
Monetize Telegram Mini App with Telega.io
Connect your app, set CPM, and watch your revenue grow!
Start monetizing
27.6

Advertising on the Telegram channel «TIKVAH-ETHIOPIA አዲስ ሪፖርተር - NEWS ዜና»
5.0
3
News and Media
Language:
Amharic
0
0
Share
Add to favorite
Buy advertising in this channel
Placement Format:
keyboard_arrow_down
- 1/24
- 2/48
- 3/72
- Native
- 7 days
- Forwards
1 hour in the top / 24 hours in the feed
Quantity
keyboard_arrow_down
- 1
- 2
- 3
- 4
- 5
- 8
- 10
- 15
Advertising publication cost
local_activity
$2.40$2.40local_mall
0.0%
Remaining at this price:0
Recent Channel Posts
በመሰረተ- ልማት፣ በመልካም አስተዳደር፣ በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ከሕዝቡ የተነሱ ጥያቄዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ተገለጸ
----------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 24፣ 2017 ዓ.ም ፤በኦሮምያ ክልል በመሰረተ-ልማት በሰላምና ፀጥታ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከሕዝቡ የተነሱ ጥያቄዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ የምክር ቤት አባላት ገልፀዋል ።
ይህ የተገለጸው፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የክልል ምክር ቤት ተመራጭ አባላት ከመረጣቸው ሕዝብ ጋር በልማትና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።
በተለይም በመሠረተ ልማት መንገድ እና የንፁህ ውሃ ተደራሽነት እና የፕሮጀክቶች አፈፃፀምና ጥራት መንግሥት አትኩሮት ሊሰጥ እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቶል ፡፡
በተደጋጋሚ ከሕዝብ ተነስተው ምላሽ ባልተሠጣቸው የመራሮ ስልጣና የአስፓልት መንገድ ጥያቄ እና ከነጌሌ እስከ ዋከና ሮቤ ገርጄዳ ከተማ የአስፓልት መንገድ ባልተጠናቀቁ የውሃ ፕሮጀክቶች ፣ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች የአከባቢው ስላምና ፀጥታ ዙሪያ ላይ ያተኮረ ነበር ፡፡
ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ አቶ ስንታየሁ ጥላሁን በመልካም አስተዳደር ፣በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና በሰላም ጉዳዮች ከሕዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎች ትኩረት በመስጠት በወቅቱ ምላሽ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ከዚህ በፊት በተደረገው የሕዝብ መድረክ በሕዝቡ የተነሱ ጥያቄዎች አንዳንዶቹን ምላሽ ለመሥጠት ጥናት መጀመሩንና ተሠርተው በጥራት ምክንያት አገልግሎት የማይሰጡ ፕሮጀክቶች አገልግሎት መሥጠት እንዲችሉ እየተደረገ ያለው ጥረት የወረዳው የመንግስት አመራሮች ቁርጠኛ ሆኖ መሥራት እንዳለባቸው ተመላክቷል።
ሕዝቡ በበኩሉ፣ ትምህርት ቤቶች ከትምህርት ጥራት አነፃር ትኩረት እንዲሠጠው፣ የአስፓልት መንገድ ጥያቄ ምላሽ የሚፈልግ እና ፣የንፁህ መጠጥ ዉሀ ተደራሽነት ፣የመብራት ዝርጋታ ይደረግ፣ወጣቱ ተደራጅቶ ወደስራ እንዲገባ መንግስት ትኩረት ይሰጥ የሚሉ አስተያየቶች ከሕዝብ ተነሥቷል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች በርካታ መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንደተመለሱ ገልፀው፣ ቀጣይም ለልማት እንቅፋት የሚሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት በጋራ መስራት አለብን ብለዋል።
ህዝቡን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የየወረዳው መሥተዳድር አካላት በጥናት በመደገፍ መፍታት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR
በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
135
18:47
30.08.2025
ከሕዝብ የተነሱት የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ እያገኙ መሆኑን ተገለፀ
----------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 24፣ 2017 ዓ.ም፤ ባለፉት አራት ዓመታት ከመራጩ ሕዝብ የተነሱት የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ እያገኙ ስለመሆኑ ተገልጿል::
ይህ የተገለፀው በኦሮምያ ክልል አርሲ ዞን ዲክሲስ ወረዳ የመራጭ ተመራጭ መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአካባቢው ተወካይ የተከበሩ ሐጂ ከዲር (ዶ/ር) እንዲሁም የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት አባል የተከበበሩ ወ/ሮ ሰዓዳ ቃሶ እና የተከበሩ ወ/ሮ ሸዋዬ አይደፈር በጋራ በመሆን የውይይት መድረኩን መርተውታል።
በመድረኩ ባለፉት አራት ዓመታት ደረጃ በደረጃ ምላሽ የተሰጣቸው ዋና ዋናዎቹ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በዝርዝር ለውይይቱ ተሳታፊዎች በተከበሩ . ዶ/ር ሐጂ ቀርቧል፡፡
ማህበረሰቡ ባለፋት ዓመታት ለተነሱት የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎች ከቀበሌ ጀምሮ በየደረጃው ባሉት የመንግስት መዋቅሮች እየተሰጣቸው ያለው ህደት አበረታች መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም ምላሽ ያልተሰጣው ጥያቄዎች እና ያልተቀረፉ ተግዳሮቶች በትኩረት እንዲሰራላቸው ጠይቋል፡፡
የዲክስስ ወረዳ የሆስፕታል ጥያቄ ፤የድክስስ መልቲ ቪሌጂ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጠናቆ በሚፈለገው መልኩ አገልግሎት አለመስጠት ፤ የአስፓልት መንገድ ካሳ ክፍያ አለመጠናቀቅ፤ የመብራት ተደራነሽነት ችግር ፤ የሥራ አጥነት እና የኑሮ ውድነት ችግሮች በህበረተሰቡ ከተሰነሱት ጥያቄዎ ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በተጨማሪ ከሀያ ዓመት በላይ በሁለት ቀበሌዎች ሲተዳደሩ ቆይታው በአሁኑ ጊዜ በአንድ ቀበሌ ብቻ እንዲተዳደሩ የተደረገው አዲሱ የድክሲሲ ከተማ መዋቅር በከተማዋ ልማት፤ መልካም አስተዳደር እና ሰላምን በቀጣይነት ከማስፈን አንጸር ከፍተኛ ተግዳሮት እያመጣ መሆኑን የውይይቱ ተሳታፊዎች በአጽኖት አብራርቷል፡፡
ህበረተሰቡ ከተነሱት ጥያቄዎች በወረዳ ደረጃ ምላሽ በሚያገኙት ላይ ከሁሉም ሴክተሮች ጋር በመሆን እንደሚሰሩበት በውይይቱ ላይ የተገኙት የወረዳው አፈ ጉባኤ አቶ ሙክተር አማን እና የወረዳው ምክትል አስተዳደር እና የግብርና ቢሮ ኃለፊ አቶ ከዲር ቡባ በትኩረት እንደሚሰሩ በሰጡት አስተያየት አብራርቷል፡፡
በመቀጠል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ ዶ/ር ሐጂ ከዲር በተነሱት ጥያቄዎች እና ቅሬታዎች ላይ ከክልል ምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን ለሚመለከተው አካል አቅርበው ምላሻቸውን እንደሚከታተሉ ገልጿል፡፡
በመጨረሻም በዘንድሮ ዓመት የተገኘው የወረዳው ውጤታማ የሥራ አፈጻጸም በበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እስከ አሁን ያለው ውጤታማ የሆነው የወረዳው ሰላም በዘላቂነት እንዲቀጥል ሁሉም ወረዳው ነዋሪዎች ከወረዳው አመራር ጋር በመሆን በትኩረት እንዲሰሩ የተከበሩ ዶ/ር ሐጂ ከዲር ማሳሰባቸውን ገልጸውልናል።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR
በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
113
20:06
30.08.2025
በአድዮ ካካ ምርጫ ክልል በልማትና መልካም አስተዳደር ዙሪያ የመራጭ ተመራጭ ዉይይት ተደረገ
----------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 24 ፣ 2017 ዓ.ም ፤ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ ሕዝቦች ክልል የካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ አድያ ካካ ምርጫ ክልል ተወካይ የተከበሩ ወ/ሮ ፋናዬ መለሠ በወረዳው ከሚገኙ 13 ቀበሌዎች ከተውጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በልማትና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ዉይይት አድርገዋል።
ነዋሪዎቹ ከጎጀብ ከተማ አድዮ ወረዳን የሚያገናኝ የመንገድ ጥገና አለመደረጉን፣ ንጹህ የመጠጥ ዉሃ እጥረት መኖሩን፣ የመብራት ዝርጋታ ጥያቄ እና በጅምር ያለው የጎጀብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጠናቆ ወደ ስራ ያልገባ መሆኑን አንስተዋል።
የተከበሩ ወ/ሮ ፋናዬ በበኩላቸው በምርጫ ክልሉ መብራት የማያገኙ ቀበሌዎች መኖራቸው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ጥያቄ ይቀርብበት እንደነበረ አንስተው በሾምባ ሼካ ቀበሌ ላይ መንግስት ምላሽ መሰጠቱን፤ የቀሩት ቀበሌዎችም መብራት እንዲያገኙ የሚመለከተዉ አካል ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል::
ወ/ሮ ፋናዬ በአሁኑ ወቅት በትምህርት ዘርፍ ያለዉን እንቅስቃሴ በተመለከተ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር እንዲጨምር ከማድረግ ባሻገር ህጻናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲገቡ በማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፍነቱን መወጣት አለበት ብለዋል።
የጊምቦ ወረዳ የላይኛዉን የመንግስት መዋቅር ሳይጠብቅ ህዝቡን በማስተባበርና የዉስጥ ገቢን በማጠናከር እያከናወነ ያለው የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የመፍታት ጥረት የሚደነቅ ነዉ ሲሉ ወ/ሮ ፋናዬ መለሠ ተናግረዋል።
በወረዳዉ አስተዳደር ጥረት በቤዬሞ ቀበሌ የሚሰራዉ የሌማት ትሩፋት ተግባር በቱሪዝም ዘርፍ ዞኑንና ወረዳውን ለማስተዋወቅ የሚሰጠዉ ፋይዳም ከፍተኛ ነዉ ብለዋል።
ከህዝብ የሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት በፌደራል፣ በክልል እና በዞን መንግስት የሚመለሱ የመብራት የመንገድ፣ የድልድይ ፣ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ፣ የሆስፒታል፣ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ተቋም ግንባታና ሌሎች የልማት ጥያቄዎች እንዲፈቱ በየደረጃ ላሉ የመንግስት መዋቅር ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።
በመንገድ መሰረተ ልማት በወረዳው ሰፊ ስራዎች መሰራታቸዉን የገለጹት የወረዳዉ አስተዳዳሪ አቶ ትብብሩ አሰፋ ምላሽ ላላገኙ መንገዶች ማህበረሰቡን በማስተባበር የወረዳዉ መንግስት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በወረዳው ከሚገኙ የሾቻና የዬርታቺቲ ቀበሌዎች መንገድ ባለሀብቱንና ህዝቡን በማስተባበር እንደምሰሩም ጠቁመዋል::
በጤና አገልግሎት አሰጣጥ በቀጣይ ለማህበረሰብ የሚያስፈልጉ መድሃኒቶችን በየጤና ተቋማት የማቅረብ ስራ ተግባራዊ እየሆነ ነዉ ያሉት አቶ ትብብሩ አሰፋ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ክፍተቶ ክትትል በማድረግ ይፈታሉ ብለዋል።
በመጨረሻም የጎጀብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤተ ግንባታ እና በቤዬሞ ቀበሌ የባህል መንደር ልማት እንቅስቃሴን ተዟዙረው ምልከታ አድርገዋል።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR
በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
124
20:06
30.08.2025
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤት አባላት ከመረጣቸው ህዝብ ጋር ተወያዩ
--------------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 24፣ 2017 ዓ.ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ፕ/ር ሙሐመድ አብዶ በተወከሉበት ምርጫ ክልል ከወከላቸው ህብረተሰብ ጋር ተወያዩ፡፡
በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን የምርጫ ክልል በተካሄደው የመራጭ ተመራጭ መድረክ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ተወካዮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ በደሎ መና እና በሀረና ቡሉቅ ወረዳዎች ከአሁን በፊት በውክልና መድረኮች ላይ ለተነሱ የሰላምና ፀጥታ፣ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንዲሁም የፕሮጀክት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በራሳቸው ተነሳሽነት በንቃት እየጠበቁ እንደሆነና ፍላጎታቸው የልማት ጥማት ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
መንግስት ለዞኑ ለልማት የሰጠው ትኩረትና የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች የሚያበረታቱ መሆኑን ጠቁመው፤ ተጀምረው የተጓተቱ ፕሮጀክቶች ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲከናወኑ ጠይቀዋል፡፡
የመንገድ፣ የመብራትና የኔትዎርከ ተደራሽነት ችግሮች እንዲፈቱላቸው ያነሱት ተሳታፊዎች በተለይ የምዕራብ አርሲ ዞንን ከባሌ ዞን ሀረና - ቡሉቅ ወረዳ፣ የአዳባ - አንጌቱ መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ከ13 ዓመታት በፊት የተጀመረ መሆኑን ጠቁመው፤ መንገዱ ባለመጠናቀቁ ችግር ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ ፕ/ር መሐመድ አብዶ፤ ህብረተሰቡ በራሱ ተነሳሽነት በወረዳዎቹ እና በዞኑ ሰላምና ፀጥታን ለማስከበር የሰራው ሥራ ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆን መሆኑን ገልፀው ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
መንግስት ችግሮቹን በእቅድና አቅም በፈቀደ መጠን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ የጎባ - በርበሬ -ደሎ መና የመንገድ ስራ ፕሮጀክትን ጨምሮ ተጠናቀው ለመመረቅ የተዘጋጁ የመስኖ ስራ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን አመላክተዋል፡፡
ከህበረተሰቡ የተነሱ ጥያቄዎች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ተቋማት የቀረበ መሆኑንና ተቋማቱም ችግሩን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት በእቅድ ይዘው ለመፍታት ጥረት እያደረጉ መሆኑን አስረድተው ህብረተሰቡም በትዕግስት እንዲጠባበቅ ጠይቀዋል፡፡
ከመራጭ ተመራጭ መድረኩ በተጨማሪ በየወረዳዎቹ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች ተጎብኝተዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR
በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።
108
21:26
30.08.2025
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የመራጭ ተመራጭ የውይይት መድረክ ተካሄደ
----------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 24 ፣ 2017 ዓ.ም.፤ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት ከወከላቸው ማህበረሰብ ጋር በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ የመራጭ ተመራጭ የውይይት መድረክ አካሄዱ።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ረዳት ፕ/ር እንዳልካቸው ሌሊሳ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሀገር ደረጃ በዲፕሎማሲ ፣ በሰላምና ፀጥታ ፣ በኑሮ ማረጋጋት ፣ በስራ ዕድል ፈጠራ ፣ በልማት ፕሮጀክት በርካታ አመርቂ ስራዎችን መስራት መቻሉን አንስተዋል።
የምክር ቤት አባላት የህዝብ ድምፅ በመሆን የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ሲያነሷቸው የነበሩ የመልካም አስተዳደር እና ሌሎች ችግሮችን እንዲፈቱ መደረጉንና ነገር ግን አሁንም ቀሪ ስራ በመኖራቸው ያልተፈቱ ችግሮችን በመሸንሸን በዕቅድ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እንዲያገኙ የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል ።
የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፣ በክፍለ ከተማው የሚጨበጡ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን በመግለፅ በመድረኩ የተነሱ ጥያቄዎችን ለሚመለከተው አካል በማድረስ ተፈፃሚነታቸውን የመከታተል ስራ የሚሰራ መሆኑን አባላቱ ተናግረዋል።
ነዋሪዎች የተሰሩ የመሰረተ ልማት ስራዎችን የመጠበቅ የመንከባከብ ፣ የአካባቢውን ሰላም ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሊያስጠብቁ እና ከአስተዳደሩ ጋር በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ የተከበሩ አቶ አለማየሁ ሚጀና ከመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የ2017 በጀት ዓመት በከባድ ተግዳሮት ተጀምሮ በብልፅግና ዕሳቤ በመስራት በመሰረተ ልማት ፣ በኑሮ ማረጋጋት ፣ በፕሮጀክት አፈፃፀም ፣ በሰው ተኮር ስራዎችና በሌሎችም ተግባራት ስኬታማ ስራዎችም መስራት የተቻለበት እንደነበር ተናግረዋል።
ለዚህም የምክር ቤት አባላትና የነዋሪዎች ሚና ጉልህ እንደነበር በማንሳት በመድረኩ የተነሱ ጥያቄዎች በዕቅድ ውስጥ በማስገባት በየደረጃው የሚመለስ መሆኑን ገልፀዋል ።
የክ/ከተማው ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ሙሉጌታ አሰፋ መድረኩ በዓመት ሁለቴ ተመራጩ ከመራጩ ህዝብ ጋር በመገናኘትና የተሰሩ ስራዎችን የሚገመገምበት ለቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ለመወያየት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
የምክር ቤት አባላቱ ማህበረሰቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በየደረጃው እንዲፈቱ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተግባራቱ እንዲሳኩ የክትትልና የድጋፍ ስራዎችን ሲሰሩ መቆየታቸውን እና በዚህም ክፍለ ከተማው በበጀት ዓመቱ በከተማ ደረጃ ተመዝኖ የተሻለ አፈፃፀምና ስኬት ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል ።
87
21:26
30.08.2025
imageImage preview is unavailable
#HaileHotelShashemene
“ድሮ ከነበረው አስፍተን ነው የከፈትነው፡፡ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ወጥቶበታል ” - አቶ ጋዲሳ ግርማ
በጸጥታ ችግር ውድመት ደርሶበት የነበረው ሻሸመኔ ኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት ግንባታ "በይቻል መንፈስ" ተጠናቆ ዛሬ አገልግሎት መስጠር መጀመሩን የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ግሩፕ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡
ዳግም ግንባታው ስንት ብር ፈሰስ ተደረገበት ? በምን ያክል ጊዜስ ተጠናቀቀ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው የግሩፑ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ፣ “ ድሮ ከነበረው አስፍተን ነው የከፈትነው፤ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ወጥቶበታል ” ብለዋል፡፡
ግንባታው በሁለት ዓመታት ማለቁን ያስረዱት አቶ ጋዲሳ፣ የተጨመረው ምን እንደሆነ ስንጠይቃቸውም፣ “ ድሮ የክፍሎቹ ብዛት 40 ነበር፤ አሁን 84 ሆነዋል፡፡ ድሮ አንድ ነበር አሁን ሦስት አዳራሽ ሆነዋል፡፡ አንዳንድ ፋሲሊቲዎችን፣ ሬስቴራንቶችን ጨምረናል፤ የነበሩትንም አስፍተናል ” ነው ያሉት፡፡
ሆቴሉ አሁን የተስፋፋው ድሮ ከነበረው ቦታ አዲስ የካሬ ጭማሬ ተደርጎ ሳይሆን የነበሩ ቪላዎችን አፍርሶ ፎቅ በማድረግ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን፣ ሆቴሉ ተስፋፋቶ ከሆነ ድሮ ከነበረው ተጨማሪ የሥራ እድል ተፈጥሯል ? ስንልም ጠይቀናቸዋል፡፡
እሳቸውም በምላሻቸው፣ “ ክፍሎቹም ስለጨመሩ ሠራተኞች ጨምረናል፤ ድሮ 125 አካባቢ ነው የነበረን አሁን ስንከፍት 210 ሰዎችን ነው የቀጠርነው፡፡ ወደፊት በደንብ ሥራው እየሰፋ ሲሄድ ቁጥሩ ወደ 300 ከፍ ይላል የሚል እምነት አለን ” ብለዋል፡፡
ሆቴሉ የዳግም ግንባታ ወጭ የተደረገለት በክልሉ በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ውድመት ስለደረሰበት መሆኑ የሚታወቅ ነው፤ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ በበኩላቸው “ ሙሉውን አፍርሰን እየገነባን ነው፤ ከመንግስት ምንም አይነት ማካካሻ አልተደረገልንም ” ሲሉ ከዓመት በፊት ተናግረው ነበር፡፡
ይህን ካሉ ከወራት ቆይታ በኋላም ለሻሸመኔው ሆቴል መንግስት ካሳ ከፈለዎት ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠይቋቸው፣ “የካሳዋን ጉዳይ እየጠበኳት ነው፡፡ ግን የለችም እሷን ነገር እጠብቃለሁ፡፡ የውጭ ኢንቨስተሮች እንዲመጡ እንዲህ አይነት አደጋዎች ሲደርሱ ካሳ ቢከፈል መልካም ነው፤ ዞሮ ዞሮ አልተቀበልኩም ” ማታለታቸው ይታወሳል፡፡
ለዳግም ግንባታው አሁንስ ከመንግስት የተገኘ የካሳ ክፍያ ነበር ? ብለን ዛሬ የጠየቅናቸው የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርቶች ግሩፕ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ፣ “ ጉዳዩን የህግ አካል ስለሆነ ማኔጅ የሚያደርገው ሙሉ መረጃ የለኝም፡፡ ከተማ አስተዳደሩ ግን በገንዘብም ባይሆን በሌሎች ጉዳዮች እየረዳን ነበር ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የድሮው ሆቴልና ሪዞርት የተገነባው በምን ያክል ወጭ እንደነበር ሲጠየቁ ደግሞ፣ ያኔ ገንብተው ሳይሆን ገዝተውና የተገዛውን ትንሽ አሻሽለው ገብተው እንደነበር፣ ሆኖም ግን ለጊዜው ዳታውን እንደማያስታውሱት አስረድተዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
1
22:48
30.08.2025
close
Reviews channel
keyboard_arrow_down
- Added: Newest first
- Added: Oldest first
- Rating: High to low
- Rating: Low to high
5.0
1 reviews over 6 months
Excellent (100%) In the last 6 months
c
**ffeennew@******.io
On the service since June 2022
13.04.202523:32
5
Everything is fine. Thank you!
New items
Channel statistics
Rating
27.6
Rating reviews
5.0
Сhannel Rating
5
Subscribers:
4.5K
APV
lock_outline
ER
3.1%
Posts per day:
23.0
CPM
lock_outlinekeyboard_double_arrow_left
shopping_cart
Channels:
0
Subscribers:
0
Views:
lock_outline
Total:
$0.00
Add to Cart
Clear the cart
Are you sure you want to clear the cart?
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
You will be able to add channels from the catalog to the cart again.
Clear my cart
Cancel
Комментарий