
Monetize Telegram Mini App with Telega.io
Connect your app, set CPM, and watch your revenue grow!
Start monetizing
21.5

Advertising on the Telegram channel «Hasen Injamo»
5.0
8
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$48.00$48.00local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
ባንኮቻችንን ብሔር አያድናቸውም:: ኃይማኖት አያድናቸውም:: ኔጣኒያሁ አያድናቸውም:: ኻመንዒ አያድናቸውም:: ምናልባት የሀጅ ኑረዲን ልጅ የሚላቸውን ከሰሙና ካመኑ ይድናሉ::
ሰከንዶች ዋጋ የሚያስከፍልም የሚከፍልም የፋይናንስ ዘመን ላይ ነው ያለነው:: ስለዚህ ጥራት ያለው አገልግሎትና አዳዲስ ፕሮዳክት ፈጠራ ላይ ያተኩሩ::
4391
08:50
30.07.2025
የሁለተኛው ዙር ተጓዦች እንቅስቃሴ ጀምረዋል:: የሦስተኛው ካለ አሳውቃለሁ:: ሆኖም ግን ከዚያ በፊት የገበያ ትስስር መፍጠር የሚባል ነገር አንስቼ ነበር:: ይህንን በመንተራስ ብዙዎቻችሁ የተለያየ ዓይነት ዕቃ order አድርጋችኋል:: እንደየሁኔታው እገባበታለሁ:: ምላሽ ሳልሰጣችሁ የቆየሁት መሴጆች በዝተውም እንዲሁም Coordination points ማለቅ ስላለበት ነው::
ብር ይዘው ግን ዕቃ መሸጥ ውስጥ ያላለፉ አሉ:: ልክ እንደዚሁ ኢትዮጵያ ላይ በተለያዩ ዘርፎች መረከብ የምትፈልጉ አላችሁ:: ትስስሩን አዘምነን እንቀጥላለን::
(ምስጢሮች የተጠበቁ ናቸው)
3974
11:03
30.07.2025
ነጻን በነጻ ሽጦ
አተረፍኩ የማለት ብክነት
================
የአፍሪካ መንግሥታት ማለት ደሃ ሰካራም ባል እንደማለት ናቸው:: አንዳንድ ደሃ ባል ጠዋት ሲወጣ "ይኸውልሽ እግሮችሽ ደጃፍ ይረግጡና ለነገ ከዘራና ክራንች አዘጋጂ:: ሁለቱንም 70ብሬ ነው የምጥልልሽ" ይልና ምንም ብር ሳይጥል ይወጣል:: ከመሰሎቹ ጋር በልቶ ማታ በጠጅ ወይም ባረቄ ቂቅ ብሎ ይመጣና ኬትም ከዘመድም አስቸግራ የተበደረችውን ሽሮ ስታቀርብ "በቃ እዚህ ቤት ሁሌ ሽሮ ነው?" ብሎ ከሽሮው በላይ ይደነፋል:: ጥላው እንዳትሄድ ትዳር ነው:: ልጆች አሉ:: በቃ እንደተ70በረች ወደ መቃብር ትሄዳለች:: Actually መቃ-ብር ነው የቀየረችው::
መንግሥቶቻችን ሉዓላዊ ሀገር መሆናቸውን ረስተዋል:: ሉዓላዊ ገንዘብ እና ማዕከላዊ ባንክ መያዛቸውንም አያውቁም:: የብሔራዊ ባንክ ገዢ ከነበሩት ውስጥ አንዱ ዲግሪው "የአፈር አጠባበቅና የቦይ ክተራ" የሚል ነበር:: ከሙያው ጋር መራራ-ቅ ብቻ ሳይሆን ምን ላይ እንደተቀመጡ አለማወቅም በሽ ነው በየቦታው:: መንግሥታት ሉዓላዊ ገንዘብ ይዘው በየሱቁ ደጃፍ ጋርቤጅ የሚለቃቅሙ በየኬላው ካልሲ የሚቆጥሩ, የሚቀርጡና የሚጨርቡ ደንቦችን ይበትናል:: መሠረታዊ ነገር ማሟላት ቤት ለሁሉም ማቅረብ የመንግሥት ግዴታ ሆኖ ግን በየስብሰባው በሕዝብ ላይ ይጮኻል:: ሕዝቡ ምን ያድርግ? መንግሥቶቻንች ባንኩም ታንኩም በእጃቸው ይዘው ሕዝብ ላይ መጮኽ በልጅነታቸው አባቶቻቸው በእናቶቻቸው ላይ ሲያደርጉ ያዩትን የሚደግሙ ነው የሚመስሉት::
መንግሥት እጁ ላይ የማያልቅ ብር ይዟል:: በየኬላው ኮረሪማና የጥርስ ብሩሽ ከመቁጠር ወጥቶ ማስመረት ይችላል:: ለማስመረት ግን እጁ ላይ የማያልቅ ሀብት እንዳለ ማወቅ አለበት:: ሦስት ሜትር ብንቆፍር ውኃ አለ:: ግን በጥም እናልቃለን:: ድፍን አፍሪካ ቢሰፍር የሚበቃ መሬት ተኝቶ ውሎ ያድራል:: በኩርማን መሬት ግን በጥ^ይት እንቆላላለን:: ነጻ መሬትም የመንግሥት ... and ነጻ ገንዘብም የመንግሥት:: መንግሥት ግን ነጻን በነጻ እየሸጠ ገቢ ሰበሰብኩ ይላል:: አበበ የሚለው ቃል ውስጥ የመሃሉን "በ" በዳረኛው "በ" እንደመቀየር ነው:: በነጻ የተሰጠውን ነጻ መሬት በነጻ በተሰጠው ነጻ ብር ማለዋወጥ ሥራ መሥራት ሳይሆን በድፍን ሀገርና ሕዝብ መቀለድ ነው:: Yes የተጨመረ እሴት አለ:: እርሱን እሴት ማለዋወጥ ይቻል ይሆናል:: ግን ነጻን በነጻ ከማለዋወጥ እራሱ እየቀጠረ huge ፕሮጀክቶችን መገንባት ይችላል:: ልክ እንደ ቻይና:: ይህ ያልገባው ኢኮኖ-ሚስት ሰክሮ ከሚስቱ ጋር ሲጋጭ ይኖራል::
አንድ ሰው ግን እየታየኝ ነው:: ኧረ የብዙ ሰዎችን ጭንቅላት ሳልቀይር አይቀርም::
3813
04:09
31.07.2025
imageImage preview is unavailable
ሀጅ ዐሊኮ ዳንጎቴ ቻይና ውስጥ ትልቅ ፋብሪካ አላቸው:: በየሥፍራው ልጆቻቸውን እየመዳደቡ ናቸው:: እዚሁ ቻይና ባለሁበት ዝምድና ለመቀጠል አስቤ አጣራሁ:: ማሳመኑ ለኔ ቀላል ነው:: ካሳቫ የሚቆላ ምላስ አለኝ:: ይኸውልሽ የእኛ family name አጎቴ ይባላል:: ከቤተሰብሽ ስም ጋር ይመሳሰላል:: በእኛ ሀገር ቋንቋ አጎቴ ማለት ትልቅ የክብር ስም ነው:: ዝርያችን ከሙዓዚኑ ቢላል رضي الله عنه ስለሚመዘዝ ነው አጎቴ የምንባለው:: የእናንተም ዳንጎቴ እንደዚያ ሳይሆን አይቀርም:: እንደውም እኔ ነኝ የማጣራልሽ ብዬ ከነጃሺ ጋር ማያያዝ ነው::
ነገሩን ለማጥበቅ ወይ ነጃሺ ናይጄሪያዊ ናቸው ወይ እናንተ ወደ ናይጄሪያ ሄዳችሁ ነው ብሎ በሐሳብ መክበብ:: የነጃሺ አያት ዳንጎይቶም እንደሆኑ ታሪክ ማጣቀስ:: ችግሬ ምን መሰላችሁ? ከሚስት መበደር ቀርቶ እራሴው ከሰጠሗት ላይ አምጪ ማለት አልወድም:: ከፊትለፊት ሱቅ ብበደር ይሻለኛል:: ኮምፕሌክስ ምናምን የሚል አይጠፋም:: በሉ:: እና የሆነ በሥራ የደከምኩ ወይም በሰዓት ያልተነሳሁ ቀን "እስካሁን ተኝተሃልኣኣኣ ... አባቴ ሲሚንቶ ቦኖበት የሰበሰበውን አንተ እንደ ሲሚንቶ በትነው አሉህ:: ይልቅስ ጋርዶቼ ከመጡ እንደ ከረጢት እንዳያራግፉህ" ያለችኝ ቀን ሊሆን እና ሊፈጠር የሚችለውን ነገር ሳስብ ጊዜ ...
3699
11:32
31.07.2025
አፓርትመንት በኃይሌ ጋር-መንት
🤜🏾 መነሻ ክፍያ: ቢያንስ 2 ሚሊዮን ብር ጀምሮ
🤜🏾 ከፍተኛ ክፍያ: ቢበዛ 13 ሚሊዮን ብር
🤜🏾 ስፋት: 110 ካሬ Net
🤜🏾 የተናጠል ሱቅ እና የጋራ መገልገያ ሲደመር: 160 ካሬ (አማካይ)
🤜🏾 መኝታ: ሁሉም ባለ ሦስት
🤜🏾 ዲዛይን: ሁሉም አንድ ዓይነት
🤜🏾 ምክንያት:
ለማቀያየር🔀🔄
ለ ⬆️upgrade
⬇️downgrade እንዲመች
🤜🏾 የአከፋፈል ሁኔታ: በየስላቡ
🤜🏾 ዋጋ:- በቁርጥ
🤜🏾 የሚፈጀው:- ቢበዛ ሦስት ዓመት
🤜🏾 አባልነት:- መብት በውልና ማስረጃ ስለሚዞር "ብርህን ይዘህ" ውጣ የሚልህ የለም::
አፓርትመንቶቹን ለመግዛት
ስልክ:- +251 937 974 444
ቴሌ-ግራም
https://t.me/AbdulkadirN
ከዚያ:- ቢሮ መምጣት
የከዚያ ከዚያ:- ሳይት ጉብኝት
የከዚያ ከዚያ ከዚያ:- ወስኖ መግዛት
XinGuang ነኝ:: ከቹንግ::
____
ብዛት:- አንድ ቦታ ብቻ 30 ሳይቶች
መሠረት ከወጣ እስከ ተጠናቀቁ::
3347
13:34
01.08.2025
በቻይንኛ "ጌታ" ማለት ስጠው ወይም ስጭው ማለት ነው:: ጌ = መስጠት ... ታ = እሱ/እሷ:: ከዚያ ውጭ ጌታ አያውቁ:: አይሰግዱ:: ጁማዓና ጀማዓ ሐጃቸው አይደለ:: ዐርብ ረቡዕ አይመለከታቸው:: አይጾሙ:: አይቅሙ:: አያስቅሙ:: ጌታዬ ሥራዬን አሳካው አይሉ:: ዱዓ አያስደርጉ:: ጸ-በል አያስረጩ:: በገንዘብ ይራጫሉ:: ስነሥርዓታቸው ያስቀናል:: ቀጠሮ አክባሪነታቸው, ታማኝነታቸው ይገርማል:: ባየናቸው ግዛቶች ልመናና ሌብነት almost none. ስለሥራ ካልሆነ ብዙም አያወሩም:: እንደውም አፋቸው ውስጥ ምላስ እንዳለ የሚታወቀው ምራቅ ሲተፉ ብቻ ነው:: እንደዚህ ያፈላሰፈኝ የቻይንኛ ቋንቋ ልማር አስቤ ቶሎ እንዲበራልኝ በእንቁራት መረቅ ልጀምረው ብዬ ነበር:: ግን መብረቅ ቢዘንብስ ብዬ ተውኩት::
____
ሪል ኢስቴት ጋርመንት እና ጋዜቦ ጋር አለ:: ከ2 ሚሊዮን ቅድመ ክፍያ ጀምሮ አለ:: ቀሪ ክፍያ ቢበዛ ሦስት ዓመት:: በቻይኖች ፍጥነት ነው የሚገነባው:: ዝርዝሩ
ከስር:: 👇🏼👇🏼
2997
13:33
01.08.2025
ተጓዦቼን ወዳገር ቤት ሸኝቻለሁ:: ለጭነት ዝግጁ የሆኑትንም ጭምር እንዳይጭኑ ከልክለናል:: Coz ሀገር ቤት ላይ ቀሪ ሥራ ስለሚቀራቸው የቻይናን field work ከጨረሱ በሗላ remotely ይሠራል:: የሎጂስቲክሱን ሥራ በአካል ቢኖሩም ባይኖሩም ችግር የለም:: ዋናው ሀጃ አገር ቤት ነው:: ሁሉም ነገር እልቅ ጥንቅቅ ካለ በሗላ “የላ ጫነው" ብሎ ቁልፉን መጫን::
ከመካከላችን አንድ አሜሪካዊ ነበር:: እንግሊዝኛውን ተማምኖ በራሱ ተነሳሽነት ለሆነ ሀጃ ወጣ:: በፈጣን ባቡር 50 ደቂቃ የሚፈጅን መንገድ 26 ሰዓት ወስዶበታል:: እርሱንም ሲደክመው ጀማዓውን contact አድርጎ:: ለቻይናውያን እንግሊዝኛም ጉራጊኛም አንድ ናቸው:: እንደውም ጉራጊኛውን በተሻለ ሊረዱት ይችላሉ:: 22 ዓመት የተማርከውና የተማርክበትን እንግሊዝኛ ዋጋ የለውም:: በተለይ ወደ ቻይና ስትገቡ በቂ ዝግጅት ካላደረጋችሁና በደንብ coordinate ካልተደረገ "እዬዬዬዬ" ብላችሁ ታለቅሳላችሁ:: Why? ጎግል ካልሠራ እነርሱም ቆንቋ ካልቻሉ በምን ልትግባባ? VPN እራሱ የመንግሥት ነው:: የነጻው VPN አይሠራም:: ስለዚህ ወደ ሲስተም ለመቀላቀል የግድ ቀላቃይ ያስፈልግሃል:: ኢምንት ጉዳይ ጉዱ ብዙ ነው::
ሌላ ደግሞ የገቢዎች ሠራተኛም ነበረን:: አንድ መደዳ ከተሰለፉ ከመቶ ሺዎች ሱቆች ውስጥ ቅኝቱ ሁላ የሚያስመጣውን እቃ ሳይሆን የታሸገ ሱቅ መፈለግ ሆኗል:: የሆነ በር ላይ የተለጠፈ ሲያይ በጎግል ፎቶ መተርጎሚያ ይተረጉማል:: ማስጠንቀቂያ ከሆነ በሚል:: "በዚህ ሁሉ ሱቅ እንዴት አንድ እንኳ የታሸገ ይጠፋል?" ይላል ደጋግሞ:: እንደውም ሱሱ ብልጭ ካለበት ቻይኖቹ ከሚሸጡት Marker ሳብ አድርጎ "ታሽጓል" ብሎ ለጥፎ ጉድ እንዳይሠራን እየጠበቅነው ነበር::
1285
14:45
02.08.2025
የሕዝብ ቁጥር ማነስ ለዕድገት ችግር ቢሆን ኖሮ ኢማራት ትደኸይ ነበር:: መብዛትም ችግር ቢሆን ኖሮ ቻይና ትደኸይ ነበር:: በተፈጥሮ ሀብት መንበሽበሽ ሀብታም ቢኮን ኖሮ አፍሪካ ይሆን ነበር:: በተፈጥሮ ሀብት ማነስ ቢሆን ሲንጋፖራውያን ያኩ ይፎክቱ ነበር:: የሀብትም ይሁን የድህነት ቁልፍ ያለው አስተዳዳሪው ላይ ነው::
ወደ ኢስጠምቡል ለመድረስ መንገድ ላይ ሻይ ልጠጣ ወርጄ ቡርጅ ኸሊፋ ስር ጥላ ስር ሆኜ የተጻፈ::
2638
21:12
02.08.2025
ገራሚ መልክዓምድርና የአየር ንብረት, ከ100 ሚሊዮን በላይ ሠራተኛና ሉዓላዊ ሀገር ይዘን ዛሬም ውጭ ውጪውን እናያለን:: ዶላር እንፈልጋለን:: የመንግሥት ባለሥልጣናት አድምጡኝ:: ከፀሓይ መውጫ እስከ መጥለቂያ ያለ የኢኮኖሚክስ ዘርፍና ፍልስፍና ላይ የምርት ግብአት ከ LLC አያልፍም:: Land Labor Capital እንደማለት ነው:: ለአንድ ምርት መሠረታዊ አስፈላጊ ነገሮች መሬት, ሠራተኛና ካፒታል ናቸው:: እንደውም አንዳንድ የሌበር ቲዎሪ ሰዎች መሬት እና ላብ ብቻ ይበቃል ይላሉ:: Well, እኛ ሦስቱም በበቂ ሁኔታ አገር ውስጥ አሉን:: ሆኖም ግን ከአሸዋማ ዱባይ, ከኩርማኗ እንግሊዝ የሆነ ነገር እንፈልጋለን:: ምን እንደምንፈልግ ግን አናውቅም:: ምክንያቱም እጃችን ላይ ምን እንዳለ አናውቅም:: የሆነ የማዕድን ኤግዚቢሽን ላይ የድንጋይ ዓይነቶችን አየሁ:: አንዱ ድንጋይ ውስጡ 9 ማዕድናት ይዟል:: ወዲያው በሓሳብ ሀገር ቤት ሄድኩ:: ድሮ ጠርበን ለከብቶች መኝታ ያነጠፍናቸው ድንጋዮችን ማሰላለል ጀመርኩ:: ምክንያቱም ማዕድናቱ የሚወጡት ድንጋዩ ተፈጭቶ በተለያየ ሙቀትና ኬሚካል በማበጠር ስለሆነ ለእኛ ለጠራቢዎቹ አይገቡንም::
እንደው መሬትን ለማረስ ዶላር ምን ያደርጋል? አራሹም, ታራሹም, ማረሻውም እዚሁ ናቸው:: ለከተማ ውበት ሳርና ዛፍ መትከል ዲርሃም ወይም ዩዋን ምን ይሠራሉ? ሳሩም, ዛፉም, ተካዩም እዚሁ ናቸው:: ቢያንስ ለዜጎች የሳር ቤት ሠርቶ ለማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ምን ይሠራል? በፖለቲካል ፍልስፍና መንግሥት ያስፈለገው እኮ ቤት, መንገድ, ሰላም, ጤና, ትምህርት እንዲያሟላ ነው:: ለመከልከልና ለማፍረስ እኮ መንግሥት መሆን አያፈልግም እኮ:: ይህማ የአሸ^ባሪዎች ሚና ነው::
ከ1968 በሗላ ኢትዮጵያውያን መሬት አላገኙም:: ያኔ ያገኘ ሰው በርስት መልክ እያዋረሰ ቤተሰብ ይመሠርት ነበር:: እርሱንም ኢሕአዴግ ቀየረውና ባለሥልጣናቱ የመሬትን እጥረት በመፍጠር መቸብቸብ ውስጥ ገቡ:: አስፋፍተው ሊይዙ ሲሉ አመጽ ተነሳ:: ተበታተኑ:: ትንሽ ወጣ ስንል በላንድ ክሩዘር ተነድቶ የማያልቅ መሬት ተኝቶ ውሎ ያድራል:: አክሱም ወይም ላሊበላ ወይም ጀጎል ሲገነባ ዶላር አላስፈለገም:: እጃችን ላይ ያለውን ሀብት mobilize ማድረግ ብቻ በቂ ነው:: መሬትን የሚያስወድደው ኢንፍራስትራክቸር እንደሆነ ይታወቃል:: ውጭ ውጭውን ሳናይ የምንሠራውን መች ነካነው? መንግሥት እጁ ላይ ነጻ መሬት, ነጻ ካፒታል, በነጻነት የሚያዘው መቶ ሚሊዮን ሠራተኛ አለው:: ሆኖም ግን ሠራተኛን ያሳድዳል:: ከዚያም እድገትን ይመኛል::
ለአንዳንድ ግብዓት የውጭ ምንዛሪ ያስፈልጋል:: እርሱንም የምናገኘው እላይ በጠቀስኳቸው ግብዓቶች ቅንጅት ነው:: ለምሳሌ ሠራተኛ (labor) አለን:: ፈረንጆች እያዋጉ ካስቸገሩን ከምንተላለቅ አሰልጥነን ወደ አዋጊዎቹ ሀገሮች ፋብሪካዎች መላክና ምንዛሪ መሰብሰብ ነው::
የአፍጋኒስታን ገበሬ ለእንግሊዝና አሜሪካውያን ሀ^ሺሽ እየሸጠና እየላከ አልጀዚራ "ሀራም አይደለም ወይ?" ብሎ ጠየቀው:: እነርሱ እኛን በጥይት ሊገድሉ ሲመጡ ለጊዜው መሳሪያ ስለሌለን በቅጠላቅጠል እየተዋጋን ነው:: ቤተሰቦቻችንን ሊገ^ድሉ ለመጡ ፈረንጆች ቤተሰቦቻቸውን ለመበቀል ሀገራቸው አንሄድም:: እራሳቸው ይዘው ይሄዳሉ ያለው ነገር የሰማሁት 20 ዓመት ቢያልፈውም ዛሬ የሰማሁት ይመስለኛል:: ምንዛሪ ሲይዙብን እኛ ምንዛሪው ሀገር ሄደን ምንዛሪውን ሳይሆን ጥሬ ዕቃና ማሽን ይዘን መምጣት ነው:: ይህ አንዱ መንገድ መሆኑን ለመግለጽ እዎዳሎ::
2396
05:51
03.08.2025
imageImage preview is unavailable
ምንም ያህል ወርጅናሌ አንበሳ ብትሆኑ እንኳ የአንበሳነት ዲግሪ ብትይዙ ጥሩ ነው::
2297
07:37
03.08.2025
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
1 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
f
**biubiu@*****.com
On the service since January 2025
26.02.202518:13
5
Precise task compliance
Show more
Channel statistics
Rating
21.5
Rating reviews
5.0
Сhannel Rating
16
Subscribers:
14.2K
APV
lock_outline
ER
18.5%
Posts per day:
0.0
CPM
lock_outlineSelected
0
channels for:$0.00
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий