
- Main
- Catalog
- Religion & Spirituality
- Advertising on the Telegram channel «የእምነት ጥበብ»
Advertising on the Telegram channel «የእምነት ጥበብ»
"የኦርቶዶክስ ክርስትና ጥልቅ ትምህርቶችን እና ጊዜ የማይሽረው እውነቶችን እወቅ።በእምነት ጥበብ በእምነታችን ላይ የተመሰረቱ ትርጉም ያላቸው መልሶችን እናካፍላለን። በመንፈሳዊ ጉዞዎ ላይ እድገትን፣ ግልጽነትን እና የሚያበረታቱ ትርጉም ላለው ንግግሮች እና ግንዛቤዎች ይቀላቀሉ
Channel statistics
“ታዲያ ያች ሴት ይህንን ከሰማች በኋላ ምን አደረገች? ዝም አለችን? ወይስ ተስፋ ቆርጣ ተወች? ወይስ ጥረቷን አላላች? በፍጹም! ይልቁንም ከመጀመሪያው በበለጠ ሁኔታ አጥብቃ ለመነች። የእኛ ሁኔታ ግን እንደ እሷ አይደለም፤ እኛ የፈለግነውን ነገር ወዲያው ካላገኘን ጸሎታችንን እናቆማለን። እንዲያውም (መልሱ በዘገየ ቁጥር) ይበልጥ አጥብቀን መለመን ነበረብን። በእውነት ግን፣ በዚያ ሰዓት በተነገረው ቃል ግራ የማይጋባ (ተስፋ የማይቆርጥ) ማን አለ? የጌታ ዝምታ ብቻውን እሷን ለተስፋ መቁረጥ በቂ ነበር፤ የሰጣት መልስ ግን ከዚያ በላይ የሚያስደነግጥ ነበር። ምክንያቱም ራሷ በጭንቅ ላይ ሆና ሳለ፣ ስለ እሷ የሚለምኑላት ደቀ መዛሙርቱ እንኳ ግራ መጋባታቸውን ስታይ፣ ደግሞም ልመናዋ ሊፈጸም የማይችል ነገር መሆኑን (ከእስራኤል ውጭ አልተላክሁም የሚለውን) ስትሰማ፣ ይህ ነገር ሊነገር በማይችል ግራ መጋባት ውስጥ ሊጥላት ይችል ነበር። ይሁን እንጂ ሴቲቱ ግራ አልተጋባችም (ተስፋ አልቆረጠችም)፤ ይልቁንም አማላጆቿ (ደቀ መዛሙርቱ) ምንም ማድረግ እንዳልቻሉ ስታይ፣ እሷ ራሷ በመልካም ትዕቢት (Goodly shamelessness/ቅዱስ ድፍረት) ራሷን አደፋፈረች።"
†“በክርስቲያን ሃይማኖት አጽኝኝ። ክርስቲያን አድርጊኝ ። ፣ ክርስቲያን ልባል ምስጋና በክበበ ትስብእት በመንፈስ ቅዱስ በመጣ ጊዜ ክርስቲያን ሁኜ ልገኝ ።”†‒ ማር አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ያው እግዚአብሔር ክርስትያን ሁነን እንድንገኝ ሁላችንም ይርዳን እራሳችን እንድናይ ነው ይሄን የጻፍኩት
መረን የለቀቀ ዝማሬ የስካር የቅርብ ጓደኛ ነው። በመጠጥ የሚያልፍ ሌሊት ስካርን ይጋብዛል፣ ፍትወትን ይቀሰቅሳል፣ ለነውር ተግባርም ድፍረትን ይሰጣል። ሰዎች ጊዜያቸውን በዋሽንት፣ በበገና፣ በጭፈራ፣ በግብፃውያን የጭብጨባ ዓይነትና በሌሎች ሥርዓት አልበኛ በሆኑ ከንቱ ነገሮች የሚያሳልፉ ከሆነ፣ እፍረተ ቢስና የማይገሩ ይሆናሉ፤ በጸናጽልና በከበሮ እየመቱ በአሳሳች መሣሪያዎች ድምፅ ያሰማሉ፤ እንዲህ ዓይነቱ ግብዣ ለእኔ የስካር ቲያትር ቤት ይመስለኛል። ሐዋርያው የጨለማን ሥራ ጥለን የብርሃንን ጋሻ እንድንለብስ፣ በቀን እንደምንሆን በአክብሮት እንድንመላለስ፣ በዘፈንና በስካር፣ በዝሙትና በመረንነት እንዳንኖር አዝዟልና (ሮሜ 13:12-13)።
Reviews channel
2 total reviews
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «የእምነት ጥበብ» is a Telegram channel in the category «Религия и духовность», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 19.0K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 27.7, with 2 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 2.4 ₽, and with 3 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий