🌸 May Sale Weeks on Telega.io
Up to 70% off + 3.5% extra discount with promo code 4C8C39F0!
Go to Catalog
7.5

Advertising on the Telegram channel «የገጣሚያን ማኅበር»
5.0
Motivation & Self-Development
Language:
Amharic
0
0
እዚህ ማኅበር ውስጥ የሚካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች፦ 👉መንፈሳዊ ግጥም ፦ስለ ሀገር ፦ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ፦ስለ ወንጌል ፦ስለቤተክርስቲያን👉መነባነብ 👉ግጥማዊ ትረካ ይቀላቀሉን
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
Advertising publication cost
local_activity
$3.60$1.80local_mall
50.0%
Remaining at this price:1
Recent Channel Posts
Rediet Aseffa በ Adhanom Mitiku መፅሐፍ ምረቃ ላይ ያነበበውን ውብ ግጥም አንብቡትማ።🥰
ከ'ሳተ ገሞራ
እንደማር ወለላ
በጣት
ዝቆ ማውጣት
አውጥቶ ጣት መጥባት፣
መላስ ሲንጠባጠብ
በዲን ምላስ ማርጠብ
ቀላጭ ፍሙን ማኘክ
ማኘክና ማድቀቅ
ማድቀቅና ማላም
እንደዚያች ወላድ ላም
ላስ አርጎ እሳቱን
ቻል አርጎ ፍጅቱን
መዋጥ በዝምታ
እንዲያ ነው ይቅርታ።
በእግሮቻችን ዳና
ባተምነው ጎዳና
ስንጓዝ የቀና
እንቅፋት ሲቀስፈን
ጥጉን ተደግፈን
ቁስላችንን ማፈን፤
እግራችን ምስኪኑን
ዝምታ ክኒኑን
ዋጥ አርጎ የግዱን
ተወግቶ እንዳይደማ
አቁሳዩ ሳይሰማ
ግሽልጡን ደምድሞ
ቁስል ላይ ጠምጥሞ
ካህን መሆን መፍታት
ጸሎት ለእንቅፋት
ማድረስ በዝምታ፣
እንዲያ እንጂ... መች ዋዛ?
መች ቀላል ይቅርታ?
ይቅርታ መች ቀላል?
ለሰጪ ይከብዳል
ለሰጭ ካልከበደ፡ ተቀባይ ያለምዳል
ለማዳ ተቀባይ ፡ ከርሞ ያቃልላል
ከርሞ የቀለለ፡ ይነሳል ይወድቃል
ከዚያ በኋላማ ፡ምኑ ይጠየቃል?
እንቅፋት ይረክሳል፡ እግር ይደነዝዛል
የተጠመጠመው፡ ቁስል ያመረቅዛል
ድንጋይ የበዛበት፡ ድንጋይ ልብ ያፈራል
ከዛ በኋላማ ፡ ምኑ ይነገራል?
ማን ማንን ይፈራል? ማን ለማን ይራራል?
ጠጠር ያናቀፈው፡ ዓለት ሆኖ ያድራል።
ወድቀው ሳይነሱ
ሳይዘሩ ሳያርሱ
እንደ ኦሪት መና
ይቅር ከደመና
አይውረድ ከሰማይ፤
ሲያቀሉት ይከብዳል
ይቅርታና ሲሳይ።
የሬት gድቃይ
ሲቀምሱት በስቃይ
«ሁለተኛ!» ብለው
እንደምጥ ላይደግሙት
በወለዱት ምለው
ፍም እሳት ተረግጠው
በጥፍር አፈሩን፡ሳር ቅጠሉን ቧጥጠው
ከፍሙ ማር ቆርጠው
ጎመራ እሳት ውጠው
አምጠው አምጠው
ማቅቀው ተንሰቅስቀው፡ በጊዜ ይሁንታ
እስኪነሱ ድረስ፡ መሞት ነው ይቅርታ።
Rediet Assefa
Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA

1300
17:41
13.05.2025
🌿Good Morning እጅግ የምወዳችሁና መልካምን ነገር የምመኝላችሁ ቤተሰቦቼ🥰!
እንኳን በሰላም ለዛሬዋ ቀን አበቃችሁ!
እስቲ የዛሬዋን ቀን አርፋችሁ ጀምሯት!
ቀንን አርፎ መጀመር ማለት እረፍትና እርካታ ፍለጋ ምንም ነገር ለማድረግ ከመታገል መረጋጋት ማለት ነው፡፡
ውስጣችሁ እርፍ እንዲል ማንም ሰው ሊቀባለችሁ አይገባም፣ ማንንም ሰው ማስደሰትም የለባችሁም፡፡ ስላረፋችሁ ግን ከሰዎች ጋር ያላችሁን ግንኙነት ሚዛነዊ አድርጋችሁ የመያዝ መረጋጋት ታገኛላችሁ፡፡
ውስጣችሁ እርፍ እንዲል የትኛውም ስራ ስኬታማ መሆን የለበትም፡፡ ውስጣችሁን አሳርፋችሁና አረጋግታችሁ የምትሰሩት ስራ ራሱ መነሻው ስኬታማነት መሆኑን አስታውሱ፡፡
ከእነዚህ ሁለት ምሳሌዎች ተነስቼ ከጀመርላችሁ ሌሎቹን እናንተው አስቧቸው፡፡
ምንም ነገር ስታደርጉ፣ የውስጣችሁን እረፍት ነገሩ እስከሚሳካ አታዘግዩት፡፡
መጀመሪያውኑ ፈጣሪ በሰጣችሁ ማንነት፣ ባላችሁ የሕይወት ራእይና አጠገባችሁ ካለምንም ቅድ-ሁኔታ በሚወዷችሁ ሰዎች እርፍ በሉ፡፡
ከዚህ አይነቱ ሁኔታ ስትነሱና ስትጀምሩ ሰዎችም ሆኑ ሁኔታዎች የእናንተን ስሜት እንደፈለጉ አያደርጉትም፡፡
Dr Eyob

1200
06:17
13.05.2025
በእርጅና ዕድሜህ ላይ ጸጸትን ሊያስከትሉብህ የሚችሉ ነገሮች!
ክፍል-1
በወጣትነት ጊዜያችን ስለ ወደፊቱ ብዙም ሳናስብ የተለያዩ ውሳኔዎችን እናደርጋለን። አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ውሳኔዎች በመካከለኛ ዕድሜያችን ላይ ክፉኛ ዋጋ ያስከፍሉናል። አንድ ሰው ሲያረጅ ሊጸጸትባቸው ከሚችላቸው ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ እነዚህ ናቸው፦
1. የተሳሳተ ሰውን ማግባት
በወጣትነት ጊዜ፣ የማግባት ዝንባሌያችሁን መርምሩ። እኩዮቻችሁን ለመፎካከር፣ ለማህበራዊ ክብር ወይም በጫና ምክንያት አታግቡ። ለፍቅርና ለጓደኝነት ብላችሁ አግቡ፣ ትክክለኛውን ሰው አግቡ፣ የልብ ጓደኛችሁን አግቡ። ምክንያቱም የተሳሳተውን ሰው ወይም በተሳሳተ ምክንያት ካገባችሁ፣ ቀሪውን ህይወታችሁን ከዛ ሰው ጋር መጋፈጥ ይኖርባችኋል። በሁለታችሁ መካከል ነገሮች ሊከፉ ይችላሉ፤ ከዚያም በመካከለኛ ዕድሜያችሁ ድብርት፣ አካላዊ ጥቃት፣ ምንዝርነት፣ ህመም፣ እፍረት፣ የፍርድ ቤት ጉዳዮች፣ ምሬት የህይወታችሁ መገለጫ ይሆናሉ፤ ይህ ሁሉ የሆነው የተሳሳተውን ሰው ስለመረጣችሁ ነው። ልጆች ሲኖሩ ደግሞ ነገሮች ይበልጥ ይከፋሉ። በወጣትነታችሁ ትክክለኛውን የትዳር አጋር ምረጡ።
2. ያልተጠቀምንባቸው አጋጣሚዎች
በወጣትነታችሁ ብዙ በሮች ይከፈታሉ፣ ብዙ እድሎች ታገኛላችሁ። ብዙ ወጣቶች በፍርሃት፣ በስንፍና ወይም በትዕቢት ምክንያት እነዚህን አጋጣሚዎች ያልፏቸዋል። ነገር ግን ወጣትነትና ጉልበት እያለ አዲስ ሥራ ለመጀመርና ለራሳችሁ ስም ለመገንባት ምርጡ ጊዜ ነው። አንዳንዶች እድሎቹ ለእነርሱ በጣም ትልቅ እንደሆኑ ያስባሉ። እነዚህን አጋጣሚዎች ተጠቀሙባቸው፤ አለበለዚያ አንድ ቀን ስታረጁ ወደ ኋላ ተመልሳችሁ እነዚያን ያመለጡ እድሎች ለመያዝ ትመኛላችሁ።
3. ያፈረስናቸው ድልድዮች (ያቋረጥናቸው ግንኙነቶች)
በወጣትነት ጊዜያችን ለግንኙነቶች ብዙም አንጨነቅም፤ አብዛኛው ሰው የሚያስበው በማንኛውም ዋጋ ገንዘብ ማግኘትና የስኬት መሰላልን መውጣት ነው። ብዙዎች ለመሻሻል ሲሉ ሰዎችን ይጠቀማሉ ይረግጣሉም፤ ግንኙነቶችን እንደ ቀላል ነገር ይቆጥራሉ፣ ትስስሮችን ያበላሻሉ፣ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ከሰዎች ጋር ይተኛሉ። ነገር ግን እነዚህ መጥፎ ድርጊቶች ወደፊት ዋጋ ያስከፍሏችኋል። ህይወት ያለ ፍቅርና ጓደኞች ምን ያህል ባዶ እንደሆነ ስትገነዘቡ። ስኬታማ ስትሆኑ ነገር ግን በዙሪያችሁ ማንም ሳይኖር ወይም የሚታመን ሰው ስታጡ።
4. ያስወረድነው ጽንስ
በወጣትነት ጊዜ እርግዝና ተከስቶ ፍርሃት ሲኖር፣ ስለዚያች ቅጽበት ብቻ በማሰብ የጽንስ ማቋረጥ አማራጭ በፍጥነት ሊወሰድ ይችላል። ነገር ግን ዕድሜ ገፍቶ በእጅጉ ሲያረጁ፣ ወደ ኋላ መለስ ብሎ ያንን ህጻን ቢይዙት ኖሮ ይመኛሉ። ሀብታም እና ስኬታማ ሲሆኑ፣ ያ የተዉት ልጅ አብሯቸው ሆኖ የልፋታቸውን ፍሬ ቢደሰት ይመኛሉ። ነጠላ ወላጅ መሆን በህይወት ስኬታማ መሆንን ወይም ወደፊት አጋር ማግኘትን አያግድም።
5. የካድነው ልጅ
አንድ ሰው ሴትን አስረግዞ፣ ልጅ እንደፀነሰች ስትነግረው ኃላፊነትን ሳይወስድ ሲቀር። ነገር ግን ከዓመታት በኋላ በ50ዎቹ ዕድሜ ላይ ስትሆኑ፣ ኃላፊነት ቢሰማችሁ ኖሮ ትመኛላችሁ፣ ለዚያ ልጅ ወላጅ ብትሆኑ ኖሮ ትመኛላችሁ። ያ ልጅ ሲያድግና ትልቅ ሰው ሲሆን ታያላችሁ ነገር ግን ከመጀመሪያው የካዱት ያደገ ልጅ ላይ ምንም አይነት የወላጅነት መብት አይኖራችሁም። በራስ ምርጫ ኃላፊነት የጎደለ ወላጅ በመሆን ትጸጸታላችሁ።
6. ያፈረስነው ትዳር
ጥሩ እጮኛችሁን አገባችሁ፤ በትዳር የመጀመሪያዎቹ ወራት ጥሩ ነበሩ ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ፣ በገንዘባችሁና በመልካችሁ ምክንያት፣ ምንዝርና ጀመራችሁ። ታማኝ አልነበራችሁም። የትዳር አጋራችሁ ለመኗችሁ፣ ልጆቻችሁ መጎዳት ጀመሩ፣ ትዳራችሁ እየፈረሰ ነበር። አንድ ቀን ስታረጁ፣ ያንን መገንባት የጀመራችሁትን ጥሩ ትዳር ምንም ላልጠቀሟችሁ ጊዜያዊ የውጭ ግንኙነት ደስታዎች ስትሉ እንዴት በሞኝነት እንዳፈረሳችሁት ይገለጽላችኋል። በልጆቻችሁና በትዳር አጋራችሁ ላይ ያደረሳችሁትን ጉዳት ትገነዘባላችሁ።
7. የካድነው አምላክ/እግዚአብሔር
በእጅጉ ስታረጁ የበለጠ ጠቢብ ትሆናላችሁ፣ ህይወትን ይበልጥ ትርጉም ባለው መንገድ ስትመለከቱ እግዚአብሔር የበለጠ እውን ይሆናል። ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ግንኙነት ለመደሰት እርጅናን አትጠብቁ። በወጣትነታችሁ እግዚአብሔርን እወቁ፣ የወደፊት ህይወታችሁን ከእግዚአብሔር ጋር ገንቡ። ዕድሜ ሲደርስባችሁ ወደ እግዚአብሔር የምትመለሱ ወጣት ዓመጸኞች አትሁኑ።
......ይቀጥላል....

16:39
12.05.2025
play_circleVideo preview is unavailable
እግዚአብሔር ሊቀይራችሁ ሲፈልግ እነዚህን 3 ጥያቄዎች ይጠይቃችኋል .....❤️
1200
05:40
12.05.2025
🎤አዳዲስ መዝሙሮች እና አልበሞች እየተለቀቁ ስለሆነ የምትፈልጉት ዘማሪ ስም በመንካት መሉ አልበም እና አዳዲስ ዝማሬዎችን ያገኙበታል 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
259
17:22
11.05.2025
ካይንህ ጋር ሚያቀራርበኝ ፤ ባላገኝ ከፍ ያለ ሾላ
ፍቅርህን ከድምፅህ ልስማው ፤ ከኔም ጋር እራት እንብላ?
አይመጥንህም እቤቴ ፤ አጢሃት እድፌን ታውቃለህ
ወዳጅ ነህ የማትፀየፍ ፤ አውቃለው ትወደኛለህ
ማረኝ ብል አያምርብኝም ፤ ወዳጁን ሚበድል የለም
አውቃለው አውቆ መበደል ፤ ለወዳጅ ቀላል አይደለም።
እውነት ሆይ ! እውነትህን አልመረጥኩም።
መንገድ ሆይ! በመንገድ ላይ አልሄድኩም።
ህይወት ሆይ ! ህይወትህንም አልኖርኩም።
እስትንፋስ ሆይ ምንም መተንፈስ አልቻልኩም።
ታፈንኩኝ ባለም ፤ በገዛ እጄ
ስጋን መረጥኩት ፤ ተው ስትል ልጄ
አልሰማውክም ፤ እየሰማውክ
በምስክር ፊት ፤ ጀርባ ሰጠውክ
በሰነፍ ድርሻ ፤ ምሄድበት አጣሁ
የእንደገና አምላክ ደግሜ መጣሁ።
የእንደገና አምላክ ልጅ አትፈልግም?
የሞተ ለእራስ የሞተ ለዓለም ?
ተስፋ የቆረጠ ትፈልጋለ?
አሁን ገብቶኛል መስቀልህ የታለ?
መልሰኝ
መልሰኝ ፤
ወደ በሩ የህይወት ውሃ
ልጄ በለኝ ፤
እኔም አባ ልበልሃ
እቀፈኝ ፤
ከመቅበዝበዜ ልሰብሰብ
አሳርፈኝ ፤
ደክሞኛል ስለ ዓለም ማሰብ።
ካይንህ ጋር ሚያቀራርበኝ ፤ ባላገኝ ከፍ ያለ ሾላ
ፍቅርህን ከድምፅህ ልስማው ፥ ከኔም ጋር እራት እንብላ?
@debi~isa
https://t.me/+h5vKp6KEheEzYTg8
Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
ፍቅርህን ከድምፅህ ልስማው ፤ ከኔም ጋር እራት እንብላ?
አይመጥንህም እቤቴ ፤ አጢሃት እድፌን ታውቃለህ
ወዳጅ ነህ የማትፀየፍ ፤ አውቃለው ትወደኛለህ
ማረኝ ብል አያምርብኝም ፤ ወዳጁን ሚበድል የለም
አውቃለው አውቆ መበደል ፤ ለወዳጅ ቀላል አይደለም።
እውነት ሆይ ! እውነትህን አልመረጥኩም።
መንገድ ሆይ! በመንገድ ላይ አልሄድኩም።
ህይወት ሆይ ! ህይወትህንም አልኖርኩም።
እስትንፋስ ሆይ ምንም መተንፈስ አልቻልኩም።
ታፈንኩኝ ባለም ፤ በገዛ እጄ
ስጋን መረጥኩት ፤ ተው ስትል ልጄ
አልሰማውክም ፤ እየሰማውክ
በምስክር ፊት ፤ ጀርባ ሰጠውክ
በሰነፍ ድርሻ ፤ ምሄድበት አጣሁ
የእንደገና አምላክ ደግሜ መጣሁ።
የእንደገና አምላክ ልጅ አትፈልግም?
የሞተ ለእራስ የሞተ ለዓለም ?
ተስፋ የቆረጠ ትፈልጋለ?
አሁን ገብቶኛል መስቀልህ የታለ?
መልሰኝ
መልሰኝ ፤
ወደ በሩ የህይወት ውሃ
ልጄ በለኝ ፤
እኔም አባ ልበልሃ
እቀፈኝ ፤
ከመቅበዝበዜ ልሰብሰብ
አሳርፈኝ ፤
ደክሞኛል ስለ ዓለም ማሰብ።
ካይንህ ጋር ሚያቀራርበኝ ፤ ባላገኝ ከፍ ያለ ሾላ
ፍቅርህን ከድምፅህ ልስማው ፥ ከኔም ጋር እራት እንብላ?
@debi~isa
https://t.me/+h5vKp6KEheEzYTg8
Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
1500
04:52
11.05.2025
የኔ ቤት አይቆርቁርህ
የኔ ጓዳ አይሻክርብህ
ይሰማህ ብዙ ምቾት
እኔ ቤት ስትሰነበት።
Via:- Gospel Literature
የኔ ጓዳ አይሻክርብህ
ይሰማህ ብዙ ምቾት
እኔ ቤት ስትሰነበት።
Via:- Gospel Literature
1400
18:31
10.05.2025
....ኧረ የእርሱስ lጉድ ነው
አንድ ነገር ልበል የጨዋታ መነሻ
ያ መሲህ የታየው በመጨረሻ
ለካስ ነበር ቀድሞ ፍጥረተ ጅማሬ
የወግ መጀመሪያ እናድርገው ዛሬ
የሚገርም ክስተት ካለማ በምድር
እሱ ክርስቶስ ሰው የመሆኑ ነገር
ድንቅማ ከተባለ ለእኛ
አማኑኤል መኖሩ ነው ከኛ
ሌላውማ ነበር ሆኖ ቀረ እንጂ
ችሎቱ ተደንቆ ነገርን ሲያበጅ
እድሜ ገደበውና ከንቱ ሆነ ልፋቱ
ሰው ስለነበር አበቃ አመቱ
ዘመን ያልሻረው ከሰማይ የመጣ
በመስቀል ተሰቅሎ ሰይጣንን የቀጣ
በግርማው አለ ግሩም ድንቅ ሀያል
የሰላም አለቃ ኢየሱስ ይባላል
ስልጣናት ሀይላት ከስሩ ይፈልቃሉ
አማልክት ለክብሩ ይንበረከካሉ
በመላዕክት ቀን ማታ ስግደት የተገባው
ለንጉሰ ነገስት አምልኮ ይግባው
የዘመኔ ቀመር ቁጥሩን ያውቀዋል
ሊሰራ ስላለው ማንስ ይመክረዋል
ሰማይን አንጧልሏል ያለ ምሶሶ
ምድርንም አጸና እንዳሰምጥ ተደርምሶ
ጸሀይን አዘዘ ቀትርን ሰጠና
ለጨረቃ ከዋክብት ምሽት አለና
ደመናትን አዝዞ ዉሃን ያዘንባል
ኧረ እንደ ጌታ ጠቢብስ የታል
ለዚህ ነው እንግዲ ድንቅ ከተባለ
እንደ ጌታማ ድንቅ ከፍጥረት የታለ
ሚታየውን አለም ከማይታይ ሲጣራ
በሰማየ ሰማይ እኔን እኛን ሲሰራ
እግዚኦ ለችሎቱ በክብር ሲያበራ
ድምቀት ምንጩ ነው ከጸሀይ ይልቃል
ጨለማ መች እሎ ከሱ ይቀመጣል
ዉበትስ ቢባል የውበት መደምደሚያ
የደናግል ናፍቆት የአይን ማረፊያ
ከሩቁ ይጣራል መአዛው የሱ
የሳሮን ጽገሬዳ ያንጻል መንፈሱ
ደግሞ ዉበት የለው ደምግባትን ያጣ
አይተን እንዳንወደው በደዌ የተቀጣ
ኧረ የእርሱስ ለጉድ ነው ተአምር አድራጊ
ኢየሱስ ገናና ጀግና ነው ተዋጊ
✍✍ በ ጌታሁን አናሞ✍✍

1600
15:51
09.05.2025
⚠️ለአንተ❓ወይም ለአንቺ❔ ምርጡ አገልጋይ ማነው
በትምህርቶቹ እና በስብከቶቹ ይበልጥ የተባረካቹበትን አገልጋይ ምረጡ የሚመጣላቹሁን ቻናል ተቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በትምህርቶቹ እና በስብከቶቹ ይበልጥ የተባረካቹበትን አገልጋይ ምረጡ የሚመጣላቹሁን ቻናል ተቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
187
09:09
09.05.2025
ዳዊት እባላለሁ
ዳዊት እባላለሁ እንደልቤ የተባልኩ
ቤት እንኳን የረሱኝ በእረኝነቴም የታወኩ
ሁሉም በረሱኝ ወቅት ለዘይት የተፈለኩ
ከአውሬው ከነጣቂው ከአንበሳም የተረፍኩ
ማንም ሚፈራውን ጠላትን የዘረርኩ
በእኔ አቅም ሳይሆን ጌታን የተደገፍኩ
💫ዳዊት እባላለሁ እንደልቤ የተባልኩ
ምህረት የበዛልኝ በኪዳን ያለሁኝ
የጎሊያድ ጦር የሳኦል ቀስት ጭራሽ ያላገኘኝ
በቸርነት ያለው ለንግስና የተመረጥኩኝ
💫 ዳዊት እባላለሁ
ቦታዬን ያላወኩ በሰው ሚስት የወደኩ
ስሜቴን ያልጠበኩ እራሴን ያረከስኩ
በሉዋንም ያስገደድኩ አልፎም ያስገደልኩ
ለልጄ መሞት ምክንያት የነበርኩ
💫ዳዊት እባላለሁ በምህረት የቆምኩ
ከዛ ሁሉ ትርምስ ከዛ ሁሉ ውድቀት ቦኃላ የተረፍኩ
በምህረቱ ብዛት መቅደሱ የገባውኝ
ሁሉም ነገር አልፎ ሰለሞንን የሰጠኝ
ከዚህ ሁሉ በኋላ የይዲዲያ አባት
ብዙ የወደኩኝ ግን የምማር ከስህተት
ምህረት የበዛልኝ የምህረት ውጤት ነኝ
💫 ዳዊት እባላለሁ እንደልቤ የተባልኩ
ገጣሚ የአብስራ አማኑኤል (ፌቨን)
03/09/2016
Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
ዳዊት እባላለሁ እንደልቤ የተባልኩ
ቤት እንኳን የረሱኝ በእረኝነቴም የታወኩ
ሁሉም በረሱኝ ወቅት ለዘይት የተፈለኩ
ከአውሬው ከነጣቂው ከአንበሳም የተረፍኩ
ማንም ሚፈራውን ጠላትን የዘረርኩ
በእኔ አቅም ሳይሆን ጌታን የተደገፍኩ
💫ዳዊት እባላለሁ እንደልቤ የተባልኩ
ምህረት የበዛልኝ በኪዳን ያለሁኝ
የጎሊያድ ጦር የሳኦል ቀስት ጭራሽ ያላገኘኝ
በቸርነት ያለው ለንግስና የተመረጥኩኝ
💫 ዳዊት እባላለሁ
ቦታዬን ያላወኩ በሰው ሚስት የወደኩ
ስሜቴን ያልጠበኩ እራሴን ያረከስኩ
በሉዋንም ያስገደድኩ አልፎም ያስገደልኩ
ለልጄ መሞት ምክንያት የነበርኩ
💫ዳዊት እባላለሁ በምህረት የቆምኩ
ከዛ ሁሉ ትርምስ ከዛ ሁሉ ውድቀት ቦኃላ የተረፍኩ
በምህረቱ ብዛት መቅደሱ የገባውኝ
ሁሉም ነገር አልፎ ሰለሞንን የሰጠኝ
ከዚህ ሁሉ በኋላ የይዲዲያ አባት
ብዙ የወደኩኝ ግን የምማር ከስህተት
ምህረት የበዛልኝ የምህረት ውጤት ነኝ
💫 ዳዊት እባላለሁ እንደልቤ የተባልኩ
ገጣሚ የአብስራ አማኑኤል (ፌቨን)
03/09/2016
Link For Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
1400
07:58
09.05.2025
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
1 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
c
**ffeennew@******.io
On the service since June 2022
07.04.202518:59
5
Everything is fine. Thank you!
New items
Looking for more recommendations?
Launch ad campaigns
Create channel packages
Add channels to favorites
Channel statistics
Rating
7.5
Rating reviews
5.0
Сhannel Rating
1
Subscribers:
21.1K
APV
lock_outline
ER
--%
Posts per day:
3.0
CPM
lock_outlineSelected
0
channels for:$0.00
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий