቿ ደክሟል ወደ ውስጥ ስገባ ደነገጥኩ ቀልቤ ነው የተገፈፈው ፍቅርተ ከሰውነት ጎዳና ወጣለች እንደ ህፃን ልጅ ብቻዋን ትስቃለቸ እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ እግሯ ስር ቁጭ አልኩ ፀጉሬን አየነካቸው ትስቃለች ምነው አምላኬ በደሌን ብታበዛው አልኩ ተነስቼ አቅፊያት ቁጭ አልኩ እጄ ይንቀጠቀጣል ትንሽ እንደ ቆየች እንቅልፏን ተኛች እኔ ላይ እኔስ ምሆነውን አጣሁኝ ለወንድ ልጅ ብዬ ጓደኛዬን ገደልኳት በህይወቷ ቀለድኩባት ህይወቷን አበላሸሁት እንባዬ የለበስኩትን ልብስ አራሰው ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ነቃች ረዱ አለችኝ ወዬ እልኳት እንባዬን ጠራርጌ ምን ሁነሽ ነው ምታለቅሺ መች መጣሽ ቆየሽ እንዴ አለችኝ ማበድ ብቻ ነው የቀረኝ እንባዬ አልቻልኩም እናቷ ወደ ውስጥ ገብታ እኔን ስታይ አፏን አፍና ወደ ውስጥ ገባች በኔ ምክንያት ይሄ ሁሉ ሲፈፀም መኖሬን ጠላሁ ረዱ አብሪሽ እኮ ናፍቆኛል አለች አይኗቿን እያንከራተተች ምመልስላትን አጣሁ ትንሽ ቆይታ እንደ ገና ክትክት ብላ ሳቀች ከተቀመጥኩበት ደነግጬ ተነሳሁ እዩት እዩት ሮጠ ትላለች አምላኬ ምን አደረኩ የሰው ልጅ ሳሳብድ እንደ ምን ፈቀድክልኝ ብዬ ከቤት ሩጬ ወጣሁ ግቢ ውስጥ ተነበርክኬ አለቀስኩ ወድያው እንባዬን ጠራርጌ ወጣሁ ወደ መድሃኒት አዋቂው ቤት ተነስቼ በረርኩ መሰር ላይ እስክ ወጣ ነፍሴን አላውቅም አንድ ትልቅ እንቅፋት ጥፍሬን ነቀለው አበድኩ ዳር ላይ ተቀምጠው ያሉ ወንዶች እየተሯሯጡ ወደ እኔ መጡ ወደ አንድ ሱቅ ተሸከመው አስጠጉኝ ከዛን በኋላ ምን እንዳደረጉልኝ አላውቅም ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ከሃሳቤ ስመለስ አንድ ልጅ አጠገቤ ተቀምጧል እግሬን በጨርቅ ጠቅልለውልኛል ደነገጥኩ ተነስቼ ወደ መሰመሩ በፍጥነት ልወጣ ስል እረ ትንሽ ተረጋጊ ይድረቅልሽ ይለኛል ልጁ እየተከተለኝ ልቤ የሰው ህይወት እያደረቅሽ የራስሽን ምታለመልሚ ይመስልሻል ይለኛል ልክ መሰመሩ ላይ ስደርስ ከየት መጣ ያልተባለ ሞተር እኔን እየተከተለ ያለውን ልጅ አየር ላይ አዋለሁ ልጁ ለብቻ ሞተሩ ለብቻ ተገነጣጥለው ቁጭ አሉ እኔ ለመጨውም ለማልቀስም አቅሙን አጣሁ ተዝለፍልፌ ወደኩ ስነቃ ሆስፒታል ውሰጥ ነኝ እህቴ አጠገቤ ተቀምጣለች ነገሮችን ለማስታወስ ሞከርኩ መውደቄን አውቀዋለሁ ከዛን በኋላ ያለው እንዴት እንደ ሆነ ግን ምንም ሊገባኝ አልቻለም ልነሳ ስል የወደኩበት ጎኔ እና እንቅፋት የመታኝ ጥፍሬ በጣም አመመኝ እህቴ ትንሽ አረፍ በይ ብላ መልሳ አስተኛችኝ ምን እየተፈታተነኝ እንዳለ አላውቅም እንድ ማላውቀው ሃይል ውስጤ ላይ ይገፋፋኛል እህቴ ግን እንደው ምንድ ነው የሆንሽው አለችኝ መልስ አልሰጠኋትም ወደ ቤት እንሂድ ብዬ እንደ ምንም ለመነሳት ሞከርኩ ቀና ስታደርገኝ ተነሳሁ ራሴን መሸከም ከብዶኛል እንደ ምንም እቤት ደረስን እቤት ላይ በፍቅርተ መታመም እና በእኔ እንዲህ መሆን በጣም ተደናግጠዋል አዳሬን ሳልተኛ አደርኩ በጥዋት ስነሳ እግሬ አብጦ መጓዝ አቃተኝ ግን ስራዬ ሰለ ሆነ ይበለኝ አልኩ ወደ ቤተክርስትያን ሂጄ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ይሄ ሁሉ ምን ቢኖርብኝ ነው ክፋትን አርግዤ እርኩሰትን የዘራው አልኩ ወደ መድሃኒት አዋቂው ቤት ልሄድ የነበረውን ሃሳቤ ሰረዝኩ ምን እንደ ማደርግ አላውቅም ግን ያበላሸሁትን የፍቅርተ ህይወት ወደ ቦታው መመለስ እንዳለብኝ ውስጤ ይነግረኛል ከዛውጭ መቼም ሰላም እንደ ማላገኝ ይሰማኛል አሁድ ሰለ ነበር ቤተ ክርስትያን ለብዙ ሰአት ተቀመጥኩ ከሰአታት በኋላ ፀበል በአንድ ትንሽ ህቃ አስቀዳውና ቀስ ብዬ እያነከስኩ ወደነ ፍቅርተ ቤት ሄድኩ ታክሲ ሰለፍ ሰለ ነበር በላዳ ኩንትራት ይዤ ሄድኩ ሁሉም ነገር ምስቅልቅል ብሎ ብኛል ነገሮች ጠመውብኛል ለነገሮች ያለኝን አመለካከት በሰፊው ቀየረብኝ ሳስበው አንድም በራሴ ያደረኩት ያለ ነገር አልመስለኝ አለ እኔ እስከ ማውቀው ድረስ እንደዚህ አይነት ክፉ ሴራ አይደለም እኔ ልስራባቸው ተደረገ ሲባልና ስሰማ እንኳ ይቀፈኛል ዛሬ ግን እኔው ራሴ በገዛ እጄ አደረኩት እነ ፍቅርተ ቤት እንደ ደረስኩ ግቢው ታምሷል ደነገጥኩ ሁሉም በግርምት ቁሞ ያያል ፍቅርተ ሰው አልቀርብ ብላ ሰውን እንደ ውሻ ልትባላ ምንም አልቀራትም የሰፈር ሰዋች በጉልበት አስረው ይዟታል ሳያት መሬት ተከፍታ በዋጠችኝ አልኩ እንደዛ እያበደች ከሩቁ እኔን ስታየኝ ረዱ አለች ፊቷ ተፎነጫጭሯል እንደዛ በንዴት እና በእልህ ተሞልታ የነበረችው እኔን ስታይ አይኗቿ እንባ ቋጠሩ ሰዋችን አልፌ ወደ እሷ ስሄድ እረ ባክሽ ትጎዳሻለች ቆይ አሉኝ ዙሬ ስላያቸው ሂጄ አቀፍኳት ረዱ አሰሩኝ እኮ አለች አይዞሽ መጣሁልሽ እኮ አልኳት የያዟት ወንዶች መረጋጋቷን ሲያዩ ልቀቋት የታሰረችበትን ገመድ ፍትቼ በሱ መታነቅም አማረኝ ወደ መኝታ ክፍሏ ይዣት ገባሁ ረዱ እኔን እኮ ማንም አይወደኝም አደል አንቺ ብቻ ነሽ አደል ትላለች እንደ ህፃን ልጅ አይን አይኔን እያየች እንባዬ ይፈሳል ጉንጬ እንደ እሳት ይለበልበኛል እንደ ምንም አባብዬ ትንሽ እንድታርፍ አደረኳት እኔ ላይ ተኝታ ግንባሯን ስነካው እንደ እሳት ይፋጃል ያመጣሁትን ፀበል ትንሽ በእጄ አድርጌ ግንባሯ ላይ ሳደርግላት አይኗ ግልብጥብጥ አለ በድንጋጤ ደርቄ ቀረሁ…
✎ ክፍል 9 የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል... አንብበው ሲጨርሱ LIKE
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
ፀበል ትንሽ በእጄ አድርጌ ግንባሯ ላይ ሳደርግላት አይኗ ግልብጥብጥ አለ በድንጋጤ ደርቄ ቀረሁ ነፍሱ ሊወጣ እንዳለ ሰው ሚያደርጋትን አሳጣት በጣም ደነግጫለሁ ፊቷ ቅይር ይር አለ ነገሩ በፈጣሪ እጅ መሆኑን ገባኝ ሳልውል ሳላድር ወደ ፀበል ቦታ ይዣት ለመሄድ ወሰንኩ ቀስ ብዬ ለእናቷን ያለውን ነግሬ ፀበል መሄድ እንዳለብን ስነግራት እንኳን ፀበል ልትሄድ ከዚህ ግቢ እግሯ ሲወጣ እንደ እብድ ሰለ ምትወራጭ ማንም ሚችላት ሰለጠፋ እና አቅሙን እንዳጣች ነገረችኝ በለቅሶ ብዛት አይኖቿ ደክሟል ወደ ቤት ተመለስኩና ፍቅርተን ይዤ ወደ ፀበል ቦታ ልሄድ እንዳሰብኩ ስነግራቸው ምንም ሊቀበሉኝ አልቻሉም እኔ መሄድ ምፈልገው ብቻዬን ይዣት መሄድ ነው እኔ ያበላሸሁትን ህይወት ማንም እንዲያስተካክልልኝ አልፈልግም ራሴው እንጂ እንደ ምንም ከስንት ጭቅጭቅ በኋላ እያጉረመረሙም ቢሆን እሺ አሉኝ ማታ ላይ ነገ ይዤ ምሄደውን ልብስ እያዘጋጀው አብሪሽ ደወለ ድንግጥ አለ ልቤ ሳላገኘው ሳምንት ሁኖኛል ይፅፍልኛል ይደውልልኛል ምን ብዬ ልመልስለት ይሄ ሁሉ ነገር በእሱ ምክንያት አይደል የተፈጠረው ስልኩን ከማንሳቴ ነፍስ ገዳይ እንኳ ይቅር ይባላል እኮ አለኝ አብሪሽ እንዴት ነህ አልኩት ሚገርመው እንዲህ ተናድጄ ራሱ ግን ይናፍቀኛል ጥፋቴን በግልፅ ማትነግሪኝ አንቺ እና ፍቅርተ መሃልስ የተፈጠረው ምንድ ነው እቤት ስመጣ የለችም ይሉኛል ስደውልልሽ ስልክ አታነሺም ምንድ ነው ችግርሽ አለኝ በልቤ የኔ ችግር እና ጉድ መች ተዘርዝሮ ያልቃል ብለህ ነው ብዬ ሁሉንም በቅርብ ስንገናኝ ያለውን እና የተፈጠረውን በግልፅ አስረዳሃለው እስከዛው ግን ታገሰኝ አልኩት እስኪ እሺ ይሁን ብሎኝ የተወሰነ አወራን ጥዋት ላይ ወደነ ፍቅርተ ቤት ሄድኩኝ ስሄድ ፍቅርተ ተኝታለች እናቷ ልብሷ አዘጋጅታልኝ ነበር ግን ሁሌም የኔን ልብሶች መልበሰ ሰለ ምትወድ ከእኔ ልብሶች እሷ ምትወደውን ልብስ ይዤላት ነበር የመጣው እና የሷን ልብስ ተይው ብዬ ፍቅርተ ቀስቀስኳት ለተወሰነ ደቂቃ ዝም አለችኝ ረዱ ምነው ከመሸ መጣሽ አለችኝ ሳቄ ለቀኩኝ ደብሮኝ አልኳት እና ልዝፈንልሽ አለች በፊት ደበረኝ ስላት እኔ ካለሁበት ስሜት እኔም ለማውጣት የማታደርገው ነገር የለም አይ እኔ ለሽርሽር ሌላ ሀገር እንድትወስጂኝ ነው ምፈልግ አልኳት ሳቅ አለችና እመዬንስ እንዴት አድርገን አለች አንቺ ጠይቂያት አልኩ የእውነት ለመናገር እንደ ህፃንም ያደርጋታል ግን በቃ ሁሉንም የቤተሰቦቿን ቁጥጥር ምንም አልረሳችውም ቀስ ብላ ወደ ላይ ቤት ብቻዋን ሄደች ሁኔታዋ ሰለ ሰገረመኝ ከኋላ ተከተልኳት እናቷ ስታያት ደነገጠች እማ ረዱ እኮ መዝናናት እፈልጋለሁ ብላ ከከተማ ወጠን እንምጣ ብለን አለች እየተሸኮረመመች ግን እንቆይም አለቻት እኔ ሳቄም መጣኝ በቃ ጤነኛ ሰው ሆነች እናቷ ግራ ተጋብታለች ከኋላ ሁኜ ጠቀስኳት አይሆንም እኔ ዛሬ ስራ አለብኝ አለቻት እማ ደግሞ አንቆይም እኮ አለቻት ትንሽ እንደ ማቅማማት ብላ ሳምንት በላይ እንዳትቆዩ ስትላት ተነስታ አቅፋ ሳመቻት እማ ወደኔ ሩጣ መጣች ፈቀደችልን እኮ አለች እንዲህ ሁና ሳያት ደስ አለኝ በመሃል ግን ስልብ ያደርጋታል የት ፀበል መውሰድ እንዳለብኝ ወስኜ ሰላደርኩ ለእነሱ ግን መናገር አልፈለኩም እኔ ከምሄድበት እቅጣጫ ሌላ ቦታ ነገርኳቸው እና ፍቅርተ ጋር ተያይዘን ወጣን ጉዟችንን ወደ ባህር ዳር አደረግን እንደ ደረስን ትንሽ አረፍ ብለን ጉዞ ጀመርን ትንሽ ኪሎ ሜትር እንደ ተጓዝን ሃንዳስ ጊዮርጊስ ደረስን በእግር እየሄድን ልንደርስ ስንል ወዴት እየ ሄድን ነው አለችኝ አንድ ማሳይሽ ነገር አለኝ አልኳት ያንጠራራት ጀመር ያስፏሽካታል ረዱ እኔ ከአሁን በኋላ መሄድ አልችልም አለችኝ ምን አልኳት… አዋ እኔ ደስ አላለኘም ብላ አንድ ድንጋይ ላይ ቁጭ አለች አሁን አማራጭ መፈለግ እንዳለብኝ ወሰንኩ ወደ ቤተ ክርስትያኑ የሚሄዱ ከሩቅ ወደኛ እየመጡ ይታዩኛል የተሸከምኩትን ሻንጣ አስቀመጥኩና ወደነሱ ኋላ ተጓዝኩ ትንሽ ርቄ ቆምኩ ሰዋች አጠገቤ ሲደርሱ ሰላም ብያቸው ያለውን ነገርኳቸው እና ወንዶች ችግር የለውም አሉኝና ከኋላዬ ሆኑ ወደ ፍቅርተ ተመለስኩና ነይ በቃ ሻንጣውን አስቀምጠን እንመለስ አልኳት አንቺ ደርሰሽ ነይ አለችኝ እዚህ ቦታ መጥፎ ነው ወንዶች ይታናኮሉሻል አልኳት ማንም አይነካኝም አለች ከኋላ ተመልከቻቸው ባርዝፍ ውስጥ ተደብቆ ሚያዩንን አልኳት ዞር ስትል ያልታዩ መስሎ ግን እኛን እየተከታተሉን ያሉ መሰላት ከተቀመጠችበት ደንግጣ ተነሳች እንደ ምንም እየተቀራፈፈችም ቢሆን ቤተክርስትያኑ ለሰይ ደረስን ከዛን በኋላ መሄድ አልቻለችም ያነጫንጫት ጀመር ከኋላ የነበሩ ወንዶች መጠው እጇቿን ያዙልኝ እንደጉድ ተወራጨች የፀበልተኛ ቤትም ገባን ለአንድ አባት ያደረኩትን ሁሉንም ነገር አንድ ሳይቀር ነገርኳቸው አባ እባኮትን የቻሉትን ሁሉ ይርዱኝ አልኳቸው ልጄ አንቺ የበደልሻትን ነፍስ አንቺው ለማንፃት ማምጣትሽ እደለኛነሽ ዛሬ ባትመጣ ኑሮ ህይወትሽ እንደ ተመሰቃቀል እንቅልፍ እንዳጣሽ ትኖሪ ነበር አለኝ ተመስገን አልኩ በልቤ ፈጣሪ ቸር ነው ምን ይሳነዋል ፍቅርተ ፀበል ቦታ ላይ እንደ ማነኛውም እብድ ያደርጋታል መንገድ ላይ ከኋለችን የተዋወኳቸው ሰዋች በጣም ረዱኝ ፍቅርተን እንደ እህታቸው ነው ስትዘል ስትነሳ ምንም ነገር ስትሆን ጠብቋት እንደ ተባለ ሰው ከስሯ አይጠፉም ግራ ቢገባኝ ግን ትዕግስታቹ በጣም ይፈትናል አልኳቸው ከመሃከላቸው አንዱ እቺ ምታያት እህታችን እንዲህ ነበር አምሮዋን ስታ የነበር ዛሬ ድና መጣች እንጂ አሉኝ ተስፋዬን አለመለሙት ግን ይሄ ህመም ቆየባት እንዴ አሉኝ ዝም አልኩ እንባዬ ጉንጬ ላይ ፈሰሰ ይቅርታ ተይው ማይሆን ነገር ነው ያነሳንብሽ አሉኝ እረ አልቆየባትም ሰበቡ እኔው ነኝ ብዬ ያደርኩትን ነገርኳቸው ከምንም በላይ የገረማቸው መድሃኒት ለእሷ መስጠቴ ሳይሆን እኔው ራሴ ይዤ መምጣቴ ነው ከዛን በኋላ በጣም አቀረቡኝ ምንም ነገር ሲሆን ከጎኔ ናቸው ፍቅርተ መፀበል ከመጀመሯ በፊት እጣን እና ጧፍ ከከተማ ሰዋች ጋር ልገዛ ወጣሁ ዝናብ ሰለ ነበር መመለስ ግን አልቻልኩም እዛው አድሬ ጥዋት ላይ ሰመለስ ፍቅርተ ትንቀጠቀጣለች ትናት አንቺ ከሄድሽ በኋላ እኮ የመጨረሻ ሊያሳብዳት ሲደር አባ ፀበል አስገቧት ብሎ አንደ ገባች እና ብዙ ነገር እንደ ለፈለፈች ነገሩኝ በድንግጤ ክው አልኩ እኔ መምጣቴ በፊትም ተፀብለሰ እንደወጣች ነገሩኝ ደንጋጤ ሊያራምደኝ አልቻለም በሳምንት ውስጥ ሙሉ ጤናዋ ተመለስ ለሁለት ሳምንት ድጋሚ ተፀብለን ሙሉ በሙሉ ድና ሳይ ፈጣሪን አመስገንኩት ፍቅርተ መች እና እንዴት እንደመጣን ምንም አታውቅም እኔም አብሪሽን ካወኩበት ቀን ጀምሮ እስከ አሁን ያለውን እና ያደረኩባትን ሁሉ ነገርኳት በአንባ ታጠበች ሰለ ሁሉም ነገር ይቅር አለችኝ ልቤ በደስታ ተሞላ ከአንድ ወር በኋላ ወደ ቤታችን ተመለስን እናቷ ስታያት ይሄን እውነት መቀበል አቃታት ቤታቸው በኔ ምክንያት የደፈረሰው ሰላም እንደ አዲስ በፍቅር ተሞላ በሚቀጥለው ቀን ከአብሪሽ ደወልኩ ስልኬ ዝግ ሰለ ነበር ስደውል አላመነም በደስታ አበደ…
♾ተፈፀመ♾
ምስጋና ፦ ታሪኩን በመከታተል ሀሳባችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ ምስጋናዬ ይድረስልኝ
፦ ሁላችሁንም ክበሩልኝ በቅርቡ በአዲስ ስራ እመጣለሁ ሀሳባችሁን Comment ላይ አሳውቁኝ 🙏
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
አንብበው ሲጨርሱ Like & Share ♥️ ማድረግ አይርሱ
┄┄┉┉✽✽✽ ┄┄┉┉
ይልቅ ምን ነበር ያልሽኝ አልኳት ምን መሰለሽ ረዱ አብሪሽ ጋር እንድታስታርቂኝ እፈልጋለሁ አለችኝ ልቤ ስንጥቀ አለ አንድ ትልቅ ነገር ልትነጥቀኝ እጇን የሰነዘረች ያህል ተሰማኝ ፍቅርተ ጋር ብዙ ወንዶችን ሼር ተደራርገናል አሁን ግን በምወደው ሰለ መጣች ይሆን ላያትም አስጠላችኝ አልገባኝም ለምንድ ነው ምትታረቁት አልኳት እህ ረዱ እንዲህ ይባላል አለችኝ የተናገርኩትን እንኳ በቅፅበት ማስታወስ አቃተኝ ፈገግ አልኩና በምን ተጣልታቹ ነው አልኳት እሱ ለእኔም ጥያቄዬ ነው ምን እንዳስከፋሁት አላውቅም አለች ታድያ ምን ችግር አለው ለእኔ ተይው አልኳት ውስጤ እያረረ ግን ያልገባኝ እስከ ማውቅሽ ድረስ አንዴ ጥሎሽ የሄደን ወንድ ዞር ብለሽ አታይውም ታድያ አሁን ምን አዲስ ነገር ተገኘ አልኳት አብሪሽ ይለያል ሰልሽ አለች እየሳቀች መሆን አለበት በዬ እኔም አብሪያት ሳኩ እንዳይመሽ የለ መሽቶ ወደ ቤቷ ሄደች ያለችው ነገር በጣም አናደደኝ እየቆየ ሲሄድ አብሰለሰለኝ በሁለተኛው ቀን አብሪሽ ጋር ተቀጣጥረን እየሄድኩ ድነገት በልቤ አንድ ሃሳብ መጣ አሁን ይሄን ነገር ለአብሩሽ ነግሬው እሺ ቢለኝስ አልኩ ግራ ተጋባሁ እኔስ ብሆን ላስታርቃችሁ ብዬ ማወራው ምን ነክቶኝ ነው ብዬ የመጠየቅ ሃሳቤን ተውኩ አብሪሽን እንዳገኘሁት ደስ አለኝ አብረን ዋልን ነገሩንም አላነሳሁበትም ግን ልቤ ፍረሃት ፍረሃት ብሎኛል እንደ ተለመደው በራችን ላይ አድርሶኝ ስሞኝ ተመለሰ ፍቅርተ ጋር ሳንገናኝ ሳምንት አለፈን እስከ አሁን እንዴት እንዳልደወለች ገርሞኛል አብሪሽ ጋር ሳንደዋወል ሁለት ቀን ሆነን የፍቅርተ ነገር ሰለ ማይታመን እቤታቸው ልሄድ ብዬ ስደውልላት ስልክ አታነሳም ደንገት ማልሄድ ብዬ ወደ ቤታቸው ሄድኩ ውስጤ ምንም እረፍት ሊሰጠኝ አልቻለም መንገድ ላይ ጄሎ ምንለውን ጓደኛችንን አገኘሁ ሰላም ተባብለን ወደነ ፍቅረተ ቤት እየሄድኩ እንደ ሆነ ነገሬው አብረን እንሂድ አልኩት ኳስ ላይ እየሄድኩ ነው ብሎኝ በግድ አብረን እንድን ሄድ አደረኩት ሲናገር ትንሽ ኮልተፍ ስለሚል አንደበቱ ደስ ይላል በዚህ ማሃል ሰፈራቸው ልንደርስ ትንሽ ሲቀረን ፍቅርተ ካፌ ላይ ሰው ጋር ቁጭ ብላለች የሰውዬው ማንነት አልለየኝ አለ ፀሃይ ሰለ ነበር ጥላ ወዳለበት ጥግ ያዝኩኝና ደወልኩላት ልክ ሲጠራ ስልኩን አይታው የእኔን መሆኑን ስታውቅ ቁጭ አደረገችው በጣም ተናደድኩ ጄሎን ቆየኝ ብዬ ወደ ካፌው በር ስጠጋ ጀርባውን ወደ እሷ አዙሮ የተቀመጠው አብሪሽ ነው ደነገጥኩ በፍጥነት ወደ ኃላ ተመለስኩ እንዴት ተገናኙ ማለት አልችልም ማደርገውን አጣሁ ጄሎ ምን ሆንሽ አለኝ መልስ ሳልሰጠው ወዴት እንደ ሚሄድ ማላውቀው ታክሲ ውስጥ ገባሁ ንዴት ይሁን ቅናት አላውቀውም ውስጤ ግን ተቃጥሏል የተወሰነ መንገድ ከሄድኩ በኋላ ከሃሳቤ ያነቃኝ ረዳቱ ሂሳብ ሲለኝ ነው ሁለት ሴቶች አጠገቤ ተቀምጦ ያንሾካሹካሉ ወሬያቸው ጆሮዬን አቆመው ሰለ አንድ አዋቂ ደብተራ ነው ሚያወሩ…
✎ ክፍል 7 ይቀጥላል... አንብበው ሲጨርሱ LIKE
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
ሰለ አንድ አዋቂ ደብተራ ነው ሚያወሩ ሚኖረው ወደ ቃሊት እንደሆነ አንደኛው ለጓደኛዋ ሰፈሩን ሳይቀር ነገረቻት ልቤ ክፉ ሆነብኝ አስቤ ማላውቀውን አሳሰበኝ ወራጅ ብዬ ወድያው ወረድኩ ላዳ ኩንትራት ይዤ ወደ ቃልቲ ሄድኩ የልቤ ምት ጨምሯል ወደሚባለው ሰፈር እያጠያየኩ ሄድኩኝ እዛ ስደርስ የተባለውን አዋቂ ሳጠያይቅ በቀላሉ አገኘሁት ገብቼ ሰውዬውን በሚስጥር ያለውን ነገር ነገርኩት እሱም ክፍያው እንደሚወደድብኝ ነገረኝ የፈለገው ይሁን እከፍላለሁ አንተ ብቻ ያልኩህን አዘጋጅልኝ አልኩት ለሱ አታስቢ ብሎ ነገ ጠዋት ብሩን ይዤ መጥቼ መዳኒቱን መውሰድ እንደምችል ነገረኝ ምንም አላመነታሁም በነጋታው የጠየቀኝን ገንዘብ ይዤ ሄድኩኝ ልቤ እንደ መፍራት ብሏል መዳኒቱን የምታደርጊበት ሰው በሚወደው ምግብ ወይም በሚጠጣው ነገር ውስጥ አድርገሽ ብትሰጪው ከጥቂት ቀናት በኃላ ውጤቱን ታያለሽ አለኝ እኔም ብሩን ከፍዬ መዳኒቱን ይዤ ወደ ቤቴ ሄድኩኝ እንዴት አድርጌ ለፍቅርተ መስጠት እንዳለብኝ ሳስብ ውዬ አደርኩ ነገውን እራሷ ደውላ ከልተገናኘን አለችኝ እኔም ከእሷ ስጠብቅ ሰለ ነበር ነገሮች ተመቻቹልኝ ወደነሱ ቤት ሄድኩ ሰደውልልሽ እኮ አታነሺም አልኩ ሰው ጋር ሰለ ነበርኩ እኮ ነው ያላነሳሁልሽ ደግሞ ሳልነግርሽ አብሪሽ ጋር እኮ ታረቅን አለችኝ ነው እንዴ ደስ ይላል አልኳት ምነው ደስ ያለሽ አትመስይም ስትለኝ እኔ ላስታርቃቹ ብዬ ደፋ ቀና እያልኩ ነበር አልኳት እዛው በደፋሽ ብላ ተሳስቀን ቡና ማፍላት ጀመረች ውስጤ እርር ብሏል እና አብሪሽ ምን አለሽ አልኳት ሰርፕራይዝ እኮ ነው ያደረገኝ አለች ምን አልኩ ረዱ ሙች እዛኔ ልብድካም ቢኖርብኝ ዛሬ አጠገብሽ አታይኝም ነበር አለች አሁንስ ቢሆን ባላይሽ ደስታዬ አይደል አልኳት ምን አልሽ አለች በይማ ንገሪኝ ጉዴን አልኳት እህ ሰለ ምን ጉድ ነው ምታወሪ አለችኝ ስቀለድሽ ነው ምንድ ነው ከመጀመርያ ጀምረሽ ንገሪኝ አልኳት ቆይ መጀመርያ ይሄን ልጨርስ ብላ ስራዋን ቀጠለች ትንሽ ቆይታ ሚባላ አመጣችና ውሃ ልታመጣ ወደ ውስጥ ገባች እኔም ይዤ የመጣሁትን መድሃኒት በፍጥነት አውጥቼ በእሷ በኩል አድርጌበት ደረቅ እንጀራውን አለባበስኩት እንዳይታወቅ እጄ በጣም ተንቀጠቀጠ ውሃውን አምጣ አስጣጥባኝ ቁጭ አለች ልትበላ ስትል ልቤ ወጦ ሊሄደ ደረሰ ምን ሆንሽ ረዱ ፊትሽ እኮ ልክ አይደለም አለች አፌ ተሳሰረ ምን ብዬ ልመልስላት ብይ ብላኝ በራሷ በኩል ቆርሳ ስትጎርስ እኔ መብላት አቃተኝ እንዴት አድርጌ ልጉረስ እጄ አልታዘዘኝ አለ እንደምንም የግዴን 2 ግዜ ጎርሼ በቃኝ አልኩ ግን ምን ሁነሽ ነው አለችኝ ምንም አልሆንኩም አልኳት እሷም ትንሽ በልታ አነሳችው ሰለ እውነት መድሃኒቱ ከሰጠኋት በኋላ ውስጤ በጣም ተረበሸ ምን አለ በቀረብኝ አስባለኝ አዋቂው ደብተራ የሰጠኝ መድሃኒት እሱን እንድትጠላው የሚያደርግ ነው አለኝ ግን ቢሆንም ፍቅርን በፍቅር እንጂ በብልጠት ፍቅርን የራስ ማድረግ መች ይቻላል አልኩ በልቤ አጠገቤ ተቀምጣ ቡና እያፈላች እና ረዱ እልሻለሁ አብሪሽ ሳላስበው አንዲት ልጅ አፍቅሬልሻለሁ ብሎኝ ሰረፕራይዝ አላደረገኝም መሰለሽ አለች እየሳቀች ግራ ተጋባሁ እህ እንዴት እንዴት ነው ምታወሪው አልኳት የደወልሽልኝ ቀን እኮ አብሪሽ ጋር ነበርኩ በጣም አናዶኝ ሰለ ነበር ነው ስትደውይ ያላነሳሁልሽ አለችኝ እና ይሄን ነው ሰርፕራይዝ አደረገኝ ምትይ አልኳት ረዱ ደግሞ እኔ ወድጄሃለው ብዬው ስሄድ እሱ ሌላ አፍቅሪያለሁ ብሎ ሲነግረኝ ታድያ ከዚህ በላይ ሰርፕራይዝ አለ እንዴ ብለ ሳቀችብኝ የእውነት ለመናገር ከቅድሙ የባሳ መድሃኒቱን ሰለ ሰጠኋት ውስጤ ሰላም አጣ ትንሽ ቆይቼ ወደ ቤት ተመለስኩ ምን አይነት ሴጣናዊ ስራ እንደ ሰራሁ አምሮዬ አምኖ መቀበል ተሳነኝ እኔ የማውቃት ረድኤት ጥላኝ የሄደች መሰለኝ ከቀናት በኋላ ፍቅርተ እንደ ታመመች ሰማሁ በጣም ነው የደነገጥኩኝ ስራዬን ሰለ ማውቅ ምን ብዬ ምን ሁና ልበል ግን ደግሞ ግራ ተጋባሁ የሰጠኋት መድሃኒት ሚያሳምማት ነው እንዴ የጥላቺ እንጂ ብዬ ውስጤ እረፍት አጣ እንደምንም ከሰአት በኋላ ራሴን አረጋግቼ ላያት ሄድኩ ተኝታለች ሰላም ብያት አጠገቧ ቁጭ አልኩ ምንሽን ነው አልኳት ራሴን ነው አለች እንኳንም ሆዷ አልሆነ አልኩ በልቤ ትንሸ ካወራን በኋላ ግን ረዱ አንድ ልጠይቅሽ ምፈልገው ነገረ አለ አለችኝ ልቤ ስንጥቅ አለ ምገባበት አጣሁ ምን ሆንሽ አለችኝ ምን ልመልስላት አፌ ቃል አላወጣ አለኝ ዝም ስላት ረዱ አለች እ አልኳት ከዚህ በፊት……
✎ ክፍል 8 ይቀጥላል... አንብበው ሲጨርሱ LIKE
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
አልጋ ላይ የወረወርኩትን ስልኬን አነሳሁት አልተዘጋም ነበር ሄሎ አብሪሽ ስለው ዝም አለኝ ድምፄ ውስጥ ምንም መረጋጋት የለም በይ ለነገ ቀጠሮሽ እንዳይረፍድብሽ ቶሎ ተኚ ብሎኝ ስልኩን ዘጋው በጣም ተናደድኩ የመጨረሻ ንግግሬን ብቻ ነው እንዴ የሰማው እኔን መረዳት ሲገባው እንዴት እንደዚህ ብሎ ስልኩን ይዘጋል ብቻ ብዙ ነገር አሰብኩኝ ደጋግሜ ደወልኩለት ስልክ አያነሳም ከዛ ማልቀስ ሆነ ስራዬ ለሊቱን ሙሉ እያለቀስኩ አደርኩ ለሊት 11 ሰአት ላይ በሬ ተንኳኳ የሴት ሚዜዎች እንደሆኑ ስለገመትኩ ፊቴን ታጥቤ በሩን ከፈትኩ ሁሉም ጮሁብኝ ምንድነው ፊትሽ? ምንድነው አይንሽ የጥያቄ ውርጂብኝ የኔ መልስ ግን አንድ ነው "ምንም አልሆንኩም" ወጣንና ፀጉር ቤት ሄድን ሰዕቱን ሳይ ከጠዋቱ 1ሰዕት ተኩል ሆኗል ስልክ ደወልኩ አሁንም አያነሳም ራሴን ሰብስቤ ወደ ሰርጉ ለማተኮር እንዲረዳኝ ስልኬን ዘጋሁት በደመነፍስ የሚዜነት ግዴታዬን ተወጣሁ እንዳይመሽ የለም መሸ ወደ ክፍሌ ገባሁ ያ ሚዜዬ እንኳን የፊቴን ልክ አለመሆን አይቶ አደብ ገዝቷል ክፍሌ እንደገባሁ ስልኬን ከፈትኩ ደቂቃም ሳይቆይ አብሪሽ ደወለ አንቺ እብድ አለኝ አንተ አፈር ብላ ሙት እሺ ኖረህም አጠቅመኝም አልኩት በጣም ይቅርታ አጥፍቻለሁ አለኝ ቀኔን እንዴት እንዳበላሸህው ብታውቅ አንተ እኔን መረዳት ያቅትሀል በዚህ ደነዝነትህማ አላገባህም አልኩት በጣም ሳቀ ምነው አታገባኝም እንዴ አልኩት ሚዜ ስትሆኚ ሰርግ አማረሽ በይ ነገ ቶሎ ነይ እሰካይሽ ቸኩያለሁ አለኝ እኔም ናፍቀህኛል አልኩት ትንሽ ካወራን በኃለ ስልኩን ዘጋሁና ደክሞኝ ሰለ ነበር ተኛሁ ጥዋት ላይ ቁርስ በላልተን እንደ ጨረስን የኔው ሚዜ ጠጋ አለና አስቀየምኩሽ እንዴ በጣም ይቅርታ አለኝ ዝም አልኩት ይሄን ታክልም አትዝጊኝ ሲለኝ ተቀበይሄለው አልኩት ምኑን ይቅርታዬን አለኝ ታድያ የፍቅር ጥያቄህን ልበልህ አልኩት ኮስተር ብዬ አትናደጂያ ባይሆን ለማስታወሻ አንድ ሰለፊ እንነሳ ብሎ ስልኩን ከኪሱ ሲያወጣ ጥዬው ሄድኩ ብዙም ሳንቆይ አንዷ ሚዜ ጋር ወደ አ,አ ተመለስን እንደ ገባን ለአብሪሽ ደወልኩለት አያነሳም እኛም ከመሸ ሰለ ገባን መንገድ ተዘጋግቶ ሰለ ነበር አብሪሽ አላነሳልኝ ሲል ወደ ቤት ሄድኩ ልክ እቤት ገብቼ ሻወር ወስጄ እራት በልቼ መኝታ ክፍሌ ገብቼ ለአብሪሽ ደወልኩ አያነሳም ትንሽ ተደናገጥኩ ምን ሁኖብኝ ይሆን አልኩ ከ1 ሰአት ቆይታ በኋላ ስደውል ስልኩ ጠርቶ ጠርቶ ሊዘጋ ሲል ሄሎ አለችኝ …
✎ ክፍል 5 ይቀጥላል... አንብበው ሲጨርሱ LIKE
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
ስልኩ ጠርቶ ጠርቶ ሊዘጋ ሲል ሄሎ አለችኝ ዝም አልኩ ሄሎ ስትል ይቅርታ አብሪሽ የለም አልኳት ስራ ቦታ ስልኩን ረስቶ ሂዶ ነው አለችኝ ታድያ የሰው ስልክ ይነሳል አልኳት በጣም በተደጋጋሚ ሰለ ሆነ ብዬ ነው አለችና ዘጋችብኝ አዳሬን ሰለ እሱ እያሰብኩ አደርኩ ጥዋት ላይ ከእንቅልፌ ሳልነሳ ደወለልኝ ስልኩን ረስቶት እንደወጣ ነግሮኝ ይቅርታ ጠየቀኝ ምንም አይደል በኋላ ሰፈር ከመጣህ እንገናኝ አልኩት እሺ እመጣለሁ እንደውም አንድ ልነግርሽ ምፈልገው ነገር አለ አለኝ ልቤ ደነገጠ እሺ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት አንድ ነገር አምሮዬ ላይ ያቃጭልብኛል አብሪሽ ጋር ይሄን ታክል መንገድ ብንመጣም ግን ሰለ ሁለታችን አውርተን አናውቅም ፍቅረኛሞች ነን ተባብለን አናውቅም ጓደኝነታችን አብረን እንድን ቀጥል አደረገን ታድያ አሁን እኔ ለአብሪሽ ምኑ ነኝ እኔ በቃል ከምገልፀው በላይ ነው ምወደው ቀኑን ሙሉ እንደ ተጨነኩ ዋልኩ አይመሽ የለ መሽቶ ከቤት ወጥቼ እሱ የቆመበት ቦታ እስክደርስ እንዴት እንደምስመው እያሰብኩ ነበር አጠገቡ ደረስኩና ጉንጩን ስሜው ቁጭ አልኩኝ ተቀምጠን ትንሽ እንዳወራን ስአቱን አይቶ ኧረ ቤት እንዳይቆጡሽ ግቢ በቃ አለኝ በጣም ተናደድኩ እኔ ገና አይቼው አልጠገብኩም እሱ እንዴት ሂጂ ይለኛል ስል አሰብኩኝ በዛ ላይ ምነግርሽ ነገር አለ ብሎ እንዴት እንዲህ ይለኛል ብዬ ተናደድኩ በዚህ ስሜትወሰንኩ ውስጥ እንዳለሁ ቻው ብሎ ጉንጬን በደንብ ሳመኝ እኔ ግን ቁጭ ብዬ ቀረሁ በቃ ሂጂ ግቢ አለኝ ከዛ በኋላ እሱ ስለኔ ስላለው ስሜት መጠራጠር ጀመርኩኝ ስንገናኝ ግን የማይካድ ኬሚስትሪ አለ አንድ ቀን ለአብሪሽ ሳልደውል ልውል የሚገርመው እሱም ሳይደውል ዋለ አደረ በማግስቱ እኔም ስልኬን ዘጋሁ እና ወደ ማታ ላይ ስልኬን ስከፍተው ደወለልኝ ሰልኩን ሳየው በ ደስታ ዘለልኩ ስልኩን ሳነሳ "ፍቅር ሲቀዘቅዝ እንዲህ ነው አለኝ" ኧረ አይቀዘቅዝም አልኩትና ትንሽ ስራ በዝቶብኝ እንደ ሆነ ነግሬው ነገ ላግኝህ ላወራህ እፈልጋለሁ አልኩት" እሺ አለኝና ተሰነባብተን ስልኩን ከዘጋሁ በኋላ እንዴት ብዬ የልቤን እንደምነግረው ብዙ ጊዜ አሰብኩኝ እንቅልፍ ነሳኝ ያ ሌሊት ነግቶ የማይገፋው የቀን ውሎ እየሄደ ገና መሰሎኝ ሳለ ሰአቱ ደርሶ አብሪሽ ደወለልኝ ቶሎ ብዬ ወጥቼ ሁሌም ወደ ምንቀመጥበት ስፍራ አመራሁ አብሪሽ ከወትሮው በተለየ ከላይ እስከ ታች ጥቁር በጥቁር ለብሷል አይኑን ሳይ እንባዬ ሆን ይችላል ብዬ ብዙ ሃሳብ በውስጤ መጣ ምን ሆንክ ለማለት ራሱ አፌ ተሳሰረ አቅፎ ሰላም አለኝ አይኖቹን በስስት ከማየት ውጪ ምንም ልረዳው አልቻልኩን ምን ሁነሻል አለኝ ምን ልበላው እሱ እንዲህ ሁኖ እያየሁት የግዴን አንተን ልጠይቅህ እንጂ አልኩት እኔማ እ ደህና ነኝ አለ እንዲህ ሁነህ እንዴት እንደዛ ትለኛለህ አልኩት ዝም አለኝ ላስጨንቀው አልፈልኩም በመሃከላችን ዝምታ ሰፈነ በሃሳብ ተዋጥኩኝ አብሪሽን ከዚህ በፊት ከረጅም አመታት በፊት ማውቀው ይመሰልኛል አንድ የማላውቀው ግን የተሰወረ ሚስጥር ያለ ይመስለኛል እሱን ከሃሳቤ ማውጣት አልችልም ቢጨንቀኝ ምን ሁነሃል ብዬ ባፋጠው የበፊት ፍቅረኛዬ በመኪና አደጋ አርፋ አለኝ በጣም ደነገጥኩ ከዚህ በፊት ሰለሷ ነግሮኛል ምንም አላልኩትም ጠጋ ብዬ ትክሻው ላይ ደገፍ ብዬ ቁጭ አልኩ የዛን ቀን ምንም አልተባባልነም አብሪሽ ጋር ፍቅራችን ቀጠለ ከወራት በኃላ ፍቅርተ እቤት ድረስ መጣ እስኪ የበደልንሽን ንገሪን አለች አየሳኩ ሳልለተመቸኝ እንደ ተጠፋፋን ነገርኳት ከስንት ጭቅጭቅ በኋላ እያማረረችኝም ቢሆን ተቀበለችኝ ቀኑን ሙሉ አብረን ዋልን ፍቅር ፍቅርተ ሲመጣባት ጨዋታዋ አፍ አያስከከድንም እንዲህ እያወራን እያለ ድንገት ወደ አንድ ሰው አማላጅ ልልክሽ ነበር ነው አለችኝ ምን ብዬ ተሳሳቅን ለአንቺ ሲኦል አይሁ እንጂ የትም እሄድልሻለሁ አልኳት ወረኛ ያን ሞባይሌን አቃብይኝ ብልሽ ምታቅማሚ ልጅ እኮነሽ ስትለኝ ተነሰቼ ሞባይሏን ሰጠኋት በጣም ሳቀች ለውጥማ አለ አለችኝ ከአስተማሪው ነው አልኳት እረ ጭራሽ ሌላ ታሪክ ውስጥ ገብተሽልኛላ አለችኝ እ አልኳት ይልቅ ምን ያልሽኝ አልኳት ምን መሰለሽ ረዱ አብሪሽ ጋር …
✎ ክፍል 6 ይቀጥላል... አንብበው ሲጨርሱ LIKE
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
ሳየው እንደ መደንገጥ አልኩ እሱም ወደ እኔ እየተጓዘ ነው እኔ በመሃል ቆምኩ እሱም ቆመ ይሄኔ የባሰ አሰደነገጠኝ ከረጅም አመታት በፊት ማውቀው ሰውም መሰለኝ ግን ምንም ሊመጣልኝ አልቻለም እንደ ምንም ብዬ በድፍረት ተንቀሳቀስኩ አጠገቡ ስደርስ አትኩሮ አየኝ ሰላም አልኩትና ልብሱን ከሰጠኝ በኋላ ይቅርታ አውቅሻለሁ ልበል አለ እኔጃ ይሆናል ብዬ ተቀብዬው በፍጥነት ተመለስኩ ልቤ ልትወጣ ያለች ያህል ተሰማኝ ግራ ተጋብቻለሁ የት እንደ ማውቀው አልመጣልኝ ወደ ቤት እንደ ገባሁ ፍቅርተ መደናገጤን ስታይ ምን ሆንሽ ብላ በጥያቄ አጣደፈችኝ ምንም አልሆንኩም ግን ልጁን የት ነው ምታውቂው አልኳት ማን አብሪሽ ጋር አለችኝ አዋ አልኩት ምን ብሎሽ ነው ተናገርሽ እንዴ አለች እረ የለም ልጁን ማውቀው ሰለ መሰለኝ ነው አልኳት እዚህ ላይ ኮስተር አለች የት ነው ምትተዋወቁት መቼ ነው ምታውቂው የት ነው ምታውቂ እያለች የጥያቄ ናዳ አወረደችብኝ ማውቀው መሰለኝ አልኩ እንጂ አርግጠኛ ሁኜ አውቀዋለሁ እኮ አላልኩሽም ብዬ አልፊያት ወደ ቤት ገባሁ ለምን አንደ ተደናገጠች አልገባኝም ነገሩ በሰአቱ ባይገባኝም ሰለሱ ማሰብ ሰለ ማልፈልግ ለጊዜው ጉዳዩን ተውኩት ሚገርመው ግን እየዋልኩ እያደርኩ ይሄን ልጅ በሃሳቤ አመላልሰው ጀመር በቀን ውስጥ የተለያዩ ወንዶች ጋር እደዋወል የነበረውን አቆምኩ ምንም ከሃሳቤ ባይጠፋ እንኳ ፍቅርተን ግን ሰለ ልጁ መጠየቅ ሽንፈት መስሎ ታየኝ በዚህ መሃል አንድ ቀን ፍቅርተ ጋር ወክ እያደረግን የበፊት ጓደኛዋ መንገድ ላይ አገኝነንና ሻይ ቡና ካላልኳቹ አለን ሲፈጥራት መግደርደር ሚባል አያውቃትም በአንድ አፍ እሺ አለች እየተሳቀኩም ቢሆን አብረን ሄድነ አንድ ካፌ ውጭ ላይ ቁጭ ከማለታችን አብሪሽ አንድ ልጅ ጋር ከካፌ ወጣ ሲል አኩል ተያየን እኔ በድንጋጤ ፈዘዝኩ ፍቅርተ አብሪሽ ብላ አቅፋ ሰላም አለችውና ተዋወቃት ጓደኛዬ ምልህ እሷን ነው ስትለው እጁን ዘረጋልኝ ለሰላምታ አብረሃም ስሊኝ የተወሰን ሰከንድ በኋላ ረድኤት ብዬ እጄን ዘረጋሁለት እኛ ጋር ያለውን የበፊት ፍቅረኛዋን የእሷ ፍቅረኛ ነው ተዋወቀው አለችው በአንድ ግዜ ፊቴ ተቀያየረ ሳፈጥባት ጠቀሰችኝ ንዴቴን እንደምንም ቻልኩት እና ቁጭ በሉ ስትላቸው እንሂድ ብለው ሄዱ ምን ሁነሽ ነው አልኳት ምን ችግር አለው ታድያ የእኔ ጓደኛ ነው እንድል ጠብቀሽ ነበር እንዴ አለችኝ ከእሷ ብሶ አፈጠጠች ምንም ስልላት ተነስቼ ሄድኩ ጓደኛዋ ቆይ እንጂ ተረጋጊ አለኝ መልስ ሳልሰጠው ሄደኩ ብዙም ርቄ ሳልጓዝ ከኋላዬ ረዱ ትሸኚኝ የሚል ድምፅ ሰምቼ ዞር ስል…
✎ ክፍል 3 ይቀጥላል... አንብበው ሲጨርሱ LIKE
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
አብሪሽ ነው ንዴቴ አንድ ጢስ በኖ ጠፋ ግራ እስኪገባኝ ፈገግ አልኩና አልሄድክም እንዴ አልኩት አዋ ሰው አየጠበኩ ነበር ጓደኛዬ ጥሎኝ ሲሄድ እኔም መጠበቁ አስጠላኝ ተሸኚኝ አለ እእ
አልኩት አዋ ምነው አለ ምናልባት ወንድ ልጅ ሸኚኝ ሲል የመጀመርያዬ ሰለ ሆነ ይሆን አልኩት በቃእኔ የመጀመርያሽ እሆናለኋ ብሎ እየተሳሳቅን ግማሽ መንገድ ድረስ አብረን ሄድን በቃ ከዚ በኋላ በታክሲ እሄዳለሁ አለኝ እሺ ቻው ሲለኝ አንተ በቃ የምርህን ነው እንዴ አትሸኘኝም እንዴ አልኩት ሸኚኝ እንጂ ለሽኝሽ አላልኩም ደግሞ ሚስቱካዬን ለውሽማዋ ጥለሽልኝ መጣሻ አለኝ እ አልኩ በመሃል ታክሲ ሲቆምለት ደውይልኝ ብሎኝ ሄደ እኔም ግራ እየተጋባሁ ወደ ቤት ሄድኩኝ ፍቅርተ ጋር ሳምንቱን ሙሉ አልተገናኘንም አብሪሽ ልክ በተገናኘን በሳምንቱ ሚሴጅ ላከለኝ ሰለ ፃፈለኝ ደስ አለኝ ቡና አትጋብዢኝም እንዴ አለ በልቤ ይሄ ልጅ አርጉልኝ እንጂ ላድርግላቹ አያውቅም እንዴ አልኩኝ እሺ ግብዣ በእኔ ሂሳብ በአንተ አልኩት በይ እሺ አስር ሰአት ላይ እንገናኝ ደግሞ እንደ ሚታነቅ ሰው በዶ ኪስሽን አትምጪ አለኝ ስቄ እሺ አልኩት እስካየው ሰለ ቸኮልኩ ነው መሰለ ሰአቱ አልሄድልኝ አለ ጓደኞቼ ደውለው ጠፋሽብን ብለው ጨሁብኝ በኋላ እንገናኛለን ብዬ ወደ ፀጉር ቤት ሄድኩኝ ብዙም ወራፍ ሰላልነበረው ቶሎ ጨረስኩ ሚገርመው ስንት ስራ ስስራ ቆይቼ ሰአቱ ግን አልሄደም የትኛውንም ወንድ ለማግኘት እንዲህ አጣድፎኝ አያውቅም ብቻ ሰአቱ አይደርስ የለ ደርሶ ተገናኘን በትኩረት አየኝና።እኔን ለማግኘት ወደ ሶስት መቶ ብር አውጠሻል አለኝ ሳቄ አመለጠኝ ያውም የታክሲ ሳይጨምር ነው አለኝ ምነው የቢዝነስ አማካሪ ነኝ አልክሳ አልኩት እሱም ሳቀና ፍቅርተ ደህና ናት አለ ከአንድ መቶ ስልሳ ስምንት ሰአታት በፊት ደህና ነበረች አልኩት ሳቁን እዛኔ አየሁለት በጣም ደስ ይላል ከልቡ
ሚስቀው ነገር ውስጥን ደስ ያሰኛል ተጫዋች ነሽ አለ ምነው አልተገናኛቹም አልኩት አፍራ ነው መሰለኝ አንዴ ደውዬላት አታነሳም አለኝ እንዴት ምን ያሳፍራታል ስለው የዛሬ ሳምንት እኮ ጓደኛዋ ነው ብላ ያስተዋወቀች ለእኔ እኮ ምርጥ ጓደኛዬ ነው እንዳትደናበሩ ሰለ ፈለገ ነው ዝም ያለው አለኝ እኔ ራሱ እንደዚህ ሲለኝ ተሸማቀኩ
ለማነኛው ያለፈው አልፏል እርሺው አለኝ ከዛን ቀን ጀምሮ አብሪሽ ጋር እንገናኝ ጀመር ግንኙነታችን በጣም ጠበቀ ፍቅርተ ጋር ሙሉ በሙሉ አቆመ እሷም ሌላ ጓደኛ ያዘች አንድ ቀን ኤሚ ምንላት
ጓደኛችን ልታገባ ቀን እንደ ቆረጠች ነገረችን በጣም ደስ ብሎን እያለ አንዷ ሚዜ እኔ አንደ ሆንኩ ነገረችኝ ምን ልበላት በጣም ጨነቀኝ ኤሚ ማለት በጣም ብዙ ሚቀርቧት ጓደኞች አሏት ግን እኔን መርጣ ሚዜዋ ስላ ደረገችኝ ምን ብዬ እንቢ ልበላት ለመጀመርያ ጊዜ ነው ለሚዜ ነት ስመረጥ
ሳምንቱን ሙሉ ለእሷ የተለያየ ነገር ስናዘጋጅ ቆየን ቤተሰቦቿ ባህር ዳር ናቸው በዚህ መሃል ለአብሪሽ ሚዜ እንደ ተመረጥኩ ነግሬው ነበር ደውዬ አልልሽም በሎ ሳቅ አለና ስትደርሺ ደውይልኝ አለ እሺ ብዬው ስልኩን ከመዝጋቴ ነይ ውጪ መኪና መጧል ብለው አዋከቡኝ እና በግዜ ወጣን ባህር ዳር እንደደረስኩ የወንዶችና የሴት ሚዜዎች ጊዜ አለ ተብሎ ለባብሰን ከምን አይነት ሰው ጋር እንደሚገጥመን እያሰብን ወደ ሆቴል ጉዞ ጀመርን ሆቴል ስንደርስ ወንዶቹ ሚዜዎች ቀድመውን ደርሰዋል ሞቅ አርገው ተቀበሉን ማን ከማን ጋር
እንደሆነም ተወሰነ የኔም ሚዜ መጥቶ አጠገቤ ቁጭ ብሎ ማውራት ጀመርን የኔ ሚዜ እንደ አጋጣሚ ሆኖ የተሻለ መልክና ቁመና ያለው ነበር
ሌሎቹ ሴት ሚዜዎች ረዱ አፈስሽ አሉኝ ኧረ እኔ ለኔ የተመዘነውን ካፈስኩ ቆይቻለሁ አልኳቸው በዚህ መሀል ለአብሪሽ ስልክ እንዳልደወልኩ ትዝ ሲለኝ ስልኬን ሳየው 12 ሚስኮል አገኘሁ አብሪሽ ደውሎ አላየሁትም ነበር ዘወር ብዬ ደወልኩለት አንዴ እንደጠራ አነሳውና "አንቺ እብድ ቢያንስ ገባሁ አይባልም አለኝ" በጣም ይቅርታ ተዋከብኩና ረሳውት አልኩት። አሁን ያለንበትን
ሁሉንም ነገርኩትና ሩም ስገባ እደውልልሀለው አልኩት ስመለስ የኔ ሚዜ ዞር ብሎ ስልክ ማውራት እኮ ባለትዳር ነኝ ማለት ነው አለኝ አልተሳሳትክም አልኩት ይቺ እጅሽ ጨክና ፈረመች አለኝ አይ እጄስ ገና አልፈረመችም ልቤ ነው የፈረመው አልኩት እሺ ለኔ የእጁን ፈርሚልኝ አለኝ ልብ የሌለበት የእጅ ፊርማ ምን ያደርግልሀል አልኩት ኧረረ አልቻልኩሽም አለኝና ተነስተን ወደ
ሌሎቹ ሚዜዎች ተቀላቀልን እየተጫወትን ድንገት ሚዜዬን ሳየው እያየኝ ነው ፈራሁት ሌሎቹ ሚዜዎች በጣም ተግባብተዋል ተጫወትን እንደጨረስን ለሊት ወደ ፀጉር ቤት ስለምንሄድ እንግባ ተብሎ ወደ ሩም ለመሄድ ተነሳን ሁላችንም በተለያየ ሰአት ስለደረስን የተለያየ ቦታ ነበር አልጋ የያዝነው የኔ ሚዜና አንድ ሌላ ሚዜ መኪና ይዘው ስለነበር ሊሽኙን ተነሱ እኔንና ሌላ ሶስት ሚዜዎች የኔ ሚዜ ሸኝን ሌሎቹን መጀመሪያ ሸኝናቸው መጨረሻ ላይ እኔን አደረሰኝና አመሰግናለሁ የነገ ሰው ይበለን ብዬው ወረድኩኝ ግባ አትይኝም አለኝ ወዴት አልኩት ወደ ልብሽ አለኝ ውይ ትርፍ አንጭንም አልኩትና ወደ ሩም ገባሁ እንደ ገባሁ ለአብሪሽ ስልክ ደወልኩ በፍቅር ጋደም ብዬ እያወራሁት እያለ ናፍቀሺኛል አለኝ እኔ ደሞ ርበህኛል አልኩት በዚህ መሀል የክፍሌ በር ተከፈተ በጣም ደነገጥኩ ስዞር ይበልጥ የሚያስፈራ ነገር አየሁ "ሚዜው ቆሟል ምን ታደርጋለህ እዚህ አልኩት ስልኬን አልጋው ላይ ወርውሬ ተነሳሁ ልብሽ ባይፈቀድልኝ ክፍልሽ ልግባ ብዬ እኮ ነው አለኝ በጣም ተናደድኩ...ውይ በጣም ትቀልዳለህ አልኩት ቀና ብዬ ሳየው ወደኔ እየመጣ ነው በዛ ላይ በጣም ሞቅ ብሎታል በጣም ፈራሁና በዚህ ሰአት ጉልበት ሳይሆን ብልጠት አንደሚያስፈልገኝ አሰብኩኝ ወዲያው አንተ ምን ሆነህ ነው በአንድ ቀን ታመረዋለህ እንዴ ነገም እኮ የኔና ያንተ ነው ቢያንስ እንድግደረደር እንኳን ዛሬን ስጠኝ ነገ ብትን ብለን አብረን እናድራለን አልኩት እስቲ ሙት በይኝ አለኝ እኔ ልሙት ብዬ ማልኩለት እሺ ብሎኝ ከክፍሌ ወጣ እኔም ኡፈይ አልኩኝና በሬን ቆልፌ አልጋ ላይ የወረወርኩትን ስልኬን አነሳሁት አልተዘጋም ነበር ሄሎ አብሪሽ ስለው…
✎ ክፍል 4 ይቀጥላል... አንብበው ሲጨርሱ LIKE
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
ህይወት ምትባል ሴት እንጂ ህይወት ሚባል ወንድ አላውቅም ነገር ግን ህይወት የሚባል ኑሮ ግን ገጥሞኛል አሁን ላይ ሳስብው ህይወት የሚባለው ስም ለሴት ብቻ የተሰጠው ያለ ምክንያት እንዳልሆነ ገብቶኛል ሁሌም የህይወት ውጣ ወረድ ከወንድ ይልቅ በሴት ልጅ ይበረታል ለዛም ነው ሴቶች በትንሽ ነገር ተቆጪና ተሸናፊ የምን ሆነው ስሜን ሳልነግራቹህ ረድኤት እባላለሁ
ተወልጄ ያደኩ አ,አ ውስጥ ነው ሰለ ራሴ ህይወት ብዙም የመናገር ልምዱ ባይኖረኝም ከህይወቴ ለሚማር ሰው ግን ሁሌም ዝግጁ ነኝ ከጓደኞቼ ውስጥ የእኔ ባህሪ ትንሽ ለየት ይላል ለማስመስል ብዬ አንድ እርምጃ አልራመድም ነገር ግን ሰው
ውሎውን ነው የሚመስል እንደ ሚባለው እኔም ጓደኞቼ ጋር መዋል ስጀምር የሌለብኝን አመል ሳይቀር ተማርኩ ለጓደኞቼ ስል ማልገባበት የለም ለነሱ ደስታ እንደ እኔ ሚሆን የለም ለእኔ ሲሆን
ግን አንድ ሰው አላገኝም በዚህ ሁሉ ነገር በቁጥር ባላውቃቸውም የተለያዩ ወንዶች ጋር የፍቅር ህይወት ጀምሬ ነበር ግን አልዘልቅም ሚስጥሩ በማይገባኝ መንገድ እንለያያለን እኔም ሆንኩ ጓደኞቼ የወንዶች ባህሪ ነው ብለን ምንም ሳንደነቅበት እናልፋለን ሁሉ ጓደኞቼ ባልልም ወንድን እንደ ቲሸርት ሚቀያይሩ ጓደኞች ነበሩኝ
ለየት ከሚለው ባህሪያችን ፍቅረኛ እንዋዋሳለን ይሄን ሚስጥር ማወቅ ከባድ ነው ከኛ ውጭ ማንም መንገዱ አይገባውም ምኖረው ከቤተሰቦቼ ጋር ነው ታላላቆቼ አግብተዋል የመጨረሻ
እቤት ውስጥ ምጠበቅ እኔ ነኝ እኔም ደግሞ ቤተሰቦቼ ባያውቁኝም ጩሉሌ ነኝ ወንድ ልጅ ጋር ጥግ ድረስ እሄዳለሁ ሴትነቴን ግን እንዲህ በቀላል ማርከስ ሰለ ማልፈልግ ስሜቴን አሽንፈዋለሁ በዚህ ደግሞ እራሴን እወደዋለሁ ጓደኞቼ ቀጠሮ
ሲኖርባቸው አንዷ የአንዷን ልብስ ለብሳ መሄድ የታወቀ ቢሆንም እኔ ግን ልብሴንም አላሳነካም እኔም አልጠይቃቸውም አንድ ቀን ግን ፍቅርት ምላት ጓደኛዬ አንድ የምወደው ለብሴን ካልሰጥሽኝ ብላ ተሟዘዘችብኝ መስጠት ባልፈልግም በግድ ሰጠኋት የሚገርመው እዛኔ ሳትመጣ እዛው አደረች የአሷ ማደር ሳያሳስበኝ የልብሴ ነገር አሳሰበኝ ልብስ አልተቸገርኩ
ምንድ ነው እንደዚህ ሚያብሰለስለኝ እያልኩ በራሴ እገረማለሁ ሳያት የሰጠዃትን ልብስ ሳይሆን ሌላ ልብስ ነበር የደረበችው ገና ሰላም ሳትለኝ ልብሴሳ ነው ያልኳት መጀመርያ ምን ሆንሽ ነው
ሚባል ብለ አልፋኝ ወደ ቤት ገባች ማታውን ስትነግረኝ ዝናብ ዘንቦ ሰለ ነበር በስብሶባት እዛው ፍቅረኛዋ ቤት ጥላው እንደ መጣች እና ነገ እንደ
ሚያመጣላት ነገረችኝ ምንም አላልኳትም በውስጤ ግን ትንሽ ተናደድኩ ነገውን እነሱ ቤት ፍቅረተ ጋር ቁርስ እየበላን ጓደኛዋ ደወለላት ሰፈር መጥቻለሁ ልበስሽን ልሰጥሽ አላት አንደ ምንሜና
አደረጋት እኔ እናቴ ጋር ስራ ይዣለሁ ጓደኛዬ ትቀበልህ ቆይ ልደውልላት ብላ ቶለ ዘጋችበት ምን ሁነሽ ነው እንዲህ ምትቃዢው አልኳት በዚህ ልብሴ እንዴት ነው ምወጣ ብላ እኔን ላከችኝ
ስልኩን ተቀብያት ወደ ውጭ ወጥቼ ስደውልለት ከእሩቁ እጁን አወራጨልኝ ልጁን ሳየው እንደ መደንገጥ አልኩ እሱም ወደ እኔ እየተጓዘ ነው እኔ በመሃል ቆምኩ እሱም ቆመ ይሄኔ የባሰ አሰደነገጠኝ…
ይቀጥላል ………………
✎ ክፍል 2 ይቀጥላል... አንብበው ሲጨርሱ LIKE
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
☬ @ልብ ወለድ የፍቅር ታሪኮች ☬
❍━━━━━━━ლ━━━━━━━❍
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
Reviews channel
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «ልብ❤️ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች💞» is a Telegram channel in the category «Книги, Аудиокниги и Подкасты», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 7.1K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 27.5, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 2.4 ₽, and with 1 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий