
Get clients in any niche!
Delegate the launch of advertising to us — for free
Learn more
23.0

Advertising on the Telegram channel «የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች»
5.0
2
Religion & Spirituality
Language:
Amharic
719
5
It teaches people about all created things, happening things and things that will happen around the world, not only the world but also in the universe.
Share
Add to favorite
Channel temporarily not accepting requests
Choose another channel from recommendations or get a tailored list within your budget using AI
AI Channel Picker
Recent Channel Posts
play_circleVideo preview is unavailable
"እናታችን ጽዮን"
እናታችን ጽዮን ይድረስሽ ምስጋና፤
መጠጊያ ማረፊያ ጥላችን ነሽና።
ከገነት ብንወጣ ማረፊያ ሆንሽን፤
የምሕረት ደመና ውኃ ሰጠሽን፤
የሕይወት እንጀራ አመጣሽልን፤
በአስራትም በአደራም ለአንቺ ተሰጠን።
አዝ
የኤልሳቤጥ አጽናኝ የጭንቅ ቀን ደራሽ፤
የኃጢአታችን ብዛት ዳገት ሳይሆንብሽ፤
ምሥራችን ደስታን ይዘሽልን መጣሽ፤
ማርያም ስንልሽ ደረስሽልን ፈጥነሽ።
አዝ
ውለታሽ ብዙ ነው ከልብ የማይጠፋ፤
ስምሽ መጽናኛ ነው አዝኖ ለተከፋ፤
በእንተ ማርያም ብሎ ለለመነ፤
የሰማይ የምድርም ማንም አልጨከነ።
አዝ
በትራችን አንች ነሽ የምትደግፊን፤
ባሕረ እሳትን የምታሳልፊን፤
ጽርሐ ሥላሴ ነሽ ማኅደረ መለኮት፤
ሁልጊዜ አንጠግብሽም እንላለን ብጽእት።
አዝ
©በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2160
15:06
29.11.2024
imageImage preview is unavailable
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2090
15:06
29.11.2024
ኅዳር ፳፩
ጽዮን ማርያም
ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓሏ መታሰቢያ ነው።
“ታቦተ ጽዮን” የሚለውንም ስያሜ ያገኘችው ጽዮን ተብላ በምትጠራው የእስራኤል ከተማ ስም ነው፡፡ ጽዮን ማለት ተፀወነ፡ ተጠጋ፣ ተማጠነ ማለት ነው፡፡ ክቡረ ዳዊትም ጽዮንን አምባ፣ መጠጊያ አድርጎ ብዙ ጠላቶቹን ተዋግቶ አሸንፎ ድልን ተጎናጽፏል።
ጽዮን የተባለችው የታላቁ የዳዊት ከተማ የተገፉና የተበደሉ ሕዝቦች ሁሉ እውነተኛ ፍርድ ለማግኘት፣ ተሰብስበው የሚሰነብቱባት ከተማ ስለነበረች፣ ጽላተ ሙሴም በዚያ ስለነበረች በርሷ ተማጽነውም ችግራቸው ሰለሚቃለል ታቦቷ “ታቦተ ጽዮን” ተብላለች፡፡
ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን፣ ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች። "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው። "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው።
"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው። ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል። ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው። በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን። (2ቆሮ.6፥16 ፣ ራዕይ.11፥19)
የአምላክ ማደሪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በቃል ኪዳን ታቦት ትመሰላለች ይኽቺም ፦
✿ የእግዚአብሔር የጌትነቱ መግለጫ የኾነችው፤
✿ በፍልስጥኤም ይመለክ የነበረ ጣዖትን ቀጥቅጣ ያጠፋች፤
✿ በድፍረት ሊነካት የሞከረ ኦዛን የቀሰፈች፤
✿ በታላቅ ክብር ወደ ሀገሯ ስትመለስ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በታላቅ መንፈሳዊ ደስታ በፊቷ የዘመረላት ፤
✿ ልጁ ሰሎሞንም ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርቶ በክብር ያኖራት ናት፡፡
ጌታ የታቦቷን አሠራር ሲነግረው "ሽምሽር ስጢን ከሚባል ከማይነቅዝ እንጨት ቀርጸኽ አብጅ ከታች እንደ ዙፋን አራት እግር አውጣለት ሞላልነቱን ኹለት ክንድ ከስንዝር ቁመቱ ክንድ ከስንዝር ወርዱን ክንድ ከስንዝር ኹለት ክንድ ከስንዝር ምስሃል ለዚኽ ቁመት የለውም አራት ቀለበት ኹለት ሙሎጊያ አበጅለት አፍአውን ውስጡን በንጹሕ ወርቅ ለብጠው በምስማኩና በምስማኩ ኹለቱን ኪሩቤል እንደሚናተፉ አውራ ዶሮዎች አንገታቸውን ደፋ አድርገኽ በላይ ሣልበት ዙሪያውን ፈለግ አውጣለት ብጽብጽ ወርቅ አፍስበት ጽላቶቹን በውስጡ አኑር" ብሎታል፡፡
ይኸውም ምሳሌ
✅ታቦት ፡- የእመቤታችን
✅ወርቅ፡- የንጽሕናዋ የቅድስናዋ
✅ታቹ መቀመጫው ፡- የንጽሓት እንስት
✅ላዩ መግጠሚያው ፡- የንጹሓን አበው
✅ግራ ቀኙ ፡- የሐና የኢያቄም
✅ወደ ውስጥ የገባችው:-የድንግል ማርያም ያቺ በመኻከላቸወም እንደኾነች እመቤታችንም ከሐና ከኤያቂም ለመገኘቷ ምሳሌ ነው።
✅ኹለት ክንድ ከስንዝር:- ከአዳም እስከ ኖኅ ባለው ዘመን 2260 ዘመን ይመስላል ይኸውም በኖኅ ዘመን አርአያ ድንግል ታቦተ ኖኅ ለመገኘቷ ምሳሌ፡፡
✅አንድ ክንድ ከስንዝር ቁመቱ :- ከኖኅ እስከ ሙሴ ባለው ዘመን ይመስላል ይኸውም 1600 ዘመን ነው። በዚህ ዘመን አርአያ ድንግል ጽላተ ሙሴ ለመገኘቷ ምሳሌ ነው፡፡
✅አንድ ክንድ ከስንዝር ወርዱ:- ከሙሴ እስከ እመቤታችን ባለው ዘመን ይመስላል ይኽውም 1640 ዘመን ይኾናል ይኽ በኾነ አርአያ ድንግል ታቦተ ኖኅ አርአያ ድንግል ጽላተ ሙሴ ምሳሌዎቿ የሚሆኑ አማናዊት ድንግል ማርያም ለመገኘቷ ምሳሌ ነው፡፡
✅አራቱ ቀለበት:- የአራት ወገን ንጽሕናዋ ምሳሌ ይኸውም ከርእይ /ኃጢአትን ከማየት/፤ ከሰሚዕ/ኃጢአትን ከመስማት/ ፤ ከገሲስ/በእጅ ዳሰሶ ኃጢአትን ከመሥራት እና ከአጼንዎ /የኃጢአት መዐዛን ከማሽተት/ እመቤታችን ከነዚኽ ኹሉ ተጠብቃለችና
✅ኹለቱ ቀለበት:- የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ ምሳሌ
✅ኹለቱ ሥዕለ ኪሩቤል:- የጠባቂ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልና የአብሳሪ መልአክ የቅዱስ ገብርኤል ምሳሌ ናቸው ይኽውም የብሉይ ሊቀ ካህናት በዓመት አንድ ቀን ገብቶ ከኹለቱ ኪሩቤል መካከል ቃል ሰምቶ ይወጣ ነበር ቅድስት ድንግል ማርያም በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ተጠብቃ ከቅዱስ ገብርኤል ቃል ሰምታ አካላዊ ቃልን በግብረ መንፈስ ቅዱስ ያለ ዘር ያለ ሩካቤ ፀንሳ ተገኝታለችና።
ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ይኽንን መንፈሳዊ ምስጢር በጥልቅት በመመርመር ድንግል ማርያምን ፡-
👉በምስጢር የተመላች ታቦት
👉 እሳትን የተመላች ታቦት
👉የቅዱስ ቃል ታቦት
👉የቃል ኪዳን ታቦት በማለት ገልጿታል፡፡
ኅዳር 21 ቀን የሚከበረውም የእመቤታችን ምሳሌዎች የተገለጡበት እና የተለያዩ ሥራዎች የተሰሩበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ እነዚህም፡-
1. ነቢዩ ዘካርያስ ሁለንተናው ወርቅ የሆነ፣ የዘይት ማሰሮ በራሱ ላይ የነበረበትንና ሰባት መብራቶች ያሉትን መቅረዝ ሲያበራ ያየበት ዕለት ነው፡፡ ዘካ. 4፤1-2። ዘካርያስ ያየው ብርሃን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ ዮሐ. 8፤12፡፡ ይህ ብርሃን የታየባትና የተገለጠባት መቅረዝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡ ብርሃን መቅረዝ እንዲያዝና እንዲገለጥ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ተገልጦልናል፡፡ ጨለማ ዓለምን አብርቷል፡፡ ብርሃን ክርስቶስን ወልዳለችና እርሷም እመ ብርሃን / የብርሃን እናት/ ትባላለች፡፡
2. ታቦተ ጽዮን ዳጎንን ገልብጣ በመጣል ኃይሏን የገለጠችበት ዕለት ነው፡፡ በፍልስጥኤማውያን ተማርካ ቤተ ጣዖት ወስደው ከጣዖታቸው ከዳጎን በታች አስቀምጠዋት ነበር፡፡ ታቦተ ጽዮን ግን በላይዋ ያለውን ዳጎንን ገልብጣ ጥላ እርሷ ከላይ ተቀመጠች፡፡ በታቦት የሚገለጠው የእግዚአብሔር ኃይል ነው፡፡ ምክንያቱም በታቦቱ ላይ ያለው ሕገ እግዚአብሔርና ስመ እግዚአብሔር ነው፡፡ የእግዚአብሔር ስም የጸና ክንድ ነውና ሁሉን ያሸንፋል። ስለዚህ ምንም እንኳ ለጊዜው ስትማረክ ደካማ ብትመስልም መማረኳ ግን ኃይሏን ለመግለጥ፣ ለአሕዛብ የጣዖትን ከንቱነት የታቦትን ክቡርነት ለመግለጥ ነበር፡፡
3. ቀዳማዊ ምኒልክ ታቦቱን ይዞ አክሱም የገባበት፣ ንግሥት ሳባ ታላቅ በዓል አድርጋ የተቀበለችበት፣
4. አብረሃ ወአጽብሐ በአክሱም ከተማ 12 ቤተ መቅደስ ያለው ቤተ ክርስቲያን በአስደናቂ ሁኔታ ሠርተው ከጨረሱ በኋላ ቅዳሴ ቤቱን ያከበሩበት፣ እንዲሁም
5. በ9ኛው መ/ክ/ዘመን ዮዲት ክርስትና ለማጥፋት በተነሳች ጊዜ በእርሷ ምክንያት ታቦተ ጽዮን ወደ ዝዋይ ሐይቅ የተሰደደችበት፡፡ በኋላም የሰላሙ ዘመን ሲመጣ ተመልሳ አክሱም የገባችበት በዚሁ በኅዳር 21 ስለሆነ በእነዚህ በተደራራቢ ታሪኮች ምክንያት በየዓመቱ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል “ኅዳር ጽዮን በአክሱም ጽዮን” የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡
የእመቤታችን ልመናዋ ክብሯ አማላጅነቷም ከእኛ ከህዝበ ክርስቲያን ጋር ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር! አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2337
15:06
29.11.2024
imageImage preview is unavailable
መምህር ኢዮብ ይመኑ እባላለሁ!
በኢኦተቤ ሰባኬ ወንጌል ነኝ!
መምህራን በተለያዩ ቦታዎች እየተዘዋወርን ወንጌልን እናዳርሳለን! እርስዎ የማኅበረ ቅዱሳንን ዩቱዩብ ሰብስክራይብ በማድረግና በማጋራት ብቻ ወንጌልን ለዓለም ማድረስ እንደሚችሉ ያውቃሉ?
እኔ ዘመቻውን ተቀላቅያለሁ እናንተስ?
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
3789
17:13
26.11.2024
play_circleVideo preview is unavailable
ፈቃዴ ነውፈቃዴ ነው የሰውን ነገር ላልናገር/፪/ የእኔ ተሸፍኖ ከቆምኩኝ በክብር ፈቃዴ ነው የሰውን ነገር ላልናገር
አዝ.....ሕይወቴ በሙሉ በኃጢአት ተሞልታ አምላኬ ከማረኝ በፍቅሩ ዝምታ የሰው በደል ላላይ በእውነት ምያለሁ እኔን ከታገሠኝ ፍቅር ተምሬያለሁ/፪/
አዝ.....በዐይኔ ፊት ተጋርዶ ያለውን ምሶሶ እያየ ካለፈኝ በምሕረት ታግሦ የሰው በደል ላላይ በእውነት ምያለሁ እኔን ከታገሠኝ ፍቅር ተምሬያለሁ /፪/
አዝ.....አንተ ቀራጩ ሰው ያለህ አቀርቅረህ በምሕረት ተመለስክ ከእኔ ይልቅ ድነህ በአንተ ላይ ስጠቁም የእኔን ጸሎት ትቼ የመዳኑ ሰዐት አለፉ ቀኖቼ/፪/
አዝ.....ተቆጥሮ የማያልቅ ኃጢአቴ ተጠርቶ በሞትና በደል በኃጢአት ሸፍኖ ሰው አርጎ አቁሞኝ በሰው ፊት ጌታዬ በማንም አልፈርድም ኃጢአተኛ ብዬ በማንም አልፈርድም በደለኛ ብዬ
አዝ.....ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
4200
13:26
25.11.2024
play_circleVideo preview is unavailable
"ፈቃዴ ይህ ነው"
ፈቃዴ ይህ ነው የሰውን ነገር ላልናገር/፪/
የእኔ ተሸፍኖ ከቆምኩኝ በክብር
ፈቃዴ ነው የሰውን ነገር ላልናገር
አዝ.....ሕይወቴ በሙሉ በኃጢአት ተሞልታ አምላኬ ከማረኝ በፍቅሩ ዝምታ የሰው በደል ላላይ በእውነት ምያለሁ እኔን ከታገሠኝ ፍቅር ተምሬያለሁ/፪/
አዝ.....በዐይኔ ፊት ተጋርዶ ያለውን ምሶሶ እያየ ካለፈኝ በምሕረት ታግሦ የሰው በደል ላላይ በእውነት ምያለሁ እኔን ከታገሠኝ ፍቅር ተምሬያለሁ /፪/
አዝ.....አንተ ቀራጩ ሰው ያለህ አቀርቅረህ በምሕረት ተመለስክ ከእኔ ይልቅ ድነህ በአንተ ላይ ስጠቁም የእኔን ጸሎት ትቼ የመዳኑ ሰዐት አለፉ ቀኖቼ/፪/
አዝ.....ተቆጥሮ የማያልቅ በደሌ ተከድኖ በሞትና በደል ኃጢአቴን ሸፍኖ ሰው አርጎኝ በሰው ፊት አቁሞኝ ጌታዬ በማንም አልፈርድም ኃጢአተኛ ብዬ በማንም አልፈርድም በደለኛ ብዬ
አዝ.....ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
4200
13:26
25.11.2024
imageImage preview is unavailable
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
3483
13:26
25.11.2024
close
New items
Selected
0
channels for:$0.00
Followers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий