
🔥 Get Clients in Any Niche
We’ll set up and launch your ads — free of charge
Learn more
Channel statistics
group
Subscribers:
2.1K
visibility
APV
lock_outline
monitoring
ERR
32.7
thumb_up
ER
4.72
payments
СPM:
lock_outline
update
Posts per day:
1.0
Recent Channel Posts
መልካም ንባብ 🙋♀
ቲና
ክፍል ሶስት
......... ከዃላዬ ሲነካኝ ሀሳቤ ሁሉ እሱ ላይ ስለነበር ክው ነው ያልኩት ።
ሳላስበው ቅጥን ቅብጥ ያለች ቀጭን የእሪታ ጩኸቴን ለቀኩት ና ዞርኩኝ ።
ስዞር ግን ወደዃላ የምትሸሸውን የብዙ ጊዜ ደንበኛችንን ነው ያየሁት ።
ወንድሜ ደንግጦ ወደኔ ሲቀርብ እሷ ደንግጣ ከኔ ስትሸሽ መሀል ላይ እኔ እጆቼን አፌ ላይ ይዤ ቀረዋ !!!
አይ የኔ ነገር ልጁን በጣም ከመፈለጌ የተነሳ ተከትሎኝ እዚህ ድረስ እንደመጣ አስቤ እኮ ነው ? ሆሆሆሆ !
" ምን ሆነሻል እህቴ " ብሎ ወንድሜ ጭምቅ አርጎ ሲያቅፈኝ ነው ከነበርኩበት ሰመመን የነቃሁት ።
ለምን ያን ያህል እንዳጋነንኩት በዛ ልክ መደንገጤ አልገባኝም ??
ወንድሜ ይቅርታ ደንግጬ እኮ ነው ሰኒ ይቅርታ አርጊልኝ ብዬ ፈገግ አልኩና ወደ ልብስ መሞከራው ገብቼ በደንብ ተንፍሼ አንድ አራት አምስት ጊዜ ጭንቅላቴን ከእጆቼ አጋጭቼ ያልመጣብኝን እየሳኩ ለመምሰል ሰላሳ ሁለት ጥርሴን እያሳያው ወጣሁ ።
" ምን ሆነሽ ነው ሪታ " አለኝ ወንድሜ ደንግጧል አስጨንቄው ነበር !
አንተ ቡሀላ ነግርካለሁ ጉዴን አረ በሳቅ ለመፍረስ ተዘጋጅ ምናምን ብዬ በቀልድ አሳመንኩት እሱም በቃ የሆነ ነገር አርጋ ነው ብሎ ችላ አለኝ ።
ከስተመራችንን በእንክብካቤ አስተናግደን የድንጋጤ ድባቡን አጥፍተን ሸኘናት !
እኔ ከላይ ብስቅም በውስጤ ለወንድሜ የምነግረውን ውሸት ሳስብ ሳሰላስል ነበር የቆየሁት ።
ሌላ አማራጭ የለኝማ !!
ከዛማ ልክ ቤቱ ጭር ሲል
" አንቺ ጉደኛ ደግሞ ደግሞ ምን አረግሽ ነው ለምን ክላስ ቀረሽ ? አለኝ ።
በዛች ደቂቃ ውሸት እንዴት እንደመጣልኝም አላቅም
ክላስማ ከወጣሁ ቡሀላ ዛሬ የለም አላሉ መሠለክ አልኩ እንደተናደደ ሰው አክት እያረኩ ።
" እሺ እንደዛ ምጧ እንደመጣባት ሴት እሪሪ ያልሽውስ ? " አለኝ ።
እሱማ እየመጣሁ መታጠፊያው ጋ ስደርስልክ የሆነ የሚያስፈራ እብድ ቀጥ ብሎ ወደኔ ሲመጣ ደንግጬ እዚህ ድረስ ስሮጥ መጣሁልሀ አልኩት ።
ወንድሜ ውሸት በጣም ነው የሚጣለው በጣም !!!
ለዛ እኔ ውሸት እንዳልዋሽ እየተነገረኝ አድጌ አውግዤ የኖሩኩ ልጅ እዛ ቦታ ላይ ውሸቴን ስተረተር ግን የተካንኩ ነበር የምመስለው ።
ምንም ብለው የሚያምነኝ ወንድሜ ደግሞ የምር መስሎት እየሳቀ
" ራስሽን ፈርተሽ ነው ታዲያ ? " ብሎ ቀልዶ ትንሽ ደብድቤው በዛው አለፈልኝ ።
ወደ ቤታችን ተመልሰንም የእናቴን ጣፋጭ ምግቦች አጣጥሜ ከጨረስኩ ቡሀላ መኝታ ቤቴ ገብቼ ፈጥጬ ቁጭ አልኩኝ ።
እስከዛሬ ቤት እንደገባሁ ወይ ሻውር ወስጄ በልቼ ታጥቤ አዳዲስ ልብሶችን ስፈልግ ፋሽን ሳስብ ወይ ዲኮሩን ለመማር ስሞኮር የምታይ ልጅ እንደ ጅል አፍቃሪ በልቼ ገብቼ ቲክቶክ እና ኢንስታግራም ላይ ናኦድ ብዬ ሰርች እያረኩ መፈለግ ጀመርኩኝ አይ የኔ ነገር !!!
ከዛ እነሱስ ምን ጨነቃቸው ናኦድ የሚባሉ ከአስር በላይ አካውንቶችን ደረደሩልኛ ።
ሳየው ትንሽ ተረጋጋሁ መሠለኝ ስልኬን ዘጋሁና ወደራሴ ለመመለስ ብዬ ለጥ አልኩኝ ።
በቀጣይ ቀን በጥሩ ሙድ ተነስቼ ቁርስ በላልተን ከወንድሜ ጋር ወደ ስራ ሄድን ።
ሙሉ ቀኑን ዲኮር ክላስ የምሄድበትን ሰአት ስጠባበቅ ቆይቼ ለአስር ሰአት ኮርስ ወንድሜን ሰባት ሰአት ላይ ክላስ ቶሎ መድረስ አለብኝ ብዬው ራሴን በመስታወት አይቼ ወጣሁ ።
የምማርበትና የስራ ቦታዬ ያን ያህል ሩቅ አይባሉም ሰላሳ ደቂቃ ቢፈጅ ነው በዛ ቢባል እና ሳላስበው ቶሎ ደረስኩ ።
ቶሎ መድረሴ ላይ ሳይሆን ሀሳቤ እዚህ ይሆን የት አለ እሺ ተደብቆ እያየኝ ይሆን እንዴ ?
ትላንት ስልኬን ሊጠይቀኝ ሲል ቢሆንስ ጥዬው የሄድኩት ?? ሳናድድ!! እያልኩ ብቻዬን ማውራት ጀመርኳታ !!
የጠሉት ይደርሳል ነው መሠለኝ ለኔ መቼም ብዬ የተኩራራውበትን ረስቼ እንደ ጅል አፍቃሪ ሆኜ አረፍኩታ !!
ጊቢ ውስጥ ተማሪ ባለመኖሩ እስኪሰባሰቡ ብቻዬን ሁለት ሰአት አካባቢ ቁጭ ለማለት ተገደድኩኝ !!
ያ የመጀመሪያ ቅጣቴ ሆኖ አረፈዋ !
ተማሪ መሠባሰብ ጀመረ ወደምንማርበት አዳራሽ መግባት ጀመሩ ።
ጊቢ ውስጥ ከማንም ጋ አለመግባባቴ ሳልፈልግ ኮስታራ አርጎኛል መቼም ፊቴን ዘፍዝፌ ግንባሬን ቋጥሬ ወደ ክፍሉ ገባሁኝ ።
ተማሪው ገብቶ እስኪያልቅ ውጪ ስለነበርኩ ልጁ በቃ ትላንት አጋጣሚ ነበር አይቼው የማላቀው ተማሪ ሲሆን መጠርጠር ነበረብኝ ቲሽ እያልኩኝ ነበር የገባውት ።
እንደሁሌው ቃል ሳልያገር ጥጌን ይዤ ቁጭ ብዬ ቀና ስል ናዖድን ስለዲኮር ውበት ስልጠና ከሰጠችን ሀይማኖት አጠገብ ቆሟል ???
ፀሀፊ ✍✍
376
21:48
16.04.2026
ሪታ
ክፍል ሁለት ✌️
........ እንግዲህ በአንድ አስጠሊ ቀን ሀገር ሰላም ብዬ ከወንድሜ ጋር ሱቅ ስንሰራ ቆይተን ወደ ዲኮር ክላስ ፏ ብዬ ሄድኩኝ ።
እዛ ስደርስ ገና አልተጀመረም ነበርና ከምደበር ብዬ ጥግ ደረጃው ላይ ቁጭ ብዬ በቴክስት ከወንድሜ ጋር እየተሰዳደብኩኝ ጎን ለጎን ደግሞ ስልኬ ላይ አዳዲስ የልብስ ፋሽኖች እያየሁ ነበር ።
ወንድሜ አስቂኝ ቴክስ እየላከ ስለነበር አነበብኩትና ብቻዬን እየሳኩ ቀና ስል አይን ለአይን ተገጣጠምን !!
ከማን ጋ አትሉም
ከሱ ጋ የመጀመሪያ ፍቅሬ ናኦድ ጋር ተያየን ።
በመጀመሪያው ቅፅበት በአንድ እይታ የልቤን ምት አዛባው ።
መጀመሪያ ላይ ባላየ ለማለፍ አይኔን ለመንቀል ብሞክርም ከሴኮንዶች ቡሀላ እዛው አገኘዋለሁ ።
ደሞኮ እኔ ብቻ ባየው እሺ እሱም ፍጥጥ ብሎ አየኝ ።
ተረጋጊ ሪታ ተረጋጊ ሀሳብሽን ሰብስቢ እያልኩ ለራሴ ስነግረው ነበር ።
አማርጬ መርጬ ስል የነበርኩት ልጅ በሱ ፍቅር ውድቅ አልኩላችሁ ።
ደስ የሚለው እሱ ወደኔ መጣ እንጂ ቢሄድ እንደምከተለው እርግጠኛ ነኝ ግን ወደኔ መጣ ።
አይናችን እየተያየ አጠገቤ ደረሰ ። ያመዋል እንዴ ይለኛል የሆነ ልቤ የሆነ ልቤ ደግሞ ወይኔ ሲያምር ይለኛል ?
ግን እኮ አያምርም የወንድ አቋም አለው ቀይ ነው ሪታ ደግሞ ቀይ ሰው አትወድም ታዲያ የትኛው አሽቃባጭ ልቤ አይኑን እንደተከለ ፈጣሪ ይወቀው !!!
ቀጥታ ሲመጣ ፈዝዤ ሳየው ትንሽ ፈገግ አለና
" የሆነ ቦታ አቅሻለሁ ልበል ?" አለኝ ።
ትንሽ ለመኮሳተር እየሞከርኩኝ
አይ አታቀኝም ብዬ መልሼ ወደ ስልኬ ትኩረቴን መለስኩት ።
" የምር አቅሻለሁ " አለኝ ፈጣሪዬ ሆይ የት ነው የሚያቀኝ ያመዋል እንዴ ከኔ ራቅ እባክህ እያልኩ በልቤ እየለፈለፍኩ
የት ? አልኩት ፍጥጥ ብዬ ግን ከልብስ ቤቱ አያልፍም እያልኩ
"" አላስታውስም ግን ሳስበው ሰማይ ላይ ? " አለኝ ።
ወይኔ ጉዴ ምንድነው የሚያወራው እብድ ነው እንዴ እያልኩ እያሰብኩ ማለት አልኩት መልሼ
" ማታ ማታ የምትወጪው ጨረቃ ወይም ኮከብ ነሽ አ አስታወስኩ " ብሎ እግር እግር ያለ ቀልዱን ለቀቀብኝ 😂😂
በሰአቱ እንደጀማሪ ትንሽ ተሽኮርምሜ ፈገግ ማለት እያማረኝ ነበር ግን ምንም እንደማያስቅ አስመሰልኩኝ ነገር ።
" ናዖድ እባላለሁ " ብሎ እጁን ዘረጋ ።
እሱን መንካት አልፈለኩም ግን ላገረጣውም ስላልፈለኩኝ ሰላምታውን መልሼ ሪታ ብዬ ጥዬው መሄድ ጀመርኩኝ ።
ልብ በለሊት እባብ እግሩ ላይ እንደተጠመጠመበት ሰው እግሬ መተሳሰር ጀመረ ።
አትሂጂ ቢለኝም እንደምንም ራሴን እያሳመንኩ ክላስ እንደመጣሁ ረስቼው ቀጥ ብዬ ወደ ወንድሜ ሮጥኩኝ ።
እዛ ስደርስ የወንድሜ የፍጥጫ ጥያቄ መመለስ እስኪከብደኝ ድረስ እየተርበተበትኩ ነው !!!
ደንግጫለሁ የማላቀው አዲስ ስሜት እያስተናገድኩ ነው በጣም ከባድ ስሜትና ፍራቻ !!!!
" እህቴ ምን ሆንሽ ደግሞ ክላስሽስ ?? አረ ምን ተፈጠረ " የሚሉ የተከታተሉ ጥያቄዎች አዘነበብኝ ።
እኔ ለአንዳቸውም ለመመለስ ዝግጁ አደለሁም !!!!
ዝም ብዬ አየውት ከዛ የራሴ መደናገጥና የሚታይብኝ ስሜት ደግሞ አስደነገጠኝ!!
ከወንድሜ ጋር እየተፋጠጥን እያለ ከዃላዬ እጅ ትከሻዬ ላይ እርፍ ሲል ክው ብዬ ዞርኩኝ ....
ፀሀፊ ፊደል ✍✍
709
22:05
15.04.2026
ሳንታ ተመልሷል 😂😂
መልካም ንባብ !!
ልክ እንደጨረሳችሁ የልብ ምልክቷን በመንካት ይቀጥል የሚለውን ሀሳብ አሳዩኝ !!!
ሼር እያደረጋችሁ 🙏
835
20:49
14.04.2026
✍ ፊደል ✍
እንደተለመደው በአዲስ ታሪክ ተመልሰናል ሼር በማረግ አብራችሁኝ ቆዩ !
ከየተቀነጨበ እውነተኛ ታሪክ ከየተቀነጨበ
ሪታ
ክፍል አንድ ✍
ሰላም ሪታ ነኝ ።
የምኖረው ከሙሉ ቤተሰቦቼ ጋር ነው ።
የህይወቴን ከግማሽ በላይ ያደኩት ከአያቴ ጋር ነው ።
አያቴ እንደሚባለው አቅብጣ ሳይሆን ከትምህርት በላይ ስለክብር እና ስርአትን አሳይተው ነው ያሳደጉኝ !
እንደውም ቤት ስመለስ ነው እናቴ ላይ እየቀበጥኩ ነው ያደኩትመሰ !
በትምህርት ቀልድ የለም መቼም በደንብ ነው የተማርኩት ግን ጊቢ የመግባት ፍላጎት ስላልነበረኝ ከታላቅ ወንድሜ ብሩኬ ጋር አንድ ላይ ሆነን የልብስ መሸጫ ቡቲክ ከፍተን ጎን ለጎን የዲኮት ኮርስ እየተማርኩ ነው ።
አባቴ ዳግማዊ ይባላል በስራው ቀልድ አያቅም እሱም እንደ አያቴ በክብሩም ቀልድ አያውቅም !!!
መንገድ እንዳልስት ይመክረኛል በዛው ልክ ደግሞ ለፍላጎቴ ራሴን እንዳዳምጥ እየነገረ በነፃነት ነው ያሳደጉኝ ።
ለዛም ነው አሪፍ ውጤት ይዜ ጊቢ አልገባም ስል የተቀበለኝ ።
እናቴ መስከረም ደግሞ እንደስሟ መስከረም አንድ ቀን የተወለደች ቆንጅዬ ሴት ናት !!!
እቃ ለመግዛት ምናምን ካልሆነ አባቴ ከቤት ስትወጣም ደስ አይለውም !!??
ስራ መስራት ካቆመች አስር አመት አካባቢ ይጠጋል ።
ሁለቱም ሲተዋወቁ አነስተኛ ኑሮ ነበራቸው አብረው ሰሩ አደጉ ተቀየሩ ሁሉ ነገር ሲሟላላቸው አባቴ ይሰራል እናቴን የቤት እመቤት አድርጎ እየኖርን ነው !!
ታላቅ ወንድሜ ብሩኬ ደግሞ የኦንላይን ስራ እየሰራ ጎን ለጎን እኔን እያገዘኝ ይገኛል !
ከሚባለው በላይ ኩርት ያለና ቆንጅዬ ነው በጣም !!!!
ታናሽ እህቴ ሊዲያ የቤቱ ውብ ሴት ናት!!!!
የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን እኔን የምታስንቅ ጎበዝ ተማሪና ምርጥ ሰዐሊ ናት !!
እንግዲ ቤተሰቦቼን በዚህ ልክ ካስተዋወኳችሁ ይበቃል ።
የኔ ህይወት ከአስተዳደጌ ጋር ብዙም አይሄድም ።
ሳላስበው በጣም አስቸጋሪና አሰቃቂ ህይወት ውስጥ ራሴን አገኘውት , ጥልቅ ሀዘን , በሚወዱት መፈተን , እስር ቤት ለቅሶ ከህይወት ፈተናዎቼ ጥቂቶቹ ናቸው ።
ገና ወጣትነትን እየጀመርኩ ባለሁበት ነው መፈተን የጀመርኩት ።
ከወንድሜ ጋር በምንሰራው ስራ በጣም ትርፋማ ሆነናል የሴት የወንድ የህፃን የአዋቂ ሁሉን አዘል ስለሆነ እና አሪፍ ቦታ ስለነበር አሪፍ እየሰራን ነው !!
ሱቃችን የማይመጣ የለም እንግዲህ ብዙ አይነት ሰው ይመጣል ።
እኔና ወንድሜ የምንለያየው በሁለት አመት ከአምስት ወር ነው ።
እሱ አሪፍ ቁመት የተላበሰ ቆንጆ እና ረዘም ያለ ልጅ ነው ።
እኔ መካከለኛ አቋም ላይ የምገኝ አጠር ያልኩ ልጅ ።
አብዛኞቹ ከምለው ሁሉም ማለት በሚቻልበት ሁኔታ ባልና ሚስት ወይ ፍቅረኞች ሆነን አንድ ላይ የምንሰራ ነው የሚመስላቸው ።
ከሚመጡ ደንበኞች ወጣት ሴቶች 80per የሚሆኑት ቀልባቸውን ጥለው ተመኝተውት ነው የሚሄዱት !!
ችግሩ ግን እኔን ያዩኝና ለመጠየቅ አይደፍሩም ዝም ብለው ተመኝተው ይሄዳሉ ።
አንዳንዶችም በየሳምንቱ ሱቅ እየመጡ አይተውት ጠይቀው ይሄዳሉ እሱ ከሆነ የሚሸጠው ይገዛሉ !!😂
ለዛም ነው " ወንድሜ ቢዝነሴ ነው " የምለው !!!
እሱን የሚፈልጉትን ሴቶች አይቼ እንዴት ነው ሰውን በእይታ ብቻ ሚፈቀረው ቆይ ያማቸዋል እንዴ እያልኩ እፈርድ ነበር ??
" አትፍረድ " የሚለውን ቃል ረስቼ !!!!
የሚወዱት ሴቶች በርካታ የፍቅር መግለጫ ወረቀቶች ሲሰጡት ያማቸዋል እንዴ ሲያስጠሉ እል ነበር ??"
አይደርስ መስሎኝ !!!
ከዛው ከኛ ሱቅ የሚያምረውን እያሉ አስመርጠውት ገዝተው በቀጣዩ ቀን ስጦታ ሲሰጡት ይገርመኛል እስቃለሁ !!??
ያማቸዋል እንዴ ለክብራቸው አይጨነቁም ሴት አይደሉ ምን አይነት ፍቅር ነው ?? እያልኩ እናደድ ነበር?
ሳላቀው !!!!!!
ወንድሜም
" አትፍረጂ ተይ አንቺ ምን አይነት ሰው እንደምታፈቅሪ አታቂም " ሲለኝ
..
አረ አታቀኝም እኔን ማለት ነው መርጬ አማርጬ እንደ አንተ ቆንጆ እንደ አባቴ ኮራ ያለ ሰው ነው የማፈቅረው ፍቅር እውር ነው ብለህ እንዳትጃጃል ብቻ !!!
እያልኩ አፌዝ ነበር ???
ከዛ ግን የመጀመሪያ ፈተናዬን በአንድ የተረገመች ቀን ሀ ብዬ ጀመርኩት ??..........
ፀሀፊ ፊደል ✍
852
20:48
14.04.2026
የነገው ማንነትህ ዛሬ ይወሰናል🙋♀
በወጣትነት ዘመንህ ላይ ሆነህ የምትሰራቸው ትናንሽ ነገሮች፣ ነገ የምትሆነውን ትልቅ ሰው ይቀርፁታል። ብዙ ጊዜ ወጣትነትን እንደ መዝናኛና ጊዜ ማሳለፊያ ብቻ እናየዋለን፤ ነገር ግን ወጣትነት ለዘላለም የሚኖር የህይወት መሰረት የሚጣልበት ወቅት ነው።
ልብ ልትላቸው የሚገቡ ነጥቦች፦
ጊዜን አትናቀው፦
ዛሬ የምታባክናት እያንዳንዱ ደቂቃ ነገ ዋጋ ያስከፍልሃል። ጊዜህን ለንባብ፣ ለአዳዲስ ክህሎቶችና ለራስህ እድገት ተጠቀምበት።
ጓደኞችህን ምረጥ፦
"ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሃለሁ" እንደሚባለው፣ ካንተ የተሻለ ራዕይና ግብ ካላቸው ሰዎች ጋር ተቀረብ።
ውድቀትን አትፍራ፦
በወጣትነትህ መሳሳትህና መውደቅህ ጥንካሬ እንጂ መጨረሻ አይደለም። ከስህተትህ ተምረህ ለመነሳት ዝግጁ ሁን።
"ትልቁ ስኬት ዛሬ በጀመርከው ጥቃቅን ጥረት ውስጥ ተደብቋል። ነገህን ለማሳመር ዛሬ ለራስህ ታማኝ ሁን!"🙌🙌ፊደል
947
19:13
13.04.2026
ሰላም ቤተሰብ እንዴት ናችሁ 🙌
ነገ በአዲስ ታሪክ እንመለሳለን እስከዛ ሼር እያረጋችሁ ጠብቁኝ 🏆🏆
891
19:10
13.04.2026
imageImage preview is unavailable
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ !
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ዓልፋና ኦሜጋ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ሊይዘው አልቻለምና የተገነዘበትን ልብስ ትቶ ልብሰ መንግስቱን ለብሶ ተነሳ፤ በተወለደ ጊዜ የእናቱን መኃተመ-ድንግልና እንዳልለወጠ ሁሉ፥ በትንሳኤውም መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በብርሃን መላእክት ታጅቦ እነሆ በክብር ተነሳ።
ዛሬም እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ እኛ ህዝበ ክርስቲያኖችም “ትንሳኤከ ለእለ አመነ ብርሃነ ከፈኑ ዲቤነ” (ትንሳኤህን ለምናምንህ ለእኛ ብርሃንን ላክልን ወደ እኛ) እያልን ስለተገለጸልን ምስጢረ ትንሳኤ እንዘምር።
በመኾኑም የጌታ ትንሣኤ ለእኛ ለክርስቲያኖች የድል፣ የሰላም፣ የደስታ፣ የሕይወት፣ የማሸነፍ በዓል ነውና ይኽ ሰላምታ ይድረሳችሁ ፤
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም ! !
የተወደዳችሁ የኪነጥበብ ቤተሰቦች ፥ እንኳን ለ2017 የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዐለ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !!
መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንልን ! ! !
ትንሳኤ በዓል 2018 ዓ.ም 💚💛❤️
1213
04:03
12.04.2026
imageImage preview is unavailable
* ቅዱሳን መላእክት በፊቱ በፍርሃት የሚቆሙትን በጲላጦስ አደባባይ አቆሙት
* ለሰማዕታት የድል አክሊል ለሚያቀዳጃቸው ጌታ የእሾህ አክሊል አደረጉልት
* ለኪሩቤል የክብር ልብስ ለሚያለብስ አምላክ ቀይ ግማጃ አለበሱት
* በሰማያት ካህናት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ የሚመሰገን ጌታ በምድር ካህናት ስቀለው ስቀለው ተባለ
* ሰማይ ዙፋኑ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆነ ጌታ በመስቀል ላይ ዋለ
* አለምን የጨበጠበት እጆቹ ተቸነከሩ
አዳምን በገነት ለመፈለግ የተመላለሰበት እግሩ ተቸነከረ
* ህይወት እፍፍ ብሎ የሰጠበት አፉ መራራ ሀሞትና ከርቤ ተጎነጨ
* የብርሃን ፊቱ በጥፊ ተመታ እርኩስ ምራቅም ተተፋበት።
ለመላው የቻናላችን የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዚህች የነፃነት ቀን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን እንዲሁም ለእየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በአል በሰላም አደረሳችሁ እንላለን።🙏
1371
16:29
10.04.2026
"የዛሬው ማንነትህ የነገው መሰረትህ ነው
"
ወጣትነት ልክ እንደ እርሻ ነው። ዛሬ የምትዘራው ማንኛውም ዘር (ልምድ፣ እውቀት፣ ጓደኝነት እና ስነ-ምግባር) ነገ በህይወትህ የምታጭደው ፍሬ ነው።
ጊዜህን አትናቀው፦ ዓለም ላይ ማንም ሰው በገንዘብ ሊገዛው የማይችለው ትልቁ ሀብት "ጊዜ" ነው። ለምታጠፋው እያንዳንዱ ደቂቃ ነገ ዋጋ መክፈልህ አይቀርም።
ለራስህ ታማኝ ሁን፦ ሰው እንዲወድህ ብለህ ማንነትህን አትቀይር። የሌላ ሰው "ኮፒ" ከመሆን፣ የአንተ ምርጥ "ኦሪጅናል" ስሪት መሆን ይበልጣል።
መውደቅን አትፍራ፦ ወጣትነት ስህተት የመስሪያና የመማሪያ እድሜ ነው። ትልቁ ውድቀት መውደቅ ሳይሆን ወድቆ መቅረት ነው። ከእያንዳንዱ ስህተትህ ትምህርት ውሰድና ጠንክረህ ተነሳ።
ውስጣዊ ሰላምህን ጠብቅ፦ ስኬት ማለት ዝና ወይም ገንዘብ ብቻ አይደለም፤ ስኬት ማለት በምታደርገው ነገር ደስተኛ መሆንና ማታ ስትተኛ ህሊናህ ሲያርፍ ነው።
አስታውስ፦ ዓለም የምትለወጠው በምኞት ሳይሆን በቁርጠኝነት ነው። ዛሬ የምታደርጋት ትንሿ መልካም ነገር፣ ነገ ትልቅ ታሪክ ትሆናለች።
1393
21:28
08.04.2026
close
2.1K
Subscribers*
+2
yesterday
+4
in the last week
+195
in the last month
lock
Views per post*
lock
in the first 24 hours
32.7%
ERR*
32.66
ERR over 24 hours
38.56
ERR over 48 hours
43.25
ERR over 72 hours
4.72%
ER*
0.0
Average reach (over 24hr)
0
Average number of ad placements per month
0
over 24 hours
0
over 48 hours
0
over 72 hours
0%
Emoji Reaction Rate of promotional posts over 7 days
*Changes within 30 days
324
Total number of posts*
1
Completed orders on Telega.io
--
Repeat orders on Telega.io
0 years и 9 months
Channel age
30%
men
70%
women
Reviews channel
5.0
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
c
**ffeennew@******.io
13.08.202518:18
Order format: 1/24
Segment: Education
Landing page: Telegram
5
Everything is fine. Thank you!
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
ፊደል✍✍ is a Telegram channel in the category «История», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 2.1K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 6.1, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 18.0 ₽, and with 1 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
keyboard_double_arrow_left
shopping_cart
Channels:
0
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Total:
$0.00
Add to Cart
Clear the cart
Are you sure you want to clear the cart?
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Clear my cart
Cancel
Комментарий