
Monetize Telegram Mini App with Telega.io
Connect your app, set CPM, and watch your revenue grow!
Start monetizing
23.5

Advertising on the Telegram channel «ያሬዳውያን/yaredawyan»
5.0
Religion & Spirituality
Language:
English
0
0
የየበዓላቱ ስርአተ #ዋዜማ ፤ #ማኅሌት ፤ #ወረብ ከ፯ ቀናት በፊት እንዲሁም የየሳምንቱ መዝሙራት እና ምስባክ በጽሑፍ እና በድምጽ የሚቀርቡበት ቻናል ነው #ሁሉም_ነገር_ስለ_ማህሌት ለማስታወቂያ እና ለማንኛውም ጥያቄ ከፈለጉን ያናግሩን
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$11.64$11.64local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
play_circleVideo preview is unavailable
መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ
ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤ወተክለ ሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዐጽሙ፡፡
@EOTCmahlet
ዚቅ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር፤
ዘኢይነውም ትጉህ በውስተ ቅዱሳን ስቡሕ፤ከመ ቀስተ ደመና የዓውዶ ሱራሄ ሎቱ ለባሕቲቱ ይደሉ ስባሔ፡፡
7838
00:27
25.08.2025
play_circleVideo preview is unavailable
ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙለወልድኪ፤ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ለሙ፤እግዚአብአሄር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ፤
ዚቅ
አመ ኖኅ ይእቲ መድኀኒት፤
እንተ ኮነት አንቀጸ ሕይወት ማርያም ቅድስት፡፡
8308
00:27
25.08.2025
play_circleVideo preview is unavailable
መልክአ ተክለ ሃይማኖት
ሰላም ለአዕይንቲከ ዘአርአያሆን ሐዋዝ፤እለ ጽዱላት እማንቱ ከመ ሠርቀ ቤዝ፤ተክለ ሃይማኖት ኅብዓኒ እሞተ ኃጢአት አዚዝ፤ለከሰ አኮ ከመዝ፤ኢይረክበከ ሞት ዳግመ እምዝ፡፡
@EOTCmahlet
ዚቅ
ዳግመ እምዝ ኢይረክቦ ሞት ከመዝ ዳግመ እምዝ፡፡
6526
00:27
25.08.2025
play_circleVideo preview is unavailable
በመልዕልተ አድባራት ቀራንዮ መድሐኔአለም ቤተ-ክርስቲያን ጥቅምት 27 ዋይዜማ ፡ ቁም መረግድ ፅፋት
ሃሌ ሉያ ፡ እስመ በዛቲ እለት አርዐየ ቆስጠንጢኖስ ፡ ዕፀ-መስቀሉ ለአኅዛብ ፡ በበነገዶሙ ወበበአስማቲሆሙ ለፃድቃን ፡ ሞዑ ወአግረሩ ፀሮሙ በሃይማኖት ።
ዋይዜማው በወንበር አይገኝም ፡ ከድጓ ላይ አቋቋም ተፈጥሮለት ነው
ድምጽ በደብሩ የአቋቋም መምህር በሆኑት ሊቀ ጠበብት ዮሐንስ
7205
11:10
25.08.2025
imageImage preview is unavailable
በባለፈው ዙር ትምህርተ ንስሓ 60 ተማሪዎች ተመዝግበው ተምረው፣ንስሓ አባት ይዘው፣ንስሓ ገብተው ሁሉም በሚባል ደረጃ ቅዱስ ቍርባን ተቀብለዋል።
አሁን ደግሞ ከ100-120 ተማሪዎችን ለማስተማር እና ለቅዱስ ቍርባን ለማብቃት እቅድ ይዤያለሁ።
* ለመማር የምትፈልጉ ተመዝገቡ !
* እንዲማር ለምትፈልጉት ሰው Share አድርጉለት/ አስመዝግቡት/
Notice፦
* ምዝገባው በዚህ ሳምንት ብቻ ነው !
ለመመዝገብ 👉 @Bet_Gubai
https://t.me/Terha_Tsion
2619
22:07
25.08.2025
ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በነገደ መላእክት ላይ ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ ሁለተኛ ሆኖ የተሾመ አንዱ ቅዱስ ገብርኤል ነው። ዲያብሎስ በመላእክት መካከል ሽብር በፈጠረ ጊዜ
❝ንቁም በበ ህላዌነ እስክ ንረክቦ ለእግዚእነ — የፈጠረንን እስክናገኝ ድረስ በያለንበት እንጽና❞
ብሎ ዓለመ መላእክትን ስላረጋጋ መልአከ ሰላም - የሰላም መልአክ ይባላል።
ሊቀ መላእክትነቱን ኤጲፋንዮስ አክሲማሮስ በሚል ድርስቱ «አርባብ» ለሚባሉ መላእክት አለቃቸው ሲያደርገው፤ ነቢዩ ሄኖክ ደግሞ:-
❝በሠራዊት ሁሉ ላይ የተሾመ ቅዱስ ገብርኤል ነው❞
ሲል ይገልጠዋል - (ሄኖ I፥፲፬)።
ሹመቱም በየትኞቹ እንደ ሆነ ሲገልጥ:-
❝ከቅዱሳን መላእክት አንዱ ገብርኤል በእባቦች ላይ በገነትና በኪሩቤልም ላይ የተሾመ ነው❞
ይላል (ሄኖ ፮÷፯)። ቅዱስ ገብርኤል በእባቦች ላይ መሾሙ ከዘንዶ ጀምሮ ልዩ ልዩ የእባብ ዓይነት ሁሉ ስውን እየነደፈ ገድሎ እንዳይጨርስ በእግዚአብሔር ቸርነት ከሰው እስከ እንስሳት ለመጠበቅ ነው:: ዳግመኛም አጋንንት በክፉ መርዛቸው ውኃውን እንዳይመርዙት ጠባቂ መልአክ ሁኖ በውኃዎችም ላይ የተሾመ ነው::
«በገነት ላይ የተሾመ» የሚለውን የትርጓሜ መምህራን በገነት ባሉ ዕፀዋት ላይ የተሾመ ማለት ነው ብለው ተርጉመዋል:: «በኪሩቤል ላይ» የሚለውን ቅዱስ ሚካኤል በሱራፌል ላይ እንደ ተሾመ ቅዱስ ገብርኤልም በኪሩቤል ላይ ተሹሟል ብለው ተርጉመዋል፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በግዕዝ መዝገበ ቃላቸው ❝አርባብ የኪሩቤል ስም ጌቶች፥ አለቆች ማለት ነው❞ ብለዋል። ሰሎሞንም በመኃልይ መጽሐፉ
❝ወንበር ዲበ ሳሬል ወዲበ አርባዕቱ አርባብ - በሱራፌል ላይ፥ በኪሩቤልም ላይ ተቀመጥ❞
— (መኃ ፪÷፲፯) ያለውን የትርጓሜ ሊቃውንት ሱራፌልን፣ ኪሩቤልን ይዘህ ተራዳኝ አለ:: ሳሬል ያለው ሱራፌልን ሲሆን፤ አርባብ ያለው ደግሞ ኪሩቤልን ነው፤ ሱራፌል ነገደ ሚካኤል ሲሆኑ ኪሩቤል ነገደ ገብርኤል ናቸው ብለው ተርጕመዋል፡፡
እግዚአብሔርን ፀንሳ እንደምትወልድ ለድንግል ስለ አበሠራት ገብርኤል ማለት
❝አምላክ ወሰብእ - ሰው የሆነ አምላክ የእግዚአብሔር ልጅ❞
ማለት ነው፡፡
❝ወገጹ ለራብዓይ ከመ ወልደ እግዚአብሔር ይመስል - አራተኛውም የእግዚአብሔር ልጅን ይመስላል❞
እንዳለ (ትን. ዳን ፫፥፳፭)።
ናቡከደነፆር አራተኛው የእግዚአብሔር ልጅ ይመስላል ያለውን ቅዱስ ያሬድ ደግሞ:-
❝ገብርኤል ብሂል ወልደ እግዚአብሔር ወዲበ ርእሱኒ አክሊል ጽሑፍ በትእምርተ መስቀል — ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ነው፤ በራሱም ላይ የመስቀል ምልክት ያለበት አክሊል አለ❞
ብሎ ገልጾታል - (ድጓ ዘሚካኤል)
የመልክአ ገብርኤል ደራሲም በሰላም ለዝክረ ስምከ ላይ «ገብርኤል» ስለሚለው ስም ሲገልጽ:-
❝ሰላም ለዝክረ ስምከ፥ ዘኢይተረጐም ምሥጢር ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር — ገብርኤል ሆይ፦ ተመራምሮ ለማይደረስበት ለስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፤ ነገር ግን አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ይመስላል❞
ብሏል።
ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድም በድጓው፦
❝ገብርኤል ብሂል ብእሲ ወአምላክ እምኀበ እግዚአብሔር ዘተፈነወ ላእክ ሥጋዌ ቃል ለድንግል ይስብክ — ገብርኤል ማለት ሰው የሆነ አምላክ፥ የቃል ሰው መሆንን ለድንግል ምሥራችን ይነግራት ዘንድ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ አገልጋይ❞
ማለት ነው ብሏል (ድጓ ገጽ ፻፸)
ዙፋኑን ከሚሸከሙ ኪሩቤል ጋር እንደ አንዱ ሆኖ እንደሚቆጠርም
❝ገብርኤል ሆይ የአንበሳ የገጸ ላሕምና የንስር ሥነ ገጽ ካላቸው ኪሩቤል ጋር የእግዚአብሔርን ዙፋን ተሸክመህ በከበረ ሰው አምሳል ሕዝቅኤል ያየህ ከኪሩቤል አንዱ አንተ ነህ❞
ብሏል፡፡
ነገር ግን እዚህ ጋ ማስተዋል ያለብን "ገብርኤል ኪሩብ ጸዋሬ ዐቢይ መንበር" ማለት እንደ ቅኔ ምሳሌያዊ ምስጋና እንጂ ቀጥታ ገብርኤል ኪሩብ ሁኖ ዙፋኑን ይሸከማል ማለትም አይደለም፡፡ ሕዝቅኤልም ያየው የበፍታ ልብስ በለበሰና የሰንፔር መታጠቂያ በታጠቀ ሰው አምሳል ሁኖ በኢየሩሳሌም ከተማ ስለሚሠራው ኃጢአት በሚያለቅሱ ሰዎች ላይ ኃጢአተኞች ከእግዚአብሔር በታዘዙ መላእክት ሲጠፉ አብረው እንዳይጠፉ በግንባራቸው ላይ ምልክት የሚያደርግበት የቀለም ቀንድ ይዞ ነው እንጂ የጌታን ዙፋን ተሸክሞ አይደለም (ሕዝ፱÷፩-፱)። ዳግመኛም አንዱ ኪሩብ ከኪሩቤል መካከል ካለው እሳት ወስዶ በእጁ ሲሰጠው አይቷል (ሕዝ ፲÷፮) ሠለስቱ ደቂቅን ከሚነድ እሳት ያወጣቸው ይኸው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው::
ቅዱስ ገብርኤል ክርስቲያኖችን ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት በአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው ታማኝ መልአክም ነው፡፡
ሐምሌ ፲፱ ቀንም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ የተቀበሉበት፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ደግሞ ከእቶን እሳት ያዳናቸው ዕለት ነው።
የ፫ ዓመት ሕፃን የእናቱ የእምነት ጉድለት በጸሎት አራቀላት። በእጁም ይዟት ወደ ሕይወት መራት። እናቱም
❝ልጄ ሆይ አንተ ከእንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ፤ ያች የተወለድክባት ዕለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት❞
አለችው።
ከፍላቱ የተነሣ እንደነጎድጓድ የሚያስፈራ የነበረው እንደ ማለዳ ውርጭ ቀዘቀዘላቸው ከእግዚአብሔር የታዘዘ የታመነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና።
❝በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል❞
— አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ
===================================
https://t.me/DnHaileRaguel
4570
20:18
25.08.2025
play_circleVideo preview is unavailable
ገብርኤል ገብርኤል መላከ ራማ(፪)
ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ ድምፅህን እንስማ(፪)
ትንቢቱ ሲፈፀም ዘመኑ ሲያበቃ
ከቀናት ሳትዘገይ ሳይጎድል ደቂቃ
ወደ ድንግል መጠህ ደስታን አበሰርክ
የአምላክን ሰው መሆን ለአለሙ ሰበክ(፪)
ከውሃ እና ከእሳት ከሞት አመለጡ
በእሳቱ መካከል ለጥፋት ቢሰጡ
አንተ ባለህበት በየትኛውም ስፍራ
ምንም ቦታ የለው ሞትና መከራ(፪)
የመንገዴ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ
ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ
ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና
ዛሬም ላገራችን ምስራች ይዘህ ና(፪)
አንጌቤናይቱ ቅድስት እየሉጣ
ስላንተ ትመስክር እስከ ልጇ ትምጣ
እሳት ነህ ገብርኤል ነበልባል አስወጋጅ
የአምላክን መወለድ ለአለም የምታውጅ(፪)
5250
18:07
25.08.2025
play_circleVideo preview is unavailable
ቤተክርስቲያንን አንተውም ከቶ | ዘማሪት ፋሲካ መኮንን
ቤተክርስቲያንን አንተውም ከቶ
የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ
የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ
የአምላካችንን ቤት አንተውም ከቶ
አዝሁሉንም በሁሉ በሚሞላው ጌታ ሙሽራው የሆነች ቤቱ ተሰኝታ በክብር በሞገስ በጸጋ ተሞልታ ደምቃ ትኖራለች ለዓለም አብርታ/2/
አዝዲያብሎስ ቢጨርስ ቀስቶቹን በሙሉ ወጥመድ ቢዘረጋ በጉዞአችን ሁሉ እንሻገራለን የአምላክን ስም ጠርተን አንዳች አይነካንም እርሱን ተጠግተን/2/
አዝበስሙ መሰብሰብ በስሙ መስራት ስለ ስሙ መኖር ለስሙ መሞት ጠላት ዲያብሎስን ምን ባያስደስት ይህ ነው ክርስትና ይኼ ነው ሕይወት/2/
አዝከትውልድ ለትውልድ የምናስረክበው ለልጅ ልጅ አውርሰን ደስ የምንሰኘው አይደል ብርና ወርቅ አይደል ሌላ ሀብት ሃይማኖታችን ነው የእኛ ርስት ጉልት/2/
1
08:10
26.08.2025
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
2 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
d
**ssundg@*****.com
On the service since December 2023
22.08.202511:45
5
Prompt placement
Show more
New items
Channel statistics
Rating
23.5
Rating reviews
5.0
Сhannel Rating
3
Subscribers:
81.5K
APV
lock_outline
ER
8.8%
Posts per day:
14.0
CPM
lock_outlineSelected
0
channels for:$0.00
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий