
Monetize Telegram Mini App with Telega.io
Connect your app, set CPM, and watch your revenue grow!
Start monetizing
27.9

Advertising on the Telegram channel «ጎጃም ሚዲያ gojjam media»
5.0
16
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$7.20$7.20local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
play_circleVideo preview is unavailable
በኢንተርኔት ምክናየት ዘግይቶ የደረሰን መረጃ‼
ጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር በ28/11/2017ዓ.ም በኮሎኔል አበበ የሚመራውን የ23ኛ ክፍለጦር የወራሪውን ሀይል አሽፋ መገንጠያ ፦ ጁጋ ተራራ ፣ ደረዋ ተራራ እና ኤልያስ ተራራ ላይ ድባቅ የመቱት እና የነበረው ምሽግ እና ጅምላ መቃብር በቪዲዮ።ታሪክን ሁሌም በእጃቸው የሚጽፉት
ግዮን ብርጌድ
ዘንገና ብርጌድ
ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ እንጅባራ ብርጌድ
፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ
መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ 5ቱ ብርጌድ በጋራ በዝህ መልኩ ነበር የአገዛዙን ሰራዊት ከምሽጉ ድረስ በመሄድ ሙት ቁስለኛና ምርኮኛ አድርገው ከነፍስወከፍ እስከ ቡድን መሳርያ የቀሙት።
977
12:10
12.08.2025
የገዳ ኮማንዶ በዋና ከተማው ሊሰማራ ነው‼️
የኦሮሚያ ክልል “ገዳ ልዩ ኮማንዶ” የተሰኘ ኃይል በአዲስ አበባ ከተማ ሊያሰማራ ነው። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ገዳ ልዩ ኮማንዶ የተሰኘ ወታደራዊ ኃይል በአዲስ አበባ ከተማ ሊያሰማራ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል።
በከተማዋ ይሰማራል የተባለውና “ገዳ ልዩ ኮማንዶ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ኃይል የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ መዋቅር ክንፍ ሲሆን፣ በአዲስ መልክ የሚዋቀርና በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ልዩ ስምሪት የሚሰጠው መሆኑ ተነግሯል።
ልዩ የኮማንዶ ኃይሉ ከፌዴራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ ጎን ለጎን በከተማዋ ስምሪት የሚሰጠው ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማትን እንዲጠብቅ ይደረጋል መባሉ ታውቋል።
የኦሮሚያ ክልል ለገዳ ልዩ ኮማንዶ ኃይል የሚሆን የሰው ኃይል መልምሎ መጨረሱን እና ልዩ ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት ላይ እንደሚገኝ መረጃውን ለመጽሔታችን ያደረሱት ምንጮች አያይዘው ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ በርካታ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ህንፃዎች ያሉት ሲሆን፣ በስልጠና ላይ የሚገኘው የገዳ ልዩ ኮማንዶ ኃይል ስልጠናውን ሲያጠናቅቅ እነዚህን ተቋማት እንዲጠብቅ ይደረጋል ተብሏል። የመረጃ ምንጫችን አክለውም፣ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ መምሪያ መቀመጫውን በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ ካደረገ በኋላ አስራ አራት የሚጠጉ ቦታዎችን ለወታደራዊ ካምፕ አገልግሎት እንዲውሉ አጥሮ ማስቀመጡን በመጠቆም፣ የገዳ ልዩ ኮማንዶ ኃይል እነዚህን ቦታዎች እንዲጠብቅ እንደሚደረግ ለመጽሔታችን አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪ የገዳ ልዩ ኮማንዶ ኃይል ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንን እንዲጠብቅ እንደሚደረግ እና በሞጆ እና ናዝሬት ዙሪያ ስምሪት እንደሚሰጠው የመረጃ ምንጫችን ለዞብል ፖስት ገልጸዋል።
zoble post
978
12:56
12.08.2025
imageImage preview is unavailable
በቀን 06/12/2017 ዓ.ም የአፋጎ ሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር የየቦቅላ አባይ ብርጌድ ፡ የደጅ አዝማች ተድላ ጓሉ ብርጌድ እንዲሁም የራሱ የፈጠራ ውጤት በሆነው የዘሪሁን 13 ምድብ የአረመኔውን ሰራዊት አፈር ድሜ አስገብተውታል።ነበልባሎቹ የቅጥረኛውን ሀይል እጅና እግሩን እየቆራረጡ በየሆስፒታሉ አስተኝተውታል።
በዚህ ከፍተኛ ትንቅንቅ በተደረገበት ውጊያ ክንደ ነበልባሎቹ በሚገርም መናበብ የአረመኔውን አገዛዝ ሰራዊት እግሬ አውጪኝ ያሯሯጡት ሲሆን የአድማ ብተና አመራሩ ጀርባውን ተነድሎ ህክምና ደ.ማ ሆስፒታል ገብቷል።
ይህ ውጊያ የተደረገው የቦቅላ መገንጠያ ላይ ሲሆን ከ25በላይ የጠላት ሀይል ሲደመሰስ ከ14 በላይ ቁስለኛ ሆኗል።ውጊያው በየቦቅላ አባይ ብርጌድ ጦር አዛዥና በተድላ ጓሉ ብርጌድ ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ ተመርቷል።
በሌላ ዜና በዚህ ውጊያ መሐል 2የአገዛዙ አሽከር የነበሩ የፖሊስ አባላት ተድላ ጓሉ ብርጌድን ተቀላቅለዋል።
አዲስ ትውልድ፡
አዲስ አስተሳሰብ፡
አዲስ ተስፋ!!
ፋኖ መ/ር እንደሰው ታምሩ የሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር ህ/ግ ሀላፊ
805
15:21
12.08.2025
imageImage preview is unavailable
የጁላ የግል ቅጥረኛ መናዱን ቀጥሎበታል።
ስርዓቱ በቃን ያሉ ከዋሸራ የወጡ የመከላከያ አባላት የአርበኛ ዘመነ ካሴን ጥሪ ተቀብለው የዮሐንስ አለማየሁን ብርጌድ ተቀላቅለዋል።
አብርሀም ችሎት እና ማሾ ኡስማን የተባሉ የአማራና የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ የመከላከያ አባላት ከ59ኛ ክፍለጦር፣ 1ኛ ሬጅመንት፣ 304ተኛ ኮር፣ 1ኛ ሻለቃ ፣ 5ኛ ሻምበል ወጥተው በሰላም ፋኖን ተቀላቅለዋል።
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
በአፋጎ 2ተኛ/ተፈራ ዳምጤ/ ክፍለጦር የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት
ጎንጅ ቆለላ:- ነሀሴ 06/2017 ዓ.ም
644
16:53
12.08.2025
imageImage preview is unavailable
አይሸሽም ብርጌድ የአፋብኃ አባት አርበኞችን የአንድነት ጥሪ በመቀበል ወደ አፋብኃ ተቀላቀለ!
በዛሬው ዕለት ነሀሴ 6 ቀን 2017 ዓ/ም የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በበጌ ምድር ክፍለ ጦር ስር መጠሪያዋን በጀግናው አይሸሽም ዮሀንስ ስም ያደረገችው አይሸሽም ብርጌድ ከአይንባ እስከ ቋራ፣ ከደንቢያ እስከ አርማጭሆ፣ ከሰቀልት እስከ ጎንደር ከተማ ድረስ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ታሪኳን በጀግኖች የወርቅ መዝገብ የፃፈች ብርጌድ ስትሆን አሁን የበለጠ ለመድመቅና ለመጠንከር፣ ለማሸነፍና ለድል ለመብቃት መድሀኒቱ በአማራዊ አንድነነት ጥላ ስር መሰባሰብ በመሆኑ በጋራ ደማቸውን ለማፍሰስ ፣ አጥንታቸውን ለመከስከስ፣ ህይዎታቸውን ለመገበር ሲሉ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር ጋር ተሰልፈዋል።
የአማራ ፋኖ ይህን የሕልውና አደጋ ለመቀልበስና የህዝባችን ነፃነት ለማስከበር የተጀመረው እምቢ ባይነት በታሪካችን ልዩ ቦታ የሚሰጠው እና የምንፈፅመው ጉዳይ ስለሆነ ይህን ታሪካዊ ወርቃማ እድል ለመጠቀም ከአገዛዙ ሀይል ጋር ሌት ተቀን፣ በጋ ከክረምት ከምድር እስከ አየር ሀይል ድረስ እየተፋለምን ከሁለት አመት በላይ አስቆጥረን በስኬት እየተጓዝን ነው።
ይህን የጀመርነውን አገዛዙን የማስወገድ ትልቅ ስራ በሚገባ ለመከወን እና ለማጠናቀቅ ያመች ዘንድ ውስጣዊ አንድነታችን በማጠንከር ሊለያዩን የሚችሉ ጥቃቅን ጉዳዮችን በብስለት በመፍታት መቻቻልና መግባባትን አስቀድመን ለአማራ ህዝብ ሲባል በአንድ በድርጅት ጥላ ስር መታገል እጅግ አስፈላጊ ነገር በመሆኑ የአይሸሽም ብርጌድ አመራሮች እና አባላት ወደ አንድነቱ ሲመጡ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ አመራሮች ፣ የታድሎ ብርሃን እና የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አመራሮች ተገኝተው እንኳን ደህና መጣችሁ ወንድማዊና ጓዳዊ አቀባበል በደመቀ መልኩ ተደርጎላቸዋል።
“ከዛሬ ጀምሮ ከአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ወጥተን ወደ አማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ (5ተኛ) ኮር አካል ሁነን ለተከበረው የአማራ ህዝብ ዋጋ ለመክፈል መጥተናል፣ ይህ አዲሱ የፋኖ ትውልድ ልክ እንዳባቶቹ ለጠላቶቹ የማይንበረከክ የሰለጠነ ሰራዊት ይዞ ጠንካራ ህዝባዊ መሰረት ገንብቶ የህዝቡን የህልውና እና የፍትህ ርዕት ጥያቄዎች በተሎ ለመመለስ ሀገራዊ እና ታሪካዊ ተጋድሎ እያደረገ ያለ መሆኑ ይታወቃል። ስለዚህ ወደ አንድነቱ ያልመጣን ልዩነታችንን ሁሉ ትተን በአንድነት ቆመን ይህን አረመኔአዊ ስርአት ከምድረ ገፅ እንድናጠፋው ጥሪ እናቀርባለን።” ብለዋል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር
የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ )
621
16:59
12.08.2025
ሰበር
1ኛ ክ/ጦር ጣና መብረቅ ብርጌድ የጠላት ሂሊኮፍተር ላይ የተሳካ ጥቃት ፈጸመ::
©ሞገስ አማራው
719
17:02
12.08.2025
ነሐሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም
የጥንቃቄ መልዕክት ‼️
👉 ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሀሳባችሁን ለምትገልፁ አመራር እና አባላት:-
"እንደ ፋኖ እንምከር" ሲል ሰብሳቢያችን ለአቻ የፋኖ አመራሮች ያቀረበው ጥሪ እና አጀንዳ ድርጅታዊ ነው፤ የሚመራውም በድርጅታዊ አሰራር ነው። ጥሪውን ተከትሎም መሬት ያሉ ስራወች አሉ።
ከዛ ባለፈም የድርጅት ምስረታ ሂደቱ እንዴት መጠናቀቅ እንዳለበት እንደ አፋጎ ለሚመለከተው አካል ግልጽ አቅጣጫ ተቀምጧል።
እስካሁን ያለውን ሂደት እና ያጋጠሙ ችግሮችን ከነ መፍትሔ አቅጣጫወች ከሚመለከተው አካል ጋር "በየመድረኮች " ተነጋግረናል፤ ውሳኔም አሳልፈናል። ቀጥሎ የሚኖረዉ ሂደትም ለሚመለከተው አካል በመድረክ ይቀርባል፤ አስተያዬት እና ውሳኔ ይሰጥበታል።
ሆኖም ውሳኔ የተሰጠበትን ጉዳይ እንደ አመራርም ይሁን እንደ አባል በአደባባይም ይሁን በጓዳ መቃወም በድርጅታዊ አሰራር ላይ ማመፅ ነው። ይህን አለማድረግ ደግሞ የእያንዳንዱ አባልም ሆነ አመራር ግዴታ ነው።
የምንመራው በመርህ እንደ መሆኑ መጠን በሞቅታም ይሁን በጩኸት አለያም በሳቦታጅ ውሳኔ አይተላለፍም፣ ውሳኔም አይታጠፍም።
የሚያስፈልገው እርማት ደግሞ በሚመለከተው አካል ይፈጸማል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
አስርስ ማረ ዳምጤ
474
18:46
12.08.2025
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
7 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
f
**biubiu@*****.com
On the service since January 2025
19.03.202513:53
5
Precise task compliance
Show more
New items
Channel statistics
Rating
27.9
Rating reviews
5.0
Сhannel Rating
42
Subscribers:
8.0K
APV
lock_outline
ER
18.1%
Posts per day:
14.0
CPM
lock_outlineSelected
0
channels for:$0.00
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий