
Channel statistics
ባህሉል የአካባቢውን ሀብታም ሰው ጋር ሄዶ፤
...
"እባክህን ዛሬ እንግዳ ስላለብኝ አንድ ትልቅ ማሰሮ አበድረኝ” አለው። ሰውየውም ፈቅዶ አበደረው።
...
ከጥቂት ቀናት በኋላ ባህሉል ማሰሮውን ሊመልስ መጣ። ነገር ግን ከትልቁ ማሰሮ ውስጥ ሌላ ትንሽ ማሰሮ ጨምሮ ነበር።
...
ባለቤቱም"ይህች ትንሽ ማሰሮ የማን ናት?" ሲል ጠየቀው። ባህሉልም በቁምነገር "ትላንት ማታ ማሰሮህ እኔ ቤት ሳለች ምጥ በምጥ ተይዛ ይቺን ትንሿን ማሰሮ ወለደች። ስለዚህ ልጇ ስለሆነች ካንተ ጋር ልትሄድ ይገባል።" አለው።
..
ሰውየው በልቡ "ይህ እብድ ነው። " እያለ በነጻ ማሰሮ ስላገኘ ደስ ብሎት ተቀበለው።
..
ከሳምንት በኋላ ባህሉል እንደገና ሄዶ፤ "እባክህ ያንን ትልቅ ማሰሮህን ድጋሚ አበድረኝ።" አለው።
...
ሰውየውም ሳያቅማማ ወዲያውኑ ሰጠው።
ሳምንታት አለፉ፣ ባህሉል ግን ማሰሮውን አልመለሰም። ሰውየው ትዕግስቱ አልቆ ወደ ባህሉል ቤት ሄዶ።
...
"ማሰሮዬ የት አለ? ለም አትመልስልኝም?" አለው። ባህሉልም በሀዘን ፊቱን አክስሎ። "በጣም አዝናለሁ ወዳጄ፣ ማሰሮህ ትላንት ማታ በምጥ ላይ እያለች ታማ ሞተች።"አለው።
..
ሰውየው በቁጣ እየጮኸ "ለመሆኑ አእምሮ አለህ? ማሰሮ ግዑዝ ነገር ሆኖ ይሞታል?" አለው።
...
ባህሉልም በረጅሙ ተንፍሶ "ለመሆኑ ማሰሮ ሲወልድ የምታምንበት አእምሮህ፣ ማሰሮ ሲሞት ለምን ማመን አቀተው? መወለድ ባለበት ቦታ ሁሉ መሞትም አለ!"
...
ብዙዎቻችን ጥቅምን ያለምንም ጥያቄ እንቀበላለን፤ ጉዳትን ወይም ማጣትን ግን አንቀበልም። አንድን ህግ ለጥቅምህ ስትቀበለው፣ ያው ህግ ጉዳት ይዞ ሲመጣም የመቀበል ግዴታ አለብህ።ንታዊቷ ጃፓን አንድ ወጣት ነበር። ይህ ወጣት በጣም ብሩህ አዕምሮ ቢኖረውም አንድ ትልቅ ችግር ነበረበት። እጅግ በጣም ሰነፍና ነገሮችን ነገ 'አስራለሁ እያለ' ስራዎችን የሚያሳድር ነበር።
...
አባቱ አንድ ስራ ሲሰጡት "ነገ ጠዋት በጊዜ ተነስቼ እሰራዋለሁ" ይላል። ጠዋት ሲሆን ደግሞ "ከሰዓት በኋላ ብሰራው ይሻላል" ይላል። በዚህ ሁኔታ ቀኖቹ በከንቱ ያልፋሉ።
...
አንድ ቀን አባቱ ወጣቱን ወደ አንድ ትልቅ ኮረብታ ወሰዱት። ኮረብታው ላይ ሲደርሱ አባቱ ለወጣቱ አንድ ባዶ የሻይ ኩባያ ሰጡትና "ይህንን ኩባያ እስከ ምሽት ድረስ እጅህን ሳታወርደው ይዘህ ቁም" አሉት።
...
ወጣቱም "ይህማ ቀላል ነው፤ ኩባያው ባዶ ነው፣ ምንም አይከብድም" ብሎ አሰበ። የመጀመሪያው አንድ ሰዓት ቀላል ነበር። ነገር ግን ሁለት ሰዓት፣ ሦስት ሰዓት እያለ ሲሄድ ያ ባዶ ኩባያ እንደ ድንጋይ እየከበደው መጣ።
...
እጁ መንቀጥቀጥ ጀመረ፣ ትከሻውም በህመም ሊቀደድ ደረሰ። በመጨረሻም አባቱ መጥተው "እንዴት ነው? ኩባያው ከበደህ?" ብለው ጠየቁት።
...
ወጣቱም በስቃይ ሆኖ "አባቴ! ኩባያው ባዶ ቢሆንም፣ ረጅም ሰዓት ስለያዝኩት ሊገድለኝ ነው!" ሲል መለሰ።
..
አባቱም ኩባያውን ከእጁ ላይ አንስተው እንዲህ አሉት።
"ሰንፍናም ልክ እንደዚህ ኩባያ ናት። አንድን ስራ ዛሬውኑ ሰርተህ ብታሳርፈው ቀላል ነው። ነገር ግን 'ነገ እሰራዋለሁ' እያልክ በጭንቅላትህ ውስጥ ተሸክመኸው ስትዞር፣ ስራው ባይሰራም እንኳ ክብደቱና ጭንቀቱ በየቀኑ እየጨመረ ይሄዳል። ሰነፍ ሰው ከሚሰራው ሰው በላይ ይደክማል፤ ምክንያቱም የሚሰራው ሰው ስራውን አውርዶ ሲያርፍ፣ ሰነፉ ግን ያልተሰራውን ስራ በሃሳቡ ተሸክሞት ይውላል።"
...
ሰንፍና ማለት እረፍት ማለት አይደለም። ያልተሰራ ስራ በውስጣችን የሚፈጥረው ጭንቀትና ጸጸት፣ ከስራው ድካም በላይ አእምሮአችንን ያደክመዋል።
...
ዛሬ መደረግ ያለበት ነገር ዛሬውኑ መከናወን አለበት።Reviews channel
14 total reviews
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
እንማር is a Telegram channel in the category «Образование», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 122K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 9.7, with 14 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 18.0 ₽, and with 36 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий