
Channel statistics
የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከፊታችን ማክሰኞ የካቲት 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለስምንት ቀናት ይሰጣል።
የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ሊከተሏቸው የሚገቡ የስነ-ምግባር መመሪያዎች፦
➫ ተፈታኝ ተማሪዎች በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የሞባይል ስልክ፣ ሚሞሪ ያለው የእጅ ሰዓት፣ ሳይንቲፊክ ካልኩሌተር፣ የራስ ያልሆነ መታወቂያ እንዲሁም ማንኛውም አይነት የጦር መሳሪያ ይዘው መገኘት አይችሉም፡፡
➫ ተፈታኝ ተማሪዎች ከ3ዐ ደቂቃ ቀድመው በተመደቡበት ክፍል መገኘት አለባቸው፡፡
➫ ተፈታኝ ተማሪዎች ከተመደቡበት ክፍል ውጪ መፈተን ውጤት ያሰርዛል፡፡
➫ ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና አስፈጻሚን ትዕዛዝ ማክበር ይጠበቅባቸዋል።
➫ ተፈታኞች የፋይዳ መታወቂያ መያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ራሳቸውን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
➫ በሌላ ሰው ስም፣ መለያ ቁጥር (Username) እና የይለፍ ቃል (Password) መፈተን አይቻልም፡፡
@tikvahuniversity
ለትምህርት ማህበረሰቡና ለባለድርሻ አካላት በሙሉ
በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፉ በተዘጋጁ ረቂቅ ደንብና መመሪያዎች ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤
1. በትምህርት ሚኒስቴር የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የራስ-ገዝነት የሽግግር መመሪያ https://forms.gle/KiRAQn6kjsZ6yymt6
2. የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የመንግስት ጥቅል የበጀት ድጋፍ ለመደንገግ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ https://forms.gle/YEsQJwjE3wYUypJz6
3. በትምህርት ሚኒስቴር ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራር አሰያየምን ለመደንገግ የወጣ መመሪያ
https://forms.gle/HLqZm83W2ANMWMLt5
============////==========
1. ስትራቴጂካዊ ራዕይ እና እቅድ ማጣት
ደካማ አመራር ትምህርት ቤቱን ከ5 ወይም ከ10 ዓመት በኋላ የት ማድረስ እንደሚፈልግ ግልጽ ራዕይ የለውም።
#በዘመቻ_መስራት፦ ችግሮች ሲፈጠሩ ብቻ ምላሽ መስጠት እንጂ፣ አስቀድሞ ችግሮችን የሚተነብይ እና መፍትሄ የሚያስቀምጥ እቅድ አለመኖር።
#የግብ_ማጣት፦ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ወይም የትምህርት ቤቱን ደረጃ ለማሳደግ የሚለኩ እና ግልጽ የሆኑ ግቦች (SMART Goals) አለማስቀመጥ።
2. የመምህራን አስተዳደር እና ተነሳሽነት መጓደል
አንድ ደካማ መሪ መምህራንን እንደ አጋር ሳይሆን እንደ ተራ ሰራተኛ ብቻ ያያቸዋል።
#ግልጽነት_የጎደለው_የጥቅማጥቅም_አሰጣጥ፦ ብቃት ያላቸውን መምህራን ከማበረታታት ይልቅ በዝምድና ወይም በትውውቅ ላይ የተመሰረተ አሰራር መከተል። ይህም መምህራን በስራቸው ተስፋ እንዲቆርጡ ያደርጋል።
#የሙያ_ድጋፍ_አለመስጠት፦ መምህራን ሲሳሳቱ ከመቅጣት ባለፈ፣ ክህሎታቸውን የሚያሳድጉበትን ስልጠና እና የውስጥ ለውስጥ የልምድ ልውውጥ (Peer-to-Peer learning) አለመመቻቸት።
3. የክትትልና ግምገማ (Supervision) ድክመት
የትምህርት ጥራት የሚረጋገጠው በመማር-ማስተማር ሂደት ላይ በሚደረግ ጥብቅ ክትትል ነው።
#የክፍል_ምልከታ_አለማድረግ፦ ርዕሰ መምህራን ወይም ሱፐርቫይዘሮች መምህራን እንዴት እያስተማሩ እንደሆነ በክፍል ተገኝተው አለማየታቸው።
#በመረጃ_ላይ_ያልተመሰረተ_ውሳኔ፦ የተማሪዎችን ውጤት (Data) በመተንተን የትኛው ትምህርት ላይ ክፍተት እንዳለ ለይቶ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ፣ በግምት ውሳኔዎችን ማሳለፍ።
4. የሀብት አጠቃቀምና የፋይናንስ አስተዳደር ጉድለት
ትምህርት ቤቶች ያሉዋቸውን ውስን ሀብቶች (ገንዘብ፣ ቁሳቁስና ጊዜ) በአግባቡ አለመጠቀም ትልቅ ማነቆ ነው።
#የቅደም_ተከተል_ስህተት፦ ለአስፈላጊ ጉዳዮች (ለምሳሌ ለቤተ-ሙከራ ዕቃዎች) ቅድሚያ ከመስጠት ይልቅ፣ ለአስተዳደራዊ ወጪዎች ወይም ለታይታ ስራዎች ገንዘብ ማባከን።
#ግልጽነትና_ተጠያቂነት_ማጣት፦ ለትምህርት ቤቱ የሚመደበው በጀት ወይም ከማህበረሰቡ የሚሰበሰበው ገቢ የት እንደዋለ ለወላጆችና ለመምህራን ግልጽ አለማድረግ።
5. ከማህበረሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት መላላት
ትምህርት ቤት እንደ አንድ ደሴት ተነጥሎ ሊቆም አይችልም።
#የወላጆችን_ተሳትፎ_አለመጠቀም፦ ወላጆች ገንዘብ እንዲያዋጡ ብቻ ከመፈለግ ባለፈ፣ በትምህርት ቤቱ አስተዳደርና በልጆቻቸው ውጤት ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ አለማድረግ።
#አጋርነትን_አለመፍጠር፦ ከአካባቢው ባለሀብቶች፣ ከቀድሞ ተማሪዎች (Alumni) እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ለትምህርት ቤቱ ድጋፍ አለማሰባሰብ።
6. የስነ-ምግባርና የዲሲፕሊን ቁጥጥር መላላት
የአመራር ድክመት ሲኖር በትምህርት ቤቱ ውስጥ የአሰራር መዝረክረክ ይፈጠራል።
#የደንብ_ተፈጻሚነት_ማነስ፦ በተማሪዎችም ሆነ በመምህራን ላይ የተቀመጡ ደንቦች በእኩልነትና በአግባቡ ተፈጻሚ አለመሆን።
#የሰዓት_አጠቃቀም_ችግር፦ ትምህርት በሰዓቱ አለመጀመርና መምህራን ክፍለ-ጊዜያቸውን በአግባቡ አለመጠቀማቸው።
ባጭሩ፦ የአመራር ድክመት ማለት "አቅጣጫ ጠቋሚ ኮምፓስ" እንደሌለው መርከብ ነው።
በባሕር ዳር የኒቨርሲቲ ልዩ አማራጭ መምህራን ትምህርት ስልጠና አመልካቾች በሙሉ፤
በልዩ አማራጭ መምህራን ትምህርት ስልጠና ለመሳተፍ ካመለከታችሁት ምሩቃን መካከል በአማርኛ፤ እንግሊዝኛ እና ፊዚክስ ትምህርቶች ዘርፍ የተመረጣችሁ ስልጣኞች ስማችሁን ከዚህ ጋር በተዘረዘሩት ሰንጠረዦች ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የምዝገባ ጊዜ የካቲት 2 እና 3፣ 2018 ዓ፣ም በፔዳ ካምፓስ መምህራን ትምህርት ትምህርት ቤት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
Announcement
To all applicants of Bahir Dar University Special Alternative Teacher Education Training:
We would like to inform you that, among the graduates who applied to participate in the Special Alternative Teacher Education Training in Amharic, English, and Physics, the names of the selected candidates are presented in the attached tables.
The registration period will be February 10–11, 2026, at the Teacher Education School, PEDA Campus.
@bahrdar_university
በባሕር ዳር የኒቨርሲቲ ልዩ አማራጭ መምህራን ትምህርት ስልጠና አመልካቾች በሙሉ፤
በልዩ አማራጭ መምህራን ትምህርት ስልጠና ለመሳተፍ ካመለከታችሁት ምሩቃን መካከል በአማርኛ፤ እንግሊዝኛ እና ፊዚክስ ትምህርቶች ዘርፍ የተመረጣችሁ ስልጣኞች ስማችሁን ከዚህ ጋር በተዘረዘሩት ሰንጠረዦች ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የምዝገባ ጊዜ የካቲት 2 እና 3፣ 2018 ዓ፣ም በፔዳ ካምፓስ መምህራን ትምህርት ትምህርት ቤት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
Announcement
To all applicants of Bahir Dar University Special Alternative Teacher Education Training:
We would like to inform you that, among the graduates who applied to participate in the Special Alternative Teacher Education Training in Amharic, English, and Physics, the names of the selected candidates are presented in the attached tables.
The registration period will be February 10–11, 2026, at the Teacher Education School, PEDA Campus.
@bahrdar_university
የተሰጠው መግለጫ ከስር ቀርቧል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሟላ የማክሮኢኮኖሚ ሪፎርም መደረግ ከጀመረበት ሀምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ፤ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማጎልበት የሚያስችሉ የተለያዩ የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም የውጭ ምንዛሪ ገበያን የበለጠ ለማጎልበት በማሰብ በውጭ ምንዛሪ መመሪያ ላይ የሚከተሉትን ማሻሻያዎች ማድረጉን ያሳውቃል፡፡
1. የአገልግሎት ላኪዎች ከወጪ ንግድ የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ሙሉ በሙሉ በሪቴንሽን ሂሳባቸው ያለ ምንም የጊዜ ገደብ እንዲይዙ ተፈቅዷል፡፡
2. ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ላላቸው ደንበኞቻቸው ለውጭ ሀገር ክፍያ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ጨምሮ የሚያገለግል ዓለምአቀፍ ካርድ ማዘጋጀት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡
3. ማንኛውም የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ያለው የባንክ ደንበኛ ሕጋዊ ስነዱን ሂሳብ ለከፈተበት ባንክበማቅረብ፤ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቡን በመጠቀም ለትዳር አጋሩና ለልጆቹ የትምህርት፤የህክምናና የጉዞ ወጪ ክፍያ ማድረግ ይችላል፡፡
4. ማንኛውም ለትርፍ የተቋቋመ ድርጅት የውጭ ምንዛሪ ምንጩ ከወጪ ንግድ የሚገኝን የውጭምንዛሪ ሳይጨምር በእርዳታ/ስጦታ አለያም ከሌላ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የተገኘ መሆኑ ከተረጋገጠ የተንቀሳቃሽ፣ የቁጠባና የጊዜ ገደብ የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ መክፈት ይችላል፡፡
5. ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል የውጭ ምንዛሪ የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ይጠየቁት የነበረው አነስተኛ 100 የአሜሪካ ዶላር እንዲቀር ተደርጓል፡፡
6. ድርጅቶች የመዋእለ ነዋያቸውን ሁኔታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እያስመረመሩ ከሀገር ውጭበሌላ ሀገር መዋእለ ነዋያቸውን ፈሰስ ማድረግ እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡
7. ማንኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ ወደ ሀገር ይዞት የተመለሰውን የትኛውንም ያህል መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪ ያለ ጉምሩክ ሰነድ በባንኮችና ሕጋዊ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ቢሮዎች በኩል ወደ ብር መመንዘር አለያም ወደ የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ በማስገባት ተቀማጭማድረግ ይችላል፡፡
8. ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ ሰነድ ለባኮች በማቅረብ መጠኑ ከ3,000 የአሜሪካ ዶላር ያልበለጠ የውጭምንዛሪ ከሀገር ውጭ ለሚኖሩ ዘመዶቻቸው እገዛ እንዲውል ከሀገር ወደ ውጭ ማስተላለፍ የሚችሉበት ሥርዓት ተፈቅዷል፡፡
9. ባንኮች የፎርዋርድ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ያለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ ማካሄድ እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡
10. የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስተሮች፣ ኤምባሲዎችና በሀገር ውስጥ የሚሰሩ ዓለምአቀፍ ተቋማት የተራድኦ ድርጅቶችን ጨምሮ ያለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ በባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ፡፡
11. ድርጅቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚያመጡት የውጭ ብድር (በገንዘብና በዓይነት) እና የስፕላዬርብድርን የማጽደቅ ሥራ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መስፈርቶችን በተከተለ መልኩ ሙሉ በሙሉ በባንኮች እንዲከናወን ተፈቅዷል፡፡
12. ማንኛውም በወጪ ንግድ ላይ የተሰማራ ላኪ ድርጅት ከማንኛውም የውጭ አካል የቅድመ ክፍያ ስምምነት ላይ በመድረስ እና በሁለቱ ወገኖች የተደረሰውን የስምምነት ሰነድ ለላኪው ድርጅት ደንበኛ ባንክ በማቅረብ የቅድመ ክፍያ ማከናወን ይችላል፡፡
13. በተጨማሪም የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለወደፊት የወጪ ንግድ ክፍያ እንደ ቅድመ ክፍያ የሚቆጠረው (ሀ) ስምምነቱ ገዥውን ለማመላከት ታስቦ “ቅድመ ክፍያው ለወደፊት ወጪ ወይም ገቢ ንግድ የሚውል" ወይ (ለ) ወደፊት ወደ ውጭ የሚላኩ ሸቀጦችን ከዘረዘረ ወይም የደረሰኝ ቁጥሩ ከተጠቀሰ አለያም የግብይት የውል ስምምነት ሰነድ ቁጥር በሚላከው የውጭ ምንዛሪ ደረሰኝ ላይ ከተጠቀሰ ይሆናል፡፡
14. ባንኮች ከካፒታላቸው ከ10 በመቶ ያልበለጠ ለግሉ ዘርፍ የውጭ ሀገር ብድር ዋስትና መስጠት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡
15. ባንኮች የውጭ ተቋም በሚሰጠው የማረጋገጫ ደብዳቤ እና ደንበኛው በሚያቀርበው ጥያቄ ላይበመመርኮዝ በአንድ ጉዳይ ከ20,000 የአሜሪካ ዶላር ወይም ከተመጣጣኝ የሌላ ሀገር ገንዘብ ያልበለጠ የውጭ ምንዛሪ ለህክምናና ለትምህርት ያለ ቪዛ እና የአውሮፕላን ትኬት ቅድመ ክፍያ ማከናወን ይችላሉ፡፡
16. ያለምንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ የውጭ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መሰረት አስፈላጊውን ሰነድ ለባንካቸው በማቅረብ እንዲሁም ባንኮች በመመሪያው መሰረት የቀረበው ሰነድ መሟላቱን በማረጋገጥ በትርፍ ክፍፍል መልክያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ከሀገር ማስወጣት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡
17. የውጭ ምንዛሪ ግብይት ቢሮዎችን የገንዘብ ፍሰትና ካፒታል የበለጠ ለማጎልበት በማሰብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፈቃድ አሰጣጥ ወቅት የሚይዘውን ተቀማጭ ገንዘብ፤ (አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ በሥራ ላይ ለሆኑ ቢሮዎች 30 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ቢያንስ ለስድስት ወራት በሥራ ላይ ላሉ ቢሮዎች 15 ሚሊዮን ብር) ተመላሽ ያደርጋል፡፡
18. የውጭ ምንዛሪ ግብይት ቢሮዎች በእጃቸው የሚይዙት ጥሬ የውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ቀደም ሲል ከነበረው የካፒታላቸው 10 በመቶ ወደ 25 በመቶ ተሻሽሏል፡፡ ከዚህ በላይ የሆነ ትርፍ የውጭምንዛሪ ገንዘብ ለባንኮች መሸጥ አለበት፡፡
19. ሁሉም የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች አስፈላጊውን ሰነድ በመጠየቅ ለቪዛ፣ ለጋስፖርትና ለፈቃድ እድሳት ጥሬ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ እንዲያከናውኑ ተፈቅዷል፡፡
Via National Bank of Ethiopia
ይህ ሊንክ የ12ኛ ክፍል የግል ተፈታኞች መመዝገቢያ ሊንክ ነው።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ በሁሉም የሕዝብ ትራንስፖርት አይነቶች ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።
📌ታሪፉ ተግባራዊ የሚሆነው ከነገ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ነው።
📌ማሻሻያው የሚመለከታቸው
✔️ የከተማ አውቶብስ፣
✔️ሚኒባስ፣
✔️ሚዲባስ እና
✔️ባጃጅ ናቸው።
📌 ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉትን በነፃ ስልክ መስመር 9417 መጠቆም ይቻላል ተብሏል።
ተጨማሪ ማሳሰቢያ፦
📌የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት በሁሉም መስመሮች 10 ብር መሆኑ ተገልጿል።
Reviews channel
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
ትምህርት መረጃ( academic info) is a Telegram channel in the category «Образование», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 9.9K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 17.6, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 6.0 ₽, and with 2 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий