
- Main
- Catalog
- Religion & Spirituality
- Advertising on the Telegram channel «ስርዓተ ማህሌት»
Advertising on the Telegram channel «ስርዓተ ማህሌት»
አይናችን ነሽ ማርያም አንቺን አይንኩብን የተዋህዶ ልጆች አንወድሻለን ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ በሀሴት ቆመናል ደስታን ስለወለድሽ
Channel statistics
በኩር ናት የበዓላት ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት በእሷ ደስ ይበለን በሰንበተ ክርስቲያንበዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና መልካም ስራ የሚሰራባት ሰንበት ቅድስት ናት እና ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነፃነት እግዚአብሔር ይህን ሰጠን ደስ ይበለን በሰንበት
ለአብርሃም ተገልጣለች ለሙሴም በደብረ ሲና በነቢያት የታወቀች ሰንበት ዳራዊት ናት እና በሳምንቱ ሰለጠነች ተሰበከች በሐዋርያት ሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት ተሰጠችን ልናርፍባትበእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍር በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ በመቅደሱ ናቸው እና ቅዱስነትና ግርማ ውዳሴያችን ይሰማልን ከምድር እስከ እዮር እራማ
እግዚአብሔር አብ የባረካት እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት ከእለታት ሁሉ መርጦ መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት በእርሷ ሀሴት እናድርግ እናክብራት እንድንከብር የደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብዲ/ን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
❝አቤቱ ከቤትህ በረከትን እንጠግባለን። ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነው፤ በእውነት ድንቅ ነው❞— ሲል ዘምሯል። ቤተ መቅደሱን ቅዱስና ድንቅ ያደረገው አሠራሩና የሥነ ሕንጻ ውበቱ አይደለም። በውስጡ የሚከናወነው ሥርዓት አምላካዊና ዘለዓለማዊ ሥርዓት በመሆኑ ነው (መዝ ፷፬፥፭)። ነቢዩ ዳዊት ከቤትህ በረከትን እንጠግባለን ያለውን ቃል ነቢዩ አብድዩ ደግሞ:-
❝በቅዱስ ተራራዬ ላይ እንደጠጣችሁ ሁሉ አሕዛብ ዘወትር ይጠጣሉ❞— በማለት አሕዛብ አምነው ተጠምቀው በመቅደሱ የሚቀዳውን የአምላክ ክቡር ደሙን ጠጥተው ቅዱስ ሥጋውን በልተው እንደሚጠግቡ ተናግሯል (አብድዩ ፩፥፲፮)። ዳግመኛም ወደ እግዚአብሔር የሚያርገውን መሥዋዕትና ቁርባን የሚቀድስ ስለሆነ ነው። ሊቀ ነቢያት ሙሴ እንዲህ እንዳለ:-
❝ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው እንስሳም ቢሆን ሰው ከእነዚህ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል❞— በማለት ቤተመቅደስ ቅዱስ በመሆኑ በውስጡ የሚቀርበውን መሥዋዕት ሁሉ እንደሚቀድስ ተናግሯል (ዘሌዋ ፳፯፥፱)። ስለዚህ ቤተመቅደስም የእግዚአብሔር ዙፋን ስለሆነ ንጉሥ በዙፋኑ ተቀምጦ በበደለ ይፈርድበታል፤ ለተበደለ ይፈርድለታል፤ ካሣ ያስከፍልበታል፤ የቀማውን ያስመልስበታል፤ ዕርቀ ሰላም ያውጅበታል። እግዚአብሔርም ቤተመቅደሱን ዙፋን አድርጎ ወደ እርሱ የተጮኸውን ጩኸት የተዘመረውን መዝሙር ያዳምጥበታል፤ የቀረበውን መሥዋዕት ይቀበልበታል፤ የሰውን እንቆቅልሽ ይፈታበታል፤ የሕዝቡን ዕንባ ያብስበታል፤ በካህናትና በጳጳሳትም ላይ እያደረ መንፈሳዊ ዳኝነት ይሰጥበታል፡፡ ነቢዩ ዳዊት ሲዘምር:-
❝እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድሀ አደጎች አባት፤ ለባልቴቶች ዳኛ ነው❞— በማለት በቅዱስ ቦታው የአባትነት ሥራና የዳኝነት ተግባር እንደሚሠራ ተናግሯል (መዝ ፳፯፥፭)። ስለዚህ እንኳን የሰማያዊውን ንጉሥ ቤት ቀርቶ የምድራዊ ንጉሥ ቤት ይከበራልና የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ልናከብረው፣ ልንፈራው ይገባል። እግዚአብሔር የቤተመቅደስን ክብር ለሙሴ ገልጦለታል፡፡ ልበ አምላክ ዳዊትም ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የአክብሮት ስግደት እንደሚገባ ሲናገር:-
❝ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መረገጫ ስገዱ፤ በቅዱስ ተራራውም ስገዱ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና❞— በማለት ለእግዚአብሔር ያለንን ክብርና ፍቅር ከምንገልጥበት መንገድ አንዱ መቅደስ ውስጥ በምናደርገው አምልኮትና አገልግሎት መሆኑን ተናግሯል፡፡ እግዚአብሔር ረቂቅ መንፈስ ነው፤ እኛ ግዙፋን ነን፥ እርሱ ምሉዕ ነው፤ እኛ ውሱኖች ነን፥ እግዚአብሔር እርሱ በፈቀደውና በወደደው መንገድ እየተገለጠ፤ እኛ ለእርሱ ያለንን ፍቅርና አክብሮት፥ እርሱ ለእኛ ያለውን ፍቅርና አክብሮት የሚገልጠው በመቅደሱ ነው ምክንያቱም እኛ ለእግዚአብሔር ያለን ክብር ለመግለጥ እንስገድለት ቢባል ከመቅደሱ ውጭ የት ልንሰግድለት እንችላለን፤ እኛ ምድራውያን የሰው ልጆች በአየር ላይ መስገድ አንችልምና ስለዚህ ለባሕርያችን የሚስማማ ኮእግዚአብሔር ጋር ሊያገናኘን የሚችል የተወሰነ ምድራዊ ቦታ ያስፈልግ ስለነበር ቤተመቅደሱን አክብሮ ሰጠን (መዝ ፺፰፥፭ ና ፱) ስለሆነም ቤተመቅደስ ሰዎችንና መላእክትን በአምልኮተ እግዚአብሔር የሚያገናኝ ድልድይ ነው፤ የመላእክትና የሰዎች ሕብረት መስብሰቢያ ሰማያዊና ምድራዊ አዳራሽ ነው፤ ነቢዩ ዳዊትም:-
❝በመላእክትህ ፊት እዘምርልሃለሁ፤ ወደ ቅዱስ መቅደስህም እሰግዳለሁ። ስለምሕረትህ ስለእውነትህ ስምህንም አመሰግናለሁ❞— በማለት ዘምሯል (መዝ ፻፴፯፥፪)። ዳዊት መላእክትን የት አግኝቷቸው ነው በፊታቸው የዘመረው? የሚል ጥያቄ ቢነሣ ቅዱሳን መላእክት በቤተመቅደስ ስለሚገኙ በመቅደሱ ቆሞ ያመስገነውን ምስጋና ሲናገር ነው፡፡ ዛሬም ቅዱሳን መላእክት ዘወትር በቤተ ክርስቲያን በማኅሌት፣ በቅዳሴና በልዩ ልዩ አገልግሎቶች እንደማይለዩን ሊቃውንት ይናገራሉ፤ በተለይ በቅዳሴ ጊዜ አሐዱ አብ ቅዱስ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ፍጻሜው ድረስ እንደ ሻሽ ተነጥፈው፤ እንደ ቅጠል ረግፈው እንደ ግንድ ተረብርበው የቅዳሴውን ሥርዓት እንደሚሳተፉና የተሠዋውን መሥዋዕት የቀረበውን ቁርባን የታጠነውን ዕጣን እንደሚያሳርጉ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ መፍቀሬ ጥበብ ሰሎሞንም ታላቁን ቤተመቅደስ ሠርቶ ሲጨርስ እግዚአብሔር አምላክ ተገልጦ በታነጸው ቤተ መቅደስ መደሰቱን እንዲህ ሲል መስክሮለታል:-
❝በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዐይኖቼ ይገለጣሉ፤ ጆሮቼም ያዳምጣሉ አሁንም ስሜ ለዘለዓለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጬዋለሁ ቀድሼዋለሁ ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ❞— ሲል ተናግሯል (፪ኛ ዜና ፮፥፲፮)። ለጊዜው ለሰሎሞን ቤተመቅደስ ቢሆንም ፍጻሜው ግን በየጊዜው በስሙ የተሠሩትንና ወደፊትም የሚሠሩትን አብያተ ክርስቲያናትን ሲናገር ነው:: ስለዚህ ማለዳ ተነሥተን ወደ ቤተመቅደስ የምንገሠግሠው የእግዚአብሔር ዐይኖች በዚያ ናቸው ብለን ነው:: ዘወትር በመቅደሱ ተገኝተን ደጅ የምንጠናው፤ የእግዚአብሔር ልብ በዚያ አለ ብለን ነው:: አሁን «ዐይኖቼ በዚያ ይሆናሉ» ሲባል የእግዚአብሔር ዐይኖች በሌላ ስፍራ የሉም ወይም ሌላ ስፍራን አያዩም ማለት አይደለም፤ ዐይኖቹ የሌሉበትም ስፍራ የለም። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ:-
❝በእኛ በሚቆጣጠር በእርሱ ዐይኖቹ ፊት ሁሉ ነገርየተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ የተሠወረ ፍጥረት የለም❞— ዕብ ፬፥፲፫ በማለት የእግዚአብሔር ዐይኖች ፍጥረታትን ሁሉ እንደሚያዩ ተናግሯል:: ነገር ግን ‹‹ዐይኖቼ በዚያ ይሆናሉ›› ማለቱ የምሕረትና የረድኤት ዐይኖቹ በመቅደሱ መኖራቸውን ሲነግረን ነው። እናስተውል! (፫/፫) ዲ/ን ኃይለራጉኤል
❝በምድር ላይ እንደተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደተጣራ የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው❞— (መዝ ፲፩፥፮) ብሎ እንደተናገረው የእግዚአብሔር ቃል እንደ ፍጡራን ቃል የሚለዋወጥ፣ የሚነዋወጥ፣ የሚቀያየር፣ የሚስረዝ፣ የሚደለዝ፣ በየጊዜውም እርማት የሚያስፈልገው አይደለም። አይታረምም አይገመገምም፤ ጥርጥር የሌለበት የማይለወጥ የማይናወጥ ለዘለዓለም የጸና፤ የተደላደለ ቃል ነው። ይኸውም ቅዱስ ወንጌል ነው። ወንጌላዊ ማርቆስ እንዲህ እንዳለ:-
❝ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ራሱ ለዘለዓለም ድኅነት የሆነውን የማይለወጠውን ቅዱስ ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ በእጃቸው ላከው❞— በማለት ለታመሙት ፈውስ፣ ለደከሙት ኀይል፣ የሚሆን ሥርየተ ኀጢአት የሚያሰጥ የመንግሥተ ሰማያት ዜጋ የሚያደርግ ይህንን የረከሰውን ዓለም የሚቀደስ ቅዱሱን ወንጌል ለዓለም ስበኩ አልጫውን ዓለም በቃለ ወንጌል ጨውነት አጣፍጡ፤ ጨለማውን ግለጡ ብሎ በሐዋርያት እጅ እንደላከው ነግሮናል (ማር ፲፮፥፰)። ይህ ቅዱስ ወንጌል እንደ ፍጡራን ድርሰቶች በጊዜ ሂደት አይለወጥም፣ አይፋለስም፣ አይሰረዝም፣ አይደለዝም፣ አይሻርም፣ አያልፍም፣ አያረጅም:: የቃሉ ባለቤት እንዲህ ሲል እንዳስጠነቀቀን:-
❝እውነት እላችኋለሁ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፤ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ እንግዲህ ከእነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉም ታናሽ ይሆናል❞— በማለት አሳስቦናል (ማቴ ፭፥፲፰)። አሁን «ከትእዛዛቱ አንዲቱን የሚሽር በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉም ታናሽ ይሆናል» ማለቱ በመንግሥተ ሰማያት ትንሽ ትልቅ እየተባለ በተዋረድ መኖር የሚባል ነገር የለም፤ በመንግሥተ ሰማያት በሚሰጠው ዋጋ ታናሽ ተብሎ ተፈርዶበት ወደ ሲኦል ይጣላል ሲል ነው:: ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ከሚያልፍ ይልቅ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል ያለው የቃሉን ክብርና ዘለዓለማዊ ቅድስናውን ሲናገር ነው:: ይህ ቅዱስ ቃል ሸክማችንን የሚያቀልል፤ የተቆረጠውን ተስፋችንን የሚቀጥል፤ ነውራችንን የሚያንከባልል፤ ወጥመዳችንን የሚበጥስ፤ ዕንባችንን ከዐይናችን ላይ የሚያብስ፤ የቆሰለውን ልባችንን የሚፈውስ፤ የተሰበሩትን የሚጠግን፤ እንቆቅልሻችንን ሁሉ የሚፈታ፤ ከድካም የሚያበረታ፤ ለጥያቄዎቻችን ሁሉ መልስ የሚያመጣ፤ ኀዘናችንን ለደስታ ጭንቀታችን ለእርጋታ የሚለውጥ፤ ውስጣችንን በደስታ የሚሞላ፤ ዕለት ዕለት የምንጋተው የእግዚአብሔር ቃል ወተት፣ የምንጎርሰው የእግዚአብሔር ቃል ፍትፍት፣ የምንበላው የእግዚአብሔር ቃል እንጀራ የምንጠጣው የእግዚአብሔር ውኃ፣ የምንቆርጠው የእግዚአብሔር ቃል ጮማ የምንጎነጨው የእግዚአብሔር ቃል ወይን ነው። ምስጋናውም ቅዱስ ነው ምስጋናውም እንደ ወንጌሉ ቅዱስ ነው ስንል ለእግዚአብሔር የምናቀርበው ምስጋና ለፍጡራን ከሚቀርቡ ምስጋናዎች ሁሉ የተለየና የተቀደሰ ስለሆነ ነው:: አንድ ምስጋና የተቀደሰ ሊያደርገው የሚችለው ቅድሚያ ሦስት አካላት መቀደስ ሲኖርባቸው ነው። እነዚህም አመስጋኙ፣ ተመስጋኙና ምስጋናው ናቸው:: ይህ ማለት መጀመሪያ ምስጋናውን የሚያቀርበው አካል የተቀደሰ መሆን አለበት፤ እንዲሁም ምስጋና የሚቀርብለት አካልም ሆነ ምስጋው የተቀደስ መሆን አለበት:: ምስጋናው መቀደስ አለበት ሲባል የምስጋናው ይዘት ከአመስጋኙና ከተመስጋኙ ጋር ሲመጣጠንና ሲዛመድ ምስጋናው የተቀደስ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ምስጋና ለማይገባው አካል የሚቀርብ ከሆነ ምስጋናው ከንቱ ውዳሴ እንጂ የተቀደስ ምስጋና አያሰኝም:: የእግዚአብሔር ምስጋና ግን «ቅዱስ ነው» የምንለው ከዚህ ሁሉ የተለየ ነው:: የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ምስጋና ምትክ ልክ፤ አቻ አምሳያ የሌላት አንዲት መሆኗ ነው:: ይኽቺውም ማንም የማይቋደሳት መለኮታዊ የባሕርይ ምስጋና ናት:: ነቢዩ ኢሳይያስ የእግዚአብሔርን ክብርና ምስጋና ለሌላ መስጠትም ሆነ በሌላ መተካት እንደማይቻል ሲናገር:-
❝አነ እግዚአብሔር አምላክከ ከመዝ ስምየ ወኢይሁብ ክብርየ ለባዕድ ወኢስብሐትየ ለግልፎ — እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜም ይህ ነው። ክብሬን ለሌላ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልስጥም❞— ሲል ንጉሥ በመንግሥቱ፤ ባላባት በርስቱ፤ ጎልማሳ በሚስቱ ቀናተኛ እንደሆነ፤ አምላክም በአምላክነቱ ቀናተኛ ነውና የባሕርይ ጌትነቱን፣ ክብሩንና ምስጋናውን አሳልፎ ለፍጡር መስጠት እንደማይገባ ያስጠነቅቀናል (ኢሳ፵፥፰)። እግዚአብሔር የሚመስገንበት ምስጋና የተለየ እንደሆነ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ መጽሐፈ ኪዳንን ሲያስተምራቸው:-
❝ወብርሃነ ለነ ዘኢይጠፍእ አሰፎከነ ስብሐተ ወአኰቴተ ንፌኑ ወቅድሳተ ንጹሐ፡፡ ንብል ንሕነ እሊአከ አግብርት:: ወሕዝብኒ ኪያከ ይሴብሑ — ከተሰጠ የማይነጠቅ ካደረ የማይለይ ዕውቀት እሰጣችኋለሁ፤ የማይመረመር ክብርን አወርሳችኋለሁ ብለህ የተናገርህ አንተን እናመስግንሃለን፤ ላንተ ምስጋና እናቀርባን:: ስቡሕ እኩት ቅዱስ እያልን ፍጹም ምስጋና እናቀርብልሃለን እኛ ቤተሰቦችህ ባሮችህ አገልጋዮችህ ባለሟሎችህ እኛ ቀሳውስት እንዲህ እያልን እናመስግንሃለን❞— በሉኝ ሲል ተናግሯል፡፡ «ንጹሕ ምስጋና» ማለቱ በዚህ ምስጋና ፈጣሪ እንጂ የትኛውም ፍጡር አይመስገንበትምና:: ሁለተኛ እግዚአብሔር የሚመስገነው ቅድስና ባለው አካል በመሆኑ ነው:: ለዚህ የመጀመሪያ ተጠቃሽ የሚሆኑት ምስጋናቸው ዕረፍት፥ ዕረፍተቸው ምስጋና ሆኖላቸው የሚኖሩ ቅዱሳን መላእክት ናቸው። እነርሱ ከቅዳሴ ውጭ ሌላ ግብር ስለሌላቸው እነርሱም ቅዱሳን ናቸው፤ ቅዳሴያቸውም ቅዱስ ነው:: ነቢዩ አሳይያስ መሠረታዊ ግብራቸው ሰማያዊ ምስጋናቸው ምን ይመስል እንደነበር ሲናገር:-
❝እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው። በኹለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር። በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር:: አንዱም ለአንዱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር:: የመድረኩም መሠረት ከጭዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ ቤቱንም ጢስ ሞላበት❞— በማለት የመላእክት መደበኛ ግብራቸው በቅዱስ ልሳናቸው ቅዱስ ምስጋና ለቅዱስ እግዚአብሔር ማቅረብ መሆኑን ነግሮናል (ኢሳ ፮፥፩ ፤ ራእ ፬፥፰)። (፪/፫) ( የዚህ ጽሑፍ ክፍል ፫ ከስር ባለው ጽሑፍ ይቀጥላል ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️)
«እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ»— በማለት ስለማስተማሩ ሰፊ ትምህርት ይሰጥበታል፡፡ እግዚአብሔርን ማየትና የእግዚአብሔር የሆነውን ሥርዓት መከተል ስለሚያስችል ዕለት ዕለት መልካም በማድረግ ቤተ-መቅደስ ተብሎ የተነገረለትን ሰውነታችንን በንጽሕና በመጠበቅ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕቃ ሆነን መቅረብ እንደሚገባን ይዘከርበታል። እግዚአብሔር አምላካችን ቅዱስ ነው እያልን በልባችን አምነን በአፋችን መስክረን በተግባር ግን ከቅድስና ርቀን እንዳንኖር እግዚአብሔር እንደቀደሰንና ልጅነትን እንደሰጠን በማመን በተቀደስ ሁኔታ መኖር ይገባናል። ለመሆኑ ቅድስና ምንድነው? «ቅድስና» ማለት ቀደሰ፣ ባረከ፣ ለየ፣ አከበረ፣ አመሰገነ፣ አነጻ፣ ሰውነቱን ከርኩሰት ልቡን ከትዕቢት አራቀ ... ከሚለው ከግዕዝ ሥርወ ግሥ የተገኘ ኀይለ ቃል ሲሆን ቅድስና ማለት መለየት፣ መክበር፣ መመስገን፣ መንጻትና መጽናት ማለት ነው። ሰውም ሆነ ሌላውም ነገር ቅዱስ የሚሆነው የእግዚአብሔር ስለሚሆን ብቻ ነው። ሰው ሃይማኖት ይዞ በሥነ ምግባር እየተቀደሰ ሊሄድ ይችላል (ዮሐ ፲፯፥፲፯) ፤ ዳግመኛ የሰው ልጅ ከመንፈስ ቅዱስ ሲወለድ የቅድስና ሥራ ይጀምራል። በሕይወቱ ደግሞ ቅድስናውን እያሳደገ ይሄዳል፤ በስተመጨረሻም በዕለተ ምጽአት ቅድስናው ፍጹም ይሆናል (፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፶፩ ፤ ፩ኛ ተሰ ፬፥፬) ፤ ቅድስና በአማኝ ሕይወት ውስጥ የሚያድገው በእግዚአብሔር ኀይል ነው። ነቢዩ ሕዝቅኤል:-
❝መቅደሴ ለዘለዓለም በመካከላቸው በሆነ ጊዜ እኔ እስራኤልን የምቀድሰው እግዚአብሔር እንደሆንኩ አሕዛብ ያውቃሉ❞— በማለት ተናግሯል (ሕዝ ፴፯፥፳፰)። የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ በመሆኑ በፍጹም ኀይሉ በፍጹም ነፍሱ በፍጹም ልቡ እግዚአብሔርን መውደድ አለበት:: ቅድስናውና ፍቅሩ ደግሞ ትእዛዙን በመጠበቅ ይገለጣል (ማር ፲፪፥፴፫ ፤ ዮሐ ፲፬፥፳፩ ፤ ፊል ፪፥፲፪ ፤ ዘሌዋ ፲፱፥፪ ፤ ፩ኛ ዼጥ ፩፥፲፭)። የእግዚአብሔር ቅድስና ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ የሚመሰገን የቅድስና ሁሉ ምንጭ፤ በባሕርዩ የተቀደሰ፤ ከፍጥረት ያልተለገሰ፤ ቅድስናውን ጾሞ ጸልዮ ወድቆ ተነሥቶ ተዋግቶ ተሟግቶ ያልተቀበለው፤ ቅድስናው የባሕርዩ የሆነ ቅዱሳንን የሚቀድስ የቅዱሳን ሁሉ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው፡፡ ኀጢአት ለባሕርዩ የማይስማማው፤ ነውር ነቀፋ የማይገኝበት በባሕርዩ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር አምላክ ብቻ ነው:: ቅድስናው የማይረክስና የማይጓደል እስከ ዘለዓለምም ቅዱስና ሕያው ሆኖ የሚኖር እግዚአብሔር ብቻ ነው:: ሊቀ ነቢያት ሙሴ እንዲህ እንዳለ:-
❝አቤቱ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማነው? በምስጋና የተፈራህ፣ ድንቅንም የምታደርግ፣ በቅድስና የከበረ እንደ አንተ ያለ ማነው?❞— በማለት አምላከ አማልክት እግዚአ አጋዕዝት እግዚአብሔር በቅድስና የከበረ መሆኑን ተናግሯል (ዘጸ ፲፭፥፲፩) ፤ መተርጉማን «ቅዱስ» የሚለውን ቃል ለእግዚአብሔር ሰጥተው ሲተረጉሙት በአምልኮት ጽኑዕ፣ በሰውና በመላእክት አንደበት ምስጉን፣ ከአማልክት ሁሉ ልዩ፣ ኀያል እምድካም፣ ባዕል እምንዴት ማለት ነው ይላሉ:: የሳሙኤል እናት ነቢይት ሐና ለተደረገላት ቸርነት በደስታ ስትዘምር:-
«እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ የለም»— በማለት የእግዚአብሔር ቅድስና እንደ እስትንፋስ ሳያቋርጥ እንደ ምንጭ ውኃ ከባሕርዩ ሲፈልቅ የሚኖር በቅድስና የሚመስለውና የሚተካከለው እንደሌለ መስክራለች (፩ኛ ሳሙ ፪፥፪)። ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስም በራእዩ ሲናገር:-
❝ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ መንገድህ ጻድቅና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና የጽድቅም ሥራህ ስለተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ በፊትህም ይሰግዳሉ እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ❞— በማለት የእግዚአብሔር ቅድስና የእርሱ ብቻ እንደሆነ መስክሯል (ራእ ፭፥፫)። ነቢዩ ኢሳይያስም የዮሐንስን ቃል ሲጋራ እንዲህ ብሎናል:-
❝እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ ይላል ቅዱሱ❞— በማለት እግዚአብሔርን በቅድስና የሚመስለው በባሕርይ የሚተካከለው አቻ አምሳያ እኩያ ባልንጀራ የሌለው ብቸኛ አምላክ መሆኑን ነግሮናል (ኢሳ ፵፥፳፭)። እግዚአብሔር ስሙ ቅዱስ ነው እግዚአብሔር በባሕርዩ ቅዱስ በመሆኑ ስሙም ከስሞች ሁሉ የበለጠ የተለየ፤ የተከበረ፤ የተፈራና ከፍ ያለ ቅዱስ ስም ነው:: ለዚህም ነው «የእግዚአብሔር ስም በከንቱ አትጥራ!» ተብለን የታዘዝነው። የእግዚአብሔርስም ቅዱስ በመሆኑ እንዲሁ በከንቱ ሊጠራ አይገባም:: ነቢዩ ዳዊት:-
❝ስሙ የተፈራና የተቀደሰ ነው❞— በማለት ዘምሯል (መዝ ፻፲፥፱)። ነቢየ ልዑል ኢሳይያስም ስለእግዚአብሔር ቅዱስ ስም ሲመስክር:-
«ዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ»— በማለት ቅድስናው የማያልቅ፣ የማይነጠቅ፣ ማንም የማይሳተፈው የዘለዓለም ቅዱስ ስም መሆኑን ተናግሯል (ኢሳ ፶፮፥ ፲፩)። ቅዱሱን የወለደችው የቅዱሱ እናትም እመቤታችንም ልጇን ወዳጇን ባመሰገነችበት ምስጋናዋ ላይ እናታዊ ምስክርነት ስትሰጥ:-
❝ስሙም ቅዱስ ነው፤ ምሕረቱም ለሚፈሩት ለልጅ ልጅ ነው❞— በማለት የድርሻዋን መስክራለች (ሉቃ ፩፥፶)። ይህን ቅዱስ ስም መጥራት ይቀድሳል፣ ያከብራል፣ ይለያል፣ ያጸናል፣ ያነጻል። ባለቤቱም:-
❝ቅዱስ ስሜን አረከሱ፤ እኔ ግን የእስራኤል ቤት በመጡባቸው በአሕዛብ መካከል ስላረከሱት ለቅዱስ ስሜ ስል አራራለሁ❞— በማለት ስለቅዱስ ስሙ ሲል በስሙ ለሚማፀነት ሁሉ ምሕረት እንደሚያደርግ ተናግሯል (ሕዝ ፴፮፥፳)። በአፈ መላእክት የሚመስገነውና የሚቀደሰው አምላክ በልሳነ ሰብእም ቢሆን:-
❝ይትቀደስ ስምከ — ስምህ ይቀደስ❞— ብለን እንድናመሰግነው የቅድስና ባለቤት እግዚአብሔር አስተምሮናል:: ለዘለዓለም በስሙ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እየተባለ ይመስገናል (ራዕ ፬፥፰)። ስሙ ቅዱስ የሆነ ፈጣሪም በቅድስናው የእርሱ የሆኑትን ሁሉ ይቀድሳል (ዘጸ ፳፰፥፵፩)።
❝ስሙን መጥራት ይቀድሳል እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው፤ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ❞— የተባለውም ለዚህ ነው (፩ኛ ዜና ፲፮፥፲)። ነቢዩ ዳዊትም:-
❝ግሩምና ቅዱስ ነውና ሁሉም ታላቅ ስሙን ያመስግኑ❞— መዝ ፺፰፥፫ ብሏል፡፡ ራሱ እግዚአብሔርም ለሙሴ:-
❝የተቀደሰውን ስሜ እንዳያረክሱ ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው!❞— ሲል መመሪያ እንደሰጠው እንመለከታለን (ዘሌ ፳፪፥፪)። (፩/፫) (የዚህ ጽሑፍ ክፍል ፪ እና ፫ ከስር ባሉት ጽሑፎች ይቀጥላል ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️)
Reviews channel
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «ስርዓተ ማህሌት» is a Telegram channel in the category «Религия и духовность», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 3.4K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 12.4, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 12.0 ₽, and with 1 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий