
- Main
- Catalog
- Religion & Spirituality
- የክርስትና መልስ
Channel statistics
ይህ ጽሑፍ እህቴ/ወንድሜ እንድታስቡባቸውና እንድትመራመርባቸው የቀረቡ ነጥቦች ናቸው፦
1. "የሰይጣን ጥቅሶች" እና የመልእክቱ መበከል (Satanic Verses)
አንድ መለኮታዊ ቃል በምንም ተአምር ከሰይጣን ጋር ሊቀላቀል አይችልም። ሆኖም ቁርዓን ራሱ ሰይጣን በነቢዩ ንባብ ውስጥ ቃላትን ሊጨምር እንደሚችል ያምናል።
ማስረጃው፦ ሱረቱ አል-ሐጅ 22:52 ላይ እንዲህ ይላል፦ "ከአንተ በፊትም ከመልክተኛም ሆነ ከነቢይ፤ (ተምኝቶ) ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ውስጥ (ውሸትን) የጣለ ቢሆን እንጅ አንድንም አልላክንም።"
ሙግቱ፦ ሙሐመድ ጣዖታትን የሚያወድስ ቃል ተናግረው በኋላ "ሰይጣን ነው የከተተብኝ" ማለታቸው የታወቀ የታሪክ ሀቅ ነው (ምንጭ፦ Tafsir al-Jalalayn እና History of al-Tabari Vol. 6)። አምላክ መልእክተኛውን ከሰይጣን ጣልቃ ገብነት መጠበቅ ካልቻለ፣ ዛሬ በእጅሽ ያለው ቁርዓን በሙሉ ከሰይጣን ንክኪ ነፃ መሆኑን በምን ማረጋገጥ ይቻላል?
2. ቁርዓን የሙሐመድን የግል ፍላጎት ለማርካት መውረዱ (Tailor-made Revelations)
በቁርዓን ውስጥ የሚገኙ ብዙ ጥቅሶች የዓለምን ሕዝብ ለማዳን ሳይሆን፣ የሙሐመድን የግልና የሥጋ ፍላጎት ለማሟላት የወረዱ ይመስላሉ።
የሚስቶች ጉዳይ፦ ሙስሊሞች ሁሉ እስከ 4 ሚስት ብቻ እንዲያገቡ ተገድበው ሳለ፣ ለሙሐመድ ግን ያልተገደበ ቁጥር ተፈቅዶላቸዋል። (ሱረቱ አል-አሕዛብ 33:50)
የዘይነብ ታሪክ፦ ሙሐመድ የአሳዳጊ ልጃቸውን (ዘይድን) ሚስት በፈለጉ ጊዜ፣ ያን ለማመቻቸትና ትችቱን ለማስወገድ ጥቅስ ወርዷል። (ሱረቱ አል-አሕዛብ 33:37)
የአይሻ ምስክርነት፦ የገዛ ሚስታቸው አይሻ እንኳ ሳይቀር ጥቅሶቹ ለሳቸው ፍላጎት ሲሉ እንደሚወርዱ ታዝባ እንዲህ ብላለች፦ "ጌታህ ያንተን ስሜት/ፍላጎት ለማርካት የሚቸኩል ነው የሚመስለኝ።" (Sahih al-Bukhari 4788)። አምላክ የሰውን ሥጋዊ ፍላጎት ለማሟላት ጥቅስ ያወርዳል ወይ?
3. የመልእክቱ ምንጭ እርግጠኛ አለመሆን (Lack of Witnesses)
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ሲናገር ሕዝብ ምስክር ነበር። በቁርዓን ግን ምስክሩ ሙሐመድ ብቻ ናቸው።
ሙግቱ፦ ሙሐመድ መጀመሪያ መልእክት ሲመጣላቸው በድንጋጤ ወደ ቤታቸው ሮጠው "ሰይጣን ያዘኝ/ሊገድለኝ ነው" (I fear for my life) ብለው ነበር። (Sahih al-Bukhari 3)። ራሳቸው መልእክቱ ከማን እንደሆነ ተጠራጥረው ሳለ፣ እኛ እንዴት የአምላክ ነው ብለን እናምናለን? መልአኩ ገብርኤል መሆኑን ያረጋገጠላቸውም መለኮታዊ ምልክት ሳይሆን ወረቃ የተባለ የሰው ልጅ ነው።
4. ተቀያያሪና የሚቃረኑ ህጎች (Abrogation)
አምላክ ሁሉንም ነገር አስቀድሞ የሚያውቅ ከሆነ፣ ቃሉን ዛሬ ተናግሮ ነገ ለምን ይለውጠዋል?
ማስረጃው፦ ሱረቱ አል-በቀራህ 2:106 ላይ አምላክ ጥቅሶችን እንደሚሽርና በሌላ እንደሚተካ ይናገራል።
ሙግቱ፦ መጀመሪያ "በሃይማኖት ማስገደድ የለም" ይልና (2:256) በኋላ ግን "ከአላህ ሌላ የሚገዛን ግደሉ" የሚሉ ጥቅሶች ይመጣሉ። ይህ የሚያሳየው ቁርዓን እንደየሁኔታውና እንደ ሙሐመድ ጥንካሬ የሚቀያየር የሰው ሰራሽ ቃል መሆኑን ነው።
5. የታሪክ ስህተቶች (Historical Anachronisms)
ቁርዓን የአላህ ቃል ከሆነ ታሪካዊ ስህተት ሊኖርበት አይችልም። ነገር ግን ግልጽ የሆኑ የታሪክ ግድፈቶች ይታዩበታል።
የማርያም ማንነት፦ ቁርዓን የኢየሱስን እናት ማርያምን "የአሮን እህት" እና "የእምራን ልጅ" ይላታል። (ሱረቱ መርየም 19:28 እና ሱረቱ አል-ኢምራን 3:35-36)።
ሀቁ፦ ሙሴና አሮን የኖሩት ከኢየሱስ እናት ከማርያም 1,500 ዓመታት ቀድመው ነው። ሙሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለችውን የሙሴን እህት ማርያምን እና የኢየሱስን እናት ማርያምን አንድ ሰው አድርገው በስህተት ቀላቅለዋቸዋል።
የሃማን ታሪክ፦ ቁርዓን "ሃማን" የተባለው ሰው በግብፅ የፈርኦን ሚኒስትር እንደነበር ይናገራል። (ሱረቱ አል-ቀሰስ 28:38)።
ሀቁ፦ የታሪክ ድርሳናት እንደሚያረጋግጡት ሃማን የፋርስ (Persia) ንጉሥ የአርታዘርክስ ሚኒስትር እንጂ በግብፅ የፈርኦን ሰው አልነበረም። ይህም ታሪኩ በወሬ እንጂ በመለኮታዊ እውቀት እንዳልተገኘ ያሳያል።
6. የጦር ምርኮና የባርነት ሕግ
የጦር ምርኮ ድርሻ፦ ሱረቱ አል-አንፋል 8:41 ላይ ከምርኮው "አምስተኛው እጅ ለአላህና ለመልክተኛው ነው" ይላል። ፈጣሪ ለምን የወርቅና የንብረት ድርሻ ይፈልጋል? ይህ ሙሐመድ ሃብት የሚያገኙበት መንገድ አልነበረምን?
የወሲብ ባሪያዎች (Concubines)፦ ቁርዓን ሙሐመድና ሙስሊሞች በጦርነት የያዟቸውን ሴቶች ያለ ጋብቻ "በቀኝ እጃቸው ስር ያሉ" አድርገው ለወሲብ እንዲጠቀሙ ይፈቅዳል። (ሱረቱ አል-አሕዛብ 33:50 እና ሱረቱ አን-ኒሳእ 4:24)። ቅዱስ የሆነ አምላክ እንዲህ ያለውን ግፍ ይፈቅዳልን?
7. ቁርዓን የተሰበሰበበት መንገድ
ሙሐመድ በሕይወት ሳሉ ቁርዓን በአንድ መጽሐፍ አልተሰበሰበም ነበር። የተሰበሰበው ከሳቸው ሞት በኋላ በሰዎች ምርጫ ነው።
ሀቁ፦ ኡስማን የተባለው ሦስተኛው ከሊፋ፣ እሱ ካጸደቀው አንድ ቁርዓን ውጪ ያሉትን ሌሎች የተለያዩ ቅጂዎች በሙሉ እንዲቃጠሉ አዝዟል። (Sahih al-Bukhari 4987)። ቁርዓን የአምላክ ቃል ሆኖ ተጠብቆ ቢሆን ኖሮ፣ ለምን ሌሎች ቅጂዎች ተቃጠሉ? በቃጠሎው ውስጥ የጠፉና የተለወጡ ቃላት እንደሌሉ በምን ይታወቃል?
እህቴ/ወንድሜ ሆይ፣ እስልምናን የተቀበልሽ/ህው 'የአላህ ቃል ነው' ተብሎ ተነግሮህ/ሽ ነው። ነገር ግን የሰይጣን ንግግር የተቀላቀለበት፣ ለነቢዩ የግል ጥቅም (ሚስትና ምርኮ) የሚመች፣ የታሪክ ስህተቶች ያሉበት መጽሐፍ እንዴት የፈጣሪ ቃል ሊሆን ይችላል? እውነተኛው አምላክ እንዲህ አይሳሳትም፣ ለሰው ልጅ የሥጋ ፍላጎትም አያደላም።(ስታነቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ቁራን አታንብቡ እሱ በትክክል አልተተረጎመም 😁)
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:28)
💧ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል ሲል ምን ማለት ነው?
ተወዳጆች ይሄ ቃል ገና ወደፊት የሚፈጸም እንጅ ያለፈ ታሪክ አይደለም ጳውሎስ በዚያን ግዜ ልጁ ራሱ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል በማለት ገና ያልተፈጸመ እንደው ይነግረናል ጳውሎስ ደግሞ እየተናገረ ያለው ጌታ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኃላ ነው እና ይሄን ጌታ ለሞት ይገዛል ብለን ከተረጎምንው ኢየሱስ አልሞተም ገና ወደፊት ይሞታል ወደሚል ስህተት ትምህርት እንሄድ አለን በእርግጥ ይሄን ቃል "ገ" ጠብቆ እና ላልቶ ሲነበብ ሁለት አይነት ትርጉም ነው ያለው በአማርኛው ቢሆንም ግን በሌሎች ቋንቋ ስናረጋግጥ "ገ" ጠብቆ መነበብ እንዳለበት እንረዳለን ላልቶ የሚነበብ ቢሆን ወልድ ለሞት ይገዛል ብለን ሳይሆን ሞት ለወልድ ይገዛል ብለን እንተረጉመው ነበር ግን እንደዚያ አይደለም ከአውዱም ጋር ሲንሄድ የማያስኬደን ሁኖ እናገኘው አለን
💦የጳውሎስ ንግግር ስለትንሣኤ ሙታን ነው ለቆሮንቶስ ሰዎች እሱ በሚጽፍላቸው ግዜ ትንሳኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዎች ነበሩ ጳውሎስም ከሚያምኑ ሰዎች ምስክርነት እየጠራ " ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ የሚሰበክ ከሆነ ግን ከእናንተ አንዳንዶቹ። ትንሣኤ ሙታን የለም እንዴት ይላሉ?"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:12) በማለት ይጠይቃቸዋል ትንሣኤ ሙታን እንደሌለ የሚናገሩትን ለማሣመን እነሱ ባመኑት ከክርስቶስ ትንሣኤ በመጀመር " ትንሣኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሣማ፤"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:13) በማለት ያስረዳቸዋል ።ጳውሎስ የክርስቶስ ትንሣኤ ለሰዎች ትንሣኤ ውጤት መሆኑን በመግለጽ ሙታን የማይነሱ ከሆነ ክርስቶስ ተነሥቷል ማለታቸው ሐሰተኞች የሐሰት ምስክሮቹ እንደሚያደርጋቸው ይነግራቸዋል ክርስቶስ ተነሥቷል ብለው መመስከራቸውን እየነገረ " ሙታን የማይነሡ ከሆነ ክርስቶስ አልተነሣማ፤"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:16) " ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት፤ እስከ አሁን ድረስ በኃጢአታችሁ አላችሁ።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:17)በማለት ያስረዳቸዋል አስቀጥሎም " አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:20) በማለት በሰው በኩል የመጣ ሞት በሰው በሆነው ክርስቶስ እንደቀረ ይነግራቸዋል
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ. 15)
----------
21፤ ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና።
22፤ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። በማለት እንድህ እያለ ከሄደ በኃላ የዓለም ፍጻሜ እንደት እንደሚሆን ሲነግራቸው
እንድህ ይላል
📖" በኋላም፥ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትንም ሁሉና ሥልጣንን ሁሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፥ ፍጻሜ ይሆናል።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:24)
ተወዳጆች መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ግዜ ይላል ምን ማለት ነው?
መንግሥቱ የተባለችው የአማኞች ቤተክርስቲያን ናት እና የተመረጡት ጉባኤ ያለባት ;
እግዚአብሔር አሁን እንደ ነገሠበት አይደለም ፤
እግዚአብሔር አሁን አልገዛም ብሎ ሳይሆን ክርስቶስ " ደግሞም። እንኋት በዚህ ወይም። እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።"
(የሉቃስ ወንጌል 17:21) ይላል።
💧ነገር ግን ኃጢያት፣ክፋት፣ሞት ሥልጣን ነበረው ምክንያቱም ሰይጣን ሰዎችን ያጠቃ ነበርና ። ስለዚህም አለቅነትንም ሁሉና ሥልጣንን ኃይልንም በሻረ ግዜ ፍጻሜ ይሆናል አለ በሌላ አገላለጽ በሌላ አገላለጽ ሥጋ ከቃል ጋር ሲዋሐድ የአብን ልጅነት እንደማግኘቱ መጠን ልጅ ከአባቱ አደራ እንደሚቀበል ቤተ ክርስቲያን ተቀብሏል ጌታ ኢየሱስ እንድህ እንዳለ " ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፥ እነርሱም በዓለም ናቸው፥ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 17:11) ስለዚህም ጳውሎስ መንግሥቱን ባስረከበ ግዜ ፍጻሜ ይሆናል አለ
ልጁ ከአባቱ የተቀበላቸውን በደሙ ቀድሶ ንጹህ አድርጎ ያስረክባልና በአባቱ እና በሱ እና በመንፈስ ቅዱስ በአንድቷ ፍቃድ በገዛ ደሙ ገንዘቡ አድርጓታልና
የዲያብሎስን ኃይል አገዛዝ ሲያጠፋ ከእንግድህ የእግዚአብሔር መንግሥት የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ማጥቃት አይችሉም የዚያኔ መንግስቱ የተባለች ቤተ ክርስቲያን ለአባቱ ያስረክባል የዝያኔ ፍጻሜ ይሆናል ሲለን ነው
ይቀጥል እና ጳውሎስ እንድህ ይላል " ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:25) ምን ማለት ነው ተወዳጆች ከዚያ በኃላ አይነግሥም ማለት ነው? አይደለም ይልቁንስ አጋንንትን እና ክፉዎችን ሁሉ ከእሱ በታች እስኪያደርግ ድረስ ቤተ ክርስቲያንን መምራት እንዳለበት በቤተ ክርስቲያን ላይ ሊነግሥ እንደሚገባው ሲነግረን ነው ማለትም በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ መንግሥ የሚገባው ጠላቶቹን ድል እስከሚያደርግ እና ከእግሩ በታች እስኪያደርግ መሆን እንዳለበት እንጅ ድል ካደረገ በኃላም ሁሌ እንደሚነግሥ ጥርጥር እንደሌለው ሲነግረን ነው
እንድህ ካለ በኃላ " የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው፤"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:26)በማለት ይነግረናል። እንድህ እያለ ከሄደ በኃላ
ጳውሎስ እንድህ ይለናል " ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን። ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:27)
ተወዳጆች ጳውሎስ ሊነግረን የፈለገው ምንድነው
" ይላል፤ ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።"
(ወደ ዕብራውያን 1:8)
" ይላል። ደግሞ። ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤"
(ወደ ዕብራውያን 1:10)
" እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም"
(ወደ ዕብራውያን 1:12) ብሎናል
" እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።
"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:21)
በማለት የነገረን ጳውሎስ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጽ ነው ይለናል ጳውሎስ ሁሉን ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችል ነግሮን ሲያበቃ ሁሉን ካስገዛለት በቀር ሲል ምን ማለቱ ነው?
ሁሉን እንደመጎናጽፊያ እንደሚጠቀልላቸው የነገረን ጳውሎስ ዓመቶቹም ከቶ እንደማያልቁ የነገረን ጳውሎስ ምን ማለት ፈልጎ ነው ተወዳጆች ጳውሎስ ሊነግረን የፈለገው እነዚህን ጥቅሶች ሲጠቅስልን ወልድ ከአብ ይበልጣል ብለን እንዳናስብ በሥልጣን አንድ መሆናቸውን ሊነግረን ሲፈልግ የተዋሐደውን ሥጋ መሠረት አድርጎ ይነግረናል አብ ይበልጣል እንዳንል ደግሞ ወልድ በሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለው ይንግረናል ስለዚህ የጳውሎስ ዓላማ በአባቱና እና በልጁ በአንድት ሥልጣን ሥጋን እንዳከበሩት መናገር ነው።
" ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት #ይገዛል።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:28) ተወዳጆች የወልድ ለአብ መገዛት ምንድነው? እስኪ ንገሩኝ ?
ተወዳጆች ትልቁ መታዘዝ እና መገዛት የባሪያን መልክ መውሰዱ ነው ።
እርሱ ልጅ እና መለኮታዊ አካል ነው ስለዚህ ይታዘዛል ። እንደኛ አይነት መታዘዝ ሳይሆን ይልቁንስ በልግልጽ እንደሚሠራና ሁሉንም ሥልጣን እንዳለው ሁሉን ወራሽ እንደሆነ ልጅ አለበለዚያማ እንዴት አብሮ ዙፋን ላይ ይቀመጣል ስለዚህ ተወዳጆች የወልድ ለአብ መገዛት ይሄ ነው ። የጳውሎስ ሃሳብ ምንድነው ስለመለኮቱ ብቻ ከተናገረ በኃላ በሌላ መንገድ ደግሞ የተዋሐደውን ሥጋ ሲያስብ እሱን የሚያወርዱትን ቃላት ሁላ ይጠቀማል ያለፍርሃት ። እንግድህ ንግግሩ በቀላሉ ስለአምላክነቱ መሆኑ ወይም በተዋሕዶ ሥጋው የሚነገረው ሁሉ ለእርሱ እንደሚያረጋግጥ እንመልከት
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕ. 2)
----------
6፤ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥
7፤ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥
8፤ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።
9፤ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤
ስለመለኮቱ ሲናገር እነዚህ ታላቅ ነገሮችን እንደተናገረ አየ እርሱም በአምላክ መልክ እንዳለ እና ከወለደውም ጋር እኩል መሆኑን እንደገናም ሥጋ የለበሰበትን ጊዜ ሲያስብ ደግሞ እንደገና ንግግሩን አወረደ በተነገሩት መካከል ትልቅ ልዩነት አለና ። ከአምላክ ጋር እኩል ከሆነ ያለልክ እንደት ከፍ ከፍ አደረገው? በእግዚአብሔር መልክ ከሆነስ እንዴት ስም ሰጠው ? የሚሰጥ ለሌለው ይሰጣልና ፣ከፍ ከፍ የሚያደርገውም የተዋረደውን ከፍ ከፍ ያደርልና ። ነገር ግን ሥጋ መልበሱን መጨመር ካለበው እነዚህ ነገሮችን በመናገረዎ አይሳሳቱም ምክንያቱም ሥጋ አምላክነትን አግናቷልና ሥጋ ከቃል ጋር ተዋሕዶ ኢየሱስ የሚለውን ስም አግኝቷል እና እርሱም መድኃኒት ማለት ነው መድኃኒት ያልነበረው ሥጋ መድኃኒት ሁኗልና
ተወዳጆች ጌታ ኢየሱስ እራሱ " ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 11:42) እንዳለ እንድሁም
" ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ። ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል አልሁ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 16:15)
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 5)
----------
21፤ አብ ሙታንን እንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል።
22-23፤ ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም። እንዳለ ተወዳጆች ሥጋ ከቃል ጋር በተዋሐደ ግዜ ልጅነትን አገኘ ሥጋ በቃል ከአብ ዘንድ አንተ ልጅነህ በባልን ገንዘብ አደረግ ልጅ እንደመሆኑም መጠን ፍርድ ሁሉ ተሰጠው ልጅ እንደመሆኑ መጠን ሁሉን ወራሽ ሆነ አንድያ ልጅ እንደመሆኑ መጠን የአብ የሆነው ሁሉ የእርሱ ሆነ ተወዳጆች ታድያ ይሄን ከያዝን ጳውሎስ በዚያን ግዜ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል ማለት ምን ማለት ነው ስንል በዳግም ምጻት ጊዜ ከአባቱ የተቀበለውን የመፍረድ ሥልጣን በለበሰው ሥጋ መተግበር ነው ተወዳጆች ጳውሎስ ልጁ ራሱ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል ሲል የወልድን አምላክነት አንድያ ልጅ መሆኑን የሚያስረዳ እንጅ እሱን ዝቅ የሚያደርገው አይደለም ሁሉን ላስገዛለት ሲልም ፍርድን ሁሉ የሱ የሆነውን ገንዘብ ሁሉ በመስጠት በሁሉ ላይ ፈራጅ ስላደረገው እንጅ ተወዳጆች አንድ ምሳሌ ልስጣቹ አንድ ንጉሥ አንድ ብቸኛ ልጅ ቢኖረው አባቱም ልጁን በዙፋኑ ላይ አስቀምጦ ቢያነግሠው አባቱ ሁሉን ነገር ለልጁ አላስገዛለትምን? አስገዝቶለታል እንጅ ልጁስ ከአባቱ የተቀበለውን ሥልጣን እሽ ብሎ የአባቱን ሥልጣን በፈጽም ልጅ ለአባቱ አልታዘዘምን አልተገዛምንስ? ተወዳጆች ልጁ ከአባቱ ተቀብሎ የአባቱን ትዛዝ በፈጸሙ ልጅ ለአባቱ ታዟል አባትም ልጁ በዙፋኑ ላይ ማስቀመጡና መሾሙ ልጁን ከፍ ከፍ አደረገው እንጅ ዝቅ አላደረገውም ከእርሱ ጋር እኩል አደረገው እንጅ አላሳነሰውም ተወዳጆች የወልድም ለአብ መገዛት እንድሁ ነው ሥጋ ቃልን ሲዋሐድ የአብን ልጅነት ስላገኘ አንድያም ልጅ ስለሆነ ከአብ ዘንድ ያለውን ሁሉ ገንዘቡ አድርጓል ፍርድን ንግሥናን ሁሉ የራሱ አድርጓል ስለዚህም በዚህ በተቀበለው ሥልጣን በደግም ምጻት ግዜ ከአባቱ የተቀበለውን የመፍረድ ስልጣን ስተገብር ለወልድ ለአብ መገዛት ይሄ ነው በለበሠው ሥጋ መፍረድ ይገዛል ተብሎ ተነገረለት ተወዳጆች ሥጋ ምን ይኃል ከፍ ከፍ እንዳለ አያችሁ ጳውሎስም ያለልክ ከፍ ከፍ አደረገው ያለው ይሄን ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር
ይቆየን
ሼር አድርጉ ተወዳጆች
@felgehaggnew
@felgehaggnew
Reviews channel
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
የክርስትና መልስ is a Telegram channel in the category «Религия и духовность», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 4.0K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 7.2, with 0 reviews and an average score of 0.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 60.0 ₽, and with 0 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий