
- Main
- Catalog
- Books, Audiobooks & Podcasts
- Advertising on the Telegram channel «Pawli Geez school»
Advertising on the Telegram channel «Pawli Geez school»
ቅኔ ትምህርቱን የሚያግዙ መሠረተ ቅኔ ትምህርቶች የሚለቀቅበት ቻናል ኘው
Channel statistics
"በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮህ ናስ ወይም እንደሚንሸዋሸው ጸናጽል ሆኜአለሁ።"የሊቃውንት ምልከታ፦ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በ፩ኛ ቆሮንቶስ ድርሳኑ (Homily 32 on 1 Corinthians) እንደገለጸው፤ ሐዋርያው የልሳንን ስጦታ መጀመሪያ እጅግ ከፍ አደረገው—"የመላእክት ልሳን" በማለት። ነገር ግን ያለ ፍቅር ከሆነ ይህ ስጦታ "እንደሚጮህ ናስ" (sounding brass) መሆኑን ተናገረ። ናስ ድምፅ ያወጣል እንጂ ነፍስ የለውም፤ ፍቅር የሌለው ሰውም እንዲሁ ድምፅ ቢያሰማም "በከንቱና ያለ ዓላማ" እንደሚጮህ መሣሪያ ይቆጠራል። 👉 እመቤታችን ከመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ጋር ስትነጋገር ፣ ንግግሯ ዋጋ ያገኘው በትሕትናና በፍቅር ተሞልታ "እንደ ቃልህ ይሁንልኝ" በማለቷ ነው። ታላቅ ስጦታ ሳይሆን፣ ለጌታ ያለን ታላቅ ፍቅር ነው ዋጋ የሚያሰጠን። ፪. ምሥጢርን ሁሉ ባውቅ... (ቍ. ፪)
"ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራራዎችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።"💬 ተራራን የሚያፈልስ እምነትና ምሥጢርን የመግለጥ ጸጋ እጅግ ታላላቅ ስጦታዎች ናቸው። ነገር ግን ሐዋርያው እነዚህ ሁሉ ቢኖሩህና ፍቅር ቢጎድልህ "ምንም አይደለህም" (I am nothing) በማለት የፍቅርን ልዕልና ያሳያል። ፫. መሥዋዕትነት ያለ ፍቅር (ቍ. ፫)
"ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለቃጠሎ አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።"👨⚖️ * ቅዱስ አውግስጢኖስ (Letter to Donatus)፦ ሥጋን ለቃጠሎ መስጠት ራስን የመግደል ፈቃድ ሳይሆን፣ ክፉ ነገርን ላለማድረግ የሚከፈል ጽኑ መሥዋዕትነት መሆኑን ይገልጻል። 👨⚖️ ተርቱሊያን (Against Praxeas)፦ በትዕቢትና በመለያየት መንፈስ ውስጥ ሆነው "ለጥቂት ጊዜ መታሰርን" እንደ ትልቅ መመኪያ የሚጠቀሙ ሰዎች፣ "ሥጋቸውን ለቃጠሎ ቢሰጡ እንኳ" የእግዚአብሔር ፍቅር ስለሌላቸው ምንም እንደማይጠቅማቸው ያብራራል። 🤲 መስጠትና መሥዋዕት መሆን የሚከብረው ከውስጣዊ ፍቅር ሲመነጭ ነው። ፍቅር የሌለው ስጦታ "ለሰው መታያ" (Show) ብቻ ስለሚሆን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ የለውም። @EOTCwengel ይቀላቀሉ 🕊️ ▬▬ ♱ ▬▬🕊️
የሮሜ መልዕክት ማብራሪያዎች ማውጫመግቢያ ንካው ❤️ ሮሜ ምዕራፍ 1 እዚህ ጋር ነኝ ሮሜ ምዕራፍ 2 እዚህ ጋር ነኝ ሮሜ ምዕራፍ 3 ንካው ሮሜ ምዕራፍ 4 ንካው ሮሜ ምዕራፍ 5 ንካው ሮሜ ምዕራፍ 6 ንካው ሮሜ ምዕራፍ 7 ንካው ሮሜ ምዕራፍ 8 ንካው ሮሜ ምዕራፍ 9 ንካው ሮሜ ምዕራፍ 10 ንካው ሮሜ ምዕራፍ 11 ንካው ሮሜ ምዕራፍ 12 ንካው ሮሜ ምዕራፍ 13 ንካው ሮሜ ምዕራፍ 14 ንካው ሮሜ ምዕራፍ 15 ንካው ሮሜ ምዕራፍ 16 ንካው የምዕራፎቹ ማጠቃለያ ንካው Join here
🏛️ ፩ኛ ቆሮንቶስ (1st Corinthians)[የመጀመሪያው መልእክት መግቢያ] [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፩ (1)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፪ (2)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፫ (3)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፬ (4)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፭ (5)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፮ (6)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፯ (7)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፰ (8)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፱ (9)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፲ (10)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፲፩ (11)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፲፪ (12)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፲ ፫ (13)] —click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፲፬ (14)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፲፭ (15)] — click [፩ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ፲፮ (16)] — click የሮሜ መልዕክት ማብራሪያዎች ማውጫ
የቀተለን ዝርዝር በክፍል 2 እናያለን1 ቀደሰ=አመሰገነ 2 ይቄድስ=ያመሰግናል 3 ይቀድስ=ያመሰግን ዘንድ 4 ይቀድስ=ያመስግን 5 ቀድሶ/ሶት=ማመስገን 6 ቀዳሲ/ቅዱስ=የሚያመሰግን ወንድ 7 ቀዳስያን/ቅዱሳን=የሚያመሰግኑ ወንዶች 8 ቀዳሲት/ቅድስት=የምታመሰግን ሴት 9 ቀዳስያት/ቅዱሳት=የሚያመሰግኑ ሴቶች 10 መቀድስ/መስተቀድስ/መስተቃድስ=የሚያመሰግን 11 መቀድሳን/መስተቀድሳን/መስተቃድሳን=የሚያመሰግኑ 12 መቀድስት/መስተቀድስት/መስተቃድስት=የምታመሰግን 13 መቀድሳት/መስተቀድሳት/መስተቃድሳት=የሚያመሰግኑ 14 ቀደስት=የሚያመሰግኑ 15 መቅደስ=ማመስገኛ መመሰጋገኛ መመስገኛ ማመሰጋገኛ ማስመስገኛ 16 ቅዳሴ=ምስጋና 17 ቅድስና=ቅድስና እያለ ይረባል የቀደሰ ቤት የሚባለው መካከለኛው ፊደል ጠብቆ የሚነበበው ነው።የቀደሰ ቤት ቀደሰን መስሎ ይረባል 1 ተንበለ=ለመነ 2 ይተነብል=ይለምናል 3 ይተንብል=ይለምን ዘንድ 4 ይተንብል=ይለምን 5 ተንብሎ/ተንብሎት=መለመን 6 ተንባሊ/ትንቡል=የለመነ 7 ተንባልያን/ትንቡላል=የለመኑ 8 ተንባሊት/ትንብልት=የለመነች 9 ተንባልያት/ትንቡላት=የለመኑ 10 መተንብል/መስተተንብል/መስተተናብል=የለመነ 11 መተንብላን/መስተተንብላን/መስተተናብላን=የለመኑ 12 መተንብልት/መስተተንብልት/መስተተናብልት=የለመነች 13 መተንብላት/መስተተንብላት/መስተተናብላት=የለመኑ 14 ተንበልት=የለመኑ 15 ትንባሌ=ልመና የተንበለ ቤት የሚባለው ቅድመ መድረሻውን ሳድስ አድርጎ ሌላውን ግእዝ ያደረገ ሁሉ ነው። ተንበለ ከሚለው "ን" ቅድመ መድረሻ ሳድስ እንደሆነች አስተውል። 1 ባረከ=አመሰገነ 2 ይባርክ=ያመሰግናል 3 ይባርክ=ያመሰግን ዘንድ 4 ይባርክ=ያመስግን 5 ባርኮ/ባርኮት=ማመስገን 6 ባራኪ/ቡሩክ=ያመሰገነ 7 ባራክያን/ቡሩካን=ያመሰገኑ 8 ባራኪት/ቡርክት=ያመሰገነች 9 ባራክያት/ቡሩካት=ያመሰገኑ 10 መባርክ/መስተባርክ=ያመሰገነ 11 መባርካን/መስተባርካን=ያመሰገኑ 12 መባርክት/መስተባርክት=ያመሰገነች 13 መባርካት/መስተባርካት=ያመሰግኑ 14 ባረክት=ያመሰገኑ 15 በረከት=በረከት 16 ቡራኬ=ቡራኬ የባረከ ቤት የሚባለው መነሻውን ራብእ ያደረገ ግስ ነው።ይህን የመሰለ ግስ እንደ ባረከ ይወርዳል ማለት ነው። 1 ጦመረ=ጻፈ 2 ይጦምር=ይጽፋል 3 ይጦምር=ይጽፍ ዘንድ 4 ይጦምር=ይጻፍ 5 ጦምሮ/ጦምሮት=መጻፍ 6 ጦማሪ/ጡሙር=የጻፈ 7 ጦማርያን/ጡሙራን=የጻፉ 8 ጦማሪት/ጡምርት=የጻፈች 9 ጦማርያት/ጡሙራት=የጻፉ 10 ጦመርት=የጻፉ 11 መጦምር/መስተጦምር/መስተጡዋምር=የጻፈ 12 መጦምራን/መስተጦምራን/መስተጡዋምራን=የጻፉ 13 መጦምርት/መስተጦምርት/መስተጡዋምርት=የጻፈች 14 መጦምራት/መስተጦምራት/መስተጠዋምራት=የጻፉ 15 ጦመርት=የጻፉ 16 ጦማር=ጽሑፍ/ደብዳቤ የጦመረ ቤት ጦመረን መስሎ ነው የሚረባው መነሻው ሳብእ የሆነ ግስ የጦመረ ግስ ይባላል። 1 ገብረ=ሠራ 2 ይገብር=ይሠራል 3 ይግበር=ይሠራ ዘንድ 4 ይግበር=ይስራ 5 ገቢር/ገቢሮት=መስራት 6 ገባሪ/ግቡር=የሰራ 7 ገባርያን/ግቡራን=የሰሩ 8 ገባሪት/ግብርት=የሰራች 9 ገባርያት/ግቡራት=የሰሩ 10 ገበርት=የሰሩ 11 መግብር/መስተግብር/መስተጋብር=የሰራ 12 መግብራን/መስተግብራን/መስተጋብራን=የሰሩ 13 መግብርት/መስተግብርት/መስተጋብርት/የሰራች 14 መግብራት/መስተግብራት/መስተጋብራት=የሰሩ 15 ግብር=ሥራ 16 ተግባር/ምግባር=ሥራ የገብረ ቤት የሚባል ሦስት ፊደል ሆኖ መካከሉ ሳድስ የሆነ ሲሆን የሚረባ ገብረን መስሎ ነው። ። ጥያቄ??
የሚከተሉትን ግስ አርባ1 ናፈቀ (ባረከ) 2 ሠምረ (ገብረ) 3 ደመረ (ቀደሰ)
Reviews channel
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «Pawli Geez school» is a Telegram channel in the category «Книги, Аудиокниги и Подкасты», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 4.1K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 2.2, with 0 reviews and an average score of 0.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 1.2 ₽, and with 0 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий