
- Main
- Catalog
- Cryptocurrencies
- 🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™
🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™
#አባቶችን_ጠይቅ_ይነግሩሃል ● ጠቢብ ከሰነፍ ጋር ቢጣላ፥ ሰነፍ ወይም ይቈጣል ወይም ይስቃል፥ ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ፍጹሙን ሰው ይጠላሉ፥ ደግሞም የቅኑን ሰው ነፍስ ይሻሉ። ሰነፍ ሰው ቍጣውን ሁሉ ያወጣል፤ ጠቢብ ግን በውስጡ ያስቀረዋል።
Channel statistics
❝ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር እንደ ልጅም አስብ ነበር፤ እንደ ልጅም እቆጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬያለሁ። አሁን ግን ታወቀኝ በግልጥም ተረዳኝ❞— ፩ኛ ቆሮ ፲፫፥፲፩ ብሎ እንደተናገረ መምህር ኒቆዲሞስም የአሪት መምህር ሳለ እንደ ኦሪታውያን ያስብ ነበር፤ የወንጌልን ዕውቀት ሲጨምር ግን ያላወቀው ብዙ ነገር እንዳለና ከኦሪት እውቀት የወንጌል እውቀት የበለጠ ጸጋ እንደሚያሰጥ ተረዳ፤ ስለዚህ ኦሪታዊ ባሕርይውን በወንጌላዊ ባሕርይ ለወጠ። በዚያም ሳያበቃ መማር ብቻውን እንደማያጸድቅ አውቆ የተረዳውን እውነት ደግሞ በምግባር ገለጠ። ፩. አዋቂ ነን የሚሉትን አሳፈራቸው ወቅቱ የአይሁድ የፋሲካ በዓል የቀረበበት፤ ጻፎችና የካህናት አለቆች ጌታን ለመያዝ የሙሴ ፈጣሪ መሆኑን ባለማወቃቸው እንደ ሙሴ ሕግ ሊያስፈርዱበት የቋመጡበት ጊዜ ነበር። የካህናት አለቆች ተሰብስበው ክርስቶስን ለመያዝ በሚመካከሩ ጊዜ ከሙሴ መጻሕፍት ሕግ ጠቅሶ ሊቃውንተ ኦሪትን አፋቸውን ያስያዛቸው ኒቆዲሞስ ነበር። በዚህም የተነሣ ሳይስማሙ ወደ የቤታቸው እንዲበተኑ ያደርጋቸው ነበር:: ይህንን እውነት ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደ መዘገበልን:-
❝ከእነርሱም አንዱ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ የሄደው ኒቆዲሞስ እንዲህ አላቸው ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን? አላቸው፤ አንተም ከገሊላ ነህን ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሣ መርምርና እይ አሉት፤ ሁሉም እያንዳንዳቸው ወደ ቤታቸው ሄዱ❞— በማለት ያጠፋው ጥፋት ሳይጠና ቀኝና ግራ ሳይታይ እንዲሁ ሰውን በከንቱ መወንጀል እንደማይገባ ይህንንም ሕገ ኦሪት እንደማትፈቅድ በመናገር ጸሐፍት ፈሪሳውያንን ምክንያት አሳጥቶ ወደየቤታቸው እንዲበታተኑ ያደረገ ታላቅ ሰው ነው (ዮሐ ፯፥፶፩)። ፈሪሳውያን የተጠየቁትን የሕግ ጥያቄ በሕግ መመለስ ሲያቅታቸው «አንተ ከገሊላ ነህን?» በሚል ጉዳዩን ወደ ወገንተኝነት ለመውሰድ ቢሞከሩም ኾኖም በቂ ምክንያት ሊያቀርቡ ባለመቻላቸው አፍረው ወደ ቤታቸው ገብተዋል፡፡ ፪. ከሥርዐተ ግንዘቱ ተሳተፈ ጌታችን በቀራንዮ አደባባይ ራሱን ለዓለሙ ቤዛ አድርጎ ሲሰጥ እስከ ሞት ድረስ ከአንተ አንለይህም ያሉት፤ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ ከእግሩ ስር ቁጭ ብለው የተማሩ ከዮሐንስ በቀር ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ሲበታተኑ በዘጠኝ ሰዓት ቀራንዮ የተገኘው ኒቆዲሞስ ብቻ ነበር። ሦስት ዓመት ሙሉ ከእጁ የበሉ የጠጡ የቃሉን ትምህርት የሰሙ የእጁን ተአምራት ያዩ መደበኞቹ ተማሪዎች ከምስክርነት ሲሸሹ በትርፍ ጊዜው ይማር የነበረው የማታው ተማሪ ኒቆዲሞስ ለምስክርነት ተገኘ።
❝ለጠቢብ አሐቲ ቃል ትበቁዖ — ለብልህ ስው አንዲት ቃል ትበቀዋለች❞የተባለውን ቃል ተፈጸመ። ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ:-
❝ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረው ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ❞— ብሎ እንደመዘገበልን ከአርማትያሱ ከዮሴፍ ጋር ሆኖ የክርስቶስን ሥጋ ከጲላጦስ ለምኖ የገነዘ፣ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋ ከርቤና የእሬት ቅልቅል ያርከፈከፈለት ለራሱ ባሳነጸው ሐዲስ መቃብር የቀበረው ኒቆዲሞስ ነበር (ዮሐ ፲፱፥፴፰)። ቅድስት በረከቱ በእውነት ትደርብን። (፫/፫) ዲ/ን ኃይለራጉኤል
❝እኔ ለእውነት ልመሰክርመጥቻለሁ❞— በማለት እውነትን እንድንመስክር አብነት ሆኖናል (ዮሐ ፲፰፥፴፯)። በተጨማሪም:-
❝በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው አባቴ ፊት እመስክርለታለሁ:: በሰው ፊት የሚክደኝን ሁሉ ደግሞ በሰማያት ባለው አባቴ ፊት እክደዋለሁ❞— ሲል ስለ ሃይማኖታችን መመስከር እንደሚገባን አስተምሮናል (ማቴ ፲፥፴፪)። እንዲሁም ለኒቆዲሞስ ሲያስተምረውም:-
❝እውነት እውነት እልሃለሁ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን❞— በማለት ለእውነት መመስከር እንደሚገባ አስገንዝቦታል (ዮሐ ፫፥፲፩)። ኒቆዲሞስ በተማረው ትምህርት መሠረት ያለፍርሃትና ያለ ሐፍረት በካህናቱ ፊት እውነትን መስክሯል። ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱ:-
❝ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፤ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም❞— በማለት እውነተኛ ፍጹም ፍቅር ላፈቀረው አካል ማንኛውንም መሥዋዕትነት ለመክፈል እንደሚዘጋጅ ተናግሯል (፩ኛ ዮሐ ፬፥፲፰)። ኒቆዲሞስም እውነትንና ጸሐይን ፈርቶ የትም መድረስ እንደማይቻል ስለተረዳ መጽሐፍ እየጠቀሰ እውነቱን በመናገር ካህናቱን አሳፍሯቸዋል:: በመሪዎችና በታላላቅ ሰዎች ፊት ቆሞ እውነትን መመስከር ክርስትናችን የሚያስገድደን አንዱ ቁም ነገር ነው (ሉቃ ፲፪፥፰)። ቤተክርስቲያን «ሰማዕታት» አያለች የምትዘክራቸው በሙሉ ለእውነት ብለው ራሳቸውን ለክርስቶስ አሳልፈው የሰጡ በአላውያን ነገሥታት ፊት እውነቱን የመሰከሩ ቅዱሳንን ነው:: በፍርሃት፣ በሐፍረትና በይሉኝታ እውነትን መካድና መሸፈን በክርስቶስ ፊት ያስጠይቃል እንጂ አያስመሰግንም (ማቴ ፲፥፴፪)። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ:-
❝ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ማድረግ እንችልም❞— ያለውም ለዚህ ነው (፪ኛ ቆሮ ፲፫፥፰)። ይህን የተገነዘበው የኦሪቱ ሊቅ ኒቆዲሞስ:-
❝መምህር ሆይ አእግዚአብሔር ዘንድ ተልከህ ልታስተምር እንደመጣህ እናውቃለን፤ አንተ የምትሠራውን ሥራ መሥራት የሚቻለው የለምና፤ እግዚአብሔር ካደረበት ሰው በቀር አንዱ ስንኳ አንተ የምታደርገውን ተአምራት ማድረግ አይቻለውምና። ስለዚህ ከእብ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ተወልደህ ልታስተምር እንደ መጣህ እናውቃለን❞— ሲል በምሥጢር የተሟላ የአእምሮን ክፍተት የሚሞላ ምስክርነት ሰጥቷል:: ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድም:-
❝ወሀሎ አሐዱ ብእሲ እምፈሪሳውያን ዘስሙ ኒቆዲሞስ ዘሖረ ኀቤሁ ቀዲሙ ሌሊተ ኀበ ኢየሱስ ወይቤሎ ረቢ ነአምን ብከ ከመ እምኀበ አብ መጻእከ አልቦ ዘይገብር ተአምረ ዘአንተ ትገብር ወይቤልዎ አይሁድ ኢየሐውር በሕገ ኦሪትነ ወይቤሎሙ ኒቆዲሞስ ኦሪትክሙኑ ትኴንኖ ለሰብእ ዘእንበለ ትቅድሙ ወትሕቱ ምግባሮ ወይቤሎ ለኢየሱስ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ ወበትንሣኤከ ተንሥእ ርድአነ ወአድኅነነ በእንተ ስምከ ዘተሰምየ በላዕሌነ — አስቀድሞ ሌሊት ወደ እርሱ ይሄድ የነበረ ከፈሪሳውያን ወገን ስሙ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ መምህር ሆይ ከአብ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ተወልደህ ወደዚህ ዓለም እንደ መጣህ እናምንብሃለን፤ አንተ የምትሠራውን ተአምር የሚሠራ የለም አለው፤ አይሁድ ግን በአሪታችንን ሕግ አይሄድም አሉት፤ ኒቆዲሞስ ኦሪታችሁ አስቀድሞ ሥራውን ሳትመረምር በውኑ ሰውን ትኮንናለችን አላቸው የሕይወታችን መሪ ኀጢአታችንን ይቅር የምትል ነህ አለው፡፡ የአንበሳ ልጅ ኢየሱስ ሆይ ተኛህ አንቀላፋህ በትንሣኤህ ተነሥ እርዳን፤ በእኛ ላይ ስለተሠየመው ስምህ አድነን አለው❞— በማለት መጋቤ ብሉይ ኒቆዲሞስ ለኦሪት ሕግ ተቆርቋሪ እግዚአብሔርን አክባሪ ነን እያሉ ለሚመጻደቁ ፈሪሳውያን ተገቢውን መልስ እንደሰጣቸው ሊቁ በዜማው ነግሮናል፡፡ ፭. ትግሐ ሌሊት ትግሐ ሌሊት ማለት ከቆሙ ሳይቀመጡ ከጀመሩ ሳያቋርጡ በተደሞ በተመስጦ ሆኖ በጸሎትና በስግደት ተግቶ ማደር ማለት ነው:: ለትግሐ ሌሊት፣ ለመንፈሳዊ የኅሊና ቅኝት፣ ለተመስጦ የሚመቸው ደግሞ የሌሊቱ ክፍለ ሰዓት ነው፡፡ ቀን ለሥጋ ሥራ ሲሮጥ - ሲራወጥ የነበረ ሰውነት ሌሊቱን ለነፍስ በመገዛት ሥጋውን መጎስም አለበት፡፡ ለዚህም ነው ቅድስት ቤተክርስቲያን ቀኑን በቅዳሴ፤ ሌሊቱን ደግሞ በማኅሌት፤ በሰዓታትና በኪዳን እግዚአብሔርን ስታመሰግን የምታድረው:: ማር ይስሐቅም:-
❝ሌሊትስ ጌታን ለማመስገን የተፈጠረ ድንቅ ጊዜ ነው❞— ያለው ባልባከነ ሐሳብ በተረጋጋ ልብ ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ሌሊት ምቹ ሰዓት ስለሆነ ነው:: ጌታችንም ሐዋርያቱን:-
❝ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ!❞— ያላቸው ሌሊት ተኝተው ስላገኛቸው ነው (ማቴ ፳፮፥፵፩)። አሁንም ቤተክርስቲያን እንደ ኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ ለኪዳን ለማኅሌት ለጸሎት የሚመጣ ምእመን ትፈልጋለች:: የኒቆዲሞስ በሌሊት ገሥግሦ መምጣት ለምሥጢረ ጥምቀት ትምህርት መገለጥ ምክንያት እንደሆነ ሁሉ በቅዳሴው፣ በኪዳኑ በሰዓታቱና በማኅሌቱ መገኘትና መሳተፍ ረቂቅ የሆነው ሰማያዊ ምሥጢር ፍንትው ብሎ እንዲገለጥልን ምክንያት ይኾናል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ:-
❝መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ❞— (፪ኛ ዼጥ ፩፥፲) ብሎ እንደተናገረው ለተጠራንበት ሕይወትና ሰልፍ በሰዓት ሳንወሰን ችግር ሳይበግረን እንደ ኒቆዲሞስ በቀንና በሌሊት መትጋት ይገባል:: ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም:-
❝በሌሊት አንሥኡ እደዊክሙ በቤተ መቅደስ፥ ወባርከዎ ለእግዚአብሔር — በሌሊት በቤተ መቅደስ እጆቻችሁን አንሡ እግዚአብሔርንም አመስግኑት❞— ብሎናል (መዝ ፻፴፫፥፪)። ፮. እስከ መጨረሻ መጽናት ጌታችንን በመዋዕለ ስብከቱ ብዙ ሺህ ሕዝብ ቢከተለውም እስከ መስቀሉ አብረውት የነበሩ ከሺዎቹ መካከል ግን አንድ ሰው ብቻ ነው:: የተወሰነው ሕዝብ ቀድሞም የተከተለው ለምግበ ሥጋ ነበርና ቀራንዮ ላይ አልተገኘም:: ቀራንዮ ላይ ምግበ ነፍስ እንጂ ምግበ ሥጋ የለም። ሌሎችም በቤተሰብ በሀብት በፍርሃት ምክንያት መስቀሉ ስር አልተገኙም:: ምንም እንኳ ኒቆዲሞስ በስድስት ሰዓት ባይገኝም የክርስቶስ ሥጋ ከነፍሱ በምትለይበት ሰዓት ክርስቶስን ከመስቀል አውርዶ ለሐዲስ መቃብር ያበቃው እሱ ነበር:: በዚህ የመከራ ሰዓት ከዮሐንስና ከእናቱ ከድንግል ማርያም ውጭ ማንም እንዳልነበረ መጻሕፍት ከገለጡልን በኋላ የምናገኛቸው የቁርጥ ቀን ልጆች ዮሴፍንና ኒቆዲሞስን ነው:: ይህም ፈተናውን ሁሉ ተቋቁሞ እስከ መጨረሻው ለመጽናቱ ምስክር ነው:: በክርስትና ሕይወታችንም የምናያቸው ነገሮች ከዚህ የተለዩ አይደሉም:: በምቹ ጊዜ የምናገለግል ፈተና ሲመጣ አገልግሎታችንን ጥለን የምንሮጥና ሰበብ ፈልገን የምናፈገፍግ በጣም ብዙዎች ነን (ማር ፲፬፥ ፶፩)። ዕውቀትና ሀብት ጣዖት ሆነውበት መሐል መንገድ ላይ እንደ ዴማስ ሩጫውን ያቋረጠውን፤ ጊዜ ጣዖት ሆኖበት ቅዳሴ የሚቀረውን ቆጥረን አንጨርሰውም። ጌታ በትምህርቱ:-
❝ለዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን — እስከ መጨረሻው የሚጸና እርሱ ይድናል❞— እንዳለ (ማቴ ፳፬፥፲፰)። ክርስትና ለጀመሩት ሳይሆን ለጨረሱት፤ ለወጠኑት ሳይሆን ለፈጸሙት የድል አክሊል የምትሰጥ መንገድ እንጂ የመሮጫ መንገዱ ጠበበን፥ ሩጫው ረዘመብን ለሚሉ ዴማሶች ቦታ የላትም (፪ኛ ጢሞ ፬፥፱)። (፪/፫) ⤵️⤵️⤵️⤵️
❝ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርሷም አይወሰድባትም❞— ያለው ለዚህ አይደል? (ሉቃ ፲፦፵፪)። ብዙዎቻችን ባለን የኑሮ ደረጃ፣ የዕውቀት ደረጃ፣ የሥልጣን ደረጃ ... ራሳችንን የማይሆን ከፍታ ላይ ሰቅለን የመማር አቅም አጥተናል፡፡ ቁጭ ብሎ መማር ደረጃችን የማይመጥን የሚመስለን ስንቶች እንሆን? ዘወትር ለመማር የተዘጋጀ ልቡና ካለን እግዚአብሔር በብዙ መንገድ ያስተምራል። ማን ያውቃል በአንድ ሰዓት ስብከት ውስጥ እግዚአብሔር ሊያስተምረን የፈለገ አንዲት ዐረፍተ ነገር ቢሆንስ? ትሑት ማለት ሳያውቁ አላውቅም ማለት ሳይሆን እያወቁ አላውቅም የሚል ሰው ነው:: ሳይማሩ ተምሬያለሁ ማለት ሳይሆን ተምረው ልክ እንደ ኒቆዲሞስ ለመማር ራስን ዝቅ ማድረግ ነው:: ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን የትምህርት ገበታ የሕግ መውጫ የመሲሁ መገለጫ እንደሆነች:-
❝እስመ እምጽዮን ይወጽእ ሕግ ወቃለ እግዚአብሔር እምኢየሩሳሌም ብእሲ ጻድቅ ዘእምኀበ እግዚአብሔር ነዋ ንጉሥኪ በጽሐ — ሕግ ከጽዮን ቃለ እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ይወጣልና፤ ጻድቅ ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እነሆ ንጉሥሽ ደረሰ❞— በማለት አምላካዊ ሕግ የሚረቀቅባት የሕዝብ ሁሉ መጠጊያ የሆነች ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ለሚጠይቃት ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጀች መሆኗን በመዝሙሩ ነግሮናል። ፪. ጎዶሎን ማወቅ ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት እንጂ ምሁረ ሐዲስ አይደለም። ያ ማለት መምህረ እስራኤል ዘሥጋ እንጂ መምህረ እስራኤል ዘነፍስ አይደለም። ክርስትና አለቃንና አገልጋይን አንድ እንደምታደርግ አያውቅም፤ ስለዚህ የጎደለውን ፍለጋ ወደ ክርስቶስ መጣ (ገላ ፫፥፳፮)። ኒቆዲሞስ ያለውን ሳይሆን ያጣውን፤ የሞላለትን ሳይሆን የጎደለውን ፍለጋ መጣ። ዕውቀት ብቻውን ምሉእ አያደርግም፤ አለቅነትም ቢሆን ገደብ አለው:: የሕይወቱን ክፍተት ሊሞላ የሚችል አንድ ክርስቶስ ብቻ መሆኑን ተረድቶ ጎደሎነቱን አምኖ ወደ ክርስቶስ መጣ:: «የሚጎድለኝ ምንድን ነው?›› ብሎ እንደጠየቀው ሰው ጎደሎን ማመን ምንኛ ታላቅ ነገር ነው? (ማቴ ፲፰፥፳፩)። ብዙኀን ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ሕይወታቸው አደጋ ላይ የሚወድቀውና ለሥጋ ፈተና የሚጋለጠው ክፍተትንና ጎዶሎነትን ካለማወቅ የተነሣ ነው። እንዲሁም ሕይወታችን ባዶነት እየተሰማው «ምሉእ ነኝ» ብሎ ማሰብ ራሱን የቻለ ፈተና ነው:: ኒቆዲሞስ በጊዜው በነበሩ የክብር መስፈርቶች መሠረት ‹‹አንቱ›› ሊያስኙት የሚችሉ ነገሮችን ያሟላና በሰው እይታ አዋቂና የተከበረ ሰው እንደነበረ ታሪኩ ያስረዳል። የተከበረ መሆኑ ቢታመንም አዋቂነቱ ግን ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፡፡ ጌታችን:-
❝አንተ የእስራኤል መምህር ሆነህ ይህን አታውቅምን?❞— ሲለው ገና ማወቅ የሚገባው ብዙ ነገር እንዳለ ያሳየናል:: ለእኛ ይህ መነሻ ነጥብ ነው። ማናችንም ብንሆን በእግዚአብሔር ፊት ገና በየቀኑ ማወቅ የሚገባንና ማድረግ የሚጠበቅብን ብዙ ነገር እንዳለና በሕይወት እስካለን ድረስ ዘወትር ለበለጠ ነገር መዘጋጀት እንዳለብን የምንረዳበት ታሪክ ነው። የክርስትና ሕይወት በአንድ ቀን ተአምራዊ ለውጥ ተሠርቶ የሚያከትም ሕይወት ሳይሆን ሁልጊዜም ለማያልቀው የእግዚአብሔር ጸጋ ራስን ከፍቶ እንደ ሕፃን መሆንን የሚጠይቅ ጥሪ ነው:: ድኛለሁ፣ አውቂያለሁ፣ በቅቻለሁ ብለን የምንቆም ሳይሆን ክርስቲያናዊ ሕይወታችን በየቀኑ እያደገ የሚሄድ መሆኑን መገንዘብ ይገባል:: ኒቆዲሞስ የክርስቶስ «ዳግም ተወለድ» የሚለው ትእዛዝ ግራ ቢገባው «እንዴት ሊሆን ይችላል?›› ብሎ ጠየቀ፤ ይህ የአንዲት የፍጡር ነፍስ የሁልጊዜ ጥያቄ ነው:: ነፍስ ስለማንነቷ ከመጠየቅ መቼም ቢሆን አትቦዝንም። ዘወትር እንዴትና ወዴት መጓዝ እንዳለባት ታስባለች:: ነፍሳችን ነገሮችን ሁሉ የምታውቅ ይመስላት ይሆናል፤ ሆኖም ግን ነገሮችን ጠንቅታ የማወቅ ብቃት ስለሌላት በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜም «ምንና እንዴት ማድረግ አለብኝ?» ማለቷ የግድ ነው፡፡ ምናልባት በሰው ፊት ስንቆም የፈለግነውን ሥዕላችንን ማስተላለፍ እንችል ይሆናል፤ በክርስቶስ ፊት ግን ገና ብዙ ማወቅ የሚገባን ነገር እንዳለ እንገነዘባለን:: ለዚህም ነው በእርሱ ቃል ፊት መምሰልና ማስመሰል ለማንነታችን ቦታቸውን የሚለቁት:: መወለድ ማለት መለየት፤ ከአንድ ዐይነት አናኗር ወደ ሌላ ዓይነት መምጣት ማለት ነው:: ሕፃን ከነበረበት ከጠባብ ዓለም ከእናቱ ማኅፀን ወደ ሰፊው ዓለም ወደዚህ ምድር መውጣት እንዳለበት ሁሉ ዳግም ከእግዚአብሔር ስንወለድም ከዚህ ጠባብ ዓለም ወደ ሰፊው ዓለም ከዚህ ከጨለማው ዓለም ወደ ብርሃናማው ዓለም እንወጣለን፤ ሕፃን ሲወለድ የምግብ ማስተላለፊያ የነበረው እትብቱ መቆረጥ የግድ እንደሆነ ሁሉ እኛም መንፈሳዊ ልደት ስንወለድ መቆረጥ ያለበት ሕይወት ይቆረጣል፡፡ መሠረታዊ ህልውናችንን የሚፈታተን፤ መንፈሳዊ ልደታችንን የሚያጨነግፍ ነገር እንዳይከሠት መጠንቀቅ አለብን። ያ ካልሆነ ማደግ አንችልም:: ዕድገታችን ደግሞ የሚረጋጠው ከራስ ወዳድነት ተላቅቀን የእግዚአብሔርን ፈቃድና የሰዎችን ሸክም ስንጋራ ብቻ ነው። ከእኔነት ቅርፊት ካልወጣን ከኛ ውጭ የሆነውን ሕይወት መገንዘብ አንችልም፤ ያልተፈለፈለ ማንነት፥ ያላደገ እምነት ይዘን በሥጋ ወደፊት የምንጓዝ ከሆነ እንደተበላሸ እንቁላል መጣል ነው ትርፉ:: በዚህ ሰብእና የክርስቶስን ሕማማትንና ትንሣኤን ማክበሩ ትርጉም አይኖረውም። የኒቆዲሞስ ታሪክ ከማንነታችን ወጥተን ለክርስቶስና ለሌሎች የመኖርን ሕይወት፣ በእምነታችን ዕለት ዕለት እንድንለማመድ ይጋብዘናል:: ፫. አርቆ ማስተዋል መምህር ኒቆዲሞስ ወደ ክርስቶስ ይዞ የመጣው ሥጋዊ ሕዋሳቱን ነበር፥ ጌታችን ግን አመጣጡ ለመልካም እንደሆነ አውቆ ለሥጋዊ እውቀት እጅግ የሚከብደውን ምሥጢረ ጥምቀትን ገለጠለት:: መጀመሪያ ኒቆዲሞስ ይህን ምሥጢር ለመቀበል አልተቻለውም ነበር። ክርስቶስ ምሥጢሩን ፍንትው አድርጎ ሲያብራራለት ግን ልቡናው ይህን ምሥጢር ለመቀበል ከፍ ከፍ አለ:: የእምነታችን መሠረት በሥጋ ዐይን ማየት፤ በሥጋ ጆሮ መስማት በሥጋ እጅ መዳሰስ ብቻ ከሆነ ልክ እንደ እንቧይ ካብ ቶሎ የሚናድ ይሆናል:: ኒቆዲሞስም ምሥጢሩ መጀመሪያ ቢከብደውም ቅሉ በኋላ ግን ልቦናውን ወደ ሰማያዊው ዓለም ከፍ ስላደረገ ምሥጢሩ ተገለጠለት፡፡ ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እየተፈታተኗት ያሉ አካላት የስሕተታቸውን ምንጭ እንደ ግያዝ ከአካባቢያቸውና ከምናየው ቁሳዊ ዓለም ውጭ መመልከት አለመቻላቸው ነው (፪ኛ ነገ ፮፥፲፯)። ለዚህም ነው ካህኑ በሥርዓተ ቅዳሴ ጊዜ ከሚታየው ወደማይታየው ምሥጢር እንድንመጥቅ የቁርባኑን ምሥጢር እንድናደንቅ:-
❝አልዕሉ አልባቢክሙ — ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ❞— የሚለን። (፩/፫) (ቀጣይ ፪ ክፍሎችን ከስር ይመልከቱ ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️)
Reviews channel
2 total reviews
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™ is a Telegram channel in the category «Криптовалюты», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 26.7K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 12.8, with 2 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 3.6 ₽, and with 28 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий