
KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /
Kotebe University of Education Community / አዲስ ነገር መረጃ /
Channel statistics
የልጅ ኤልያስ ዩኒቨርሲቲ መቋቋም ለሚመጣው ትውልድ ከትምህርት ባለፈ የአስተሳሰብ የማንነት ኩራት በራስ መተማመን እንዲያዳብር ያደርጋል።
ለረጅም ዘመናት ሳይንስና ቴክኖሎጂ የውጭ አገር ዜጎች ብቻ የሚሰሩት ተደርጎ ሲታሰብ ቆይቷል። ትውልዱ የኳንተም ፊዚክስን ወይም የሶፍትዌር ምህንድስናን በገዛ ቋንቋው ሲማር እኛም መስራት እንችላለን የሚል የሥነ-ልቦና ጥንካሬን ያገኛል። ቋንቋን ከዕውቀት ጋር ማዋሃድ ለትውልዱ ትልቅ ኩራትን ይፈጥራል።
የፈጠራ አቅምን (Creativity) ያሳድጋል አንድ ተማሪ በትምህርት ገበታ ላይ ግማሽ ጊዜውን ቃላትን ለመተርጎም ካሳለፈ ለፈጠራ የሚሆን ጊዜ ይሻማዋል ትውልዱ በገዛ ቋንቋው ሲማር ግን ትኩረቱ ይህ ነገር እንዴት ይሰራል? እና "አዲስ ነገር ምን ልፍጠር? በሚለው ላይ ይሆናል። አገራችን ኢትዮጵያን ወደፊት የራሷን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዓለም እንድታበረክት በር ይከፍትላታል። ትዉልዳችን በተግባር ላይ የተመሰረተ Practical ትምህርት ስለሚማር ከዩኒቨርሲቲ ሲወጣ ሥራ ፈላጊ ሳይሆን ሥራ ፈጣሪ ይሆናል። በአገር ውስጥ በሚገኙ ቁሳቁሶች ማሽኖችንና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መስራት መቻሉ ለትውልዱ የኢኮኖሚ ነፃነትን ያጎናጽፈዋል።
ልጅ ኤልያስ ዩኒቨርሲቲ ለትውልዱ የሚሰጠው ትልቁ ስጦታ "የዕውቀት ቁልፍ" ነው።
ይህ ቁልፍ ደግሞ በውጭ ቋንቋ መቆለፊያ የታሰረ ሳይሆን፣ በማንኛውም ኢትዮጵያዊ እጅ የሚከፈት በቀላሉ የሚገባና የሥልጣኔን በር የሚከፍት ነው።
ይህ ተቋም በተለይ ሳይንስና ቴክኖሎጂን በአፍ መፍቻ ቋንቋ በአማርኛ ለማስተማር የያዘው ራዕይ ከሀገራችን አልፎ እንዲሁም ለአፍሬካዉያን የትምህርት ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው።
ኢትዮጵያ ካሏት በርካታ ጥንታዊ ዕውቀቶች መካከል አብዛኞቹ ከዘመናዊው ሳይንስ ጋር ጥልቅ ቁርኝት አላቸው።
እነዚህን ዕውቀቶች ከዘመናዊው ሳይንስ Physics, Chemistry, Engineering, Medicine አንጻር ስንመዝናቸው አባቶቻችን ምን ያህል የረቀቀ ጥበብ እንደነበራቸው እንረዳለን።
ዋና ዋናዎቹን ትስስሮች እንዲህ ማየት ይቻላል የሕንፃ ምህንድስና Civil Engineering & Architecture የአክሱም ሐውልቶች ግዙፍ ድንጋዮችን ከአለት ፈልፍሎ ማውጣት ማጓጓዝ እና ቀጥ አድርጎ መትከል ከፍተኛ የፊዚክስ Statics and Dynamics እና የሜካኒካል ምህንድስና ዕውቀትን ይጠይቃል። በተለይ የስበት ማዕከልን Center of Gravity ጠብቆ ማቆም መቻላቸው የሚደነቅ ነው ። የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፦ ከአንድ ወጥ ድንጋይ ተፈልፍለው መሰራታቸው የጂኦሎጂ Geology እና የከፍተኛ መዋቅራዊ ምህንድስና Structural Engineering ውጤቶች ናቸው። የውኃ መውረጃ መስመሮቻቸውና የድጋፍ ምሶሶቻቸው ስሌት ዛሬም ድረስ መሐንዲሶችን ያስደምማል።
የሕክምና ሳይንስ Medical Science & Pharmacology ባህላዊ መድኃኒቶች ጥንታውያን ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ዕፅዋት፣ ማዕድናትና የእንስሳት ተዋጽኦዎች መድኃኒት የመቀመም ጥበብ ነበራቸው። ይህም ከዘመናዊው የፋርማሲ Pharmacognosy ሳይንስ ጋር ይያያዛል። ለምሳሌ እንቆቆ እና ኮሶ ለሆድ ትል መድኃኒትነት መጠቀማቸው በዘመናዊ ሳይንስ የተረጋገጠ ውጤት አለው ቀዶ ሕክምና በጥንታዊ የቤተክህነት መጻሕፍት ውስጥ ስለ ዓይን ሞራ ማውጣት እና ስለ ተሰበሩ አጥንቶች ጥገና ውጋት የሚገልጹ መረጃዎች አሉ። ይህ ከዘመናዊው Surgery እና Orthopedics ጋር ይመሳሰላል ። የሥነ-ከዋክብት ጥናት Astronomy & Mathematics የአቡሻህር ስሌት የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር በከዋክብት፣ በጨረቃና በፀሐይ ዑደት ላይ የተመሰረተ ነው። ይህ ስሌት ከፍተኛ የሒሳብ Mathematics እና የሥነ-ከዋክብት Astronomy ዕውቀትን ይጠይቃል። የፀሐይና የጨረቃ ግርዶሽን ቀድሞ መተንበይ መቻላቸው የጥበቡን ጥልቅነት ያሳያል የብረታ ብረትና የኬሚስትሪ ጥበብ Metallurgy & Chemistry የቀለጣ ጥበብ ጥንታውያን ኢትዮጵያውያን ብረትን አቅልጠው ለጦር መሣሪያ፣ ለቤት መገልገያና ለጌጣጌጥ ይጠቀሙ ነበር። ይህ የኬሚስትሪንና የሜታለርጂን Metallurgy ሳይንስ በተግባር መረዳታቸውን ያሳያል የቀለም ቅመማ በጥንታውያን መጻሕፍት ብራናዎች ላይ የሚታዩትና ለዘመናት የማይለቁ ቀለሞች ከዕፅዋትና ከማዕድናት የተቀመሙ የኬሚስትሪ ውጤቶች ናቸው።
የግብርና ሳይንስ Agricultural Science የእርከን ስራ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለሺህ ዓመታት የቆዩ የእርከን ስራዎች የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል የተሰሩ የኒያክ ኢንጂነሪንግ Hydraulic Engineering ስራዎች ናቸው የሰብል ዝርያዎችን ማላመድ እንደ ጤፍ እና እንሰት ያሉ ሰብሎችን ለይቶ ማልማትና ለምግብነት ማዋል ከዘመናዊው የዕፅዋት ዘረ-መል Genetics እና ባዮቴክኖሎጂ ጋር የተያያዘ ነው።
እነዚህ ጥንታዊ ዕውቀቶች በዘመናዊ ሳይንሳዊ ስም ባይጠሩም፣ በተግባር ግን ሳይንሳዊ ሕጎችን የተከተሉ ነበሩ። ልጅ ኤልያስ ዩኒቨርሲቲ እነዚህን ጥበቦች በምርምር አግኝቶ ከዘመናዊው ቴክኖሎጂ ጋር በማገናኘት ለትውልዱ በማሰተላለፍ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የሳይንስ ማንነት እንዲኖራት ያደርጋል።
ትዉልዳችዉን በገዛ ቋንቋቸው ሳይንስና ቴክኖሎጂን በማሰተማር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ዓለም አቀፍ የሥልጣኔ ማማ ላይ የደረሱ በርካታ አገሮች አሉ እነዚህ አገሮች የቋንቋን መሰናክል በመስበር ዕውቀትን ለሕዝባቸው ተደራሽ በማድረጋቸው ውጤታማ ለመሆን በቅተዋል።
ለምሳሌ እነዚህ ዋናዎቹን አገሮችና ተሞክሯቸውን እንደሚከተለው መመልከት ይቻላል።
1.ጃፓን (Japan) ከምዕራባውያን አገራት ውጭ በቴክኖሎጂ ቀዳሚ መሆን የቻለችው በቋንቋዋ በመጠቀሟ ነው የተከተሉት መንገድ፦ በ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን በሜይጂ ዘመን የነበሩ የጃፓን ምሁራን የዓለምን የሳይንስና የቴክኖሎጂ መጻሕፍት ወደ ጃፓንኛ ተረጉመዉ ዛሬ ጃፓን በሮቦቲክስ፣ በአውቶሞቢል እና በኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ የዓለም መሪ መሆን የቻለችው ልጆቿ በገዛ ቋንቋቸው የሳይንስን ጥልቀት ስለሚረዱ ነው።
2.ደቡብ ኮሪያ South Korea
ከ፶ ዓመታት በፊት ከኢትዮጵያ በታች በኢኮኖሚ ደካማ የነበረችው ደቡብ ኮሪያ አሁን ካለችበት የዕድገት ደረጃ ላይ የደረሰችው በትምህርት ሥርዓቷ ነው። ሳይንስን፣ ሒሳብንና ምህንድስናን በኮሪያኛ Hangul ቋንቋቸው ብቻ ነው የሚማሩት። ውጤቱ እንደ ሳምሰንግ Samsung እና ሂዩንዳይ Hyundai ያሉ የዓለም ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማትን ማፍራት ችለዋል።
3. ጀርመን Germany
ጀርመን በአውሮፓ የምህንድስና እና የኢንዱስትሪ ማዕከል ናት። በጀርመን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አብዛኛው የምህንድስና እና የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት የሚሰጠው በጀርመንኛ ቋንቋ ነው። ጀርመን በዓለም ላይ ጥራት ያለው የማሽነሪና የሕክምና መሣሪያዎችን በማምረት የታወቀችው፣ ዜጎቿ ሳይንሱን በገዛ ቋንቋቸው ጠልቀው ስለሚመራመሩበት ነው።
4. ቻይና China
ቻይና በአሁኑ ወቅት በጠፈር ምርምር እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዓለምን እየመራች ነው። ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ፒ.ኤች.ዲ (PhD) ድረስ ትምህርታቸው በማንዳሪን ቻይንኛ ቋንቋ ነው። ውጤቱ፦ የቋንቋ እንቅፋት ስለሌለባቸው በቢሊዮን የሚቆጠረው ሕዝባቸው በፈጠራ ስራ ላይ በቀላሉ እንዲሰማራ አድርገዋል።
ሩሲያ በጠፈር ምርምር Space Science በኑክሌር ፊዚክስ እና በምህንድስና ዓለምን ከሚመሩ አገራት አንዷ ናት። ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛው የሳይንስ ምርምር ድረስ ትምህርታቸው በሩሲያኛ ቋንቋ ነው። ሩሲያ የራሷን የጠፈር መንኮራኩሮች፣ የጦር መሣሪያዎችና ውስብስብ ማሽነሪዎችን የምታመርተው በገዛ ቋንቋዋ በሰለጠኑ ምሁራን ነው።
6. እስራኤል Israel
እስራኤል በቴክኖሎጂና በግብርና ምርምር Agro-Tech በዓለም እጅግ የረቀቀች አገር ናት ለብዙ ዘመናት በሥራ ላይ ያልነበረውን ዕብራይስጥ Hebrew ቋንቋን በማነቃቃት፣ ለዘመናዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲመጥን አድርገውታል። ዛሬ እስራኤል የስታርት-አፕ አገር Start-up Nation ተብላ የምትጠራው፣ ዜጎቿ በገዛ ቋንቋቸው የፈጠራ ሥራ ላይ ስለሚሰማሩ ነው።
7. ፈረንሳይ France
ፈረንሳይ በሳይንስና በሒሳብ ትምህርት ረጅም ታሪክ ያላት አገር ናት በፈረንሳይ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሳይንስ፣ ሕክምና እና ምህንድስና የሚሰጠው በፈረንሳይኛ ነው። የራሳቸው የሳይንስ አካዳሚ French Academy of Sciences አዳዲስ ሳይንሳዊ ቃላትን ወደ ፈረንሳይኛ የመተርጎም ኃላፊነት አለበት በዓለም ላይ ከፍተኛውን የሒሳብ ሽልማት Fields Medal ካሸነፉ አገራት መካከል ፈረንሳይ ቀዳሚዋ ናት።
8. ቱርክ Turkey
ቱርክ በአሁኑ ወቅት በወታደራዊ ቴክኖሎጂ እና በግንባታ ምህንድስና በፍጥነት እያደገች ያለች አገር ናት ምንም እንኳን የእንግሊዝኛ ተጽዕኖ ቢኖርም፣ አብዛኞቹ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሳይንስን በቱርክኛ ያስተምራሉ ቱርክ የራሷን ሰው አልባ አውሮፕላኖች Drones እና ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማምረት የቻለችው በዚህ መንገድ ነው።
9.ስካንዲኔቪያን አገራት ኖርዌይ፣ ስዊድን፣ ዴንማርክ
እነዚህ አገሮች ምንም እንኳን እንግሊዝኛን በሚገባ ቢናገሩም፣ መሰረታዊ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ትምህርታቸውን የሚሰጡት በገዛ ቋንቋቸው ነው በዓለም የኑሮ ደረጃ እና በፈጠራ ሥራ Innovation ሁልጊዜም ቀዳሚዎቹ ናቸው።
ልጅ ኤልያስ ዩኒቨርሲቲም ይህንን ተሞክሮ ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት
የኢትዮጵያን የትምህርት ሥርዓት ከውጭ ጥገኝነት ነፃ በማውጣት በራሷ ዕውቀትና ጥበብ የምትመራ የበለጸገች ሀገር ለመመሰረት ነዉ።
- ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ
*** *** *****
(ኮትዩ፣ መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም) - ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡
በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የእንኳን ደስ ያላችሁ ንግግር ያሰሙት የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ፣ “በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ “50 ዓመት የሴቶች ድምጽ ለእኩልነት እና ለበለጸገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የሚከበረው ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን፣ ሴቶች በማኅበረሰብ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በልማት ዘርፎች ያበረከቱትን አስተዋፅኦ፣ ይልቁንም በቀጣይ የሚያከናውኗቸውን ታላላቅ ተግባራት የምንዘክርበት ቀን ነው” ብለዋል፡፡ በዚህ ረገድ ዩኒቨርሲቲው ሴቶች በምርምር፣ በማስተማር እና በአመራርነት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን የገለጹት ፕሬዘዳንቱ፣ ይህንንም ጥረት በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣ “ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ለእኛ ለሴቶች ትርጉሙ ጥልቅ ነው፤ ይህም የሆነበት ምክንያት በታሪክ ውስጥ ሴቶች ወደ ትምህርት ገበታና ወደ ጥናትና ምርምር አዳራሾች እንዳይገቡ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ተከልክለው ከነበረበት ዘመን ወጥተው ለዛሬው ማንነታችን መሠረት የተጣለበት፤ የእናቶቻችን ጽናት ፍሬ አፍርቶ ውጤት የታየበት ዕለት በመሆኑ ነው” ብለዋል።
“ዛሬ በዚህ አዳራሽ የተሰበሰብነው በዓሉን ለመዘከር ብቻ ሳይሆን ባለፉት አምስት አስርት ዓመታት ውስጥ lሴት ምሁራን በሀገራችን የተፈጠረውን ጉልህ ለውጥና እድገት እንዲሁም ታሪካዊ ጉዞዎችን እውቅና ለመስጠት ጭምር ነው” ያሉት ሚኒስትሯ፣ በዓሉ በዓለምአቀፍ ደረጃ ሴቶች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጅና በፖሊሲ ቀረጻ ዘርፍ ያላቸውን እምቅ አቅም በተግባር ያሳዩበት፣ እውቀት ጾታ እንደማይለይ ለዓለም ያረጋገጡበት፤ የሴቶች ጉዞ የሚታወስበት ታላቅ መድረክ መሆኑንም አውስተዋል።
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሴት ተመራማሪዎች ማኅበር ፕሬዘዳንት ዶ/ር አልማዝ ደብሩ “የኢትዮጵያ ሴቶች ምሁራን ያበረከቱት አስተዋፅኦና ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች”፤ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ስብዕና ግንባታ ምክትል ዲን ወ/ሮ ምኞት ጌታቸው፣ “የ50 ዓመታት የለውጥ ጉዞ እና የማርች 8 ታሪካዊ ፋይዳ” በሚሉ ርዕሶች በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተዘጋጁ ሁለት የመወያያ ሰነዶችን በማቅረብ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱም የሴቶች ሁለንተናዊ ሀገራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከቀደመው ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ፣ በቀጣይም የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ መቀጠል፣ ለዚህም በመድረኩ የተነሱ ሃሳቦችን በተግባር ወደ ውጤት መቀየር፣ ለተፈጻሚነቱም የወንዶችን አጋርነት በአወንታዊ አመለካከት ማጎልበት እና ሴት ምሁራን ትስስር በመፍጠር የግንባር ቀደምትነት ሚና መጫወት እንደሚጠበቅባቸው ከመግባባት ላይ የተደርሷል፡፡
በዩኒቨርሲቲው በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በተከበረው በዚህ በዓል ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፤ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨሰትመት ሆልዲንግ ምክትል ዳይሬክተር ክብርት መልዕክተ ሳህሉ፣ የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፋሲካ በላይ እና ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የመጡ እንግዶች ሃሳባቸውን አካፍለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተሳተፉ የዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኛች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአዲስ አበባ ከተማ ከተማ ውስጥ እየተካሄዱ ያሉ የልማትና ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት
#Kotebe_University_ofEducation_committed_to_excellence_in_Education
ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾችችንን ይከታተሉ:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/@kueducation
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
******
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መንግሥት እና ሕዝብ የጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት እና ትርጉም ያለው ውጤት ለማስመዝገብ በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሳሰቡ።
ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር የገባውን የ2018 ዓ.ም የቁልፍ ውጤቶች አመላካቾች ስምምነት አፈጻጸም በአዲስ አበባ አዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል እየገመገመ ይገኛል።
ተቋማቱ ከመማር ማስተማር ባለፈ የአካባቢያቸውን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በጥናት እና ምርምር እንዲፈቱ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠይቀዋል።
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥም ከአመራር እስከ ታችኛው የሥራ ክፍል የተቀናጀ ርብርብ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሸኔ እንዳሉት፣ ተቋማቱ በሥራ ባህል እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ መሻሻል ቢያሳዩም በቅንጅት የመሥራት ክፍተቶች ይታይባቸዋል።
ይህንን የአመራር ችግር ለመቅረፍም “የአመራር አካዳሚ” እየተቋቋመ መሆኑን እና በቅርቡ ሥልጠና እንደሚጀመር ጠቁመዋል።
ግምገማው ተቋማቱ ከሚኒስቴሩ ጋር በገቡት ውል መሠረት ያከናወኗቸውን ተግባራት እና ያጋጠሟቸውን ፈተናዎች በጥልቀት ለመለየት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በሰናይት ብርሃኔ
#Ethiopia #EBC #HigherEducation #AcademicExcellence #MoE
Reviews channel
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ / is a Telegram channel in the category «Образование», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 4.3K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 12.3, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 4.8 ₽, and with 2 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий