Monetize Telegram Mini App with Telega.io
Connect your app, set CPM, and watch your revenue grow!
Start monetizing
16.9

Advertising on the Telegram channel «Eytachn»
4.5
4
የኔ፣የአንተ፣የአንቺ እና የእኛ እይታ የሚዳሰስበት የሁላችንም እይታ የሆነውን የምንገልጽበት ባለሙያዎች አዋቂ ሰዎችን ጋብዘን የምንወያይበት 'እይታችን' የምናሰፋበት የዚህ ቻናል አላማ ነው። ischannel & Group ይቀላቀሉን።
USDT$ ~ TRC20
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$1.92$1.92local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
ወደ ህልሜ እየተራመድኩኝ ነው? ወይስ ቁጭ ብዬ ሕልሜን እየጠበኩኝ?
እኛ ወደ ሕልማችን እንሄዳለን እንጂ ሕልማችን ወደ እኛ አይመጣም፡፡ ትክክለኛ ሕልም እውን እንዲሆን የእኛን እንቅስቃሴ ይፈልጋል፡፡ ወደፊትና ወደኋላ በሚወዛወዝ ወንበር ላይ ተቀምጦ አይኖችን ጨፍኖ በመወዛወዝ፣ “አንድ ቀን ሃብታም እሆናለሁ፣ አንድ ቀን አዋቂ እሆናለሁ፣ አንድ ቀን ጎበዝ ሯጭ እሆናል . . . ” እያሉ በመዋል ሕልም እውን አይሆንም፡፡
ሕልማችን ጋር እንደርሳለን እንጂ ሕልም እኛ ጋር አይደርስም፡፡ ወደ ሕልም የሚደረሰው ደግሞ ካለሙ በኋላ በማቀድ፣ ወዳቀድነው አቅጣጫ በመንቀሳቀስ፣ ከዓላማ ግራና ቀኝ ባለማለት፣ ባለመሰልቸት፣ ሲወድቁ በመነሳት . . . ነው፡፡ በአጭሩ፣ ወደፊት ካልተራመድን ወደ ሕልማችን አንደርስም፡፡
ሕልም ማለት ንድፍ (Blue Print) ማለት ነው፡፡ የአንድን ሕንጻ ንድፍ የሰራ መሃንዲስ ያንን ውብ የሆነ ንድፍ ባለው የኮምፒውተር ክህሎት አሳምሮ ካስቀመጠ በኋላ በየቀኑ ያንን እያየ በመደነቅና ለሰዎችም እያሳየ አድናቆት ስላገኘ ሕንጻው አንድ ቀን ብቅ አይልም፡፡ ከንድፍ በኋላ ብዙ ስራ፣ ወጪና መስዋእትነት ይጠብቀዋል፡፡
ሕልምህ፣ ሕልም ብቻ ሆኖ እንዲቀር አትፍቀድለት፡፡ ተነሳና ተንቀሳቀስ፣ መክፈል ያለብህን የመስዋእትነት ተመን አውጣና ተራመድ፡፡ አደጋ ይደርስብኛል ብለህ አትፍራ፡፡ የአደጋው መጠንና አደጋውን የተጋፈጥንበት ምክንያት አስፈላጊነት ይለያይ እንጂ ማንኛውም ምርጫ ከአደጋ ነጻ ሊሆን አይችልም፡፡
አየህ፣ ባለህበት ሕልምን እያመነዠጉ መኖር ባሉበት “የመበስበስ” አደጋ አለው፡፡ ሕልምን ተከትሎ መውጣት ደግሞ ከአዳዲስ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የሚመጣ የተጋላጭነት አደጋ አለው፡፡ የትኛውን እንደምትመረጥ ውሳኔው አንተው እጅ ላይ ነው ያለው፡፡ ባሉበት ሳይንቀሳቀሱ ከማለፍ፣ ሕልምን እየተከተሉ ማለፍ እንዴት የላቀ ነው!
ሕይወት ከሕልምና ሕልምንም ከመከታተል ውጪ ከሞት አትተናነስም፡፡ ዛሬ ሕልምህ ምን እንደሆነ በሚገባ በማሰብ አጣራውና ከቻልክ የየቀን ማስታወሻህ (Diary) ላይ ጻፈው፡፡

32
17:50
12.07.2025
ሃላፊነቱ የእናንተው ነው!
የደረሰባችሁ ጉዳት እና ቁስል መንስኤው የእናንተ ሃላፊነት ላይሆን ቢችልም፣ ከዚያ ጉዳት እና ቁስል የመውጣቱ ሃላፊነት ግን የእናንተ እንደሆነ አትርሱ!
• ያቆሰሏችሁን ሰዎች ይቅር ብላችሁ መንገዳችሁን ቀጥሉ!
• በተመሳሳይ ሰውና ሁኔታ መላልሶ ከመቁሰል ራሳችሁን ጠብቁ!
• ሁሉም ነገር ምላሽ እንደማያስፈልገው በማስታወስ ዝም ብላችሁ ፈውሳችሁና እድገታችሁ ላይ አተኩሩ!

30
19:04
12.07.2025
ሕልም አለኝ? ካለኝ፣ እየኖርኩት ነው? ከሌለኝስ፣ ለምን?
ሕልማችሁን ዓላማ፣ ራእይ ወይም ደግሞ ሌላ ስም እንድትሰጡት ነጻነቱን ለእናንተው ልተወውና፣ እዚህ ጋር እንድታስቡት የምፈልገው ለነገ የምትኖሩለትን ነገርና ከኖራችሁት በኋላ መለስ ብላችሁ፣ “እንኳን ይህንን መንገድ ተከተልኩኝ” የምትሉለትን ነገር ነው፡፡ ይህንን እውነታ በትክክለኛ ስሙ ከጠራነው ምንም እንኳን “ራእይ” ብለን ልንጠራው ቢገባንም፣ የመጠሪያ ስሙን ለእናንተው በመተው ወደ ዋናው ሃሳብ ልግባ፡፡
አንዳንድ ሰዎች “ሕልም የሌለው ሰው እንዴት ሊኖር ይችላል?” በማለት አክርረው ሲሞግቱ ይታያሉ፡፡ ጉዳዩ እንደዚህ በአንድ የአቋም መግለጫ መልስ የሚያገኝ ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ ሕልምን አስመልክቶ አራት አይነት ሰዎች አለን (የምንነጋገረው ጤናማ ሕልምን አስመልክቶ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ)፡፡
አንዳንዶቻችን ሕልም የለንም፡፡ ማለትም፣ በውስጣችን የሚቀጣጠል፣ የወደፊታችንን በጉጉት እንድንጠብቀውና ለዚያ የሚያስፈልገንን ነገር አሁን እንድንሰራና እንድናጠራቅም የሚያደርገን የምናየው ነገር የለንም፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ዛሬውኑ ሕልማቸውን የማግኘት ጉዞ እንዲጀምሩ ይመከራሉ፡፡
አንዳንዶቻች ሕልም ነበረን ሕልማችን ግን ሞቶብናል (ጥለነዋል)፡፡ ማለትም በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ በማሳለፋችን ምክንያት ተስፋ ቆርጠን፣ በአጉል ሰዎች ተጽእኖ ስር ከመውደቃችን የተነሳ ጫና ተደርጎብንና አንዳንድ ውስብስብ ፍልስፍናዎች ውስጥ ከመተብተባችን የተነሳ ግራ ተጋብተን ሕልማችንን ትተነዋል፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ሕልማቸውን የጣሉት የቱ ጋር እንደሆነ ፈልገው በማግኘት እንደገና እንዲያነሱት ይመከራሉ፡፡
አንዳንዶቻችን ሕልም ነበረን፣ ሕልሙ አሁንም አለ፣ ነገር ግን ሕልሙ እውን የሚሆንበት ጊዜው ረዝሞብንና ሕልማችን ሌላ፣ የምንኖረው ኑሮ ደግሞ ሌላ ሆኖብን ዝለናል፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ሕልም ጊዜ እንደሚጠይቅና አጥብቀው ከተከታተሉት በርግጥም እውን እንደሚሆን በማወቅ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ ይመከራሉ፡፡
አንዳንዶቻችን ሕልም አለን፣ ሕልማችንንም በንቃት እየተከታተልን ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች በዚያው እንዲቀጥሉ ይመከራሉ፡፡
ሕልምን ማግኘት ማንነትን የማግኘት አንዱና ዋነኛው ክፍል ነው፡፡ ዛሬ ይህንን ጥያቄ በሚገባ ለመጠየቅና ከቻልክ የየቀን ማስታወሻህ (Diary) ላይ ከተጠቀሱት ደረጃዎች በየትኛው ላይ እንዳለህና ምን ለማድረግ እንደምታስብ ሃሳብ ለመጻፍ ሞክር፡፡

34
19:40
12.07.2025
የሃሳባችሁ ጉዳይ!
• በየቀኑ የምታሰላስሉት ሃሳብ በየቀኑ የሚሰማችሁን ስሜት ይወስናል . . .
• በየቀኑ የሚሰማችሁ ስሜት ማድረግ የምትፈልጉትን ነገር ይወስናል . . .
• በየቀኑ የምታደርጉት ነገር ልማዳችሁን ይወስናል . . .
• በየቀኑ የምታደርጉት ልማዳችሁ በራሳችሁ እና በሰዎች የምትታወቁበትን “የመታወቂያ ማንነት ስም” (identity) ይወስናል . . .
ይህ ሂደት በጊዜ ካልተስተካከለ ፍጻሜያችሁን ይወስነዋልና ምንም ነገር ላይ ከመስራታችሁ በፊት የሃሳብና የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት ስሩ!

28
20:40
12.07.2025
የብዙ ሰዎች ጥያቄ!
ቁጥራችሁ ብዙ የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸውን መርሆች ከክርስትና እምነት (መጽሐፍ ቅዱስ) አንጻር መማር እንደምትፈልጉ inbox እያረጋችhuልኝ በመሆኑ ይህንን መልስ እሰጣለሁ፡፡
በአጠቃላይ የምሰጣቸው ትምህርቶች አቀራረባቸው በሁለት ይከፈላል፡-
1. እምነት-ተኮር (Faith-Based)
2. እሴት-ተኮር (Value-based)
እንደምታዩት ሁሉ፣ በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸው ትምህርቶች እሴት-ተኮር (Value-based) ናቸው፡፡
ይህ ማለት የማንኛውም እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ለሕይወቱ የሚጠቅሙ ተግባራዊ መመሪያዎችን የሚያገኝባቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡
እምነት-ተኮር ትምህርቴን ለምትፈልጉ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች በቅርቡ የጀመርኩት የmentorship network ስላለና ለእሱም ቻናል ስለከፈትኩ እዚያ በመቀላቀል ያንን ትምህርት መከታተልና ወደፊትም በአካል የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ መካፈል ትችላላችሁ፡፡
ከዚህ በታች ባለው link በመጠቀም ቻናሉን join አድርጉ፡፡

26
08:45
13.07.2025
የስሜት ብልህነታችን ደረጃ ሲመዘን!
ጥናቶች እንደሚነግሩን ከሆነ በስራም ሆነ በማንኛውም የማህበራዊ ኑሮ 80 በመቶው ስኬታችን የሚመጣው ከስሜት ብልህነት ሲሆን፣ የአእምሮ ብልህነት የሚሰጠን የስኬት መጠን ግን 20 በመቶ ብቻ ነው፡፡ በሌላ አባባል ከፍ ያለ የአእምሮ ብልህነት (IQ) ኖሮህና አእምሮህ በብዙ እውቀት ተሞልቶ ሳለ፣ ስሜታዊ ብልህነት ከሌለህና የራስህንና የሌሎች ሰዎችን ስሜት አያያዝ ካላወቅህበት የአእምሮ እውቀትህ ብቻውን የትም አያደርስህም፡፡
የስሜት ብልህነት ያላቸው ሰዎች ምልክቶች፡-
1. አስቸጋሪ ሰዎችንና ሁኔታዎችን በስኬታማ መልኩ አያያዝ
2. ራሳቸውን ግልጽ በሆነ መልኩ የመግለጽ ብቃት
3. በሰዎች የሚከበር ማንነትን ማንጸባረቅ
4. በሰዎች ላይ ተጽእኖ የማምጣት ብቃት
5. ሰዎች እንዲደግፏቸው የማነሳሳት ብቃት
6. በውጥረት ውስጥ የውስጥን መረጋጋትና ሚዛናዊነትን አለማጣት
7. ለሰዎችና ለሁኔታዎች የሚሰጡትን ስሜታዊ ምላሽ ማወቅና ለመቆጣጠር መብቃት
8. የተፈለገውን ውጤት ለማግኘት ትክክለኛውን ነገር መናገርና ተገቢውን ነገር ማድረግ
9. በድርድር ጊዜ ተገቢውን አቀራረብ በመምረጥ ራሳቸውንም ሆነ ሌላኛውን ሰው መምራት
10. አንድን ነገር ከግቡ ለማድረስ ራስን ማነሳሳት
11. በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሲያልፉ እንኳ አዎንታዊ ሆኖ መቆየት
አንድ ሰው ምንም ያህል በአእምሮ ብልህነት ቢበስል የስሜት ብልህነት መጠኑ አናሳ ከሆነ በውስጡ ያለው እውቀትና ችሎታ የሚወጣበትና የሚገለጥበት “መስኮት” የለውም፡፡ ስሜት ሲወድቅ፣ ሲዘጋ፣ ሲዛባም ሆነ አላግባብ ሲገለጥ በአንድ ሰው ውስጥ ያለውን ብቃት የመጨቆን ወይም ደግሞ ተቀባይነት እንዳያገኝ የማድረግ ተጽእኖ አለው፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት 11 ነጥቦች የትኞቹን በማዳበር ላይ ናችሁ?
የትኞቹ ላይስ በበለጠ መስራት ይጠበቅባችኋል?

38
11:27
13.07.2025
የመኖራችሁና ያለመኖራችሁ ጉዳይ
በአንድ ቦታ ወይም ግንኙነት ውስጥ አለመኖራች የሚያጎድለው ነገር ከሌለ፣ መኖራች የሚሞላው ነገር የለም ማለት ነው፡፡
በተቃራኒ ደግሞ በአንድ ቦታ ወይም ግንኙነት ውስጥ መኖራችሁ የሚሞላው ነገር ካለ፣ አለመኖራች የሚያጎድለው ነገር አለ ማለት ነው፡፡
ይህንን ለማወቅ ከፈለካችሁ ደግሞ ሁለት ጥያቄዎችን ጠይቁ፡-
1) መኖሬን የሚያደንቁ ሰዎችና ቦታዎች የትኞቹ ናቸው?
2) አለመኖሬ ምንም እንዳላጎደለባቸው የሚያሳዩኝ ሰዎችና ቦታዎችስ የትኞቹ ናቸው?
በሕይወታችሁ እንደቀፈፋችሁ፣ የውስጥ አቅም እንዳጣችሁና ሰላማችሁ እንደተረበሸ እንድትኖሩ ከሚያደርጉ ልምምዶች መካከል አንዱ ብትኖሩም የማትደነቁበት፣ ባትኖሩ ደግሞ የማትናፈቁበት አካባቢ በግድ የመገኘት ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን ልምምድ በሚሰጣችሁ አካባቢ ወይም ጓደኝነት ውስጥ መቆየት በማንነታችሁ ላይ ይህ ነው የማይባል የራስ-በራስ ንቀትን ከማስከተሉም በተጨማሪ ራሳችሁን በመናቅ ሌሎች እንዲንቋችሁና እንዲቆጣጠሯችሁ ፈቃድ እንድትሰጧቸው መንገድን ይጠርጋል፡፡
መኖራችሁ የሚሞላው ነገር፣ አለመኖራችሁ ደግሞ የሚያጎድለው ነገር እንዳለ በማመን በብርቱ የሚፈልጓችሁ ሰዎች እያሉ፣ ብትኖሩም ሆነ ባትኖሩ ምንም የምትሞሉትም ሆነ የምታጎድሉት ነገር እንደሌለ ከሚያስቡና ያንንም ከሚያሳዩህ ሰዎች አካባቢ ጊዜያችሁን አታባክኑ፡፡
በዚህ ምድር ላይ ሁል ጊዜ ተለጣፊ፣ ተንጠልጣይ፣ ለማኝና ተለማማጭ ሆናችሁ ለመኖር አልተፈጠራችሁም፡፡ የራሳችሁ ስፍራ ያላችሁ ሰዎች ናችሁ፡፡ የምትወደዱበት፣ የምትደነቁበትና የምትፈለጉበት ቦታ ያላችሁ ሰዎች ናችሁ፡፡
ዛሬ ከእናንተ ጋር ምንም ግንኙነት ባለማድረግ ውስጥ ምቾት ከሚሰጣቸው ሰዎች ጋር ያላችሁን ግንኙነት እንደገና የምትፈትሹበት ቀን ይሁንላችሁ!
ዛሬ መኖራችሁ የማያጓጓቸው፣ አለመኖራችሁ ደግሞ የማይናፍቃቸው ሰዎች ጉዳይ ይታሰብበት!
ያን ጊዜ ለራሳችሁ ያላችሁን ክብር ትመልሳላችሁ፡፡ ያን ጊዜ ሰውን መለማመጥ አቁማችሁ ቀና ብላችሁ ከዓላማችሁ አንጻር መኖር ትጀምራላችሁ፡፡

40
08:29
16.07.2025
የምቹ ስፍራ ውበትና አደገኛነት!
“Comfort Zone is a beautiful place but nothing ever grows there” – Kevin David
“ምቹ ቀጠና ውብ የሆነ ስፍራ ነው፣ ሆኖም በዚያ ስፍራ ላይ ምንም ነገረ በቅሎ አያውቅም”
በሕይወታችን እጅግ ከባድ ከሚባሉ ልምምዶች መካከል አንዱ፣ የለመድነውንና ምቹ የሆነን ቀጠና ለቆ የሚቀጥለው የሕይወታችን እድገት ደረጃ ወደሚፈልገው አዲስ ቀጠና መሄድ ነው፡፡ ይህንን ዝንባሌ ለዘጠኝ ወራት ተደላድለን ከኖርንበት የእናት ማሕጸን የመውጫውና ወደሚቀጥለው የእድገት ደረጃ መሸጋገሪያው ጊዜ ሲደርስ በማልቀስ ገልጸነዋል፡፡ ምቹ ስፍራን ለቆ ከመሄድ ውጪ ግን የሚቀጥለውን የእደገት ደረጃና አዲስ አለም የእኛ ማድረግ አይቻልም፡፡
ምቹውን አልፈን አዲሱንና እንግዳ የሆነውን የእድገት አለም ለመቀላቀል . . .
1. ምቹ ስፍራችን የሚሰጠንን ጥቅም አጣለሁ የሚለውን የፍርሃት ዝንባሌ (Fear of loss) ማሸነፍ ወሳኝ ነው፡፡
2. ለውጥን የመፍራትን ዝንባሌ (Fear of change) ማሸነፍ የግድ ነው፡፡
3. አዲሱንና የማይታወቀውን ቀጠና የመፍራት ዝንባሌ (Fear of the unknown) ማስወገድ አስፈላጊ ነው፡፡
ወደ አዲሱ፣ ወዳልተለመደውና ዋጋ ወደሚያስከፍለው የእድገት ቀጠና እንንቀሳቀስ!

37
08:53
17.07.2025
አርብ - እድገት
ለእድገት የተዘጋጀ ማንነት
እድገት ሁለንተናዊ ለውጥ ነው። እድገት በህይወት የመኖራችን ማሳያ ነው። እድገት ስንል ለሰዎች የምንጠቀምበት መንገድ አለ፦
👉አዕምሮአዊ
👉መንፈሳዊ
👉ኢኮኖሚያዊ እና
👉አካላዊ መሻሻልን ያጠቃልላል። በእነዚህ ጤነኛ ሆናችሁ ለመኖር እና ህይወታችሁን ትርጉም ባለው መንገድ ለማስቀጠል በሚረዱ ጉዳዮች ላይ እራሳችሁን ሁል ጊዜ መስራት እና መኮትኮት አለባችሁ።
ለእድገት የተዘጋጀ ማንነት ሲኖረን ከምናሳያቸው ምልክቶች መሀከል ከላይ ለጠቀስናቸው ጉዳዮች ትኩረት የምንሰጥ መሆናችን እና እለት እለት መሻሻል የምናሳይ መሆናችን ነው። ስለዚህ ለእድገት የተዘጋጀ ማንነት ይኑራችሁ።
Friday - Growth
A growth-oriented identity
is a foundation for transformation. Growth is a visible sign of life. When we talk about growth, it involves different aspects:
👉 Mental
👉 Spiritual
👉 Financial
👉 Physical improvements.
To live a healthy life and continue living meaningfully, we must consistently work on and invest in these areas. Having a growth-oriented identity means paying continuous attention to these dimensions and showing progress every day.
So, cultivate an identity that is prepared for growth.

44
08:46
18.07.2025
ሀሙስ - በጥልቀት ማሰብ
አስቡት ሁሉም እውነታዎች የሆኑ ጊዜያት ላይ ታሪኮች ሆነው ሲቀሩ።
አዶልፍ ሂትለር 6 ሚሊየን አይሁዳውያንን እና ሌሎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 11 ሚሊየን ሰዎችን ከ 1939-1945 ድርስ አጥፍቶአል። አስቡት በ 6 አመታት ወስጥ ነው ይሄን ሁሉ ህዝብ የጨረሰው። ጊዜው በጣም ቅርብ ነው። አይገርምም ከዛሬ 80 አመት በፊት ማለት ነው።
ዛሬ ላይ አለም ይሄንን ክስተት ታሪክ ብላ ወደሁዋላ ትዘግበዋለች። የዛሬ 80 አመት የተፈጠረ እውነታን ከ80 አመት በሁዋላ ያለው ትውልድ ታሪክ ነበር እያለ ያወራዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በ1945 አለም የማትረሳው ሌላ ክስተት ነበራት የጃፓኑዋ ከተማ ሒሮሺማ ያስተናገደችው የ ኒኩሌር ቦንብ ድብደባ ። በአንድ ጊዜ ብቻ ማለትም አንዴ ቦንቡ ሲወድቅ የሞተው የሰው ቁጥር 80 ሺ ነበር። ቀስ እያለ 140 ሺ ህዝብ አለቀ። ይሄም ከተፈጠረ 80 አመት ነው አይገርምም ዛሬም አለም ወደሁዋላ ታሪክ ብላ ትዘግበዋለች።
ሀገራችን ኢትዮጵያም በተመሳሳይ ሁኔታ የዚህ አይነት ጊዜያትን አስተናግዳለች። ቀይ ሽብርን መውሰድ በቂ ምሳሌ ነው። ከ 30 ሺ አስከ 500 ሺህ ህዝብ አልቆበታል። ጊዜው የዛሬ 50 አመት ብቻ ነው። አለም ዛሬም ይህንን ጉዳይ ታሪክ ብላ ትወስደዋለች።
ወዳጆቼ ዛሬ ላይም ሀገራችንን በተለያዩ ጉዳዮች ትውልዱዋን እያጣች ትገኛለች። በጦርነት ፣ እርስ በእርስ ግጭት ፣ በሀይማኖት።
አይገርማችሁም ይሄ ሁሉ ክስተት ግን የሆነ ጊዜ ላይ ነበር ብቻ ይሆናል። ለምን ለልማት ፣ ለማደግ ፣ ለመለወጥ ፣ ለመበልፀግ እና ከፍታ ላይ ለመድረስ መተባበር አቃተን ?
ለዚህም ይመስለኛል አልበርት አንስታየን ሲናገር ፦ "ጦርነቱን አሸንፈናል ፤ ሰላምን ግን አላሸነፍንም " ያለው። ሁላችችሁም የአደይ ቤተሰቦች አይምሮአችሁን እና እድሜያችሁን ለማደግ እና ለመለወጥ እንጂ ለጥፋት እንዳታስተባብሩት እጠይቃችሁዋለው። ምንም ሰራችሁ ምን ታሪክ ሆናችሁ ብቻ ነው የምትቀሩት።
Thursday – Think Deep
Think deeply: All real moments eventually become history. Adolf Hitler killed 6 million Jews and a total of about 11 million people between 1939 and 1945.
Imagine that — all of this happened in just 6 years. The time is not far off. It’s only 80 years ago from today. Today, the world looks back on this tragedy as history.
An event that happened 80 years ago is now considered history by today's generation.
In a similar way, another unforgettable global tragedy happened in 1945: the nuclear bombing of Hiroshima, Japan.
In a single moment, around 80,000 people were killed instantly when the bomb dropped. Gradually, the death toll reached 140,000 due to radiation and injuries.
That, too, happened 80 years ago.
Again, the world remembers it as history.
Our country, Ethiopia, has also gone through similar painful times.
The Red Terror (Qey Shibir) is a powerful example. Even this, the world now sees as history.
Dear friends, even today, our country continues to suffer from internal problems, wars, conflicts among people, and even religious divisions.
But remember — all these may just be “a time of conflict”. So let’s ask ourselves:
Why don’t we unite for growth, transformation, and progress instead of destruction?
I think this is why Albert Einstein once said:
To all Adey family members,
Please use your mind

“We have defeated war, but we have not won peace.”
To all Adey family members,
Please use your mind
24
19:47
24.07.2025
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
4.5
1 reviews over 6 months
Average (100%) In the last 6 months
t
**milisa126@*****.com
On the service since April 2025
11.04.202505:16
2
nonono
Show more
Channel statistics
Rating
16.9
Rating reviews
4.5
Сhannel Rating
13
Subscribers:
414
APV
lock_outline
ER
3.4%
Posts per day:
1.0
CPM
lock_outlineSelected
0
channels for:$0.00
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий