Monetize Telegram Mini App with Telega.io
Connect your app, set CPM, and watch your revenue grow!
Start monetizing
2.1

Advertising on the Telegram channel «✞ ፀሐየ ጽድቅ ✞»
👉ፀሐየ ጽድቅ የሕይወት መብራት የጽድቅ ብርሃን በዚህ channel ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቁ ትምህርቶች እና መዝሙሮች እንዲሁም ቅዱሳንን እንዘክራለን ስለቅዱሳን እንማማራለን ዕለታዊ ዜና ቤተ-ክርስቲያ ስንክሳር ግጻዌ ጥያቄና መልስ እንዲሁም በየእለቱ አጥንትን የሚያጠነክሩ መንፈስን የሚያለመልሙ ጽሁፎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡ ቻናሉን ይቀላቀሉ ሼር ያርጉ!!
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$1.20$1.20local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
አንድ ደግ መምህር ነበሩ ከመልካም ነገር በቀር ሌላ አያወሩም ነበርና ተማሪዎቻቸው ቀርበው የኔታ "አንድ ቀን አንኳ ተሳስተው ክፉ ንግግርን ተናግረው አያውቁም ምስጢርዎ ምንድን ነው?" ቢሏቸው "አይ ልጆቼ ደግ ደጉ ነገር መቼ አልቆብኝ ክፉ ክፉውን ልናገር" አሉ ይባላል።
እና ምን ለማለት ነው.....
ሁሌም አዎንታዊ አስተሳሰብን በሕይወታቸን ውስጥ ዋና መርህ እናድርገው፣ ክፋትን ከመናገር ይልቅ ሌሎችን የሚያንጹ፣ የሚያበረታቱ እና የሚያስተምሩ ቃላትን ብቻ እንጠቀም። ይህም ሕይወታችንን በአዎንታዊ መልኩ ለመምራት የሚያስችል ጥበብ ነውና።
~ @Tsehaye_Tsidk

277
09:07
03.09.2025
imageImage preview is unavailable
+• አንተ ማለት ለእኛ... •+
ኃጢአታችን ተጽፎ ተደጎሰ። ነውራችን ሞልቶ ፈሰሰ። ክፋታችን ከአጋንንት ባሰ። ደዌያችን ሊቀጥፈን ደረሰ። አሥር ለክተን አንድ መቁረጥ የማይሳካልን፥ መቶ አስበን አንዱ ስንኳ የማይሰምርልን ድውያን ሆንን። ከእኛ ወደ ትፋቱ የሚመለሰው ውሻ፥ ከእኛ ቀና ማለት የማይችለው እሪያ ተሻለ።
በዚህም ሁሉ ውስጥ ግን አንተን ማየት አላቆምንም። ለምን? ምክንያቱም...
አንተ የፍጥረታት ሀለዎታቸው፥ የመነኮሳት ሕይወታቸው፥ የጻድቃን ክብራቸው፥ የሰማእታት መመኪያቸው፥ የምእመናን አርአያቸው፥ የመላእክት ጌታቸው፥ የአጋንንት እሥራቸው፥ የኃጥአን ተስፋቸው ነህ።
ለእኛስ?
ጨለማን የገፈፍክ ብርሃናችን፥ የጥል ግድግዳን ያፈረስክ ኃይላችን፥ ረሃባችንን የምትገታ ምግባችን፥ ጥማችንን የምትቆርጥ መጠጣችን፥ ባለንበት የምታጸናን መልሕቃችን፥
የጥርጣሬን ነፋስ የምትገስጽ ሰላማችን፥ ኃጢአትን ቆርጠህ የምትጥል ሰይፋችን፥ ከደዌ የምትፈውስ መድኃኒታችን ነህ።
Via Fresenbet G.Y Adhanom

318
09:07
05.09.2025
ጳጉሜን
የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡
ጳጉሜን ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ ጳጉሜን ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃች ትለያለች፡፡ ጳጉሜን በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ በዘመነ ሉቃስ ማብቂያ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 15 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡
በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡ ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡
የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፥2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡
የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡

243
07:13
06.09.2025
የቤተክርስቲያን ውበት❗️
......
በተሰራች ቤተክርስቲያን የእኛ ድርሻ በሕጓ ጥላ ስር አርፎ መኖር ነው።በክርስቶስ የተመሠረተች፣በነቢያት ትንቢት፤በሐዋርያት ትምህርት የታነጸች በክብሯ የምንከብርባት፤ በውበቷ የምንደምቅባት ፤አነሰ ይቀነስ፤ረዘመ ይጠር የማትባል የክርስቶስ ልክ የበጉ ቀሚስ ናት ቅድስት ቤተክርስቲያን። የኦርቶዶክሳዊት ሙሽሪት ቤተክርስቲያን ሙሽራዋ ኢየሱስ ነው። ክርስቶስ ራሷ ሆኖ እርሷ (ቤተ ክርስቲያን) ደግሞ የእርሱ አካል ነች። ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የሚመግባት - በማየ ገቦው የሚቀድሳት - በቃሉ የሚያጠጣትና የሚያሳድጋት አካሉ ናት። ዶግማዋ፣ትውፊቷና ቀኖናዋም ሕገ እግዚአብሔር ነው። የሥርዓቷ ጌጥ የአምልኮዋና የትምህርቷ ማዕከልም ኢየሱስ ነው። ለውበት ብለን የምንጨምረው፤ለድምቀት ብለን የምናሻሻለው ሥርዓት የላትም። የማያረጅ ውበቷ፣ የማይደበዝዝ ድምቀቷ ኢየሱስ ነው። በከበረች ቤተክርስቲያን ለመክበር መፋጠን የተገባ ነው። በእኛ ጌጥ የምትከብር ሳይሆን የምንከብርባት ቤተክርስቲያን ነው ያለችን። ወጥ ዶግማ፣ ያልተቋጠ ትውፊት ፣ያልተበረዘ ሥርዓት (ቀኖና) ያላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለሌላው ታስተምራለች እንጂ ከሌላው አትቀበልም። የቤተክርስቲያን ፍቅሯን፣የድንግልን በረከቷን ያድለን።
👇ቤተሰብ ይሁኑ👇
~ @Tsehaye_Tsidk
✍️ ፀሐየ ጽድቅ

248
10:38
07.09.2025
ጳጉሜ 3
ዝ ክ ረ - ቅ ዱ ሳ ን
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
እንኳን ለርኅወተ ሰማይ: ለቅዱስ ሩፋኤል: መልከ ጼዴቅ: ዘርዓ ያዕቆብና ሰራጵዮን ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን!
✟ ርኅወተ ሰማይ ✟
✞ ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት: አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት: ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ዕለት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ-ሰማይ የሚከፈትባት ቀን።" ትባላለች።
አሁን በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም። የሰው ልጆችን ልመና ቅዱሳን መላእክት ያለ ከልካይ የሚያሳርጉበት: አንድም ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንዲህ ተባለ እንጂ።
እመቤታችን ድንግል ማርያም ለአጼ ናዖድ እንደ ነገረቻቸው በዚህች ዕለት ሁሉም ቅዱሳን ስለሚታሰቡ: የእግዚአብሔር የምሕረት መዝገቡ ስለሚከፈት: ዕለቷን ክብርት ያሰኛታል። በቅዱስ ሩፋኤል አበጋዝነት (መሪነት) በዚህች ዕለት ለዓመት የሚበቃ ምሕረት ይገኛል።
ስለዚህም አባቶቻችን በዚህች ሌሊት ሦስት መቶ ስልሳ አምስት አቡነ ዘበሰማያትን ሲጸልዩ ያድራሉ። በሌላ ወገን ደግሞ የጌታ ዳግም ምጽዓቱ መታሰቢያ እንደ መሆኗ ትልቅ ትኩረትም ይሰጣታል።
ቸሩ ጌታችን ከተከፈተች ገነት ከተነጠፈች ዕረፍት ሁላችንንም ያድርሰን።
✟ ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት ✟
✞ ቅዱስ ሩፋኤል በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በደረጃው ሦስተኛ ነው። በመጀመሪያዋ ዕለተ ፍጥረት እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክትን ፈጥሮ በአሥር ከተማ ሲያኖራቸው የቅዱስ ሩፋኤል ዕድል ፈንታው ራማ ሆነች።
በዚያም "መናብርት" ተብለው ለሚጠሩ አሥሩ ነገድ አለቃ (መሪ) ሆኖ በፈጣሪው ተሹሟል። በኋላም "መጋብያን" በሚባሉ በሃያ ሦስቱ ነገድ ላይ ሹሞታል። ይህች ዕለትም በዓለ ሲመቱ ናት።
አንድ ቀን ጌታችን ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ሐዋርያቱ ቅዱስ ሩፋኤልን እንዲያስተዋውቃቸው ለመኑት። ጌታም ሦስቱን ሊቃናት (ሚካኤል: ገብርኤል እና ሩፋኤል) ይመጡ ዘንድ አዘዛቸው።
ቀጥሎም ቅዱስ ሩፋኤልን "ክብርህን ንገራቸው።" አለው። እርሱም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምሥጢር ነገራቸው። በተለይ ስሙን ለሚጠሩ: መታሰቢያውን ለሚያከብሩ የሚደረገውን ጸጋ አብራርቶላቸው ዐረገ።
በመጽሐፈ ጦቢት ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ቅዱሱ መልአክ ሰው (አዛርያን) መስሎ: ጦብያን ለትዳር አብቅቶ: ሣራን አስማንድዮስ ከሚባል ሰይጣን አድኖ: የጦቢትን ዓይን አብርቷል። በገድላተ ቅዱሳን እንደምናየውም ለብዙ ቅዱሳን ረዳታቸው ሆኖ ገድላቸውን አስፈጽሟል።
ታሪክ እንደሚለው ይህች ቀን ለቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱም ናት። በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘእስክንድርያ አማካኝነት ቤቱ ታንጿል:: የሚገርመው ደግሞ የታነጸው በዓሣ አንበሪ ጀርባ: ደሴት ላይ ነው። በመልአኩ አጋዥነትም ለሦስት መቶ ዓመታት አገልግሏል።
✟ ቅዱስ ሩፋኤል
✞ መስተፍስሒ (ልቡናን ደስ የሚያሰኝ)
✞ አቃቤ ሥራይ (ባለ መድኃኒት ፈዋሽ)
✞ መዝገበ ጸሎት (የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው)
✞ ሊቀ መናብርት (በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት መሪ)
✞ ፈታሔ ማኅጸን (የሰውንም ሆነ የእንስሳትን ማኅጸን የሚፈታ)
✞ መወልድ (አዋላጅ: ምጥን የሚያቀል) ይባላል።
"ለሰብእ ወለእንስሳ ፈታሔ ማኅጸኖሙ አንተ" እንዲል።
-------------------------------------------------
"እውነት እውነት እላችኋለሁ። ሰማይ ሲከፈት: የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ።"
(ዮሐ. ፩፥፶፪)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
#ስንክሳር_ዘወርሃ_ጳጉሜ
ለሌሎች ያካፍሉ!!
~ @finote_tsidk

411
22:27
07.09.2025
ዘመን ማን ነው? ዘመን ማለት እኛ ነን..ስንከፋ የሚከፋ ደግ ስንሆን ደግ የሚሆን የእኛው ነጸብራቅ ነው ዘመን። ለዚህ ነው አበው በአንጋረ ፈላስፋ "ዘመን ማለት አንተ ነህ፡፡ አንተ ሰላማዊ ስትሆን ሰላማዊ ትሆናለች፡፡ አንተ የከፋህ እንደሆነ ትከፋለች፡፡" በማለት የተናገሩት።
እናም ዘመን እኛ እኛም ዘመን ነንና ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለው በዕሜያችን ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰብን ራሳችንን እንዲህ ብልን እንጠይቅ፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፣ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፣ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፤ ታዲያ ምን በጎ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፤ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ (ዘመኔ) መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፤ ታዲያ ዕድሜዬ (ዘመኔ) ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውን የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንደ አቅሜ እያደረግኩ ነውን?” በማለት ልቡናችንን እንጠይቅ።"
“አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ።” ሰቆ.ኤር 5፥21
ቤተሰብ ይሁኑ!!
👇👇👇
@Tsehaye_Tsidk

255
14:22
09.09.2025
imageImage preview is unavailable
መዝሙር 65፥ 11-13
==================
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
11 በቸርነትኽ፡ ዓመትን: ታቀዳጃለኽ፥ ምድረ በዳውም፡ ስብን፡ ይጠግባል።
12 የምድረ፡ በዳ፡ ተራራዎች፡ ይረካሉ፥ ኰረብታዎችም፡ በደስታ፡ ይታጠቃሉ።
13 ማሰማሪያዎች፡መንጋዎችን፡ለበሱ፥ ሸለቆዎችም፡ በእኽል፡ ተሸፈኑ፤ በደስታ: ይጮኻሉ፡ ይዘምራሉም።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ለአዲሱ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ!!!
ዘመኑ የሰላም፤ የፍቅር፤ የመተሳሰብ፣ ሁላችንም በአንድ ልብ ወደ ፈጣሪ የምንቀርብበት ክፉ ነገር የማንሰማበት የምህረት ዘመን ያድርግልን!!! ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ይባርክልን በምህረቱ ይጎብኝልን፤ ክፉ ነገርን ሁሉ አስወግዶ ዳሯን እሳት መሃልዋን ገነት አድርጎ ይጠብቅልን፤ አፍጣኒተ ረድኤት፣ ሰዓሊተ ምህረት ድንግል ማርያም በረድኤት በበረከቷ ትጎብኘን!!!
ተወዳጆች በዓሉ የሰላም የፍቅር የበረከት፤ ዘመኑ የሰላም የፍስሐ ይሁንልን!!!🙏🙏🙏
161
02:02
11.09.2025
“አንድ ቀለም ቀቢ ባለሙያ አስቀድሞ የሚቀባውን ግድግዳ በደንብ አድርጎ ሊጠርገውና ሊወለውለው፣ መፍረስና መፈነቃቀል ያለበት ጭቃ ካለም ሊያፈርሰውና ሊፈነቃቅለው ይገባል፡፡ ምክንያቱም እንዲያ ካላደረገ አዲስ የሚቀባው ቀለም ብዙም ሳይቆይ ግድግዳው ላይ በቆየው አሮጌ ቀለም ምክንያት ይወድቅበታልና፡፡
ልክ እንደዚሁ አንድ ክርስቲያንም በእርሱነቱ ላይ ያለውን አሮጌ ቀለም (ማንነት) ሳይወለውልና ፍቆ ሳይጥል ዘላቂነት ያለውን ቀለም መቀባት (አዲስ ሕይወትን መጀመር) ያቅተዋል፡፡ አሮጌ ማንነቱ አዲስ ሰውነቱን ያበላሽበታል፡፡ እንኳንስ በኹለንተናው ያለውን ይቅርና በአንዲት የሰውነት ሕዋሱ ላይ አንዲት ያረጀች ማንነት ካስቀረም በዚያች ምክንያት አካለ ጎደሎ ይሆናል፡፡ ያውም በነፍሱ፡፡
እንግዲያውስ እኛም በጦም በኹለንተናችን እንጠቀምና እንለወጥ ዘንድ አስቀድመን በየትኛውም ሕዋሳቶቻችን ላይ ያሉትን አሮጌ ቀለሞች በንስሐ መዶሻ ፈረካክሰን ልንጥላቸው ይገባናል፡፡ ምንም ዓይነት አሮጌ ቀለም በየትኛውም የሰውነት ክፍላችን ላይ ልናስቀር አይገባም፡፡
በዓይን የሚቀር ያረጀ ቀለም (ምኞት)፣ በእጅ የሚቀር ያረጀ ቀለም (ስርቆት)፣ በእግር የሚቀር ያረጀ ቀለም (ወደ ኃጢአት መንደር የሚሄድ ማንነት)፣ ሁለንተናችን ተቀብቶ ማለትም ታድሶ እንዳይታይ ዕንቅፋት ይሆነዋል፡፡ ተቀብተን አሮጌ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ይኸውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዲስ ቁራጭ ባረጀ ልብስ የሚጥፍ የለም እንዳለው ነው፡፡”
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የማቴዎስ ወንጌልን ሲተረጉም በ30ኛው ድርሳኑ የተናገረው)
~ @Tsehaye_Tsidk
104
16:35
15.09.2025
ሁለቱን ሐሳቦች ተረዷቸውና ተጠንቀቋቸው አንደኛው "አንተ ቅዱስ ነህ" የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "መቼም ቢሆን ልትድን አትችልም" የሚለው ነው፡፡
ሁለቱም ሐሳቦች ከጠላት ናቸው፤ በትዕቢትና ተስፋ በመቁረጥ የተሞሉ እውነት የሌላቸው ናቸው፡፡
አንተ ግን ለራስህ ይህን በለው "እኔ ታላቅ ኃጢአተኛ ነኝ ስራዬ በፊቴ ነው ግን አምላክ መሐሪ ነው! ሰዎችንም በጣም ይወዳል፤ ስለዚህ ኃጢአቴን ይቅር ይለኛል፡፡"
አባ ስልዋኖስ ዘአምድ
~ @Tsehaye_Tsidk
58
09:32
16.09.2025
close
Reviews channel
No reviews
New items
Channel statistics
Rating
2.1
Rating reviews
0.0
Сhannel Rating
0
Subscribers:
1.7K
APV
lock_outline
ER
--%
Posts per day:
0.0
CPM
lock_outlinekeyboard_double_arrow_left
shopping_cart
Channels:
0
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Total:
$0.00
Add to Cart
Clear the cart
Are you sure you want to clear the cart?
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.

Clear my cart
Cancel
Комментарий