
🎙Zena Adis Ethiopia🎙
"Zena Addis Ethiopian is a premier Telegram news outlet providing rapid, reliable, and up-to-the-minute information on Ethiopian current affairs. We cover breaking news, social issues, and local developments that matter to the Ethiopian community.
Channel statistics
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የናይጄሪያ ዜጎች የሚናገሩት እንግሊዝኛ ቋንቋ ለመረዳት የማይቻል እና ተርጓሚ ያስፈልገዋል ብለው በይፋ ከገለጹ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።ሰኞ እለት በጣሊያን ለሚኖሩ ኬንያውያን ንግግር ያደረጉት ሩቶ ናይጄሪያዊ ሲናገሩ የምትሰሙ ከሆነ የሚናገሩትን አታውቁም ፤ተርጓሚ ያስፈልጋችኃል በማለት ኬንያውያን “በአለም ላይ ካሉ ምርጥ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህ ንግግራቸዉ ግን የአፍሪካን ሀገር አዋርደዋክ ሲሉ የተቹት ናይጄሪያውያን እና ሌሎች አፍሪካውያን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ውግዘት አስከትሏል።የዚምባብዌ ጋዜጠኛ ሆፕዌል ቺኖኖ "እንግሊዘኛ የቅኝ ግዛት ቋንቋ እንጂ የእውቀት፣ የችሎታ ወይም የሀገር እድገት መለኪያ አይደለም" ሲል ጽፏል።
የቀድሞ የብሪታንያ ቅኝ ግዛቶች የሆኑት ሁለቱም ኬንያ እና ናይጄሪያ እንግሊዘኛን እንደ ይፋዊ ቋንቋ ይጠቀማሉ፣ ነገር ግን እያንዳንዱ ሀገር የተለያየ የፎነቲክ አወቃቀሮች ያሏቸው የተለያዩ የንግግር ዘዬን አዘጋጅተዋል።እነዚህ ልዩነቶች የአገሬው ተወላጆችን ተፅእኖ የሚያንፀባርቁ ናቸው፡፡ ናይጄሪያ ከ 500 በላይ ቋንቋዎች ያሏት ሲሆን ኬንያ ደግሞ ባንቱ ፣ ኒሎቲክ እና ኩሺቲክ ድብልቅ የራሷን የእንግሊዘኛ ንግግሮች ያስገኛሉ።
ነገር ግን ሩቶ ለዲያስፖራዎች ስብስብ ባደረጉት ንግግር የኬንያ የትምህርት ስርዓት ጠንካራ የእንግሊዘኛ ቋንቋን ያዳብራል በማለት ናይጄሪያውያን እንግሊዝኛ ሲናገሩ ለመረዳት አዳጋች ነው ብለዋል።
#Zena_Addis_Ethiopian
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንኩን ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በከፈተው የፖለቲካ አካዳሚ ከ50 በላይ አባላቱን ማሠልጠኑን አስታውቋል።
የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኢዩኤል ሰለሞን ለአሐዱ ሬዲዮ እንደተናገሩት፤ አካዳሚው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሥልጠና በመስጠት ዓላማውን ማሳካት የሚችሉ ግለሰቦችን ለማፍራት ታስቦ የተመሠረተ ነው።
አካዳሚውን የመገንባት እቅድ ፓርቲው ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ሲታሰብ የነበረ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በይፋ ሥራ መጀመሩ ተገልጿል።
አካዳሚው ሥራ ከጀመረ በኋላ በአዲስ አበባ በሚገኙ አባላቱ ላይ ያተኮሩ ሁለት ዙር ሥልጠናዎችን ሰጥቷል።
ይሁን እንጂ የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መቃረብን ተከትሎ በመጡ ተደራራቢ ሥራዎች ሳቢያ ሥልጠናውን ለጊዜው ማስቀጠል እንዳልተቻለ ኃላፊው ገልጸዋል።
ከምርጫው መጠናቀቅ በኋላ ግን በዋናነት ከአባላት ውጭ ለሆኑና መማር ለሚፈልጉ ዜጎች ዕድሉን ለማመቻቸት መታቀዱን ለአሐዱ ሬድዮ በደረሰው መረጃ ተመልክቷል።
በአካል ተገኝቶ ሥልጠናውን ለመካፈል ለማይችሉ ሰዎች በበይነ መረብ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አቶ ኢዩኤል ጠቁመዋል።
በአካዳሚው ገብቶ ሥልጠና የሚወስድ ማንኛውም ሰው የኢዜማ አባል ይሆናል ማለት እንዳልሆነም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
#Zena_Addis_Ethiopian
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንኩን ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአኅጉር ደረጃ ዘርፉን እንዲመሩ የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ሹመቱን እንደሰጣቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ በዘርፉ እያሳየች ያለው ተሞክሮ እውቅና ማግኘቱ፣ በሀገሪቱ የተቋቋመው የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ኢንስቲትዩት እና የተቀረጸው ብሔራዊ ስትራቴጂ ውጤታማነት ተመራጭ እንዳደረጋቸው ፅ/ቤታቸው የሹመት ደብዳቤውን ጠቅሶ ገልጿል፡፡
አኅጉራዊው ሹመት ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ነፃነት እና በክህሎት ልማት የምታደርገውን እንቅስቃሴ ለአፍሪካ አህጉር ተሞክሮ እንዲሆን ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርም ተመላክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው የካቲት ወር የኅብረቱ የሰው ሠራሽ አስተውህሎትና ዲጂታል ጤና አምባሳደር ሆነው መሾማችው ይታወሳል።
#Zena_Addis_Ethiopian
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንኩን ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
የትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ የሚያደረገዉን ሰፈራ ካስቆሙ በኃላ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ኃይሎችን ያገዙ የአፍጋኒስታን ዜጎች ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሊላኩ እንደሚችሉ አንድ ዘገባ አመልክቷል።
ተሟጋች ቡድኖችን እና ባለስልጣናትን በመጥቀስ ኤቢሲ ኒውስ እንደዘገበው ለትርፍ ያልተቋቋመዉ እና የተጠፋፉ ሰዎችን በማገናኘት ላይ የሚሰራዉ የአፍጋኒስታን ኢቫክ ኃላፊ የሆኑት ሾን ቫንዳይቨር 1,100 የሚጠጉ አፍጋኒስታን አስተርጓሚዎችን እና ቤተሰቦቻቸዉን ጨምሮ በአሜሪካ በሚተዳደረው ተቋም ዶሃ ውስጥ እንደሚገኙ እና ወደ ኮንጎ እንዲዛወሩ ወይም ወደ አፍጋኒስታን እንዲመለሱ ሊደረግ ይችላል ተብሏል።
እቅዱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘገበው በኒውዮርክ ታይምስ ነበር።የዩናይትድ ስቴት ዲፓርትመንት “በፍቃደኝነት የሰፈራ” አማራጮችን እየተከታተለ ነው ብሏል፤ ነገር ግን ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ አልሰጠም ሆኖም ወደ ሶስተኛ ሀገር መዛወሩን “አዎንታዊ መፍትሄ” ብሏል።
ቫንዳይቨር እርምጃው ተጋላጭ የሆኑትን የአፍጋኒስታን ዜጎችን ወደ አደጋ የመመለስ ስጋት እንዳለው አስጠንቅቋል፡፡ 1,100 አፍጋኒስታንን ወደ አፍጋኒስታን ለመላክ እየሞከሩ ፤ ይህን እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ሽፋን በመጠቀም ነዉ ሲሉ አክለዋል።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ኮንጎ የከፋ መፈናቀል ቀውስ ውስጥ ገብታለች፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በቀጠለው ግጭት ለስደት ተዳርገዋል፡፡ቫንዳይቨር አክለውም "የዓለምን ቁጥር 1 የስደተኞች ቀውስ ያለባቸዉን ወደ ዓለም ቁጥር 2 ሀገር ወስዶ መጣል የስደተኞችን ቀውስ አይፈታውም" ብለዋል፡፡
#Zena_Addis_Ethiopian
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንኩን ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
በህገ ወጦች ተይዘናል በማለት ቤተሰቦቻቸው 3መቶ ሺ ብር እንዲልኩላቸው የጠየቁ ታዳጊዎች ከአነ ግብረ አበሮቻቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው የካ አባዶ አካባቢ ነው፡፡ የ15 እና የ16 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት ታዳጊዎቹ ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ/ም ለትምህርት ብለው እንደወጡ ሳይመለሱ ይቀራሉ፡፡
በልጆቹ መጥፋት ቤተሰቦቻቸው ተጨንቀው በነበሩበት ወቅት ታዳጊዎቹ ስልክ በመደወል 3መቶ ሺህ ብር እንዲላክላቸው ነገር ግን ገንዘቡ ካልተላከላቸው የያዟቸው ግለሰቦች ጉዳት ሊያደርሱባቸው መሆኑን ይገልፃሉ፡፡
የወንጀሉ ጉዳይ ሪፖርት የደረሰው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ክትትል እና ፍለጋ ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ታዳጊዎቹን ከሁለት ወንዶች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡
ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ታዳጊዎቹ ከሁለት ወንድ ጓደኞቻቸው ጋር ሲዝናኑ እንደነበር ያረጋገጠ ሲሆን አራቱን ታዳጊዎች እና ለታዳጊዎቹ የመኝታ ክፍል ያከራየን ግለሰብ ይዞ ምርመራው መቀጠሉን ገልጿል፡፡
ወደ ውጭ ሀገር ለመሄድ አስበው እና ተነጋግረው ድርጊቱን አቀነባብረው እንደፈፀሙት ታዳጊዎቹ ለፖሊስ ከሰጡት ቃል መረዳት ተችሏል፡፡
ሆቴል ቤቶች ሆኑ የመኝታ ክፍል የሚያከራዩ ተቋማት ለህፃናት ሆነ ለታዳጊዎች የመኝታ ክፍል ማከራየትና አልኮል መጠጥ መሸጥ እንደሌለባቸው ፖሊስ አሳስቦ ቤተሰብም ልጆቻቸው የት እና ከእነ ማን ጋር እንደሚውሉ የማረጋገጥ ልምድ ሊያደብር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
#Zena_Addis_Ethiopian
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንኩን ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
የኢትዮጵያ የጥበብና የእምነት ብርሃን ዓለምን አስደመመ!
(በጉርሻ ፔጅ የተዘጋጀ ልዩ ዘገባ)
ከ7.9 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉትና በርካታ አሜሪካውያን የሚከታተሉት "Donald Trump For President" የተባለው ታዋቂ የፌስቡክ ገጽ፣ በባለፈው በኢትዮጵያ የተከበረውን ሥነ-ሥርዓት አስመልክቶ እጅግ የሚመስጥ ዘገባ አጋርቷል።
"በኢትዮጵያ የታየው ግዙፍ እምነት" በሚል ርዕስ የቀረበው ይህ ዘገባ፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በነጭ ባህላዊ ልብስ አጊጠው፣ በጧፍና በሻማ ብርሃን ደምቀው ያሳዩትን የአንድነትና የጸሎት ሥነ-ሥርዓት በድሮን የተቀረጸ ምስል አያይዞ አቅርቧል።
ዘገባው ምን ይላል?
ጋዜጣዊ ይዘት ያለው ይህ ጽሁፍ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስቷል፦
1. ኢትዮጵያ ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ እምነቷን ጠብቃ የቆየች ጥንታዊት ሀገር መሆኗንና የዓለም ሥልጣኔ በሌላ አቅጣጫ ቢጓዝም፣ ኢትዮጵያውያን ግን በእምነታቸው ጽኑ መሆናቸውን ገልጿል።
2. ምዕመናኑ ለ55 ቀናት በጥብቅ ከጾሙ በኋላ፣ የክርስቶስን ስቅለትና ትንሣኤ ለመዘከር ያሳዩት ቁርጠኝነት "ታላቅ የእምነት ማሳያ" ተብሎ ተገልጿል።
3. በምዕራቡ ዓለም ሃይማኖታዊ እሴቶች እየተዳከሙ በመጡበት በዚህ ዘመን፣ ይህች የአፍሪካ ሀገር እውነተኛ ታማኝነትና መንፈሳዊነት ምን እንደሚመስል ለዓለም ትልቅ ትምህርት እየሰጠች መሆኑን ዘገባው ይገልጻል።
ይህንን የፌስቡክ ገጽ ከአሜሪካ የሚገኙ አራት ግለሰቦች የሚያስተዳድሩት ሲሆን፣ ዘገባውን ዶናልድ ትራምፕ ራሳቸው ሊመለከቱት እንደሚችሉ ተገምቷል።
በብዙ ሚሊዮኖች ዘንድ የተጋራው ይህ መረጃ፣ ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ገጽታ ግንባታ እና ለሕዝቡ መንፈሳዊ ጥንካሬ ትልቅ እውቅና የሰጠ ሆኗል።
ዘገባው "ኢትዮጵያ የእምነትና የተስፋ ብርሃን ሆና ትቀጥላለች!" በሚሉ አስተያየቶች ታጅቦ፣ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ 'ላይክ'፣ 'ኮሜንት' እና 'ሼር' እያገኘ ይገኛል።
ጉርሻ page
#Zena_Addis_Ethiopian
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንኩን ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
ከኢራን ጋር በእግረኛ ጦርነት ካልተደረገ በስተቀር ምንም መፍትሄ የለም' ሲሉ 'የሳውዲ ንጉሣዊ ቤተሰብ' ለ N12 ገልፀዋል።
እ.ኤ.አ 'በ 2003 በሳዳም አገዛዝ ላይ የተካሄደው የመሬት ላይ ጦርነት በኢራን ላይ መደገም አለበት፣'የኢራን መንግስት የኒውክሌር አላማ ስላለው በጣም አደገኛ ነው ብለዋል።
ለዚህ ብቸኛው መፍትሔ ወደ ኢራን እግረኛ ጦር ማስገባት ነው፣ ሌላ መፍትሔ የለውም ብለዋል።
#Zena_Addis_Ethiopian
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንኩን ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
በዓለም ላይ ትልቁ የሚታወቀው የዱር ቺምፓንዚዎች ቡድን ለሁለት ተከፍሎ በአስከፊ "የእርስ በርስ ጦርነት" ውስጥ መቆየቱን ተመራማሪዎች ገለጹ።
በአንድ ወቅት በኡጋንዳ ኪባሌ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኘው የንጎጎ ቺምፓንዚ ማህበረሰብ ለምን ግጭት ውስጥ እንደገባ በትክክል ግልፅ ባይሆንም፣ ከ2018 ጀምሮ ግን ሳይንቲስቶች 17 ጨቅላዎችን ጨምሮ 24 ግድያዎች መዝግበዋል።
አሮን ሳንደል “እነዚህ እጆችን የሚጨብጡ ቺምፖች ነበሩ” ብሏል። "አሁን ግን እርስ በርስ ለመገዳደል እየሞከሩ ነው" ሳይንስ በተባለው ጆርናል ላይ የታተመው ጥናቱ የጥቃት ጥንካሬ እና የቆይታ ጊዜው የሰው ልጅ እንዴት ግጭት እንደተፈጠረበት በራሱ ላይ ሊያውቅ ይችልበታል ብሏል።
በአሜሪካ የቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ አንትሮፖሎጂስት እና የንጎጎ ቺምፓንዚ ፕሮጀክት ተባባሪ ዳይሬክተር ሳንደል ቺምፓንዚዎች “በጣም ክልላዊ” እንደሆኑ እና “ከሌሎች ቡድኖች ጋር የጥላቻ ግንኙነት አላቸው” ብለዋል።
ለሳይንስ ፖድካስት " የማያውቁትን የመፍራት ባህሪ ይታይባቸዋ" ብለዋል። ነገር ግን በበርካታ አስርት አመታት ውስጥ፣ ሳንደል ወደ 200 የሚጠጉ የንጎጎ ቺምፓንዚዎች ተስማምተው እንደኖሩ ተናግሯል።አሁን ግን ባለመግባባት ጎራ ለይተው እየተፋለሙ ይገኛል።
#Zena_Addis_Ethiopian
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንኩን ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
ባለፉት ጥቂት ቀናት በጅቡቲ ወደብ ተከስቶ የነበረው የቴክኒክ እና የሎጅስቲክስ መስተጓጎል በመፈታቱ፣ በርካታ የነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ወደ ሀገር ውስጥ መግባት መጀመራቸውን የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
ይህንንም ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ ዴፖዎች ነዳጅ በማራገፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ፈጣን የሆነ የስርጭት ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
በአዋሽ፣ ሱሉልታ፣ አቃቂ፣ ኮምቦልቻ፣ ሻሸመኔ፣ ባህር ዳር እና ጎንደር የሚገኙ ዋና ዋና ዴፖዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ ደርሷቸዋል።
መንግስት በዓለም አቀፍ ደረጃ (በተለይም በሆርሙዝ ወሽመጥ አካባቢ) በተከሰተው ቀውስ ምክንያት አጋጥሞ የነበረውን አቅርቦት ለማካካስ ተጨማሪ ግዢዎችን በመፈጸም እና ስርጭቱን በማፋጠን ላይ ይገኛል።
የነዳጅ ቦቴዎች ማደያዎች ላይ ደርሰው ማራገፍ በመጀመራቸው፣ በተለይም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የታየው ረጅም የሰልፍ ተርታ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚቀንስ ይጠበቃል።
ስርጭቱ ፍትሃዊ እንዲሆንና ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለመከላከል ጥብቅ የክትትል ስራ እየተሰራ መሆኑን የሚመለከታቸው አካላት ገልጸዋል።
ይህ እርምጃ በሀገሪቱ የትራንስፖርት እና የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተፈጥሮ የነበረውን ጫና በማቃለል ረገድ ትልቅ እፎይታ እንደሚሰጥ ይታመናል። ኢትዮጵያ በዋናነት ነዳጅ የምትገዛው ከኩዮት የነበረ ቢሆንም የሆርሙዝ ሰርጥ በመዘጋቱ ከህንድ እና ከሌሎች ሀገራት የተገዛ ነዳጅ በሶስት መርከቦች ተጭኖ በቅርቡ ጅቡቲ መግባቱን መዘገባችን ይታወሳል።
#Zena_Addis_Ethiopian
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንኩን ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
🇪🇹🇸🇸 የሀገሪቱ ሲቪል አቪዬሽን ልዑካን ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዮሐንስ አበራ ጋር በአዲስ አበባ ውይይት አድርገዋል፡፡
የደቡብ ሱዳን ትራንስፖርት ሚኒስቴር ምክትል ዋና ፀሐፊ ፖል ቼል ገም፣ ድጋፉን ተግባራዊ ለማድረግ የሁለትዮሽ የአየር አገልግሎት ስምምነት ከኢትዮጵያ ጋር ለመፈራረም እንደሚፈልጉ አብራርተዋል፡፡
🗣 ዮሐንስ አበራ በበኩላቸው፣ “ጠንካራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የሌላት ሀገር ጠንካራ አየር መንገድ ሊኖራት አይችልም፤ እኛ ከዚህ አንፃር ከ80 ዓመታት በላይ ልምድ ያለን በመሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደምናደርግላችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡” ብለዋል፡፡
📝 ሁለቱ ወገኖች የአየር አገልግሎት ስምምነት በቅርቡ እንደሚፈራረሙ ከውይይታቸው መረዳት እንደተቻለም ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡ ስፑትኒክ
#Zena_Addis_Ethiopian
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንኩን ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
Reviews channel
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
🎙Zena Adis Ethiopia🎙 is a Telegram channel in the category «Образование», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 35.8K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 17.7, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 18.0 ₽, and with 2 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий