
🌸 May Sale Week on Telega.io
From May 12 to 18 — advertise across all niches with up to 70% off!
Go to Catalog
17.6

Advertising on the Telegram channel «መጽሐፍ ቤት Bookstores»
5.0
Books, Audiobooks & Podcasts
Language:
English
443
0
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
%keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$12.00$12.00local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
✨✨ፍቅር ቅብ-8✨✨
እጁን ከዘረጋበት ቅፅበት ጀምሩ...ስሜ እስኪጠፋኝ ድረስ ልቤ ደንግጦለታል...
"እድል ትባላለች..."...ብላ ሀኒ ስሜን ስታስታውሰኝ በልቤ አመስግኛታለሁ...
"እንደዚች አይነት ቆንጆ ጓደኛ እንዳለሽ ነግረሺኝ አታውቂም...."...ከማለቱ እንደመሽኮርመም ነገር አረገኝ...
"ኧረ መሽኮርመም ካካካ...."...አንዴ ከተጀመረ ማቆሚያ የሌለው ሳቋ ተከተለ...
"ካካካካ ቆ...ቆንጆ ትርጉሙ ተቀየረ መሰለኝ ካካካካ"....ይሄን ስትል ንዴቴ ጣሪያ ነካ.....እንደደበረኝ እንድታውቅልኝ ፊቴን በመዘፍዘፍ ምልክት ሰጠኃት.. በአይኔም ላወራት ሞከርኩ...እሷ ወይ ፍንክች....
"መኬ ግን ጨምረሀል...ቆንጆ ምናምን ካካካ"
"ቆንጆ ናት...እውነቴን ነው..."....ይሄን ያለው እኔን እኔን እያየ ስለነበር የድብርት ፊቴን ፈታሁለት....
"ኧረ መፋጠጥ...እሺ ልነሳላችሁ..."....ይሄን ስትልም ሳቋ አፍኗት ነበር....
"ወሬ አለብሽ..."...ካላት በኃላ አስተናጋጇን በምልክት ጠራት...
"ወሬ አይደለም ይሄ...በት በት ጀምረህልኛል እ...ብትበረታ ነው ጥሩ...ፀጉርህም ወደማለቁ ነው ካካካካ...."
"ቆይ ውበት ማድነቅ አይቻልም..."...አስተናጋጇን ከሸኘን በኃላ መለሰላት...
"ይቻላል...በደንብ ይቻላል...ግን በእኔ ፊት ስታደንቅ ለመጀመሪያ ጊዜህ ነው ብዬ ነው...."
"ለምን አልተደነቅኩም መሰለብሽ..."...ሲላት ሀይለኛ የቃላት ጦርነት እንደሚጀመር ገባኝና ደራሽ ጥይት እንዳያገኘኝ በውስጤ መፀለይ ጀመርኩ።
"ለምን ይከነክነኛል...አይን እንደሌለህ የገባኝ እኮ እድልን ቆንጆ ስትል ነው...ለዚህ ይታዘናል እንጂ አይቀናም..."...የፈራሁት አልቀረልኝም...ለእርሱ የተተኮሰ ጥይት ሽራፊው ደረሰኝ....
ከዚህ ንግግር በኃላ ምግባችን መጣ...ቀጣይ ጥይት ሳይተኮስ በፊት እጄን ልታጠብ በሚል ከመሀላቸው ተነሳሁ...እውነቱን ለመናገር እጄን መታጠብ ሳይሆን መስታወት ማየት ነበር ዋና አላማዬ...ፊቴን በአእምሮዬ መሳል ራሱ ከበደኝ...ሀኒ ምን ሆነች...?...ጠየቅኩ ራሴን።እኔን በማላውቀው ሰው ፊት ማጥላላት ከመቼ ጀምሮ...በእርግጥ እነርሱ በደንብ ይተዋወቃሉ...ከዩንቨርስቲ ጀምሮ...ግን ይሄ እኔን ለማጥላላት በቂ ምክንያት አይደለም...ስደነቅ በእኔ ፈንታ ኩራት የሚሰማት ጓደኛዬ የት ገባች...?ይቺን ሀኒ አላውቃትም...ከማላውቃቸው ሁለት ሰዎች ጋር ያለሁ ያህል ተሰማኝ....
ፊቴን ብቻ በደንብ አይቼ እጄን ውሀ ሳላስነካ ተቀላቀልኳቸው...የቃላት ጦርነቱ በርዶ የደራ ጨዋታ ላይ ደረስኩ...ከመቼው አልኩኝ በሆዴ...መቼስ ስለ እኔ ውበት እንዳይወራ ሆን ብላ ነው ወሬውን ያደራችው አልኩ ደግሜ።..
ወይ ጦጣ መሆን...ቼክም አላደርግ አሉኝ...የእርሷስ ይቅር እሱ ግን ውበቴን ትቶ ምን አባቱ ነው የሚያወራው...ከእኔ ውበት የሀኒ ወሬ በለጠበት...?
"እሺ ቢያንስ ምግቡን ደጅ አታስጠኑት..."...አልኩ አምልጦኝ...
"ማለት ቢያንስን ምን አመጣው...አንቺን ደጅ አስጠናንሽ እንዴ....?"...ሀኒ ናት...አሁን በደንብ ገባኝ...የጥይቷ ኢላማ በትክክል እኔ እንደነበርኩ...እየተፈጠረ ያለው ነገር ጭራሽ ሀገር የማይሰጥበት እንቆቅልሽ ሆነብኝ....
"አይ እንደዛ ማለቴ ብዬ ሳይሆን ከበረደ አያስበላም ብዬ ነው..."
"ልክ ነሽ...እጄን ታጥቤ ልምጣ..."...አለ ባኮፍያው...ይሄን አጋጣሚ ከሀኒ ጋር ለማውራት ልጠቀምባት እያሰብኩ "ጠብቀኝ መኬ እኔም እመጣለሁ"...ስትል ከጥያቄዬ እየሸሸች እንደሆነ ፍንትው አለልኝ።
ከምንም የማልቆጠርበት ቦታ ላይ የተቀመጠች አሻንጉሊት የሆንኩ መሰለኝ...ምን ብዬ ተነስቼ መሄድ እንዳለብኝ ማሰብ ጀመርኩ...
ብዙም አልቆዩም እያሽካኩ መጡ...
"ምንድን ነው ይሄ ሁሉ ሳቅ...ንገሩኝና እኔም ልሳቅ..."...አልኩኝ ልቀላቀላቸው በማሰብ።
"ካካካካካካ...."....አሽካካች...ሳቂልኝ አላልኳትም አይደል...በገነኩ...ይሄን ጊዜ ባለኮፍያው አብሯት አልሳቀም...
"ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለህ...."...አሁንም ወሬው ላይ የለሁበትም...
"ምን ትዝ አለሽ...አያልቅብሽ..."...ምን አልባት ስለ ጊቢ ትውስታቸው ልታወራ ነው ብዬ ባልጠራም ለወሬ ቀላወጥኩ...
"ድሮ ታች ክላስ ስንስቅ አስተማሪዎቻችን ንገሩንና እኛም እንሳቅ የሚሏት ነገር...ካካካ"...ያማታል እንዴ...አሁን ይሄ ከእርሱ ጋር ነው ሊታወስ የሚገባው ወይስ ከእኔ ጋር...እንዳልኳችሁ ነው...ይቺን ሀኒ አላውቃትም...የማይናገረውን መብላት ጀመርኩ።
አላለቀም.....
✍ሸዊት
377
05:45
12.05.2025
imageImage preview is unavailable
የልጅነት ጉዳት (childhood trauma)
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ወይም እነዚህን መሰል አጉል ልምምዶች በልጅነታችሁ ካሳለፋችሁ፣ ምናልባት አሁን የምትታገሏቸው የስሜት፣ የስነ-ልቦና ወይም ማሕበራቢ ቀውሶች የእዚያ ሰበብና ውጤት ሊሆን ይችላል፡፡
1. ለእድሜ የማይመጥን ስራን ሰርቶ ማደግ
2. ጨዋታን ተከልክሎ ማደግ
3. በቤተሰብ (በአሳዳጊ) ስድብንና የቃላት ጥቃትን አስተናግዶ ማደግ
4. ከፍተኛ አደጋ አይቶ ማደግ
5. የወሲብ ጥቃትን ወይም ሙከራን አስተናግዶ ማደግ
6. አካላዊ ድብደባን አስተናግዶ ማደግ
7. የጉልበተኛን (bullying) ጥቃት አስተናግዶ ማደግ
እነዚህ የልጅነት ጉዳት (childhood trauma) ልምምዶች አሁን በሚኖረን ስሜት ላይ፣ የፍቅርም ሆነ ማሕበራዊ ግንኙነት ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽእኖ አላቸው፡፡
ያላችሁ አማራጭ በጉዳዩ ላይ በሚገባ በማጥናት፣ በመማርና እርምጃ በመውሰድ መቅረፍ ነው፡፡
ያንን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን የምክር እገዛ ያስፈልጋችኋል፡፡
ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር በአካል በመገናኘት የግል Counseling, Mentorship, Coaching and Guidance ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?
(በውጪ ሃገር ያላችሁም በTelegram and WhatsApp ከዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ፡፡)
ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም አካውንት inbox በማድረግና ፍላጎታችሁን በማሳወቅ የበለጠ መረጃ ማግኘት ትችላላቸሁ፡፡
@DrEyobmamo
512
16:59
11.05.2025
✨✨ፍቅር ቅብ-7✨✨
እህቴ እግር ማውጣቷን ጠብቃ እናቴም እግር አወጣች....
ብዙ ጥያቄ አሸክማን ደብዛዋን አጠፋች....ለወቀሳ እንኳን የሚሆን የተሸነቆረች ደይቃ አልተወችልንም..... የመጨረሻዋ ምሽቷ ላይ እንኳን የመሄድ አዝማሚያ አላሳየችንም....
እናቴ ከመሄዷ በፊት ጥድፊያ ያለበት ሙያ ስታስተምረኝ እንዴት አልጠረጠርኩም .....ጠብቃ ነበር.....አባቴ የሚወዳቸውን ምግቦች አጣፍጬ መስራት እስክጀምር ታግሳለች....ጠብቃ ነበር....እህቴ እግር እስክታወጣ በትዕግስት ጠብቃለች....'እህት ሁለተኛ እናት ናት' ብላ እጇን አስይዛ መቼም እንደማልተዋት በስሟ ስታስምለኝ መጠርጠር ነበረብኝ አይደል....አልጠረጠርኩም።
እህቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የደብረብርሃን አረቄ እንደቀመሰ ሰው እየተንገዳገደች በእግሯ ስትሄድ አይታት ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ እንዴት አልጠረጥርም....
ጡጦ አስጠጣጠብ እና አዘገጃጀት ከጥናት ሰአቴ ቀንሳ ስታስጠናኝ እንዴት አላስተዋልኩም....
በአስር አመቴ ስለ ወር አበባ ቁጭ አርጋ ስታስረዳኝ እና እኔ ባልኖር እንደዚህ አድርጊ ብላ ሞዴስ አጠቃቀም ስታስተምረኝ እንዴት ዝግጅቷ አይተገለፀልኝም....
**
የአመት በአል እለት ማልዳ ቤተክርስትያን ስማ ትመጣ ነበር.... ከእንቅልፋችን ስንነሳ ከቤተክርስትያን ተመልሳ ሽንሽኗን ለብሳ ጉድ ጉድ ስትል ማየት ለምደናል....
ቀጤማው....ቡናው....እጣኑ.....የማናለቦሽ ዲቦ ዘፈን....እና እናቴ ናቸው ለኔ የበአል ጠዋት ትውስታዎች።
በሆነኛው ቀን በአል ግን ቀጤማውም ቡናውም እጣኑም የማናለቦሽ ዲቦ ዘፈንም እናቴም አበሩብን....ዝም ጭጭ እንዳልን እሷን ጥበቃ ያዝን።
አባቴ ትሄድባቸዋለች ካላቸው ደብሮች ያልበረበረው አልነበረም....ቤተልሄሙ ሲቀረው ጊቢውን....ቤተመቅደሱን....የክርስትና ቤቱ ውስጥ ሳይቀር አገላብጦ ፈትሿል.....የዘበኛ ቤት እና መቃብር ስፍራም አልቀረውም....
የአባቴ አይኖች ለመጀመሪያ ጊዜ እንባ ሲያረግዙ ያየሁት ያኔ ነው....."አስካል መጣች....?"...ብሎ የጠየቀው እኔና አፍ ያልፈታችውን እህቴን ነበር....ደብሩን አዳርሶ ሲመለስ ቤት እንደሚያገኛት ጭላንጭል ተስፋ ነበረችው....እንዳልተመለሰች ሲያውቅ እንዴት አንገቱን ደፍቶ እንደተንሰቀሰቀ ሳስታውስ አሁን ድረስ እንባዬን መቆጣጠር ያቅተኛል....እናቴ አንጀቴን ከምታላውሰው በላይ ሆዴ ተገለባበጠለት.....
እሷ ከሄደችበት ቀን ጀምሮ የአባቴን ድምፅ ያለ ገደብ እንሰማው ጀመር....
ዝምታው የሸኛት መለጎሙ ያስኮበለላት እንደመሰለው ለማወቅ ጊዜ አልፈጀብኝም....በሚያሳብቅ ሁኔታ ማውራት እኛን ማጫወት ጀመረ....አንድም አለመኖሯ እንዳያጎለን እየተጋጋጠ ....ደግሞም ያስኮበለላት ዝምታው እኛ ልጆቹንም እንዳያሳጣው የሰጋ መሰለኝ.....
እናቴ ጥላን ሄዳለች....ምክንያቷ ምንም ይሁን ምን ውጤቱ መሄዷ ነው....እንደ እኔ እንደ እኔ እኛን መተው ባይቀላት እግሯን አታነሳም ነበር....ብዙ የማላውቃቸው ነገሮች መሄጀ ቀኗን እንደወሰኑላት ግልፅ ነው....ምን አልባት ብዙ መከፋት....ውጤቱ ግን ጥሎ መሄድ ነው....ምን አልባት ብዙ እንባ...ውጤቱ ግን አሁንም መሄድ ነው....ምክንያት ከቅጣት ቢያድን አዳምና ሄዋን ከገነት አይባረሩም ነበር አይደል....እንደዛ....የእናቴ ምክንያት ምንም ይሁን ምን ከልቤ ላለመባረር አላዳናትም....
እናቴ ጥላኝ ሄዳለች....
ከማህፀኗ ያወጣችኝ ጥላኝ ከሄደች ማህፀን የማይመርጥ አክሱሙን ተሸክሞ የሚዞር ዮናስ መሄዱ ምን ይገርማል.....
*
አንድ ሁለት እያለ ወራትን ቆጠርኩ.....የእናቴ የውሀ ሽታ መሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቀመኝ.....ሰው ሲርቀኝ ሳይሆን ሲቀርበኝ የምደነግጥ አይነት ሰው አረገኝ....ነካክቶ 'ሂድ ሂድ ብረር ብረር' የሚለው በበዛበት ዘመን የእናቴ መሄድ በማንም መሄድ እንዳልደነግጥ አረገኝ....በዚህ በኩል ደግሞ የአዲስ አበባ ስፋት ጠቀመኝ....ከዮናስ ጋር በአጋጣሚ እንኳን ተገናኝተን አናውቅም... ግዛቱ የመሰሉኝ ሰፈሮችም ቀስ በቀስ ዮናስ ዮናስ መሽተታቸውን ቀነሱ...
ከእርሱ ጋር የማሳልፋትን ቅዳሜ ለአባቴ ቡና በማፍላት ማሳለፍ ጀመርኩ...የእርሱ "አፈቅርሻለሁ" ትርክት በአባቴ እውነተኛ ምርቃት ተተካ...
**
ከሀኒ ጋር በትርፍ ጊዜያችን ብቻ ሳይሆን እንዲሁ ገርበብ ባለ ጊዜያችን መገናኘት የበፊት ልምዳችን ነው...ምሳ ሰአት አብሮ መብላት...አልያም ከስራ ስንወጣ አብረን መሄዱ አስር አስር ፍቅረኛ እንኳን ብንይዝ የማይቀየር ህጋችን ነው....ዮናስ የውሀ ሽታ ከሆነ በኃላ ደግሞ ብሶብናል...
እንዳልኳችሁ ነው...ባገኘናት ሽንቁር መገናኘት ለምደናል...አንዱ ሽንቁር ደግሞ ምሳ ሰአት ነው....የዛሬው ሽንቁራችን ላይ ድንኳን ሰባሪ እንደነበር ያወቅኩት ከደረስኩ በኃላ ነው...ሀኒ ከሆነ ሰው ጋር ናት...
"መክብብ እባላለሁ..."....ብሎ እጁን ለትውውቅ ከዘረጋበት ቀን ጀምሮ የሆነ ነገሩ ውስጤ ቀርቷል...እንደተነገረኝ ከሆነ መክብብ እሳት የላሰ ጠበቃ ነው...እድሜው ከሰላሳ መግቢያ አካባቢ የሚሆን...ቁመቱ ብቅል አውራጅ የሚባል አይነት ባይሆንም ዘለግ ያለ...ግርማ ሞገስ ያለው...ፊቱ የሀብታም ወዝ ያለው...እጁ ከጥጥ የሚለሰልስ....አናቱ ላይ የደፋው ጥቁር ኮፍያ ፊቱ ላይ ካጀበው ፂሙ ጋር ተደምሮ የሆነ ዘፈን ላይ የማውቀው የትግርኛ ዘፋኝ የሚመስል....ለሰላምታ ገርበብ ያደረገው ከንፈሩ ውስጥ ተአምር የሚመስሉ ባዘቶ ጥርሶቹን ያየ እንደ እኔ ቆሞ አይሄድም..... እፍፍፍፍ ሚያስብለኝ አይነት ውበት ያለው ....
አላለቀም....
✍ሸዊት
540
15:33
11.05.2025
✨✨ፍቅር ቅብ -6✨✨
"ዮ..ዮናስ...."....አልኩኝ ሀፍረተ ስጋዬን ስገልጥ እንኳን እንማልሸማቀቀው ሸምቀቅ ብዬ....
"ማን ልበል..."....ያለኝ የሴት ድምፅ ነበር...
"ዮናስ ይኖራል...."
"ሻወር ገብቶ ነው...መልዕክት አለሽ...?"......'እባክህ አምላኬ የቴሌ አዲስ አሰራር ነው በለኝ....ቤት ለቤት ኦፕሬተር መላክ ጀምረዋል በለኝ.....'......እያልኩኝ የማስቀምጠውን መልእክት ማሰብ ጀመርኩ።
እሺ ይሁን እንበል የኔ ዮናስ ነው ሻወር ቤት ያለው ፔንሲዮን ከሴት ጋር የገባው....የኔ ዮናስ አያደርገውም....ከየት አምጥቶ...
'ኦኦኦኦኦ'.....አልኩኝ የሆነ ነገር ብልጭ ሲልልኝ.....ዮናስ እና እኔ የጀመርን ሰሞን መሬት አይንካሽ የሚለኝ ነገር ታወሰኝ....
'ቆይ ለእኔ ለእኔ ሲሆን ነው ሉሲ ደንበኛ ከነበረችባቸው ቤቶች የሚወስደኝ'....ብዬ ራሴን ለጠየቅኩት ጥያቄ 'የምርጫ ቅስቀሳ ላይ እኮ ዮናስ እንዲህ ነው' የሚል መልስ ከራሴ አገኘሁ።
"አይ ምንም መልዕክት የለኝም...ሰላም ልለው ብቻ ነው..."......አልኩኝ የማስቀምጠው መልዕክት ባጣ።
"ማነሽ ግን...?".....ከማለቷ ስልኩን ጆሮዋ ላይ ዘጋሁት።
ምንድን ነው የተፈጠረው...? "ከምኔው ከምኔው" አለች ዘፋኟ....ከምኔው እኔን በሌላ ተካ...
እኔን ማጣት ያን ያሀል ቀላል ነው....?
ቀላል ነው መሰል....
ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ለተሸከመችኝ ሴት ከቀለለ ለሱ እንዴት አይቀለው....
*
እናት እና አባቴ ሲጣሉ ቀርቶ "ያቺን ውሀ አቀብለኝ እስኪ" አይነት ወሬ በተደጋጋሚ ሲያወሩ አይቻቸው አላውቅም.....አባቴ ፊቱ አይፈታም.....እንደውም አንድ አንዴ እናቴን ምን ብሎ ጀንጅኖ እንዳገባት ሳስብ መልስ አጣለሁ....
ከስራ ይገባል....እሱ ሲመጣ ራት ይቀርባል....ሁልጊዜ 'በስመአብ' ብሎ አለመጀመሩን ሳይ 'ይሄ ሰው ከፈጣሪ ጋርም በሳይለንት ነው ሚግባባው' እላለሁ....እናቴን ቀና ብሎ ካያት 'ወጥ ጨምሪ ማለቱ ነው'....አንድ ሁለቴ ለስለስ ያለ ሳል ካሳለ 'ውሀ አምጪ' ነው....ሳያጎርሳት እንደጀመረ ሳያጎርሳት ይነሳል....አነሳሱ ደግሞ 'እሳት እሳት' የሚል ጩኧት እንደሰማ አይነት ነው።
እናቴ የምር አንጀቴን ታላውሰው ነበር....
አይኗን ከእሱ ላይ አትነቅልም ነበር.....
እናንተ አንዳንዴ ዝምታ ወርቅ አይደለም.....
"ይሄ የእድል ትምህርት ቤት ክፍያ ነው.....ይሄ የወር አስፔዛ....ይሄ የመብራት ነው....."....በወር አንድ ጊዜ የሚያደርገው ረጅም ንግግሩ ነበር....
"እንደው አስፔዛው ወር ሳይሞላኝ አለቀ....ሁሉም ነገር ጣሪያ ነካ.....".....እናቴ ድምፁ ሲናፍቃት አስፔዛ ቶሎ ትጨርሳለች.....አንድ አንዴ "ቆጥበሽ ተጠቀሚ" ብሎ ይሰጣታል....አንድ አንዴ ደግሞ ዝም እንዳለ ብር ጠረጴዛው ላይ ያስቀምጣል.....ይሄን ጊዜ እናቴ ጫማውን ትደብቃለች....."አስካል ጫማዬን አጣሁት" ይላል....ስሟን የሚጠራበት አጋጣሚ ሁሉ ላይ ያለውን ቁልምጫ ሳይ "ይሄ ሰውዬ ፍቅር አለበት" እላለሁ።
"ይሄ አባትሽ...."....የሚል ስሞታ ደርሶኝ አያውቅም....
ዝም እንዳለ ታናሽ እህቴ ተወልዳ እግር አወጣች.....
አላለቀም.....
✍ሸዊት
562
08:08
11.05.2025
✨✨✨ፍቅር ቅብ....5✨✨✨
ፍቅር ይሁን መላመድ እንጃ....ብቻ አንዳች ከዚህ ቀደም የማላውቀውን ነገር ከተበኝ....
በየሄድኩበት ሁሉ እንዳስታውሰው አይኔ ላይ ምስሉን ሳለ...ቦታው ሁሉ የእርሱ ግዛት መሰለኝ...
በተለይ ፒያሳ አፄዎቹ በቅርስ ያወረሱት እስኪመስለኝ ድረስ ፤ ከግዛቴ ዘወር በይ ይለኛል ብዬ እስክሸሽ ድረስ ፤ በምንይልክ ፈረስ ላይ በእሳቸው ፈንታ እርሱ ተቀምጧል ብዬ እስክሟገት ድረስ ፤ ወደ እኔ ሽቅብ እንዳይጋልብ እስክፈራ ድረስ ...ፒያሳን የግሉ አደረግኩት...
ከቅፅበት ባጠረች የአብሮነት ጊዜያችን ፤ ሽርፍራፊ ሰከንድ በምትመስል ፍቅር ብለን በሰየምነው ነገራችን ከአዲስ አበባ ከተሞች እግራችን ያልረገጠው ፔንሲዮን የለም ብዬ ብናገር ግነት አይሆንብኝም...ከተወደደ ጠይቀን በችግራችን ስቀን አቅማችንን ካማከለ ደግሞ ጉድጉድ ብለን መውጣት ልማዳችን ነበር....
**
የቡና ሰአቴን ከማሳልፍ ፊት አውራሪ በሆንኩት የታስሲ ሰልፍ ከጀርባዬ ያሉ ሀምሳ ሰዎችን ባሳልፍ ይቀለኛል......
ቡና የምጠጣበትን ቤት በጥንቃቄ ነው የምመርጠው....ወደውስጥ ገባ ያለ....ጫጫታ ማይበዛው....ያልሞቀም ያልቀዘቀዘም አየር ያለው....ረጋ ያለ ሙዚቃ የሚከፈትበት.....ቡና ደግሞ ብቻውን አይደለም.....ጭሱ....ቀጤማው ከነቡና ቁርሱ....የኔ የቡና ፉል ፓኬጅ መስፈርት ይሄ ነው....
ከጫጫታው እና ከግርግሩ ውጪ ሌላው መስፈርቴን የሚያሟላ "ኑ ቡና ጠጡ" ቤት ፒያሳ መሀል ያገኘሁ ሰሞን ነበር ዮናስንም ያገኘሁት....
መፅሀፉን ይዞ የሚቀመጥባት ስፓት ነበረችው.....እልፍ ሲል ንፁህ ንፁህ የሚሸት ሰው ነበር....ንፅህና ይማርከኛል....."እድል" ብሎ ሳይጠራኝ ነው "አቤት" ያልኩለት.....ከአካሄዱ ጀምሮ ግርማ ሞገሱ ሌላ ነበረ....ቡናውን እንዴት ካናቷ ፉት እንደሚላት እያየሁ ሁላ እደነቅ ነበር(አሁን ከሰዉ የተለየ አጠጣጥ ጠጥቶ ነው ሲያዝብኝ እንጂ)
እንዳየው የሚሆናቸውን ከእውነተኛ ማንነቱ ጋር እንዳምታታው ያስተዋልኩት ዘግይቼ ነው.....
ቤቱ እዚም እዚያም በኳስ መልክ ተጠቅልለው የተወረወሩ ቆሻሻ ካልሲዎቹን ሳይ ነው ድራማው የተገለፀልኝ....
የበረሮ መናሀሪያ የሆነው እና የተቆለለውን ቆሻሻ መመገቢያ ሳህን ሳይ ነው ትንሽ ትንሽ የገባኝ.....ቦክሰር ከማጠብ መገረብ እንደሚቀለው ሲነግረኝ ነው እንደመባነን ያልኩት።
ትዝ ይለኛል እኔ ነበርኩ ከፊት ለፊቱ ያለችውን ዱካ ወንበር ባለቤት ያላት እንደሆነ የጠየቅኹት.....
ወሬ ለማስጀመር ያህል ስለሚያነበው መፅሀፍ እንደጠየቅኩትም ትዝ ይለኛል.....ሌላ ጊዜ በሰፊው እንደሚያብራራልኝ እና አሁን ስለቸኮለ መሄድ እንዳለበት ሲነግረኝ አምኜው ነበር....."በጣም ገራሚ መፅሀፍ ነው ....አሁን ስራ ገቢ ስለሆንኩ ሌላ ጊዜ በሰፊው አብራራልሻለሁ.....".....ብሎኝ ከወጣ ቀን ጀምሮ ስለዛ መፅሀፍ አንስቶም አያውቅም....
እኔም ሳነሳበት "ይሄ የእኔ እና ያንቺ ግዜ ነው....ስለገፀባህሪያት የምናወራበት አይደለም....".....ይለኝ ነበር.....ለምናሳልፋት ጊዜ ዋጋ እንደሰጠ እንጂ መፅሀፍ የደረሰበት ደርሶ እንደማያውቅ የነገረኝ አልነበረም(ሲያውርብኝ እንጂ ሶስት ወር ሙሉ አንድ መፅሀፎ ይዞ ሲቀመጥ እንዴት አልጠረጥርም)
ዮናስ ለአልጋ አላመቻቸኝም ነበር.....ያኔ ነው ሁለቴም ሳላስብ ጨዋ ነው ብዬ የደመደምኩት.....
ለዚህ ጨዋ ምንስ ቢሰጠው ብዬ ነበር ጭኔን የከፈትኩለት.....ያልፈለጉ በመምሰል ሴት ላይ እርግጠኝነት የመፍጠር የጭንቅላት ጨዋታ እንደተጫወተ የገባኝ እንደተለመደው ዘግይቶ ነው።
ዮናስን መርሳት አልቀለለኝም.....
እንዴትስ ሊቀለኝ ይችላል.....
ነጋ ጠባ የማስበው እንዴት አይደውልልኝም የሚለውን ነው....."እንደዚህ ይደረጋል" ብዬ በሌለበት የምጯጯኧው በየደቂቃው ነው.....
ብላክ ሊስት ውስጥ ባስገባውም አንድ አስራ አራት ጊዜ "ሞክሮ ገርጥቷል" የሚለውን ዝርዝር እንደማይ እርግጠኛ ነበርኩ...
...ከ2 ወር ምጥ በኃላ ብላክ ሊስት ወዳስገባሁት contact ልደውል እጄን አነሳሁ...ደወልኩ...ስልኩ ተነሳ።
አላለቀም......
✍ሸዊት
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
669
08:21
09.05.2025
✨✨ፍቅር ቅብ....4✨✨
"መነጋገር አለብን...."...አልኩት ባንደኛው ቀን ወደ ነገርየው ልንሄድ ስንል እንደሚሆነው ሲሆን...
"ምነው እድሌ..."...በትንፋሹ እያወራ ነው...የምወድለት አስተያየቱም ተከተለ....እስከ አሁን ፍንክች አላልኩም.....አኳሀኑን ለመናቅ እየተፍጨረጨርኩ ራሴን እገስፃለሁ.....
"ምንድን ነው ግንኙነታታችን...ትርጉም ያጣ አልመሰልህም....?"....ያልጠበቀው ጥያቄ ነበር መሰለኝ ደነገጠ...ውስጤን ሲያራውጠው የነበረ ጥያቄ አፌን ገፍትሮ ሲወጣ እኔ ራሴ ከእርሱ እኩል ደነገጥኩ....
"እንጋባ...."....ይሄን ሲለኝ የስላቅ ሳቄን ልስቅ ቃጣኝ....
"እንጋባ ማለት...."....በምናቤ ቆሎ እየበላን ስንኖር ታየኝ...ለበአል ለበአል ዶሮ ወይ በግ ሳይሆን የተፈጨ በሶ ይዞ ሲገባ....እንደ መናኝ ያለ እህል እየኖርን እንደ አለመኛ ደግሞ ጉድጉድዱን እያደራን ስንፈስክ እና ለእዜሩም ግራ ስንሆን ታየኝ..
"እንጋባ ማለትማ ያው እንጋባ ነዋ...."
"wow በጣም አስረዳኧኝ...ምን ይዘን ነው የምንጋባው....?...ትዳር ምን እንደሆነ ታውቃለህ ግን...."
"በትንሹ...."...አለኝ ከአይኔ ፈቀቅ እንደማለት እያለ...
"በትንሹ...ካካካካ በትንሹ አይደል...."...የምሬን ነው የተበሳጨሁት...በትንሹ የሚያውቀው ነገር ውስጥ ነው ይዤሽ ካልገባሁ ሲለኝ ያሳነሰኝ መሰለኝ.....
"የትዳር ግማሹን መንገድ እኮ already ሄደናል..."...አለኝ ደግሞ...የባሰው መጣላችሁ...ጉድ አልኩኝ በሆዴ...
"የምን ግማሽ መንገድ ነው...በትንሹ ለምታውቀው ነገር ግማሽ እና ሙሉ ምዕራፍ ለማበጀት አልቸኮልክም...."
"ያልተያየነው ምን ቀረ..."....አለኝ ሰውነቴን በአይኑ ስካን እያደረገ....የአይኑን ማረፊያ ጭኖቼ መሀል እንቁዬ ላይ አድርጎ...እኔ እንቁዬ አልኩት እንጂ በእርሱ አይን ከድንጋይም ቀሏል...
"ድሮም እንካ ያሉት እ*ስ ርካሽ ነው"......ትል ነበር ሀያቴ።
"ምን አልክ..."...አልኩ እያጉረጠረጥኩበት...ወዲያው ደግሞ እንዳይደግመው ጥያቄዬ ላይ ጥያቄ ደረብኩ....
"አላማህ ምንድን ነው....?"
"አንቺን ማግባት...."
"እኔን ማግባት ነው የህይወትህ የመጨረሻ ግብ....እሺ ከዛስ...ከዛስ...ነገስ...."
" ለነገ ነገ ያውቃል..."...አለኝ ፈርጠም ብሎ...በገንኩ...ምንም ባልሰሩበት ነገን ተስፋ ማድረግ ምን ይሉታል...?...ቆይ የዚን ወና ጭንቅላት ባለቤት ነበር ሳፈቅር የኖርኩት....?
"ቆይ ታፈቅረኛለህ....?"
"በጣም...በጣም..."....አለኝና ከሽፋሽፍቴ በላይ ለአይኔ ቀረበ...ከዛ እንደ ድመት ይተሻሸኝ ጀመር....
"እድሌ በጣም አፈቅርሻለሁ...እጅግ በጣም....".....ይሄን ብሎ አፌን ወደሚያዘጋበት አቅጣጫ እጁን ሰደደ....ሰውነቴ እግዜር ይስጠው ያለወትሮው በረዶ ሆነ...
"አታፈቅረኝም...የምታፈቅረው ይሄንን ነው...አሁን እያደረግክ ያለውን ነገር...."...ስለው ከመቅፅበት እጆቹን ከሰካበት ነቀለ....
"ማፍቀር ላንቺ ምንድን ነው...."
"ማፍቀር...ማፍቀርማ ለምታፈቅረው ሰው.....".....ጀምሬ ተውኩት....
"እየሰማሁሽ ነው...ጨርሺልኝ እንጂ...."...ጀምሬ መተዌን አስታወሰኝ.....
"አልጨርሰውም...ይልቅ ማለቅ ያለበት ሌላ ነገር አለ...."
"ምን...."
"ትርጉም የሌለው ግንኙነታችን...."
"ማለት እድሌ እንለያይ እያልሺኝ ነው...."
"መስሎህ እንጂ ቀድሞም አንድ ላይ አልነበርንም....እርማችንን አንድ ቀን ብንነጋገር መግባባት አቅቶን አንተ እንጋባ ትላለህ...ስሙኒ ሳይኖረን ቤተሰብ እንመስርት ትላለህ...ገንዘቡን ተወውና በሞተ የስራ ሞራል አብረን እንኑር ስትል ትንሽ አታፍርም...አልገባህም...አንተ ምኑም አልገባህም...."
"ላስረዳሽ ቆይ"....አለኝ እጄን እንደመያዝ ብሎ...ከተቀመጥኩበት ተነሰቼ በጨርቅ የሞላሁት ቦርሳዬን ሳንጠለጥል....
"ያልገባህን ምን ብለህ ልታስረዳኝ ነው....?"...መልሱን ሳልጠብቅ የያዘኝ እጁን መንጭቄ ሄድኩ።
****
"ወንድ ልጅ ያስስገደደ ሳያስመስል ማስገደድ ይችልበታል...ጠንቀቅ በይ...በቀላሉ ጭንሽን የከፈትሽለት ወንድ ጭንሽን ከቤቱ በር ለይቶ አያየውም..."....ብዬ ታናሽ እህቴን የመከርኳት ምክር እና ስራዬን እያሰብኩ በሀሳብ ጭልጥ ብዬ ከሄድኩበት "ኧረ ሂሳብ" የሚል ረዳት ድምፅ አባነነኝ.....
ሰባት ቦታ የተጣጠፈች ከሀያቴ የተበደርኩትን ሀያ ብር ከፍዬ አምስት ብር መልሴ ጋር ሀሳቤ ሄደ.....(ትላልቅ ሰዎች ግን ለምን ብር ያለልክ እንደሚያጣጥፉ አላውቅም).....ረዳቱም እግዜር ይስጠው ደጅ አላስጠናኝም.....ወደ ቀደመው ነገሬ ተመለስኩ.....
'ለእህቴ ሌላስ ምን አልኳት....'....ጭንቅላቴን የኃሊት ስልከው እሱም የተመላለስነወን ቃል በቃል ይዞልኝ መጣ.....
"ተከፍቶ የኖረን ጊቢ ሁሉም ቆሻሻውን ያራግፍበታል...."....ስላት
"ግን እኮ እህቴ ተዘግቶ የኖረን ደግሞ ድር ያደራበታል....."....ነበር ያለቺኝ።
"ድር እኮ መድሀኒትነት አለው....ቁስልን ለዘብ ያደርጋል....ላፅዳህ ብትዪውም በጄ ይልሻል.....የዘመናት ቆሻሻን ዘወር ብታደርጊው እንኳን ጠረኑ ከርቤም አይበቃውም....."....ስላት አስታውሳለሁ።
አላለቀም.....
✍Shewit
891
18:01
07.05.2025
የሆስፒታል ወግ...
የህፃናት ክፍል ተመድበን ካርድ ስናገላብጥ "አሳጥረው ሲፅፉት ከባድ ነገር አይመስልም እንደውም የሰው ስም ነው የሚመስለው አይደል?" አለቺኝ ዶክተሮቹ የፃፉት ካርድ ላይ አልነበብ ያለውን ፅሁፋቸውን ለማንበብ እየሞከረች
አየሁት የበሽታ አይነት የሚለው ላይ "SAM" ይላል severe acute malnutrition ማለት ነው በምግብ እጥረት በጣም የቀነጨረ ህፃን ማለት ነው።
"ቆይ ግን SAM ላለበት ሰው ምንድነው የሚደረገው?!" አለችው አጠገቧ ላለው ነርስ
"ያው acute malnutrition ከሆነ ቶሎ ቶሎ ምግብ እና ፈሳሽ እንሰጠዋለን በጣም severe ደረጃ ላይ ከደረሰ ግን ምግብ ትንሽ ትንሽ ነው የሚሰጠው" አላት እጁን በአልኮል እያፀዳ
"እንዴ እንደውም በደንብ የሚያስፈልገው ለባሰበት አይደለ እንዴ ጭራሽ ትንሽ እንሰጠዋለን?!" አለች ወገቧን ይዛ
"አየሽ ሰውነትሽ አንድን ነገር በጣም ፈልጎ ሲያጣ ያለሱ መኖርን መለማመድ ይጀምራል ስለዚህ ያ በጣም የተፈለገው ነገር ጠላት ይሆናል ሰውነትሽ ያለሱ ለመኖር ሲጣጣር አሰራሩ ይቀየራል ምግብን በአግባቡ ከመጠቀም በትንሽ ምግብ መኖር መለማመድ ይጀምራል
ስለዚህ ብዙ ምግብ ሲያገኝ እንደባዕድ ነገር ይቆጥረው እና ለማውጣት ሲጨነቅ ያልተጠበቀ ጉዳት ሊያመጣበት ይችላል አሁን ገባሽ" አላት
"ዋው ወይ ጉድ ሰውነታችን እኮ ሁሌም ነው የሚደንቀኝ" አለችው እና ወደ እኔ ዞራ "አይገርምም" አለቺኝ
"ቀላል እንደውም ከዘመኔ ትውልድ ጋር ተመሳሰለብኝ" አልኳት ራሴን በግርምት እየነቀነቅኩ ተመሳስሎው ገርሞኝ
"ረሀብ ላይ ስለሆንን ብለሽ ነው?!" አለች ግራ መጋባቷ ፊቷ ላይ እየተስተዋለ
"አይደለም ስለ አካላዊ ርሀብ እና መቀንጨር አይደለም እኔ የማወራው ስለ ፍቅርን እንደ ምግብ ስለተራበው ልባችን ነው የፆታዊ ብቻ ሳይሆን ሁሉም አይነት ፍቅር ነው የምልሽ እና በጣም የሚያስፈልገን ፍቅር ሆኖ acute የሆነውን ፍቅር ብናገኝ የምናልፍበትን stage አልፈን
አሁን severe love-deficit ሆነን ብቻችን መኖር ብቻችንን መደሰት ብቻችንን ማዘን ብቻችንን ከሀዘን መውጣት እየተለማመድን ሳለ ልባችን "ሰውን መውደድ" የነበረው መደበኛ ስራዋን ትታ "ብቻ መኖርን" ለመደች
አሁን ጠብታ ፍቅር ሲቀርበን ልባችን ይገፋዋል ምክንያቱም መራራቅን እንጂ መቀራረብን ረስተናል ፍቅር እንዴት መቀበል እንዳለብን እንዴት መስጠት እንዳለብን ባጠቃላይ እንዴት ፍቅርን handle ማድረግ እንዳለብን ረስተናል
ስለዚህ እንደ SAM ታካሚ ፍቅርን በጥቂት በጥቂቱ መለማመድ አለብን ምክንያቱም በብዙ የመጣ ፍቅር ለእኛ ጠላት ነው እንዴት እንደሚያዝ አናውቅበትም ለዛ እኮ ነው የቀረበንን በሙሉ ሰበብ እየፈለግን ስንርቅ የኖርነው አይገርምም መመሳሰሉ" አልኳት ጥርስ ጥርስ ሆኜ
"ለዛ እኮ ነው ነርሲንግን ትተሽ ፍልስፍና ተማሪ ስልሽ የነበረው አሁን ነይ ለልጆቹ መድሀኒታቸውን እንስጣቸው በረሀብ ሳያልቁ" አለች
የእኛንስ ልብ ማነው በትንሽ በትንሽ በትንሹ ፍቅር የሚያስለምደው??
✍ናኒ
981
17:28
06.05.2025
✨✨ፍቅር ቅብ...3✨✨
"በናትሽ ሀኒ አትቀልጂ...ጭንቅ ብሎኛል..."...ስላት የማያባራ የመሰለኝ ሳቋን ባንዴ ቁርጥ አደረገችውና ማውራት ጀመረች...
"ይኧውልሽ ዮናስ ትዳር በትክክል ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቀው ነገር የለም...'ለምን ማግባት ፈለግክ' ተብሎ ሲጠየቅ ውስጡ ቢመልስ ኖሮ መልሱ 'የአልጋ ላይ ቡጊ ቡጊን የመሰለ ምን አለ...ያለ ገደብ እሱን ለማስነካት ነው' ነበር የሚሆነው..ግን የሚመልሰው አፉ ነው...'ስለምወድሽ ስለማፈቅርሽ...ማሬ ቅብርጥሴ' እያለ ይጠግርሻል....አይንሽን ክፈቺ...ከቃላቱ በላይ ድርጊቱን እይው...ላንቺም ቢሆን በባዶ ሆድ ነጋ ጠባ አልጋ ላይ መጨፈሩ ጥሩ አይደለም...u know energy የሚባል ነገር አለ...በባዶ ሆድ ስራ ካካካካካ...."...የተለመደው ሳቋን አስከተለች።
እኔ ውስጤ በጥያቄ መራወጥ ጀመረ...
ስራ ላይ የሌለ ትዕግስት ለኔ ከየት መጣ...ለሌላ ሰው የሌለው አክብሮት ለእኔ ከየት ተፈበረከ....የሚበላው አጥቶ እርሱን ለሚለምን ህፃን የሌለ ርህራሄ ለእኔ ከወዴት ተገኘ....?....በጥያቄ ታጨቅኩ....
****
ሶስት ቀን ከሞላው የልብ ካልሆነ ኩርፊያ በኃላ የሉሲ እኩያ የሚመስል ካፌ ቀጠረኝ...ዛሬ ስለዚህ ግንኙነት በግልፅ ላወራው ነበር ሀሳቤ....በአልጋ ላይ ትርኢት እና በውብ ቃላቶች ብቻ የታጀበው ግንኙነት እንዲያበቃ አልያም መስመር እንዲይዝ...
"እድሌ..."
"እድልክ አይደለሁም...እድል ካልከኝ ይበቃል...."...ከዚህ አጠራሩ በኃላ ምን እንደሚከተል ስለማውቅ እየተጠነቀቅኩ ነው...በኔ ቤት።
የፈራሁት አልቀረልኝም ተጠጋኝ...ከእርሱ ሌላ ማየት እስከማልችል ድረስ ቀረበኝ...ከዛም የምወድለትን አስተያየት አየኝ...እጄን አጥብቆ ይዞ ወደራሱ ሲያስጠጋኝ አር የነካው እንጨት እንደያዝከኩ ነገር መነጨቅኩት...'ጎበዝ እድል እንዲህ ነው መጀገን' ብዬ ራሴን አበረታታው...ቢያንስ እናውራ አይባልም...?...አኩርፌ ነበር እኮ...
"እድሌ ይገባኛል አጥፍቻለሁ...በጣም እያበሳጨሁሽ እንደሆነ ይገባኛል...ግን እመኚኝ እለወጣለሁ...በቅርቡ አንድ አሪፍ ስራ አግኝቻለሁ...እንደሚሳካ አልጠራጠርም...ከዛ እንጋባለን...."
"ኧረ ጉድጓድ ግባ"....በሆዴ ነው...በአፌ ምንም አልተነፈስኩም...ግን ምናለ ትንሽ ራቅ ብሎ ቢያወራ...የትንፋሹ ሙቀት እስኪሰማኝ ድረስ ተጠግቶኛል...ከአይኑ ግጭት እንዳልወድቅ እየተጠነቀቅኩ ነው....
"አፈቅርሻለሁ...አፈቅርሻለሁ...ሌላውን እርሺው..."...ካለኝ በኃላ ገፄን ገፁ ውስጥ አገኘሁት...አላስገደደኝም...ግን አስገድዶኛል...ዝብርቅርቅ ያለ ስሜት ነው...ግራ መጋባት አለው...መወሰንም አለመወሰንም...አዎ ከዚህ በኃላ በ'አፈቅርሻለሁ' ትርክት ላለመቀጠል መወሰኔን ላውጅ ነበር አመጣጤ...በነበር ቀረ እንጂ...
"ክክክ-ክክክ".....የሆነ አጠገባችን ያለ ሰው ጉሮሮውን ሲጠራርግ ነው ከንፈሮቻችን ወደየ ቦታቸው የተመለሱት...
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ገና ስሙ ሲጠራ ያ ለግላጋው ቁመቱ አይታወሰኝም...ከዛ ይልቅ የሚጎላብኝ የአክሱሙ ርዝመት ነው...ዘናጩ ዮናስ አእምሮዬ ውስጥ የለም...ራቁቱን ቅልብጭ ይልብኛል...
ዮናስ ሲባል ሰው ሁሉ የሚደነግጥለት መልኩ እና ጆሮ ሚጠልፈው ድምፁ ጭራሽ አይታወሰኝም...ከጠራው ቆዳው በላይ በላብ የተጠመቀ ሰውነቱ ነው የሚመጣልኝ.....ከምወድለት ድምፁ በላይ አልጋ ላይ ስንጨፍር የሚያወራቸው ትርጉም የለሽ መዘላበዶች እና ቅስቻዎች ናቸው ትውስታዎቼ....
ገና "እድሌ" ከማለቱ ከስሜ በላይ ኩርፊያዬን የሚያስረሳ አለም ውስጥ እንደሚከተኝ በስውር ስለሚነግረኝ ነው ከራሴ ጋር ትግል ውስጥ የሚጨምረኝ....የሚያንቀለቅለኝ መጨረሻዬ ሁለት በሁለት የሆነች ጎጆ ውስጥ እንደሚሆን ስለማውቅ ነው....በራሱ ሜዳ... ራሱ ፈረስ ሆኖ...ራሱ ጋሪ ሆኖ... ራሱ ነጂ ሆኖ ነው የሚሾፍረኝ...
ከባነንኩ በኃላ ተበሳጨሁ...'ለዚህ ነበር ይሄ ሁሉ ፉከራ'...ጠየቅኩ ራሴን...በቃ በቅፅበት ለምረሳው ነው እንዲህ ያዙኝ ልቀቁኝ አልኩ ደግሜ።
"ይቅርታ ከዚህ ካፌ ብዙም ሳትርቁ ፔንሲዮን አለ...."....አለ የቀሰቀሰን አስተናጋጅ...ጉሮሮ አጠራረጉ ግን ይቺን ለመናገር ብቻ አይመስልም ነበር...ነብሳቸውን ይማረውና የክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ጉሮሮ እንኳን ያን ሰረቅራቃ ድምፅ ጀባ ለማለት እንደዚህ የሚጠራረግ አይመስለኝም።
"እሺ እሺ ሂሳብ አምጣልን..."....እኔ የሆነ ቦታ ለመሄድ ስጣደፍ በማወጣው ድምፅ ከአስተናጋጁ ጋር ያወራል...እኔ ሽምቅቅ እንዳልኩ አለሁ...
"የኔ ጌታ ምንም አላዘዛችሁም እኮ...."....ከማለቱ ሳቄ አመለጠኝ...አስተናጋጁም ከእኔ ጋር ተደመረ...የዮናስ ግንባር ላይ ችፍ ያለው ላብ የሀፍረት ብቻ አይመስልም...አይኑም በመደፍረስ አገዘው...ከመርበትበቱ የተነሳ ላልተጠቀምነው ነገር ቲፕ ሰጠ...ባሁኑ አልሳቅኩም ጤንነቱን ጠረጠርኩ እንጂ.....
ከካፌው ወጣንና ከእኔና እሱ ውጪ ደንበኛ ከሌለው ቁርቁዝ ካለ ፔንሲዮን ገባን...የተለመደው እርግጫ...የተለመደውን ጭፈራ ጨፈርን....ይሄን ጭፈራ ለሳምንት ቀጠልን...እንዳይደብረኝ ብሎ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ፖዝሽን መቀየር ብቻ ነው...ያኔ አንድ ጭፈራ የነበረው ወደ ብሄር ብሄረሰቦች ጭፈራ ይቀየራል...'በባዶ ሆድ ስራ' አለች ሀኒ...
***
✍ሸዊት
ይቀጥላል....react እያረጋች
928
09:13
06.05.2025
✨✨✨ፍቅር ቅብ 2✨✨✨
ኳኳኳኳኳኳኳኳ....የሚል የሚዘገንን ድምፅ ወደዚኛው አለም መለሰን....
"ዮናስ...ኧረ ዮናስ...."....አከራይዋ ሁለቴ ተጣርተው ሲያበቁ አሰራ ሁለት ጊዜ ያንኳኳሉ...
"አቤት ማዘር..."....በቅጡ ባልከፈተው አይን ማታ ያሽቀነጠራቸው ልብሶቹን ለመፈለግ እየሞከረ...ከብዙ መንደፋደፍ በኃላ ቅርብ ያገኘውን ለብሶ ከፈተላቸው....
"የመዳኒያለም ያለ..."...አሉ አፍንጫቸውን በነጠላቸው እየሸፈኑ...
"ደህና ደሩ ማዘር..."....አለ አንገቱን ወዴት ማድረግ እንዳለበት ሳይወስን አንዴ ደፋ አንዴ ደሞ ቀና እያደረገ እና የብርድልብስ ርጋፊ የሞላውን ትብትብ ፀጉሩን በግራ እጁ እየፈተገ(ወንዶች ሼም ሲቆነጥጣቸው ፀገራቸውን ለምን እንደሚያሰቃዩት አላውቅም)...
"ምን ደህና ይታደራል ስትዘሉብኝ እያደራችሁ....እኔ ምለው ቁንጫ የሚዘልብኝ መች አነሰኝ እእ...ደግሞ ቤቱ ትኃን ትኃን አይደል እንዴ ሚለው...እስቲ አየር ይግባው መስኮቱን ክፈቱት...ምንድን ነው እንደዚህ መግማማት...."...አሉ ወደ እኔ እያፈጠጡ።
ጠቆር ያለ ፊታቸው ላይ ማድያት ጣል ጣል ቢያደርግባቸውም አስራ አንድ የወለዱ አይመስሉም....አንዳንዴ አስራ አንድ መውለዳቸውን ሳስብ 'አይተኙም ነበር ማለት ነው' እላለሁ....ደርባባ ናቸው....አይናቸው ወደውስጥ ገባ ያለ ነው... ትንሽ ሲናገሩ ኩፍ የምትለውን ነጥብ አፍንጫቸውን ሳይ ሳቅ ሳቅ ይለኛል....አንገታቸው ስር የተንዘላዘለው ድርብርብ ጥልጥል ስጋ ሲውረገረጉ ልወድቅ ነው ልነጠፍ ነው ቅለቡኝ የሚል ይመስላል...
ቤቱ እንደታፈነ ለእኛ አልታወቀንም...ሲጀመር ይሄ ቤት ገነታችን ነበር...ሌላ አለም እያልኩ ሳወራችሁ የነበረው ይቺን የክብሪት ቤት የምታህለውን ጎጆ ነበር...
"ግም ለግም አብረህ አዝግም ኤድያ...."....ልፉ ሲላቸው እንጂ ሳይሉንም እያዘገምን አይደል...ቀጠሉ።
"እሺ ዮናስ ይሄ የአባትህ ቤት ነው እንዴ የሚመስልህ...እስቲ እየኝ እናትህን እመስላለሁ እንዴ..."....አሉት አይናቸውን ለማጉረጥረጥ እየሞከሩ... የተቀበረው አይናቸውን ና ውጣልኝ አይነት ትግል ሲታገሉት በቅፅበት በእንባ ሞላ...
"ኧረ ማዘር ደሞዝ ስላልገባ ነው በቅርቡ ከፍላለሁ...."....አለ ለእሳቸው ሳይሆን ለእኔ የሚያወራ ይመስል በጥልቀት እያየኝ...እንዲህ ሲል የትናንቱ ቅንጡ ምሽት ትዝ አለኝ...በእርግጥ ከእራቱ በኃላ ወደ ቤት እንሂድ ሲለኝ ገንዘብ እንደጨረሰ ገምቼ ነበር...ለሆቴል አልጋ የሚከፍለው ስለሌለ ወደተከፈለበት ቤቱ የወሰደኝ መሰለኝ እንጂ....
"በዚህ ሁለት ቀን ካልከፈልክ ቤቴን ጥለህ ውልቅ...."....አሉና ወደ እኔ ዞረው የመፀየፍ አይነት አስተያየት አይተውኝ ወጡ....የሌላውን ጊዜ ባላቅም እሳቸው ቢያንስ አስራ አንድ ጊዜ ተንጎዳጉደዋል....አኳሀናቸውን ላየ ግን እሳቸው እና ባለቤታቸው ነገርየውን 'በስመአብ' ብለው አማትበው ጀምረው በ'አቡነዘበሰማያት' የሚያሳርጉ ነው ሚመስሉት።
"ህይወቴ ገንዘብ ነበረኝ ለቶማስ አበድሬው አቆይቶብኝ ነው...ማለት ዛሬ ይይመልስልኛል..."...አለኝና መልስ በሚጠብቅ ሰው አስተያየት አየኝ...ንግግሩ ላይ መሸማቀቅ አለ...
ምናል ይሄ መሸማቀቅ "እንጋባ".....በሚለኝ ቅፅበት ቢከሰት....ምንም ሳልለው የተጠቀለልኩበትን አንሶላ ጥዬ ልብሴን ለባብሼ ወጣሁ።
***
"ከዚህ በኃላ እንጋባ አይደለም በ 'እ' ጀምሮ በ 'ባ' የሚያልቅ ቃል ከአፉ ቢወጣ የመጨረሻችን ነው ሚሆነው አልኳት የልብ ጓደኛዬን....
ስለማታውም ስለጠዋቱም ትርኢት ከተረኩላት በኃላ...
"ካካካካካካካ...."....አሽካካች....
"በናትሽ አሁን ይሄ ምኑ ያስቃል..."...አልኳት ኮሶ እንደቀመሰ ሰው ፊቴን አጨማድጄ..
"ሞራሉ ነዋ የሚያስቀው....እሱ እኮ ለመኖር ያንቺ ዳቦ እና የእሱ አክሱም በቂ እንደሆነ ነው የሚያስበው...wow simple life ይልሻል ይሄ ነው ካካካካ...."...ከቅድሙ የቀጠለ ሳቋን አስነካችሁ....
"ታውቂያለሽ በጣም አፈቅረዋለሁ...የዋህነቱን...ትዕግስቱን...አክብሮቱን ከእርሱ ውጪ ሌላ ወንድ ላይ አይቼው አላውቅም...ግን ሰርቶ መለወጥ የሚለው ነገር ሀሳቡ ውስጥም የለም...ሰባት ታቦት ጋር ሄዶ ተስሎ ያገኘውን ስራ ተጣልቶ ለመልቀቅ ሰባት ቀንም አይፈጅበትም...ትሁትነቱ ከአውሬም ጋር ሳይቀር ያስማማዋል ብዬ በአስር ጣቴ ልፈርም እልና ከእኔ እና ከአከራዩ ውጪ የሚያከብረው ሰው አለመኖሩ ግር ይለኛል..."
"ምን አልባት ትክክለኛ ባህሪውን የሚያሳየው ሌሎች ሰዎች ላይ ቢሆንስ...በሌላ አማርኛ አንቺ ጋር እያስመሰለ ቢሆንስ...."
"ምን አገኝ ብሎ ያስመስላል...?"
"ዳቦሽን ነዋ ካካካካካካካ...."....ሳቋን ማቆም አቃታት....
አላለቀም.......
✍Shewit
623
05:09
05.05.2025
imageImage preview is unavailable
☑️ ቆንጆ ናት... አፍላ .... 15 አመቷ ነው።
ጎረምሶች ሲያዩዋት አይናቸው ይጎለጎላል። ጎልማሶች አይተው ይመኛታል። ወንዶች ይከጅሏታል። ሴቶች በቅናት እንደ ሽንኩርት ይልጧታል።
☑️ አንድ ቀን እንዲህ ስል ጠየቅኳት።
<<ማግባት የምትፈልጊው ባል ምን መስፈርት እንዲያሟላ ትፈልጊያለሽ?
>>
☑️ በፍጥነት መለሰችልኝ
የተማረ መሆን አለበት፤ ማስተርስ ያለው ይመረጣል። ከተቻለ የግል ቢዝነስ የሚሰራ፤ ኢንቨስተር ቢሆን አሪፍ ነው፤ ካልሆነ ግን አሪፍ ደሞዝ ሊኖረው
ግድ.ነው። መኖሪያ ቤቱ G+2 ቢሆን ደስ ይለኛል፤ ከG+1 በታች ግን
አልፈልግም።
✅ መኪና በጣም ነው የምወደው። አሪፍ መኪኖች ቢኖሩት አሪፍ ካልሆነም
ከተጋባን በኋላ እኔ እንዲገዛ አደርገዋለሁ። ሙድ የገባው ቢሆን ደስ
ይለኛል። ሁሌ ግን የሚቅም፤ የሚጨብስ እና የሚያጨስ መሆን
የለበትም። ጨዋታ የሚያውቅ ሁሌ የሚያስቀኝ!!!
✅ ቁመቱ በጣም እንዲረዝም አልፈልግም። እኔ አጠር ስለምል በጣም
እንዳይበልጠኝ። ደረቱ ሰፋ ያለ ሆኖ ቦርጭ የሚባል እንዲኖረው
አልፈልግም።
✅ጸጉሩ ፍሪዝ ቢሆን ደስ ይለኛል፤ ድሬድ ቢሆን ደግሞ ነፍስ ነው። አይኑ
የሚያምር፤ መልኩ ጸይም መሆን አለበት በጣም ቀይ ወይም በጣም ጥቁር
ወንድ አልወድም። አለባበሱ ዘናጭ መሆን አለበት። የሚወደኝ፤
የሚንከባከበኝ፤ ሮማንቲክ የሆነ፤ በሳምንት ቢያንስ ሁለቴ የሻማ
እራት ያለበት ሆቴል የሚጋብዘኝ፤ ቢያንስ በወር ሁለቴ ጭፈራ ቤት
የሚወስደኝ፤.ከበዓላት እና ከልደቴ ቀን በተጨማሪ ስጦታ እያመጣ ስርፕራይዝ
የሚያደርገኝ፤ ፍቅር የሚያውቅ፤ በተለያየ ቁልምጫ ስም የሚጠራኝ እና
ታማኝ ከእኔ ውጪአንዲት ሴት የማያይ ...
☑️ >>ይበቃል አልኳት እንደማታቆም ስለገባኝ። እንዲህ አይነት ወንድ
ኢትዮጵያ ውስጥ ቀርቶ አስቴር አወቀ ዘፈን ውስጥ እንኳን አይገኝም አልኩ
በውስጤ። ለሷ ግንአልነገርኳትም።
✅ ከአስር አመት በኋላ ሳገኛት 25 አመቷ ነበር። አላገባችም። ዩኒቨርስቲ
ጨርሳ.ስራ ይዛለች። ጥቂት ቦይ ፍሬንዶች ይዛ ለቃለች። አሁንም ታምራለች
እንደድሮው ግን የሰው ሁሉ አይን ማረፊያ አይደለችም። መልሼ ያንኑ ጥያቄ
ጠየቅኳት።
✅ <<ማግባት የምትፈልጊው ባል ምን አይነት ነገሮች ማሟላት አለበት?>>
የማፈቅረው ሰው መሆን አለበት፤ ፍቅር ከሌለ ላገባው አልችልም።
ከማልወደው ሰው ጋር አንድ ቀን ላድር አልችልም። ታማኝ እንዲሆን
እፈልጋለሁ። እንዲያከብረኝ እፈልጋለሁ። ጥሩ ስራ ቢኖረው፤ ማንበብ
የሚወድና በሃሳብ የምንግባባ ቢሆን ደስ ይለኛል። ቆንጆና ሃብታም ከሆነ ጥሩ ነው፤ ካልሆነም ግን አብረን ሰርተን መለወጥ እንችላለን። ዋናው መግባባት ነው። በተረፈ ቤተሰቡን የሚወድ እና የማይዋሽ መሆን አለበት። ወንዱ ሁሉ
የማይታመን ሆነብን እኮ። ዋናው የሚታመን ከሆነ ሌላው ችግር
የለውም>>
✅ ጊዜው ይሮጣል!!! ከአስር አመት በኋላ ስንገናኝ አላገባችም። 35 አመት
እያለፋት ነበር። ደግሜ ያንኑ ጥያቄ ጠይቅኳት።
<<ማግባት የምትፈልጊው ባል ምን አይነት ነገሮች ማሟላት አለበት?>>
ትንሽ አሰብ አደረገኝና
<<የምግባባው ሰው ከሆነ ሌላው ችግር የለውም>> አለችኝ
መልኩ፤ ጸጉሩ፤ ሃብቱ፤ እውቀቱስ አልኳት።
<<ወንድ ልጅ ደግሞ መልክ ምን ያደርግለታል? ከቺምፕ (ቺምፓንዚ)
መለስ ካለ ሌላው ችግር የለውም>> አለች እየሳቀች።
☑️ ከአስር አመት በኋላ ሳገኛት አግብታ ሁለት ልጆች ወልዳ ነበር።ባሏ
አጭር፤ ጥቁር፤ መላጣ፤ የከባዳ መኪና ሾፌር አይነት ቦርጭ
ያለው፤ሱሪውን ቦርጩ መሃከል ላይ የሚታጠቅ፤ ሁልጊዜ መላጣውን
የሚያልበው ዝጋታም ነገር ነው
✅<<እንዴት ነው ትወጂዋለሽ>> አልኳት
✅<<ምን ማለትህ ነው ትዳር አይደል?>>
✅<<ማለቴ ድሮ የነገርሽኝ አይነት ሰው አይደለም ብዬ ነው?>>
✅<<ያኔማ አየር ላይ ነበርኩ፤ እድሜ መስታወት ነው፤ ብዙ ያስተምራል፤
አሁን
ተምረን ልብ ገዝተን ነው>> አለች ተከዝ ብላ።
✅ <<ሁሌ የማይቀያየር አንድ መስፈርት ነበረሽ፤ ታማኝ መሆን አለበት ትይኝ
ነበር።
ባልሽ ታማኝ ነው?>>
<<ታማኝ እግዜር ብቻ ነው፤ በቃ ግን ... ትዳር ስለሆነ ከማይታመን ሰው
ጋር መኖር ትለምዳለህ፤ አየህ አሁን የገባኝ ነገር ትዳር ማለት እንደ ፖለቲካ
ነው።
☑️ ፖለቲከኞች ውሸት እየነገሩን አብረን እንደምንኖር ትዳር ውስጥም ይሄ
ያጋጥማል>> አለች
<<በትዳርሽ ደስተኛ ነሽ?>> አልኳት እያዘንኩ
✅ <<ደስታ አንጻራዊ ነው፤ በልጆቼ ደስ ይለኛል፤ ትዳሬን አከብራለሁ። በተረፈ
ግን እየኖርኩ ነው>> አለች ፈገግ ብላ። በዛች ቅጽበታዊ ፈገግታ ውስጥ
የጊዜን ኃይለኝነት አየሁ።
ጊዜ ነው እንጂ ቁምነገራም
ባላባትነት አያኮራም እንዲሉ እመው።
አንብበው ከወደዱት 👍👍
📨@Enmare1988
📨@Enmare1988
631
19:01
04.05.2025
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
2 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
c
**ffeenold@******.io
On the service since June 2022
24.04.202515:42
5
Everything is fine. Thank you!
Show more
New items
Channel statistics
Rating
17.6
Rating reviews
5.0
Сhannel Rating
6
Subscribers:
4.4K
APV
lock_outline
ER
10.8%
Posts per day:
0.0
CPM
lock_outlineSelected
0
channels for:$0.00
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Add to CartBuy for:$0.00
Комментарий