Get clients in any niche!
Delegate the launch of advertising to us — for free
Learn more
6.1
![Advertising in Telegram. Telegram Channel logo "ታሪካዊት ኢትዮጵያ [ History of Ethiopia ]" Advertising in Telegram. Telegram Channel logo @Historical_Ethiopia](/system/channels/avatars/000/150/951/original/IMG_20240411_100746_551.jpg)
Advertising on the Telegram channel «ታሪካዊት ኢትዮጵያ [ History of Ethiopia ]»
5.0
Education
Language:
Amharic
337
0
Share
Add to favorite
Channel temporarily not accepting requests
Choose another channel from recommendations or get a tailored list within your budget using AI
AI Channel Picker
Recent Channel Posts
የታሪክ ምሁሩ ተክለፃዲቅ መኩሪያ
በፓሪስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዋና ፀሐፊ፣ የጡረታ ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር፣ በረዳት ሚኒስትርነት ማዕረግ የብሔራዊ ቤተመዛግብት ወመዘክር ዋና ኃላፊ፣ በሚኒስትር ማዕረግ በእየሩሳሌም ቆንስል፣ በቤልግሬድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገራቸውን አገልግለዋል። የአፄ ኃይለሥላሴ ስርዓት በኃይል ከተወገደ በኋላም በዘመነ ደርግ እስከ ፲፱፻፷፯ 1967 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ የትምህርትና የባሕል ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸውን ታሪካቸው ያወሳል። ከዚያም በጡረታ ተገለሉ። እኚሁ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ለንባብ ያበቋቸውን የኢትዮጵያን የታሪክ መፃሕፍት በአብዛኛው የፃፉት በመንግሥት ሥራ ላይ እያሉ ነው። ለሕትመት ከበቁላቸው አያሌ ሥራዎቻቸው መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።
፩ 1. የኢትዮጵያ ታሪክ ከአፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፣
፪ 2. የኢትዮጵያ ታሪክ ከአፄ ልብነድንግል እስከ አፄ ቴዎድሮስ፣
፫ 3. የኢትዮጵያ ታሪክ ከአፄ ይኩኖ አምላክ እስከ አፄ ልብነድንግል፣
፬ 4. የኢትዮጵያ ታሪክ ከአክሱም ዛጉዌ እስከ ይኩኖ አምላክ፣
፭ 5. የኢትዮጵያ ታሪክና ኑቢያ፣
፮ 6. ከጣኦት አምልኮ ወደ ክርስትና፣
፯ 7. ጥንታዊት ኢትዮጵያና ግብፅ
፰ 8. የሰው ጠባይና አብሮ የመኖር ዘዴ፣
፱ 9. የግራኝ አሕመድ ወረራ
፲ 10. አፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጵያ አንድነት
፲፩ 11. አፄ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ አንድነት፣
እና ሌሎችም ያልታተሙ አያሌ ስራዎች አሏቸው። እነዚህ ከላይ የሰፈሩት የታሪክ መፃሕፍት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ታላላቆቹ ቅርሶች እንደ አክሱም፣ ላሊበላና ጎንደር የሚታዩ እንደሆነ ፀሐፊያን ይናገራሉ። አሁን ያሉ ወጣት ፀሐፊያን የታሪክ መፃህፍት እያሉ የሚያሳትሟቸው ስራዎቻቸው በአብዛኛው ከአቶ ተክለፃዲቅ መኩሪያ ስራዎች የተገለበጡ ናቸው። ለአንዳንዶቹ ደግሞ የመነሻ ሃሳብ የሚሰጡ ናቸው። ተክለፃዲቅ መኩሪያ በኢትዮጵያ የታሪክ ፅሁፍ ውስጥ ዘላለማዊ ብርሃን ረጭተው ያለፉ ብርቅዬ ደራሲ ነበሩ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!
YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia
ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia

219
10:20
25.11.2024
🗝ጥንተ አክሱም ስትመረመር
👉የቤተ ሳማዕቲው ቁፋሮና አንድምታው
የሥነ-ቅርሥ ጥናት(Archeology) ታሪክን በተጨበጠ መልኩ እንድናይና እንድናጠና የሚያስችል የሳይንስ ዘርፍ ነው፡፡ በመዛግብት ላይ የሰፈሩ ወይም በሥነ-ቃል የሚተላለፉ ታሪኮች እጅግ አስፈላጊ ቢሆኑም፤ የሥነ-ቅርስ ጥናት ደግሞ ታሪኩን ተጨባጭ በማድረግ ለማንጸሪያነት ያገለግላል፡፡ በእርግጥ ቅርሶች ተፈጥሯዊ ወይም ሰው ሠራሽ በሆነ ሁኔታ ይጎዳሉ፤ አንዳንዴም የተገኙትን ቅርሶች በአግባቡ ለማጥናት የተለያዩ እክሎች ይገጥማሉ፡፡
ይህ ቢሆንም ግን ዛሬም ድረስ ሳይንሱ ስለ ሰው ልጅ ታሪክ ብዙ እይታዎችን እንድናዳብርና የታሪክ ጥናት ላይም ብርሃን በማብራት አንድ ደረጃ ወደፊት እንድንራመድ ያስቻለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የሥነ-ቅርስ ባለሞያዎች ከሚሠሩባቸው ቦታዎች አንዱ አክሱምና አካባቢው ነው፡፡
የአክሱም ሥልጣኔ የገነነውን ያህል በዘመናዊ የሥነ- ቅርስ መጻሕፍት ላይ ብዙ አልተባለለትም፡፡ አንድ በአክሱም ላይ የጻፉ የታሪክ ምሁር፤ የጠየቋቸው የሥነ-ቅርስ ባለሞያዎች በአጠቃላይ አክሱምን ሲያነሱባቸው እንደማያውቁት እንደነገሯቸው ማውሳታቸውን በመጽሐፋቸው ላይ ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ቦታው ለሥነ-ቅርስም ሆነ ለታሪክ ተመራማሪዎች ጎላ ያለ ሥፍራ እንደሚኖረው የሚያሳብቁ የጥናት ውጤቶች እየወጡ ነው፡፡
ከነዚህ መካከል በቤተ-ሳማዕቲ የተደረገው ተከታታይ ቁፋሮ እና ውጤቱ ተጠቃሽ ነው፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት Southern Red Sea Archaeological Histories (SRSAH) የተሰኘ እና በቀይ ባህር በስተደቡብ በኩል ባሉ አካባቢዎች ጥናቱን የሚሠራ ፕሮጀክት፤ ከየሃ በስተደቡብ በመቶ ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ ምርምር ማድረግ ጀመረ፡፡
አካባቢው ለሥነ-ቅርስ ጥናት ያለው አስፈላጊነት ከዚህ በፊት የተገለጸ ቢሆንም፤ ዙሪያውን ያለው አካባቢ ግን ተዘንግቶ ቆይቷል፡፡ እ.ኤ.አ 2011፣ 2012፣ 2015 እና 2016 ላይ በቤተ ሳማዕቲ የተደረገው ጥናት ግን በአካባቢው ከመሬት በታች እስከ 3 ሜትር የሚደርሱ የተለያዩ ቤቶች መኖራቸው አሳየ፡፡
እነዚህ ላይ የተደረገው ጥናት ከክርስቶስ ልደት በፊት እስከ ስምንተኛው መቶ ክፍለዘመን እድሜ ያላቸው ሥነ-ሕንጻዎች እና በአራተኛ መቶ ክፍለዘመን እንደተገነቡ የሚታመኑ የሕንጻ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ የቦታው መገኘት በራሱ ትልቅ ግኝት ቢሆንም፤ ተጨማሪ ምርመራዎች ግን የግኝቱን ግዙፍነት የበለጠ የሚመሰክሩ ነበሩ፡፡
በነዚህ ቁፋሮዎች ወቅት የሥነ-ቅርስ ተመራማሪዎቹን ቀልብ ከሳቡት ግኝቶች ዋነኛው በምሥራቅ አፍሪቃ እስካሁን በእድሜ ጥንታዊ የሆነው ቤተክርስቲያን መገኘት ነው፡፡ በዚህ ቤተክርስቲያን ክፍሎች ላይ የተደረገው ጥናት እንዳሳየው፤ በአራተኛው መቶ ክፍለዘመን መጀመሪያ ላይ እንደተገነባ የሚጠቁም ሲሆን በውስጡና አካባቢው ላይ የተገኙትን የተለያዩ ቅርሶችም ይህንን የሚመሰክሩ ናቸው፡፡
ይህም የሮሙ ቅዱስ ቁስጥንጢኖስ ክርስትናን በሮም ሕጋዊ ካደረገበት የጊዜ ተመን ጋር መሳ ለመሳ ያስኬደዋል፡፡ ይህ የኢትዮጵያን ቀደምት ክርስትና የሚመሰክር በእድሜ እጅግ ጥንታዊው የሥነ-ቁፋሮ ማስረጃ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፤ የተገኙት መስቀሎች ተጨማሪ ማስረጃ ሲሆኑ፤ በአካባቢው የተገኘው የበሬ መልክ የተቀረጸበት ቀለበት እና ሌሎች አነስተኛ የእንስሳት ቅርጻ ቅርጾች የአክሱም ሥልጣኔ ቅድመ-ክርስትና ምን እንደሚመስል፤ ከዚያም ባሻገር ደግሞ ቦታው በወቅቱ ማኅበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ መስተጋብር ውስጥ ያለውን ቦታ የበለጠ ለማወቅ ትልቅ ፍንጭ እንደሚሰጥ ተመራማሪዎቹ ባሳተሙት ጥናታዊ ጽሑፍ አሳውቀዋል፡፡

212
10:20
25.11.2024
imageImage preview is unavailable

190
10:20
25.11.2024
close
New items
Selected
0
channels for:$0.00
Followers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий