
Advertising on the Telegram channel «Orthodox Tewahdo new»
#Orthodox_Tewahdo_new Ethiopian Orthodox Tewahdo Church is a channel that broadcasts current news and teachings to the Christian public. የመዝሙር ቻናል👉
Channel statistics
ከዚህ የተነሣ አደንቃለሁ
❝ የተዋሐደውን ሥጋ ከመላእክት ባሕርይ የነሣው አይደለም ፥ ከአብርሃም ባሕርይ ነሣው እንጂ።
ዕብ.፪፥፲፯።
ለዚህ ታላቅ ፍቅር አንክሮ ይገባል ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሰው ወገን ለተደረገ ፤ ለማይመረመር ለዚህ ፍቅር አንክሮ ይገባል ፥ ይህ ለመላእክት ያላደረገው ነው።
የተነገረውን አስተውል ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ባሕርይ የተዋሐደው ተዋሕዶ ጥቂት ክብር አይምሰልህ ፥ ይህንን ለመላእክት አላደረገውምና የመላእክት ባሕርይም አልተዋሐደችውምና የተዋሐደችው የኛ ባሕርይ ናት እንጂ።
ባሕርያችንን ተዋሕዶአል እንጂ ከባሕርያችን ከፍሎ ተዋሐደ ለምን አላለም
ለማይደፈር ለዚህ ድንቅ ምሥጢር አንክሮ ይገባል ፤ ከእግዚአብሔር ጋር በመተካከል የሚኖር መላእክትና የመላእክት አለቆች ሱራፌልና ኪሩቤል የሚሰግዱለት ሥጋ ከእኛ ባሕርይ ይገኝ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ አንድነት አለን
ዕብ.፩፥፫-፰።
ይህን መላልሼ ባሰብሁት ጊዜ ሰው ያገኘውን ፤ ልክ መጠን የሌለውን ፍጹም ክብር ከእግዚአብሔር የተደገረውን ፤ ባሕርያችን ያገኘውን ታላቅ ፍቅር አይቼ ከዚህ የተነሣ አደንቃለሁ።
ዮሐ.፫፥፲፮-፲፰ ። ፲፯ ። ፳፮ ። ፩ዮሐ.፫፥፩። ❞
አሜን።
╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|•✧══╮
@Orthodox_Tewahdo_new
╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧•✧══╯
ከ ቄራ ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው ዋና አስፋልት ከመብራቱ አለፍ ብሎ
ከ ባለ 1 መኝታ ቤት እስከ ባለ 3 መኝታ ቤት
📍ባለ 1 መኝታ ቤት 60ካሬ
📍ባለ 2 መኝታ ቤት 90 -116 ካሬ
📍ባለ 3 መኝታ ቤት 125-157 ካሬ
✅ቅድመ ክፍያ 20%
✅100% ለሚከፍል 30% ቅናሽ ይደረጋል፡፡
ከ 7ኛ ፎቅ እስከ 13 ፎቅ የፍሎር አማራጭ አላቸው ፡፡
ከ ግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ የንግድ ሱቆች
6ኛ ፎቅ የጋራ መገልገያ
👉ባለ 1 መኝታ ቤት 60ካሬ
አጠቃላይ ክፍያ = 6,900,000
20% ቅድመ ክፍያ = 1,380,000
👉100% ለሚከፍል 30%ቅናሽ ተደርጎ የሚከፍለው ክፍያ = 4,830,000
👉 ሱቆችን ደግሞ በፒያሳ፣በገላን እንዲሁም በቡልጋሪያ ከፈለጉ
ቅድመ ክፍያ ለ ንግድ ሡቆች:
👉Ground 3,500,000
1st :- 2,500,000
3rd :- 1,300,000
5th Floor :- 900,000
ፈጥነው ይያዙ❗️
👉ማሳስቢያ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ አናደርግም
🏗️ ቀሪውን ክፍያ በ 3 አመት በግንባታ ሂደት የሚከፍሉት ይሆናል፡፡
☎️+251974163592
https://t.me/yichalemtilahun
☦️ ቸሩ መድኃኔዓለም አባቴ እንኳን አደረሳችሁ/ አደረሰን🛐 🔥 ☦️
ራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን።ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁትን መሰቀልን ናቀው። በፈጠራቸው ፍጥረታት ተተፋበት።እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የማያውቁትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር። ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር።
ታድያ እኛ ደግሞ ራሳችንን ለማዳን ሰዎች ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩብን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል።ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንባላለን። በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት።በመስቀል የተገኙ ድንግል ማርያምና ሐዋርያው ዮሐንስ ነበሩ።አንተም በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግህ ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን ገንዘብ አድርግ።
🤩 አማኑኤል በቸርነቱ ይቅር ይበለን።
አሜን(፫)🛐 🔥 ☦️
🤩 "የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"☦️ ምሳ 1፥33📕
╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|•✧══╮
@Orthodox_Tewahdo_new
╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧•✧══╯
Call:- 0912323064
Dema Hope Real Estate ዴማ ሆፕሰ ሪል እሰቴት በመሀል አዲሰ አበባ:-
✔️መገናኛ ሲግናል ,
✔️ቦሌ መድሀኒአለም
✔️መገናኛ ሾላ,
✔️ቦሌ አትላሰ እና
✔️ቦሌ 24 ሙሉ ያለቁ ጠዋት ገዝተው ከሰአት የሚገቡበት
✔️ቦሌ መድሀኒአለም ኤድናሞል ጋር ግንባታቸው 90% የደርሱ እጅግ ቅንጡ የመኖርያ አፓርታማ ከባለ 1 መኝታ እሰከ 4 መኝታ ድረሰ እና የንግድ ሱቆች በመሀል ቦሌ ከኢንተርናሸናል ሰቴዲየም በቅርብ ርቀት ከግራውንድ ፍሎር ጀምሮ ከ 20ካሬ ጀምሮ ሸያጭ ላይ ነን በተጨማሪ የመኖርያ አፓርታርትመንቶቻችን እና የንግድ ሱቆቹ ዛሬ ገዝተው ዛሬ የካርታ ሰም ማዞር ይችላሉ ማየት ማመን ነው ፈጥነው ይደውሉ።
Dema Hope Real Estate
ቅንጦት ይገባዎታል ።
ለበለጠ መረጃ
0912323064
0921305626
በዚች ቀን በታላቁ ንጉሥ በቈስጠንጢኖስ ዘመን የከበረ አባት የአንጾኪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ትምህርቱ በዓለም የመላ አንስጣስዮስ አረፈ።
የከበሩ አባቶችም በኒቅያ ከተማ የአንድነት ስብሰባ በአደረጉ ጊዜ በዚህ ጉባኤ ከተሰበሰቡት ሊቃውንት አንዱ እርሱ ነው በዚህም ጉባኤ ተስማምተው አርዮስን ከባልንጀሮቹ ጋርአውግዘው ለይተውታል ባልንጀሮቹም የቂሣርያ አውሳብዮስ የኒቆምድያ አውሳብዮስና አርናሲስ ናቸው።
እሊህም በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ታውቀዋል።
እሊህም የከበሩ አባቶች ሥርዓትን ሠርተው ወደየሀገራቸው በተመለሱ ጊዜ እሊህ ከኤጲስቆጶስነት ሹመት የተሻሩት ወደ ኢየሩሳሌም የሚሔዱ መስለው ወጡ ወደ አንጾኪያም ከተማ ገብተው ከአንዲት አመንዝራ ሴት ዘንድ ተሰበሰቡ ብዙ ገንዘብም ሊሰጧት ቃል ገቡላት ወደ ቤተክርስቲያን እንድትገባ ይህ አባት ከእርሷ ጋር እንዳመነዘረ የወለደችውም ልጅ የእርሱ እንደሆነ በዚህ ቅዱስ አባት አንስጣስዮስ ላይ ለካህናቱና ለሕዝቡ እንድትናገር አስተማሩዋት።
ሕዝቡም እንዲህ አሏት አንቺ ሐሰተኛ ነሽ በዚህ ቅዱስ አባትም ላይ ሐሰትን ተናግረሻል በከበረ ወንጌል ካልማልሽ በቀር ቃልሽን አንቀበልም አሏት እርሷም ስለ ገንዘብ ፍቅርበሐሰት ማለች።
ከዚህም በኋላ ለንጉሥ ነግረው ከመንበረ ሢመቱ ወደ አጥራክያ ደሴት አሳደዱት በስደትም ሳለ በርሷ አረፈ።
ነገር ግን ለእሊህ ከሀድያን ወዮላቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ከመለኮቱ ባሕርይ ለይተው ፍጡር ነው ብለውታልና ይህንንም ንጹሕ አባት ሰይጣን አባታቸው እንዳስተማራቸው ከአመንዝራ ጋር አንድ ሁነው በተንኰል ከመንበረ ሢመቱ አውጥተውታልና።
እግዚአብሔር ግን ቸለል አላለም ይህን አባት ከአሳደዱት በኋላ ያቺ አመንዝራ ሴት ጭንቅ በሆነ ደዌ ተይዛ ብዙ ተሠቃየች ለሞትም ተቃረበች ያን ጊዜም ይህ ሁሉ የደረሰባት በከበረ ወንጌል በሐሰት ስለማለች እንደሆነ ተገነዘበች።
በአንጾኪያም ሰዎች ሁሉ ፊት በደሏን አመነች እንዲህም አለቻቸው ይህ ቅዱስ አንስጣስዮስ ከዝሙት ንጹሕ ነው እነዚያ ከሀድያን ብዙ ገንዘብ ሰጥተውኝ በእርሱ ላይ ሐሰት እንድናገር በከበረ ወንጌልም በሐሰት እንድምል አደረጉኝ እንጂ።
የአንጾኪያ አገር ሰዎችም ኃጢአቷን ማመኗን በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ ካህናቱም በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜ ስሙን የሚያነሱ ሆኑ ዮሐንስ አፈወርቅም አመሰገነው በመታሰቢያውም ቀን ስለ ርሱ ብዙ ቃላትን ደረሰ።
ምንጭ፦
😇 "የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ📖 📖 🌟 ፥🌟 🌟
╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|•✧══╮
@Orthodox_Tewahdo_new
╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧•✧══╯
ትዕቢትና ውዳሴ ከንቱ ...
❝ ለትዕቢተኛ ሰው እግዚአብሔር የፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ በኃይል የሌላቸው ይመስለዋል።
በሸረሪት ድር የሚጫን ወዲያው ይወድቃል ፤ በራሱ ኃይል የሚመካም እንዲሁ ይጠፋል፡፡
የፍሬው ብዛት ዛፉን ያዘነብለዋል ፤ ሰውንም የበጎነት ፍሬ ብዛት ትሑት ያደርገዋል፡፡
የነቀዘ የስንዴ ቅንጣት ለዘር አይጠቅምም ፤ የትዕቢተኛ ሰው በጎ ሥራም መቼም መች እግዚአብሔርን ደስ አያሰኘውም፡፡
የአትክልት ቦታን የሚቆርጥ ፍሬን የተመላችውን ተክል ለይቶ ከፍ ከፍ ያደርጋታል ፤ የፈሪሃ እግዚአብሔር ፍሬም በጎነትን የተመላችውን ሰውነት ታጸናታለች።
ሌሊት የምትሐት ሕልሞችን እንዳታይ ልቡናህን ለትዕቢት አሳልፈህ አትስጥ፡፡
ከምትታጀር ነፍስ እግዚአብሔር ፈጥኖ ይለያታል ፤ ምንጊዜም የአጋንንት መሳለቂያ ትሆናለች። ❞
╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|•✧══╮
@Orthodox_Tewahdo_new
╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧•✧══╯
ለኑሮ ሰላማዊ፣ ለንግድዎ ስኬታማ የሆነውን የቤትና የሱቅ ባለቤት የመሆን ዕድል አሁኑኑ ይጠቀሙ። ደስታዎ እዚህ ይጀምራል!
🏠 ለመኖሪያ በተመረጡ የካሬ አማራጮች፦
* ባለ 1 መኝታ፦ ከ77 ካሬ ጀምሮ
* ባለ 2 መኝታ፦ ከ111 ካሬ ጀምሮ
* ባለ 3 መኝታ፦ ከ150 ካሬ ጀምሮ
* ባለ 4 መኝታ፦ ከ190 ካሬ ጀምሮ
* ፔንት ሃውስ (Penthouse)፦ ከ169 እስከ 295 ካሬ ድረስ
🛒 ለንግድ ሱቆች፦ ከ27 ካሬ ጀምሮ።
💰 ልዩ የክፍያ አማራጮች፦
* በ 10% ቅድመ ክፍያ ብቻ ውል ይጀምሩ።
* የ 60% የባንክ ብድር ተመቻችቶለት፣ እስከ 25 ዓመታት ድረስ ቀስ እያሉ የሚከፍሉበት።
* ሙሉ ለሚከፍሉ 35% ታላቅ ቅናሽ (እስከ 3,000,000 ብር እውነተኛ ቅናሽ!) ቅደመው ለሚመጡ ዝቅተኛ ፍሎር አለ
💎 ሙሉ ምቾቶች የተሟሉለት፦
🏊♂️ መዋኛ ገንዳ |
🏃♂️ የመሮጫ ትራክ |
🏋️ ጂም |
🛒 ሱፐር ማርኬት
🅿️ ሰፊ ፓርኪንግ |
💧 የከረሰ ምድር ውሃ |
⚡ አውቶማቲክ ጄኔሬተር
📍 አድራሻ፦ ለቡ መብራት ኃይል (በሁለት ታላላቅ ተቋማት መካከል)
"የነገ ቅርሶን ዛሬ ይገንቡ፤ በብዙ ያተርፋሉ!"
📞 አሁኑኑ ይደውሉና ሳይቱን ይጎብኙ፦
0918965096
ዲ ኤም ሲ ሪል እስቴት
ደስታዎ እዚህ ይጀምራል
@henokab2730
https://t.me/henokdmcreal
ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል::
+ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም (አልቦ ትንሳኤ ሙታን) የሚሉ ናቸው::
+መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ ዲዲሞስ ሲሆን ጌታችን ቶማስ ብሎታል::
+ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: (ዮሐ. 11:16)
+ጌታችን ትንሳኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም:-
1.ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው
2.አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤውን አየን እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር::
+ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ (ጌታየና አምላኬ)" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን (መለኮትን) ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች::
+ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት:: ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ (ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት)" ሲሉ ያከብሩታል::
+ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል::
+በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት:-
"ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ:
አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ" ብለዋል ሊቃውንቱ::
+በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል::
+ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ38 ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል::
+በመጨረሻም በ72 ዓ/ም በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል::
+እንደ አባቶቻችን ትርጉም ቶማስ (ቶማስስ) ማለት ጸሐይ (ኦርያሬስ) እንደ ማለት ነው:: በተሰጠው የወንጌል ጸጋ በሃገረ ስብከቱ አብርቷልና::
=>ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን::
=>ግንቦት 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
2.ቅድስት አርሶንያ (የቅዱስ ቶማስ ተከታይ)
3.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
2.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
3.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
=>+"+ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን "ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን" አለው:: ቶማስም "ጌታዬ አምላኬም" ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም "ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው" አለው:: +"+ (ዮሐ. 20:26-29)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|•✧══╮
@Orthodox_Tewahdo_new
╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧•✧══╯
ከ ቄራ ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው ዋና አስፋልት ከመብራቱ አለፍ ብሎ
ከ ባለ 1 መኝታ ቤት እስከ ባለ 3 መኝታ ቤት
📍ባለ 1 መኝታ ቤት 60ካሬ
📍ባለ 2 መኝታ ቤት 90 -116 ካሬ
📍ባለ 3 መኝታ ቤት 125-157 ካሬ
✅ቅድመ ክፍያ 20%
✅100% ለሚከፍል 30% ቅናሽ ይደረጋል፡፡
ከ 7ኛ ፎቅ እስከ 13 ፎቅ የፍሎር አማራጭ አላቸው ፡፡
ከ ግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ የንግድ ሱቆች
6ኛ ፎቅ የጋራ መገልገያ
👉ባለ 1 መኝታ ቤት 60ካሬ
አጠቃላይ ክፍያ = 6,900,000
20% ቅድመ ክፍያ = 1,380,000
👉100% ለሚከፍል 30%ቅናሽ ተደርጎ የሚከፍለው ክፍያ = 4,830,000
👉 ሱቆችን ደግሞ በፒያሳ፣በገላን እንዲሁም በቡልጋሪያ ከፈለጉ
ቅድመ ክፍያ ለ ንግድ ሡቆች:
👉Ground 3,500,000
1st :- 2,500,000
3rd :- 1,300,000
5th Floor :- 900,000
ፈጥነው ይያዙ❗️
👉ማሳስቢያ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ አናደርግም
🏗️ ቀሪውን ክፍያ በ 3 አመት በግንባታ ሂደት የሚከፍሉት ይሆናል፡፡
☎️+251974163592
https://t.me/yichalemtilahun
Reviews channel
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Advertising on the Telegram channel «Orthodox Tewahdo new» is a Telegram channel in the category «Образование», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 16.9K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 7.3, with 0 reviews and an average score of 0.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 9.6 ₽, and with 0 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий