

- Main
- Catalog
- Health & Medicine
- Advertising on the Telegram channel «Ethio Psychiatry»
Advertising on the Telegram channel «Ethio Psychiatry»
No Health Without Mental Health!
Channel statistics
Full statisticschevron_rightብዙ ሰዎች ከሌሎች ፊት ሲሆኑ መጠነኛ መረበሽ ወይም ተፈጥሯዊ ፍርሃት ይሰማቸዋል—ይህ የተለመደ የሰውነት ምላሽ ነው። ነገር ግን፣ ከላይ እንደተገለጸው ዓይነት ስሜት የማህበራዊ ፍርሃት (Social Anxiety Disorder) ሊሆንብን ይችላል።
📌
ማህበራዊ ፍርሃት (Social Anxiety Disorder) ማለት በሰዎች ፊት በምሆንበት ወይም ልንገመገምም በምንችልበት ማህበራዊ ሁኔታዎች ላይ ከመጠን ያለፈ እና ዘላቂነት ያለው ፍርሃት የመሰማት የአእምሮ ጤና ሁኔታ ሲሆን ፍርሃቱ በዋናነት የሚመነጨውም በአሉታዊ መልኩ የመገምገም ወይም የመዋረድ ስጋት ስለሚያድርብን ነው።
ማህበራዊ ፍርሃት ከተለመደው በሰዎች ፊት ጊዜያዊ የመረበሽ ስሜት የሚለየው በየዕለት ኑሮሯችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማድረጉ ነው።
🎯 በDSM-5 መሠረት ማህበራዊ ፍርሃት የሚከተሉት ዋና ዋና መገለጫዎች አሉት።
1. በሌሎች ሰዎች ልገመገም በምችልበት ማህበራዊ ሁኔታ ውስጥ ስሆን ከፍተኛ የተለየ ፍርሃት እና የመረበሽ ስሜት ይሰማኛል።
ምሳሌ: - በገበያ መደብር ውስጥ ወይም ከጓደኞቼ ጋር በምመገብበት ጊዜ እንኳን ሰው ያየኛል ብዬ እፈራለሁ።
2. ፍርሃቱ የሚመጣው ሰዎች ስለ እኔ በአሉታዊ መልኩ ይፈርዳሉ፣ ይተቹኛል፣ ወይም ይስቁብኛል ከሚል ስጋት ነው።
ምሳሌ: "ድምፄ ይንቀጠቀጣል፣ ስለዚህ ሁሉም ሰው ደንባራ እንደሆንኩ በቀላሉ ያውቃል ብሎ ማሰብ።"
3. የሚያስፈሩኝን ማህበራዊ ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ እሞክራለሁ ወይም በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ሆኜ እታገሳለሁ።
ምሳሌ: -ስልክ ከመደወል እሸሻለሁ፣ ስብሰባ ላይ አስተያየት ከመስጠት እቆጠባለሁ፣ ወይም አዲስ ሰው የማውቅበትን ግብዣ እተዋለሁ።
4. የሚሰማኝ ፍርሃት ከሁኔታው እውነተኛ አደጋ ጋር ሲነፃፀር በጣም ከመጠን ያለፈ ነው።
ምሳሌ:- ስልክ ለመደወል መፍራት ያን ያህል ከባድ አደጋ የማያስከትል ቢሆንም፣ እኔ ግን የልብ ምት መጨመር እና የእጅ መንቀጥቀጥ ይሰማኛል።
5. ፍርሃቴ ቢያንስ ለስድስት ወራት ወይም ከዚያ በላይ የቆየ ሲሆን በስራዬ፣ በትምህርቴ ወይም በግል ግንኙነቶቼ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጥሮብኛል።
ምሳሌ:- ፍርሃት ስላለብኝ ጥሩ የሥራ ዕድል አምልጦኛል ወይም የቅርብ ጓደኛ የለኝም።
✅ የመጨረሻ መልዕክት
ይህ የማህበራዊ ፍርሃት በብዙ ሰዎች ላይ የሚታይ ቢሆንም፣ ሊታከም የሚችል የጤና ችግር ነው። ታዲያ እርስዎም ሆኑ ሌሎች የሚያውቋቸው ሰዎች ከላይ የተገለጹትን ምልክቶች ለረጅም ጊዜ እያስተናገዱ ከሆነ፣ የሥነ-ልቦና ባለሙያ (Psychologist) ወይም የሥነ-አእምሮ ሐኪም (Psychiatrist) ማማከር ትልቅ እፎይታ ያስገኛል።
እርዳታ መፈለግ ጥንካሬ እንጂ ድክመት አይደለም!
Via: EthioPsychiatry
We feel your invisible pains!!
Begin your Healing and Recovery journey with Ethio Psychiatry!
✅For any Inquiries & Bookings please reach out:
+251949114685 +251942863930 +251964192737 +251925801544 to book your session
Telegram:@Ethiopsychiatrysupport
📧 Email: [email protected]Reviews channel
4 total reviews
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «Ethio Psychiatry» is a Telegram channel in the category «Здоровье и медицина», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 5.7K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 29.4, with 4 reviews and an average score of 4.8.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 1.2 ₽, and with 17 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий