
- Main
- Catalog
- Books, Audiobooks & Podcasts
- Yeshua Apologetics Ministry
Yeshua Apologetics Ministry
➟የሹዋ ዐቅበተ እምነት አገልግሎት አላማ ከክርስትና እምነት አንጻር ደርዛቸውን የጠበቁ ስነ መለኮታዊ ፍልስፍና፤ አመክንዮአዊና ታሪካዊ ጽሑፎችን ማቅረብ በክርስትና ላይ የሚነሱ የተቃውሞ ሀሳቦችንና የኑፋቄ ትምህርቶችን መመከት የሌላውን እምነተ መርህ ከሎጂክና ከታሪካዊ ዳራዎች አንጻር መመርመር ▼ ▲
Channel statistics
----
ይገርማል...ይደንቃል....!
ድንቅ ነው!! አምላክ ሥጋን ለብሶ ወደ ምድር መጣ የሃጥያት መከራችንንና የዲያቢሎስ የሹፈት ነጋሪት ዝም ለማስባልም ተገለጠ። ነገር ግን የእኛን መከታን ነፃ አውጪያችንን፦ በአክሊል ፋንታ የእሾህ ጉንጉን፣ በፍቅር ከማቀፍ ፋንታ ሰጠነው ጅራፍ፣ በእጆቻችን። እሱም አልበቃ ብሎ አዳኙን ራሱን ራስህን አድን አልነው፤ ሙሾ በሚመስል ቅላጼ እያላገድን አሾፍንበት፤ ከዛም ብሶ ሰቀልነውም በእንጨት በችንካር አድርገን። ይሄ ሁሉ ሆነና ጀንበርም ሳትጠልቅ፣ ፀሐይም ሳትገባ ሥራው ድንቅ ነው የሚል ድምጽ ሰማይ ምድር ሁሉ መወደስ ጀመረ። የጩኸቱ ድምድምታ ምን ይሆን? ብለን ተነሳን፤ እኛም ያኔ ጎኑን የተወጋው፣ እጆቹም ተቸነከሩ፣ ሄዷልና ሞቷል የተባለው አዳኙ ራሱ ያው መሢህ መሆኑን አወቅን። በፍርሃትም ያየነውን በመገረም ድንቅ ነው አልን። ከእላፋት ጋር አእላፋት ሆነን፥ ባሾፍንበት ከንፍራችን ከሙታን በኩር፣ የነገስታት ንጉስ፣ የጌቶች ጌታ፣ የምድር ሁሉ ባለቤት እርሱን አመሠገንን። ጨመር አድርገንም ተነስቷል በዚህ የለም መቃብሩ ባዶ ነው ተመልከቱ በዚህ የለም፤ በሚል ክብሩ ሁሉ በአርያም በምድር ይሁን ስንል ጣፋጭ መዓዛ ያለውን ዝማሬ ለታረደው በግ አቀረብን። ለአንባቢው መልዕክቴ በዚህ በዓል ላይ የጥሞና ጊዜ ያጣህ እና ረፍት የሌለህ ሆይ "እርሱ ሰላም የሚሰጥ እረፍት ነውና በልብህ ታስገባው ዘንድ አሳሰብኩህ"። አሜን።[፩][፪]
❤.....መልካም በዓል ይሁንላችሁ.....❤
[፩] ከሚባለው በላይ ከደረሰበት መከራ አንጻር ይገርማል ጥቂት ሆና ትታየን ዘንድ አንባቢው ያስተውል።
[፪] ይደንቃል ስንል ከእውነት የሆነ መደነቅ እንዲሆን ሰሚው ከንግግል ባለፈ ከልብ በኾነ ፍቅር ትል እንደሆን አሳሰብኩህ።
------
@Yeshua_Apologetics_Ministry
------
➙ @YESHUAapolo
« የክርስትና ሕይወት ቁልፍ በልባችን ውስጥ የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ፍቅር ማወቅ ነው። በአካዳሚያ ያለውን የትምህርተ መለኮት ዕውቀትን ማዳበር ለዚህ ምትክ ሊሆን አይችልም ወንጌልን መስበክም ቢሆን እንዲሁ እነዚህ ነገሮች በየራሳቸው መንገድ መልካም እና ትክክል ቢሆኑም ለላቀው መንፈሳዊ ዲሲፕሊን ካልተገዙ ግን ሌሎችን በሃይማኖታቸው እንደሚያንጹት ሁሉ እኛንም ከመንገድ ሊያስወጡን አልያም ሊያሳስቱን ይችላሉ...... » - Gerald Bray
God Is Love: A Biblical and Systematic Theology page 125
ጦርነቱ አልቋል ድላችንን እናጣጥም!😎
በህማማት ሳምንት ሦስተኛው ቀን እለተ ማክሰኞ ወደ መስቀል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ ትልቅ ትርጉም ያለው እለት ነው። አባቶች ሶስተኛው ታላቁ እለት በግሪኩ ሜጋሌ ትሪቴ/Μεγάλη Τρίτη የሚል ስያሜ ይሰጡታል። ይህ ቀን በጌታችን እና በመድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠጣር እና ስለታማ ትምህርቶችን የሰጠበት፣ ትንቢታዊ ምሳሌዎች እና ከሃይማኖት መሪዎች ጋር ትላልቅ ክርክሮችን እና ምላሾችን ባደረገበት ጊዜ ከሰዱቃውያን ፈሪሳውያን እና አልፎም ጸሐፍት ጋር ግጭት የተከሰተበትን ጊዜ የምናስብበትና ወንጌላትን የምናነብበት እለት ነው። በዚህም ቀን የክርስቶስን ጥበብ እና ስልጣን፣ ታማኝነት ጥሪውን፣ ስለ ፍርድ እና ለግብዛን ሐይማኖተኞች የሰጠውን ማስጠንቀቂያዎችን እንመለከታለን።
እለተ ማክሰኞ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌያዊ ተግሳጻዊ እና ትንቢታዊ ትምህርቶች(መርገመ በለስ)
ማቴዎስ 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ።
¹⁹ በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና፦ ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።
²⁰ ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው፦ በለሲቱ ያንጊዜውን እንዴት ደረቀች? ብለው ተደነቁ።
²¹ ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤
²² አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ አላቸው።
²³ ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና፦ በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት።
²⁴ ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ ደግሞ አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም ያችን ብትነግሩኝ እኔ ደግሞ እነዚህን በምን ሥልጣን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፤
²⁵ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይን ወይስ ከሰው? አላቸው። እነርሱም እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ፦ ከሰማይ ብንል፦ እንኪያስ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤
²⁶ ከሰው ግን ብንል፥ ዮሐንስን ሁሉም እንደ ነቢይ ያዩታልና ሕዝቡን እንፈራለን አሉ።
²⁷ ለኢየሱስም መልሰው፦ አናውቅም አሉት። እርሱም ደግሞ፦ እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም አላቸው።
ይህንን እለት መርገመ በለስ ጋር አብዝሃኛውን ጊዜ የክርስትናው ትውፊት ያገናኘዋል። ፍሬ አልባ የሆነችው የበለስ እጽ መካንነትን የሚያመላክት ትዕምርት ሆኖ እናገኘዋለን። በተለይም የአይሁዳውያን የሐይማኖታዊ መሪዎች በውጫዊ መልክ ለአምላክ ያደሩ ወይም በቅንዓት የሚኖሩ ቢመስሉም ውስጣቸው ግን መራርነት፣ ግብዝነትን እና ፍሬ ቢስ ሐይማኖትን የተጎናጸፉ ናቸው። ይህ ትዕምርት መንፈሳዊ ፍሬ የማፍራትን አስፈላጊነት እና በግብዝነት ባለው የሕይወት ጉዞ ላይ መለኮታዊ ፍርድ የሚሰጠውን ማስጠንቀቂያ የያዘ ድርብ መልእክት ሁኖ እናገኘዋለን። የበለሷ እጽ ዕጣ ፈንታ ያለክርስቶስ ያለውን የሰውን ልጆችን መንፈሳዊ ሁኔታ የሚያሳይ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ለዓለም ቤዛ ለማቅረብ ሲዘጋጅ፣ ደቀመዛሙርቱን በእምነት እና በመታዘዝ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ እንዲያፈሩ ጠርቷቸዋልና። ከወይኑ ግንድ ጋር በመጣበቅ በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ፍሬዎችን ማፍራት መልክ ብቻ ሳይሆን ኑሮም ያለው ህይወት ይጠበቅብናል። አምላካችን ይህንን ጸጋ ማስተዋል ለሁላችን ያድል። አሜን!!!
@Yeshua_Apologetics_Ministry
የጋቪንን መጽሐፍ በማነብበት ጊዜ ቡክ ማርክ ካደረኳት ውስጥ ነች....ትርጉሙ እንዲህ ብናስቀምጠውስ ምን ታስባላችሁ? የSchaff እጅ ይባረክ lol
@Yeshua_Apologetics_Ministry
ጓደኝነታችን በዝቷል...
------
ልጋብዛችኹ!
የሙስሊሞች ነቢይ ሙሐመድ ነቢይነቱን ሰዎች እንዲቀበሉለት ከተጠቀማቸው ሙግቶች መካከል አንዱ ከኖረበት ቦታና ጊዜ ርቀው የተከሰቱ ሁነቶችን በመዘገብ ይህ ከፈጣሪ ካልተገለጠ በቀር የሚቻል አይደለም የሚል አመክንዮ ማቅረብ ነው። ሙሐመድ ፈጣሪ ገልጦልኝ ዘግቤያቸዋለሁ ካላቸው ታሪኮች አንዱ በአረቡ ምድር ዙልቀርነይን (ባለ ሁለት ቀንዱ) በመባል የሚታወቀው የታላቁ እስክንድር ታሪክ ይጠቀሳል። በቁርኣን መሰረት ይህ ሰው መጀመሪያ ወደ ምዕራብ ቀጥሎም ወደ ምስራቅ አቅጣጫ በመጓዝ ፀሐይ የምትጠልቅበትንና የምትወጣበትን ቦታ ከማግኘቱ በተጨማሪ ወደ ሰሜን በመጓዝ “መናገር የማይችሉ” ሕዝቦችን አግኝቶ እነዚህን ሰዎች የእጁጅ እና መእጁጅ ከተሰኙ ወራሪዎች ለመጠበቅ ታላቅ ግድብ ሠርቷል (18:83-100)።
ይህ አፈታሪክ ሙሐመድ እንዳለው መለኮታዊ መገለጥ ሳይሆን በሰባተኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ እንደተጻፈ ከሚገመተው “የታላቁ እስክንድር ድንቅ ስራዎች” ከተሰኘው የሲሪያክ አፈታሪክ እንደተገለበጠ በእርግጠኝነት መናገር እንችላለን። የሁለቱን ዘገባዎች ጥልቅ መመሳሰል ለማስተዋል አንባቢው ከስር የተቀመጠውን የሲሪያክ አፈታሪክ በቅንፍ ከተቀመጡት የቁርዓን አያዎች ጋር እያስተያየ እንዲያነብ ይመከራል። በዚህ አፈታሪክ መሠረት ታላቁ እስክንድር የምድርን ጫፎች ለማየት ይወስንና ከጉዞው በፊት ወደ ፈጣሪ ይጸልያል። ፈጣሪውንም “ቀንዶች እንዲያበቅልለትና ምድር ላይ ስልጣን እንዲሰጠው” ይለምናል (18:84)። በመርከብ ጉዞ ላይ ሳለም አንድ መርዛማ ባሕርን ለመሻገር የፈራው እስክንድር ይህንን መንገድ በመተው “ፀሐይ የምትጠልቅበት ብሩህ ውኅ” የሚታይበትን አቅጣጫ ይከተላል (18:86)፤ ከዚህ ተነስቶም ፀሐይን በመከተል “ፀሐይ የምትወጣበትን” ምስራቃዊ ጫፍ ያገኛል (18:90)። በአፈታሪኩ መሠረት ፀሐይ በምትወጣበት ሰዓት በአካባቢው የሚኖሩት ሰዎች በሃሩሩ እጅግ ከመቃጠላቸው ብዛት ዋሻ ውስጥ ወይም ውኅ ውስጥ ይደበቁ ነበር (18:90)። በመቀጠልም እስክንድር ወደ ሰሜን አቅጣጫ ይጓዝና የእጁጅና ማእጁጅ በተባሉ ነገሥታት የሚመሩ ክፉ ወራሪዎች ያስቸገሯቸውን ሕዝቦች ያገኛል። ታላቁ እስክንድር የሰዎቹን ችግር ሲገነዘብ ከእነርሱ ጋር በመተባበር “ነሃስና ብረት በመጠቀም” ታላቅ ግድብ ይሰራላቸዋል (18:94-96)። በስተመጨረሻም ይህ ግድብ የዓለም ፍጻሜ ሲደርስ እንደሚፈርስና በዚያ ጊዜም ህዝቦቹ “ከፊሉ በከፊሉ እንደሚቀላቀሉ” (Fall upon each other) ትንቢት ይናገራል (18:98)። [1]
ይህ ዘገባ ከቁርኣን ታሪክ ጋር የሚመሳሰል ብቻ ሳይሆን በቃላትና ሐረጋት ደረጃ እንኳ አንድ ዓይነት ነው። በሁለቱም ታሪኮች መሠረት እስክንድር ቀንድ ያለውና ምድር ላይ ሥልጣን የተሰጠው ተደርጎ ቀርቧል፤ ፀሐይ የምትወጣበትንና የምትጠልቅበትን የምድር ጫፍም ተመልክቷል። ከዚህ ባለፈም የእጁጅና ማእጁጅ የተባሉ ወራሪዎችን ለመከላከል ከነሃስና ብረት የተሠራ ግድብ አኑሮ ግድቡ በዓለም ፍጻሜ እንደሚፈርስ ትንቢት ተናግሯል። ይህንን መመሳሰል ያስተዋሉት የሥነ-ሃይማኖት ታሪክ አጥኚው ጋብሬል ሬይኖልድስ “ቁርኣን ውስጥ የሚገኘው ሁሉም የታሪኩ ክፍል ማለት ይቻላል እጅግ በሚደንቅ ሁኔታ የሲሪያክ አፈታሪኩ ውስጥ በበለጠ ግልጽና ሰፋ ባለ መልኩ ይገኛል” ይላሉ።[2]
በእርግጥም ይህ አስገራሚ መመሳሰል ተራ አጋጣሚ ሊሆን እንደማይችል ግልጽ በመሆኑ ሦስት አማራጭ ሐሳቦች ይቀሩናል። ወይ ይህ የሲሪያክ አፈታሪክ ከቁራኣን የተቀዳ ነው፤ አልያም ሁለቱም አንድ ምንጭ አላቸው ወይም የቁርኣን ደራሲ በቀጥታ ከዚህ አፈታሪክ ኮርጇል።
በእጃችን የሚገኘው ታሪካዊ ማስረጃ የመጀመሪያዎቹን ሁለት አማራጮች አይደግፍም። እንደ ሬኒንክ ያሉ በዘርፉ ሰፊ ጥናት ያካሄዱ ምሁራን እንደሚገልጹት ይህ አፈታሪክ የተጻፈው ሮማውያን ከፋርሶች ጋር ያደረጉት ጦርነት ማብቂያ (628-630AD) አካባቢ ነው።[3] የአፈታሪኩ ዋና አላማ የጦርነቱ ድል የሮማውያን ክርስቲያኖች እንደሚሆንና ይህም በታላቁ እስክንድር ሳይቀር ቀድሞ የተተነበየ እንደሆነ ማስረዳት ነው። ጋብሬል ሬይኖልድስ እንዲያውም የእስክንድር ወደ ሦስቱ አቅጣጫዎች (ጉዞው የመስቀል ቅርጽ እንዳለው ልብ ይሏል) መጓዝ የታሪኩ ጸሐፊ ሊያስተላልፍ የፈለገውን “የመጨረሻ የክርስቲያኖች ድል” ያመለክታል ይላሉ።[4]
ታዲያ እስልምናም ሆነ ቁርኣን ገና በደንብ ባልታወቁበት ሰዓት የሶርያ ክርስቲያኖች ይህንን ታሪክ ከቁርኣን ይገለብጣሉ ብሎ ማሰብ የሚመስል አይደለም። የአፈታሪኩ ደራሲ ቁርኣንን ለማንበብ/ለመስማት ያለው ዕድል አናሳ መሆኑንና ታሪኩን ለመገልበጥ ምንም ዓላማ ሊኖረው እንደማይችል ስናገናዝብ ድርሰቱ ከቁርኣን የተኮረጀ አለመሆኑ ግልጽ እየሆነ ይመጣል። ይህ ብቻ ሳይሆን ጋብሬል ሬይኖልድስ እንደሚሉት የሲሪያኩ አፈታሪክ ከቁርኣን ገልብጦ ቢሆን ኖሮ ከአረብኛ እንደተተረጎመ የሚጠቁሙ ቃላትና ሐረጋት ይኖሩት ነበር።[5] ይህ አፈታሪክ በሲሪያክ ክርስቲያኖች የተፈበረከበት ግልጽ የፖለቲካ አላማ መኖሩ የአፈታሪኩ ጸሐፊ ከሌላ መጽሐፍ ገልብጦ እንዳልወሰደው የሚያስረግጥ ሌላ ማሳያ ነው።
ወደ ሁለተኛው አማራጭ ስንመጣ ሁለቱ ዘገባዎች ከአንድ የቀደመ ምንጭ እንደተቀዱ ማሰብ ከባድ ነው። የሲሪያኩ አፈታሪክ የተፈበረከው በዘመኑ የነበረውን ጦርነት ክርስቲያኖች እንደሚያሸንፉ ለማመልከት በመሆኑ ታሪኩ ከዚያ በፊት ባሉ ምንጮች መዘገቡ ስሜት አይሰጥም። ሬይኒንክ እንደሚሉት “የሲሪያኩ አፈታሪክ የተፈበረከው ለዚህ ዓላማ ብቻ ከሆነ በቁርኣንና በአፈታሪኩ መካከል ያለው መመሳሰል ሁለቱም በቀደመ ምንጭ ላይ ተመሥርተው በመጻፋቸው ምክንያት የመጣ ሊሆን አይችልም።”[6]
በመሆኑም የቀረው ብቸኛ አማራጭ እንደ ቫን ብሌደል እና ፒተር ቢቴንሆልዝ ያሉ ምሁራን እንደሚሉት የቁርኣን ደራሲ ታሪኩን በእርግጥም ከዚህ አፈታሪክ በመገልበጥ እንደወሰደው መደምደም ነው።[7][8] ምንም እንኳን አንዳንድ ምሁራን ከአፈታሪኩ የድርሰት ጊዜ በመነሳት ታሪኩ መካ ደርሶ የቁርኣን ደራሲ ሊሰማው ይችላል የሚለውን ሐሳብ ቢጠራጠሩትም ታሪኩ ግን ቁርኣን በተደረሰበት ሰዓት የአረቡ ምድር ውስጥ በደንብ ሊታወቅ የማይችልበት ምክንያት አይኖርም። አረቦች ከቀድሞ ጀምሮ በሮማውያንና ፋርሶች ጦርነት በወታደርነት መሳተፋቸው የታሪኩን ወደ አረቡ ሕዝብ የመስፋፋት ዕድል ይጨምረዋል።
“ከዙልቀርነይንም ይጠይቁሃል” የሚለው የቁርኣን ንግግርም በሙሐመድ ዙሪያ በነበሩ አረቦች ዘንድ የዙልቀርነይን ታሪክ ይታወቅ እንደነበር ያመለክታል። በተለያዩ ተፍሲሮች መሰሠረት ይህ አያህ የወረደው አይሁዶች ሙሐመድን “የአለም ጫፍ ድረስ ስለተጓዘው ሰው” ጠይቀውት ስለነበረ መነገሩ ታሪኩ በእርግጥም በአረቡ ምድር ይታወቅ እንደነበር የሚያሳይ ሌላ ማስረጃ ነው።[9] ለዚህም ነው ቫን ብሌደል “አፈታሪኩ በስፋት ይታወቅ እንደነበር መጠራጠር ይከብዳል” የሚሉት።[10]
ጽሑፋችንን ስናጠቃልል ይህ አፈታሪክ በሶሪያ ክርስቲያኖች የተፈበረከበት ጊዜያዊና ፖለቲካዊ አላማ ቢኖረውም የቁርኣን ደራሲ ግን ይህንን አላማ ባለመገንዘቡ ምክንያት ትርክቱን ቀጥታ ከዚሁ ምንጭ በመገልበጥ ከእስላማዊ ዕይታ አንጻር ትርጉም የለሽ የሆኑ ዘገባዎችን ሊዘግብ ችሏል። የመጽሐፉ ሰዎች (አይሁዶች) ሙሐመድን ለመፈተን ስለ ታላቁ እስክንድር ቢጠይቁትም ሙሐመድ ግን አዲስ ታሪክ ከመናገር ይልቅ በዙሪያው ባሉ አረቦች ቀድሞም ይታወቅ የነበረውን አፈታሪክ በማስተጋባት ሐሰተኛ ነቢይነቱን አስመስክሯል።
Reviews channel
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Yeshua Apologetics Ministry is a Telegram channel in the category «Книги, Аудиокниги и Подкасты», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 4.1K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 12.3, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 3.6 ₽, and with 2 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий