
- Main
- Catalog
- Books, Audiobooks & Podcasts
- Advertising on the Telegram channel «ከፍልስፍና ዓለም™»
Advertising on the Telegram channel «ከፍልስፍና ዓለም™»
አዋቂ ሰው ማለት ፍላጎቱን የመግታት እውቀቱ ከፍተኛ የሆነ ማለት ነው በሕይወት ዝቅተኛው ደረጃ ራስን በፍላጎት አጥር ውስጥ ማስቀመጥ ነው አብዛኛው የሰው ልጅ በብዙ ፍላጎትና በጥቂት እውቀት የተሞላ ነው ፤ አዋቂነት ግን ብዙ እውቀትና ጥቂት ፍላጎት ብቻ ይበቃታል አርተር ሾፐንሀወር
Channel statistics
Full statisticschevron_rightአለማችን ላይ ካሉ ተፈጥሯዊ ሃይሎች ሁሉ ምናብ እንደ ትልቁ የሰዉ ልጅ ዝግመተ ለዉጥ ስኬት መታየት የሚችል ገፀበረከት ነዉ፤ የሚፈጠረዉም የሰዉ ልጅ በአከባቢዉ የሚያገኘዉን እና ያየዉን እዉነታ እንደ መጨረሻ ላለመቀበል ሲዳዳዉ እና በተፈጥሮ ካለዉ ባይሎጂካዊ ስብጥር እርቆ ሲከንፍ ነዉ፤ በእሱም የተነሳ የህልዉና ተዋንያን እና ከዋኒያን ብቻ ሳይሆን ፀሃፊም ለመሆን በቅተናል።
ዝግመተ ለዉጥና ምናብ
ሌሎች እንስሳዎች እራሳቸዉን ለአከባቢያቸዉ ተስማሚ ሲያረጉ የሰዉ ልጅ ግን በተቃራኒዉ አከባቢዉን ለራሱ ተስማሚ ያረገ ብቸኛ እንስሳ ነዉ።ይህ የተፈጥሮን ተፈጥሮአዊ ሂደት እስከ ማስቀየስ ያበቃዉ ገደብ የለሹ የሰዉ ልጅ ምናብ ነዉ፤ገና ድሮ ድንጋይ ለ መሳሪያነት ሳያገለግል፣ እሳት በብልጭታ መልክ በሰዎች ቁጥጥር ስር ሳይዉል በፊት የሌሉትን እና የማይታዩትን ነገር በምናብ ስሎ ወደ ማኖር ያመጣ፤ደመነፍስን ወደ ፈጠራ፣ትዉስታን አርቆ ወደ ማሰብ እና ማሰላሰል ድልድይ ሆኖ ያሻገረ በገደቦች ላይ ያመፀ የሰዉ ልጅ አይምሮ አፀግብሮት ነዉ።በምናብ የተነሳም በአካላችን ላይ ብቻ ሳይሆን በህልዉናችን ላይ ብዙ ለዉጦችን ፈጥረናል! በዚህም ምክንያት የዉስብስብ ሃሳቦች ባለቤት እስከመሆን ደርሰናል።
የጀርመኑ ፈላስፋና የታሪክ ተመራማሪ Ernest Cassirer ሰዎችን Animal symbolicum(The symbolic animal) ወይም ተምሳሌታዊ እንስሳ ነዉ በማለት የ ጥንቱን የአርስቶትል ሰዉ ምክንያታዊ እንስሳ ነዉ የሚለዉን እሳቤ ሞግቷል፤ በዚህ እሳቤዉም የሰዉ ልጆች እንደ ሌሎች እንስሶች ተፈጥሮን እንደ ወረደች በደመነፍስ እና በስሜት ተቀብለዋት ምክንያታዊነትን ብቻ ጨምረዉ የሚኖሩ ሳይሆኑ በፈጠሩት ተምሳሌታዊ አለም ዉስጥ የሚኖሩ እንስሶች ናቸዉ ሲል አስተላልፏል። ይህም ተምሳሌታዊ አለም ቋንቋ፣አፈታሪክ፣ስነ ጥበብ እና ሳይንስን ያካተተ ሲሆን እነዚህም መሳሪያ ብቻ ሳይሆኑ ከተፈጥሮ ጋር መስተጋብር የፈጠርንባቸዉ እና የምንመለከትባቸዉ ሌንስዎችም ናቸዉ ይላል። በዚህም እሳቤ ዉስጥ የሰዎች መለያ ምክንያታዊ የሆነ ተፈጥሯቸዉ ሳይሆን ተምሳሌታዊ የሆነ አለምን መፍጠር የመቻል አቅማቸዉ ነዉ ሲል ተናግሯል።
ፍልስፍና እና ምናብ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች
በፍልስፍናዉ ዘርፍም ምናብ የንቃተ ህሊና መሰረት እንደሆነ ተደጋግሞ ይነገራል፤ David Hume እይታዎችን እና የተበጣጠሱ ሃሳቦችን አዛምዶ ወጥ የሆነ ምስል የሚሰጠን ነዉ ሲል ይገልፀዋል፤በአንፃራዊነት Immanuel Kant ደሞ የመረዳትን ንድፈሃሳብ የሚፈጥር እይታን ከምክንያት ጋር አገናኝቶ እዉቀትን የሚሰጠን መሳሪያ ነዉ ሲል ይገልፀዋል፤Paul Sartre ደሞ ምናብ የነፃነት መወለጃ ስፍራ ነች ሲል የምናብን የገነነ ሃይል አሻግሮ ያሳያል አያይዞም አሁን ላይ ሊሆን ያልቻለዉን እና የሌለዉን ነገር በምናብ አሻግረን በመመልከታችን "የአሁን" እስረኛ እንዳልሆንን ማረጋገጥ እንችላለን በዚህም የተነሳ በምርጫችን ወደፊታችንን እንሰራዋለን ሲል ይገልፃል።
ለዚህም ነዉ ምናብ የሰዎች ቅንጦት ሳይሆን የህልዉናቸዉ መሰረት የሆነዉ፤ ተፈጥሮ ባዶነትን ስትጠቁም የሰዉ አይምሮ እሱን ለማካካስ ትርጉም፣እሴት፣ግብ እና ስርአትን ይፈጥራል።እያንዳንዱ ፍልስፍና፣ስርአት እና የሞራል ኮድ ሳይቀር በምናብ የተቀረፁ ዉጥንቅጡ በወጣ ተፈጥሮ ዉስጥ እራሱን አቀናጅቶ ለመመራት የሰዉ ልጅ የፈጠራቸዉ ነገሮች ናቸዉ ።
ምናብ እንደ ነፃነትም እንደ ግዳጅም
ምናብ ነፃ ያወጣል ለስቃይም ደሞ ምንጭ ሊሆን ይችላል፤በምናብ ማነብነብ ህይወት የተሻለች ልትሆን እንደምትችል፣እዉነታ ከዚም ሊጠልቅ እንደሚችል እኛ እራሳችን አሁን ነን ብለን ከምናስበዉ በላይ ልንሆን እንደምንችል አሻግሮ ማየት ነዉ። ምናብ ጥበብን ሊወልድ ይችላል ጭንቀትንም እንደዛዉ ዉጤቱም የድላችን ወይ የመጥፊያችን ሊሆን እንደሚችል በመረዳት ዉስጥ ነዉ፤ አልበረት ካሙስ ይህን ዉጥንቅጥ አይቶ ከተረዳ ቡሃላ ነበር የሰዉ ልጆች እራሳቸዉን መሆን እና ተፈጥሯቸዉን ለመኖር አሻፈረኝ ያሉ ፍጡሮች ናቸዉ ያለዉ፤ ምናብ በራሳችን ተፈጥሮ ላይ እንድናምፅ አርጓናል ተፈጥሮም እንዳረገች ታርገን ብለን እጃችንን አጣጥፈን እንደ ሌሎቹ እንስሳት መሆን ተስኖናል።
በምናብ ስቃይን ስያሜ ፈጥረንለታል፣ዉጥንቅጥን መስመሮች አበጅተንለታል ለሞትም ትርጓሜን ሰጠነዋል።ተፈጥሮ ትርጉም አልባ ስትመስል እራሱ በምናብ ትርጉሞችን ፈጥረንላታል፣ እዉነታን በማምለጥ ሳይሆን እዉነታን በራሳችን መንገድ አስማምተን ሰፍተነዋል እናም ያ ብቸኛዉ ትርጉም አልባ በሆነቺዉ አለም ላይ ትርጉም መፍጠሪያ መሳሪያችን ነዉ።
የምናብ ተፈጥሯዊ ዉበት
ኪነ ጥበብ፣ሳይንስ፣ፍልስፍና ሁሉም የምናብ ዉበት መገለጫዎች ናቸዉ። ቅርፅ የሌለዉን ቅርፅ ለመስጠት የሚደረግ ግብግብ! የሰዉ ልጅም በዚህ ዉስጥ ተፈጥሮን ዝምብሎ አይመለከታትም ያሰባጥራታል እንጂ። እያንዳንዱ እየታዉም በይሁን እና በስሜት ዉስጥ የታሸ ነዉ። በምናብ መጓዝ ማለት ማቆሚያ የሌለዉ የእዉነታ ፈጠራ ጉዞ ላይ መሳተፍ ማለት ነዉ!
Friedrich Nietzscheም ይህን በመረዳት ነበር "we have an art in order not to perish from the truth" ያለዉ ምናብ ከ ተፈጥሮ ጥሬ ትርጉም አልባነት ( nihilism) ማምለጫ መንገድ ይሆነን ዘንድ ጥሬ እወነትን በዉበት፣ዉጥንቅጥን ቅርፅ በማስያዝ፣ህልዉናን በልምድ እየተካ ያልነበረዉን እንደነበር እያረገ ለሰዉ ልጆች ምሶሶ ሲመሰርት የኖረ የሰዉ ልጅ ሁነኛ አጋር እና አገልጋይ ነዉ።
ምናብ የአይምሮ ዉጤት ነዉ!
ምናብ ከሆነ አካል የተሰጠን ተአምር ሳይሆን ከ1200-1500 ኪዉቢክ ሜትር መጠነ ይዘት እስከ 1.4 ኪግ ክብደት ባለዉ እና 86 ቢሊየን ህዋሰ ነርቮችን በያዘዉ የሰዉ ልጅ ጭንቅላት ቀፎ ዉስጥ በሚፈጠር ተአምራዊ አፀግብሮት የሚወለድ ትልቁ በረከታችን ነዉ።
በሱም ስልጣኔዎችን ቀልሰናል፣አፈታሪኮችን ፈጥረናል፣ፍልስፍናዎችን ፈልስፈናል፣ቴክኖሎጂዎችን ፈጥረናል፣ማንነቶችን ሳይቀር አበጅተናል።እየኖርንባት ያለነዉ አለምም እንደመጣን ያገኘናት ሳትሆን እንድትሆን ፈልገን የሰራናት ናት።
ምናብ የባዮሎጂካል ተፈጥሯችንን የምንሻገርባት፣ሃሳብንም ከሊሆን አይችልም ግብ ግብ የምናስታርቅበት የሰዉ ልጅ መለያ አቅም ነዉ።
ስለዚህ ምናብ ነፃነት ነዉ! የሰዉ ልጅ አለምን ለመቆጣጠረ ያበቃዉም ጥንካሬ፣እምነት ወይ ደመነፍስ አልነበረም። በምናቡ ከአጥር ዉጪ ወጦ በማሰቡ እና ወደ መሬት እስኪያወረደዉ ድረስ መጋጋጡ ነዉ!
"To imagine is To philosophize and vise versa"
ለዚህ ምክንያቴ ደግሞ «መሪዎች ፈላስፋዎች መሆን አለባቸው የሚል ያረጀ ምልከታ» ነው። ያው ደስታዬ የነበረው ፍልስፍና ሀገር ያሳድጋል፤ ፈላስፋ ለሀገር እድገት ወሳኙን ሚና ይወጣል ብሎ በማሰብ ከተነሳ ቀና ጉጉት ነበር። ያው ወሬውን እዚህ ያመጣሁት «የሀገሬ ህዝብ ፍልስፍና ስላልዘለቀው ነው እንዲህ የሚሆነው የሚል» እኔ የነበረኝን ዓይነት የዋህ ምልከታ ላላቸው ነው።
ነገር ግን የ Behavioral science ተመራማሪዎች እንደሚሉን ከኾነ «የሰዎች ባህርይ» እንደዚህ በቀላሉ አይሰራም። የሰዎችን ሙሉ ባህርይ የሆነ ዓይነት አመለካከት ለብቻው አይቀይርም! አመለካከቶች፣ባህሪዎች የብዙ ነገሮች ጥርቅም ውጤቶች ናቸው! ህዝባዊ፣ግለሰባዊ ባህርይን «እንደዚህ ከሆነ እንደዚ ይሆናል ብለን» oversimplified ማድረግ አንችልም።
ዶክተር በለጠ ፍልስፍናንስ እሱ ይፈላሰፋት የምትሉት ዓይነት ሰው ነው! አስፈላጊ ከሆነ እኔ ጋ ያሉትን አንድ ሶስት ጽሑፎቹን እልካለሁ። ዛሬ ዝሆን ስላየሁ ደስ አለኝ የሚለው ሚኒስትር ዝም ብሎ ተራ ሰው አልነበረም። በሌላ ከሀገር ውጪም ሀገር ውስጥም ነው PHD ድረስ ትምህርቱን የተማረው! የሆነ ሀገር እንደውም የክብር ሽልማት አለው! የአዲስአባባ ዩኒቨርሲቲ ፖስት ግራጁዌት የፍልስፍና አስተማሪ ነበር። እኔ በለጠ ሞላን ይበልጥ የማውቀው ስለ «ኢሴንሻሊዝም» በጻፈውን ጥናታዊ ጽሑፉ ነው። በወቅቱ አንዳንድ ከማኅበራዊ ኑረት ጋ የሚቆራኙ የፍልስፍና ሀሳቦች በውስጤ የምከራከርባቸው ስለነበሩ «በዚህ ጉዳይ ያቀረበው ጽሑፍ ብዙ ምልከታዬን» ያቃናልኝ ነበር። ከዛ በፊት ብዙ ካንትያዊ ምልከታዎችን እንደወረዱ ነበር እንደእግዜር ቃል የምመለከታቸው። እንደ እውነቱ ከሆነ የእሱ ብቻ ተዋጽዖም ባይሆን ዛሬ ድረስ ላለሁበት የconstructivist ምልከታዬ እሱን አለማመስገን አልችልም። በተለይ የኢትዮጵያን cultural essentialism ላይ የቆመውን ethnic based politics ለመሞገት ይመስለኛል፣ ብቻ ወሳኝ እና ሚዛናዊ ዘመኑን የዋጀ የፍልስፍና ጆርናል አቅርቧል።
ታድያ የሆነ ወቅት ፖለቲካችን ከመረዳቴ ውጪ ወጣብኝ። መከታተል ስላልቻልኩ ተውኩት! ዛሬ ይኼ የማደንቀው ታላቁ ሰው «ግመል ማነው... ዝሆን አይቼ አላውቅም፣ ዛሬ ዝሆን ስላየሁ ሀገር ይያያዝልኝ እያለ ነው» አሉ። እኔ ምን ይመጣብኛል ከእንግዲህ? አንቱ መባል አለበት የምለው ሰውዬ፣ የምክንያት ሚዛኑን ከቶም የማይስት የአመክንዮ ሰው ብዬ የምክበው ሰውዬ ማይክ ይዞ፣ ሚኒስቴር ሆኖ «ዛሬ ግመል በማየቴ ደስ ብሎኛል» አለ ብለው ሰዎች ይስቃሉ እኔ አዘንኩ! አላምን ብዬ ሄጄ አጣራሁ። እውነትም ብሏል።
«ለማንኛውም ስለድንቅ ጆርናሎቹ እናወራበት ዘንድ እመለስበታለሁ..»
ይህ ጽሑፍ ፖለቲካ ነክ አደለም! ከፈለጋችሁ ደግማችሁ አንብቡት🤕
ለዚህ ምክንያቴ ደግሞ «መሪዎች ፈላስፋዎች መሆን አለባቸው የሚል ያረጀ ምልከታ» ነው። ያው ደስታዬ የነበረው ፍልስፍና ሀገር ያሳድጋል፤ ፈላስፋ ለሀገር እድገት ወሳኙን ሚና ይወጣል ብሎ በማሰብ ከተነሳ ቀና ጉጉት ነበር። ያው ወሬውን እዚህ ያመጣሁት «የሀገሬ ህዝብ ፍልስፍና ስላልዘለቀው ነው እንዲህ የሚሆነው የሚል» እኔ የነበረኝን ዓይነት የዋህ ምልከታ ላላቸው ነው።
ነገር ግን የ Behavioral science ተመራማሪዎች እንደሚሉን ከኾነ «የሰዎች ባህርይ» እንደዚህ በቀላሉ አይሰራም። የሰዎችን ሙሉ ባህርይ የሆነ ዓይነት አመለካከት ለብቻው አይቀይርም! አመለካከቶች፣ባህሪዎች የብዙ ነገሮች ጥርቅም ውጤቶች ናቸው! ህዝባዊ፣ግለሰባዊ ባህርይን «እንደዚህ ከሆነ እንደዚ ይሆናል ብለን» oversimplified ማድረግ አንችልም።
ዶክተር በለጠ ፍልስፍናንስ እሱ ይፈላሰፋት የምትሉት ዓይነት ሰው ነው! አስፈላጊ ከሆነ እኔ ጋ ያሉትን አንድ ሶስት ጽሑፎቹን እልካለሁ። ዛሬ ዝሆን ስላየሁ ደስ አለኝ የሚለው ሚኒስትር ዝም ብሎ ተራ ሰው አልነበረም። በሌላ ከሀገር ውጪም ሀገር ውስጥም ነው PHD ድረስ ትምህርቱን የተማረው! የሆነ ሀገር እንደውም የክብር ሽልማት አለው! የአዲስአባባ ዩኒቨርሲቲ ፖስት ግራጁዌት የፍልስፍና አስተማሪ ነበር። እኔ በለጠ ሞላን ይበልጥ የማውቀው ስለ «ኢሴንሻሊዝም» በጻፈውን ጥናታዊ ጽሑፉ ነው። በወቅቱ አንዳንድ ከማኅበራዊ ኑረት ጋ የሚቆራኙ የፍልስፍና ሀሳቦች በውስጤ የምከራከርባቸው ስለነበሩ «በዚህ ጉዳይ ያቀረበው ጽሑፍ ብዙ ምልከታዬን» ያቃናልኝ ነበር። ከዛ በፊት ብዙ ካንትያዊ ምልከታዎችን እንደወረዱ ነበር እንደእግዜር ቃል የምመለከታቸው። እንደ እውነቱ ከሆነ የእሱ ብቻ ተዋጽዖም ባይሆን ዛሬ ድረስ ላለሁበት የconstructivist ምልከታዬ እሱን አለማመስገን አልችልም። በተለይ የኢትዮጵያን cultural essentialism ላይ የቆመውን ethnic based politics ለመሞገት ይመስለኛል፣ ብቻ ወሳኝ እና ሚዛናዊ ዘመኑን የዋጀ የፍልስፍና ጆርናል አቅርቧል።
ታድያ የሆነ ወቅት ፖለቲካችን ከመረዳቴ ውጪ ወጣብኝ። መከታተል ስላልቻልኩ ተውኩት! ዛሬ ይኼ የማደንቀው ታላቁ ሰው «ግመል ማነው... ዝሆን አይቼ አላውቅም፣ ዛሬ ዝሆን ስላየሁ ሀገር ይያያዝልኝ እያለ ነው» አሉ። እኔ ምን ይመጣብኛል ከእንግዲህ? አንቱ መባል አለበት የምለው ሰውዬ፣ የምክንያት ሚዛኑን ከቶም የማይስት የአመክንዮ ሰው ብዬ የምክበው ሰውዬ ማይክ ይዞ፣ ሚኒስቴር ሆኖ «ዛሬ ግመል በማየቴ ደስ ብሎኛል» አለ ብለው ሰዎች ይስቃሉ እኔ አዘንኩ! አላምን ብዬ ሄጄ አጣራሁ። እውነትም ብሏል።
«ለማንኛውም ስለድንቅ ጆርናሎቹ እናወራበት ዘንድ እመለስበታለሁ..»
ይህ ጽሑፍ ፖለቲካ ነክ አደለም! ከፈለጋችሁ ደግማችሁ አንብቡት🤕
ለዛሬ በለጠ ሞላ የጠቀሰውን የዊትገንስቴይን ሀሳብ ይዘን ለውይይት ማስጀመርያ እናድርገው:- እንዲህ ይላል:-
We . . . say of some people that they are transparent to us. It is;
however, important as regards this observation that one human being can be a complete enigma to another. We learn this whenwe come into a strange country with entirely strange traditions; and, what is more, even given a mastery of the country's language. We do not understand the people (quoted in Geertz, 1973: 13).
አገባባዊ ትርጉም:-
አንዳንድ [የማኅበረሰብ ክፍሎች] ከሌላ [የማኅበረሰብ ክፍል] አንጻር እንረዳቸዋለን እንላለን! ደግሞም ነው! ለምሳሌ:- ከአንድ ማህበረሰብ ክፍል የተገኘ ሰው ከሌላ ማኅበረሰብ ለተገኘ ሰው ፍፁም እንቆቅልሽ ሊሆን እንደሚችል መረዳት ያስፈልጋል። ይህን በግልጽ የምንመለከተው ደግሞ ሙሉ በሙሉ እንግዳ የሆኑ ባህሎች ወዳለው አዲስ ማኅበረሰብ\ሀገር ስንገኝ ነው! የዛን ማኅበረሰብ ቋንቋ ጠንቅቀቀን ብንረዳ እንኳ ህዝቡ አይገባንም።
ያው «ሀበሻን ከሀገሩ እንጂ ከልቡ ሀገሩን ማስወጣት አትችልም» የሚል የዲያስፖራዎች ጥቅስ አለች🙄😃። ያው ሀሳቡ ሲጠቀለል እንደዛ ነው! ማኅበረሰባችን ምንም እንኳ ባይስማማን፣ ይስማማናል ወዳልነው ማኅበረሰብ ስንሄድ ሙሉ በሙሉ የእኔነት ስሜት አይሰማንም። ለምሳሌ:- አንድ ኦሮሞን ጎጃም ላይ ብንወስደው፣ ወይንም አንድ ጎጃሜን ወለጋ ብንወስደው እንደራሱ ህዝብ አድርጎ ማየት ይችላል ወይ? ያላደግንበት ማኅበረሰብን ከልባችን የእኔ ማኅበረሰብ ነው ብለን ለማሰብ እንቸገራለን ይላል ሀሳቡ! እዚህ ጋር የሚከተለው ጥያቄ «ባህሎች የማንነት መሰረት ናቸው የሚል ፍልስፍና \cultural essentialism » ነው።
እና ዝም ብለን በደፈናው «ባህሎች፣ የማኅበረሰብ ኑረቶች፣ የሰው ልጅ ማንነት መሰረቶች ሳይሆኑ just constructed ናቸው» ከምንል ለምን በፍልስፍና፣ በአመክንዮ ሃሳቦቹን አንሞግታቸውም? የCultural essentialismን ሀሳብ ከተቀበላችሁም ሀሳቡን ማበልጸግ ይቻላል! ዝም ብሎ የሚጣል ሀሳብ አደለም። ታላላቅ ፈላስፋዎች የሚደግፉት፣ የሚነቅፉት፣ የሚከራከሩበት ዓለምአቀፋዊ ሀሳብ ነው።
Just to be more clear
Nb:- cultural essentialism ማለት ማኅበረሰቡ በተለምዶ «ዘረኝነት\ብሔረተኝነት» የሚለው ሀሳብ ነው! ቃል በቃልም ባይሆን🙄
ብርሀኑ ደቦጭ ይመስለኛል ይህንን ለመጽሐፉ መግቢያ የተጠቀመበት! ቃሉን የሚመጥነው ቦታ ስላገኘሁ ነው ይህንን ለ'ርዕስ የተጠቀምኩት። «የፈጣሪ አለ የለም ጥያቄዎች» መሰረታዊ ከመሆናቸው የተነሳ እዛ ሰፈር መልሱን በእርግጥ አገኘን የሚሉ ሰዎች እራሳቸውን የሁሉም ነገር expert አድርገው ያያሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ጥያቄዎቹ በሳይንስ እና በፍልስፍና ሰፈር አሁናዊ ዋና የመከራከርያ አጀንዳዎች አይደሉም። ጥያቄው ለአንድ ትልቅ ሳይንቲስት ወይንም ለአንድ ትልቅ ፈላስፋ it's irrelevant! ባይሆን አገልግሎታቸውን በመጠየቅ ዙርያ የተወሰነ ዲስኮርስ አለ። በአጭሩ የዚህ ጥያቄ መልሱ አይታወቅም፣ ተፈጥሮን ለመርመርም ዋና tool አይደለም።
የቄስ ልጅ እግዜር አጎቱ ይመስለዋል የሚባል ነገር አለ! ጳጳሳት ምድሪቷን ያስተዳድሩ፣ ቄሶች ፖለቲካዊ አመራር ይስጡ ፣ የእስልምና ሀይማኖታዊ አባቶች የሀገሪቷ የበላይ ጠባቂ ይሁኑ፣ የአየር ትንበያ ባለሙያዎች ኡስታዞች ይሁኑ፣ ሚኒስቴሮችና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነብያትና ፓስተሮች ምናምን መሆን አለባቸው የሚለው አስቂኝ አመለካከት ከ[እግዜር አለ የለም] ጥያቄ ይዘት ጋር፣ ማለትም መልሱን አገኘን ከሚሉት ይዘት ጋር ይገናኛል።
ብዙ ጊዜ ከማገኛቸው ጽንፍ የረገጡ ኢአማኞች ውስጥ እራሳቸውን የሚያዩበት መንገድ ሁሌ እንደደነቀኝ ነው። የዚህ መጽሐፍ ደራሲም እራሱን ያቀረበበት መንገድ አስቆኝ አልፏል። ፍልስፍና እንዲሁም ሌሎች «ጥልቅ ምርምር የሚካሄድባቸው ዘርፍ ምሁራን» እራሳቸውን የሚያቀርቡት ሰማይ አስነክተው አይደለም። ደራሲው «ከእሱ በላይ መከራን ያሳለፈ እንደሌለ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ አሻራውን ማሳረፉን፣ ምሁርና የተለየ ዕንቁ ማዕድን አድርጎ ነው። [ቃል በቃል ነው ያለው...]
መጽሐፉ ውስጥ ባቀረባቸው ሀሳቦች «ከዐቢይ ፍንዳታ አንስቶ፣ ዝግመተ ለውጥን አስከትሎ፣ የሀይማኖት አመጣጥን ተከትሎ ታሪክን፣ ስነጠፈርን፣ ስነህይወትን፣ ስነልቦና፣ የማህበራዊ ሳይንስን፣ የአእምሮ ጥናቶችን» ጢባ-ጢቤ ተጫውቶባቸው አልፏል። ትን የሚሉ የስህተት ትንታኔዎች በጥላቻ ከታጀቡ የስነጽሑፍ ውበት በሌላቸው ገለጻዎች አቅርቧል። በሳይንስ ዙርያ እውነት ለመናገር «አንድ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ሳይንስን ከዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ በላይ» ይረዳል!
«ሳይንስን፣ ፍልስፍናን፣ ማህበራዊ ሳይንስን፣ እና የስነልቦና ጽንሰሀሳቦችን የአንባቢዎችን ክብር በማይመጥን መልኩ አዝረክርኮ አቅርቧል። ይሄንን ያነበበ «የሰባተኛ ክፍልን አካባቢ ሳይንስን በአግባቡ ተምሮ ያለፈ፣ አንድ ሚዛናዊ ሰው ትክክለኛ ሳይንሳዊ ሀሳቦች ቀርበዋል» ካለ አካባቢ ሳይንስን ከሁለተኛ ክፍል ጀምሮ መከለስ ይኖርበታል።
ያው እግዚአብሔር አለ ወይንም የለም የሚለው ጥያቄ ግዘፍነት የተነሳ መልሱን አገኘን ብለው የሚያስቡ ሰዎች በሁሉም ዘርፍ እየገቡ እራሳቸውን እንደ expert ያያሉ ከሚሉ የስነልቦና ጥናቶች ጋር የሚስማማ ነው። በስሙ ልጥራውና በዚህ አካባቢ ያሉ ሰዎችን በብዛት የሚከተላቸው Dunning-Kruger effect ይባላል! ይህንኑ ጉዳይ ፈላስፋዎች Philosophical Naivety ይሉታል። ያው በጣም የተለመደ ነገር ነው። አማኝ ሆኑም አልሆኑም! ኤለመንተሪ እንኳ ላሉ ተማሪዎች በትምህርት መልኩ የሚቀርቡ «መሰረታዊ የሳይንስ ሀሳቦችን» የሳተ ሀተታ እንዴት በመጽሐፍ መልኩ ይቀርባል? ሊያውም እራሱን «እኔ ተራ ሰው ሳልሆን ዕንቁ ማዕድን ነኝ » በሚል ሰው?
ለማንኛውም:-
አንድ ቄስ፣ ኡስታዝ ወይ አባገዳ «ስለፖለቲካ፣ ስለስነልቦና ሳይንስ፣ ስለማህበራዊ ሳይንስ» ተው! ታለሙያህ ገብተህ በራስህ እየፈጠርክ አትተንትን ሀሳቡን ለባለሙያዎቹ ስጥ፣ ወይንም የባለሙያዎቹ ጥናት ላይ ተንተራስ! መባል እንዳለበት ሁሉ እንደዚህ ዓይነት ሰዎችም በዛው መልክ መታየት ይገባቸዋል። አንድ ኢአማኝ automatically ፈላስፋ፣ automatically የሳይንስ expert፣ automatically orator፣ automatically የስነአእምሮ ባለሙያ expert፣ automatically የማህበራዊ ሳይንስ expert፣ automatically የታሪክ expert ፣ automatically የስነህይወት ጥናት expert ልሁን ካለ ጠይቆት ከነበረው ጥያቄ ግዙፍነት የተነሳ የሚከተለው የስነልቦና ችግር ውጤት ነው።
ህመሞችን ህመም እንበላቸው! ምሁርነት ብለን አናሽሞንሙን! ጸሐፊው እንኳን እኛ እንዲገባን ቴክኒካል ተርም ሊያቀልልን ለእራሱም አልገባውም!
መጽሐፉን ከግማሽ ገጽ በላይ የመሻገር አቅሙ አልነበረኝም የሚተርፋችሁ ጊዜ ካገኛችሁ አንብቡትና ታዘቡኝ!
ኅዳግ
ሳይንስ እንዲሁም ፍልስፍና ከሀይማኖት ጋ ይጋጫል ወይ? It depends! አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ:-
አንድ ነጭ እና አንድ ጥቁር ቀለም!
ሁለቱን ለማቀላቀል እንሞክር! ሀይማኖት ነጭ ቢሆን ፍልስፍናን እና ሳይንስን ጥቁር አድርገን እንውሰዳቸው! ብዙ ነጭ ውስጥ ትንሽ ጥቁር ብናስገባ የነጭነት ይዘቱን ሙሉ በሙሉ አይለቅም። ሀይማኖት ውስጥ ፍልስፍናን እና ሳይንስን በትንሹ ብንቀላቅል የሀይማኖት ይዘትን ላንለቅ እንችላለን። እኩል እኩል ካደረግን ነጣ ያለ ግራጫ ይዘት እናገኛለን። እሱ ለዘብተኝነት፣ ተራማጅነት ይባላል።
ጥቁሩ ውስጥ ትንሽ ነጭ ብናስገባ የጥቁርነት ይዘቱን አይለቅም። ልክ እንደዛው pragmatic atheist ወይንም agnostic\liberal athiesm የሚል ጠቆር ያለ ግራጫ ቀለም እናገኛለን። ሰብዓዊነት ማለት ይሄ ነው። ሁለቱንም 100% አድርገን ከነሙሉ ክብራቸው ቀላቅለን እንያዝ የሚለው መንገድ እራስን መዋሸት ነው። አለመቀላቀልም ይቻላል! ነጩን ወይ ጥቁሩን መተውም ይቻላል። ግዴታ አደለም! ብቻ ብዙ ብሩህ ጭንቅላት ያላቸው ኢአማኝ ልጆች አውቃለሁ! በዚህ መጽሐፍ ልክ «ኢአማኝነትን መለካት» እነሱን መስደብ ነው!
ብዙ እምነትን የሚፈታተኑ masterpiece ናቸው የሚባሉ «ኃይማኖታዊ ኂስ ላይህ ያተኮሩ» መጽሐፎች አሉ። ነገር ግን «ሳይንስን፣ እራሱ ዝግመተ- ለውጥም፣ እራሱ ፍልስፍናም፣ እራሱ ታሪክንም፣ እራሱ ዐቢይ ፍንዳታም በዚህ መጽሐፍ የቀረቡበት መንገድ» ኀልዮቶቹ ትክክል ናቸው ብለው ለሚያምኑ ሰዎች (obviously እኔም አምናለሁ) ሽሙጥ ነው።
ደግሞ የሆሞ-ሳፒየንስ አጽም አገኘን ብሎ እንደ ሳይንሳዊ break through ማቅረብ ሊገባኝ አልቻለም። አሁን ያለው የሰው ልጅ እኮ ነው homosapiens የሚባለው! ይሄንን መንገድ ላይ ያገኘሁትን አንዱን የሁለተኛ ክፍል ተማሪን ጠርቼ ብጠይቀው አይጠፋውም።
After all በትህትና የተጻፈ መጽሐፍ ስላልሆነ፣ በስድቦች የተሞላ መጽሐፍ ስለሆነ በዚህ መልክ ከማቅረብ ውጪ አማራጭ አላገኘሁም። ትህትናንም፣ መከባበርንም እንደ ሀይማኖት ብቻ ውጤቶች አድርጎ በማቅረብ እየወረደባቸው ነበር።
ጥቂት ስሞች ብቻ በዚህ ሳይንቲስት ስም ልክ በዘመናዊዉ የሳይንስ ጉዞ ላይ ገነዉ ይገኛሉ ግን ወደ ዉስጥ ጠልቆ ገብቶ ለሚመለከት ብቻዉን ነጥሮ የሚወጣ አንድ ስም ብቻ እንዳለ ይረዳል። እንግሊዛዊው የፊዚክስ ሊቅ እና ተመራማሪ Stephen William Hawking ! በተንቀሳቃሽ ወንበር ላይ ሆኖ የሰዉ ልጆችን ስለ አለም ያላቸዉን ግንዛቤ ያሰፋ፤ በማይታዘዝ ገላ ዉስጥ ሆኖ ጋላክሲዎችን አሻግሮ የመረመረ እና መረዳትን ያካበተ፤ ለአማኞች የማስፈራሪያ ምሳሌያቸዉ ለኢአማኞች የጥንካሬ እና የአይበገሬነት አቅም ማሳያቸዉ፤ የሰዉ ልጆችን የመቻል ጥግ ጥያቄ ምልክት ዉስጥ የከተተዉ የተቀፀፈዉ ሳይንቲስት!
በ ጃንዋሪ 8፣ 1942 እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር የተወለደዉ እንግሊዛዊዉ ብላቴና የትዉልዱ ቀን በሚያስደንቅ ሁኔታ ከጋሊልዮ የ 300ኛ ሙት አመት ጋር የገጠመ ነዉ። በልጅነቱ ያደረበትን የተፈጥሮን መመርመር አባዜን በመከትል በ17 አመቱ oxford universityን ለመቀላቀል በቃ፤ ቀጥሎም እስከ phd ያለዉን መዓረግ በ Cambridge university አሳክቷል ግን ገና በ 21 አመቱ ተስፈኛዉ ወጣት amyotrophic lateral sclerosis (ALS) የሚባል በጊዜ ሂደት ሰዉነቱን ፓራላይዝድ እያረገ የሚመጣ ግን አይምሮዉን የማይነካ የነርቭ በሽታ እንዳለበት በምርመራ ታዉቆ ዶክተሮች ያረዱታል። ዶክተሮቹ አያይዘዉ ጥቂት አመታት ብቻ በህይወት ሊቆይ እንደሚችል ቢነግሩትም እሱ ግን ከ አምስት አስርት አመታት ቡሃላ ለሰዉ ልጆች ይበል የሚያሰኝን የህዋ እዉቀት አሸክሞ ነዉ ያለፈዉ።
ሁኔታዉ እየተባባሰ በመጣ ወቅት Hawking ሙሉ ለሙሉ የመንቀሳቀስ ክህሎቱን እና የመናገር አቅሙን አጣ። ግን እጣፈንታዉን ተቀብሎ በዝምታ ከመክረም ይልቅ በልዩ ሁኔታ በተሰራ ጉንጩ ላይ ያለን ጡንቻ በመጠቀም የሚንቀሳቀስ የንግግር ማሽን ሃሳቡን ለማስተላለፍያነት እንዲጠቀም ተደርጎ ተዘጋጀ። የሚንቀሳቀስበትም ዊልቸር ከመደበኛዉ ወጣ ያለ እና በጣም በጥቂት አካላዊ ጥረት እንዲፅፍ እና እንቅስቃሴዉን እንዲቆጣጠር ተደርጎ የተሰራ ማሽን ነዉ።
በተፈጥሮአዊ መንገድ መናገር ሆነ መንቀሳቀስ የተሳነዉ Hawking በተንቀሳቃሽ ወንበሩ ላይ ሆኖ የሰዉ ልጆች ስለ ብላክ ሆል፣ቢግባንግ እና የጊዜ ጅማሬን (the origin of time) ላይ ያላቸዉን እዉቀት እያሰፋ እና እያሳደገ መጧል። በጣም ከሚጠቀሱ ስራዎቹ አንዱ ብላክ ሆል የሚለቀዉ ጨረር መኖሩን ያገኘበት እና እሱም ግኝት በስሙ Hawking radiation የሚባል ስያሜ የተሰጠዉ የዘመናችን የ ፊዚክስ እዉቀት ላይ አዲስ እይታ እና እምርታን የጨመረ ግኝት ነዉ። በተጨማሪ ለዘመናት ለማዛመድ ሲሞከር እና ሲከሽፍ የነበረዉን የታዋቂዉን ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን relativity ከ quantum mechanics ጋር በማዛመድ ታላቅ አበርክቶ አድርጓል።በ 1988 ያሳተመዉ መፅሀፍ "a Brief history of time" ዉስብስብ የሆነን የህዋ አረዳድ እና ምልከታ ያሰፈረ በሚሊየኖች ኮፒም የተሸጠ አበርክቶ ነዉ።
በተደጋጋሚ በ ቀረበባቸዉ ኢንተርቪዎች ላይ እና በሚያቀርባቸዉ ፅሁፎች ላይ "ሳይንስ እንጂ ሃይማኖት እና እመነት ተፈጥሮን አብጠርጥረዉ ሊያስረዱ እንደማይችሉ ተናግሯል"።በ 2010 በፃፈዉ "The Grand design" በሚለዉ መፅሀፍ ላይ "Because there is a law such as gravity, the universe can and will create it self from nothing" ብሎ አስፍሯል። በ 2014 ባረገዉ ኢንተርቪዉም "there is no God. I am an atheist,Religion believes in miracle and it's not compatible with science" የሚለዉ መልሱ አብዛኛዉ የአይምሮ ይዘታቸዉ ባዶ በሆነዉ አማኞች ዘንድ እንደ ገደል ማሚቱ እስከ ዛሬ ድረስ ያቃጭላል። በጊዜዉም እንደ blasphemy ተቆጥሮ ያልደረሰበት እርግማን እና ዉግዘት አልነበረም። ከዛም ቀጥሎ በተናገራቸዉ ንግግሮች ዉስጥ “I regard the brain as a computer which will stop working when its components fail. There is no heaven or afterlife for broken down computers; that is a fairy story for people afraid of the dark.” በማለት ከሞት ቡሃላ ህይወት እንደሚኖር እንደማያምን ተናግሯል። በመቀጠልም የሰዉ ልጅ ባለበት ተገድቦ እንዳይቀር መመርመርን ልምዱ እንዲያረግ እንዲህ ሲል ተናግሯል “Remember to look up at the stars and not down at your feet. Try to make sense of what you see and wonder about what makes the universe exist. Be curious. And however difficult life may seem, there is always something you can do and succeed at. It matters that you don’t just give up.”
እዚህ ጋር ነዉ እንግዲህ ሃይማኖታዊ ትርጓሜ ከ ሳይንሳዊ አግራሞት ጋር ግብ ለግብ ተያይዘዉ የሚገኙት። በአንድ ጊዜ "እግዘብሔር የለም ተፈጥሮንም የሚሾፍራት እንደዛዉ"ብሎ የተናገረዉ ኢአማኙ Hawking በአማኞች ዘንዳ ህመሙ እንደመቅፀፍት ተተርጉሞ መጠቋቆሚያ፣ማስጠንቀቂያ እና የክህደት ቅጣት ማሳያ እስከመሆን ደርሷል። መሰረታዊ የፊዚክስ እዉቀት የሌለዉ መሬት ላይ የሚራመደው እራሱ የመሬት ስበት እንዳለ ስለሆነ በቅጡ የማይቅ እና የማይረዳ አማኝ ተብዬ ሁሉ በፊዚክስ የላቀዉን ከዊልቸር ላይ ሆኖ ህዋን ያሰሰዉ፣የተለመዉ እና ቀመር ያስቀመጠለትን ተመራማሪ "እንደ Hawking ቆማምጦ ያሳርፍሃል" እያለ ስሙን መዘባበቻ እና ማስፈራሪያ አርጎት አረፈ። ምናልባትም በአማኞቹ ዘንድ ታዋቂ ያረገዉ ለሰዎች የሰጠዉ ሳይንሳዊ አበርክቶ ሳይሆን "እግዛብሔርን ክዶ የተሽመደመደዉ የሚለዉ" ሃሜት እና ስብከት ነዉ።
ምናልባትም ልክ ናቸዉ ግጥምጥሞሽ ወይ ተፈጥሮ እግር ነሳታዋለች፣ልሳኑን ዘግታለች በእርግጥም ቀፅፋዋለች! ግን እሱ ልሳኑን ተካዉ፣ ኮቴዉን ቀለሰ አንገቱን ቀና ማረግ የማይችለዉ ሰዉዬ አንገቱን 360° ሲያሽከረክር ከሚዉለዉ እና የተባረኩ የተመረጥኩ ነኝ ብሎ ከሚያስበዉ አማኝ በተሻለ ህዋን ተረዳት ተመራመራት ተራቀቀባት! ለተላከበት መቅፀፍት እሱ እራሱ መቅፀፍት ሆነበት፤ የሰዉ ልጆች የእራሳቸዉን አቅም ጥያቄ ዉስጥ እንዲከቱ አረገ፤ አይቻልም የተባለዉን መቻል ብቻ አይደለም፤ አይቻልም የተባለዉን በማይቻል ሁኔታ ዉስጥ ሆኖ አስችሎ ቻለ። የሰዉን ልጅ ያድነዋል፣ያወጣዋል፣እንዲዋጋ ያስችለዋል የተባለለትን ሰዉነቱ እንኳን ሲሽመደመድ ከዛ የበለጠ መሳሪያ እና ችሎታ እንዳለዉ የሚያሳይ በሁሉም የሰዉ ልጅ ጥናት ዘርፍ ላይ መደመምን የፈጠረ ህይወት ለታሪክ አሳልፎ አለፈ።
እና ከላይ "ተፈጥሮ" በሚለዉ ቦታ ላይ ፈጣሪ የሚለዉ ቃል ቢገባ ያን ያህል ልዩነት ያመጣል? አይመስለኝም!
“The Scientist Who Never Backed Down: Stephen William Hawking.”
Reviews channel
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «ከፍልስፍና ዓለም™» is a Telegram channel in the category «Книги, Аудиокниги и Подкасты», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 19.8K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 7.3, with 0 reviews and an average score of 0.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 6.0 ₽, and with 0 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий