
- Main
- Catalog
- Religion & Spirituality
- ❤️ለይላ መጅኑን🌹
❤️ለይላ መጅኑን🌹
የፍቅር ተምሳሌት የሆኑት ለይላ እና መጅኑን real promotion 👇 and comments
Channel statistics
..........ፍርሀት🖤 .........
📝ፀሀፊ:- semi nas
==========❨ )=========
𝐋𝐞𝐲𝐢𝐥𝐚 𝐌𝐮𝐣𝐧𝐮𝐧
===========⨳ ⨳========
========+ +====
#ክፍል_ ስምንት
=======+ +======
<<አቤት ለወሬ ያለሽ አቋም ምግቡን ሳልበላ አጣደፍሽው እኮ
"ረምላ እየሳቀች አረ ባክህ እኔ መች በላው አሁን ድጋሚ ሰርቼ ልበላ ነው በቃ በቃ ምዕላድ ቀጥልልኝ
"ቀና ብሎ አይቷት ፈገግ ብሎ እእእ ያን እለት ከመተቃቀፍ ዘሎ ወደ መሳሳም አመራ እዚ ግቢ ከገባው ሁለት አመት ሆነኝ ግን አንድም ቀን ሴት ነክቼ አላቅም አደለም ለመተቃቀፍ ቀርቶ ያን እለት የሁለታችንም አብረን ብናድር ደስታችን ነበር ግን ከቾከልኩ ከዚ በዘለለ ለምን አይፈልገኝም ብላ ታስባለች ብዬ እንደምንም ስሜቴን ተቆጣጥሬ ካለንበት ይዣት ወደ ግቢ ተመለስን
"ያን እለት የጌታዬን ድንበር በማለፌ እያለቀስኩ ይቅርታ ጠየኩት ሌላ ግዜ እንደማልደግመው ለራሴ ቃል ገብቼ ተኘው
የሱቢ አዛን ይመስል በለሊት ደወለች እኔም የማታውን ቃል ረስቼ አወራዋት ትንሽ አውርተን በኋላ እንገናኝ ተባብለን ስልኩ ተዘጋ ለቅፅበት የማታው ቃል ትዝ አለኝ ነገር ግን በፍቅሯ ታውሬ ወደኋላ ተውኩት በጧት ክላስ ስለነበረኝ ተጣጥቤ ወደ ክላስ ሄድኩ ባጋጣሚ ክላስ ስገባ እኔ ምቀመጥበት አጠገብ ቁጭ ብላለች የሆነ ሀይል ሄደ እቀፋት እቀፋት አለኝ ግን ተማሪዎች ነበሩ ሄጄ አጠገቧ ቁጭ አልኩ በአይን ብቻ ሰላም አልኳት እሷም እንደዛው የዕለቱን ትምህርት ጨርሰን ወጣን ኮሊደሩ ላይ ቆመን ዛሬ የት ነው ምንውለው አለችኝ
"ባንቺ ምርጫ
"እሺ ብላ እእጄን እየጎተተች እዛኝ ከግቢ ወጣች
"ከውሲ ወዴት ነን አልኳት እንደምንም አቁምያት
"እህህህ ምዕላዴ ተከተለኝ የሆነ ደስ የሚል ቦታ ነው በቃ የራሳችንን ግዜ ምናሳልፍበት ቦታ ነው
"እሽ ይርቃል
"አይ ዝም ብለ ና
"እኔም እየተጎተትኩ ሄድኩላት ከአንድ ደስ የሚል ቦታ ደረስን ወደ ውስጥ ይዛኝ ገባች ወደ ውስጥ ስንገባ አንድ ትንሽዬ ጎጆ አለ ሌላው በአረንጓዴ ሳር የተሸፈነ ደስ የሚል ስፍራ ነው
ረምላን ቀና ብሎ አይቷት መልሶ አቀረቀረ አይኑን ጠረግ ጠረግ አርጎ ቀጠለ
የን እለት ለመጀመሪያ ግዜ ዚና ላይ ወደቁ እሷም የመጀመሪያዋ ነው ስንንሳ ተፋፈርን አፍረታችን ግን ከሁለት ደቂቃ አልዘለለም ክብሯን ማንንቷን ባልሆነ መንገድ ነፈግኳት ከዛ ጀብዱ እንደሰራን ነገር ተያይዘን እየተሳሳቅን ወጣን ወደ ዶርም የመሄዱን ሀሳብ ትተን እዛው አደረን ደስ አለን ግዜያት ለጉድ ነገዱ ወደ አምስት ወር ተጠጋን በነዚ አምስት ወር ውስጥ ጌታዬን እረሳው ኸውሰር ሁልነገሬ ሆነች እናቴ እህቴ ጓደኛዬ ሆነች
ግን ሁሌም ሁሌ ከምቀመጥበት ቦታ ሆና ታለቅሳለች ሁሌም አንዳይነት ቃል እያለች ነው ምታለቅሰው "ጌታዬ ውሳኔህ ነው አምኜ ልቀበል እሺ ጌታዬ አምኜ ልቀበል ምዕላዴስ"ትላለች አለ ወደ ረምላ ዞሮ ረምላ እያለቀሰች ነበር እሷን ሲያይ እሱም አለቀሰ
ተነስታ እንዳታባብለው አይነት የጌታዋ ትልቅ ድንበር አለ
"ያን ዕለት አጠገቧ ሄጄ ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ ብዬ ለመንኳት እንደ ህፃን እቅፌ ውስጥ ጥቅልል ብላ ገብታ ምንም አልሆንኩም አንተን በማግኘቴ ደስ ብሎኝ ነው አለችኝ"እኔም ላስጨንቃት አልፈለግኩም ዝም ብያት አለፍኩ
እኛም ከወንጀል አንርቅም ግዜውም መሄዱን አያቆምም እያለ እያለ ሶስተኛ አመታችንን ጨረስን ይሄም አመት ባልባሌ ነገር አለፈ እና አራተኛ አመት የመጀመሪያ ወር ላይ ከውሲ መጠቋቆር መክሳት ጀመረች ከንፈሯ ብልዝ ይላል እኔም ግራ ገብቶኝ ከሳሽ ደሞ እየጠቋቀርሽ ነው እላታለው እሷ ጋር ግን መልስ የለም ዝም ነው ምትለኝ ነገሩ ግራ አጋባኝ ሁሌ ምታለቅስበትን ምክኛት ማወቅ እፈልጋለሁ ግን አትነግረኝም
ቆይ እሺ ረምላ እኔ ምን አጠፋው እጠይቃታለሁ እኮ ሁሌም እሷ ግን ዝም ነው ምትለው ቆይ ምን አረኩ ሳያስበው በጣም እየጮሀ ነበር
ረምላ ብድግ ብላ አይ አይ ምንም አላጠፋህም አለችው በጣም ደንግጣ ተረጋጋ ውሃ እየሰጠችው
በደመነፍስ ተቀብሏት ጠጣ
ቀጥልልኝ ማለት ፈራች ቀና ብላ ታየውና ጎንበስ ትላለች
" አንድ ቀን ያለ ወትሯ በማታ ደወለች
"በመደንገጥ ስሜት ሄለው አልኳት
"ምንም ሳትመልስልኝ ቶሎ በል የተለመደው ቦታ ና አለችኝ ፍርሀት ፍርሀት እያለኝ ሄድኩ
አጠገቧ ስደርስ ጥቁር ወፍራም ጃኢት ለብሳለች ፊቷ በጣም ያስፈራ ነበር ወደሷ ጠጋ ብዬ ኸውሲ አልኳት ላቅፋት እየተመቻቸው እንዳትነከኝ አይነት ጠጋ አለች
"ምዕላድ የሆነ ነገር ልነግርህ ነው በደምብ ተዘጋጅ ብላኝ ለረዥም ደቂቃ ዝም አለች
"ዝምታው ሲበዛብኝ ኸውሲ ምንድነው አልኳት
"እእእ ምዕላድ እኔ
ክፍል ዘጠኝ ይቀጥላል................
ከ 100 like👍 ቡኃላ
𝐋𝐞𝐲𝐢𝐥𝐚 𝐌𝐮𝐣𝐧𝐮𝐧
ቆንጆ ያልሆነች ሴት የለችም።
አላህ ለሁሉም ሴቶች ለአንዱ ወንድ የሚታይ እንጂ
ለሌላ ወንድ የማይታይን ውበት አድርጎላታል!!💚
ምላሱዋ ብቻ ከጅማ እስከ ዉጭ ሃገር አይሁን 😂
........ፍርሀት🖤......
✎ ፀሐፊ፦ semi nas
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
┎━─━─━─━─━─━─━─━┒
𝐋𝐞𝐲𝐢𝐥𝐚 𝐌𝐮𝐣𝐧𝐮𝐧
┖━─━─━─━─━─━─━─━┚
╔════•| ✿ |•════╗
#ክፍል_ ሰባት
╚════•| ✿ |•════╝
<<ስላንተ ማወቅ እፈልጋለሁ ሁለቱም ሱብሂ አዛን ሲል ተነስተው እሷ ሰገደች እሱ ዝም ብሎ ቁጭ አለ
<<ለምን ማወቅ ፈለግሽ
<<አይ ወጣት ነህ በዚህ እድሜ ለምን እንዲህ ቶናለህ በዛ ላይ ሙስሊም ሆነ ኸምር እና ደሞ ለጋ ነህ በጣም ብዙ ነገር ካንተ ይጠበቃል ለምን ሲባል በዚ ሁኔታ የመዝሪያ ግዜህን ታሳልፋለህ
<<እኒንጃ
<<ምዕላድ አቀልድ
<<እሺ እንግዲ ማወቅ ከፈለግሽ እእእ ግን ከመጀመሬ በፊት በጣም ነው ማመሰግንሽ ስጀምርልሽ
የገጠር ልጅ ነኝ በጣም ውብ መንደር ነው አደለም ሰው እንስሳው ሚተዛዘንበት ሀገር ነው የቤቱ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ መካከለኛ ኑሮ ነው ምንኖረው በጣም ደስ የምትል ትንሽዬ አህላም የምትባል እህት አለችኝ በጣም ነው ምንዋደደው የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን የተማርኩት እዛው ነው እና ኢንትራንስ ከፍተኛ ውጤት አምጥቼ እዚ ተመደብኩ
<<የኔ ህይወት በሁለተኛ አመቴ ላይ አቅጣጫውን ቀየረ በአንድ በተረገመ እለት ኸውሰር ከምትባል ልጅ ጋር ተዋወቅኩ
ያኔ ለእረፍት ወደ ሀገሬ ሄጄ መጥቼ ነበር እና ሁሌም አዘውትሬ የምቀመጥባት ቦታ ነበረች ድንገት ከክላስ ወጥቼ ወደዛ ቦታ አመራው እና በጣም ታለቅስ ነበር የአላህ እጣፋንታዬ ይሄ ነው ጌታዬ ውሳኔክ ነው አምኜህ ልቀበል እያለች እያለቀሰ ነበረ "ረምላ በብርጭቆ ውሃ እየሰጠችው ቀጥል አይነት አስተያየት አየችው
ከዛ ጠጋ ብዬ እናት ሰላም ነው አሌኳት ፊቷን አዙራ እምባዋን ጠራርጋ እእእእእ አው ምነው ቦታህ ነው ልነሳልህ
"አረ ችግር የለውም ግን ይቅርታ የሆንሽውን ማወቅ ችላለሁ
"አረ ምንም ዝም ብዬ ነው
"እሺ ካልሽ ብሎ መፅሀፉን ገልፆ መንበብ ጀመረ
"እእእእእ መተዋወቅ እንችላለን
"እሺ ይቻላል
"እእእ ኸውሰር እባለለሁ የህክምና የሁለተኛ አመት ተማሪ ነኝ
"ምዕላድ እንዴ ታዳ እንዴት አላወቁክሽም አንድ ባች ሆነን
"አረ እኔ አውቅሃለሁ ያው ሴት ስለማታወራ ይሆናል ማታውቀኝ
ያን ቀን አብረን ዋልን በጣም የዋህ ናት የአዲስ አበበ ልጅ ናት ያለቀሰችበት ምክኛት ሲቀር ሁሉንም ነገር አጫወተችኝ በቃ ጓደኛማሞች ሆንን አንድ አመት ድረስ ምንም አይነት ግንኙነት አልነበረን ሶስተኛ አመታችንን እንደያዝን ሁለታችንም ስሜታችንን መደበቅ አቃተን ሳንተያይ መዋል አልቻልንም እንደምንም ብዬ ፍቅሬን ልገልፅላት አሰብኩ ትዕይንቱ አሁን እየሆነ እንደለ ነገር እየተሰማው ቅፅበቱን አስታውሶ ፈገግ አለ የናፍቆት ፈገግታ
"አንቺ እንደትላንት ምሳ ቁርስም ልትቀጪኝ ነው
"አረ ታሪክክ መስጦኝ እኮ ነው ቆይ እየሰራው ትነግረኛለህ ያው ደሞ ዛሬ ክላስ የለኝም ስለዚህ ሚፋታህ የለም ተነስታ አቀራርባ ቀለል ያለ ነገር መስራት ጀመረች
"እእእ አረ ቀጥልልኝ
<<እሺ ያን ቀን እንደምፈልጋት ደውዬ ነገርኳት እሷም እንደናፈቋት ገልፃልኝ ሰኣቱን ተነጋግረን ተገናኘን
"የአላህን ድንበር ለመጣስ ሰኣታት ቀሩን አለ አይደል ሰኣቱ ግን ክፋቱ አልሄድ አለ ሰኣቴን ቢያንስ ከ አስር ግዜ በላይ አይቼያለሁ ፈገግ እያለ
ተናፋቂዋ ሰኣት ደርሳ በቦታዬ ተገኘው ከሌላው ግዜ የበለጠ ተውባ መጣች ኡፍፍፍፍፍ ውበቷ አለ ፊቱን ደባብሶ
"ኸውስ አረፈድሽ በሰላም
"አይ ያው የሴት ነገር አለችው እየተሽኮረመመች
"እእእ ለምን ነበር የፈለግከኝ በጣም ጓግታ እሷ ጋር ያለው ስሜት እሱም ጋር ኢንዲኖር እየተመኘች
"እእእእ ኸውስ ለኔ ያለሽን ስሜት ማወቅ ፈልጋለው
"መጀመሪያ ያንተን ልስማው
"አቀርቅሮ አፈቅርሻለሁ አይኑን ጨፈነ ያላንቺ መኖር አልችልም በቃ የኔ ብቻ ሆኚ
"አይኗ እምባ አቅርሮ በስስት እያየችው አንተጋር ያለው እኔም ጋር አለ በጣም ነው ምወድህ ብላ ተነስታ አቅፋ ሳመችው
"ያን እለት ሁሉም ነገር ሀላል የሆነ መሰለን በቃ ተራርቀው እንደቆዩ ጥንዶች ለረዥም ሰኣት ተቃቀፍን ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ የሀራም ግዞ ሀ ብለን ጀመርን
"እእእእ ምዕላዴ እንብላ እና ትቀጥልልኛለህ አሁን ግን ፊትህን ታጠብ ከምንም ነገር በላይ የተለያዩበትን ምክንያት ማወቅ ፈለገች ሁለቱም ተጣጥበው ቁርሳቸውን በሉ።
''የበሉበትን እቃ አንስታ ፍራሿን አስተካክላ በመሀከላቸው ሁለት ሰው በሚያስቀምጥ መልኩ ርቃ ቁጭ አለች።
እእእ ቀጥልልኝ
ክፍል ስምንት ይቀጥላል ..............
ከ 100 like👍 ቡኃላ
𝐋𝐞𝐲𝐢𝐥𝐚 𝐌𝐮𝐣𝐧𝐮𝐧
መልኩን😍 ፀባዩን❤️ አስተሳሰቡን❤️🔥
book
ክፉ ደግ አይነጋገርም!!
.......ፍርሀት......
✎ ፀሐፊ፦ semi nas
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
┎━─━─━─━─━─━─━─━┒
𝐋𝐞𝐲𝐢𝐥𝐚 𝐌𝐮𝐣𝐧𝐮𝐧
┖━─━─━─━─━─━─━─━┚
╔════•| ✿ |•════╗
#ክፍል_ ስድስት
╚════•| ✿ |•════╝
"ረምላ የእለት ትምህርቷን ጨርሳ የሚያስፈልጋትን ገዛዝታ ወደ ቤት ተመለሰች ግቢውን ከፍታ ገባች በሩ ገርበብ ብሎ ነበር ሁለት ቀን ያለምንም ፍርሀት በቤቷዋ አሳድራው ዛሬ ግን ፈራች ወደ ኋላም መመለስ ፈለገች ጭንቅላቷ እና ልቧ ሙግት ገጠሙ
"ጭንቅላቷ አሸንፎ እንደምንም ኢስላማዊ ሰላምታ ሰጥታ ገባች
"ከሚያነበው መፅሀፍ ቀና ብሎ አፀፋውን መለሰላት
"ይቅርታ ፈተና ስለነበረብኝ ላይብረሪ ገባው እና አሁን ምሳ እሰራለሁ እሺ ይቅርታ እስካሁን ምሳ ሳትበላ
"አይ አመሰግናለሁ ምሳ መብላት አለመድኩም
"አረ ምዕላድ
"የምሬን ነው
"እሺ ብቻ ልስራ ምሰራራበትን እያዘገጃጀች ከሰል አቀጣጥላ ወደ ውጭ አወጣች እየገባች ውሎ እንዴት ነበር የያዘውን መፅሀፍ እያየች
"ፏ ነበር ዘ አልኬምስት ምርጥ መፅሀፍ ነው
"ምን ተማርክበት በጣም ብዙ ነገር እንደሚጠቀምበት እያሰበች
"ፈገግ ብሎ እያያት ብዙ ነገር አለ አይደል ምንም ነገር እንደሚቻል ሁሉም ሰው የተፃፈለትን እንደሚኖር
"ፈጣን አእምሮ አለክ መጠቀም አቃተህ እንጂ ሳታስበው ያመለጣት አፏን እዛ አየችው
"ጣጣ የለውም ደሞ እውነትሽን ነው ለዚ ሁሉ እሷ ናት ተጠያቂ እሷ አለ ጭንቅላቱን ይዞ
"ይቅርታ ምዕላድ ይቅርታ ማለት የሌለብኝ ነገር አልኩክ
"አይ ችግር የለውም ብሎ መፅሀፉን አስቀምጦ ወጣ
"ዊህ ረምላ ዊህ ረምላ ምላስሽ አያርፍም ኣኣኣ ግን ምን ቢሆን ነው ይሄን ያክል ሴት ሚጠላው ምሳዋን ሰርታ በልታ የደርስ ሰዓት እስኪደርስ መጥናት ጀመረች።
አስር አዛን ብሎ እንደተለመደው ሰግዳ ወደ መድረሳ ሄደች
"ልረሳሽ ነው ልረሳሽ ነው አህህህ ተይ ከፊቴ ጥፊ ተይ ጥለሽኝ ሄድሽ ከሃዲ ከሃዲ ነሽ ቆይ ባፈቀርኩ አንቺን ባልኩ ለምን አወቅኩሽ እህ የያዘውን ከምር ተጎነጨ ከከምር ቤቱ እየወጣ እረሳሻለሁ እረሳሻለሁ አለ እያጓራ
"ከመድረሳ እየመጣች ምዕላድን ከሩቅ አየችው አረ ኢሄ ልጅ ምን ይሻለው በአላህ ዝም በይ ረምላ በአሁን አንቺ ነሽ ተጠያቂ አንቺ አርፎ ቤት ተቀምጦ የነበረውን ልጅ በምላስሽ ነክተሽው አላት ውስጥዋ
"ምዕላድ ምዕላድ በአላህ ተነስ ሰው ስለለመደው ሁሉም በምፀት እያየው ያልፋል ጎንበስ ብሎ ምን ሆነህ ነው የሚለው እንኳን የለም
"ምን ፈለግሽ ከኔ ራቂ በቃ ተይኝ እኔ ምጠቅም ሰው አደለውም ደሞ ለምን ታዝኚልኛለሽ እንዴ እንዴ እሷ ናት የላከችሽ እሷ ናት አደል በቃ እሷ እኔን አቸወኝም ማለት ነው
"ምዕላድ ተነስ ወደ ቤት እንሂድ ተነስ
"አልሄድም በቃ አልሄድም
"እንደምንም አንስታው ወደ ቤት እዛው ሄደች
እንደ ለመደው ፍራሹ ላይ ከነ ጫማው ተዘረረ
"ረምላ መግሪብ ለመስገድ ውዱ አርጋ ገባች ከመስገጃዋ ሳትነሳ ቁርዓን እየቀራች ቆየች በዛውም ኢሻ ሰግዳ ስትነሳ
"ብርድ ልብስ ልታለብሰው ዞር ስትል ፍራሹ በቱከት ተበላሽቶ ነበር ምንም ሳትል ቱከቱን ጠራርጋ አልብሳው ለራሷ ፍራሽ እና ምትለብሰውን ለማምጣት በእናት አባቷ ሞት የተቆለፈውን ቤት ለመክፈት ሄደች ከፍታ እንደገባች የናት አባቷ ትዝታ ፊቷ ላይ ድቅን አለ ለማልቀስ እየዳዳት የአባቷን መኝታ ቤት አያየች ብዙ ቆየች እምባዋ አልቆም ሲላት በፍጥነት ክፍሉን ለቃ ወጣች የሚያስፈልጋት ከወንድሟ ክፍል ወስዳ ወደ ትንሽዬ ቤቷ ገባች ከምዕላድ ራስጌ መፅሀፍቶችን አነሳስታ ፍራሿን አንጥፋ ተኘች።
"ከድር ሊዛን ከተገናኛት ቡኋላ ወደ ውጭ እየወጣ ድምፁን ከፍ አርጎ ብሉ ጠጡ እያለ ለፈለፈ በባህል ዘፈን እስከ ንጋት ጨፈሩ በበነጋው በባህሉ መሰረት በጧት ገንፎ ሰርቶ ለሙሽሮች ቀረበ ሊዛ ከዚ ሰውዬ ጋር አደለም መብላት አብረው በአንድ መንገድ ባይጓዙ ደስታዋ ነው ነገሩ የተፈጥሮ ህግ ሆኖ በከድር በመጀመሪያ ምስቱ የቀረበላትን ገንፎ አንድ ጉርሻ ስትጎርስ የካሊድ ፊት መጣባት እየጮሀች ተስፈንጥራ ተነሳች ከድር ሁኔታዋ አናዶት ጎትቶ አስቀመጣት ሳቶድ በግዶ እየቀፈፋት በላች።
"ኑር ካለበት ጫቃ ማዶ አንድ ቡና ከምታፈላ ሴት ጋር በአይን ፍቅር ወደቀ እሷን ለማየት ብዙም በቀን መውጣት ያለመደው ሶስት አራቴ እሷ ዘንድ ይሄዳል
"ቡና እያቀረበችለት እጇን ያዛት ቀና ብላ ስታየው ለቀቃት ቡናውን ቀድታለት እየተመናቀረች ሄደች
ባካሆኗ ስቆ ቱኩሱን ቡና ተጎነጨው ሁኔታውን እያየች የነበረችው የልጅቷ እናት ሰቋን ለቀቀችው።ኑር እንደተኮሳተረ መቶ ብር አስቀምጦ ወጣ ልጅቷ ብሩን አንስታ ወደ እናቷ ጋር በመሄድ አዮ ታውቂዋለሽ አለቻት
"ተዬት አውቄው ማንም ይሁን ማን ብረት መዝጊያ ይሆናል ጠበቅ አርጊው አቻት ልጅቷ እየሳቀች ወደ ጓዳ ገባች።
ክፍል ሰባት 100❤ ይቀጥላል ...............
𝐋𝐞𝐲𝐢𝐥𝐚 𝐌𝐮𝐣𝐧𝐮𝐧
Reviews channel
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
❤️ለይላ መጅኑን🌹 is a Telegram channel in the category «Религия и духовность», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 5.3K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 27.4, with 0 reviews and an average score of 0.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 3.6 ₽, and with 1 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий