
- Main
- Catalog
- Psychology & Relationships
- Bini Girmachew
Bini Girmachew
English:Mental health, wellness tips, self-growth guidance and practical advice to navigate life's challenges.
Channel statistics
der (ASPD)
የዚህ ችግር ተጠቂ ግለሰቦች በሌላ ስሞ ሶሺዮፓዝ (sociopath) በመባል የሚታወቁ ሲሆን ለሰዎች፣ ግለሰቦች፣ ስራ፣ኑሮ፣ ባህሪ እና ስብዕና ምንም ግድ የማይሰጣቸዉ እና ጥላቻ ያደረባቸዉ ናቸዉ፡፡
በተጨማሪም ሰዎችን ያለምንም ምክንያት የሚቃወሙ፣ የሚያመናጭቁ፣ የሚያንቋሽሹ፣ርህራሄ በሌለዉ መንገድ ሰዎችን የሚያዋክቡ ናቸዉ፡፡
በተጨማሪም በብዛት ስርዓት በመጣስ፣ በዋሾነት፣ በአደገኛ ሱስ መጠመድ ዋነኛ መገለጫዎቻቸዉ ናቸዉ፡፡ ከዚህ ባህሪያቸዉ የተነሳ በቤተሰብ፣ በስራ፣ በትምህርት ቤት እና በማህበረሰብ ላይ ችግር ፈጣሪና ሀላፊነት የማይሰማቸዉ ናቸዉ፡፡
መንስኤዉ፡- የጸረ ህዝብ ማንነት ቀዉስ ድንገተኛ እና ቅጽበታዊ በሆነ ሁኔታ ሊገለጥ እና ሊታይ ስለሚችል የዘርፉ አጥኚዎች መሰረታዊ መንስኤዉ ይህ ነዉ ብለዉ ለመደምደም አዳጋች እንደሆነባቸዉ ይናገራሉ፡፡ ሆኖም በዘር የሚዋረስ እና በህይወት አጋጣሚ ብሎም ከወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት በአንድ ግለሰብ ህይወት ዉስጥ (ASPD) ሊከሰት እንደሚችል ያስረዳሉ፡፡ እንዲሁም በአእምሮ ስርኣት መዛባት እና የነርቭ ሲሰተም ችግር ሊከሰት እንደሚችል ይነገራል
ምልክቶች፡- ለሞራል ህግጋት ግድየለሽ መሆን መዋሸት እና ሌሎችን ማታለል የግል ባህሪ /ስራ/ ማድረግ
ሌሎች ሰዎችን ርህራሄ በሌለበት መንገድ መመለከት፣መጠርጠር ለግል ጥቅም ብቻ ሰዎችን መቅረብ እና ማታለል ግትርነት ለተሳሳተ ድርጊት እና ስህተት የማስተካከያ እርምጃ አለመዉሰድ ለስርዓት እና ህግ አለመገዛት
• ከሰዎች ጋር ጠላትነትን መፍጠር አላፈላላጊ እና አደገኛ ሃላፊነትን መዉሰድና ማን አለብኝነት የዚህ ባህሪ ግድፈት ምናልባትም በጎልማሳነት እድሜ ተከስቶ እንደሆን በወጣትነት እድሜ ችላ የተባለ ችግር ሊሆን እንደሚችል ይታሰባል፡፡ በአፍላ ወጣትነት እድሜ ላይ የሚከሰት የህብረተሰብ ጥላቻ ችግርን ችላ ብሎ ማለፍ አደጋዉ የከፋ ይሆናል። ለመሆኑ በወጣትነት እድሜ የሚታዩ ምልክቶች ምን ምን ናቸዉ።
-በሰዎች እና በተፈጥሮ (እንስሳትን ጨምሮ) ግለሰቡ ጥላቻ ማሳየት ንብረት ማዉደም እና ማበለሸት ማጭበርበር እና መዋሸት ስርቆት እና ዝርፍያ
- ዉንብድና እና የህግ ጥሰት
መከላከያዉ፡ በአብዛኛዉ ይህ ችግር በአፍላ ወጣትነት እድሜ የሚከሰት ሆኖ በጎልማሳነት ደግሞ የሚገለጥ አግባብነት ያለዉ ክትትል እና ድጋፍ ሳይደረግለት ከቀረ ለከፋ አእምሮ መቃወስ ሚያበቃ በመሆኑ ቤተሰብ፣ትምህርት ቤት፣ ብሎም በዘርፉ ልምድ ያላቸዉ ባለሙያዎች ለችግሩ ተጋላጭ የሆነን ግለሰብ ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል፡፡
የስነባህሪ ትምህርት በግል/በቡድን መከታተል,ማህበራዊ ተግባቦት፣ እና ስነ ተግባቦት ትምህርት ማስተማር
• የህይወት ክህሎት ስልጠና መስጠት የቤተሰብ ቴራፒ እና ልጅ አስተዳደግ ስልጠና መዉሰድ
የተለያዩ የሳይኮሎጂስት እና ሳይካታሪስት እገዛ እንዲያገኝ ማበረታታት እነኚህን እና ሌሎች የአእምሮ ህክምናዎችን በመከታተል የጸረ ህዝብ ባህሪ ችግርን በጊዜ መከላከል ይቻላል፡፡
እርዳታዉ፡ በዚህ ችግር የተጠቃን ግለሰብ እንዴት መርዳት ይቻላል?
ይህንን የጸረ ህዝብ ባህሪ ማከም ዉስብስብ እና ከባድ ቢሆንም ለረዝም ጊዜ የሚቆይ የስነ-አእምሮ እና ስነ ባህሪ ህክምና እና ድጋፍ መስጠት ተጎጂዉን ግለሰብ ወደ መደበኛ ባህሪ ይመልሰዋል ተብሎ ይታመናል፡፡ ይህ የስነ-አእምሮ ድጋፍ ፈጣን ለዉጥ እንዲያመጣ የችግሩ ተጠቂ የሆነዉ ግለሰብ ፈቃደኝነት ወሳኝ ነዉ ምክንያቱም የምክር አገልግሎት ሆነ ትምህርት ያለ ግለሰቡ ፈቃድ በአስገዳጅነት ስለማይሰጥ፡ እንዲሁም ብዙዎቹ የጸረ ህዝብ መሰረተ ቢስ ጥላቻ (የችግሩ ባለቤቶች) ይህ ችግር እንደሆነ ስለማይቆጥሩ ነዉ፡፡
ከምክር አገልግሎቱ ጋር ተያይዞ ሊያገኙዋቸዉ የሚገባቸዉ እርዳታዎች
-ቁጣን እና ንዴትን እንዴት መቆጣጠር እንዳለባቸዉ ማሰልጠን
-ማኛዉንም ሱስ እንዲያቆሙ ማገዝ እና የመጠጥ ሱስ ተጠቂ ከሆኑ እንዲያቆሙ ማስተማር
- የህይወት ክህሎት ስልጠና መስጠት
@binigirmachew
@binigirmachew
የትኩረት ማጣት በልጅነት ብሎም በጉልምስና እድሜ የሚከሰት ችግር ሲሆን የቅብጥብጥነት ችግር በብዛት በህጻናት ላይ የሚታይ ችግር ነዉ።
ያልተረጋጋ ማንነት፣ የተግባቦት ችግር፣ ዝቅተኛ የስራ እና የትምህርት ዉጤት፣ አናሳ በራስ መተማን በዚህ ችግር የተጠቁ ሰዎች ባህሪ መገለጫ ነዉ፡፡
መንስኤዉ፦ የዘርፉ አጥኚዎች የዚህ ችግር ሁነኛ መንስኤ ምንነትን በጥናታቸዉ ባይደርሱበትም የተወሰኑ መላምቶችን እንዲህ ያስቀምጣሉ
• በቤተሰብ /በቤተዘመድ/ ይህ ችግር ካለ በዘር ሊወረስ እንደሚችል የዘርፉ ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡
በአከባቢያዊ ተጽእኖ የአእምሮ ስርዓት /ነርቭ ሲስተም እድገት መዛባት ጥቂቶቹ ናቸዉ፡፡
ምልክቶች፦ ተደጋጋሚ የትኩረት ማጣት እና ባህሪ መለዋወጥን ተከትሎ
• ስራን ወይንም ሃላፊነትን በአግባቡ ማጠናቀቅ አለመቻል ችኩልነት እና ቁጡነት
• ከዉጥረት ቶሎ አለመዉጣት
መከላከያው፡ ጥናቶች መንስኤዎችን ይህ ነዉ ብለዉ ባልተነተኑበት እና ባልገለጹበት መከላከያዉ ይህ ነዉ ማለት ባይቻልም በዋናነት ደግሞ በዘር የሚዋረስ እንደሆነ በመጥቀስ ይህን ችግር ከስር መሰረቱ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መከላያዉን ማቅረብ አስቸጋሪ ያደርገዋል፤ ነገር ግን (ADHD) ለመከላከል እና ለመቀነስ አጋላጭ የሆኑ ክስተቶችን በመቀነስ መከላከል ይቻላል ብለዉ የዘር ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
• ከተለያዩ መጠጥ እና አልኮል፣ ሱስ መራቅ
• ዕጽን ከመጠቀም መቆጠብ
• ዉጥረትን ማስወገድ እና መቀነስ
እርዳታዉ፡- በዚህ ችግር ዉስጥ ያሉ ግለሰቦች ሳይኮሎጂካል እና ሳይካተሪካል ድጋፍ
የሚሹ ናቸዉ። ሳይኮሎጂካዊ እርዳታዎቹ፦
• የጊዜን ጥቅም ማስተማር እና የጊዜ አጠቃቀም ክህሎትን እንዲያዳብሩ ማድረግ
ቅብጥብጥነትን መቀነሻ አጋዥ ስራ እና ስልጠናዎችን ለግለሰቡ መስጠት
• የዉጥረት እና የችግር አፈታት ዘዴዎችን ማስተማር
• ካለፈዉ ስህተት የመማር እና በፍጥነት የመዉጣት ክህሎትን ማዳበር
ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ፣ ከባልደረባ ጋር ያለን ግንኙነት እና ቅርርብ ማስተካል
ቁጣን እና ንዴትን መቆጣጠር
በተጨማሪም የዚህ ችግር ተጠቂ የሆነን ግለሰብ በተናጠል ሆነ በግሩፕ እንዲሁም
የቤተሰብ ምክር አገልግትን በመስጠት ካሉበት ችግር ማላቀቅ ይቻላል፡፡
@BiniGirmachew @BiniGirmachew
YouTube Bini Girmachew
https://youtu.be/fHf3n9gS180?si=36qN8bP-XtuUdh7V
ይህ የአእምሮ መዛባት ከጭንቀት ጋር የተያያዘ ችግር ሲሆን በመደበኛነት በየእለት ተእለት ስራችን እና ድርጊታችን በትምህርት ቤት፣ በቤት ዉስጥ፣ በስራ ቦታ ከባልደረቦቻችን እና ከአለቆቻችን ጋር ያሉትን ሁኔታዎችን መጋፈጥ እና መልመድ ሲያቅተን የሚከሰት መቃወስ ነዉ፡፡
መንስኤዉ፦ የስራ ቦታ ችግር፣ ከባል-ድረባ እና ከአለቃ ጋር ያለ ችግር፣ እንዲሁም የስራ ሁኔታን መልመድ አለመቻል፣ በትምህርት ቤት ከመምህር እና ከተማሪ ጋር ያለ ችግር ፣ እንዲሁም ትምህርት ቤቱን መልመድ አለመቻል፣ ድንገተኛ ህመም ወይንም አካል ጉዳት፣ የቅርብ ዘመድ ሞት እና የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ አለመቀበል፣ የህይወት መስመር ለዉጥ፣ የሀገር (መኖርያ) ቦታ ለዉጥ ወዘተ ለ (AD) መከሰት መንስኤዎች ናቸዉ፡፡
ምልክቶቹ፡- የአድጀስትምንት ዲስኦርደር እንደየ ሰዉ ባህሪ እና እንደተከሰተዉ ክስተት ልዩነት ይለያያል፡፡ ከላይ መመልከት እንደሞከርነዉ የተለያዩ ጉዳዮች ሰዎችን ዉጥረት ዉስጥ ሊከቱት ይችላሉ። ለአንድ አንድ ሰዎች በመልካም ጎኑ ሊታይ የሚችል ዉጥረት ለሌላዉ ሰዉ ደግሞ እጅግ ጎጂ ሆነዉ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም የ (AD) ዉጥረት ግለሰቡ የሚሰጠዉ ምለሽ ነዉ፡፡
በተጨማሪም የአድጀስትመንት ዲስኦርደር አወንታዊ ሆነ አሉታዊ ዉጥረቶችን በመቀመር እና በማጤን የሚሰጥ ምላሽ ነዉ፡፡ በሀዘን ምክንያት የሚፈጠር ተስፋ መቁረጥ፣መቆዘም እና ከዚህ የተጎዳ ስሜት
መዉጣት አለመፈለግ፡፡ የማያቋርጥ ሀዘን፣ለቅሶ እና ቁዘማ
• ከመጠን በላይ መስጋት እና መሸበር
• የእንቅልፍ እጦት፣
• የትኩረት ማጣት
• የስሜት መጎዳት
እለታዊ ስራን በብቃት መስራት አለመቻል ከማህበራዊ ስራዎች ራስን ማግለል
ከስራ፣ ከጥናት/ትምህርት፣ ከአስፈላጊ ድርጊቶች ራስን ማራቅ ማቀብ ከላይ የተጠቀሱት እና ሌሎች ምልክቶች እየታዩና እየቀጠሉ እንዲሁም ምንም መከላከያ እና እርዳታ ግለሰቡ ካላገኘ ራስን መጥላት ብሎም ራስን እሰከማጥፋት የሚደርስ አደጋ ሊከሰት ይችላል፡፡
መከላከያዉ፦ የአድጀስትመንት ዲሶኦርደርን ለመቅረፍ ይህ ነዉ የሚባል ፍቱን መድሃኒት ባይኖርም ነገሮችን የመጋፈጥ እና የመልመድ ብቃትን በማዳበር ግለሰብን መርዳት ይቻላል፡፡የዉስጥ ጥንካሬን በማጎልበት (AD) እንደሚፈጠር ግንዛቤ በማስጨበጥ ራስን እና ሌሎችን መርዳት ይቻላል፡፡ በህይወት አጋጣሚ ስራ አጥ ሚኮንበት፣ በጡረታ መገለል፣ የአካል መጉደል እና የልብ ወዳጅን ማጣት ድንገተኛ ክስተት ቢከሰት ሁኔታዎችን መጋፈጥ እና መልመድ ሌሎች የተሸሉ አማራጮችን በማየት በዉስጥ ማንነት መጠንከር የዚህ አእምሮ መዛባት መከላከያ መንገዶች ናቸዉ፡፡
እርዳታዉ፡ በዚህ ችግር ዉስጥ ያሉ ሰዎች ራሳቸዉን በማጠንከር እና በማስለመድ ከችግሩ ሊወጡ ይችላሉ፡፡ በዚህ ህመም የተጠቁ ሰዎች በራሳቸዉ አቅምን አዳብረዉ እና ራሳቸዉን መርዳት ከተሳናቸዉ ወደ ህክምና ጣቢያ በመሄድ ክትትል እና ድጋፍ ሊያገኙ ይገባቸዋል፡፡
- በሳይኮ ቴራፒ፣ በግል እና በቡድን የዚህ ችግር ተጠቂዎችን መርዳት፡፡
- ስሜታዊ ድጋፍ እና እርዳታ (emotional support)
- ወደ መደበኛ ህይወት ግለሰቡን ለመመለስ ማገዝ
- ይህ ክስተት በሰዉ ልጅ ህይወት ዉስጥ ሊከሰት እንደሚችል እና የአደጋ መጋፈጥ ብቃትን ማዳበርያ ትምህርት ማስተማር
- በተጨማሪ የአእምሮ ሃኪም የሚሰጠዉን ክትትል እና ህክምና በአግባቡ መከታተል፡፡
@BiniGirmachew @BiniGirmachew
🧠 ይህ የአእምሮ መዛባት በጣም ከባድ፣ ጽኑ እና ለአእምሮ የሚከብድ አደጋ፣ሁኔታ እና ክስተት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የአእምሮ ህመም አይነት ነዉ፡፡
ይህ የአእምሮ ህመም በግለሰብ ህይወት ዉስጥ ከአቅም በላይ የሆነ አደጋ እንደተከሰተ የሚታይ እና የሚገለጥ ሲሆን ከጥቂት ወራት/ ጊዜያት ብኋላ የግለሰብን አእምሮ ቀስ በቀስ በመረበሽ ይጀምራል፡፡
መንስኤዉ፦
-ድንገተኛ ሞት
- በቤተሰብ፣በዘመድ አዝማድ፣ በቅርብ ወዳጅ ላይ የተከሰተ
እንደሆን ድንገተኛ አደጋ
- በራስ ወይንም በሌሎች ላይ የደረሰ አሰቃቂ አካላዊ ጥቃት
- በራስ ወይንም በቅርብ ዘመድ ላይ የደረሰ አካላዊ ጥቃት
ምልክቶች፦ የስነ አእምሮ ጤና ጥናት አጥኚዎች እንደሚሉት ከሆነ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት የ (ASD) ምልክቶች ሶስቱ በአንድ ሰዉ ላይ ከታዩ ግለሰቡ የዚህ አእምሮ መዛባት ተጠቂ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
➢ የደነዘዘ ባህሪ ወይንም ስሜት፣ ራስን ከማንኛዉም ማህበረሰባዊ ግንኙነት
ማግለል፣ ቁጡነት፣ስሜታዊነት
➢ ስለ ራሱ፣ ስለአከባቢዉ እና ስላለበት ሁኔታ በቂ ግንዛቤ የሌለዉ ከሆነ (ራስን
መርሳት)
➢ በእዉነታዉ አለም እንዳሉ በመዘንጋት በምናብ አለም እንደሚኖሩ መገንዘብ
የእዉነት ሳይሆን በደመነፍስ እየኖሩ እንዳለ መረዳት በራሳቸዉ ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ የደረሰዉን አደጋ የዉሸት እንደሆነ እዉነታን በመካድ ላለማስታወስ እና ላለመቀበል መሞከር
እርዳታዉ፦ በማስቀደም የስነ አእምሮ ባለሙያ ግለሰቡን መመርመር እና ችግሩን መለየት ብሎም ድጋፍ እና እርዳታዉም በመስኩ ሙያተኛ በሆነ ሰዉ መሰጠት አለበት:: ብዙዉን ጊዜ በዚህ አእምሮ ህመም የተጠቁ ግለሰቦች እራሳቸዉን አልፎም ሌሎችን የመጉዳት ዝንባሌ ስላላቸዉ በቅርበት ክትትል እና ድጋፍ እንዲሁም በቅርብ ዘመድ ቁጥጥር ስር መሆን አለባቸዉ መሰረታዊ ፍላጎቶችን እየተከታተለ የሚንከባከብ ግለሰብ ሊመደብለት ይገባል፡፡ ተጠቂዎቹ ራሳቸዉን መንከባከብ ስለማይችሉ ምግብ፣ልብስ፣ብሎም በቂ እረፍት እና እንቅልፍ እንዲያገኙ መርዳት ያስፈልጋል እያንዳንዱ ግለሰብ በራሱ ወይንም የቅርብ ሰዉ መርዳት እንዲችሉ ስለ ስነ አእምሮ ደህንነት በቂ ግንዛቤ ቢኖረን ይመረጣል፡፡
• በቤት ዉስጥ ከሚደረግ እርዳታ እና ድጋፍ በተጨማሪ ወደ ህክምና ማእከል
መዉሰድ ይገባል የስነ-ባህሪ ከትትል እና ድጋፍ ቴራፒ ማግኘት ይገባዋል (cognitive behavioral
therapy)
@BiniGirmachew @BiniGirmachew
የአእምሮ መዛባት ማለት የእእምሮ ህመም (መቃወስ) ሲሆን በሰዉ ልጅ የእለት ተእለት
ህይወት ፣ እንቅስቃሴ እና ባህሪ ዉስጥ የሚታይ መደበኛ የሆኑ ስራዎችን መከወን አለመቻል ነዉ፡፡ የአእምሮ መዛባት መለክያዉም ከሰዉ ልጅ የእለት ተእለት ህይወት ወጣ ያለ (ያፈነገጠ) ባህሪ ሲታይ ነዉ፡፡ እንዲሁም የአእምሮ ጤና እንደ የህብረተሰቡ ፣ እንደየሀገሩ ባህል እንደሚለያይ ኤፒዲሞሎጂስቶች ይናገራሉ፡፡
በአለም የጤና ድርጅት ጤና የሚለዉ ቃል ትርጉም፦ አካላዊ፣ አእምሯዊ፣ ማህበራዊ ግንኙነት መልካም ሲሆን እና አሁን አሁን ደግሞ መንፈሳዊ ህይወትንም ለማካተት እየተሰራ እንዳለ ይገለጻሉ፡፡ በተለይ መንፈሳዊ ደህንነት እንዲጨመር አፍሪካዉያን እና ኢሲያዉያን በመንፈሳዊ ህይወት ልምምድ ጤናቸዉን እየመሩና ካላይ ያየናቸዉን የሰዎችን ሁለንተናዊ ጤና የማስጠበቅ አቅሙ ከፍ ያለ ነዉ ብለዉ ስለሚያምኑ ነዉ፡፡
የሰዉ ልጅ የእለት ተእለት ገጠመኝ ዉስጥ ከቀላል እሰከ ከባድ፣ ከልል እሰከ ዉስብስብ ሃሳቦች አእምሮዉን (ሃሳብን) ሊሞሉት ይችላሉ፡፡ የሰዉን ልጅ አእምሮ የሞሉ አስተሳሰቦች አንድ አንዱ አሉታዊ ሲሆኑ አንድ አንዱ ደግሞ አወንታዊ ናቸዉ፡፡ ከዚያ በዘለል ማንነትን የሚጎዱ በየእለቱ ወጥነት በጎደለዉ ሁኔታ እና ክስተቶች አስተሰሰብ ሊዛባ፣ ሊታወክ ብሎም ሊታመም ይችላል፡፡
እንዲሁም የአንድ ሰዉ የአእመሮ መዛባት ተከስቷል በምንልበት ጊዜ መሰረታዊ የሆኑ ምርመራ እና ምልከታ የሚያስፈልጋቸዉ ጉዳዮቸች አሉ እነሱም በግለሰቡ ሃሳብ (እዉቀት) የምንለዉ እና ስሜት መካከል ያለ አለመግባባት ወይንም መናበብ አለመቻል እንደ ሆነ የስነ አእምሮ ጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
እዉቀታችን ወይንም በዉስጣችን የተፈጠረዉን ሀይል እመራለሁ የሚል ትግል ከፍላጎታችን እና ከስሜታችን ይህም አከባቢዉ ጭምር ከሚፈጥረዉ ጫና ጋር መዋሃድ ካልቻለ የአእምሮ ጤና መዛባት ተፈጠረ ይላሉ፡፡
በእርግጥ አንድ ሰዉ የአእመሮ ጤናዉ ተዛብቷል ብሎ ለመግለጽ የየእለት ስራ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ከሆነ ደግሞ የቤት ዉስጥ ጉዳዮች ፣ የመስርያቤት ስራ ወዘተ በአግባቡ መምራት እና ማስተዳደር አለመቻል መረጋገጥ አለበት፡፡
ከ300 ዓይነት በላይ የተለያዩ የአእምሮ መዛባት አይነቶች እንዳሉ የዘርፉ ተመራማሪዎች የሚገልጹ ሲሆን በዚህ ምእራፍ ዉስጥ የተለያዩ የአእምሮ ጤና ቀዉሶችን፣ የሰዉን አስተሳሰብ የሚያዛቡ ክስተቶችን፣ መንስኤዎቻቸዉን፣ ምልክቶቹን እና ይህ አይነት ግለሰብ አጠገባችን ቢኖር እንዴት እንደምንረዳዉና የአእመሮ ጤናዉን ጭምር እንዴት መጠበቅ እንዳለበት በዝርዝር እንመለከታለን፡፡
@BiniGirmachew @BiniGirmachew
ቲክቶክ ክሬተር አዋርድ በጤና ዘርፍ እጩ ሆኘ ስለተመረጥሁ አመሰግናለሁ
ለመምረጥ👉 https://www.tca2025.com/
Click Best health and Medical content creator
Vote 👉Dr.Tizazu
ይህ በፎቶው የምትመለከቱት ግለሰብ ለ15አመታት ከሚስቱ ጋር ቤት ተከራይቶ ዛምቢያ ውስጥ በካሳማ ከተማ ይኖራል።
ለ15 ዓመታት በ3500 የዛምቢያ ኪዋች(ብር) የተከራዩት ቤት የሚስቱ መሆኑን እና ኪራይ ሲከፍል የኖረው ለሚስቱ ቤት መሆኑን በድንገት የሰማው ባል ራሱን ስቶ ነፈስ ውጭ ነፈስ ግቢ ላይ ይገኛል...😂
የሰው ልጅ
Reviews channel
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
Catalog of Telegram Channels for Native Placements
Bini Girmachew is a Telegram channel in the category «Психология и отношения», offering effective formats for placing advertising posts on TG. The channel has 114K subscribers and provides quality content. The advertising posts on the channel help brands attract audience attention and increase reach. The channel's rating is 6.4, with 1 reviews and an average score of 5.0.
You can launch an advertising campaign through the Telega.in service, choosing a convenient format for placement. The Platform provides transparent cooperation conditions and offers detailed analytics. The placement cost is 12.0 ₽, and with 1 completed requests, the channel has established itself as a reliable partner for advertising on Telegram. Place integrations today and attract new clients!
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Комментарий