
Debre Haile St.Raguel General Scondary School
Debre Haile St.Raguel General Scondary School Info.Channel
Channel statistics
ከመጠን ያለፈ በስሜት መዋጥ(መጨናነቅ)/Sensory Meltdown መፍትሄዎችበኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ ህፃናት ላይ የስሜት ህዋሳትን መቆጣጠር ፈታኝ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የሁኔታዎችን ክስተት ለመቀነስና በእንደዚህ አይነት ሁነቶች ውስጥ ድጋፍ ለመስጠት የሚረዱ በርካታ ስልቶች አሉ። 1.ቅድመ መከላከያ ስልቶች 👉ቀስቃሽ ሁኔታዎችን መለየት/Identify Triggers:- የስሜት ህዋሳት ጫና የሚያስከትሉ ሁኔታዎችን ወይም አካባቢዎችን በመለየት ቀስቃሽ ሁኔታዎችን መረዳት። 👉አካባቢን ማስተካከል/Modify the Environment:- በአካባቢው ላይ ማስተካከያ ማድረግ ስንል ድምፅ፣ መብራቶችን እና ሌሎች ስሜት ቀስቃሽ ሁኔታዎችን ማስተካከልና ምቹ የድጋፍ ቦታ ማዘጋጀት ሊያካትት ይችላል። 👉ቋሚና ተገማች የሆነ ከባቢ/Routine and Structure፡- ሊተነብይ የሚችል የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴን ማዘጋጀት ጭንቀትን ለመቀነስ እና ህፃናትን ለሚቀጥለው የክህሎት ሽግግር ለማዘጋጀት ይረዳል። 👉የመቋቋሚያ ክህሎቶችን ማስተማር/Teach Coping Skills:-ልጆች መጨናነቅ ሲጀምሩ የመቋቋሚያ ስልቶችን እንዲማሩ ማድረግ (በጥልቅ መተንፈስ፣ መቁጠር ወይም አሻንጉሊቶችን መጠቀም)። 2.ባህሪውን በሚያሳዩበት ወቅት 👉መረጋጋት/Stay Calm:- የርስዎ ባህሪ የህፃኑን ስሜታዊ ሁኔታ ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ስለሚችል ተረጋግተው የልጁን ሁኔታ መክታተል የበለጠ ልጆችን ለመረዳትና ወሳኝ ነጥቦት ለማወቅ ያስችላል። 👉ቦታ ማመቻቸት/Provide Space:- ከተቻለ ህፃኑ ስሜቱን እንዲያስተካክል የተወሰነ ቦታ ይስጡት። አንዳንዶቹ ብቻቸውን መሆን ሊያስፈልጋቸው ይችላል፣ ሌሎች ደግሞ ከድጋፍ መገኘት ሊጠቀሙ ይችላሉ ስለሆነም ምቹ ቦታ ማመቻቸት አስፈላጊ ነው። 👉በግልጽ ተነጋገሩ/Communicate Clearly:- ቀላል እና ግልጽ ቋንቋ መጠቀም/በጣም ብዙ ቃላትን ወይም ውስብስብ መመሪያዎችን ከመጠቀም ይቆጠቡ። 👉አማራጮችን ማቅርብ/Offer Choices:- ተገቢ ከሆነ የቁጥጥር ስሜታቸውን መልሰው እንዲያገኙ የሚያግዙ ቀላል ምርጫዎችን ማቅርብ (ለምሳሌ፡- ወደ ውጭ መውጣት ወይም ውስጥ መቆየት ትፈልጋለህ?)። 👉ማረጋጋት/Engage in Calming Activities:- እንደየ ልጆቹ ግለሰባዊ ፍላጎት የሚለያይ ቢሆንም የተለያዩ የማረጋጊያ ተግባራትን መጠቀም አስፈላጊ ነው (እንደ ሙዚቃ ማዳመጥ፣ ኳስ መጭመቅ ወይም በጥልቅ ግፊት እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍን የመሳሰሉ የሚያረጋጉ እንቅስቃሴዎችን ይጠቁሙ)። 3.ድህረ-ባህሪ (ባህሪው ከታየ በኋላ) 👉ልጆች ከተረጋጉ በኋላ ምን እንደተፈጠረ ማዎቅና ስሜቶችን እና ቀስቃሽ ሁኔታዎችን ደጋፊ በሆነ መንገድ መርምሩ። 👉የመቋቋሚያ ስልቶችን መገምገምና ለወደፊት ሁኔታዎች እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ማሰብ። 👉ስሜታቸውን ለመቆጣጠር እና አዎንታዊ ባህሪን ለማጠናከር የሚያደርጉትን ጥረት ማጠናከር። በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ ህፃናት እያንዳንዳቸው ልዩ ሲሆኑ ለአንድ ልጅ የሚሰራው ለሌላው ላይሰራ ይችላል። ስለሆነም የልጆችን ግለሰባዊ ልዩ ፍላጎቶች እና ምርጫዎች ለማሟላት የተለያዩ ስልቶችን ማበጀት አስፈላጊ ነው። ✍ትዛዙ አበበ🙏
Reviews channel
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Debre Haile St.Raguel General Scondary School is a Telegram channel in the category «Образование», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 2.1K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 17.5, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 3.6 ₽, and with 2 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий